Telegram Web Link
#ኢትዮኢስታንቡል

ኢትዮ ኢስታንቡል ጠቅላላ ሆስፒታል በዓለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂ ከሆነውና በህንድ አገር ከሚገኘው አፖሎ ሆስፒታል ጋር በትብብር መሥራት የሚያስችለውን ስምምነት ጥቅምት 5 ቀን 2018 ዓ.ም ተፈራረመ።

ስምምነቱ ከኢትዮ ኢስታንቡል ሆስፒታል ዓላማዎች አንዱ የሆነውን ወደ ውጪ አገር የሚያስኬዱ ሕመሞችን ሕክምና በአገር ውስጥ መስጠትን መሰረት በማድረግ እንደ ካንሰር ያሉ ከፍተኛ ሕመሞች ያሉባቸውን ሕሙማን ወደ ህንድ አገር መላክ የመሰሉትን ያካተተ ነው።

እንዲሁም ሐኪሞች ከአፖሎ ሆስፒታል እየመጡ በኢትዮ ኢስታንቡል ሆስፒታል ሕክምና መስጠት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ የተደረገና በውጪ አገር ታክመው የሚመጡትን ሕሙማን ቀጣይ የሕክምና ክትትልም በኢትዮ ኢስታንቡል ሆስፒታል ለማድረግ የሚያስችል ዝግጅት መጠናቀቁን የገለፁት የሆስፒታሉ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ብርሃን ተድላ ከአፖሎ ሆስፒታል ጋር በትብብር መስራቱ የቴክኖሎጂ ሽግግር ለማድረግና ሐኪሞች የሥራ ላይ ሥልጠና እና የልምድ ልውውጥ እንዲያገኙ ዕድል እንደሚሰጥም ጨምረው አመልክተዋል።

የአፖሎ ሆስፒታል ተወካዮችም በበኩላቸው
ስምምነቱ የሜዲካል ቱሪዝምን በኢትዮጵያ በሰፊው ለማስተዋወቅ መልካም አጋጣሚን እንደሚፈጥርና በስምምነቱም ደስተኞች መሆናቸውን ተናግረዋል።

ስምምነቱን የፈረሙት በኢትዮ ኢስታንቡል ጠ/ሆስፒታል በኩል ዋና ሥራ አስፈፃሚው አቶ ብርሃን ተድላ ሲሆኑ በአፖሎ ሆስፒታል በኩል ዶ/ር ፕራሳድ ናማኒ የኢንተርናሽናል ቢዝነስ ዴቬሎፕመንት ማኔጀር እና ዶ/ር አጂሽ ራጅ ከፍተኛ የቀዶ ጥገና ሐኪም ናቸው።

@TikvahethMagazine
44👍8
እንግሊዝ ወደ ሀገሯ ለሥራ የሚገቡ የሌላ ሀገር ዜጎች የእንግሊዘኛ ቋንቋ መስፈርቶችን ከፍ አደረገች።

እንግሊዝ ከአዲሱ የፈረንጆቹ 2026 ዓመት ጀምሮ ለአብዛኛዎቹ የስራ ቪዛዎች ብቁ ለመሆን ስደተኞች B2 ደረጃ የእንግሊዘኛ ቋንቋ ክህሎት ወይም የተሻለ የመካከለኛ ደረጃ (Upper Intermediate ) ጋር ሊኖራቸው እንደሚገባ አስታውቃለች።

አዲሱ ህግ አሁን ያለውን የB1 ደረጃ የሚተካ ሲሆን ይህም ማለት አመልካቾች በመናገር፣ በማንበብ፣ በመፃፍ እና በማዳመጥ ጠንካራ የእንግሊዝኛ ችሎታዎችን ማሳየት አለባቸው።

ለውጡ በዋናነት በሰለጠነ ሰራተኛ እና በሌሎች የፕሮፌሽናል ቪዛ አማራጮች የሚያመለክቱ ሰዎችን ይመለከታል።

በዚህ መሰረት ከላይ የተጠቀሱትን ቪዛዎች ለማግኘት እንደ IELTS ባሉ ፈተናዎች 5.5–6.5 ማምጣት ይጠበቃል።

በመላው አፍሪካ ፖሊሲው ወደ እንግሊዝ የሚሰደዱ ሰራተኞችን ቁጥር እንደሚቀንስ እና ሀገራት የእንግሊዘኛ ትምህርት እና ስልጠናን እንዲያሻሽሉ ያበረታታል ተብሎ ታምኖበታል።

@TikvahethMagazine
68👎26👍6🤔2🕊2
የኢትዮጵያ_የውጭ_ሀገር_ሥራ_ስምሪት_አፈጻጸምን_ለመደንገግ_የወጣ_መመሪያ.pdf
434.7 KB
የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ማስፈፀሚያ ረቂቅ መመሪያ ላይ አስተያየት ተጠየቀ

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት አዋጅ ቁጥር 1389/2017 አንቀፅ 84(2) መሠረት የማስፈፀሚያ መመሪያ የማውጣት ሥልጣን ተሰጥቶታል።

በዚህ መሠረት የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪቱን ማስተግበሪያ ረቂቅ መመሪያ እያዘጋጀ መሆኑን ገልጿል።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ማንኛውም ዜጋ ወይም ድርጅት በተዘጋጀው ረቂቅ መመሪያ ላይ ይህ ማስታወቂያ ከተወጣ ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት አስተያየት እንዲቀርብ ጠይቋል።

ረቂቅ መመሪያውን ከላይ ተያይዟል።

አስተያየት ለመስጠትም የሚከተሉትን አድራሻዎች መጠቀም ይችላሉ ብሏል።
- [email protected] ወይም
- [email protected]

@TikvahethMagazine
40🤔4👎1
#WorldAnesthesiaDay

ዛሬ ለመጀመርያ ጊዜ ኢተር (Ether) የተሰኘውን የአንስቴዢያ መድሀኒት በመጠቀም ከህመም ነፃ የሆነ ቀዶ ጥገና ማድረግ የተጀመረበትን ቀን በማስታወስ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ179ኛ ጊዜ የአንስቴዢያ ቀን ይከበራል።

በሐረር ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ያሉ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦች ቀኑን በተለያዩ ዝግጅቶች አክብረው መዋላቸውን በላኩልን መረጃ ገልጸውልናል።

በዕለቱ መምህራን፣ የአንስቴዢያ ተማሪዎች እና በሌላ ሙያ የሚገኙ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

በዝግጅቱም የአንስቴዢያ ተማሪዎች ደም በመለገስ፣ Live Demo በሌላ ሙያ ለሚገኙ ተማሪዎች በማሳየት ፤ እንዲሁም በኮሌጁ CPD center Symposium በማቅረብ ዕለቱን በደማቅ ሁኔታ አሳልፈዋል፡፡

የሲምፖዚየም አቅራቢ የነበሩት አቶ አበባው ደምሴ   “Anesthetist – The Silent Guardian of Life” በሚል ርዕስ ለተማሪዎች ጥሩ ገለፃ ያደረጉ ሲሆን ከተማሪዎች ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራርያ ሰጥተውበታል፡፡

Happy World Anesthesia Day! 💉💙

#TikvahFamily 👋

@TikvahethMagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
110🔥6👍1
አዲሷን ጀንበር
በአዲሷ ካዛንቺስ መንደር ‼️

የሚመኙት  ያማረ  ነገዎ
እውን  ይሆን ዘንድ‼️

እጅግ ውብ ዕይታ ያላቸው ቤቶች

ከ 1 መኝታ እስከ ባለ 4 መኝታ
👉ባለ አንድ መኝታ 45, 55 ,60 ካ.ሜ
👉ባለ ሁለት መኝታ  80,ካ.ሜ
👉ባለ ሶስት መኝታ  95,105,115 ካ.ሜ
👉ባለ አራት መኝታ  140  ,160 ካ.ሜ

ቅድመ ክፍያ 10%

❇️  በ 24 ወራት የሚረከቡት ቤት💁

       📍በግቢው ውስጥ

    ➾ ት/ቤት እና የጤና ማዕከል
    ➾ እግር ኳስና ቅርጫት ኳስ መጫወቻ
    ➾መዋኛ ገንዳ
    ➾የሳይክል እና የእግር ሽርሽር ስፍራዎች
    ➾ሰፊ የመኪና መቆሚያ ከ24/7 ጥበቃ ጋር
    ➾የመኪና ቻርጀር ስፍራዎች

SHARE" @tegegnemelak
SHARE" @tegegne9752
Contact us:@tegegne123
    📞09 44 85 67 35
         09 67 76 97 52
17👎3
#Coffee

ኢትዮጵያ በ2018 በጀት ሦስት ወራት ዓመት መላክ ካቀደችው ቡና መጠን 25 በመቶ ቢቀንስም በገቢ ደረጃ ግን 23 በመቶ ጭማሪ ማስመውገብ መቻሉን የኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ባለሥልጣን አስታውቋል።

° መላክ የታቀደው - 151,969.41 ቶን ቡና

° የተላከው - 113,542 ቶን ቡና


° ለማግኘት የታቀደው ገቢ  - 622.5 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር

° የተገኘው ገቢ - 762.75 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር


ባለፉት ሦስት ወራት የኢትዮጵያ ቡና በብዛት ወዴት ተላከ ?

#ጀርመን

- በመጠን 20,793.14 ቶን (18% ድርሻ )

- በገቢ 138.18 ሚልዮን የአሜሪካን ዶላር (18% ድርሻ)፤

#ሳዉድ_አረቢያ

- በመጠን 16,088.45 ቶን (14% ድርሻ)

- በገቢ 102.18 ሚልዮን የአሜሪካን ዶላር (13% ድርሻ )

#ቤልጅዬም

- በመጠን 13,910.92 ቶን (12% ድርሻ)

- በገቢ 93.45 ሚልዮን የአሜሪካን ዶላር (12% ድርሻ)

@TikvahethMagazine
42🔥3👎2🤔1
#Update : የባንኩ ሴክተር ለውጭ ባንኮች ክፍት እንደሆነ ብሔራዊ ባንክ ካስታወቀ በኋላ እስካሁን ሁለት የኬንያ ባንኮች ዘርፉን ለመቀላቀል በሂደት ላይ እንደሚገኙ ተነግሯል።

ባንኮቹ ወደ ሀገር ውስጥ ሲገቡ በመመሪያው መሠረት ቅርንጫፎችን ወይም ወኪል ቢሮዎችን መክፈት ወይም በሀገር ውስጥ ባሉ ባንኮች የ40 በመቶ አክሲዮን ድረስ ማግኘት ይችላሉ።

ወደ ኢትዮጵያ ገቢያ ሊገቡ እንደሆነ ከተገለጸላቸው መካከል የኬንያው ብሔራዊ ባንክ አንዱ ሲሆን በስም ካልተጠቀሰ አንድ የኢትዮጵያ ባንክ የ40 በመቶ ድርሻ ሊገዛ ይችላል ተብሏል።

ሌላው የኬንያው ኢኪውቲ ባንክ ሲሆን በኢትዮጵያ የባንክ ዘርፍ ለመሰማራት በቅርቡ ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ጋር ተወያይቶ ነበር።

@TikvahethMagazine
53👍12🤝5🤬4🕊2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ቴሌግራም

ቴሌግራም አዲስ ባወጣው ማዘመኛ ላይ በ Voice chat ጊዜ ወይም በቪዲዮ ጥሪዎች ጊዜ ተሳታፊዎች የጹሑፍ መልዕክት መላክ እንዲችሉ ገልጿል።

@TikvahethMagazine
68👍29🤣3
ሙሉ ኮከብ ሪልሰቴት  በሲኤምሲ የሚገኝ ከ ስኩል ኦፍ ቱሞሮ ዝቅ ብሎ የሚገኝ እጅግ ዘመናዊ ና ጥራታቸውን የጠበቁ አፓርትመንት ቤቶች ይዘንሎት ቀርበናል
👉ግንባታቸው 100% የተጠናቀቁ  ቅንጡ አፓርታማ ቤቶች በተመጣጣኝ ዋጋ ከባለ 1 መኝታ እስከ ባለ 4 መኝታ የተለያዬ የካሬ አማራጭ የያዘ
👉60% የባንክ ብድር አማራጭ የተዘጋጀላቸው
👉ሙሉ በሙሉ የተጠናቀቁ እና በግንባታ ላይ ያሉ።
      
     🔸2 ሊፍት
      🔸️የከርሰ ምድር ውሃ
      🔸️backup ጀነኔተር
    🔸️የ ልጆች መጫወቻ እና አረንጓዴ ስፍራ የተሟላለት 3000 ካሬ ላይ ያረፈ ቅንጡ ኮምፓውንድ አፓርትመንት በኢትዮጵያ ብር ለሽያጭ አቅረበናል።

ባለ 1 መኝታ 82 ካሬ
ባለ 2 መኝታ 96,99, እና 105ካሬ
ባለ 3 መኝታ 120,124 እና 127 ካሬ
ባለ 4 መኝታ 181 ካሬ

60%ባንክ ብድር የተመቻቸላቸው ዲጅታል የተናጥል ካርታ የተዘጋጀላቸው

📣በ መሀል CMC መኖሪያ ቤቶን ይግዙ።

ለበለጠ መረጃ
💁‍♂📞 +2519-21-85-72-39
            +2519-48-74-31-71
17🤣2😢1
በሜሪጆይ ኢትዮጵያ በሐዋሳ ከተማ የተገነባው የኩላሊት እጥበት ማዕከል ተመረቀ።

ሜሪጆይ ኢትዮጵያ  የኩላሊት እጥበት ማዕከል ሐዋሳ ቅርንጫፍ ከ29 ሚሊዬን ብር በላይ በፈጀ ወጪ ተገንብቶ ተመርቋል።

የክልሉ መንግስት 10 ሚሊዮን ብር እና አንድ አንቡላንስ መኪና ድጋፍ ሲያደርግ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር በበኩሉ የ5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጋቸውን ገልጸዋል።

ማዕከሉ 13 የእጥበት ማሽን ያለው ሲሆን፤ በአንድ ጊዜ 12 ህመምተኞችን ያስተናግዳል ሲባል 10ሺህ ዙር የኩላሊት እጥበት ማከናወን እንደሚችልም ተጠቁሟል።

@TikvahethMagazine
75👍10👎2
#TanaForum

በአፍሪካ ፀጥታና ደህንነት ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደረገው 11ኛው ጣና ፎረም በባህር ዳር እና አዲስ አበባ ከተሞች እንደሚካሄድ ተገለጸ።

የፎረሙ የመጀመሪ ምዕራፍ በባህር ዳር ጥቅምት 14  እንደሚካድ በመግለጽ፤ በፎረሙ በአፍሪካ ቀንድን የሚከታተሉ ልዩ መልዕክተኞች እንደሚወያዩ ገልጸዋል።

የፎረሙ ሁለተኛ ምዕራፍ ጥቅምት 15 እና 16 በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ ጠቁመዋል። (EPA)

@TikvahethMagazine
32🤣16👎4👍1🕊1
BYD ከ115,000 በላይ የኤሌክትሪክ መኪናዎች ላይ ማሻሻያ እንደሚያስፈልጋቸው ገለጸ።

የቻይናው ግዙፉ የኤሌትሪክ መኪኖች አምራች ቢ.ዋይ.ዲ በዲዛይንና በባትሪ ተከላ ችግር ምክንያት ከ115,000 በላይ መኪኖችን ለማሻሻያ ወደ ማምረቻ እንዲመለሱ ጥሪ አቅርቧል።

ይህ ችግር የተገኘባቸው ከ2015 እስከ 2017 የተመረቱ ከ44 ሺ በላይ የታንግ እና ከ2021 እስከ 2022 የተመረቱ ከ71ሺ በላይ የዩዋን ፕሮ ሞዴሎች ላይ መሆኑ ተገልጿል።

በዩዋን ፕሮ ሞዴሎች ላይ ያጋጠመው ችግር ባትሪውን ከውኃ እንዲሁም ሌሎች ቆሻሻዎች ለመሸፈን የተገጠመው መከላከያ (Sealing Gasket) በአግባቡ አለመጥበቁ መሆኑ ተገልጿል።

ይህም ውኃ ወይም ሌሎች ነገሮች ወደ ኤሌክትሪካል ሲስተሙ እንዲገቡ እና ተግባሩን ሊረብሹ ይችላሉ።

ተቋሙ በተደጋጋሚ በምርቶቹ ላይ የማሻሻያ ጥሪ ቢያቀርብም ይህኛው ከእስካሁኖቹ በመጠን ከፍ ያለ ነው ተብሏል።

ኩባንያው ፈጠረ ያለውን ችግሮች ከክፍያ ነፃ እንደሚያስተካክል ተናግሯል።

ተጨማሪ ማንበብ ለምትፈልጉ ምንጮች ከላይ ተያይዘዋል።

@TikvahethMagazine
62🤣45👍5🤔5😢5🔥4👎2
2025/10/22 11:21:47
Back to Top
HTML Embed Code: