Telegram Web Link
#AwashBank

እንኳን ደስ አላችሁ! እንኳን ደስ አለን!
===========
አዋሽ ባንክ በዓለም አቀፍ የቁጠባ እና የሪቴል ባንኪንግ ተቋም እንዲሁም የአውሮፓ የቁጠባ እና የሪቴል ባንኪንግ ቡድን በጋራ የሚያዘጋጁትን የWSBI-ESBG አዋርድ አሸናፊ ሆነ።
ይህንኑ ሽልማት በትላንትናው እለት በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ በተካሄደው የWSBI-ESBG የሽልማት መርሃ-ግብር ላይ በመገኘት የባንካችን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ፀሀይ ሽፈራው ተቀብለዋል። ባንካችንም ይህን እውቅና ሊያገኝ የቻለው የዘላቂ ልማት ግቦች ትግበራ ላይ የላቀ አፈፃፀም በማስመዝገብ እንዲሁም አርዓያነት ያለቸውን ምርጥ አሰራሮችን በተለያዩ ዘርፎች በማስመዝገቡ ነው። ከነኚህ ዘርፎችም መካከል ፡-
* በአካታች የባንክ አገልግሎት እና ማህበራዊ ተፅዕኖ፣
* በኢኮኖሚያዊ ዕድገት እና አቅም ማጎልበት፣
* በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እና የቴክኖሎጂ ፈጠራ እንዲሁም
* ደንበኛ ተኮር የአቅም ግንባታ ማከናወን ይገኙባቸዋል፡፡
ይህ የእውቅና ሽልማት የተገኘው ክቡራን ደንበኞቻችን በባንካችን ላይ ባሳደራችሁት እምነት በመሆኑ በዚሁ አጋጣሚ የላቀ ምስጋናችንን እያቀረብን ለወደፊቱም በበለጠ ልናገለግላችሁ ዝግጁ መሆናችንን በአክብሮት እንገልፃለን፡፡
አዋሽ ባንክ!
#AwashBank #WSBI_ESBGAwards
2660👏91🙏45😡40🤔16🥰9😱4🕊4😭3😢1
“አንድ ፖሊስ ጥይት ባርቆበት ነው ልጁ የሞተው ” - የአካባቢው ባለስልጣን

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጌዲኦ ዞን ወናጎ ከተማ አስተዳደር አንድ ወጣት “በግዴለሽ አያያዝ” ከፖሊስ በተባረቀ ጥይት ሕይወቱ ማለፉን የአካባቢው ባለስልጣን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

“በወናጎ ወረዳ” አንድ በጋራዥ ሥራ የተሳማራ ወጣት ትላንት ለሻይ በተቀመጠበት አጠገቡ የነበረ ፖሊስ ጥይት ባርቆበት እንደቆሰለና ወደ ህክምና ቢወሰድም ህይወቱን ማትረፍ እንዳልተቻለ ተሰምቷል፡፡

በቦታው የነበሩ ሰዎች፣ “ፖሊሱ መሳሪያውን አቀባብሎ ጭኑ ላይ አስቀምጦት ነበር፤ ይሁን እንጅ ጥይት ለማቀባበል የሚያደርስ በአካባቢው የተለዬ የጸጥታ ችግር አልነበረም” ብለዋል፡፡

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ስለሁነቱ አንድ የአካባቢወን ባለስልጣን ያነጋገረ ሲሆን፣ ጥቃቱ መድረሱን አረጋግጠው፣ ድርጊቱ የተፈጠረው ግን “ወናጎ ወረዳ ላይ ሳይሆን ከተማ አስተዳደሩ ላይ ነው፤ ከተማ አስተዳደሩና ወረዳው ይለያያሉ” ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ሁነቱን ሲያስረዱም፣ “አንድ ፖሊስ ጥይት ባርቆበት ነው ልጁ ላይ የሞት ጉዳት የደረሰው፡፡ ፖሊስ ሆን ብሎ ያደረገው ነገር አይደለም” ነው ያሉት፡፡

“ከተማ አስተዳደሩ ውስጥ ባጋጣሚ የተፈጠረ እንጅ ሆን ተብሎ የተደረገ ድርጊት አይደለም” ያሉት እኝሁ አካል፣ “ፖሊሱ በሕግ ጥላ ሥር ነው ያለው” ሲሉም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል፡፡

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
1😭1.27K568😡186😢62💔62🕊31🙏21🤔17🥰9😱6
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ዲቫይዞቹ በኢትዮ ቴሌኮም ብራንድ፣ ስያሜ እና ዲዛይን የተመረቱ ናቸው " - ኢትዮ ቴሌኮም

ኢትዮ ቴሌኮም በክላውድ ላይ የተመሰረቱ "ዘኔክሰስ" ሲል የጠራቸው ስማርት ዲቫይስ እና የክላውድ ዎርክስፔስ መፍትሄዎችን ማቅረቡን ይፋ አድርጓል።

በዛሬው ዕለት ይፋ የተደረጉት ዲቫይዞች በከፍተኛ የስማርት ዲቫይሶች ዋጋ ምክንያት የተከሰተውን የአጠቃቀም ክፍተት (usage gap) ለመሙላት ያስችላሉ ተብሏል።

የአጠቃቀም ክፍተትን ለመሙላት ያስችላሉ የተባሉት እና ኢትዮ ቴሌኮም ይፋ ያደረጋቸው " ዘኔክሰስ " የተሰኙት ዲቫይዞች :-
- የሞባይል ስልኮች፣
- ታብሌቶች፣
- ዴስክቶፖች፣
- ላፕቶፖች፣
- ቲን ክላየንት (thin clients) እና የክላውድ ዎርክስፔስ መፍትሔዎችን ያካተቱ ናቸው።

ዲቫይዞችን ይፋ ያደረጉት የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ " ከ60 በመቶ በላይ የሚሆኑት ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት የሚገኙ የሞባይል ተጠቃሚዎች የኔትወርክ ሽፋን ያለበት አካባቢ የሚኖሩ ቢሆንም የስማርት ስልኮችን መግዛት ባለመቻላቸው ከዲጂታል አገልግሎቶች ተገልለው ይገኛሉ " ብለዋል።

ይህንን ማህበረሰብ ወደ ዲጂታል አገልግሎቱ ማስገባት እንዲቻል ዲቫይዞቹ ይፋ መደረጋቸውን ዋና ስራ አስፋጻሚዋ ገልጸው " ዲቫይዞቹ በኢትዮ ቴሌኮም ብራንድ፣ ስያሜ እና ዲዛይን የተመረቱ ናቸው " ብለዋል።

በእዚህ አመት 3.5 ሚሊየን ዲቫይዞችን በተለያየ ሞዴል ለማቅረብ አስበናል ያሉት ዋና ስራ አስፈጻሚዋ ዘ ኔክሰስ የኢትዮጵያ ማርኬት ለሌሎችም ገበያ እንዲሆን ታልሞ ይህንን ስያሜ መሰጠቱን ጠቅሰዋል።

በተጨማሪም ስማርት ፊቸር ፎን የተባለበት ምክንያት ተች ያለው በመሆኑ ፣ ከክላውድ ጋር የተገናኘ እና የተለያዩ አይነት አፕልኬሽኖችን ማስጠቀም የሚችል በመሆኑ ምክንያት መሆኑን አስረድተዋል።

ስቶሬጅን በሚመለከትም በሚያስፈልጋቸው ልክ እያሳደጉ የሚጠቀሙበት እድል ተፈጥሯል ብለዋል።

የሞባይል ቀፎዎቹ የቀረቡበትን ዋጋ በቀጥታ ያልገለጹ ሲሆን ተመሳሳይ ደረጃ ላይ ካሉ ስልኮች ጋር ሲነጻጸር ግን ከ60 -70 በመቶ ዋጋው እንደሚቀንስ አስረድተዋል።

ዲቫይዞቹ በሁለቱም (keypad + touchscreen) ማስጠቀም የሚያስችሉ ፣  ረጅም የባትሪ ዕድሜ ያላቸው፣ በተገጠመ የቴሌስቶሬጅ (teleStorage) አማካኝነት የፋይል ማከማቻ ገደቦችን የሚያስወግዱ እና የቴሌብር፣ የትምህርት ይዘቶች እንዲሁም ሚዲያዎች ያሉ አፕሊኬሽኖችን የተጫነባቸው እንደሆኑ ተገልጿል።

ይፋ የተደረጉት ስማርት ዲቫይሶች:-

➡️ ዘኔክሰስ 127 ላይት (znexus 127 Lite)፣
➡️ ዘኔክሰስ 131 ላይት (znexus 131 Lite) እና ➡️ ዘኔክሰስ 2028 ላይት (znexus 2028 Lite) ሞዴሎች ናቸው።

ዲቫይዞቹ ዩቲዩብ፣ ቲክቶክ፣ ፌስቡክ፣ ጌሞች፣ አጫጭር ፊልሞች እና ዜናዎች የመሳሰሉ መተግበሪያዎች በክላውድ በማቅረብ ተጠቃሚዎች በቀላሉ የስማርት ስልክ (smartphone-lite) ተሞክሮ እንዲያገኙ ያስችላሉ ተብሏል።

ዘኔክሰስ በክላውድ ላይ የተመሰረተ እና ስማርት ስልኮች የሚሰጡትን አገልግሎት መስጠት የሚያስችል የስልክ አይነት መሆኑን ይፋ በማድረጊያ ስነ ስርአቱ ወቅት ተገልጿል።

በተጨማሪም ኢትዮ ቴሌኮም "ዘኔክሰስ ክላውድ ወርክስፔስ ሶሉሽን" ይፋ ያደረገ ሲሆን የክላውድ ወርክስፔስ ሶሉሽኑ ቢዝነሶችን፣ የመንግስት እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን ቨርቹዋል ዴስክቶፖችን እና አፕሊኬሽኖችን ከማንኛውም ዲቫይስ ጋር ለማገናኘት የሚያስችል መሆኑን እና  የአይ.ቲ ወጪዎችን ለመቀነስ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ተነግሯል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ

@tikvahethiopia
779😡44👏34🙏15😭12🕊9🤔6🥰2😱2
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
‎" በአስክሬን ሽኝቱ ፕሮግራም ላይ በተነሳ ብጥብጥ 7 ሰዎች ሞተዋል " - ነዋሪዎች

ዛሬ ‎በናይሮቢ ካሲራኒ ለቀድሞዉ የኬንያ ጠቅላይ ሚንስትር ራይላ ኦዲንጋ የአስከሬን ሽኝት መርሃግብር ተካሂዷል።

በዚሁ ወቅት በተነሳ ብጥብጥ የሰባት ሰዎች ሕይወት ማለፉን የዐይን እማኞች ናይሮቢ ለሚገኘው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ባልደረባ ተናግረዋል።

‎እንደ ዐይን እማኞቹ ገለፃ ሁለት ሰዎች ከፀጥታ ሃይል በተተኮሰ ጥይት የተገደሉ ሲሆን አምስት ሰዎች ተኩሱን ተከትሎ በነበረ ግርግር ሕይወታቸው ማለፉን ገልፀዋል።

‎ቲክቫህ ኢትዮጵያ በስፍራው ተገኘቶ እንደተመለከዉ በስታዲየሙ የራይላ ኦዲንጋ አስክሬን ስንብት እየተካሄደ በነበረበት የተወሰኑ ወጣቶች ከፀጥታ አካላት ጋር በፈጠሩት አለመግባባት ጥይት የተተኮሰ ሲሆን አስለቃሽ ጭስም ተወርውሮ ሕዝቡ ከስታዲየሙ እንዲወጣ ተደርጓል።

‎የሀገሪቱ ሚዲያዎች የሟቾችን ቁጥር ሁለት ብለዉ የዘገቡ ሲሆን ጉዳት ስለደረሰባቸው ሰዎች እስካሁን ምንም የተባለ ነገር የለም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ናይሮቢ
#TikvahEthiopiaFamilyNairobi

@tikvahethiopia
474😢142🤔40💔20😭20😡18🕊17🥰8👏7😱7🙏4
" የስኮላርሺፑን የሙሉ አመት የትምህርት ወጪ የሩሲያ መንግሥት ይሸፍናል " - ሩሲያን ሃውስ

የሩሲያ መንግስት በማንኛውም የትምህርት መስክ በሩሲያ ትምህርት የመከታተል ፍላጎት ላላቸው ተማሪዎች ስኮላርሺፕ ማመቻቸቱን አሳውቋል።

ስኮላርሺፑ የሩሲያ መንግስት ለ155 የባችለር፣ ማስተርስ እና ፒ ኤች ዲ ተማሪዎች በማንኛውም ፊልድ እንዲማሩ የፈቀደው ነው።

ባለፈው አመት ለ100 ተማሪዎች ተፈቅዶ የነበር ስኮላርሺፕ በዘንድሮ አመት ቁጥሩ ወደ 155 ተማሪዎች ከፍ የተደረገ ሲሆን እንደ አመልካቾች ብዛት የሩሲያ መንግስት ቁጥሩን ከእዚህም ከፍ ሊያደርገው እንደሚችል የሩሲያ ሳይንስ እና ባህል ማዕከል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቋል።

የሩሲያ የሳይንስ እና ባህል ማዕከል ወይም በአዲሱ ስያሜው ሩሲያን ሃውስ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል ፤ የስኮላርሺፑ ሙሉ የትምህርት ክፍያ በሩሲያ መንግሥት የሚሸፈን መሆኑን ገልጾ የጉዞ ትኬት እና የኢንሹራንስ ወጪዎችን ብቻ በአመልካቾች የሚሸፈን ይሆናል ብሏል።

የትምህርት ሂደቱ የቆይታው ጊዜ ለባችለር አራት አመት ለማስተርስ ሁለት አመት እንዲሁም ለ ፒ ኤች ዲ አመልካቾች እንደ ትምህርቱ አይነት የቆይታ ጊዜያቸው የሚወሰን ይሆናል ተብሏል።

ስኮላርሺፑን አሸንፈው የሚሄዱ ተማሪዎች ትምህርታቸውን ከመጀመራቸው በፊት ለአንድ አመት የቋንቋ ትምህርት የሚማሩ ሲሆን እንደ ሩሲያን ሃውስ መረጃ ስኮላርሺፑ የሙሉ የትምህርቱን እና የቋንቋን አንድ አመት ቆይታ ያካተተ ነው።

ተማሪዎች ካመለከቱ በኋላ ለስኮላርሺፑ ብቁ የሆኑትን የማጣራት ሂደት የመጀመሪያው ዙር በሳይንስ ማዕከሉ ከተከናወነ በኋላ ሁለተኛ እና ሦስተኛ ዙር የማጣራት ሂደቶች በሩሲያ ዩኒቨርሲቲዎች እና በሚመለከታቸው አካላት የሚከናወን ይሆናል።

ለስኮላርሺፑ የማመልከት ሂደት ሴፕቴምበር 15 የተጀመረ ሲሆን እስከ ጃንዋሪ 15 የሚቀጥል ይሆናል ተብሏል።

በሩሲያ የሳይንስ እና ባህል ማዕከል የስኮላርሺፑ አስተባባሪ የሆኑት አቶ ናድር መሃመድ " የራሺያን ስኮላርሺፕ እንዲሳካ እናደርጋለን እያሉ ብር የሚቀበሉ ኤጀንሲዎች እያየን ነው " ያሉ ሲሆን በስኮላርሺፑ ዙሪያ ህጋዊ ሰውነት ያለው እና የሚያስተባብረው የሩሲያ ሳይንስ እና ባህል ማዕከል ብቻ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

አተባባሪው አመልካቾች ለማማከር እና ለተጨማሪ መረጃ ከሰኞ እስከ አርብ በስራ ሰአት ወደ ማዕከሉ በመደወል መረጃ በነጻ ማግኘት እንደሚችሉ ገልጸዋል።

ለስኮላርሺፑ ለማመልከት መሟላት ያለባቸው ነገሮች ምንድን ናቸው ?

ፓስፖርት አስፈላጊ ቢሆንም ስኮላርሺፑን ለማመልከት አስገዳጅ አይደለም።

በቀበሌ ወይም በፋይዳ መታወቂያ ማመልከት ይቻላል።

የአመልካቾች የ9 ፣ 10 ፣ 11 እና 12 የትምህርት ማስረጃቸው እንዲያስገቡ ይጠየቃል።

አሁን 12 ክፍል እየተማሩ ያሉ አመልካቾች እስካመለከቱበት ጊዜ ያለውን የትምህርት ማስረጃ አስገብተው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ውጤት ደግሞ ሲደርስ መስገባት ይችላሉ።

ለማስተርስ አመልካቾች ዲግሪ እና ግሬድ ሪፖርት አስፈላጊ ነው (ዲግሪው ያልደረሰለት ቴምፖራሪውን ማስገባት ይችላል)።

ለፒ ኤች ዲ አመልካቾች የሪሰርች ፕላናቸው ምን እንደሆነ ማስገባት የሚኖርባቸው ሲሆን አስገዳጅ ባይሆንም ፕብሊሽ የተደረገ የጥናታዊ ጽሁፍ ቢኖራቸው ይመከራል።

ባለፈው አመት ስኮላርሺፑ የተሰጠው 50 በመቶ ለባችለር ዲግሪ ፣ 30 በመቶ ለማስተርስ ዲግሪ እና 20 በመቶ ለፒኤች ዲ ዲግሪ ቢሆንም ይህኛው ስኮላርሺፕ እንደ አመልካቹ ቁጥር ብዛት ፐርሰንቱን ሊሸጋሸግ ይችላል።

ጥሩ ውጤት ያላቸው ተማሪዎች የመመረጥ እድላቸው ሰፊ ነው በመሆኑ ቢያመለክቱ ይመረጣል።

ጥሩ ውጤት የሌላቸው ተማሪዎች የስኮላርሺፑ የውድድር ሂደት የተማሪዎችን የትምህርት መረጃ በማስተያየት የሚከናወን በመሆኑ በአንዳንድ ትምህርቶች ጥሩ ውጤት ካላቸው ተማሪዎች የተሻሉ ሆነው ቢገኙ ባላንስ ስለሚያደርግ ማመልከት ይችላሉ።

ስኮላርሺፑን https://www.education-in-russia.com ሊንክ በመጠቀም ቋንቋውን ወደ እንግሊዝኛ በመቀየር ማመልከት ይቻላል።

ለተጨማሪ መረጃ ወደ ሩሲያ ሳይንስ እና ባህል ማዕከል በEmail - [email protected]
ወይም [email protected]

እንዲሁም በስልክ ቁጥር 251 11 155 1343 ማግኘት ይቻላል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
2.63K👏156🥰51🕊49🙏41😡38😢21🤔18😭16💔9😱6
አዲስ ባንክ አ.ማ. የአንድ አክሲዮን ትርፍ ክፍፍል ወደ 57.3 በመቶ አሳደገ

አዲስ ባንክ አ.ማ. በተጠናቀቀዉ በጀት አመት ከታክስ በፊት የተገኘውን ትርፍ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር በ397 በመቶ በማሳደግ ብር 2.9 ቢሊዮን እንዲሁም ከታክስ በኋላ የተገኘው የተጣራ ትርፍ ብር 2.2 ቢሊዮን ሆኗል። በዚህም ባንኩ ከፍተኛ የሆነ የአክስዮን ትርፋ ድርሻ ማለትም 92.43 በመቶ እንዲሁም 57.37 በመቶ የትርፍ ክፍፍል መስጠት ችሏል፡፡

በበጀት ዓመቱ የባንኩ ጠቅላላ ሀብት ካለፈው ዓመት የ53.4 በመቶ ጭማሪ በማሳየት ብር 23.4 ቢሊዮን የደረሰ ሲሆን፣ ጠቅላላ ካፒታሉ በ78.9 በመቶ አድጎ ብር 5.6 ቢሊዮን ደርሷል።

በበጀት ዓመቱ የባንኩ የውጭ ምንዛሪ ግኝት የ30 በመቶ እድገት በማሳየት 189 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ለማግኘት ተችሏል።

በተጨማሪም በበጀት ዓመቱ ባንኩ የእይታ ገጽታውን ለማዘመንና የደንበኞችን አገልግሎት ለማሻሻል የገጽታ ስም ለውጥ (rebranding) ያደረገበት ታሪካዊ ወቅት ነበር። የዚህ ጥረት አካል የሆነው እና የባንኩን የወደፊት ማንነቱን የሚያንጸባርቁ አዲስ አርማ፣ የታደሰ መፈክር እና የሥም ማሻሻያዎችን አስተዋውቋል።


አዲስ ባንክ- ለስኬትዎ የታመነ!

ለወዳጅ ዘመድ ያጋሩ!
Website- (http://www.addisbanksc.com/)
Telegram- (www.tg-me.com/AddisBank_sc)
Facebook- (http://facebook.com/addisinternationalbank)
Linked in- (https://www.linkedin.com/company/addis-international-bank/)
353👏50😢6🙏5😭1
#ማብራሪያ

ትምህርት ሚኒስቴር የ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም መከታተል የሚችሉ ተማሪዎች በግልም ሆነ በመንግሥት ተቋማት እንደተፈተኑት የትምህርት አይነት ብዛት 33 ከመቶና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ ተማሪዎች እንደሆኑ መግለፁ ይታወቃል፡፡

ሚኒስቴሩ የ2018 ትምህርት ዘመን የአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ መቁረጫ ነጥብን በተመለከተ በቀን 06/02/2018 ዓ.ም ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ማብራሪያ ልኳል፡፡

33 ከመቶና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ ተማሪዎች የሚለው ወደ ቁጥር ሲገለፅ ልዩነት መኖሩ፤ የፐርሰንቱ እና የቁጥሩ አገላለጽ በደንብ clear ለማድረግ“ ማብራራያው ማስፈለጉን የኢትዮጵያ የግል ከፍተኛ ትምህርት እና የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት ማኅበር ሥራ አስኪያጅ ተፈራ ገበየሁ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ @tikvahuniversity ተናግረዋል፡፡

የ2018 ትምህርት ዘመን የአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም መቁረጫ ነጥብ በመንግሥትም ሆነ በግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ልዩነት የሌለ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

የ2018 ትምህርት ዘመን የመቁረጫ ነጥብ ዝርዝር ፦

➡️ የተፈጥሮ እና የማኅበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች 216 ከ 600
➡️ የተፈጥሮ እና የማኅበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች 204 ከ 600
➡️ ታዳጊ ክልሎች እና የአርብቶ አደር አካባቢ የተፈጥሮ እና የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ለሁለቱም ጾታ 198 ከ 600
➡️ የተፈጥሮ እና የማኅበራዊ ሳይንስ መስማት ለተሳናቸው ተማሪዎች ለሁለቱም ጾታ 198 ከ 600
➡️ የተፈጥሮ እና የማኅበራዊ ሳይንስ ዓይነ ስውራን ተማሪዎች ለሁለቱም ጾታ 165 ከ 600

ቲክቫህ ኢትዮጵያ

Via @tikvahuniversity
466😡24👏18💔8😭7🙏6😱4🕊4😢2
#MoE

በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ወስዳችሁ ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግሥት ዩኒቨርስቲዎች የሪሚዲያል ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የተቋም ምርጫቸውን በየትምህርት ቤታቸው በተወከሉ መምህራን በኩል እስከ ጥቅምት 12/2018 ዓ.ም  ድረስ ማስተካከል እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡

የሪሚዲያል ፕሮግራም #የማያስተናግዱ ዩኒቨርሲቲዎች ፦
1.  አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
2.  አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ
3.  አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ
4.  ሲቪል ሰርቪርስ ዩኒቨርሲቲ
5.  ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ
6.  ጅማ ዩኒቨርሲቲ
7.  ኮተቤ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ናቸው።

ተማሪዎች የሞሉትን ምርጫ በ student.ethernet.edu.et በኩል ማረጋገጥ የሚችሉ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል፡፡

Via @tikvahuniversity
1.05K😭157🙏90😡75😱34🥰33🕊31👏25💔25🤔14😢13
🔵⚽️ በዲኤስቲቪ እናያለን ገና!!

ሁሉንም የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ጨምሮ ከ125 በላይ ምርጥ የመዝናኛ ቻናሎችን
👉 በስልክዎ ዳታ አልያም
👉 በቤትዎ ፋይበር በስማርት ቲቪዎ
እንዳሻዎ መመልከት ይችላሉ!

💁‍♂️ DStv Stream ሜዳ ፓኬጅ ከ10GB ጋር በ1240 ብር ወርኅዊ ክፍያ ብቻ!

ዛሬውኑ ይግዙ፤ ዘና ብለው በአማራጭ ይዝናኑ!!

🔗 ለተጨማሪ መረጃ: https://bit.ly/DSTV_Bundle

📍 የአገልግሎት ማዕከሎቻችንን ይጎብኙ!


#DSTV
#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
215😡10🙏8🥰6😭6🤔2
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray የትግራይ ኃይል አባላት ሰልፈኞች ለአራተኛ ቀን ዛሬ የመኪና መንገድ ዘግተዋል። ዛሬ ጥቅምት 6/2018 ዓ.ም የትግራይ ምስራቃዊ ዞን ዋና ከተማ ወደ ሆነችው የዓዲግራት ከተማ የሚያስገቡና የሚያስወጡ ሶስት ዋና መንገዶች ተዘግተዋል። ትናንት ጥቅምት 5/2018 ዓ.ም ከዓድዋ ወደ ዓዲግራት ሲጓዝ ሴሮ በተባለ ቦታ መንገድ ተዘግቶበት ከሰዓት በኃላ ተከፎቶ ወደ ከተማዋ የተጓዘው የቲክቫህ ኢትዮጵያ…
#Tigray

የትግራይ ኃይል አባላት ሰልፈኞች ዛሬም ለአምስተኛ ቀን የመኪና መንገድ ዘግተው ውለዋል።

ትናንት ጥቅምት 6/2018 ዓ.ም ወደ ዓዳግራት ከተማ የሚያስገቡና የሚያስወጡ በሶስት አቅጣጫ የተዘጉ መንገዶ ከምሽቱ 12:00 ሰዓት ተከፍተዋል።

ዛሬ ከእንዳስላሰ-ሽረ ፣ አክሱም ፣ ዓድዋ ፣ ተምቤንና ሌሎች አከባቢዎች ወደ መቐለ የሚያስገቡ ዋና የመኪና መንገድ በትግራይ ደቡባዊ ምስራቅ ዞን ሃገረ ሰላም ከተማ ነው የተዘጋው።

ከጥዋቱ 1:00 መንገዱ የዘጉ የትግራይ ኃይል አባላት ፦
- " የተሰውት ቤተሰብ አባላት ይደገፉ ! "
- " የቆሰሉት ይታከሙ ! "
- " የሰራዊት ድምፅ ይሰማ ! "
- " የሰራዊር መብት የማያከብር መሪ ይውረድ ! "
- " መሪ ፍረድ ወይ ውረድ ! "
- " የደመወዝ ጥያቄያችን ይመለስ ! "
- " የቤት መስሪያ መሬት ይሰጠን ! "

የሚሉና ሌሎች መፈክሮች አሰምተዋል።

እሁድ ጥቅምት 3/2018 ዓ.ም የጀመረው የትግራይ ኃይል አባላት ሰልፍና ተቃውሞ ያዳመጠው የክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር የሰራዊቱ ጥያቄ ለመመለስ ያስችላል ያለው መመሪያ አውጥቻሎህ ማለቱ ይታወሳል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
598🕊55👏28😭16🤔12🙏11😡9💔6😢5😱4🥰3
2025/10/20 15:53:10
Back to Top
HTML Embed Code: