#NewsAlert
" ህወሓት የፕሪቶሪያውን ስምምነት በግልጽ አፍርሷል " - የአፋር ክልል መንግስት
" የህወሓት ቡድን በዛሬው ዕለት በአፋር ክልል ወሰን ውስጥ በማግባት 6 መንደሮችን በጉልበት በመቆጣጠር ንጹሃንን በሞርታርና በዙ-23 ደብድቧል " ሲል የአፋር ክልል መንግሥት አስታወቀ።
ክልሉ " ቡድኑ የተለመደውን የሽብር ተግባሩን በግልጽ ጀምሯል " ሲል ከሷል።
" በዛሬው ዕለት ማለትም በቀን 26/02/2018 ዓ/ም የአዛውንቶች የህወሓት ጉጅሌ /ቡድን/ በአፋር ክልል በዞን ሁለት በመጋሌ ወረዳ ቶንሳ ቀበሌ ዋራዓ እና ሚልኪ በሚባሉ ልዩ አካባቢዎች ወሰን ተሻግሮ በመግባት ከምሽቱ አንድ ሰአት አካባቢ በንጹሐን የአፋር አርብቶ-አደሮች ላይ የከባድ መሳሪያ ተኩስ በመክፈት የፕሪቶሪያ ስምምነትን በግጭት አዋጅ በግልጽ አፍርሷል " ሲል አሳውቋል።
" ይህ የህወሓት ጣብ-ጫሪ ቡድን በቶንሳ ቀበሌ ላይ ተኩስ በሚከፈትበት ወቅት ሰላም ወዳድ የአፋር ሽማግሌዎች እንድመለሱ ቢማፀኗቸውም የህወሓት ቡድን ግን አሻፈረኝ በማለት ግጭቱን አስከትሏል " ብሏል።
" ይህ ከትናንት ጥፋቱ የማይማረው ተስፋ ቢሱ የህወሓት ቡድን ከድርጊቱ በአስቸኳይ ካልተቆጠበ የዜጎች ደህንነትና የወሰናችንን ክብር የማስጠበቅ፣ እንዲሁም ራሳችንን ከማንኛውም ውጫዊ ጥቃት የመከላከል ኃላፊነታችን እንደምንወጣ እንገልፃለን " ሲል የአፋር ክልል መንግሥት አስጠንቅቋል።
#Afar #Tigray
@tikvahethiopia

😭1.05K❤685🕊167😡77👏73🤔48😢26🙏26💔17🥰10😱3
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#NewsAlert
#Tigray #Afar
" ኃላቀሩ ቡድን የፌደራል መንግስትን ወደ ግጭት ለማስገባት በዓፋር በኩል ትንኮሳዎች ፈፅሟል ይህንንም የአዛዡና ጌታውን ሻዕብያ አጀንዳ ለማስፈፀም የተደረገ ነው " - አቶ ጌታቸው ረዳ
ጥቂት የትግራይ ኃይል አመራሮች በሻዕብያ ትእዛዝ ሰጪነት በፌደራል መንግስት ላይ ትንኮሳ እንደጀመሩና ይህን ትንኮሳ እንዲያቆሙ አቶ ጌታቸው ረዳ አሳሰቡ።
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚንስትር የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚንስትር አቶ ጌታቸው ረዳ ፤ " ፍስሃ ማንጁስና ዮሃንስ መዲድ የተባለችሁ የትግራይ ሰራዊት አመራሮች የጀመራችሁትን የግጭት ቀስቃስ እንቅስቃሴ አቁሙ " ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
ሚንስትሩ " ኃላቀር ቡድን " ሲሉ የጠቀሱት የህወሓት አመራር የፕሪቶሪያ ስምምነት ለመቅደድ ሁሉም ዓይነት ትንኮሳ ቢፈፅምም የፌደራል መንግስት የአፀፋ ምላሽ ከመስጠት ተቆጥቧል ብለዋል።
" ኃላቀር " ያሉት የህወሓት አመራር ቡድን የፌደራል መንግስትን ወደ ግጭት ለማስገባት " በዓፋር በኩል ትንኮሳዎች ፈፅሟል ይህንንም የአዛዡና ጌታውን ሻዕብያ አጀንዳ ለማስፈፀም የተደረገ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።
በዓፋር ክልል በኩል በፌደራል መንግስት ላይ የተደረገው ትንኮሳ " ጀነራል ፍስሃ ማንጁስና ጀነራል ዮሃንስ መዲድ ናቸው የመሩት ማቆም ያለባቸው እነሱ ናቸው " ሲሉ አሳስበዋል።
" ጦር አውርድ በሚል ፀሎት በራስ ህዝብ ላይ መከራና ጭፍጨፋ መጋበዝ ክህደት ነው " ያሉት ሚንስተር ጌታቸው " በትግራይና በዓፋር በኩል ያላችሁት የትግራይ ሰራዊት (TDF ) እና የትግራይ የሰላም ሃይል (TPF) የሻዕብያን ፍላጎት ለማሳካት ወደ እርስ በርስ ግጭት መግባት የለባችሁም " ብለዋል።
" ለትግራይ የሚያስብና እርባና ያለው ሰው ሦስተኛ ዓመቱ ያስቆጠረውን የፕሪቶሪያ ውል ከወዴት ደረሰ ? ብሎ መጠየቅ ብቻ ነው የሚያዋጣው " ሲሉ አቶ ጌታቸው ረዳ ገልጸዋል።
ትላንት ማክሰኞ ጥቅምት 25 /2018 ዓ.ም ከሰዓት በኃላ በትግራይ ኃይሎች እና በትግራይና ዓፋር ክልል አዋሳኝ በሚገኙት ራሳቸውን " የትግራይ የሰላም ኃይል ታጣቂዎች (TPF) " ብለው በሚጠሩት መካካል ግጭት መቀስቀሱ በማህበራዊ የትስስር ገፆች በስፋት ተነግሯል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

3❤2.06K😭739🕊338😡100🤔84👏58💔46🙏39😢37😱19🥰10
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አቢሲንያ ማስገረሙን ቀጥሏል! ገንዘብ ገቢ ወይም ወጪ ለማድረግ ወደ አቢሲንያ ቅርንጫፍ ሲሄዱ ፣ ፎርሙን ቀድመው በአቢሲንያ ሞባይል ባንክ መተግበሪያ በመሙላት ጊዜዎን ይቆጥቡ።
#ወረቀትአልባየባንክአገልግሎት #BoaPaperlessbranch #BanksinEthiopia #AddisAbaba #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ

❤137🙏16😡14👏10💔3😢1
እጥፍ ድርብ የማሸነፍ እድል በM-PESA!
አሁኑኑ የሳፋሪኮምን የበሽ ጥቅል በM-PESA በመግዛት 2 የእጣ ቁጥር በማግኘት ሚልየነር የመሆን እድላችንን በእጥፍ እንጨምር።
መተግበሪያውን ለማውረድ ይህንን ይጫኑ:
https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle
ለተጨማሪ መረጃ በቴሌግራም ያግኙን፥
https://www.tg-me.com/MPesaETCustomerCare
#MPESASafaricom #MPESAEthiopia

❤58😡9🕊3
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ቀኑ ሊያበቃ ነው!
የ2017 አመታዊ የግብር መክፊያ ጊዜ ሊጠናቀቅ ጥቂት ቀን ብቻ ነው የቀረው።
ግብሮን ከጥቅምት 30 ቀን 2018 ዓ.ም በፊት ይክፈሉ እራስዎን ካላስፈላጊ ቅጣት እና ውጣ ውረድ ይጠብቁ
ግብር ለሀገር ክብር
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ

❤108😡81😭72😢10💔7
የኢትዮጵያ የፋርማሲ ማህበር (ኢፋማ) በመድሐኒት እና የህክምና መሳሪያዎች አከፋፋዮች ላይ ተግባራዊ እንዲሆን የተጣለው የ2.5 በመቶ አነስተኛ የግብር ምጣኔ ቀሪ እንዲሆን ጠየቀ።
የኢትዮጵያ የፋርማሲ ማህበር (ኢፋማ) የመድሀኒትና የህክምና መገልገያ መሳሪያዎችን የጅምላ አከፋፋዮች ንኡስ ዘርፍ በቅርቡ በወጣው አዋጅ ቁጥር 1395/2017 የዝቅተኛ አማራጭ ግብር ምጣኔ ምክንያት ከፍተኛ ተጎጂ መሆናቸውን በመግለጽ ውሳኔው ቀሪ እንዲሆንለት ለገንዘብ ሚኒስቴር በላከው ደብዳቤ ጠይቋል።
ማህበሩ "ውሳኔው በዚህ ዘርፍ የተሰማሩ የማህበሩን አባላት የሚጎዳ በመሆኑ የማስተካከያ እርምጃ እንዲወሰድ" ሲል ጥቅምት 24/2018 ዓም ለገንዘብ ሚኒስቴር ጥያቄውን በደብዳቤ አቅርቧል።
የኢትዮጵያ የፋርማሲ ማህበር (ኢፋማ) በማህበራዊ ትስስር ገጹ ያጋራው ደብዳቤ በዝርዝር ምን ይላል ?
" በቅርቡ የተከበረው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ካወጣው የገቢ ግብር አዋጅ 1395/2017 ላይ እንደተመለከትነው አነስተኛው የግብር መጠን ከአጠቃላይ ሽያጩ 2.5 በመቶ መሆን እዳለበት ተገልጿል የዚህም ድንጋጌ መነሻ በገቢዎች ሚኒስቴር ተጠንቶ የቀረበው አማካኝ የ31 በመቶ Gross margin መሆኑን ለመረዳት ችለናል፡፡
ሆኖም ይህ ጥናት ካለው እውነታ ጋር በፍፁም የማይጣጣም ነው፡፡
እንደሚታወቀው የመድኃኒት አከፋፋዮች አማካይ Gross margin ከ 7.5 በመቶ እስከ 10 በመቶ ሲሆን ይህንን እውነታም የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በቀላሉ ሊያረጋግጠው የሚችለው ነው፡፡
ዘርፋችን መድሀኒትና የህክምና መገልገያ መሳሪያዎችን በማከፋፈል ማሀበረሰቡን በማገልገል ረገድ የአንበሳውን ድርሻ የሚወጣ ሆኖ ሳለ ይህ ዉሳኔ ዘርፉን ለኪሳራ በመዳረግ የሚያቀጭጭ እና ሊያጠፋውም የሚችል ነው።
የዘርፉ መጎዳት ደግሞ በዘርፉ ዉስጥ በቀጥታ የተሰማራውን ማህበረሰብ ብቻ ሳይሆን የመድሐኒት አቅርቦቱንም በከፍተኛ ሁኔታ በማስተጓጎል የጤናውን ዘርፍ የሚጎዳ ነው፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ የባንክ ብድር፣ገበያ ከፍ ዝቅ በማለቱ ምክንያት የሚከሰት የመድሃኒቶች የመጠቀሚያ ጊዜ ማለፍ፤ በየመድሃኒት ቤቶቹ ለማከፋፈል የሚወጣዉ ወጪ፣እንዲሁም ለማከማቻ እና ስራ ማስኬጃ የምናወጣቸዉ ወጪዎች መጨመር የመድሐኒት አከፋፋዬችን ትርፋማነት በእጅጉ እየፈተነው ይገኛል፡፡
በዚሁም ምክንያት የተጣራው ትርፍ ከጠቅላላው ሽያጭ ሲሰላ ከ 3 በመቶ የማይበልጥ ሆኖ ይታያል፡፡
በመሆኑም ይህንን ነባራዊ ሁኔታ በማገናዘብ የ2.5 በመቶ አነስተኛ የግብር ምጣኔው በ መድሐኒት እና የህክምና መሳሪያዎች አከፋፋዬች ላይ ተግባራዊ መሆኑ ቀርቶ በሂሣብ መዝገብ ወጪና ገቢ ተሰልቶ እንድንከፍል እንዲደረግልን " ሲል ማህበሩ ጠይቋል፡፡
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ

❤591😭34🕊16🙏7💔3🥰1😱1😢1
ገዳዩ በእድሜ ልክ እስራት ተቀጥቷል !
ወ/ሪት ልዋም ገ/ሄር በ2016 ዓ/ም በመቐለ ኲሓ ክፍለ ከተማ ነው በጭካኔ የተገደለችው።
ጭካኔ በተሞላበት ግድያ የተጠረጠረው ወጣት ኣማኑኤል ኣረጋዊ ይባላል።
በግድያ ወንጀል የተጠረጠረው ወጣት አማኒኤል ለሁለት ዓመታት ያህል ክዶ ሲከራከር ቆይቷል።
ቢሆንም ከሳሽና ተከሳሽ ሲያከራክር የቆየው የመቐለ ማእከላዊ ፍርድ ቤት ዛሬ ጥቅምት 27/2018 ዓ.ም ባዋለው ችሎት ወንጀሉ መፈፀሙ አረጋግጦ ገዳዩ በእድሜ ልክ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል።
በችሎቱ የተገኙ የሟች ወ/ሪት ልዋም ገ/ሄር ቤተሰቦችና በሴቶች ጥቃት መከላከል ዙሪያ የሚሰሩ የመብት ተሟጓቾች ውሳኔው የዘገየ መሆኑ ጠቅሰው አስተማሪነቱ መስክረዋል።
" ወጣቶች ከስሜት ስክነት ፣ ከማንአለበኝነት የኃላፊነት ስሜት እንዲያስቀድሙ " መክረዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ

❤835👏211😭105🙏43💔32🕊14😡14🥰8😱4😢1
TIKVAH-ETHIOPIA
#NewsAlert #Tigray #Afar " ኃላቀሩ ቡድን የፌደራል መንግስትን ወደ ግጭት ለማስገባት በዓፋር በኩል ትንኮሳዎች ፈፅሟል ይህንንም የአዛዡና ጌታውን ሻዕብያ አጀንዳ ለማስፈፀም የተደረገ ነው " - አቶ ጌታቸው ረዳ ጥቂት የትግራይ ኃይል አመራሮች በሻዕብያ ትእዛዝ ሰጪነት በፌደራል መንግስት ላይ ትንኮሳ እንደጀመሩና ይህን ትንኮሳ እንዲያቆሙ አቶ ጌታቸው ረዳ አሳሰቡ። የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚንስትር…
#Update
#Tigray
#Afar
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የዓፋር ክልል መንግሥት ትላንት ምሽት ያወጣውን መግለጫ " መሰረተ ቢስ " ሲል ውድቅ አደረገ።
ጊዜያዊ አስተዳደሩ የአፋር ክልል መግለጫን " የትግራይና የዓፋር ወንድማማች ህዝቦች ታሪካዊና ሰላማዊ ጉርብትና ለመጉዳት ያለመ ክፋት ነው " ብሏል።
የዓፋር ክልል ትላንት ምሽት ባወጣው መግለጫ የህወሓት ቡድን ኃይሎች የዓፋር ክልል ወሰንን ዘልቀው በመግባት ጥቃት መክፈታቸውን ፣ 6 መንደሮችን በጉልበት መቆጣጠራቸውን ፣ ንፁሃንን በሞርታር መደብደባቸውን እና የፕሪቶሪያውን ስምምነት ማፈረሳቸውን አሳውቆ ነበር።
የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፤ የዓፋር ክልል መንግስት ' ሓራ መሬት ' በሚል ስም የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ትግራይን እንዲያውኩ ቦታ በመፍቀድ መተባበሩን ወቅሶ " የትግራይ ሰራዊት የዓፋር ወሰን አልፎ አልዘለቅም " ሲል የቀረበበት ክስ አስተባብሏል።
ጊዚያዊ አስተዳደሩ " የፌደራል መንግስት የፕሪቶሪያ ስምምነት በአግባቡ እንዳይፈፀም እንቅፋት ሆኗል። ድርጊቱ ሰላማዊ ሃደት ከመጉዳት አልፎ የህዝብ ስቃይና መከራ እንዲቀጥል የሚያደርግ ሰላማዊ ትግል የሚረብሽ መሆኑ ግልፅ ነው " ብሏል።
" በኃይልና ህይደት በመክፈል የሚለወጥ ሁኔታ የለም " ያለው አስተዳዳሩ " ውይይት ብቸኛ የችግሮች መፍትሄ ነው " ሲል ገልጿል።
" የፕሪቶሪያ ስምምነት በተሟላ መልኩ መተግበር የዘላቂ ደህንነትና ሰላም ዋስትና መሆኑ በፅኑ እናምናለን ፤ ጊዚያዊ አስተዳደሩ ከፌደራል መንግስት ያለው ግንኙነት እንዲጎለብት ስምምነቱ ሳይውል ሳያድር ይተግበር " ብሏል።
" የትግራይ ህዝብ በዚህና በዚያ ከሚሰራጭ ወሬ ' ከጦርነትና ከትግራይ ጥፋት እናተርፋለን ' በሚል እንቅልፍ ያጡት ነውረኞች በሚፈጥሩት ያለመረጋጋት ሳይረበሽ የቀን ተቀን ውሎው ማእከል በማድረግ ተረጋግቶ እንዲረባረብ ጥሪ እናቀርባለን ፤ የዓለም አቀፍ ማህበረሰብም ከጎናችን ይሰለፍ " ብሏል።
ምንም እንኳን የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር " ወደ ዓፋር አልፌ አልዘለቅኩም " ቢልም ህወሓት በከፈተው ጥቃት በሺዎች የሚቄጠሩ የዓፋር ክልል ነዋሪዎች ተፈናቅለዋል ተብሏል።
የፌዴራል መንግሥት እስካሁን ለሚነሱት ጉዳዮች ምንም የሰጠው አስተያየት ሆነ ግብረ መልስ የለም።
የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ ትላንት በሰጡት ቃል ፤ " ኃላቀር ቡድን " ሲሉ የሚጠሩት የህወሓት አመራር ቡድን የፌዴራል መንግሥት ላይ ትንኮሳ እንደጀመረ ገልጸዋል።
ቡድኑ የፕሪቶሪያ ስምምነትን ለመቅደድ ሁሉም ዓይነት ትንኮሳ ቢፈፅምም የፌደራል መንግስት የአፀፋ ምላሽ ከመስጠት እንደተቆጠበ ገልጸዋል።
ይህ ኃላቀር የህወሓት አመራር ቡድን የፌደራል መንግስትን ወደ ግጭት ለማስገባት ፤ በዓፋር በኩል ትንኮሳዎች እንደፈጸመ ይህንንም የአዛዡና ጌታውን #ሻዕብያ አጀንዳ ለማስፈፀም የተደረገ እንደሆነ ተናግረዋል።
በዓፋር ክልል በኩል በፌደራል መንግስት ላይ የተደረገው ትንኮሳ ጀነራል ፍስሃ ማንጁስና ጀነራል ዮሃንስ መዲድ እንደመሩት በስም ጠርተው በመግለጽ ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አስጠንቅቀዋል።

❤730🕊171😡72😭42🤔37👏19🙏15💔5🥰3😱3
TIKVAH-ETHIOPIA
#DV2027 የ2027 የአሜሪካ ዲቪ ሎተሪ ምዝገባ ቀን ከተባለበት እና ከዚህ ቀደምም ከሚታወቅበት ቀን ቢዘገይም ፕሮግራሙ እንዳልተሰረዘ / ዲቪ እንዳልቀረ ለማወቅ ተችሏል። ምዝገባው የሚጀመረው በዚህ ቀን ነው የሚል መረጃ ባይኖርም በቅርቡ ይፋዊ ምዝገባ መጀመሩን ሀገሪቱ ታሳውቃለች ተብሎ ይጠበቃል። የአሜሪካ መንግሥት በይፋ የሰጠው ማብራሪያ እና ማረጋገጫ ባይኖርም ምናልባትም የዘንድሮ የዲቪ ሎተሪ ማመልከቻ…
#USA 🇺🇸
የ2027 የአሜሪካ ዳይቫርሲቲ ቪዛ (DV) ምዝገባ እስካሁን ክፍት አለመደረጉን ስቴት ዲፓርትመንት አሳውቋል።
" ምዝገባ ተጀምሯል " የሚሉ የማጭበርበሪያ መልዕክቶች እየተዘዋወሩ እንደሚገኙ እንዲሁም አንዳንድ ግለሰቦችና አገልግሎት ሰጪዎች " የምትመረጡበትን ዕድል ከፍ እናደርግላችኋለን ክፈሉ " በማለት የማጭበርበር ተግባር ውስጥ እንደተሰማሩ ገልጿል።
ምዝገባው ገና ይፋ እንዳልተደረገ የገለጸው የአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመትን " የምዝገባ ቀኑ እና ለውጥ ስለሚደርግበት የዘንድሮው ፕሮሰስ ዝርዝር መረጃ ዝግጅ ሲሆን ይፋ ይደረጋል " ብሏል።
አሜሪካ በዚህ ዓመት ለዳይቨርሲቲ ቪዛ ምዝገባ 1 ዶላር ማስከፈር እንደምትጀምር ማሳወቋ አይዘነጋም።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
#TikvahEthiopiaFamily

Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤238😭31🙏27👏13😡5🤔3