#ማሳሰቢያ
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የገናሌ ዳዋ 3ኛ የኃይል ማመንጫ ግድብ ውሃ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱን በመግለጽ የግድቡን ደህንነት ለማስጠበቅ ሲባል ውሃውን ከጥቅምት 18 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ ላልተወሰኑ ቀናት እንደሚለቀቅ አስታውቋል።
በዚህም ምክንያት በሊበን እና መዳወላቡ ወረዳዎች ኮባዲ፣ ሚኤሳ፣ መዳ፣ ኦዳ ቦጂ፣ እና ቢድሬ ቀበሌዎች እና በአካባቢያቸው ያሉ ነዋሪዎች የሚለቀቀው ደራሽ ውሃ በሰውም ሆነ በእንሰሳት ላይ ጉዳት እንዳያደርስ ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስቧል።
@TikvahethMagazine

❤33👍15👎2🤬2🙏2
ዓለም አቀፉ የህግ ተቋም ዴንቶንስ በአዲስ አበባ ቢሮውን ከፍቷል።
ተቋሙ ባለፈው አመት በኢትዮጵያ ቢሮ ለመክፈት ፍላጎት እንዳለው ካሳወቀ በኋላ ከታምራት አሰፋ ሊበን የህግ ቢሮ ጋር በመሆን ቢሮውን በአዲስ አበባ ከፍቷል።
ዴንቶንስ በአፍሪካ በ16 ሃገራት ከ280 በላይ ጠበቆች በስሩ ያሉት ሲሆን የአዲስ አበባ ቢሮውም በአፍሪካ 24ኛ ቢሮው ሆኗል።
ተቋሙ የኢትዮጵያ ቢሮውን የከፈተው በሃገሪቱ ያሉ የታዳሽ ኃይል እና የመሰረተ ልማት ኢንሼቲቮች የተነሳ ሲሆን የሰነደ መዋዕል ገበያ መጀመርም ምክንያት መሆኑን ገልጿል።
ምስረታውን እ.ኤ.አ በ2013 ያደረገውና መቀመጫውን በአሜሪካ ያደረገው የህግ ተቋሙ 5931 የህግ ሰዎችን በስሩ በማቀፍ በአሜሪካ ግዙፉ ነው።
ትኩረቱን በፋይናንስ ላይ ያደረገው ተቋሙ ድርጅቶችን ለማዋህድ እና ለማቀላቀል የህግ ድጋፍም ያደርጋል።
ተቋሙ በትራንስፖርት ፕሮጀክት፣ በኃይል፣ በማዕድን፣ በሪል ስቴት፣ በቴሌኮሚኒኬሽን እና ሚዲያ፣ በክሪፕቶከረንሲ እንደዚሁም በአየር ትራንስፖርት ዘርፎች የሚሰራም ነው።
በ2024 ከ2.7 ቢሊየን ዶላር በላይ ገቢ ያገኘው ተቋሙ በ2025 የግሎባል 200 ሰርቬይም በገቢ ደረጃ ከዓለም ካሉ የህግ ቢሮዎች 18ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
ተቋሙ ከታምራት አሰፋ ሊበን ጋር የከፈተው ቢሮም ዴንቶንስ ታምራት የሚል ስም ሲሰጠው በቦሌ መድኃኔዓለም ሮቤሎ ፕላዛ እንደሚገኝም ጠቁሟል።
መረጃው ከAfrican Law Gropu, Law.com እና ከተቋሙ ድህረገጽ የተገኘ ነው።

❤70👍16🤔4🤣2👎1
ሙሉ ኮከብ ሪልሰቴት በሲኤምሲ የሚገኝ ከ ስኩል ኦፍ ቱሞሮ ዝቅ ብሎ የሚገኝ እጅግ ዘመናዊ ና ጥራታቸውን የጠበቁ አፓርትመንት ቤቶች ይዘንሎት ቀርበናል
👉ግንባታቸው 100% የተጠናቀቁ ቅንጡ አፓርታማ ቤቶች በተመጣጣኝ ዋጋ ከባለ 1 መኝታ እስከ ባለ 4 መኝታ የተለያዬ የካሬ አማራጭ የያዘ
👉60% የባንክ ብድር አማራጭ የተዘጋጀላቸው
👉ሙሉ በሙሉ የተጠናቀቁ እና በግንባታ ላይ ያሉ።
🔸2 ሊፍት
🔸️የከርሰ ምድር ውሃ
🔸️backup ጀነኔተር
🔸️የ ልጆች መጫወቻ እና አረንጓዴ ስፍራ የተሟላለት 3000 ካሬ ላይ ያረፈ ቅንጡ ኮምፓውንድ አፓርትመንት በኢትዮጵያ ብር ለሽያጭ አቅረበናል።
ባለ 1 መኝታ 82 ካሬ
ባለ 2 መኝታ 96,99, እና 105ካሬ
ባለ 3 መኝታ 120,124 እና 127 ካሬ
ባለ 4 መኝታ 181 ካሬ
60%ባንክ ብድር የተመቻቸላቸው ዲጅታል የተናጥል ካርታ የተዘጋጀላቸው
📣በ መሀል CMC መኖሪያ ቤቶን ይግዙ።
ለበለጠ መረጃ
💁♂📞 +2519-21-85-72-39
+2519-48-74-31-71

❤13👎1
ቢቢሲ ያጋለጠው የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ፕሮፓጋንዳ በአፍሪካ
በአፍሪካ ስለ ተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በጎ ገፅታን ለማስረፅ እንደዚሁም የሱዳን የፈጥኖ ደራሽ ኃይልን የሚደግፉ ሀሳቦችን የሚያንፀባርቁ የበይነ መረብ ኔትዎርኮች መኖራቸውም በቢቢሲ ምርመራ ይፋ ሆኗል።
እነዚህ ኔትዎርኮች ከ100 በላይ ሃሰተኛ አካውንቶችን እንደ ኤክስ፣ ፌስቡክ እና ቲክቶክ ባሉ ማህበራዊ ሚዲያዎች የከፈቱ ሲሆን የሶማሊያ ሴቶችን እና ተፅዕኖ ፈጣሪዎችን በማስመሰል በቀጣናው ያሉ ተከታታዮች ስለ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በጎ ገፅታ እንዲኖር ይሰራሉ።
በእነዚህ አካውንቶች ከጥር 2023- መስከረም 2025 ድረስ ከ47,000 በላይ ልጥፎች ተጋርተዋል እንደዚሁም ከ215 ሚሊየን በላይ ተጠቃሚዎች ጋር ልጥፎቹ ደርሰዋል።
ኔትዎርኮቹ እውነተኛ እና በሰው ሰራሽ አስተውህሎት የተፈጠሩ ምስሎችን በመጠቀም የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ሶማሊያን የምታግዝ በጎ ኃይል ነች ሲሉ የሱዳን ጦርን በማጣጣል የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉን ያሞግሳሉ።
በርካታ የሶማሊ ሴቶችም ያለፈቃዳቸው ምስላቸው አገልግሎት ላይ እንደዋለ ለቢቢሲ አረጋግጠው እነሱን አስመስለው የሰሩትን ግን ምንም ሊያደርጓቸው እንደማይችሉ ተናግረዋል።
በእነዚህ ሃሰተኛ አካውንቶች የተለጠፉ ልጥፎች በአል ኦቤይድ ከተማ የሱዳን ጦር የጅምላ ግድያ መፈፀሙን ቢገልፁም እንደዚህ አይነት ጥቃት በቦታው ስለመፈፀሙ አልተረጋገጠም።
ባለሙያዎች እነዚህ አካውንቶች የተባበሩት አረብ ኤምሬቶችን የውጪ ፖሊሲ በአፍሪካ ለማስረፅ የሚሰሩ የፕሮፓጋንዳ አካላት ናቸው ሲሉ የሚሰሩትም የፖለቲካ ውል በፈፀሙ ድርጅቶች ስር ነው።
ሜታ እና ቲክቶክ ከዚህ ጋር በተያያዘ ሰዎችን የሚያስመስሉ በርካታ ሃሰተኛ አካውንቶችን ከመተግበሪያቸው ላይ ማጥፋታቸውን ገልፀዋል።

❤38👎3😢2🤯1
ሁለት ሶስተኛ የሚሆኑት የደቡብ ሱዳን ህፃናት ለህፃናት የጉልበት ብዝበዛ ይዳረጋሉ ተብሏል።
በደቡብ ሱዳን በተደረገ የዳሰሳ ጥናት ከ5-17 ዓመት ካሉ ህፃናት 64 በመቶዎቹ ለጉልበት ብዝበዛ፣ ለግጭትና የወሲባዊ ጥቃት ይዳረጋሉ።
በአንዳንድ አካባቢዎች ከ10 ህፃናት ዘጠኙ ትምህርታቸውን በመከታተል ፈንታ በወርቅ ማውጣት እና በእንስሳት እርባታ ይሳተፋሉ ተብሏል።
በሃገሪቱ ያለው ግጭት እና በህፃንነት ወደ ጋብቻ መግባት ህፃናቱ ለጉልበት ብዝበዛ እንዲዳረጉ አድርጓቸዋልም ተብሏል።
በዳሰሳ ጥናቱ ከተሳተፉት መካከል 10 በመቶዎቹ ከታጣቂ ቡድኖች ጋር እንደሚሰሩ ሲገለፅ ወንዶች ከታጣቂዎች ጋር የመስራት ሴቶች ደግሞ የወሲብ ብዝበዛ እንደሚዳረጉ ተገልጿል።
በምስራቅ አፍሪካ የህፃናት ጉልበት ብዝበዛ ምጣኔ 30 በመቶ ነው ሲባል የደቡብ ሱዳን ከቀጣናው በእጥፍ የበለጠ ነው።
እንደ ዩኒሴፍ ዘገባ በአለም አቀፍ ደረጃ በ2024 ከ138 ሚሊየን በላይ ህፃናት ለጉልበት ብዝበዛ ሲዳረጉ አሳሳቢ ጉዳይም ሆኖ ቀጥሏል።
መረጃው የአልጀዚራ ነው።

😢15❤8
#BusinessTips
ቢዝነስ ማስተዳደር ፈተና እየሆነ ነው። እናም ከወትሮው በተለየ መንገድ አስብበት። የቻሌንጅ ዘመን ነው።
የቢዝነስ ዓላማ የደንበኞችን ችግር በመፍታት ገቢ እና ትርፍ ማግኘት ነው። ለደንበኞችህ ጥቅም ከሌለህ ገቢ አታገኝም። ይህ የቢዝነስ ሀ ሁ ነው።
የቢዝነስ አቡጊዳ ደግሞ ቢዝነስህን ትርፋማ አድርጎ መምራት ነው። የሽያጭ ገቢ ማግኘት ብቻውን ትርፋማ አያደርግም። ገቢህ ለትርፍ የሚያበቃ ገቢ ነው ወይ? ካልሆነ ልታስብበት የተገባ ነው። የግርድፍ ትርፍ መጠንህ ከ30% ካነሰ ልታስብበት የተገባ ነው።
በዚህ ዘመን ብክነቶችህን ልትቀንስና ብዙ ተጠቃሚዎች ጋ ልትደርስ አስፈላጊ ነው። የተዝናናው የቢዝነስ አሠራር ዘመን አልፏል።
በዚህ ዘመን ትርፋማ ሆነህ እንዴት ትኖራለህ?
#ፍተሻ: የውስጥ አሠራርህን ፈትሽ።
የውስጥ አሠራርህ እንዴት ነው? ብክነት አለው? የብክነቱ ምንጮች ምንድን ናቸው? ስንት አስገብተህ ስንት ታወጣለህ? ከአንድ ኩንታል ዱቄት ስንት ዳቦ ይወጣል? ከአንድ ኩንታል ጤፍ ስንት እንጀራ ይወጣል? ተወዳዳሪህ 900 እንጀራ እያወጣ አንተ 600 ካወጣህ ተበልተሃል! የውስጥ ችግርህን ፈትሽ። ንቃ!
#አስተካክል: ክፍተትህን አስተካክል።
ጉድለትና ክፍተትህን አስተካክል። ብክነትን ማወቅ ብቻ በቂ አይደለም። ክፍተትህን እንዴት እንደምትዘጋው እወቅ። ክፍተትን መዝጋት ቀላል አይደለም። ችግር ችግሩን በፈጠረው አዕምሮ አይፈታም። ሌላ ፈቺ ይፈልጋል። እርዳታ ጠይቅ።
አንዳንዱ ማስተካከያ ችግሩ ተፈትቶ ሲታይ ቀላል ይመስላል። ግን ቀላል ያደረገው የብዙ ዘመን ልምድ ይሆናልና ለልፋት ሳይሆን ለልምድ ዋጋ ስጥ። አንዳንዱ ማስተካከያ ደግሞ ጊዜ ይፈልጋልና መጠበቅን ተለማመድ። አንተ ስለቸኮልህ በ6 ወር ልጅ አይወለድምና አትቸኩል።
#ተባበር: አብረውህ ከሚሠሩት ጋር ተባበር።
አንተ የያዝከው ሸክም ብዙ መሆኑን አስተውል። The more you invest, the less you become free. ብዙ ኢንቨስት ባደረግህ ቁጥር ነጻነትህ ይቀንሳል። ከሸቀጥ ነጋዴው ይልቅ የባለፋብሪካው ነጻነት ያነሰ ነው።
ሌሎቹ ግድ ባይሰጣቸው አንተ ግን ግድ ሊሰጥህና ሌሎችን ልታግባባ ያስፈልግሃል። ብዙ ኢንቨስት አድርገህ ነጻነትህ እንዲጨምር ከፈለግህ ከሌሎች ጋር ተባበር። ከሠራተኞች፣ ከማኔጀሮች፣ ከአማካሪዎች፣ ከተቆጣጣሪዎች ጋር ተባብሮ ማሠራትን እወቅበት።
#ስርዓት: ሲስተምና መዋቅር ዘርጋ።
የምትፈልገው ቦታ ለመድረስ ግርግርና ተፍ ተፍ ማለት ብቻ ሳይሆን ሲስተምና መዋቅር ያስፈልግሃል። ሲስተም ከሌለህ የዛሬ ስኬት ነገ አይደገምም። እስኪ የሽያጭ ገቢህን ተመልከት። በየወሩ፣ በየሩብ ዓመቱ እያደገ ነው? ካልሆነ ችግር እየመጣ ነው። በጊዜ ንቃ!
#ኢንቨስት: ለአዳዲስ ሀሳብና አሠራሮች ዋጋ ክፈል።
ዘመኑ አዳዲስ አስተሳሰብ የሚፈልቅበትና አዳዲስ አሠራሮች የሚዘረጉበት ነው። AI እየናኘ ነው። ሮቦቶች እየመጡ ነው። አንተ ግን ያልፋል እያልክ በጥበቃ ላይ ነህ። አትሞኝ ንቃ! የድሮው እያለፈና እየተረሳ አዲሱ እየገነነ ነው።
የድሮው ስልክ ላይመለስ ሄዷል። ሞባይል ደግሞ አዲስ ደረጃ ላይ ደርሷል። እናም ለአዳዲስ ሀሳቦችና አሠራሮች ጊዜህን፣ ትኩረትህንና ገንዘብህን ክፈል፣ ያውም በደንብ ክፈል። ከፍለህም ባገኘህ።
#ለውጥ: ከለውጥ ጋር ተራመድ።
የባንክ አሠራር ላይ ለውጥ አለ። ታክስ አሰባሰብ ላይ ለውጥ አለ። ውድድር ላይ ለውጥ አለ። የአስተዳደር ወጪ ላይ ለውጥ አለ። የደንበኞች አስተሳሰብ ላይ ለውጥ አለ። አንተስ ጋ ለውጥ አለ? ከሌለ Watch Out! ዙሪያህ ሲለወጥ አንተ ከቆምህ የአደጋ ቀለበት ውስጥ ነህ።
#ፍጠን: አትቁም! ጊዜ አታባክን።
አማራጮችን ፈትሽ። ተነጋገር፣ ተመካከር፣ ወስን። አንተ ካልወሰንክ ሌሎች ይወስኑብሃል። ፍጠን!
#ማስታወሻ: ይህ ጹሑፍ Get Toughe Zer ፌስቡክ ገጽ የተወሰደ ሲሆን ለአቀራረብ እና ለሚዲያ እንዲመች ከዋናው ጹሑፍ መጠነኛ ማሻሻያዎች ተደርጎበታል።

1❤58👍14
አሊኮ ዳንጎቴ 30 ቢሊየን ዶላር ሃብት ላይ የደረሰ የመጀመሪያው አፍሪካዊ ሆኗል።
በጥቅምት 2025 የዳንጎቴ ሃብት ከባለፈው ዓመት በ2.16 ቢሊየን ዶላር በመጨመር 30 ቢሊየን መድረሱ ሲነገር እዚህ ቁጥር ላይ የደረሰ የመጀመሪያው አፍሪካዊም ሆኗል።
ዳንጎቴ የነዳጅ ማጣሪያውን በናይጄሪያ ከገነባ በኋላ በ2024 ሃብቱ ከ13 ቢሊየን ዶላር ወደ 27 ቢሊየን ዶላር ጨምሯል።
ዳንጎቴ በአፍሪካ አሁንም በበርካታ ዘርፎቾ እየሰራ ሲሆን በኢትዮጵያም በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች እየሰራ መሆኑ ይታወቃል።
መረጃው የቢዝነስ ኢንሳይደር አፍሪካ ነው።

❤97👏30😢3🤔2👍1