Telegram Web Link
TIKVAH-ETHIOPIA
" ባለቤቴንና አምስት ልጆቼን ነው ያጣሁት " - ተጎጂ አባት ➡️ " ጥቃቱን ያደረሱት ጽንፈኛ የሚባሉ በዚሁ በወሰን አከባቢ ሸምቀው ያሉ ታጣቂዎች ናቸው ! " - የአካባቢው ነዋሪ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ኖኖ ወረዳ ቆንዳላ ቀበሌ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት ቢያንስ 14 ሰዎች ተገደሉ። ጥቃቱ ከትናንት በስቲያ ሃሙስ ሃምሌ 03 ቀን 2017 ዓ.ም. ምሽት ነው የተፈጸመው። የታጠቁ አካላት በመደዳው…
" 22 ሰዎች ወዲያው መገደላቸው ሲረጋገጥ ቀሪዎቹ አስከሬናቸው በየጥሻው የወደቁና በሆስፒታል ህይወታቸው ያለፉ ናቸው አጠቃላይ ሟቾች 29 ናቸው " - ነዋሪዎች

➡️  " ' የተገደሉት 22 ናቸው ' የሚባለው ውሸት ነው። 12 ናቸው የተገደሉት። ከ22 በላይ የተገደሉት ከታጣቂዎቹ ወገን ነው " - የወረዳው አስተዳዳሪ

በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ታጣቂዎች ህጻናትና ሴቶችን ጨምሮ በርካታ ንጹሃንን ገድለዋል።

የንጹሃን ግድያ ተደጋግሞ በተሰማበት በምዕራብ ሸዋ ዞን ኖኖ ወረዳ ሃሎዲንቂ ቀበሌ እሁድ ምሽት በግምት ሁለት ሰዓት ግድም የታጠቁ አካላት ባደረሱት ጥቃት ከ20 በላይ ሰዎች ወዲያው መገደላቸውን ተጎጂዎች እና የአከባቢው ነዋሪዎች ለዶቼ ቨለ ተናግረዋል፡፡

ነዋሪዎቹ ምን አሉ ?

" ጥቃቱ እሁድ ምሽት ነው የተፈጸመው።

አገር ሰላም ብለው እንደወትሮው ወደ ቤታቸው በገቡ ንጹሃን የኖኖ ወረዳ ሃሎዲንቂ ቀበሌ ነዋሪዎች ላይ ነው የተፈጸመው።

በአጎራባች የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ጉራጌ ዞን ወረዳዎች የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ወሰን ተሻግረው ነው ጥቃቱን ያደረሱት።

ምንም ያልታጠቁ ሰላማዊ ዜጎች ላይ ዘግናኝ ግድያ ነው የተፈጸመው። ጥቃቱን ያደረሱት ደግሞ በአከባቢው የሚንቀሳቀሱ ጽንፈኛ የተባሉ ታጣቂዎች ናቸው።

በእሁድ ምሽቱ ድንገተኛ ጥቃት 22 ሰዎች ወዲያው ተገድለዋል።

ዳርጌ በሚባል ስፍራ ምሽት ከአንድ እስከ ሁለት ሰዓት ግድም በተወሰደው በዚህ ጥቃት ህጻናት እና ሴቶች በስፋት ተጠቂ ሆነዋል። " ብለዋል።

ቤተሰቦቻቸው የጥቃቱ ሰለባ የሆኑባቸውና ለደህንነታቸው ስማቸውን መናገር ያልፈለጉ አንድ ነዋሪ " ሰላማዊ ዜጎችን በጭለማ ገብተው ነው የፈጁዋቸው፡፡ አሁን በእሁድ ምሽቱ በዚህ ጥቃት የተገደሉ ሰዎች ቁጥር 29 ደርሰዋል " ሲሉ ተናግረዋል።

" 22 ሰዎች ወዲያው መገደላቸው ሲረጋገጥ ቀሪዎቹ አስከሬናቸው በየጥሻው የወደቁና በሆስፒታል ህይወታቸው ያለፉ ናቸው " ብለዋል፡፡

ነዋሪዎቹ የተገደሉትን ለመለየት ሰኞ እስከ ምሽት የአስከሬን አሰሳ በአከባቢው ሲደረግ እንደነበር ጠቁመዋል።

ከሟቾች አባወራ የሆኑ ትልልቅ ሰዎች ከስድስት የማያልፉ ሲሆን ቀሪዎቹ ህጻናት እና አብዛኛው ደግሞ ታዳጊ ተማሪዎች እና ሴቶች ናቸው ሲሉ ተናግረዋል።

የኖኖ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ወንዳፍራሽ ሉሌሳ ፥ " የተገደሉት 22 ናቸው የሚባለው ውሸት ነው። 12 ናቸው የተገደሉት። ከ22 በላይ የተገደሉት ከታጣቂዎቹ ወገን ነው " ብለዋል።

ጥቃቱ ከተፈጸመ በኋላ የመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች በአካባቢው ተሰማርተው እርምጃ መውሰዳቸውን ገልጸዋል።

በዚህ ወረዳ ተመሳሳይ ጥቃት ለምን ተደጋገመ ?

ነዋሪዎች እንደሚሉት በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን አጎራባች በሆነው የጉራጌ ዞን አበሽጌ ወረዳ ውስጥ ወታደራዊ ስልጠና የሚወስዱ ታጣቂዎች አሉ።

እኚህ ታጣቂዎች በተደጋጋሚ እየገቡ ህጻናትን ጨምሮ ያገኙትን በምንም ፖለቲካ ውስጥ የሌሉ ሰላማዊ ሰዎችን እያጠቁ ይመለሳሉ፡፡

" እነዚህ ሟቾች ምንም ውስጥ የሌሉና ምንም ጥፋት የሌለባቸው ናቸው " የሚሉት ነዋሪዎቹ ፥ ጥላቻ እና ማንነት ላይ የሚያተኩር ጥቃት እንደሆነ ገልጸዋል።

ይህ ካልሆነ ከሶስት ዓመት እስከ 14 ዓመት እድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ህጻናት ምን ውስጥ ይሆናሉ ተብሎ ይታሰባል ? ሲሉ ጠይቀዋል።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ጉራጌ ዞን አበሽጌ ወረዳ በተለያዩ ቀበሌዎች የሚንቀሳቀሱ ጥቃት አድራሾቹ በምዕራብ ሸዋ ዞን ኖኖ ወረዳ በተለያዩ ጊዜያት በተፈጠረ ግጭት ቤተሰቦቻቸውን ይዘው የተፈናቀሉም እንደሚገኙባቸው ገልጸዋል፡፡

" ወደ ጉራጌ ዞን የሄዱት ሰዎች የኦሮሞ ነጻነት ጦር የሚፈጽመውን ጥቃት እንዲሁም በአካባቢው አስተዳደር ከመሬት ይዞታ ጋር በተያያዘ በወጣ አዲስ አሠራር ምክንያት ነው " ሲሉ ነዋሪዎች አመልክተዋል።

" አሁን ላይ ጥቃት ከሚያደርሱ ታጣቂዎቹ አብዛኞቹ በ2016 ዓ.ም. በአንድ ሰርግ ላይ ቦምብ ተጥሎ 36 ሰዎች ግድም መገደላቸውን ተከትሎ ከአከባቢው የተፈናቀሉ ናቸው " ብለዋል።

ሰኔ ወር 2016 ዓ.ም. በዚሁ ኖኖ ወረዳ ቆንዳላ ቀበሌ በአንድ ሰርግ ቤት ላይ ቦምብ ተጥሎ ሙሽሮችን ጨምሮ 36 ሰዎች ከተገደሉ በኋላ ተደጋጋሚ የንጹሃን ጥቃቶች እና የግድያ ዜናዎች ከዚህ አከባቢ ተለይቶ አያውቅም፡፡

በቅርቡ 2017 ዓ.ም. ሰኔ ወር ላይ ዳግም በንጹሃን ላይ ባነጣጠረው የዚሁ አከባቢ ጥቃት ከአንድ ቤት የተገደሉ ስድስት የቤተሰብ አባላትን ጨምሮ 14 ሰላማዊ ነዋሪዎች አልቀዋል።

የጸጥታ ስጋቱ በተደጋገመበት የኖኖ ወረዳ አዋሳኝ ቀበሌያት አከባቢ የነዋሪዎቹ ስጋት ከጊዜ ወደ ጊዜ ዘላቂ እልባት ከማግኘት ይልቅ እያደር እየከፋና እየተባባሰ መምጣቱን የአከባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል።

የኖኖ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ወንድአፍራሽ ሉሌሳ ጥቃት የሚያደርሱት ወገኖች ፤ የመንግሥት የፀጥታ አካላት የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ላይ ሲዘምት በሚያገኙት አጋጣሚ ጥቃት እንደሚፈጽም ይናግራሉ።

" ዓላማቸው በሕገ ወጥ መንገድ ሰፍረው መሬት በመውረር ግብር የማይከፍሉበት መሬት ማግኘት ነው። ' ከመሬቱ ተፈናቅለናል አሁን መመለስ አለብን ' በሚል ነው ጥቃት የፈጸሙት። ይህ ግን ሕልም ነው " ብለዋል።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ እና ቢቢሲ አማርኛ ነው።

ከዚህ ወረዳ ጋር በተያያዘ ከዚህ ቀደም ምን መረጃዎች ተላልፈው ነበር ?

በጥቂቱ ፦
https://www.tg-me.com/tikvahethiopia/86904

https://www.tg-me.com/tikvahethiopia/87947

https://www.tg-me.com/tikvahethiopia/88299

https://www.tg-me.com/tikvahethiopia/98393

@tikvahethiopia
871😭753😡60💔33🕊22😢21🙏9😱6🥰4🤔1
TIKVAH-ETHIOPIA
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የቅዱስ ሲኖዶስ ዓቢይ ጉባኤ በዛሬው ዕለት በጸሎት መከፈቱን ቤተክርስቲያኗ አሳውቃናለች። @tikvahethiopia
" የሰላምና የዕርቅ ዕድል ቅድሚያ እንዲሰጠው ጉባኤው የበኩሉን ጥረት ማድረግ ይገባዋል " - ቅዱስነታቸው

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የቅዱስ ሲኖዶስ ዓቢይ ጉባኤ መጀመሩን አስመልክቶ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በዚህም መልዕክታቸው የርስ በርስ ግጭቶች ቆመው ግጭቶች በውይይት እና በድርድር እንዲፈቱ ጉባኤው የበኩሉን ጥረት ማድረግ እንደሚገባው አስገንዝበዋል።

ቅዱስነታቸው ምን አሉ ?


" በሀገራችን ያለው ያለመረጋጋት በሕዝባችን አጠቃላይ ሥነ ልቡና በሀገሪቱ አንድነትና ዕድገት የሚያስከትለውን ጫና በቀላሉ የሚታይ አይሆንም፤ የሕዝቡ ሥነ ልቡና ከተጐዳ የነገው ዕድል ጤናማ ይሆናል ተብሎ አይታሰብም፡፡

ችግሩ እየታየ ያለው በዋናነት በሀገራችን ፖለቲከኞች በመሆኑ ነገሩ የተወሳሰበና የተራዘመ እንዲሆን አድርጎታል፤ በመሆኑም ይህ የርስ በርስ ግጭት ቆሞ ችግሮች በውይይትና በድርድር በመፍታት የወንድማማች እልቂት የሚያስቆም የሰላምና የዕርቅ ዕድል ቅድሚያ እንዲሰጠው ጉባኤው የበኩሉን ጥረት ማድረግ ይገባዋል፡፡

የነገው ትውልድ ልማታዊ ተስፋ እውን ሊሆን የሚችለው ሰላምና አንድነት ሲኖር ነውና መንግሥት፣ ተፎካካሪ ፖለቲከኞችና ነፍጥ ያነሡ ወገኖች ሁሉ ለሰላም መስፈንና ለልማት ዕድገት መረጋገጥ ሲባል ወደ መግባባት እንዲመጡ በእግዚአብሔር ስም አባታዊ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡ " ብለዋል።

(የቅዱስነታቸው ሙሉ መልዕክት ከላይ ተያይዟል)

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ

@tikvahethiopia
41.78K🙏151🕊76🥰38😭17👏13😢6😡5😱2💔1
#National_ID

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ላይ ለመቀመጥ ብሔራዊ መታወቂያ (National ID) ቅድመ ሁኔታ ተደረገ።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት " ብሔራዊ መታወቂያ (National ID) ለፈተና ለመቀመጥ ቅድመ ሁኔታ ነው " ብሏል።

" ማንኛውም የ2018 ትምህርት ዘመን 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ተፈታኝ ብሔራዊ መታወቂያ (National ID) ከፈተና ምዝገባ ቀድሞ ማውጣትና በእጁ መያዝ ይገባዋል " ሲል አሳውቋል።

" ብሔራዊ መታወቂያ (National ID) የሌለው ተማሪ ለፈተና መመዝገብ ሆነ በማንኛውም ሁኔታ መፈተን አይችልም " ሲል አስገንዝቧል።

ተማሪዎች የብሔራዊ መታወቂያ (National ID) ይዘው እንዲገኙ ፦
- የተማሪ ቤተሰብ
- መምህራን
- የትምህርት አመራሮች
- የሚዲያ አካላት ተገቢውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።

#National_ID

@tikvahethiopia
653😡232😭45🤔39🙏23🕊20👏17💔16😱14😢10
#AddisAbaba

የዘረፋ ወንጀል ፈፅመው ለማምለጥ የሞከሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ገለፀ፡፡

ተጠርጣሪዎቹ የፀጥታ አካል የሚመስል የደንብ ልብስ በመልበስ የዘረፋ ወንጀል ፈፅመው በቁጥጥር ስር የዋሉት ጥቅምት 11 ቀን 2018 ዓ/ም በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ጃክሮስ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው፡፡

አብርሃም አሸናፊ እና ዳግም ብርሃን የተባሉት ሁለት ተጠርጣሪዎች ወንጀሉን የፈፀሙት ረድኤት አህመድ በተባለች ግለሰብ ላይ እንደሆነ ፖሊስ ገልጿል።

የግል ተበዳይ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ልዩ ቦታው አባ ሳሙኤል መቶ አርባ ሰፈር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሚገኝ የንግድ ሱቋን ዘግታ በመውጣት የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 2B- 88595 አ.አ የሆነ ተሽከርካሪ እያሽከረከረች ስትጓዝ ከጥቂት ሜትሮች ጉዞ በኋላ  እንዳስቆሟት ታውቋል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ የግል ተበዳይን ከሾፌር መቀመጫ ላይ አስወርደው ከኋላ እንድትቀመጥ ካደረጉ በኋላ ተሽከርካሪውን ራሳቸው እያሽከረከሩ በሚፈልጉት አቅጣጫ እንደወሰዷት እና 500 ሺህ ብር ወደ አካውንታቸው እንድታስገባ እንዳስገደዷት የፖሊስ ምርመራ መዝገቡ ያስረዳል፡፡

የግል ተበዳይ የተጠየቀችውን ያህል ገንዘብ እንደሌላት ስትገልፅላቸው በወቅቱ በእጇ ይዛው የነበረውን 8ሺህ 700 ብር ጥሬ ገንዘብ እና ሁለት ሞባይል ስልኮችን ዘርፈው እሷን ካስወረዱ በኋላ መኪናውን እየነዱ በተቃራኒ አቅጣጫ ተጉዘውለማምለጥ ሲሞክሩ ከሌላ ተሽከርካሪ ጋር  ተጋጭተው የትራፊክ አደጋ አድርሰዋል፡፡

ከአደጋው በኋላ ከተሽከርካሪው ወርደው በመሮጥ ሰው ቤት ገብተው ሊሰወሩ ቢሞክሩም ሳጅን ፋንታሁን አለምነህ በተባለ የአዲስ አበባ ፖሊስ ሞተረኛ ትራፊክ እና በህብረተሰቡ ትብብር ከነ ኤግዚቢቱ በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

ግለሰቦቹ ከፀጥታ አካል ጋር ተመሳሳይነት ያለው የደንብ ልብስ ይልበሱ እንጂ የፀጥታ አካል እንዳልሆኑ መረጋገጡን እና ከወንጀሉ ጋር ተያይዞ ተጨማሪ ምርመራ እየተካሄደ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ገልጿል፡፡ 

የፀጥታ አካል በመምሰል እና ተመሳሳይነት ያለው የደንብ ልብስ በመልበስ ወንጀል የሚፈፅሙ ግለሰቦች ሊያጋጥሙ እንደሚችሉ ህብረተሰቡ ተገንዝቦ አጠራጣሪ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙት ለሚመለከተው የፀጥታ አካል ጥቆማ እና መረጃ በመስጠት ትብብሩን እንዲያጠናክር ፖሊስ ጥሪውን አቅርቧል።

#AddisAbabPolice

@tikvahethiopia
22.56K👏632🙏164🤔85😱66💔44😭43😡40🕊23🥰20😢20
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ገንዘብ ገቢ ወይም ወጪ ለማድረግ ወደ ባንካችን ቅርንጫፍ ሲሄዱ፣ ቀድመው በአቢሲንያ ሞባይል መተግበሪያ ፎርሙን በመሙላት ጊዜዎን ይቆጥቡ። ሲጨርሱ በእጅ ስልክዎ ልዩ ቁጥር ይደርስዎታል። የባንካችን ቅርንጫፍ እንደ ደረሱም፣ የተላከልዎትን ቁጥር በማሳየት የፈለጉትን የቅርንጫፍ አገልግሎት በቀላሉ ማግኘት ይችላሉ። #ወረቀትአልባየባንክአገልግሎት #Paperlessbranchmodel #BanksinEthiopia #AddisAbaba #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
152🙏5🕊2🥰1😡1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#SamiTech

አዳዲስ ላፕቶፕች ከአንድ ዓመት ዋስትና ጋር!!
@samcomptech

በጥራት፣ በብራንድና በባትሪ ቆይታ አስተማማኝ የሆኑ የተለያዩ ሞዴል ላፕቶፖች በፈለጉት ስክሪን መጠን፣ ኮር አይ እና ጀነሬሽን አሉን።

ለቢሮዎች፣ ለተማሪዎች፣ ለዲዛይን ባለሙያዎች፣ ለጌመሮች ወ.ዘ.ተ. ሁሉም አሉን።

የዕቃዎች ዋጋ፣ ዓይነት እና አድራሻ ለማግኘት 👉 @samcomptech

@sww2844
0928442662 / 0940141114

Telgram : https://www.tg-me.com/samcomptech
116🥰2😱2😢2🕊2🙏1
TIKVAH-ETHIOPIA
‎" ከ6 ዓመታት በፊት የተጀመረዉ መንገድ አለመጠናቀቁ ለዘርፈ ብዙ ችግሮች ዳርጎናል " - የሸካ ዞን ነዋሪዎች ‎ ‎በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ ዞን ነዋሪዎች ፥ የሸካ ዞንን ከተለያዩ ከተሞች የሚያገናኘው መንገድ ተጀምሮ ለረጅም ዘመናት አለመጠናቀቅ ለዘርፈ ብዙ ችግሮች እየዳረገን ነዉ ሲሉ ቅሬታቸዉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሰምተዋል። ‎ ‎ስማቸዉ እንዲገለፅ ያልፈለጉ ሁለት የሸካ ዞን ቴፒ ከተማ …
" የመንገድ ፕሮጀክቱን በፋይናንስ የሚደግፈው የኮሪያው ኤግዚም ባንክ ከፍተኛ አመራሮች በቀጣይ ቀናት አዲስ አበባ ይገባሉ " - የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር

" የጎሬ - ማሻ - ቴፒ መንገድ ፕሮጀክት ወደ ግንባታ ለመመለስ የሚያስችሉ ጉዳዮች እየታዩ ነው "  ሲል የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር አሳወቀ።

መንገዱ በተለያዩ ምክንያቶች ለጊዜው ተቋርጦ እንደሚገኝ ገልጿል።

አስተዳደሩ ፤ 141 ኪሎ ሜትር የሚሸፍነው የጎሬ - ማሻ - ቴፒ መንገድ ፕሮጀክት በዓለም-አቀፉ የሥራ ተቋራጭ ሃይንዳይ ዴቨሎፕመንት ካምፓኒ 4 ቢሊዮን ብር በጀት ተይዞለት ግንባታው ሲከናወን ቆይቷል ብሏል።

ኾኖም የግንባታው አጠቃላይ አፈጻጸም 62 በመቶ ከደረሰ በኋላ ከወሰን ማስከበር ጋር የተያያዙ ችግሮች በወቅቱ አለመቀረፋቸውን እንዲሁም የግንባታ ውል ዝርዝር ጉዳዮች ላይ የነበሩ አለመግባባቶችን በምክንያትነት በማንሳት የሥራ ተቋራጩ ግንባታውን ለጊዜው እንዳቋረጠ አስረድቷል።

" የመንገድ ፕሮጀክቱን በፋይናንስ የሚደግፈው የኮሪያው ኤግዚም ባንክ ከፍተኛ አመራሮች በቀጣይ ቀናት አዲስ አበባ ይገባሉ " ያለ ሲሆን " ግንባታው ዳግም በሚመለስበት ሁኔታ ላይ ከኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች ጋር የሚመክሩ ይሆናል " ብሏል።

" ከዚሁ ጎን ለጎን የትራንስፖርት እንቅስቃሴው እንዳይስተጓጎል አስፈላጊ የጥገና ሥራ በመከናወን ላይ ይገኛል። የመንገድ ግንባታው ዳግም እስኪጀመር ድረስም የጥገና ሥራው የሚቀጥል ይሆናል " ሲል አሳውቋል።

ይህ የመንገድ ፕሮጀክት ኦሮሚያንና ጋምቤላን በኢሉ አባቦር በኩል እና ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያን በሸካ ዞን በኩል በቅርበት በማስተሳሰር ከፍተኛ ጠቀሜታ የሚያበረክት ነው፡፡

ከዚህ ባሻገር ስድስት ወረዳዎች እና ከ15 በላይ ቀበሌዎችን በቅርበት በማገናኘት ማኅበራዊ እና ምጣኔ ሀብታዊ ትስስር የሚያጠናክር ነው፡፡

#ERA

@tikvahethiopia
328😭29🤔10🥰7👏5🙏4😢3😡3🕊1
" እናት ፣ አባት እና ልጃቸው ናቸው በመብረቅ ተመተው የሞቱት " - የወረዳው አስተዳደር

ጥቅምት 11 ቀን 2018 ዓ.ም በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን ዛና ወረዳ 4 ሰዎች በመብረቅ ተመተው ህይወታቸው አልፏል።

በዕለቱ ከቀኑ 11:00 - 3:00 ድረስ ኃይለኛ ዝናብ እንደነበር የወረዳው አስተዳደር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አስታውቋል።

መብረቅ የቀላቀለው ሃይለኛ ዝናብ በወረዳው 8 ቀበሌዎች ዘንቧል።

በሓድነት ቀበሌ ታሕታይ ጎና እምባ መንደር የሚኖሩ ሦስት የአንድ ቤተሰብ አባላት ማለትም እናት ፣ አባት እና ልጃቸው በመብረቅ ተመተው ህይወታቸው አልፏል።

ሌላ አንድ ሰውም እንዲሁ በመብረቅ ተሞቶ ሞቷል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
😭729264😢89💔58🙏23🕊4🥰2👏2🤔1😱1
" ነዋሪው እጅጉን ተከፍቷል በቅርቡ ወረዳውን በማመልከቻ በሰፈራ መልክ ወደ ሌላ ስፍራ እንዲያሰፍረው ቢጠይቅም አሁንም መልስ የሚሰጠው አካል ማግኘት አልተቻለም " - የቀበሌው አስተዳደር

በአማራ ክልል ዋግህምራ ዞን ሰሃላ ሰየምት ወረዳ የቢላዛ ቀበሌ ነዋሪዎች  መንግስት ወደ ሌላ ስፍራ እንዲያሰፍራቸው ጠየቁ።

የቢላዛ ቀበሌ አስተዳዳሪ አቶ ማለደ ብሬ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደተናገሩት ቁጥራቸው ከ3 ሺህ 500 በላይ የሚሆኑ ነዋሪዎች እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሱት  በቀበሌው ምንም አይነት የጤና ተቋም ባለመኖሩ ነዋሪው በቀላል ህመም እየሞተና ህክምና ለማግኘትም ብዙ እንግልት እየደረሰበት በመሆኑ ነው ብለዋል።

አክለውም " ከሳህላ ሰየምት ቢላዛ ቀበሌ የሚወስደው መንገድ በመበላሸቱ የትራንስፖርት አገልግሎት አይሰጥም በዚህ ምክንያት ወላዶችንና የታመሙ ሰዎች ለህክምና ይዘን የምንሄደው ' በቃሬዛ ' ተሸክመን ነው ፤ ይህም ለወጣቶች 7 ሰዓት የእግር ጉዞ ሲጠይቅ ለጎልማሶች ደግሞ እስከ 10:00 ይደርሳል " ብለዋል።

በዚህም ከፍተኛ እንግልት በተደጋጋሚ በመከሰቱ ወላዶች መንገድ ላይ እንደወለዱ ሽማግሌዎችም እንደሞቱ ተናግረዋል።

በዚህ የተማረረው የቀበሌው ነዋሪ መንገዱ እንዲሰራለት በተደጋጋሚ ቢያመለክትም በአካባቢው ባለስልጣናት ዘንድ ትኩረት አላገኘም ብለዋል አቶ ማለደ።

" የቀበሌው ነዋሪ እጅጉን ተከፍቷል በቅርቡ ወረዳውን በማመልከቻ በሰፈራ መልክ ወደ ሌላ ስፍራ እንዲያሰፍረው ቢጠይቅም አሁንም መልስ የሚሰጠው አካል ማግኘት አልተቻለም " ብለዋል።

በጉዳዩ ዙሪያ የሰሃላ ሰየምት ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ሲሳይ ብሩን ቲክቫህ ኢትዮጵያ በስልክ ለመነጋገር በተደጋጋሚ ቢደውልም ስልክ ባለማንሳታቸው ምክንያት አስተያየታቸውን ማካተት አልተቻለም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ባሕር ዳር
#TikvahEthiopiaFamilyBahirdar

@tikvahethiopia
408😭208💔43😢16😡16🤔12🕊6🙏5🥰2
#MinistryofRevenue

" የግብር ክሊራንስ " የምስክር ወረቀት የብድር መከልከያ ምክንያት መሆን የለበትም ሲል የገቢዎች ሚኒስትር ማሳሰቢያ ሰጠ።

የገቢዎች ሚኒስቴር ባንኮች የግብር ክሊራንስ የምስክር ወረቀት ይዘው ለብድር ለሚቀርቡ ደንበኞች የተለመደውን የብድር አገልግሎት እንዳይከለክሉ ማሳሰቢያ መስጠቱ ተመላክቷል።

ሚኒስቴሩ በቅርቡ በሚሰጠው የምስክር ወረቀት ላይ የተቀመጠው የታክስ ቅድሚያ መብት ድንጋጌ የብድር አሰጣጥ ሂደቱን የሚቀይር አዲስ መብት አለመሆኑን በማስታወቅ፣ ባንኮች የምስክር ወረቀቱን ተቀባይነት እንደሌለው ሊያስቡ እንደማይገባ አስታውቋል።

የገቢዎች ሚኒስትር ለብሔራዊ ባንክ እና ለሁሉም ባንኮች በሚል በፃፈዉ ደብዳቤ ላይ እንደተመላከተዉ ግብር ክሊራንስ የምስክር ወረቀት የሚሰጠው ግብር ከፋዩ በሕጉ መሠረት የተጣለበትን ታክስ የመክፈል ግዴታ ሲወጣ መሆኑን ገልጿል።

በተጨማሪም፣ ለታክስ ባለስልጣኑ በቅድሚያ መከፈል እንዳለባቸውና በየትኛውም ህግ ወይም ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ክፍያዎች መሆናቸው በግልጽ ተቀምጧል።

ሚኒስቴሩ እየተሰጠ ባለው የታክስ ክሊራንስ የምስክር ወረቀት ላይ የሰፈረው የቅድሚያ መብት ድንጋጌ፣ ከላይ የተጠቀሰውን የታክስ አስተዳደር አዋጅ ድንጋጌ ለማካተት እንጂ፣ ለባለስልጣኑ ሌላ አዲስ ልዩ መብት ለመስጠት እንዳልሆነ አብራርቷል።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የካፒታል ጋዜጣ ነው።

@tikvahethiopia
438👏32🤔19🥰13🙏9😭5😢3😡3🕊2
2025/10/26 17:37:32
Back to Top
HTML Embed Code: