Telegram Web Link
#ደሴ

“ ህይወቷ በማለፉ አዝነናል ነገር ግን ተማሪዋ የደሴ ካምፓስ ተማሪ አይደለችም ” - ወሎ ዩኒቨርሲቲ

➡️ “ የምርመራ ኬዝ ስለሆነ ጥንቃቄ ያስፈልገዋል ” - ጉዳዩን የሚከታተሉት ኢንስፔተክር


ተማሪ ሊዛ ደሳለ የተባለች ወጣት ሰሞኑን በደሴ ከተማ “ የአስገድዶ መድፈርና ግድያ ጥቃት ተፈጽሞባት ” መገኘቷ ተሰምቷል፡፡

መረጃዎች እንደሚያመላክቱት ወጣቷ መስከረም 27 ቀን 2018 ዓ/ም ስልኳን ለማሰራት በደሴ ከተማ ወደ ፒያሳ በወጣችበት አልተመለሰችም፡፡

ይህን ተከትሎ ፍለጋ ሲደረግ ግን “ተደፍራና ተገድላ ተገኝታለች” የተባለ ሲሆን፣ “ፍትህ ለተማሪ ሊዛ” የሚል ጥያቄዎች ኢንተርኔቱን አጨናንቀውታል።

ወጣቷ “ የወሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ናት ” የሚሉ መረጃዎች መሰራጨታቸውን ተከትሎ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ምላሽ የጠየቃቸው አንድ የዩኒቨርሲቲው አካል ጉዳዩን አጣርተው በሰጡት ምላሽ፣ “ የተማሪዎች አገልግሎት ጋር ደውየ ነበር፤ 'እንዲህ አይነት ነገር እኛ አልተከሰተም፡፡ ተከሰተ የሚባለውም ከወይዘሮ ስህን ኮሌጅ ነው' ” እንዳሏቸው ገልጸዋል፡፡

እኝሁ የዩኒቨርሲቲው አካል፣ “የደሴ ካምፓስ ተማሪ አይደለችም፡፡ የወይዘሮ ስህን ኮሌጅ ተማሪ ናት፡፡ የኛ ተማሪ አለመሆኗን አሁን ከተማሪ አገልግሎት ደውዬ አጣርቻለሁ ” ሲሉም አክለዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው በማህበራዊ ሚዲያ ስሙ በሀሰት መነሳቱን ገልጾ ይህን ባደረጉት ላይ ተጠያቂነት እንደሚከተል ገልጿል።

በሊዛ ደሳለ ሞት ማዘኑንም ገልጾ ለወዳጅ ዘመዶች መፅናናትን ተመኝቷል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ የተማሪዋን ቤተሰቦች ለማግኘት ያደረገው ጥረት ባይሳከለትም፣ ከቆቦ ከተማ ነዋሪዎች ባደረገው ማጣራት ግን ተማሪ ሊዛ ደሳለ በሰሜን ወሎ ዞን የራያ ቆቦ ወረዳ ቆቦ ከተማ ታዲጊ መሆኗን ለማወቅ ችሏል፡፡

የወይዘሮ ስህን ኮሌጅ ኃላፊዎችን ፣ የደሴ ከተማ ፓሊስን ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ ለጊዜው አልተሳካም።

የደሴ ከተማ ኮሚዩኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ አቶ ነስረዲን ኃይሌ፣ " መድረክ እየመራሁ ነው " በማለታቸው ሀሳባቸውን ማካተት አልተቻለም። ኃላፊው ቆየተው በላኩት የፅሑፍ መልዕክት ዝርዝር መረጃ ይሰጧችኋል ሲሉ ኮማንደር ሰይድ የሚባሉ አካል ጠቁመዋል።

" ጉዳዩን ተከታትለውታል " የተባሉት ኮማንደር ሰይድ አሊ ምላሽ ብንጠይቃቸውም፣ “ እኔ አልሰጥም፤ ፖሊስ ነው መግለጫ የሚሰጠው፤ ፖሊስ መምሪያ ኃላፊው ናቸው የሚሰጡት ” ብለዋል።

“ የምርመራ ኬዝ ስለሆነ ጥንቃቄ ያስፈልገዋል ” ያሉት እኝሁ አካል፣ የምርመራውን ሂደት ሳይሆን የግድያውንና ሁነት እንዲያስረዱ ስንጠይቃቸው ማብራሪያ ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthioiaFamilyAA

@tikvahethiopia
😭1.75K1.18K💔220😡72😢48🕊47😱19🙏13🤔10👏5🥰4
#ኢትዮጵያ🇪🇹

" አያሰማን ፍጹም ያንቺን ክፉ
ኢትዮጵያ
ጠባቂሽ ነው ህዝብሽ እልፍ አእላፉ
ላንቺ ክብር
ላንቺ ክብር ሞትን የማይፈሩ
ኢትዮጵያ
ልጆች አሉሽ ዛሬም የሚያኮሩ
🇪🇹
አረንጓዴ ቢጫ ቀዩ ሰንደቅሽ
አልብሽን አንድ ላይ ልጆቼ ብለሽ፤
አረንጓዴ ቢጫ ቀዩ ሰንደቅሽ
ሰላም ፣ ልምላሜ ፣ ጸጋ ያልብስሽ። "

#ኢትዮጵያ #ETHIOPIA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
401.96K🙏111🥰61🕊56😡56😭42🤔33👏12😢12💔8
የአዕምሮ ህሙማን ቁጥር በዓመት ውስጥ እስከ 15 ሺሕ ጨምሯል።

አማኑኤል የአዕምሮ ህሙማን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በሆስፒታሉ የሚስተናገዱ የአዕምሮ ህሙማን ቁጥር በዓመት ውስጥ እስከ 15 ሺሕ መጨመሩን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጸ፡፡

ይህን ያሉን፣ የአዕምሮ ህሙማን ቁጥር እየጨመረ ወይስ እየቀነሰ ነው ? ግጭትና ጦርነት የህሙማኑን ቁጥር ለመጨመር ገፊ መንስኤ አልሆነም ? ስንል የጠየቅናቸው የአዕምሮ ሐኪምና የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶ/ር ክብሮም ኃይሌ ናቸው።

ዳይሬክተሩ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በዝርዝር ምን አሉ ?

" የመሬት መንቀጥቀጥ፣ ግጭት፣ ድርቅ፣ ጦርነትና መፈናቀሎች በተደጋጋሚ አጋጥመዋል። እነዚህ ክስተቶች የአዕምሮ ጤና ችግርን እንደሚጨምሩ የሚያሻማ አይደለም።

ካለፈው ዓመት መጠነኛ ጭማሪ አለው፡፡ የ2017 እስከ ሰኔ ያለው ከ130 ሺሕ ትንሽ ከፍ ይላል፤ በዚያኛው ዓመት ካየነው 10 ሺሕ፣ 15 ሺሕ ጭማሪ አለው።

ስለዚህ የመጨመር ሁኔታዎች አሉ፤ እንደሚጨምርም ይታወቃል፡፡ ግን ሁሉም (ታማሚ) አይመጣም፡፡ ስለዚህ የሆስፒታሉ ዳታ ማህበረሰቡ ውስጥ ያለውን ሁኔታ ላያሳይ ይችላል። ስለዚህ እኛ ጋር ያለው የታካሚ ቁጥር መጨመር አለመጨመሩ የችግሩን መኖር አለመኖሩን (ሙሉ በሙሉ) አያሳይም።

የአማኑኤል ሆስፒታል የህሙማን ፍሰትን የሚያግዱ የተለያዩ ምክንያቶች አሉ። ለአብነትም በገንዘብ አቅም ማነስ፣ በሚያግዝ ሰው አለመኖር ህሙማን ላይመጡ ይችላሉ።

የመፍትሄ ሀሳብ ምን ሰጡ ?

" እኛ ነን ችግሩ ወዳጋጠመበት ቦታ መሄድ ያለብን፡፡ በአንድ ቦታ ግጭት ሲያጋጥም 'ወገኖቼ ይሞታሉ' በሚል መሸበር ይኖራል፡፡ በተለይ በዚያ ወቅት ስነ ልቦናዊ ድጋፍ ካልተገኘ ችግሩ ይብሳል።

ስለዚህ አዕምሮ ጤናም ጉዳይ ሌሎች እርዳታዎች ጋር አብሮ መሄድ አለበት፡፡ በግንዛቤ እጥረት በትራንስፖርትና በሌሎች ምክንያቶች ሰዎች ወደ ህክምና ላይመጡ ይችላሉ፡፡ ስነልቦናዊና ማኀበራዊ ድጋፉን በዚያው ማቅረብ ያስፈልጋል፣ የታመሙ ከሆኑም እኛ መሄድ አለብን።

በሌላ በኩል፣ ሰዎች ድባቴ ውስጥ በሚገቡበት ወቅት ከሚያወቋቸው ሰዎች ጋር ጊዜ ቢያሳልፉ፣ ችግራቸውን ቢወያዩ ለአዕምሮ ህመም የመጋለጥ ሁኔታው ይቀንሳል።

የሆስፒታሉ ተመላላሽ ህክምና ክፍል ኃላፊስ ምን አሉ ?

የሆስፒታሉ የተመላላሽ ህክምና ክፍል ኃላፊ ሳሙኤል ቶለሳ፣ የዘንድሮው የአዕምሮ ጤና ቀን " በድንገተኛ አደጋዎችና ሰብዓዊ ቀውስ ወቅት የአዕምሮ ጤና አገልግሎት ተደራሽነት ምን ይመስላል ? " የሚለው ላይ እንዳተኮረ ገልጸዋል።

" ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የእርስበርስ ግጭቶች አሉ፣ ያን ተከትሎ የሚመጡ ማኅበራዊ ቀውሶች አሉ " ያሉት ኃላፊው፣ በዚህም የተደራሽነት ውስነት መኖሩን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል፡፡

" በተለያዩ ክልሎች ያለው ቀውስ ራሱን የቻለ ተፅዕኖ አለው፣ ተማሪዎች እንዳይማሩ የማድረግ ሂደቶች አሉ " ብለው፣ ሰዎች ቀጥተኛ የጦርነቱ ተጠቂ ሲሆኑና የሚያስጨንቁ ነገሮች ሲፈጠሩ ለአዕምሮ ህመም ተጋላጭነታቸው እያደገ እንደሚመጣ ገልጸዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
962😭746💔83😢63🕊45🙏42😱26😡23🤔19👏9🥰7
📣 𝐉𝐢𝐦𝐦𝐚 𝐔𝐧𝐢𝐯𝐞𝐫𝐬𝐢𝐭𝐲 𝐢𝐬 𝐍𝐨𝐰 𝐢𝐧 𝐭𝐡𝐞 𝐂𝐢𝐭𝐲!
Registration is officially 𝐎𝐏𝐄𝐍 for our selected undergraduate programs at the JU-ABH Campus in Addis Ababa. Your opportunity to earn a prestigious degree has arrived!

𝐎𝐮𝐫 𝐏𝐫𝐨𝐠𝐫𝐚𝐦𝐬
1. BA degree in Accounting & Finance 💰
2. BA degree in Management 💼
3. BSc degree in Computer Science 💻
4. Bachelor of Laws (LLB) ⚖️

𝐑𝐞𝐚𝐝𝐲 𝐭𝐨 𝐀𝐩𝐩𝐥𝐲?
Visit www.allianceacademy.edu.et/degree-program

𝐐𝐮𝐞𝐬𝐭𝐢𝐨𝐧𝐬? We are ready to assist!
📞 +251978464748 / +251979464748

𝐂𝐨𝐧𝐧𝐞𝐜𝐭 𝐰𝐢𝐭𝐡 𝐮𝐬
LinkedIn|Telegram |Facebook |Twitter/X |Instagram |TikTok |YouTube |Threads
197🤔5🥰4😱4😢1😡1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ወረቀት የለም! ጊዜ ማባከን የለም!
ቀላልና ፈጣን የባንክ አገልግሎት ብቻ!

የጣት አሻራንና የፊት ገጽን እንደ መለያ የሚጠቀመው አዲሱ የአቢሲንያ ባንክ ወረቀት አልባ አገልግሎት ደንበኞች በጊዜና ቦታ ሳይገደቡ ያለማንም እርዳታ በራስ-አገዝ (Self-Service) ወይም በሠራተኞች በመታገዝ (Assisted Service) ደህንነቱ በተጠበቀና ፈጣን በሆነ መልኩ የሚፈልጉትን የባንክ አገልግሎት መጠቀም ይችላሉ፡፡ #ወረቀትአልባየባንክአገልግሎት #Paperlessbranchmodel #BanksinEthiopia #AddisAbaba #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
308😡61👏39🙏13
TIKVAH-ETHIOPIA
Video
#ETHIOPIA🇪🇹

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው መደበኛ ስብሰባዉ የኢትዮጵያ ኒውክሊየር ኃይል ኮሚሽን ማቋቋሚያ ደንብን መርምሮ በሙሉ ድምጽ አጸደቀ።

ይህ ደንብ በነጋሪት ጋዜጣ በይፋ ታትሞ ከወጣ በኋላ ተግባራዊ የሚሆን ሲሆን፣ ኢትዮጵያ የኒውክሌር ቴክኖሎጂን ለሰላማዊ ልማት የመጠቀም ጥረቷን ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚያሸጋግር ይጠበቃል።

ኮሚሽኑ በዓለም አቀፍ ማዕቀፎች መሰረት የኒውክሌር ቴክኖሎጂን ለሰላማዊ ዓላማዎች የመጠቀም ሀገራዊ ጥረትን የመምራትና የማስተባበር ዋነኛ ኃላፊነት ይኖረዋል ተብሏል።

ትኩረት አድርጎ የሚሠራባቸው ቁልፍ ዘርፎችም የኤሌክትሪክ ኃይል ተደራሽነት፣ የኢንዱስትሪ ልማት፣ የምግብ ዋስትና፣ የጤና አገልግሎት እንዲሁም ሳይንስና ምርምር መሆናቸው ተመላክቷል።

በሌላ በኩል ፥ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከጥቅምት 4 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ አቶ ሳንዶካን ደበበ የኢትዮጵያ ኒውክሊየር ኃይል ኮሚሽን ኮሚሽነር አድርገው ሾመዋል።

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
710🤔129😡70👏43🕊14😱9😭8🥰6🙏2💔1
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update " ሰላምን እንሻለን ! " - የትግራይ ኃይል አባላት ➡️ " የኛን ጥያቄ መመለስ ከማይችል አመራር የሌላው ህዝብ ጥያቄ ሊመልስ አይችልም ! " የትግራይ ኃይል አባላት ዛሬ ሰኞ ጥቅምት 3/2018 ዓ.ም ከጥዋቱ 2:30 ጀምረው የመብት ጥያቄ አንስተው በከተማዋ ዋና ዋና መንገዶች ሰላማዊ ሰልፍ አካሂደዋል። ሰልፈኛቹ ቁጣን ባዘለ ድምፅ ፦ - " የደመወዝና ጥቅማጥቅም ጥያቄያችን ይመለስ…
#Update

የትግራይ ኃይል አባላት ሰልፍ ዛሬም በሌላ አቅጣጫ ሰልፍ ማድረግ ቀጥለዋል።

በመቐለና ዙሪያዋ የሚገኙ የትግራይ ኃይል አባላይ ትናንት ሰኞ ጥቅምት 3/2018 ዓ.ም ከጥዋቱ 2:30 እስከ ምሽት ሰላማዊ ሰልፍ አካሂደው ነበር።

በዚያው ቀን ምሸት የሰላማዊ ሰልፈኞቹ ተወካዮች የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዚዳንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጀ) ከሚገኙባቸው የህወሓትና የሰራዊት አዛዦች ቢነጋገሩም ፤ ስለተደረሰው ስምምነት በይፋ ለህዝብ የተሰጠ መረጃ የለም።

ሆኖም ከሰብሰባው አዳራሽ ተቆርጦ የወጣው ቪድዮ እንደሚያመለክተው ሰላማዊ ሰልፈኞቹ የደመወዝ ፣ የጥቅማጥቅምና ለቤተሰቦቻቸው መኖሪያ የሚውል የመስሪያ ቦታ ጥያቄ አንስተዋል።

የትናንትናው ውይይት ውጤት ለህዝብ ሳይነገር ታድያ ዛሬ ማክሰኞ ጥቅምት 4/2018 ዓ.ም ከትግራይ ምስራቃዊ ዞን ወደ መቐለ ከተማ የሚያስገባው ዋና አስፋልት ከጥዋት ጀምሮ ይህ መረጃ እስከተጠናቀረበት ሰዓትና ደቂቃ በሁለት ቦታ ተዘግተዋል።

የትግራይ ኃይል አባላት ሰላማዊ ሰልፈኞች ኣጉላዕና ጉርመዶ በሚባሉ ሁለት ቦታዎች መንገድ በመዝጋታቸው ምክንያት መኪኖች ቆመዋል ተጓዦች ተስተጓጉለዋል።

ሰላማዊ ሰልፈኞቹ ጥያቄያቸው ከትናንትናው ሰልፍ ተመሳሳይ እንደሆነ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ቦታው ድረስ ደውሎ አረጋግጠዋል።

በዚህ ዙሪያ የሚኖሩ አዳዲስ መረጃዎች ተከታትለን እናቀርባለን።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
933👏89🕊75🤔38😡19😭17😢16🙏16🥰7💔1
ደንበኛዎትን በቀላሉ ካሉበት ለመድረስ የሚያስችልዎትን የዲጂታል ሱቅ በዘመን ገበያ ላይ አሁኑኑ ይክፈቱ፣ ተደራሽነትዎን ያስፉ።

የበለጠ መረጃ ለማግኘት 3131 ላይ ይደውሉ!

ዘመን ገበያ የዲጂታል ኢትዮጵያ የግብይት መዳረሻ!

#ZemenGEBEYA
#Ethiotelecom #telebirr #telebirrSuperApp #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
129😢5🙏5😱4🕊1
2025/10/22 04:11:55
Back to Top
HTML Embed Code: