Telegram Web Link
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update " በክልሉ አድማ ብተናና መደበኛ ፖሊስ እየተወሰደ ያለዉ የሃይል እርምጃዉ ቀጥሎ ከብት በመጠበቅ ላይ የነበሩ 2 ንፁሃን አርሶአደሮች ተገድለዋል " - ነዋሪዎች ➡️ " ' የሃይል እርምጃ ተወስዶ ሁለት አርሶአደሮች ተገድለዋል ' የሚባለው ፍፁም የዉሸት መረጃ ነዉ። ሽፍቶችን ለመያዝ እየተደረገ ባለዉ ኦፕሬሽን እስካሁን የሞተ ሰዉ የለም " - የጋሞ ዞን ፖሊስ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል…
" የሶስት ወጣቶች በመንግስት የፀጥታ ሃይል መገደላቸው ዳግም በአከባቢው ዉጥረት እንዲነግስ ምክንያት ሆኗል " - የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል አቶ አብርሃም አሞሼ

የዘይሴ ብሔረሰብ በአሁኑ ወቅት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን አርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ ስር የሚተዳደር ሲሆን እራስን በራስ ለማስተዳደር ባነሳዉ ጥያቄ መነሻ ባለፉት ዓመታት ለተለያዩ ችግሮች ተዳርጎ መቆየቱን ‎በኢፌዴሪ ሕዝብ ተወካዮች ም/ ቤት አባልና የዘይሴ ብሔረሰብ ተወካይ አቶ አብረሃም አሞሼ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

" ‎የዘይሴ ብሔረሰብ ህዳር 29/1987 ዓ/ም የኢፌዴሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት ከመሰረቱና ሕገ መንግስቱን ካፀደቁ ብሔረሰቦች መካከል አንዱ ቢሆንም እራሱን በራሱ የሚያስተዳድርበት መዋቅር የሌለው በመሆኑ ቋንቋ፣ ባህሉና ማንነቱ እየተበረዘ መምጣቱን ተከትሎ እራሱን በራሱ ለማስተዳደር የመዋቅር ጥያቄ ላለፉት 30 ዓመታት እየጠየቀ ቆይቷል " ብለዋል።

‎በተለያዩ ምክንያቶች የብሔረሰቡ ጥያቄ በአግባቡ ሳይመለስ መቆየቱን ተከትሎ ለተከታታይ ዓመታት ለመንግስት ጥያቄ ሲያቀርብ የቆየዉ የዘይሴ ብሔረሰብ በ6ኛዉ ዙር ሀገራዊ ምርጫ የኢዜማ ፓርቲን በሙሉ ድምፅ በመምረጡ በገዢዉ ፓርቲ ልዩ ልዩ ተፅእኖዎች ሲደረጉበት መቆየቱን ገልጸዋል።

‎በተለይም በአካባቢዉ ባለፉት ሁለት ዓመታት የኢዜማ አመራሮች እና አባላት ያለአግባብ መታሰራቸውንና ከስራም ጭምር መባረራቸዉ እንዲሁም በርካታ አርሶአደሮች ከቀያቸው መሰደዳቸውን በመግለፅ ይህ ድርጊት በአሁኑ ወቅትም መቀጠሉን አስታውቀዋል።

" ‎በጥቅምት መግቢያ የብሔረሰቡ ተወላጅ የሆኑ ሶስት ወጣቶች በመንግስት የፀጥታ ሃይሎች መገደላቸውን ተከትሎ በአከባቢው ውጥረት እንዲነግስ ምክንያት ሆኗል " ያሉት አቶ አብረሃም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህን መረጃ በሰጡበት ዕለትም በአከባቢው ውጥረት መንገሱንና የኢዜማ አመራሮችና አባላት መታሰራቸውን ተናግረዋል።

‎ይህን ተከትሎም ፦
- ለኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚንስትር
- ለብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት፣
- ሰላም ሚንስትር፣
- ለፍትህ ሚንስትር፣
- ለኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድና ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ደብዳቤ መፃፋቸዉንና ለችግሩ ዘላቂ መፍትሔ እንዲበጅለት መጠየቃቸውን አስረድተዋል።

‎ይህ በእንዲህ እንዳለ ከአርባምንጭ ኮንሶ የሚወስደዉ መንገድ በአከባቢው ባለዉ አለመረጋጋት ስጋት ተዘግቶ መዋሉን አሽከርካሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የተናገሩ ሲሆን ጉዳዩን ለማጣራት ወደ ጋሞ ዞን ፖሊስ አዛዥ እንዲሁም ወደ አርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ደዉሎ የነበረ ቢሆንም ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ሳይሳካ ቀርቷል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia
432😭148🙏16😡11🕊10👏8😱4💔4😢1
TIKVAH-ETHIOPIA
" የሰላምና የዕርቅ ዕድል ቅድሚያ እንዲሰጠው ጉባኤው የበኩሉን ጥረት ማድረግ ይገባዋል " - ቅዱስነታቸው ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የቅዱስ ሲኖዶስ ዓቢይ ጉባኤ መጀመሩን አስመልክቶ መልዕክት አስተላልፈዋል። በዚህም መልዕክታቸው የርስ በርስ ግጭቶች ቆመው ግጭቶች በውይይት እና በድርድር እንዲፈቱ…
#Update

ቅዱስ ሲኖዶስ የአህጉረ ስብከት ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ምደባ ውሳኔ አሳለፈ።

1. የምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት ብፁዕ አቡነ ቶማስ የአዊና የመተከል አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከትን ደርበው የምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከትን እንዲመሩና እንዲይዙ ምልዓተ ጉባኤው ወስኗል፡፡

2. የደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት የከሚሴ የደቡብ ወሎ ልዩ ዞን  የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ ደርበው እንዲመሩ ምልዓተ ጉባኤው  ወስኗል፡፡

3. የምሥራቅ ወለጋንና የሆሮ ጉድሩን ብፁዕ አቡነ ኒቆዲሞስ የምሥራቅ ሐረርጌ ጳጳስ ሀገረ ስብከታቸውን እንደያዙ  ደርበው እንዲመሩ የቅዱስ ሲኖዶስ  ምልዓተ ጉባኤ ወስኗል፡፡

4. ብፁዕ አቡነ ኤውስጣቴዎስ  የአሉባቦር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ  የምዕራብ ወለጋና ደርበው እንዲመሩ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ወስኗል፡፡

ውሳኔዎቹ የተወሰኑት አሁን ላይ በተደራቢ እንዲመሩ የተያዙት አህጉረ ስብከት በዘላቂነት ሊቃነ ጳጳሳት ተመድበው እስከፈታ ድረስ የተወሰነ ውሳኔ መሆኑን ቅዱስ ሲኖዶስ አሳውቋል። #EOTCTV

@tikvahethiopia
745🙏59😡41🕊32😭23🤔16🥰2👏1😢1
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update አቶ ታዬ ደንደአ ወደ ማረሚያ ቤት እንዲወርዱ ፍርድ ቤት አዘዘ። የቀድሞ የሰላም ሚኒስትር ዴዔታ አቶ ታዬ ደንደአ የዋስትና መብታቸው ተነስቶ ጉዳያቸውን ማረሚያ ሆነው እንዲከታተሉ ዛሬ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሰጥቷል። ፖሊስ አቶ ታዬን ዛሬ ፍርድ ቤት አቅርቧል። አቃቤ ህግ ከዚህ ቀደም የተዘጉ ሁለት ክሶችን ጨምሮ መዝገቡ በፍርድ ቤቱ እንዲቀሳቀስ ጠይቋል። አቶ ታየ ደንደአ…
#ችሎት

በእስር ላይ የሚገኙ የቀድሞ ሰላም ሚንስትር ዴኤታ አቶ ታዬ ደንዳአ ዛሬ ፍርድ ቤት ቀረቡ።

አቶ ታዬ " ህገወጥ የጦር መሣሪያ መያዝ፤ ጠላትን ማገዝ እና በጉልበት ህገመንግስት ለመናድ ከሚሰሩ ቡድን ጋር መተባበር " በሚሉት ወንጀሎች ነው ተጠርጥረው የታሰሩት ሲሉ የህግ ጥበቃቸው አቶ አበራ ንጉስ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

አቶ ታዬ ዳንዳአ ተጠርጥረው በተከሰሱበት ወንጀል በዋስ መብት ከተለቀቁ ከተወሰን ወራት በኃላ ዳግም ግንቦት 25 ቀን 2017 ዓ.ም ታስረው በቂልንጦ ማረምያ ቤት ይገኛሉ።

በተጠረጠሩበት ወንጀሎች የመጨረሻ ውሳኔ ለመስጠት ልደታ ፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፀረ ሽብር ችሎት ሀምሌ 30 ቀን 2017 ዓ.ም ቀጥሮ ሰጥቶ ነበር።

የአቶ ታዬ መዝገብ ተመርምሮ ዛሬ ውሳኔ ለመስጠት ቢቀጥርም ፍርድ ቤቱ በተደራራብ ስራዎች መዝገቡን አጣርቶ ውሳኔ ለመስጠት ግዜ አለማግኘቱን ገልፆ ተለዋጭ ቀጠሮ  ገልፆል።

በዛሬው ችሎት ከሳሽ አቃቢህግ እንዳልቀርበ ጠበቃቸው አቶ አበራ ተናግረዋል።

የአቶ ታዬ ዳንዳአ ጠበቃ አቶ አበራ ንጉስ ደንበኛቸው ከዚህ ቀደም ታስረው ባሉበት የሰብአዊ መብት ጥሰቶች እንደደረሰባቸው ለፍርድ  ቤቱ አቤቱታ አቅርበው በጉዳዩ ላይ ትዛዝ አለመሰጠቱን ፤ እንዲሁም  ከሁለት ወር ቆይታ በኃላ መዝገባቸው ተመርምሮ አለማለቁ ቅር እንዳሰኛቸው ለችሎቱ ማስረዳታቸውን ገልፀዋል።

ሆኖም የፌዴራል ልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፀረ ሽብር ወንጀል ችሎት ውሳኔ ለመስጠት ለጥቅምት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል ሲሉ አቶ አበራ ንጉስ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
758😢193😡90😭48💔36🙏26🕊24🤔7🥰5
#ሀዋሳ

" ባልተገባ መልኩ ተይዘዋል " ያላቸውን የመንግሥት ቤቶች በማስለቀቅ ለከተማ ነዋሪዎች ማስተላለፍ ጀምራለሁ ሲል የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር አሳወቀ።

ከተማ አስተዳደሩ ይህን ያለው በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገጹ ነው።

የግል ቤት ኖሯቸው በመንግሥት ቤት ውስጥ የሚኖሩትን በማስለቀቅ ለሚገባቸው የከተማው ነዋሪዎች አስረክባለሁ ብሏል።

በቅርቡ የተሾሙት አዲስ ከንቲባ አቶ ተክሌ ጆምባ " በተለያዩ አጋጣሚዎች በከተማዋ የሚገኙ የመንግሥት ቤቶች የመንግሥት ቤት  ወደማይገባቸው ግለሰቦች ተዘዋውሯል " ያሉ ሲሆን " በተለይ የግል ቤት ኖሮአቸው በመንግሥት ቤት የሚኖሩ ግለሰቦችን ቤት በመረከብ ለሚገባቸው የከተማዋ ነዋሪዎች ለማስተላለፍ ዝግጅት ተደርጓል " ሲሉ ገልጸዋል።

" የክልሉ መንግሥት ይህ ተፈፃሚ እንዲሆን አቅጣጫ አስቀምጧል ፤ የከተማው አስተዳደርም ለተፈፃሚነቱ በቁርጠኝነት ይሰራል " ብለዋል።

ከተማ አስተዳደሩ ፦
- ይህ ቤቶችን የማስለቀቅ ስራ በምን አግባበ እንደሚመራ፣
- ከመቼ ተጀምሮ ተፈጻሚ እንደሚሆን፣
- ስንት ቤቶች ባልተገቡ ሰዎች እንደተያዙ በይፋ  ያለው ነገር የለም።

@tikvahethiopia
668👏131😭30🤔28🙏18🕊18😡14😱11😢11🥰6💔2
የገቢዎች ሚኒስቴር የደመወዝ ስኬል መሸጋገሪያ ሰንጠረዥ ይፋ ተደርጓል።

የደሞዝ ስኬሉን ትክክለኛነት ቲክቫህ ከፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አረጋግጧል።

በ13 ደረጃዎች የተከፈለውን የደሞዝ ስኬል ከተያያዘው ፋይል ላይ ይመልከቱ።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
824😡247😭130🙏61👏49🤔43😢36😱32💔25🥰14🕊7
ልዩ የትምህርት ድጋፍ እድል ከፋዌ ኢትዮጵያ

ፋዌ ኢትዮጵያ እና ፋዌ አፍሪካ ከ ማስተርካርድ ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር በ 2018 ዓ.ም እድሚያቸው ከ 15 እስከ 25 የሆኑ ወጣቶችን በተለይም በዝቅተኛ ኢኮኖሚያዊ ደረጃ የሚገኙ ሴቶችን ፣የአካል ጉዳተኛ ወጣቶችን፣ የሀገር ዉስጥ ተፈናቃዮችን እና የውጭ ሀገር ስደተኞች ተጠቃሚ የሚያደርግ የከፍተኛ የትምህርት እድል ተጠቃሚ እንድትሆኑ ሲጋብዝ ታላቅ ደስታ ይሰማዋል፡፡ ድጋፉ ሁሉን አቀፍ የገንዘብ፣የትምህርትና ስልጠና እንዲሁም የማህበራዊ ድጋፍን የሚያካትት ሲሆን የትምህርት ድጋፉ የሚሰጠው በቴክኒክና ሙያ የትምህርት ተቋማት ውስጥ በሚሰጡ የሳይንስ፣ቴክኖሎጂ፣ምህንድስናና ተዛማጅ የትምህርት ዘርፎች/STEM/ ደረጃ 4 እና 5 ኮርሶች ነው፡፡

ትምህርት ስልጠናና ድጋፉ የሚሰጠው በአዲስ አበባ  ከተማ  በጄኔራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ እና አዲስ አበባ ተግባረ እድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጆች፣ አዳማ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ፣  ሀዋሳ ፖሊ ቴክኒክና ሀዋሳ ተግባረ እድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጆች እንዲሁም በባህርዳር ፖሊ ቴከኒክ ኮሌጅ በሚሰጡት የመደበኛ የትምህርትና ስልጠና መርሃግብሮች ሲሆን ሙሉ ዝርዝር መረጃ ከስር ባለው ሊንክ ይመልከቱ።
👉 https://shorturl.at/5w9EC

የማመልከቻ ቀን ከ ጥቅምት 17-21 ፤ 2018 ዓ.ም የሚቆይ ሲሆን ከተጠቀሰው ቀነገደብ ዉጭ የሚመጡ አመልካቾችን የማናስተናግድ መሆኑን ከወዲሁ እንገልጻለን።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥሮች
አዲስ አበባ በ 0981642541
አዳማ  በ 0981643411
ባህርዳር በ 0981638351
ሀዋሳ በ 0981630651 በመደወል ወይም በድህረገጻችን www.faweethiopia.org ይጎብኙ፡፡
ምዝገባዉም ሆነ የመረጣው ሂደት ከማንኛዉም ክፍያ ነጻ መሆኑን እናሳዉቃለን!
367🙏13😢10👏9😭2
አዲስ ባንክ ዲጂታል ዕቁብ እና እድር !

ካሉበት ቦታ ሆነው በቀላሉ የአዲስ ባንክ ሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያ በመጠቀም ዕቁብ እና እድር መሰብሰብ እና መክፈል ይችላሉ።

🟡 ዕቁብ ሰብሳቢዎች የክፍያ ሁኔታን የሚከታተሉበት እና ክፍያዎችን የሚፈፅሙበት፣
🟡 ቅጣቶችን የሚቆጣጠሩበት፣
🟡 ዕቁብ መጀመሩን ለአባላት የሚያሳውቁበት።

መተግበሪያውን 👉 Appstore / 👉 Playstore ላይ በማውረድ ወይም በUSSD *870# መጠቀም ይችላሉ።

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት በአቅራቢያዎ ወደሚገኝ የባንኩ ቅርንጫፍ ጎራ ይበሉ !!

ለወዳጅ ዘመድ ያጋሩ!
Website | Telegram | LinkedIn | Facebook | Instagram
104🙏11👏10😢9🥰4😡3
TIKVAH-ETHIOPIA
#መቐለ “ ማስክ የለበሱ ታጣቂዎች ገብተው የጽሕፈት ቤታችንን ታፔላ ነቅለውታል ” - ስምረት ፓርቲ “ ማስክ የለበሱ ” ያላቸው ታጣቂዎች ትላንት ምሽት 4:00 የመቐለ ጽሕፈት ቤቱን ለመዝረፍ ሙከራ እንዳደረጉና “ ታፔላውን ነቅለው እንደሄዱ ” በነአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው አዲሱ ስምረት ፓርቲ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል፡፡ በጽሕፈት ቤታችሁ በኩል የተዘረፈ ንብረትና የደረሰ ውድመት አለ ? ስንል የጠየቅናቸው…
#ስምረት

ዴሞክራስያዊ ስምረት ትግራይ ፓርቲ  (ስምረት) መስራች ጉባኤውን ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ እያካሄደ ይገኛል።

ፓርቲው መስራች ጉባኤውን ከትግራይ ውጭ እያካሄደ መሆኑ ከመስራቾች አንዱ የሆኑት ነጋ አሰፋ መኮነን ገልጸዋል።

ጉባኤው ከመላው ትግራይ ወደ አዲስ አበባ የገቡ አባላት በተሟሉበት እየተካሄደ ነው ተብሏል።

የገዢውን ጨምሮ የሌሎች የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች በእንግድትነት ተገኝተውበታል።

ፓርቲው ባለፈው ዓመት በወርሃ ነሀሴ 2017 ዓ.ም እንዲሁም ባለፈው ወርሃ መስከረም 2018 ዓ.ም በመቐለ መስራች ጉባኤውን ለማካሄድ ለጊዚያዊ አስተዳደሩ ያቀረበው ጥያቄ አልተሳካም ሲሉ አቶ ነጋ አሰፋ ተናግረዋል።

የህወሓት ምክትል ሊቀ-መንበር በነበሩት ጌታቸው ረዳ የሚገኙባቸው ገምቱ ወጣትና ነባር አመራሮች ተቋቁሞ ባለፈው ዓመት ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ቅድመ እውቅና ያገኘው  ስምረት ፓርቲ በመቐለ የከፈተው ዋና ፅህፈት ቤት ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች መሰበሩ ይታወሳል።

ምንም እንኳን ፓርቲው መስራች ጉባኤውን በትግራይ ለማድረግ ቢያቅድም አስቻይ ሁኔታዎች ባለመፈጠራቸው በአዲስ አበባ እያካሄደ ነው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

ፎቶ፦ ከማኅበራዊ ሚዲያ

@tikvahethiopia            
603😡115🕊47🤔20🙏15😭14👏7🥰4💔3
2025/10/31 11:18:43
Back to Top
HTML Embed Code: