Telegram Web Link
#EthiopianAirlines 🇪🇹

የኢትዮጵያ አየር መንገድ "ዴ ሃቪላንድ ካናዳ" ከተባለ ኩባንያ ባለፈው ሰኔ ወር ያዘዛቸውን ሁለት Twin Otter Classic 300-G የተሰኙ አነስተኛ አውሮፕላኖችን ተረክቧል።

እነዚህ አውሮፕላኖች በውኃ ላይ እንዲሁም ለማረፍ አስቸጋሪ በሚሆኑባቸው ገጠራማ ቦታዎች ጭምር ማረፍ ይችላሉ ሲባሉ ስሪታቸውም ከበፊቶቹ ማሻሻያዎች ተደርጎባቸው የቀረቡ ናቸው።

ከህዝብ ማመላለሻነት በተጨማሪ የካርጎ አገልግሎት ለመስጠት እንዲሁም ለአየር አምቡላንስ፣ ኤርፖርት ካሊብሬሽን እና ቻርተር አገልግሎቶችን ለመስጠት የሚያስችል ተለዋዋጭ ጥቅም ያላቸው ናቸው ተብሏል።

Twin Otter Classic 300-G የተሰኙት የካናዳ ምርት የሆኑት አውሮፕላኖች 20 ሰዎችን የመጫን ወይም 1,134 ኪግ ክብደት የመጫን አቅም እንዳላቸው ሲገለጽ አየር ላይ ለ5 ሰዓት የመብረር አቅም ያላቸው ስለመሆናቸው ይገለጻል።

ፎቶ: በኢትዮጵያ የካናዳ ኢምባሲ፤ ዴ ሃቪላንድ ካናዳ

@TikvahethMagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
85👍40👏4🤔3
#GERD

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም (ዶ/ር) የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መመረቁን አስመልክተው የቀድሞ ልጥፋቸውን በማጋራት የእንኳን ደስ አለን መልዕክት አስተላልፈዋል።

በመልዕክታቸውም፦

"ለመላው ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን እንኳን ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ምረቃ በዓል አደረሳችሁ!  የዚህ አስደናቂ ክስተት አካል በመሆኔ ኩራት ይሰማኛል።  የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ፕሮጀክቱን ለመጀመር ባሳዩት ራዕይ እና ድፍረት እናስታውሳቸዋለን፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይም ፕሮጀክቱን ስላጠናቀቁ እናመሰግናለን።"

ቴዎድሮስ አድሃኖም (ዶ/ር)


@TikvahethMagazine
218👍42👏16👎3🔥1
TIKVAH-MAGAZINE
Photo
#Update

የኔፓል ጠቅላይ ሚኒስትር በገዛ ፈቃዳቸው ከስልጣን ለቀዋል።

በኔፓል የማህበራዊ ሚዲያዎችን መዘጋት ተከትሎ አመፅ መነሳቱ የሚታወስ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትር ኦሊ ሻርማ ከኃላፊነታቸው በገዛ ፈቃዳቸው መልቀቃቸውን ገልፀዋል።

ምንም እንኳን በኔፓል የሰዓት ገደብ ቢጣልም ተቃዋሚዎች ዛሬ ወደ ፓርላማው ገብተው ፓርላማውን ማንደዳቸው ተዘግቧል።

ከፓርላማው በተጨማሪ ወደ የጠቅላይ ሚኒስትሩ እና ሌሎች የፓርቲያቸው መሪዎች ቤት በማምራት በእሳት ማቃጠላቸው ተነግሯል።

በተጨማሪ ተቃዋሚዎች በትልቁ የሃገሪቱ ሚዲያ ካንቲፑር ህትመት ህንፃ ላይም እሳት ለኩሰዋል።

የኔፓል ወጣቶች አደባባይ የወጡት ከማህበራዊ ሚዲያዎቹ መዘጋት በተጨማሪ በተንሰራፋው ሙስና ሳቢያም ጭምር ነው።

በተቃውሞው የተነሳ በዋና ከተማዋ የሚገኘው ካትማንዱ ኤርፖርት ሲዘጋ በርካታ በረራዎችም ተሰርዘዋል።

ምንም እንኳን ፕሬዚደንቱ አዲስ መሪ ለመሾም እየሰሩ ነው ቢባልም ተቃዋሚዎች አላማቸው መንግስትን መጣል እንደሆነ ገልፀዋል።

ወጣቶቹ መጀመሪያ ጥያቄያቸውን በተገቢው መንገድ መግለፅ እንደፈለጉ ሲገለፁ የፀጥታ ኃይሎች ወጣቶችን መግደላቸውን ተከትሎ ለዚህ እንደተደረሰ አንስተዋል።

ዘገባው የአልጄዚራ እና ቢቢሲ ነው

@TikvahethMagazine
88🔥12🤔7🕊7👎5🤣5
ትራምፕ በመንግስት ትምህርት ቤት ሃይማኖታዊ ፀሎት ለማድረግ የሚያስችል መመሪያ ይወጣል አሉ።

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ "በአብዛኛው የሃገራችን ታሪክ በመላው ሃገር የትምህርት ክፍሎች ውስጥ መፅሐፍ ቅዱስ ነበር፤ ዛሬ ግን በብዙ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች ፀረ ሃይማኖታዊ ፕሮፓጋንዳ ይነገራቸዋል ሃይማኖታዊ አስተሳሰብ የሚያንፀባርቁም ይቀጣሉ" ሲሉ በመግለጽ የትምህርት ቢሯቸው በመንግስት ትምህርት ቤቶች ውስጥ ፀሎት ማድረግ እንዲቻል የሚያስችል መመሪያ ያወጣል ብለዋል።

ፕሬዚዳንት ትራምፕ አክለውም፥ "እንደ ህዝብ ከፈጣሪ በታች ሆነን ማንነታችንን እናስመልሳለንም" ሲሉ ተናግረዋል።

ከ1960ዎቹ ጀምሮ የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመንግስት ትምህርት ቤቶች ውስጥ ፀሎት እንዳይደረግ እያገደ ቆይቷል።

በ2024 ሉዚያና ግዛት በመንግስት ትምህርት ቤቶቿ በሚገኙ ሁሉም ክፍሎች አስርቱ ትዕዛዛት መለጠፍን ግዴታ ስታደርግ በዚህ አመት የሉዚያናን ውሳኔ ቴክሳስ እና አርካንሳስ ተከትለዋል።

የዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ወደ ስልጣን ከመጣ በኋላ ለሃይማኖታዊ ነገሮች ትኩረት ሰጥቷል ሲባል ባለፈው ሳምንት ፆታቸውን የቀየሩ ሰዎች የአዕምሮ ህመም ስላለባቸው የጦር መሳሪያ መታጠቅ የለባቸው የሚል ሃሳብ ማቅረቡም ይታወሳል።

ዘገባው የኋይት ሃውስና የዩፒአይ ነው።

@TikvahethMagazine
448👍106👏27🤣22👎8🤝6🔥5🤯3🤔2
እስራኤል በኳታር ዋና ከተማ ዶሃ ጥቃት ፈፅማለች ተባለ።

እስራኤል የሃማስ አመራርን ለማጥቃት በዶሃ ጥቃት መፈፀሟ ሲነገር በዶሃ ከተማም ጭስ ታይቷል።

የኳታር የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ጥቃቱን እስራኤል የሃማስ አመራሮችን ለመግደል መፈፀሟን ገልፆ ተግባሩን የአለም አቀፍ ህግን የጣሰ ብሎታል።

የእስራኤል ጦር የሃማስን አመራሮች ኢላማ ያደረገ ጥቃት መፈፀሙን ገልፆ ጥቃቱ የት እንደተፈፀመ ከመናገር ተቆጥቧል።

በመግለጫው ጦሩ ከእስራኤል የደህንነት ኤጀንሲ ጋር በመሆን የተሳካ ጥቃት መፈፀሙን አንስቶ ጦሩ እና ኤጀንሲው የጥቅምት ሰባቱን ግድያ የፈፀመውን የሃማስ ቡድን ለማሸነፍ በጋራ መስራት እንቀጥላለን ብሏል።

በጥቃቱ ስለደረሰ ጉዳት የተባለ ነገር የሌለ እስካሁን የለም።

መረጃው የዋሽንግተን ፖስትና የአሶሼትድ ፕሬስ ነው።

@TikvahethMagazine
99👎39🤔12💔11🤣10🤯7👍4🤬4
#update

ሃማስ እስራኤል በኳታር በፈፀመችው ጥቃት አምስት ዝቅተኛ አመራሮቹ እንደሞቱበት አስታወቀ።

ሃማስ ከፍተኛ አመራሩ ከጥቃቱ ተርፈዋል ሲል የኳታር የደህንነት ኃይልም ተገድሏል ብሏል።

በጥቃቱ ከተገደሉት መካከል በጋዛ የሃማስ መሪ የሆኑት የካሊል አልሃያ ልጅ እና የአልሃያ ቢሮ ሃላፊ ይገኙበታል።

ጥቃቱ በዋነኝነት ያነጣጠረው የሃማስ የጋዛ መሪ በሆኑት ካሊል አልሃያ ላይ እንደሆነ ሲዘገብ አልሃያ መትረፋቸውን ሃማስ ገልጿል።

አሜሪካ ጥቃቱ ከመፈፀሙ በፊት እንደ ሁልጊዜው ሁሉ መረጃ ነበራት ሲባል አሜሪካ በኳታር ያሉ ዜግቿ ደህንነቱ በተጠበቀ ቦታ እንዲሆኑ አዛለች።

ጥቃቱን የአፍሪካ ህብረትን ጨምሮ በርካታ ሃገራት እያወገዙት ይገኛሉ።

መረጃው የAP ነው

@TikvahethMagazine
126😢42👏10👍7👎7🤣7🤬6🤔3🙏3
#NibBank

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ጳጉሜ 05 ቀን 2017 ዓ.ም ለኢትዮጵያ ልብ ሕሙማን ህፃናት መርጃ ማዕከል የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል።

የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሔናክ አበደ በመርሃ ግብሩ ላይ ባደረጉት ንግግር፥ የአዲስ ዓመት አከባበር የበለጠ ትርጉም ያለው የሚሆነው ለሌሎች ስናካፍል እና ቀጣይ ተስፋ ስናስብ ነው ብለዋል፡፡

በንብ ኢንትርናሽናል ባንክና በሰራተኞች ስም ለታካሚዎች አዲሱ አመት የተስፋ እና የመታደስ ወቅት እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል ሁሉም የበኩሉን አስተዋፆ እንዲያበረክትም አሳስበዋል፡፡
43👏12👎5👍3🤣3🔥2
እንኳን ለ2018 አዲሱ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ እያልን ሆራ ሪል እስቴት በዓለን ምክንያት በማድረግ እስከ መስከረም 10 የሚቆይ የ10% ቅናሽ አቅርበናል፣ ይህንን እድል እንድትጠቀሙ ስንል በደስታ እንጋብዞታለን፣ ለበለጠ መረጃ ሳርቤት በሚገኘው ቢሮዋችን በአካል በመምጣት ሳይቱን ጐብኝተው መረጃ መውሰድ የሚችሉ ሲሆን ካልቻሉ ደግሞ በስልክ ቁጥሮቻችን 0984676767 ወይም 0984767676 በመደወል መረጃዋችን ማግኘት ይችላሉ!!!
14
ከ10 ህፃናት ውስጥ አንዱ አሁን ከመጠን በላይ የወፈረ ነው - ዩኒሴፍ

ከተመድ ኤጀንሲዎች አንዱ የሆነው ዩኒሴፍ ለመጀመሪያ ጊዜ በአለማችን ላይ ከመጠን በላይ የወፈሩ ህፃናት ቁጥር ከመጠን በታች ክብደት ያላቸውን መብለጡን አስታውቋል።

ዩኒሴፍ ዕድሜያቸው ከ5-19 ከሆኑት ህፃናት 188 ሚሊየን ያህሉ ከመጠን በላይ ወፍረዋል ሲል ይህም ከ10 ህፃናት አንዱ ማለት እንደሆነ ተገልጿል።

በትምህርት ላይ ካሉት ደግሞ ከአምስት ህፃን አንዱ ከመጠን በላይ የወፈረ ነው ብሏል።

ከመጠን በላይ ውፍረት በአንድ ወቅት የኢኮኖሚ ዕድገታቸው ከፍተኛ በሆኑ ሃገራት ስጋት ነበር ያለው ዩኒሴፍ አሁን ድሃ ሃገሮችም ተጠቂ ሆነዋል ብሏል።

ዩኒሴፍ ከመጠን በታች ክብደት የነበራቸው ህፃናት ቁጥር ከሚሊኒየሙ ወዲህ ከ13 በመቶ ወደ 9.2 በመቶ ቀንሷል ሲል ከመጠን በላይ ውፍረት ደግሞ ከ3% ወደ 9.4% ጨምሯል።

በአካባቢ ደረጃ ከሰሃራ በታች ባለው አፍሪካና ከደቡብ እስያ በስተቀር በሁሉም አካባቢዎች ከመጠን በላይ ውፍረት ከመጠን በታች ክብደትን በልጧል።

ዩኒሴፍ ከመጠን በላይ ውፍረት ከ2035 ጀምሮ በየአመተ  4 ትሪሊየን ዶላር የኢኮኖሚ ተፅዕኖ ስላለው ሃገራት ሰፊ ስራ ይስሩ ብሏል።

የስነ ምግብ ባለሙያዎች ከመጠን በላይ ውፍረት እየጨመረ ያለው በተፈጥሯዊ መንገድ የማይሰሩ የተቀነባበሩ በስኳር የበለፀጉ ምግቦች መብዛት ነው ሲሉ ዩኒሴፍ ቤተሰቦች ልጆቻቸውን የሚመግቧቸው ምግቦች ላይ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስቧል።

መረጃው የተገኘው ከቢቢሲ ነው።

@TikvahethMagazine
49🤣37😢9👍6🤔4
ላሪ ኤሊሰን ኤሎን መስክን በመብለጥ የአለማችን ቱጃሩ ሰው ሆነ።

የክላውድ ተቋሙ ኦራክል ባለድርሻ ላሪ ኤሊሰን አጠቃላይ ሃብቱ 393 ቢሊየን ዶላር ሲደርስ ይህም ከመስክ አጠቃላይ ሃብት 384 ቢሊየን ዶላር በመብለጥ የአለማችን ቁጥር አንድ ባለሃብት እንዲሆን አስችሎታል።

የኦራክል የአክሲዮን ገበያ በ40 በመቶ ጨምሯል ሲባል ይህም ኤሊሰን የአለማችን ቱጃሩ ሰው እንዲሆን አድርጎታል።

ኦራክል የሰው ሰራሽ አስተውህሎት መስፋፋቱን ተከትሎ ተፈላጊነቱ ሲጨምር እንደ ኦፕን ኤአይ ያሉ ተቋማት በኦራክል ላይ ጥገኛ እየሆኑ ነው።

ኤሊሰን እራሱ መስክ በሚመራው ቴስላ ውስጥም ድርሻ ያለው ሲሆን መስክ ቲዊተርን በገዛበት ወቅትም የ1 ቢሊየን ዶላር ኢንቨስትመንት አድርጓል።

ከሁለቱ ወዳጆች በመቀጠል የሜታው ማርክ ዙከርበርግና የአማዞኑ ጄፍ ቤዞስ ተከታዮቹን የቢሊየነርነት ቦታ መያዛቸው ተነግሯል።

ዘገባው የዘ ጋርዲያን ነው።

@TikvahethMagazine
62👍46👎6🔥6🤔6
በየዓመቱ ከ720 ሺህ በላይ ሰዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ ራሳቸውን ያጠፋሉ።

የዓለም ጤና ድርጅት በየዓመቱ 727,000 ሰዎች ራሳቸውን እንደሚያጠፉ እና ከዚህ የሚልቁት ደግሞ ራሳቸውን ለማጥፋት ሞክረው እንደማይሳካላቸው ገልጿል።

በዛሬው ዕለት ራስን የማጥፋት መከላከል ቀን (World Suicide Prevention Day) በዓለም አቀፍ ደረጃ ይታሰባል።

ራስን ማጥፋት አሁን አሁን ሀገራችንን ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለይ እያደጉ ባሉት ሃገራት አሳሳቢ ጉዳይ እየሆነ መጥቷል።

በዓለም አቀፍ ደረጃ ከሚፈፀሙ ራስን ማጥፋቶች መካከል 73 በመቶ ያህሉ የሚፈፀመው ዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ባላቸው ሃገራት እንደሆነ የዓለም ጤና ድርጅት መረጃ ያሳያል።

ራስን ማጥፋት ለወጣቱ ዋነኛ የሞት መንስኤ እየሆነ ሲመጣ ከ15-29 ዕድሜ ውስጥ ላሉት ወጣቶች ሦስተኛው ብዙ ሞት የተመዘገበበት ምክንያትም ሆኗል።

ራሳቸውን የሚያጠፉ ሰዎችን በተመለከተ በቂ መረጃ የሌለ ሲሆን ከዓለም ጤና ድርጅት አባል ሀገራት መካከል የራስን ማጥፋት ምጣኔን ለመለካት የሚያስችል በቂ የወሳኝ ኩነት መረጃ ያላቸው 80 ሃገራት ብቻ ናቸው።

በዓለማችን ላይ ራስን ማጥፋትን እንደ ትኩረት አድርገው የሚሰሩት ጥቂት ሃገራት ከመሆናቸው በተጨማሪ ብሔራዊ የራስን ማጥፋት መከላከል ስትራቴጂ ያላቸው 38 ሀገራት የሚሆኑት ናቸው።

ራስን ማጥፋት በተለያዩ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና አካባቢያዊ ምክንያቶች ሊፈፀም ሲችል ከፍተኛ ገቢ ባላቸው ሃገራት ጭንቀትና የአልኮል መጠጥ ራስን ከማጥፋት ጋር ከፍተኛ ግንኙነት አላቸው።

አብዛኛዎቹ የራስን ማጥፋት ተግባራት በጭንቀት፣ በፋይናንስ ችገር እና በፍቅር ግንኙነቶች መረበሽ ምክንያት የሚፈጠሩ ናቸው።

መገለል እና ብቸኝነት የሚያጠቃቸው ሰዎች ራስን የማጥፋት ዕድላቸው በተለየ መልኩ ከፍተኛ ቢሆንም ሰዎች ጭንቀት ወስጥ ሲገቡ በየትኛውም ጊዜ ራሳቸውን ሊያጠፉ ይችላሉ።

በኢትዮጵያም እራስን ማጥፋት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ሲሆን በተደረገ ጥናት ዕድሜያቸው ከ10-24 ከሆኑ ሰዎች መካከል 12 በመቶ ያህሉ እራሳቸውን ለማጥፋት ይሞክራሉ።

በጥናቱ መሰረት የራስን ማጥፋት ምክንያቶች ሴት መሆን፣ የማህበረሰብ ድጋፍ ማጣት፣ የቤተሰብ ራስን የማጥፋት ታሪክ እና የትምህርት ውጤት መበላሸት ዋነኞቹ ናቸው።

የዓለም ጤና ድርጅት በ2030 በራስን ማጥፋት ምክንያት የሚከሰቱ ሞቶችን በ33 በመቶ ለመቀነስ ቢያቅድም እስካሁን የታየው ለውጥ 12 በመቶ ብቻ መሆኑን አንስቷል።

ራስን ማጥፋት እንዲቀንስ ሰዎች እንዳይጨነቁ ማድረግ ዋነኛው ሲሆን ለወጣቶች በተለይ የስሜት ብስለት እንዲኖራቸው ማስቻል በመፍትሔነት ይጠቀሳል።

የዓለም አቀፉ የራስን ማጥፋት መከላከል ማኅበር ጭንቀት ውስጥ ያለ ሰው ከሌላው አንፃር በ20 እጥፍ የበለጠ ራሱን የማጥፋት ዕድል እንዳለው ይገልጻል።

መንግስታት ራሳቸውን የሚያጠፉ ሰዎችን ቁጥር ለመቀነስ የሀገሬውን ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ከመፍታት በተጨማሪ ሰፊ ስራዎች ይጠበቅባቸዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከዚህ በፊት የህክምና ባለሙያና የሃይማኖት አባት አነጋግሮ በጉዳዩ ላይ የሰራውን ዘገባ ከዚህ ማንበብ ይችላሉ።

@TikvahethMagazine
83😢49🙏5👍3🤔1
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
መልካም አዲስ ዓመት !

2018 ዓ/ም የሰላም፣ የፍቅር፣ የደስታ ይሁንልን።

@tikvahethiopia
123🔥9👍4🕊3🙏2
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#SamiTech

አዳዲስ ላፕቶፕች ከአንድ ዓመት ዋስትና ጋር!!
@samcomptech

በጥራት፣ በብራንድና በባትሪ ቆይታ አስተማማኝ የሆኑ የተለያዩ ሞዴል ላፕቶፖች በፈለጉት ስክሪን መጠን፣ ኮር አይ እና ጀነሬሽን አሉን።

ላፕቶፕ ከመገዛትዎ በፊት ማወቅ ያለባችሁን ወሳኝ ነገሮች እናስረዳለን። በላፕቶፖቻችን ጥራት ላይ አንደራደርም!

ለቢሮዎች፣ ለተማሪዎች፣ ለዲዛይን ባለሙያዎች፣ ለጌመሮች ወ.ዘ.ተ. ሁሉም አሉን።

የዕቃዎች ዋጋ፣ ዓይነት እና አድራሻ ለማግኘት 👉 @samcomptech

@sww2844

0928442662 / 0940141114

Telgram

      👇
https://www.tg-me.com/samcomptech
25👍1🤯1
ናይጄሪያ ያወጣችውን አዲስ የታክስ ህግ ትግበራ ወደ 2026 አሸጋገረች።

ምዕራብ አፍሪካዊቷ ሃገር ናይጄሪያ ባለፈው ግንቦት ወር አዲስ የታክስ ህግ አውጥታ የነበረ ሲሆን በአዲሱ ህግ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከ7% ወደ 12.5% እንደሚጨምርና በነዳጅ ላይ ተጨማሪ የ5% ታክስ እንደሚጣል ተገልፆ ነበር።

ይሁንና የፋይናንስ ሚኒስትሩ አዲሱ ህግ 2026 ከመግባቱ በፊት ወደ ስራ እንደማይገባ ተናግረዋል።

የፋይናንስ ሚኒስትሩ ዋለ ኤዱን መንግሰታቸው አሁን ያለውን የኢኮኖሚ ሁኔታ እንደሚረዳ በማንሳት ተጨማሪ ዕዳ በናይጄሪያውያን ላይ አንጥልም ብለዋል።

ቦላ ቲኑቡ ናይጄሪያን በ2023 መምራት ከጀመሩ ወዲህ የተለያዩ የነበሩ ድጎማዎችን ሲያስቀሩ መገበያያ ገንዘቧ ናይራማ ሁለት ጊዜ እንዲዳከም አድርገዋል።

ናይጄሪያ ከድጎማዎቹ መቅረት በኋላ የመንግስትን ገቢ ያሳድጋል የተባለ የታክስ ሪፎርም ማድረጓን ብታሳውቅም አዲሱ የታክስ ሪፎርም ያለውን የኑሮ ውድነት የሚያባብስ ሆኖ ተገኝቷል።

ለዚህም ያለውን የኑሮ ችግር ለማረጋጋት ህጉ አሁን እንደማይተገበርና በመጪው ጥር ወር ወደ ስራ እንደሚገባ ተገልጿል።

መረጃው የሮይተርስ ነው።

@TikvahethMagazine
50👍8👏5
2025/10/24 11:20:24
Back to Top
HTML Embed Code: