Telegram Web Link
ብሔራዊ ባንክ ዛሬ የውጭ ምንዛሪ ጨረታ አካሂዷል።

ባንኩ መሰል ጨረታ ሲያወጣ ለ10ኛው ዙር ሲሆን በዚህ ዙር  150  ሚሊዮን ዶላር ነበር ያቀረበው።

በጨረታው የአንድ የአሜሪካን ዶላር አማካይ የምንዛሪ ተመን 148.1007 ብር ሆኖ ተመዝግቧል። / 1 ዶላር በ148.1007 ተሽጧል /

ይህ አዲስ አማካኝ ዋጋ ከሁለት ወራት በፊት በ9ኛው ዙር ጨረታ ከተመዘገበው 138.2  ብር አማካይ ዋጋ ጋር ሲነጻጸር፣ የ9  ብር ከ90 ሳንቲም ወይም የ 7.16 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል።

ዛሬ በተካሄደው የውጭ ምንዛሪ ድልድል 31 ባንኮች የውጭ ምንዛሪ በማግኘት ተሳክቶላቸዋል።

ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ ገበያው በሚፈቅደው ጊዜ ጨረታዎቹን ማካሄዱን እንደሚቀጥል አስታውቋል። #ካፒታል

@tikvahethiopia
432😡198🤔42😱27😢22🙏8💔5😭3
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#MoE

" ውጤት በቅርቡ ይፋ ይደረጋል " - ትምህርት ሚኒስቴር

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሲሰጥ የነበረው የ2018 የድህረ ምረቃ ትምህርት መግቢያ ፈተና መጠናቀቁን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

ፈተናው ለመውሰድ ከተመዘገቡ 29 ሺ491 አመልካቾች መካከል 96 በመቶ ፈተናውን እንደወሰዱ አመልክቷል።

በ2017 ዓ.ም. መጨረሻ ላይ ይሰጥ የነበረው የድህረ ምረቃ መግቢያ ፈተና በተለያዩ ምክንያቶች ተራዝሞ ጥቅምት 3 ቀን 2018 ዓ.ም. በ53 የፈተና ማዕከላት ነው የተሰጠው።

የፈተናው ውጤትም በቅርቡ ለተማሪዎች ይፋ እንደሚደረግ ሚኒስቴሩ አመልክቷል።

የድህረ ምረቃ ትምህርት መግቢያ ፈተና (NGAT) ከሌሎች አገር አቀፍ ፈተናዎች የተለየና የ2ኛ እና የ3ኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን መቀጠል የሚፈልጉ አመልካቾች ለትምህርቱ ምን ያክል ዝግጁ ናቸው የሚለውን ለማረጋገጥ ደረጃውን ጠብቆ የሚሰጥ ምዘና ነው።

#DrEbaMijena

መረጃው የትምህርት ሚኒስቴር ነው።

@tikvahethiopia
970🙏82🤔46😡42😭40👏17😢14🕊12🥰11💔9😱1
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የትግራይ ኃይል አባላት ሰልፍ ዛሬም በሌላ አቅጣጫ ሰልፍ ማድረግ ቀጥለዋል። በመቐለና ዙሪያዋ የሚገኙ የትግራይ ኃይል አባላይ ትናንት ሰኞ ጥቅምት 3/2018 ዓ.ም ከጥዋቱ 2:30 እስከ ምሽት ሰላማዊ ሰልፍ አካሂደው ነበር። በዚያው ቀን ምሸት የሰላማዊ ሰልፈኞቹ ተወካዮች የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዚዳንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጀ) ከሚገኙባቸው የህወሓትና የሰራዊት አዛዦች ቢነጋገሩም ፤ ስለተደረሰው…
#Tigray

በመቐለና ዙሪያዋ የሚገኙ የትግራይ ኃይል አባላት ትናንት ሰኞ ጥቅምት 3/2018 ዓ.ም የጀመሩት የመኪና መንገድ በመዝጋት የተደገፈ የተቃውሞ ሰልፍ ዛሬም በሌሎች አቅጣጫዎች ሲካሄድ ውሏል።

ዛሬ ማክሰኞ ጥቅምት 4/2018 ዓ.ም ከትግራይ ምስራቃዊ ዞን ወደ መቐለ ከተማ የሚያስገባው ዋና አስፋልት ከጥዋት ጀምሮ ተዘግቶ ነበር።።

ሰልፈኞቹ ኣጉላዕና ጉርመዶ በሚባሉ ሁለት ቦታዎች መንገድ በመዝጋታቸው ምክንያት መኪኖች ቆመው ተጓዦች መስተጓጎላቸው የታወቀ ሲሆን ማምሻውን መንገዶች ተከፍተዋል ብለዋል ተጓዦች።

መንገድ በመዘጋቱ ምክንያት ከፍተኛ እንግልት እንደደረሰባቸውና ሰላማዊ ሰልፈኞቹ ተቋውሟቸውን ከመንገድ መዝጋት ውጪ ቢያደርጉት የሚል ምክረ ሃሳብ ሰጥቷል።

ዛሬ ጥቅምት 4/2018 ዓ.ም ከሰዓት በኃላ መግለጫ ያወጣው  የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ፅህፈት ቤት " የሰራዊት አባላት ሰልፈኞቹ ጥያቄ ልክ ነው " ብሏል።

የሰላማዊ ሰልፈኞቹ ጥያቄዎች ኑሮን ማሻሻልና የደመወዝ ጭማሪ መሆናቸው ያስታወቀውና የተቀበለው የጊዚያዊ አስተዳዳሩ ጥያቄዎቹ እንዲፈቱ ከሚመለከታቸው አካላት በመቀናጀት እሰራለሁ ብሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
1524🕊56👏24😡17🙏9😭8🥰2😱1
#Haile

“ በየቦታው የሰራናቸውን ሆቴሎች አይነት አንዷን ድሬዳዋ እናስቀምጣለን ብለን አቅደናል” - ሻለቃ ኃይሌ

➡️ “ደብረ ብርሃን ሆቴል የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ነው፤ በቀጣዮቹ ሦስት፣ አራት ወራት ወደ ሥራ ይገባል” - አቶ ጋዲሳ ግርማ

አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገ/ስላሴ በሆቴልና ሪዞርት ግንባታ ረገድ ወደ ድሬዳዋ ከተማ እየገቡ መሆኑን፣ የከተማዋን ከንቲባና ካቢኔውን አግኝተውም ቃል እንደተገባላቸው ዛሬ ገልጸዋል፡፡

የኃይሌ ሆቴሎች ሪዞርቶች ግሩፕ ማኔጅንግ ዳይሬክተር አቶ ጋዲሳ ግርማ በበኩላቸው፣ ድሬዳዋ ላይ የሆቴልና ሪዞት ግንባታ በቅርቡ እንደሚጀመር ዛሬ ምሽት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጠዋል፡፡

ሻለቃ ኃይሌ፣ በድሬ ከተማ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር፣ “ኃይሌ ሆቴልና ሪዞርት በየከተማዎቹ እየገነባን ነን፡፡ እስካሁን በአስር ከተሞች ተከፍተዋል፡፡ ሌላ ሦስት ደግሞ በግንባታ ላይ ናቸው፡፡ አሁን ደግሞ የድሬው 14ኛው ይሆናል” ብለዋል፡፡

“መምጣት ካለብን በጣም የዘገየንበት ቦታ ነው፡፡ ግን አሁን ድሬዳዋ እየገባን ነው፤ ክቡር ከንቲባውንም ካቢኔውንም አግኝተን በጣም ጥሩ ቃል ገብተውልናል” ሲሉም ተናግረዋል፡፡

ሥራው ቶሎ እንደሚጀመር ጠቁመው፣ “በየቦታው የሰራናቸውን ሆቴሎች አይነት አንዷን ድሬዳዋ እናስቀምጣለን ብለን አቅደናል፡፡ መጀመሪያ ስናጠና ቢዝነሱ እንዴት ነው ? የሚለውን ነው፤ ድሬዳዋም ከኢትዮጵያ ቀደምት ከተሞች አንዷ ነች፤ በቢዝነሱም” ነው ያሉት፡፡

ስለድሬዳዋው ሆቴል ግንባታ ተጨማሪ ማብራሪያ የጠየቅናቸው የኃይሌ ሆቴሎች ሪዞርቶች ግሩፕ ማኔጅንግ ዳይሬክተር አቶ ጋዲሳ ግርማ፣ “የቦታ ልየታና ገበያውን ለማየት ሂደን ነበር ዛሬ፡፡ ኢንቨስትመንት ላይ የሚሰሩ የመንግስት አካላት ቦታዎችን አሳይተውናል፤ ወደ ቀጣዩ ሂደት እንቀጥላለን” ብለዋል፡፡

ግንባታውን በቅርቡ የመጀመር እቅድ እንዳላቸው፣ በዚህ ቀን ይጀመራል የሚል ቀን ገና እንዳላስቀመጡ ገልጸው፣ “የመሬት ርክክብ ባለቀ በማግስቱ ግንባታ እንጀምራለን” ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል፡፡

የጎንደርና ደብረ ብርሃን ፕሮጀክቶችን እያጠናቀቁ በመሆኑ ቀጣዩ አቅጣጫ ወደ ድሬ እንደሆነ የጠቆሙት አቶ ጋዲሳ፣ “ደብረ ብርሃን ሆቴል የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ነው ያለው፤ በቀጣዮቹ ሦስት አራት ወራት ውስጥ ወደ ሥራ ይገባል፡፡ የጎንደር ደግሞ ከሰባት ውራት እስከ አንድ አመት ይወስዳል” ብለዋል፡፡

በጎንደሩ ፕሮጀክት የጸጥታው ሁኔታ ምን አይነት እንቅፋት እንዳፈጠረባቸው ማብራሪያ ሲጠየቁም፣ በዚህ ረገድ አስተያየት አለመስጠትን መርጠዋል፡፡

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
2.07K👏292🥰33😡28🙏27🕊23😭17🤔14😢12💔12😱6
የኢትዮጵያ መንግስት ለአካል ጉዳተኞች ጤና-ነክ መልሶ ማቋቋም እና ፆታን ታሳቢ ያደረጉ አገልግሎቶች ተደራሽ መሆናቸውን ለማረጋገጥ አግባብነት ያላቸውን እርምጃዎች በሙሉ ለመውሰድ በአለምአቀፉ የአካል ጉዳተኞች ስምምነት አንቀጽ 25 መሰረት ግዴታዎችን ተቀብሏል! በተለይም የአካል ጉዳተኞች የስነተዋልዶ እና የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት መብቶች እውን እንዲሆኑ፤ አካል ጉዳተኞች ጾታዊ ግንኙነት፣ የስነ ተዋልዶ ጤና አገልግሎትን እንዲሁም ስነ ህዝብን መሠረት ያደረገ የህዝብ ጤና ፕሮግራሞችን በሚመለከት ከአድልዎ በጸዳ ሑኔታ እና ከሌሎች ሰዎች ጋር እኩል በሆነ መልኩ አገልግሎቶቹን የማግኘት መብት አላቸው! አካል ጉዳተኞች እነዚህን አገልግሎቶችን በሚያገኙበት ወቅት ለሌሎች ሰዎች እንደሚሰጠው ባለ ተመሳሳይ አይነት፣፣ ጥራትና ደረጃ መሆኑን ማረጋገጥ ይገባል! የስነተዋልዶ እና የቤተሰብ አገልግሎቶች በነፃ ወይም የአካል ጉዳተኞችን የመክፈል አቅምን ያገናዘቡ መሆን አለባቸው!
አካል ጉዳተኞች በአካል ጉዳታቸው ምክንያት አድልዎ ሳይደረግባቸው ሊደረስበት ለሚቻለው ከፍተኛው የጤና ደረጃ ባለቤትነት መብት እንሰራለን!
አካል ጉዳተኞችን ያካተተ የስነተዋልዶ እና የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት ስርአት፤ለጤናማ ማህበረሰብ የእድገት እና የጥንካሬ ጉልላት።
የኢትዮጵያ የሕግ ባለሞያ አካል ጉዳተኞች ማህበር


Tel: 9110/ +251115581164
Website:
Facebook,
Twitter:
LinkedIn
341👏22🥰7😢6🙏6😡5😭1
#Kenya

የኬንያው ጉምቱ ፖለቲከኛ ራይላ ኦዲንጋ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ ህንድ ሀገር በህክምና ሲረዱ ቆይተው በ80 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

ራይላ ኦዲንጋ ለኬንያ ፕሬዚዳንትነት 5 ጊዜ ዕጩ ሆነው ቢቀርቡም አልተሳካላቸውም።

በተጨማሪ በቅርቡ ለአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበርነት ቦታ ቢወዳደሩም ማሸነፍ ሳይችሉ ቀርተዋል።

ለረጅም አመታት በፖለቲካ ውስጥ የቆዩት ኦዲንጋ በኬንያ የበዛ ድጋፍ ያላቸው ሲሆን የኦሬንጅ ዴሞክራቲክ ሙቭመንት መሪ ነበሩ።

ለዴሞክራሲ፣ ለመድብለ ፓርቲ ስርዓት፣ ከህገመንግስት ሪፎርም በመታገል ይታወቃል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ የኢፌዴሪ ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በራይላ ኦዲንጋ ህልፈት የተሰማቸውን ሀዘን በኢትዮጵያ ህዝብ ስም ገልጸዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
461😭413🕊66😢31👏27😱13🙏13🤔12💔7😡4🥰1
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

ወደ መቐለ የሚያመሩ መንገዶች ዛሬም ለሁለተኛ ቀን በሁለት አቅጣጫ በትግራይ ኃይል ሰልፈኞች ተዘግተዋል።

የተዘጉት መንገዶች በትግራይ ምስራቃዊ ዞን ከመቐለ በ35 ኪሎ ሜትር ርቀት በምትገኘው የኣጉላዕ ከተማ ፤ በደቡባዊ ዞን ከመቐለ 100 ኪሎ ሜትር አከባቢ በምትርቀው የመኾኒ ከተማ መሆኑ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ መረጃ ደርሶታል።

በተጨማሪ በሰሜን ምዕራብ ዞን ወደ እንዳስላሰ-ሽረ ከተማ የሚወስደው መንገድ ከከተማዋ 20 ኪሎ ሜትር ርቀት በሚገኘው እንዳባጉና ከተማ በሰልፈኞች ተዘግቷል።

ሰልፈኞቹ ጥቅምት 3/2018 ዓ.ም ከመቐለ ከተማ ወደ አሉላ አባነጋ አውሮፕላን ማረፍያ የሚወስደው ዋና መንገድ ዘግተው ውለው በዚያው ቀን ምሸት ከጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕረዜዳንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጀ) ተወያይተው " ጥያቄያችሁ ልክ ነው ፤ በየደረጃው ይመለሳል " ተብለው ነበር።

ጉዳዩን ተከታትለን መረጃውን የምንልክ ይሆናል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia            
494👏55🕊36😭34😡21🤔12😱6
2025/10/21 12:55:25
Back to Top
HTML Embed Code: