Telegram Web Link
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray የትግራይ ኃይል አባላት ሰልፈኞች ዛሬም ለአምስተኛ ቀን የመኪና መንገድ ዘግተው ውለዋል። ትናንት ጥቅምት 6/2018 ዓ.ም ወደ ዓዳግራት ከተማ የሚያስገቡና የሚያስወጡ በሶስት አቅጣጫ የተዘጉ መንገዶ ከምሽቱ 12:00 ሰዓት ተከፍተዋል። ዛሬ ከእንዳስላሰ-ሽረ ፣ አክሱም ፣ ዓድዋ ፣ ተምቤንና ሌሎች አከባቢዎች ወደ መቐለ የሚያስገቡ ዋና የመኪና መንገድ በትግራይ ደቡባዊ ምስራቅ ዞን ሃገረ ሰላም…
#Tigray

የትግራይ ኃይል አባላት ለአምስተኛ ቀን ያካሄዱት የመኪና መንገድ መዝጋት ያካተተ ሰልፍ ተከትሎ የክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር የሰራዊት አባላት ተጠቃሚ የሚያረጋግጥ ደንብ ማጸደቁ አስታውቋል።

እሁድ ጥቅምት 3/2018 ዓ.ም የጀመረው የትግራይ ኃይል ሰልፍና ተቃውሞ ዛሬ ቀጥሎ ከእንዳስላሰ-ሽረ ፣ አክሱም ፣ ዓድዋና ተምቤንና ሌሎች አከባቢዎች ወደ መቐለ የሚያስገባ መንገድ ተዘግቶ ውሏል።

ይህንን ተከትሎ ዛሬ ጥቅምት 7/2018 ዓ.ም ከሰዓት በኃላ የፅሁፍ መግለጫ ያወጣው የጊዚያዊ እስተዳደሩ ፕሬዜዳንት ፅህፈት ቤት ካቢኔ ጥቅምት 5/2018 ዓ.ም ያወጣው የትግራይ የፀጥታ ሃይሎች ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ረቂቅ ደንብ ዛሬ ማፅደቁን አመልክተዋል።

ካቢኔው በዛሬው አስቸኳይ ስብሰባው  የትግራይ የፀጥታ ሃይሎች ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ደንብ በዝርዝር ተወያይቶ ተግባራዊ እንዲሆን በሙሉ ድምፅ አፅድቆታል።

የፀደቀው ደንብ ፦
- መሰረታዊ ፍላጎቶች
- የህክምና አገልግሎት
- የቤት መስሪያ መሬት
- በመንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት የሚሰጥ የክብር አገልግሎት
- ትምህርት ስልጠናና ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞች ያካተተ ነው ብሏል ከፕሬዜዳንት ፅህፈት ቤት የተሰጠው የፅሁፍ መግለጫ።

" የፀደቀው የትግራይ ፀጥታ ኃይሎች ተጠቃሚነት ደንብ ለረጅም ጊዜ ጥናት የተደረገበት ከፀጥታ አመራሮች ውይይት ሲካሄድበት የቆየ ነው " ሲል ገልጿል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
1.59K👏194🕊100😡80🤔40😭39🙏32💔16🥰15😱15😢15
‎" ወጣቶቹ ያለ ፍርድቤት ትዕዛዝ ታስረዋል፤ ቤተሰብ እንዳይጠይቃቸውም ተደርጓል " - ቤተሰቦችና ነዋሪዎች

‎በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጌዴኦ ዞን ኮቾሬ ወረዳ ፍሰሃ ገነት ተብሎ የሚጠራዉ አከባቢ ነዋሪዎች እና " ልጆቻችን ያለ አግባብ ታስረዋል " የሚሉት ወላጆች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቅሬታቸውን አሰምተዋል።

በአከባቢዉ ማህበረሰብ በተደጋጋሚ ሲጠየቅ የቆየዉን የፍሰሃ ገነት የወረዳ መዋቅርነት ጥያቄ " በማህበራዊ ሚዲያዎች አሰራጭታችኋል " በሚል ወጣቶችን እያሰሱ እያሰሩ ነው ሲሉ ነው ቃላቸውን የሰጡት።

" ‎ስድስት ወጣቶች ያለ ፍ/ቤት ትዕዛዝ ታስረዋል " የሚሉት ነዋሪዎቹ የፍሰሃ ገነት ወረዳ በቀደመዉ ጊዜ የወረዳ መዋቅር የነበረዉ መሆኑንና የመዋቅር ጥያቄዉ የሕብረተሰቡ በመሆኑ እነዚህም ወጣቶች ይህንኑ ሃሳባቸዉን በማህበራዊ ሚዲያ በማሰራጨታቸው ብቻ ከስራና የትምህርት ገበታቸው እየታሰሱ መታሰራቸውንና ቤተሰብ እንዳይጠይቃቸዉ መደረጉን ገልጸዋል።

‎" ፖሊስ ልጆቻችንን እንዳናገኝ ከማድረጉም በላይ ' በተባባሪነት አስራችኋለዉ ' እያለ እያስፈራራን ነዉ " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የተናገሩት የአከባቢው ወጣቶች " እኛም እየተፈለግን በመሆኑ አከባቢያችንን ለቀን ሸሽተናል " ሲሉ ተናግረዋል።

‎ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከጌዴኦ ዞንና የኮቾሬ ወረዳ ፖሊስ በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ያደረገው የዞኑ ፖሊስ አዛዥ ፈቃደኛ ባለመሆናቸዉ የኮቾሬ ወረዳ አዛዥ ደግሞ ስልካቸዉ ባለመስራቱ ለጊዜው አልተሳካም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia
2514😡77😭44🕊18🥰8🙏8🤔6👏5😢3
" የኑሮ ሁኔታ በጣም ከባድ ነው የሚከፈለን ብር 760 ነው፡፡ ... እኛ ሴቶች እንጨት ለቅመን ነው የምንማረው ወንዶችም እንጨት እየለቀሙ እየጋገሩ ይማራሉ " - የመምህራን ማሰልጠኛ ተማሪዎች

ከ40 አመት በላይ መምህራንን በማሰልጠን የሚታወቀዉ የደሴ መምህራን ማሰልጠኛ ኮሌጅ በመምህርነት በዲግሪና ዲፕሎማ የሚሰለጥኑ ተማሪዎች በወር ለምግብ የሚሰጣቸዉ 760 ብር ለመኖር ስላላስቻላቸዉ ሰዉ ቤት ተቀጥረዉ በቤት ሰራተኝነት ከጫካ ጭራሮ እየለቀሙ የራሳቸውን ምግብ ለማብሰል መገደዳቸውን ገልጸዋል።

ከእነዚህ ተማሪዎች አንዱ በእንጨት ለቀማ ወቅት ሕይወቱ እንዳለፈም ሰልጣኞቹ ተናግረዋል።

በወር የሚከፈላቸው 760 ብር ነው ፤ አንድ እንጀራ ለመግዛት የዋጋውን ውድነት አልቻሉትም ከዚህ ኑሮ ውድነት በመነሳት ወንዶች ኩሽና ተፈቅዶላቸው እንጀራ እየጋገሩ እየኖሩ ናቸው። 

ነገ ተማሪዎችን ለማስተማር የሚሰለጥኑ መምህራን የሚማሩትን ሳይሆን የሚበሉትን በማሰብ የማገዶ እንጨት በመልቀም፣ የቀን የጉልበት ሠራተኛ በመሆን፣ እንዲሁም ሊጥ አብኩተው ለምግባቸው የሚሆን እንጀራ በመጋገር ጊዜያቸውን ያሳልፋሉ ነው የተባለው።

ሰልጣኝ መምህራኑ ለዶቼ ቨለ ሬድዮ ምን አሉ ?

በ760 ብር የምግብ ወርሃዊ ክፍያ የመኖሪያ ቤት ተሰጥቷቸው በኮሌጅ የሚማሩ ተማሪዎች ከትምህርት በኋላ የሚመገቡትን ምግብ ለማብሰል በደሴ ወደሚገኙት የጦሳ፣ አዘዋና ሌሎች እንጨት ለመልቀም ወደሚያስችላቸው ጫካዎች ሲያመሩ ከሞት ጋርም ተጋፍጠዋል፡፡

ለመማር በጣም አስቸጋሪ ስለሆነ በጦሳ ተራራ እንደዚሁም በአዘዋ ተራራ ካለቀምን በስተቀር እንጨት አይገኝም ብለዋል።

በዚህም አንድ ሳሙኤል የተባለ የእንግሊዝኛ ክፍል የዲግሪ ተማሪ በጦሳ ተራራ እንጨት ሊለቅም ሄዶ ህዳር 28 ቀን ህይወቱ አልፏል፡፡

ችግሩ በተለይ ሴቶች ላይ የጎላ ነው የምትለው ሠልጣኝ ተማሪ የግማሽ ቀን የቤት ሰራተኝነትና በሌሎች ስራዎች እራሳችን እየደጎምን ነው ትምህርት የምንማረው ብላለች፡፡ 

" የኑሮ ሁኔታ በጣም ከባድ ነው የሚከፈለን ብር 760 ነው፡፡ ባለን አቅም እየሰራንም ነው የምንማረው በትምህርታችን ላይ ውጭ ውለን ስንገባ እየደከመን ማጥናት እንቸገራለን እንጨት ለቅመን ነው የምንማረው ወንዶችም እንጨት እየለቀሙ እየጋገሩ ይማራሉ " ስትል ተናግራለች።

" አሁን አሁንማ ሥራም ጠፍቷል ፤
አሁን የቀን ስራ ሰርተን ለመማር የማንችልበት ጊዜ ላይ እንገኛለን " የሚለው ተማሪ " ወቅታዊ ሁኔታው ተጨማሪ ስራ ሰርተን ለመማር አላስቻለንም " ብሏል።

" ሴቶች የግማሽ ቀን ስራ ካገኙ ይሰራሉ ወንዶች ቅዳሜና እሁድ ይሰራሉ። ዘንድሮ ግን የለም፤ መስራት አትችልም የተግባር ልምምድ ስለምንሄድ ትንሽ ከበድ ይላል። ባለፈው አመት ይሻላል ውጭ ላይም ትንሽ አስፈሪ ነው ሰዓቱ " ሲል ገልጿል።

በትምህርቱ ላይ ተፅዕኖ እየፈጠረ ነው መባሉን
የደሴ መምህራን ማሰልጠኛ ኮሌጅ መምህር የሆኑት መምህር አበበ ደሴ እንደሚገልፁት ተማሪዎች የዕለት ኑሯቸውን በማሰብ ስለሚጠመዱ ትምህርት የመቀበል አቅማቸው ውስን ሆኗል ብለዋል፡፡ 

" ግማሾች የቀን ስራ ሰርተው ነው የሚኖሩት። ሴቶችም ቢሆኑ በእንጀራ ጋጋሪና ካፍቴሪያ ውስጥ ተቀጥረው እየሰሩ ነው። ክፍል ውስጥም ገብተው ስታይ በአብዛኛዉ ከሚማሩበት የሚያንቀላፉበት ነው የሚበልጠው። ወጥተው የሚመገቡት የለም " ሲሉ አስረድተዋል።

የደሴ መምህራን ማሰልጠኛ ኮሌጅ ዲን ዶ/ር ሀሰን ወርቁ በበኩላቸው ተማሪዎቹ ያሉበት ችግር ለመማር ማስተማር ሂደቱ ላይ እንቅፋት ፈጥሯል ብለዋል።

ወርሃዊ የምግብ ክፍያቸውም ከ760 ብር ከፍ እንዲል ለክልሉ ትምህርት ቢሮ/ጥያቄ መቅረቡን አመልክተዋል።

" በአብዛኛው ከመማር ማስተማሩ ይልቅ ስለ እሚበሉት ፣የሚጠጡት ነው የሚያስቡት በትምህርት ላይ ተፅዕኖ አለው። ይህንን ታሳቢ አድርገን ክልል ላይም ጥያቄ እያቀረብን ነው፡፡ " ብለዋል።

Credit - ዶቼ ቨለ ሬድዮ

@tikvahethiopia
1.54K😢854😭229💔218😡47🤔39🕊33🙏31😱17👏15🥰14
ሚዛን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት !

1⃣0⃣ኛ ዙር የቴክኖሎጂና የቋንቋ ኮርሶች ምዝገባችንን በማጠናቀቅ ላይ እንገኛለን።
የመክፈል አቅም ለሌላቸው በክሬዲት (ከወለድ ነፃ በሆነ ብድር/ዱቤ) መማር የሚችሉበት እድል ከማመቻቸት ባሻገር፤
✔️ ተመርቀው ሥራ ላጡ ሁሉ 25% ቅናሽ (መስፈርት: ከቀበሌ ደብዳቤ ማፃፍ)፣
✔️ ለዩኒቨርስቲና ኮሌጅ ተማሪዎች 12% ቅናሽ (መስፈርት: የታደሰ የትምህርት ቤት መታወቂያ ማሳየት)፣
✔️ ለመምህራንና ለጤና ባለሙያዎች 12% ቅናሽ (መስፈርት: ሙያዊ ማስረጃንና ተመጣጣኝ ህጋዊ ማስረጃ ማሳየት)፣
✔️ 12ኛ ክፍል ማለፊያ ውጤት ላላመጡ 20% ቅናሽ (መስፈርት: ስም እና አድሚሽን ቁጥር ማሳየት)፣
እነዚህን እድሎች አመቻችተናል።

ለመመዝገብ፦ http://www.mizantechinstitute.com

📱 በቴሌግራም @MizanInstituteOfTechnologyEthio አግኙን።

🗺በአካል: ቤተል አፕል ፕላዛ 7ኛ ፎቅ፣ 0987143030
በማህበራዊ ሚዲያ ገፆቻችን አገኙን፦
🌐👍🌐📱▶️🌐📧 🗺
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
169🥰3😭3😱2🕊2
TIKVAH-ETHIOPIA
#MoE " ውጤት በቅርቡ ይፋ ይደረጋል " - ትምህርት ሚኒስቴር በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሲሰጥ የነበረው የ2018 የድህረ ምረቃ ትምህርት መግቢያ ፈተና መጠናቀቁን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል። ፈተናው ለመውሰድ ከተመዘገቡ 29 ሺ491 አመልካቾች መካከል 96 በመቶ ፈተናውን እንደወሰዱ አመልክቷል። በ2017 ዓ.ም. መጨረሻ ላይ ይሰጥ የነበረው የድህረ ምረቃ መግቢያ ፈተና በተለያዩ ምክንያቶች ተራዝሞ…
#NGAT

የድኅረ ምረቃ ፕሮግራም የመግቢያ ፈተና (NGAT) ውጤት ተለቋል።

የ2018 ዓ.ም የመጀመሪያ ዙር የድኅረ ምረቃ ፕሮግራም የመግቢያ ፈተና (NGAT) ውጤት ዛሬ ከሰዓት መለቀቁን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከትምህርት ሚኒስቴር አረጋግጧል።

ውጤት ለማየት 👇
https://result.ethernet.edu.et/

ከ28 ሺህ በላይ ተፈታኞች ጥቅምት 03/2018 ዓ.ም በ53 የፈተና ማዕከላት  የተሰጠውን ፈተና መውሰዳቸው ይታወሳል።

ሁለተኛው ዙር የ NGAT መግቢያ ፈተና በጥር 2018 ዓ.ም ይሰጣል።

Via @tikvahuniversity
136😢10🙏6😭5🥰2
‎" ተገቢዉን ፍትሕ አለማግኘቷ ያንገበግበኛል " - ወላጅ አባት

‎አርሶ አደር ዳንሳሞ አሌ በሲዳማ ክልል ምስራቃዊ ሲዳማ ዞን ዳኤ'ላ ወረዳ ቃዳዶ ቀበሌ ዳዱርቾ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ነዋሪ ናቸው።

ከዛሬ ሶስት ዓመታት በፊት ደጌ ዳንሳሞ አሌ የተበለች የ15 አመቷ ታዳጊ ልጃቸውን 'አበበ ክፍሌ' የተባለ ወጣት ግብራበሮቹን በማሰባሰብ ለቅሶ ቤት ተልካ ከምትመለስበት አፍነው ወደ ጫካ በመውሰድ ጭካኔ በተሞላበት መልኩ ጓደኞቹ አፍነዉ ይዘዋት በግድ ይደፍራታል።

‎ታዳጊዋ ደጌ በደም ተለውሳ፣ ትንፋሽ አጥሯት ከወደቀችበት አንስተው ቦታ በመቀየር ይህን እንስሳዊ ድርጊት ሲፈፅሙባት የተመለከች አንዲት ሴት ጩኸት ታሰማለች፤ እነሱም ተሸክመዋት ለማምለጥ ይሞክራሉ።

አባቷን ጨምሮ ከለቅሶ ቤት ሲመለሱ የነበሩ የአከባቢዉ ነዋሪዎች ጩኸቱን ወደ ሰሙበት ለእርዳታ ሲሯሯጡ በመጨረሻም ክፍሌና ጓደኞቹ ደጉን ጥለዋት ይሸሻሉ።

ሰው ለማገዝ ከሌሎች ሰዎች ጋር አብሮ ሮጦ የደረሰዉ አባቷ አቶ ዳንሳሞ አሌ የሚያየውን ማመን ያቅተዋል፤ የገዛ ልጁ በደም ተለውሳ በእርቃኗ ተዝለፍልፋ ወድቃ ሲያያት የሚይዘዉ የሚጨብጠውን ያጣል።

ከዚህ በኃላ ምን ተፈጠረ ?

‎አርሶ አደር ዳንሳሞ አሌ ስለሁኔታው ለቲክቪህ ኢትዮጵያ እስረድተዋል።

" ሰው ለመርዳት በሮጥኩበት ልጄ ተደፍራ በወደቀችበት ነበር የደረስኩት እርቃኗን ሆና ሳይ እራሴን መቆጣጠር አቃተኝ፣ የምይዘዉ የምጨብጠዉን አጣሁ፤ የለበስኩትን ጃኬት ነበር አውልቄ ሸፈንኳት፤ ጮሆኩ ሰዎች ሊያረጋጉኝ ሞከሩ፤ በጣም አሳዛኝ ልብ ሰባሪ ድርጊት ነበር " ብለዋል።

‎" አበበ ክፍሌና ጓደኞቹ ከአከባቢው ተሰወሩ ደጉ በዛኑ ምሽት ብዙ ደም ፈሷት ስለነበር ወደ ዳኤላ ሆስፒታል ተወሰደች ከዚያም ለተሻለ ሕክምና ወደ ሐዋሳ እንድትጓዝ ተደረገ " ሲሉ ገልጸዋል።

‎ደጌ ከአካላዊ መደፈር በዘለለ ከፍተኛ ስነልቦናዊ ጉዳት ስለደረሰባት እዚያዉ ሀዋሳ በአንድ ድርጅት ውስጥ እንድትቆይ ተደረገች።

‎ፖሊስ ዋናው ተጠርጣሪ ግለሰብ አበበ ክፍሌና ቀንደኛ ተባባሪ ጓደኛዉ ኢያሱ ግዴሳ ማምለጣቸዉንና ሶስቱን ግብራበሮች ግን መያዙን ገልፆ ክስ መሰረተባቸዉ።

‎ፍርድ ቤቱ በነዚህ ሶስት ግብራበሮቹ ላይ የ6 አመት ፅኑ እስር ፈርዶባቸው የነበር ቢሆንም ከ2 አመት እስር በኋላ በአመክርዎ ይለቀቃሉ።

ዋናው ወንጀለኛ እና በታዳጊዋ ላይ ጥቃት ያደረሰው " አበበ ክፍሌ" የተባለው ሰው ግን እስከ ዛሬ ድረስ አልተያዘም ለፍርድም አልቀረበምም።

የደጉ አባት ይህን ጉዳይ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ሲያስረዱ " ከተፈፀመባት ነውረኛ ተግባር በላይ ተገቢዉን ፍትሕ አለማግኘቷ ያንገበግበኛል " ሲሉ ነው የገለፁት።

‎በዚህ መሃል አርሶ አደር ዳንሳሞ ሌላ አሳዛኝ ጉዳይ አጋጠመኝ ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል። ይህም የአከባቢው ሽማግሌዎች " ነገሩን በሽምግልና ካልፈታን " ማለት መጀመራቸው ነው።

" ፖሊስ ' ማግኘት አልቻልኩም ተሰውሮብኛል ' ያለውን ግለሰብ ሽማግሌዎቹ ከየት አመጡት " በማለት ሽምግልናውን እምቢ ማለታቸውን ገልጸዋል።

ሽማግሌዎችም " እንዴት አምቢ ትላለህ ? ሌላስ ልጅህ ላይ መሰል ነገር ቢደርስ ሽማግሌ አይደል የሚፈታው ? " እያሉ ያስጨንቋቸው እንደጀመረ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ደጌ አሁንም ፍትሕ እንደተጠማች ሀዋሳ እንደርሷ ጥቃት የደረሳቸውን ታዳጊዎች ሰብስቦ በሚያኖር ድርጅት ውስጥ ናት።

" የደጌ ታናሽ ግን ገና 12 አመቷ ነው ሽማግሌዎችን እምቢ አልክ ብለው በሷ እንዳይበቀሉኝ እፈራለሁ " ሲሉ አባት ተናግረዋል።

" ‎ስለ ጉዳዩ ከወረዳው እስከ ክልሉ ባለድርሻ አካላት መስሪያ ቤት ደጅ ብጠናም ' የተዘጋ ፋይል ነው ፤ የነሱ ፋይል ጠፍቶብናል ስናገኝ እናሳውቃለን ' በማለት ብዙ አንገላቱኝ " ሲሉ ስለ ፍትህ ድምጻቸውን አሰምተዋል።

‎ቲክቫህ ኢትዮጵያ በጉዳዩ ዙሪያ የዳ'ኤላ ወረዳ እና ምስራቃዊ ሲዳማ ዞን ፖሊስና ፍትሕ (ዐቃቤ ሕግ) አካለትን ለማነጋገር ቢሞክርም " በአካል ካልተገኛችሁ መረጃ መስጠት አንችልም " በማለታቸው በዚህ መረጃ ምላሻቸዉን ማካተት አልተቻለም ፤ መረጃዉ እንደደረሰን የምናቀርብ ይሆናል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia
😭1.59K622😡200💔102🙏27😢23🤔12🥰9😱9🕊7
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA #Eurobond ኢትዮጵያ የቦንድ ብድር ወለድ በወቅቱ ያልከፈለችው ለምንድነው ? ኢትዮጵያ በዓለም ገበያ ለሸጠችው የ1 ቢሊዮን ዶላር ዩሮ ቦንድ ሰኞ ዕለት መክፈል የነበረባትን ወለድ እስካሁን አልከፈለችም። የ1 ቢሊዮን ዶላር ቦንድ ለሽያጭ የቀረበው ከ9 ዓመት በፊት በ2007 ዓ.ም ነበር። ኢትዮጵያ ይህንን ቦንድ ሸጣ ከገዢዎች አንድ ቢሊዮን ዶላር ብድር ያገኘች ሲሆን ብድሩ የሚመለሰው…
ኢትዮጵያ የዩሮ ቦንድ ዕዳዋን መልሶ ለማዋቀር ያደረገችው ድርድር መክሸፍና መዘዞቹ ምን ይሆናሉ ?

ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ. 2014 ከዓለም አቀፍ ገበያ በዩሮ ቦንድ አንድ ቢሊየን ዩሮን ለመበደር የበቃችው የአገሮችን ብድር የመክፈል አቅም የሚለኩት እንደ ፊች፣ ፑር እና ሙዲ የመሳሰሉ ተቋማት በአማካይ ‹‹B›› የተሰኘውንና በአንፃሩም ጥሩ የተባለ ደረጃ ሰጥተዋት እንደሆነ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

እነዚሁ የአገሮችን ብድር የመክፈል አቅም የሚለኩ ተቋማት አገሪቱ ብድር የመክፈል ጊዜዋ በደረሰ ጊዜ ከሁለት ዓመታት በፊት ማለትም በ2023 ዓ.ም. ደረጃዋን በእጅጉ አውርደው ወደ cc- ድረስ ዝቅ አድርገውታል።

ያኔም ብድሩ የተወሰደው በኢንዱስትሪ ፓርኮች ግንባታ ላይበማዋል ምርታማነትን አሳድጎ ብድሩንም መመለስ ይቻላል በሚል ነበር፡፡

ከዚያ ወዲህ ግን ኢትዮጵያ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ እና ከሁለት ዓመታት በላይ በዘለቀ ደም አፋሳሽ ጦርነት ስትናጥ ኢኮኖሚዋ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ገብቷል።

በዩሮ ቦንድ ከተበደረችው ብድር ባለፈ ከተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማትና መንግስታት የተበደረቻቸውን ብድሮች የመክፈሏ ነገር ችግር ውስጥ ስለገባ የብድር መክፈያ ጊዜዋ እንዲራዘምላት ከአበዳሪዎቿ ጋር ተደጋጋሚ ድርድሮችን ስታደርግ ቆይታለች፡፡

ሆኖም ድርድሩ ውጤታማ መሆን ባለመቻሉና አገሪቱ ከብድርና ዕርዳታ እየተገለለች መጥታ ብድር መክፈል እያቃታት በመሆኑ የብድር መክፈያ ጊዜ ሽግሽግ ድርድሩ እስኪሳካ ጊዜያዊ የብድር መክፈያ ጊዜ የማራዘም መርሐ ግብር ውስጥ ተገብቶ ቆይቷል፡፡

ከሰሞኑም ኢትዮጵያ ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ ዕዳዋን የመክፍያ ጊዜ ለማራዘም ያደረገችው ድርድር ያለ ውጤት የተጠናቀቀ ሲሆን፣ የአበዳሪዎቹ ኮሚቴ ጉዳዩን ወደ ሕግ ለመውሰድ እንደሚገደድ አስታውቋል፡፡

የገንዘብ ሚኒስቴር ማክሰኞ ጥቅምት 4 ቀን 2018 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ እ.ኤ.አ. በ2024 ተከፍሎ መጠናቀቅ የነበረበትን ከ13 ዓመታት በፊት በዩሮ ቦንድ ሽያጭ የተበደረችውን አንድ ቢሊዮን ዶላርና 6.625 በመቶ ወለድ ያካተተ ዕዳ መልሶ ማዋቀር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ፣ ቦንዱን ከገዙት (አበዳሪዎች) ቡድን ጊዜያዊ ኮሚቴ ጋር ለሶስት ሳምንታት ገደማ የተገደበ ውይይት ሲካሄድ መቆየቱን አስታውቋል።

ኢትዮጵያ ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ ዕዳዋን የመክፍያ ጊዜ ለማራዘም ያደረገችው ድርድር ያለ ውጤት ተጠናቀቀ፣ የአበዳሪዎቹ ኮሚቴ ጉዳዩን ወደ ሕግ ለመውሰድ እንደሚገደዱ አስታውቀዋል፡፡

በውይይቱ ላይም ከኢትዮጵያ መንግሥት ተወካዮች በተጨማሪ በኢትዮጵያ መንግሥት የተቀጠሩት ዋይት ኤንድ ኬዝ ኤልኤልፒ የተባለ የሕግ አማካሪና ላዛርድ የተባለ የፋይናንስ አማካሪ መሳተፋቸውን ገልጿል።

የኢትዮጵያን ቦንድ የገዙ ቡድኖች በመወከል ደግሞ ቡድኖቹ ያቋቋሙት ጊዜያዊ ኮሚቴና የሕግና የፋይናንስ አማካሪዎች መሳተፋቸውን ጠቅሷል።

ጉዳዩን በሚመለከት ባለሙያዎች ምን አሉ ?


የቢዝነስና ኢንቨስትመንት አማካሪው አቶ ከፈለኝ ኃይሉ የድርድሩ አለመሳካት ምንነት እንዲሁም ሊኖረው የሚችለውን ተፅዕኖ ለሪፖርተር ጋዜጣ ሲያብራሩ፣ ቴክኒካል የሚሏቸውን ሁነቶች በመጥቀስ " አለመተማመን እንዳለ አመላካች ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

" አልተሳካም ማለት መሉ በሙሉ ተስፋ የለውም ማለት አይደለም፣ መስማማት ያልቻሉት ፋይናንስ ነክ ባልሆኑ ጉዳዮች ነው። በቀጣይ በሚኖር ድርድር መስማማት ካልቻሉ ግን ኢትዮጵያ ዕዳዋን መከፍል የማትችልበት ሁኔታ (Default) ውስጥ ትገባለች ይህ ደግሞ ለኢትዮጵያ ጥሩ አይደለም " ብለዋል።

ኢትዮጵያ ዕዳዋን መክፈል ከማትችልበት ሁኔታ (Default) ውስጥ ከማስገባቱ በተጨማሪም ተሻጋሪ ተጽዕኖ እንደሚኖረው ፤ በዋናነትም ኢትዮጵያ የወሰደችውን በድር መክፈል የማትችል ተደርጋ እንድትቆጠርና በዚህም ከሌሎች የግል አበዳሪዎች አዲስ ብድር ለማግኘት እንዳትችል እንደሚያደርጋት ወይም ብታገኝ እንኳን ፍተኛ ወለድ ክፍያ እንደሚሆን ገልጸዋል።

" በአጠቃላይ ይህ ሁኔታ ከተፈጠረ የኢትዮጵያን ብድር የመክፈል እይታ ያበላሻል " ብለዋል።

ድርድሩን ያለስምምነት መጠናቀቁን ተከትሎ የአበዳሪዎቹ ኮሚቴ ጉዳዩን በሕግ አግባብ ለማየት መወሰኑ ምን ዓይነት የሕግ አግባቦችን ያካትታል በሚል ጥያቄ ቀርቦላቸው መልሰዋል።

" ኢትዮጵያ ወደ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ገበያው ወጥታ ሌሎች ብድሮችን እንዳታገኝ ሊያሳግዱ ይችላሉ። ከዚህ በተጨማሪም ሸቀጦችን ወደ አገር ለማስገባት ኤልሲ (Letter of Credit) ሙሉ በሙሉ መክፈት የማይቻልበት ሁኔታ ሊፈጥር ይችላል "  ብለዋል።


" በተጨማሪም በውጭ አገር የሚገኙ የኢትዮጵያ መንግሥት ሀብትና ንብረቶችን አስገድደው በማሸጥ እንዲከፈላቸው ሊያደርጉ ይችላሉ፣ በዚህም የኢትዮጵያ ንብረቶች ሊያዙ ይችላሉ " ሲሉ አስረድተዋል።


በሌላ በኩል በዚህ ምክንያት በኢትዮጵያ ላይ የሚፈጠረው የገጽታ መበላሸት ደግሞ የውጭ አገር ባለሀብቶች ወደ ኢትዮጵያ እንዳይመጡ ሊገድብ እንደሚችል ገልጸዋል።

የኢኮኖሚ ተንታኙ (ዶ/ር) ተስፋቸው ተፈራ ደግሞ ፥ ኃያላን መንግሥታት በአነስተኛ ወለድ ይሰጡ የነበረው ብድር እየተመናመነ በመምጣቱ አገሮች የካፒታል ፍላጎታቸውን ለማሟላት ወደ ዓለም አቀፍ የቦንድ ገበያ በመውጣት በቦንድ ሽያጭ ብድር የሚየመገኙበት ሁኔታ በገቡበት ወቅት ኢትዮጵያ በዩሮ ቦንድ ሽያጭ የተበደረችውን መክፈል ባለመቻሏ ድርድር ውስጥ መግባቷና ድርድሩም በስኬት አለመጠናቀቁ ዋጋ እንደሚያከፍል ተናግረዋል።

" ኢትዮጵያ የዩሮ ቦንድ ዕዳዋን መልሶ ለማወቀርና የክፍያ ጊዜውን ለማራዘም ያደረገችው ድርድር አለመሳካቱ እንዳለ የሚቀጥል ወይም በቀጣይ ድርድር ስምምነት የማይደረስበት ከሆነ፣ ከፓሪስ ክለብ አበዳሪዎች ተመሳሳይ የዕዳ ቅነሳና የመክፈያ ጊዜ ለማግኘት የመግባቢያ ስምምነት የደረሰችበትን ጉዳይ እንደሚያበላቸው ገልጸዋል።

የዩሮ ቦንድ አበዳሪዎች ጊዜያዊ ኮሚቴ አባላት ከኢትዮጵያ ጋርየተደረገው ድርድር ባለመሳካቱ መበሳጨታቸውንና በቀጣይከኢትዮጵያ መንግሥት የተሻሻሉ የድርድር ፍሬ ሐሳቦችን ለመስማት ዝግጁ መሆናቸውን፣ ነገር ግን አሁን ባለበት ደረጃ ድርድሩ እክል እንደገጠመውና መፍትሔ ካልተገኘም ኢትዮጵያን በሕግ እንደሚጠይቁ ገልጸዋል።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የሪፖርተር ጋዜጣ ነው።

@tikvahethiopia
464😭144🤔24💔17👏12🥰10😢6😡3🕊2
TIKVAH-ETHIOPIA
የቀድሞ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ፕሬዝዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ኡመር ኢድሪስ በጠና መታመማቸውን ከቤተሰቦቻቸው ተሰምቷል። ታላቁ የሃይማኖት አባት ህክምናቸውን እዚሁ ሀገር ውስጥ በሚገኝ ሆስፒታል እየተከታተሉ እንደሚገኙ ነው የተገለጸው። ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ኡመር ኢድሪስ ከ2011 ጀምሮ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት በመሆን ለ3 ዓመታት መርተዋል። @tikvahethiopia
ታላቁ አባት ሐጂ ኡመር ኢድሪስ አረፉ።

የቀድሞ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት የክቡር ዶ/ር ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ኡመር ኢድሪስ ወደ አኼራ ሄደዋል።

ታላቁ የሃይማኖት አባት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ኡመር ኢድሪስ ባጋጠማቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ዛሬ ወደ አኼራ ሄደዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለአባታችን ሐጂ ኡመር ኢድሪስ ቤተሰቦች እንዲሁም ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ መፅናናትን ይመኛል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
7😭11.2K💔1.45K😢620556🕊314🙏140😱92👏64🤔31😡26🥰25
2025/10/20 01:05:11
Back to Top
HTML Embed Code: