Telegram Web Link
እንኳን አደረሳችሁ!

የ14 ዓመት የልፋት፣ የመስዋዕትነት እና የጽናት ምልክት፤ የማሰብ፣ የመጀመር እና የመጨረስ የተሰናሰለ የጋራ የድል ውጤት፤ ወድቆ መነሳት፣ ጨክኖ መስራት ሞቶ ማስቀጠል፣ ሳይታክቱ መሟገት ያመነጨው ኃይል፤ የእያንዳንዱ ዜጋ የልብ ትርታ፣ ቁጭት፣ እንባና ጸሎት ያልተለየው የኢትዮጵያዊ የጋራ ስኬት የታላቁ ህዳሴ ግድብ!

እንኳን ለዚህ ቀን አደረሳችሁ!

💬 መልዕክቶቻችሁንና ኃሳባችሁን በአስተያየት መስጫው ላይ አጋሩን

@TikvahethMagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
301👏29🕊17🙏12👍9🤬1
የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሃሰን ሼህ መሐሙድ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ምርቃት ላይ ተገኝተዋል።

ከግብፅ ጋር ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ባላቸው ቅርበት በግድቡ ምርቃት ላይ የመገኘት ዕድላቸው ዝቅተኛ ነው የተባሉት ሃሰን ሼህ መሐሙድ በግድቡ ምርቃት ላይ ተገኝተዋል።

በተጨማሪ ትናንት ወደ አዲስ አባ እንደሚሄዱ የገለፁት የደቡብ ሱዳኑ ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪርም በምርቃቱ ተገኝተዋል።

@TikvahethMagazine
114🕊12👏8🔥4
#Ethiopia🇪🇹
#GERD

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ጳጉሜ 4 /2017 ዓ.ም በይፋ ተመርቋል።

@TikvahethMagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
143💯16🔥13👍9👎6
በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ምርቃት ወቅት የክብር ኒሻን ሽልማት ለእነማን ተሰጠ?

1ኛ) ኢንጂነር ኤፍሬም ወልደኪዳን - ከህዳር 24/2004 ጀምሮ እስከ ጥር 14/2017 ድረስ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ምክትል ስራ አስኪያጅ

2ኛ) ኢንጂነር ከማል አህመድ - ከሚያዝያ 2013 ጀምሮ የህዳሴ ግድብ የጣቢያ ኦፕሬሽን ኃላፊ

3ኛ) አቶ በላቸው ካሳ - በምክትል ስራ አስኪያጅ ማዕረግ የፕሮጀክት ሳይት አስተባባሪ

4ኛ) ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ- የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዋና ስራ አስኪያጅ

ፎቶ: EEP

@TikvahethMagazine
106👍21🤔13👎8🕊2😢1
#SouthSudan 🇸🇸
#GERD

ደቡብ ሱዳን ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ኃይል ለማግኘት የሚያስችል ስምምነት መፈራረም እንደምትፈልግ ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ገለፁ።

በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ምርቃት ላይ የተገኙት የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ለኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት እንኳን ደስ አላችሁ ብሏል።

ፕሬዚዳንቱ ግድቡ ፕሮጀክት ብቻ ሳይሆን የመስዋዕትነት፣ የአንድነትና የቆራጥነት ምልክት ነው ብለዋል።

ሳልቫኪር ግድቡ ህዝብ በአንድ ራዕይ ላይ በአንድነት ከቆመ ሃገር ምን መስራት እንደምትችል ያሳየ ነው ብለዋል።

ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ዛሬ ከኢትዮጵያ ባለፈ ለቀጣናችን የኩራት ቀን ነው በማለት ከግድቡ ከሚመነጨው ኃይል ለመጠቀም የሚያስችል ስምምነት ለመፈራረም እንደሚፈልጉ ተናግረዋል።

@TikvahethMagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍10471🤣19
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመጪዎቹ ጥቂት አመታት ስለሚሰሩ ፕሮጀክቶች ምን አሉ ?

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ(ዶ/ር) በታላቁ የህዳሴ ግድብ ላይ ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ በቅርቡ ከ30 ቢሊየን ዶላር በላይ ወጪ የሚጠይቁ ሜጋ ፕሮጀክቶችን እንደምታለማ ገልጸዋል።

በዚህም፦

- በመጪዎቹ ጥቂት ጊዜያት ህዳሴን የሚስተካከል ለሰላማዊ ዓላማ ብቻ የሚውል የኒውኪሊየር ፕላንት ግንባታና በአፍሪካ ግዙፉ የአየር መንገድ ማረፊያ ግንባታ ይጀመራል፤

- የመጀመሪያው የጋዝ ፋብሪካ ከቀናት በኋላ ይመረቃል፤ ከእሱ በ10 እጥፍ የሚበልጥ የጋዝ ፋብሪካ ግንባታ በምርቃቱ ቀን ይጀመረራል፤

- የጋዝ ማውጣት ሂደቱ ከተጀመረ በወር ባነሰ ጊዜ የማጣሪያ ሥራና በቅርቡ የተፈረመው የማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታ ይጀመራል፤

- በመጪዎቹ አምስትና ስድስት ዓመታት 1.5 ሚሊየን ቤቶች ይገነባሉ ሲሉ ተናግረዋል።

@TikvahethMagazine
160🤣53👏47👎9🤷‍♂7👍6
2025/10/25 15:30:45
Back to Top
HTML Embed Code: