Telegram Web Link
VAT Strategy.pdf
6.2 MB
የገቢዎች ሚኒስቴር የተርን ኦቨር ታክስን በሚመለከት ዝርዝር የሽግግር የአሰራር ስርአት አዘጋጀ።

የገቢዎች ሚኒስቴር የተርን ኦቨር ታክስ አዋጅ ቁጥር 308/95 ከሐምሌ 2017 ጀምሮ የተሰረዘ በመሆኑ የነባር የተርን ኦቨርታክስ ከፋዮችን በተመለከተ በታክስ አስተዳደሩ ለሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት አፈጻጸም እንዲያግዝ የሽግግር የአሰራር ስርዓት አዘጋጅቷል።

የተዘጋጀውን የአሰራር ስርዓት ተፈርሞ ከተላለፈበት መስከረም 21 ቀን 2018 ዓም ጀምሮ ተግባራዊ መሆን ጀምሯል።

የአሰራር ስርአቱ ከሐምሌ 1 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ በስራ ላይ የዋለው የገቢ ግብር ማሻሻያ አዋጅ ከእዚህ ቀደም በስራ ላይ የነበረውን የተርን ኦቨር ታክስ አዋጅ የሻረ በመሆኑ ፣ ከሐምሌ 1 ቀን 2017 በፊት የተርን ኦቨር ታክስ ከፋይ በነበሩ ግብር ከፋዮች ላይ ተፈጻሚ ይሆናል።

የአሰራር ስርአቱ ለስድስት ተከታታይ ወራት ተግባራዊ የሚደረግ መሆኑን የአሰራር ስርአቱ ይገልጻል።

አዲሱ የአሰራር ስርአት የታክስ ከፋይ መረጃ ማጥራት እና ማደራጀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ቅድመ ሁኔታ እና አፈጻጸም ፣ የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትን ጨምሮ የቅሬታ አፈታት ስርአት በሚመለከት ዝርዝር ጉዳዮችን ይዟል።

(ዝርዝር የሽግግር የአሰራር ስርዓት አፈጻጸሙን ይዘት ከተያያዘው ፋይል ይመልከቱ)

@tikvahethiopia
434😭26😱24😡15🙏12🕊3😢1
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
“ ጥፋት ሲፈጸም ሰሌዳ ይፈታል የሚል ሕግ የለም ” - አለሙ ስሜ (ዶ/ር)

የትራንስፓርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር በሀገር አቀፍ ደረጃ ነባሩን የተሽከርካሪ መለያ ሰሌዳ ቁጥር በአዲስ የመተካት ሥራ ለእያንዳንዱ ተሽከርካሪ የራሱ መለያና ስቲክር በመስጠት ሕገወጥ የተሽከርካሪ ሰሌዳ ቅየራን ለማስቀረት እንደሚረዳ ገለጸ።

የተቋሙ ሚኒስትር አለሙ ስሜ (ዶ/ር)፣ ያረጁ ተሽከርካሪዎች ለጨረታ ሲወጡ ብዙዎች ተሻምተው ገዝተው ያለጉምሩክ እውቅና በሕገወጥ አዲስ ታርጋ የሚቀይሩበት ሁኔታ መስተዋሉን ገልጸዋል።

በመሆኑም በአዲሱ የተሽከርካሪ መለያ ሰሌዳ መሰረት ለተሽከርካሪዎች የሚሰጠው ታርጋ እንዳይፈታ በማድረግ፣ ምናልባት ከተፈታ እንኳ ከተሽከርካሪው በሚለጠፍ ስቲከር አማካኝነት በመፈተሽ ሕገወጥ የተሽከርካሪ ሰሌዳ ቅየራን ለማስቀረት እንደሚቻል አስረድተዋል።

ጥፋት የሚፈጽሙ ታርጋቸው ተፈትቶ የሚቀጡበት አሰራር አለ፣ ታዲያ በአዲሱ አሰራር የማይፈታ መለያ ሲሰጥ ከዚህ ጋር አይጣረስም ወይ ? በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄም፣ “ ጥፋት ሲፈጸም ሰሌዳ ይፈታል የሚል ሕግ የለም ” ብለዋል ሚኒስትሩ።

በኢትዮጵያ በተለምዶ ስለሚፈታ እንጂ በሌሎች ባደጉት አገራት ጥፋት የፈጸመ ተሽከርካሪን ለመቅጣት ቤት ድረስም ይኬዳል እንጂ ማስቆም አያስልግም ያሉት ሚኒስትሩ፣ “ ጥፋተኛን ለመቅጣት ሰሌዳ መፍታት አያስፈልግም ” ሲሉም ተደምጠዋል።

የተቋሙ ሚኒስትር ዴዔታ አቶ በርሆ ሀሰንም ይህንኑ ሀሳብ ተጋርተው፣ ታርጋ እንዳይፈታ የሚያደርግ አሰራር እየተዘረጋ መሆኑን አስረድተዋል።

ሰሌዳ ለመቀየር ወጭውን የሚሸፍነው ማነው ? በሚል ለቀረበው ጥያቄ ምላሽ የሰጡት አለሙ ስሜ (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ “ሁሉም የራሱን ወጭ ይሸፍናል፣ የሚቀየረው የመስሪያ ቤት ተሽከርካሪ ከሆነም መስሪያ ቤቱ ይከፍላል” ነው ያሉት።
 
የተሽከርካሪ ምዝገባ ለመጨረሻ ጊዜ የተካሄደው በ1994 በመሆኑ በግምት ወደ 1.6 ሚሊዮን ተሽከርካሪዎች እንዳሉ ቢታመንም ትክክለኛው ቁጥር እንደማይታወቅ ገልጸው፣ “ አዲሱ አሰራር ተሽከርካሪን በአዲስ ለመለየትና የተሽከርካሪን ቁጥር ለመለየት ይረዳል ” ብለዋል።

ወደ 2 ሚሊዮን የተሽከርካሪ መለያ ሰሌዳ ለማምረት መታቀዱን፣ አዲሱን መለያ የመቀየር ስራውም ከሁለት እስከ ሦስት ወራት ባለው ጊዜ ተግባራዊ እንደሚደረግ፣ ትክክኛ ቀኑን መግለጽ ግን እንደሚያስቸግር ተገልጿል።

“ በአዲሱ አሰራር ቀደም ሲል የነበረውን የተሽከርካሪ ሰነድ በመለየት በድጋሚ የሚረጋገጥ ይሆናል ” ሲሉም ተናግረዋል።

በሌላ በኩል፣ እስከዛሬ በነበረው አሰራር ተሽከርካሪዎች የመጡበት ክልል የሚገልጽ መለያ መሰጠቱ፣ ለአድሎዓዊ አሰራር ሲዳርግ መቆየቱ የተገለጸ ሲሆን፣ በአዲሱ አሰራር "ETH" ወይም "ኢት" በሚል ኮድ ብቻ ስለሚሰጥ ችግሩ እንደሚቀረፍ ሚኒስትሩ አረድተዋል።

ነባሩን የተሽከርካሪ መለያ ሰሌዳ ቁጥር በአዲስ መልኩ መተካት ካስፈለባቸው ምክንያቶች መካከል የተሽከርካሪ ሰሌዳ አመራረትና አሰረጫጨት የአሰራር ክፍተትና የሃብት ብክነትንና ሕገወጥ የታርጋ ቅየራን ማስቀረት፣ የተሽከርካሪዎችን ብዛት ለማወቅ ማስቻል ተጠቃሽ ናቸው ተብሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
1.15K👏99🙏25😡25🤔18🕊15😢10💔9🥰7😱6😭5
የቀድሞ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ፕሬዝዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ኡመር ኢድሪስ በጠና መታመማቸውን ከቤተሰቦቻቸው ተሰምቷል።

ታላቁ የሃይማኖት አባት ህክምናቸውን እዚሁ ሀገር ውስጥ በሚገኝ ሆስፒታል እየተከታተሉ እንደሚገኙ ነው የተገለጸው።

ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ኡመር ኢድሪስ ከ2011 ጀምሮ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት በመሆን ለ3 ዓመታት መርተዋል።

@tikvahethiopia
😢2.15K😭465373💔280🙏262🕊107👏29😱20😡13🥰1
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#DV

የ2027 የአሜሪካ ዳይቨርሲቲ ቪዛ ሎተሪ (ዲቪ) ማመልከቻ ቀን በዚህ ወር ይፋ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።

ዘንድሮ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ለዳይቨርሲቲ ቪዛ (ዲቪ) ሎተሪ ምዝገባ 1 ዶላር የአገልግሎት ክፍያ ማስከፈል ይጀምራል።

ይኸው ክፍያ ተመርጦ ወይም ዲቪ ሲደርስ ከሚከፈለው 330 ዶላር ውጪ ነው። አመልካቾች ማሸነፋቸው ሲረጋገጥ ለቪዛ አገልግሎት 330 ዶላር ይከፍላሉ።

በዚህ ወር የምዝገባው ቀን ይፋ የሚደረገው የ2027 ዲቪ ሎተሪ እንደከዚህ ቀደሙ አሰራር ከሆነ እስከ ህዳር ወር ድረስ ይቆያል (ማመለከቻ ጊዜው) ፤ ውጤቱ ደግሞ በግንቦት ወር 2026 ይታወቃል።

በየዓመቱ እንደሚደረገው 55,000 አሸናፊዎች ከመላው ዓለም ይታወቃሉ።

ለዲቪ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ስለሚያመለክቱ አሜሪካ ዘንድሮ በምትጀምረው የ1 ዶላር ክፍያ ለስራ ማስኬጃዎች የሚሆናትን በሚሊዮኖች ዶላር ታገኛለች ተብሎ ይጠበቃል።

በየዓመቱ ለአሜሪካ ዲቪ ከዓለም የተለያዩ ሀገራት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች የሚያመለክቱ ሲሆን ለአብነት ለ2025ቱ ዲቪ ወደ 19,927,656 ሰዎች አመልክተዋል። ከነዚህም 131,060 ሰዎች ለቀጣይ ሂደት ተምርጠው ከነሱ ውስጥ 55,000 ሰዎች ቪዛው ተሳክቶላቸዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
511.63K🙏265😭90🤔68😡58💔43🥰36🕊32😢27👏21😱10
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ወደ መቐለ የሚያመሩ መንገዶች ዛሬም ለሁለተኛ ቀን በሁለት አቅጣጫ በትግራይ ኃይል ሰልፈኞች ተዘግተዋል። የተዘጉት መንገዶች በትግራይ ምስራቃዊ ዞን ከመቐለ በ35 ኪሎ ሜትር ርቀት በምትገኘው የኣጉላዕ ከተማ ፤ በደቡባዊ ዞን ከመቐለ 100 ኪሎ ሜትር አከባቢ በምትርቀው የመኾኒ ከተማ መሆኑ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ መረጃ ደርሶታል። በተጨማሪ በሰሜን ምዕራብ ዞን ወደ እንዳስላሰ-ሽረ…
" ያነሱትን የደመወዝ ጭማሪ ፣ የጥቅማ ጥቅምና የመሬት ጥያቄ ለመመለስ የሚያስችል መመሪያ ለማውጣት ተዘጋጅተናል " - የክልሉ ካቢኔ

ዛሬ የትግራይ ኃይል አባላት ለሶስተኛ ቀን በአራት አቅጣጫ መንገዶችን ዘግተው ነበር።

ሁለቱ መንገዶች ከምስራቃዊና ደቡባዊ ዞኖች ወደ መቐለ ከተማ የሚወስዱ ሆነው ከከተማዋ በ35 እና በ100 ኪሎ ሜትር ርቀት በኣጉላዕና በመኾኒ የተዘጉ ነበሩ።

ሶስተኛው ከእንዳባጉና ወደ እንዳስላሰ-ሽረ ከተማ የሚያስገባ ሲሆን አራተኛው ደግሞ ከዓድዋ ወደ ዓዲግራት በሚወስደው መንገድ ' ሴሮ ' የተባለው አከባቢ ነበር።

ለግል የስራ ጉዳይ ከመቐለ በተምቤን በኩል ወደ አክሱም የተጓዘው የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል በዓድዋ በኩል ወደ ዓዲግራት ከተማ ሲጓዝ ' ሴሮ ' በሚባል አከባቢ መንገድ ከተዘጋባቸው ተጓዦች አንዱ ነው።

እንደ አባላችን የአይን ምልከታ መንገዱ ከጥዋቱ 2:30 ተዘግቶ ከሰዓት በኃላ 9:40 ነው የተከፈተው።

የአከባቢው አስተዳዳሪዎች መንገዱን የዘጉትን የትግራይ ኃይል አባላት ለማነጋገር ጥረት ቢያደርጉም " ከክልሉ ፕሬዜዳንት ለተላከ አመራር ካልሆነ ለሚድያም ይሁን ለአከባቢው አስተዳዳሪዎች ቃላችን ለመስጠት ፍቃደኛ አይደለንም " በማለት ከልክለዋል።

በዚሁ ቃላቸው ፀንተው በግራና በቀኝ የተጓዙ መኪኖች በማቆም በርካታ ተጓዦች ለእንግልት ተደርገው ቆይተዋል።

ከቀኑ 9:40 መንገዱ እንዲከፈት ተደርጓል።

መንገዱ የተከፈተው በስልክ ተነጋግረው ካልሆነ በስተቀር ወደ ቦታው በአካል የመጣ የክልሉ ከፍተኛ አመራር እንደሌለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል አረጋግጧል።

ወደ መቐለና ወደ እንዳስላሰ-ሽረ ከተማ የሚያመሩ ሶስት መንገዶች ከሰዓት በፊት ሲከፈቱ ፤ አባላችን የነበረበት አቅጣጫ ከሰዓት በኃላ ነው የተከፈተው።

የክልሉ ካቢኔ በመንግስት የኮሚኒኬሽን ቢሮ በኩል ጥቅምት 5 ቀን 2018 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ፤ " የሰራዊቱ አባላት ያነሱት የደመወዝ ጭማሪ ፣ የጥቅማ ጥቅምና የመሬት ጥያቄ ለመመለስ የሚያስችል መመሪያ ለማውጣት ተዘጋጅተናል " ሲል አስታውቋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
1.28K👏88🕊52🤔37😭24🙏18😢11🥰10😡10💔7😱1
እነሆ ጊዜዎን የሚያቀል አዲሱ አገልግሎታችን ! ገንዘብ ገቢ ወይም ወጪ ለማድረግ ወደ ባንካችን ቅርንጫፍ ሲሄዱ፣ ቀድመው በአቢሲንያ ሞባይል መተግበሪያ ፎርሙን በመሙላት ጊዜዎን ይቆጥቡ። ሲጨርሱ በእጅ ስልክዎ ልዩ ቁጥር ይደርስዎታል። የባንካችን ቅርንጫፍ እንደ ደረሱም፣ የተላከልዎትን ቁጥር በማሳየት የፈለጉትን የቅርንጫፍ አገልግሎት በቀላሉ ማግኘት ይችላሉ። #ወረቀትአልባየባንክአገልግሎት #Paperlessbranchmodel #BanksinEthiopia #AddisAbaba #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
149😡13🙏7👏5🥰4😭2🕊1
ዛሬዉኑ የM-PESAን ማህበራዊ ሚዲያ ገፆች ይቀላቀሉ።

Telegram: https://www.tg-me.com/mpesaethiopia733

LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/m-pesaethiopia/

Facebook: https://www.facebook.com/61572410606905/

Instagram: www.instagram.com/mpesa.ethiopia

X (Twitter): M-PESA Ethiopia (@m_ethiopia58462) / X

TikTok: https://www.tiktok.com/@mpesa.ethiopia/

YouTube: https://youtube.com/@m-pesaethiopia?si=jldsrSE888ts2ZOe

መተግበሪያውን ለማውረድ ይህንን ይጫኑ:

https://onelink.to/ewsb22


#MPESA #MPESAEthiopia
87🙏5😡3
TIKVAH-ETHIOPIA
#Kenya የኬንያው ጉምቱ ፖለቲከኛ ራይላ ኦዲንጋ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ ህንድ ሀገር በህክምና ሲረዱ ቆይተው በ80 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። ራይላ ኦዲንጋ ለኬንያ ፕሬዚዳንትነት 5 ጊዜ ዕጩ ሆነው ቢቀርቡም አልተሳካላቸውም። በተጨማሪ በቅርቡ ለአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበርነት ቦታ ቢወዳደሩም ማሸነፍ ሳይችሉ ቀርተዋል። ለረጅም አመታት…
#Kenya

‎የኬንያ የቀድሞ ጠቅላይ ሚንስትር ራይላ ኦሞሎ ኦዲንጋ ሞት ተከትሎ በናይሮቢ ከተማ ዉጥረት ነግሶ ውሏል።

የቲክቫህ ኢትዮጵያ - ናይሮቢ

‎በሕንድ ሀገር በሕክም ላይ እያሉ ሕይወታቸው ያለፈዉን የቀድሞ የኬንያ ጠቅላይ ሚንስትር ራይላ ኦሞሎ ኦዲንጋ ተከትሎ በኬንያ ከተሞች የተለያዩ ሰልፎችና መሰል እንቅስቃሴዎች የተስተዋሉ መሆኑን ናይሮቢ የሚገኘው የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባል ገልጿል።

በዋና ከተማዋ ናይሮቢ ሱቁችን የመሰባበርና በአሁኑ ወቅት ሀገሪቱን እየመሩ የሚገኙት ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ስልጣን እንዲለቁ የሚጠይቁ መፎክሮችን ያነገቡ ሰልፈኞች በብዛት መስተዋላቸውን በስፍራው የሚገኘው አባላችን አመልክቷል።

‎በናይሮቢ ከተማ እሲሊ፣ ካሜይኮ አከባቢዎች እነዚህ እንቅስቃሴዎች የተደረጉ ሲሆን በአብዛኛው የሀገሪቱ ክፍሎች ሀዘናቸውን የሚገልፁ ዜጎች የተለያዩ ቅጠሎችንና የስራ መሳሪያዎችን ይዘዉ በየመንገዱ ታይተዋል።

‎ከዚህም በተጨማሪ በሀገሬዉ ሕዝብ በእጅጉ የሚወደዱትና በወቅቱ የኬንያ ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ 'የነፃነት ታጋይ፣ የሀገር ወዳድነት ተምሳሌትና የዴሞክራሲ አባት' ተብለዉ የተገለፁት ጉምቱዉ ፖለቲከኛ ራይላ ኦሞሎ ኦዲንጋ በተወለዱበት የኬንያ ሶስተኛዋ ትልቅ ከተማ ኪሱሙ፣ ናይኩሩና ቦባሳ አከባቢዎችም ሰልፍ መሰል እንቅስቃሴ ጎልቶ ተስተዉሏል።

‎የራይላ ኦዲንጋ አስክሬን ወደ ሀገራቸው ገብቶ እሁድ በተወለዱበት አከባቢ ኪሱሙ ሲያያ ካዉንቲ ቦንዶ በባለ ስፍራ ግብአት መሬታቸው እንደሚከናወን ተሰምቷል።

የራይላ ኦዲንጋን ሞት ተከትሎ የፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ አስተዳደር የ7 ቀን ሀዘን አውጇል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ናይሮቢ
#TikvahEthiopiaFamily

@tikvahethiopia
543😭59🤔19🕊18🙏9😡6👏5🥰2😢1
TIKVAH-ETHIOPIA
" ያነሱትን የደመወዝ ጭማሪ ፣ የጥቅማ ጥቅምና የመሬት ጥያቄ ለመመለስ የሚያስችል መመሪያ ለማውጣት ተዘጋጅተናል " - የክልሉ ካቢኔ ዛሬ የትግራይ ኃይል አባላት ለሶስተኛ ቀን በአራት አቅጣጫ መንገዶችን ዘግተው ነበር። ሁለቱ መንገዶች ከምስራቃዊና ደቡባዊ ዞኖች ወደ መቐለ ከተማ የሚወስዱ ሆነው ከከተማዋ በ35 እና በ100 ኪሎ ሜትር ርቀት በኣጉላዕና በመኾኒ የተዘጉ ነበሩ። ሶስተኛው ከእንዳባጉና ወደ…
#Tigray

የትግራይ ኃይል አባላት ሰልፈኞች ለአራተኛ ቀን ዛሬ የመኪና መንገድ ዘግተዋል።

ዛሬ ጥቅምት 6/2018 ዓ.ም የትግራይ ምስራቃዊ ዞን ዋና ከተማ ወደ ሆነችው የዓዲግራት ከተማ የሚያስገቡና የሚያስወጡ ሶስት ዋና መንገዶች ተዘግተዋል።

ትናንት ጥቅምት 5/2018 ዓ.ም ከዓድዋ ወደ ዓዲግራት ሲጓዝ ሴሮ በተባለ ቦታ መንገድ ተዘግቶበት ከሰዓት በኃላ ተከፎቶ ወደ ከተማዋ የተጓዘው የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል እንዳረጋገጠው ፤ ከዓዲግራት ወደ መቐለ ዓድዋና ዛላአንበሳ አቅጣጫ የሚያመሩ መንገዶች ተዘግተዋል።

ከጥቅምት 3/2018 ዓ.ም ወዲህ ከክልሉ ምስራቃዊ ፣ ደቡባዊ ዞኖች ወደ መቐለ የሚወስዱ መንገዶች በኣጉላዕና ፣ በመኾኒ ወደ እንዳስላሰ-ሽረ ከተማ የሚወስድ መንገድ በእንዳባጉና ከዓድዋ ወደ ዓዲግራት የሚወስድ በሴሮ ተዘግተው በዚያው ቀን በተለያዩ ሰዓቶች መከፈታቸው ይታወሳል።

የክልሉ ካቢኔ በመንግስት የኮሙኒኬሽን ቢሮ በኩል ጥቅምት 5/2018 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ፤ የሰራዊቱ አባላት ያነሱት የደመወዝ ጭማሪ  የጥቅማ ጥቅምና የመሬት ጥያቄ ለመመለስ የሚያስችል መመሪያ ማውጣቱን ትላንት አሳውቆ ነበር።

ያም ቢሆን ግን ዛሬም መንገዶች ተዘግተዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
472👏71🕊47😡30😭17😢14🤔8🥰7
2025/10/24 10:48:14
Back to Top
HTML Embed Code: