Telegram Web Link
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግደብ ከምንም ወደ ተሟላ ከተማነት

( ዊ ቢዩልድ (የቀድሞ ሳሊኒ) ገጽ የተወሰደ ጹሁፍ)

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በ2003 ዓ.ም ከአዲስ አበባ 700 ኪሎሜትሮችን ርቃ በምተገኘዋ  በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ሲጀመር አካባቢው ለመድረስ ከሚወስደው የቀናት ጉዞ በተጨማሪ አካባቢው በደን፣ በሳሮች እና በጥልቅ ጉድጓዶች የተሞላ ነበር።

አሁን ግን "ዊ ቢዩልድ" በአካባቢው የገነባው የአየር ማረፊያ ከአዲስ አበባ ሰዎች በቀጥታ ወደ አካባቢው ብዙ ጊዜ ሳይፈጅባቸው እንዲያርፉ ያደርጋል።

በ2003 ግንባታው ሲጀመር ምንም ያልነበረው አካባቢው አሁን ወደ ትልቅ ከተማነት እያደገ ነው። ፕሮጀክቱን ለመገንባት መጀመሪያ 10,000 ሰዎችን መያዝ የሚችሉ ቤቶችን እና መሰረተ ልማቶችን መገንባት አስፈላጊ ነበር።

ሦስት የመኖሪያ ካምፖች፣ በየቀኑ በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የሚመገቡባቸው ቦታዎች፣ ትምህርት ቤቶች፣ ክሊኒኮች፣ ሆስፒታሎችና የመዝናኛ ስፍራዎች ተገንብተዋል።

የግንባታው ስፍራ በውስጡ የቴኒስ መጫወቻ ስፍራና የእግር ኳስ ሜዳን ጨምሮ እያንዳንዱን ጥግ የሚያገናኙ መንገዶች አሉት።

በእንደዚህ አይነት የግንባታ ስፍራ አስፈላጊው ነገር ውሃ በመሆኑ የአባይ ወንዝ የውሃ አያያዝና ማከም ስርዓትን በመገንባት ሁለት ትላልቅ ማጠራቀሚያና የውሃ ማከሚያዎች ተሰርተዋል።

በግንባታው ስፍራ ለሰራተኞቹ ልጆች የሚሆኑ የተሟላ አስተማሪዎች ያሉት ትምህርት ቤት ተሰርቷል።

የሚሰሩ ሰዎችን ጤና መጠበቅ ቅድሚያ የሚሰጠው በመሆኑም "ዊ ቢዩልድ" 20 አልጋዎች፣ ሁለት ተንቀሳቃሽ ክሊኒኮች እና 71 ሰራተኞቸ ያሉት የጤና መሰረተ ልማት ሰርቷል።

እነዚህ የጤና ማዕከላት የሰራተኞቹ ብቻ ሳይሆኑ የአካባቢው ነዋሪዎችም በነፃ የሚገለገሉባቸው ሆነዋል። ከግድቡ መጠናቀቅ በኋላም እነዚህ የጤና መሰረተ ልማቶች ለኢፌዲሪ የጤና ሚኒስቴር ተላልፈዋል።

በአከባቢው ጥሩ እንጀራ ማግኘት ፈታኝ በሆነበት ወቅትም ከ2021 ጀምሮ ዊ ቢዩልድ 84 ሰራተኞች ያሉት በቀን 6500 እንጀራ በዓመት እስከ 3 ሚሊየን ጥራቱን የጠበቀ እንጀራ የሚያመርት ማምረቻ ሰርቷል።

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ከፕሮጀክት ቦታ ባለፈ ሰዎች ማህበራዊ ኑሯቸውን የሚኖሩበት ከተማ ሆኗል። ባለፉት 14 ዓመታት ባዶ ከነበረው መሬት ተነስቶ ዛሬ ትልቅ ከተማ የመሆንን ጉዞ ጀምሯል።

@TikvahethMagazine
280👍22🙏8😢7🕊6👏1
የደቡብ አፍሪካ ፍርድ ቤት ባሎች የሚስቶቻቸውን የቤተሰብ ስም መጠቀም እንዲችሉ ፈቅዷል።

ከዚህ በፊት በደቡብ አፍሪካ ባሎች የሚስቶችን የቤተሰብ ስም መጠቀም እንዳይችሉ ይከለከል የነበረ ሲሆን ፍርድ ቤቱ ይህንን ቀልብሷል።

ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት የወሰዱት ሄንሪ እና ጃና የተባሉ ጥንዶች መሆናቸው ሲዘገብ ባል የሚስቱን የቤተሰብ ስም መጠቀም ስለተከለከለ ወደ ፍርድ ቤት ጉዳዩን ወስደውታል።

የደቡብ አፍሪካ ህገመንግስታዊ ፍርድ ቤትም ባሎች የሚስቶችን የቤተሰብ ስም እንዳይጠቀሙ የሚከለክለው ህግ "ፆታዊ ማግለልን መሰረት ያደረገ የቅኝ ግዛት ህግ "ሲል ወስኗል።

ፍርድ ቤቱ" በርካታ የአፍሪካ ሃገራት ልጆች የእናታቸውን ጎሳ ስም ይወስዱ ነበር "በማለት ይህ ሁነት" ከክርስቲያን ሚሽነሪዎች መምጣትና ከአውሮፓ ቅኝ ገዢዎች መምጣት በኋላ ተቀይሯል" ብሏል።

ሚስት የባልን የቤተሰብ ስም እንድትጠቀም የሚፈቅደው በሮማን ደች ህግ ውስጥ ነበር ያለው ፍርድ ቤቱ ይኸው በደቡብ አፍሪካም ተተግብሯል ብሏል።

የፍርድ ቤቱ ውሳኔ ወደ ተግባር እንዲገባም ፓርላማው አዲስ የውልደት እና የሞት አዋጅ ያወጣል ተብሎ ይጠበቃል።

መረጃው የቢቢሲ ነው።

@TikvahethMagazine
98🤣33🤔5👎4😢2👍1👏1🕊1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#SamiTech

አዳዲስ ላፕቶፕች ከአንድ ዓመት ዋስትና ጋር!!
@samcomptech

በጥራት፣ በብራንድና በባትሪ ቆይታ አስተማማኝ የሆኑ የተለያዩ ሞዴል ላፕቶፖች በፈለጉት ስክሪን መጠን፣ ኮር አይ እና ጀነሬሽን አሉን።

ላፕቶፕ ከመገዛትዎ በፊት ማወቅ ያለባችሁን ወሳኝ ነገሮች እናስረዳለን። በላፕቶፖቻችን ጥራት ላይ አንደራደርም!

ለቢሮዎች፣ ለተማሪዎች፣ ለዲዛይን ባለሙያዎች፣ ለጌመሮች ወ.ዘ.ተ. ሁሉም አሉን።

የዕቃዎች ዋጋ፣ ዓይነት እና አድራሻ ለማግኘት 👉 @samcomptech

@sww2844

0928442662 / 0940141114

Telgram

      👇
https://www.tg-me.com/samcomptech
28👍3🤬1
#Canada 🇨🇦

በካናዳ ከሚማሩ አለም አቀፍ ተማሪዎች መካከል 40 በመቶዎቹ ህንዳውያን መሆናቸው ይነገራል።

በ2025 ግን ወደ ካናዳ ሄደው ለመማር ጥያቄ ካቀረቡት የህንድ ተማሪዎች መካከል 80 በመቶ የሚሆኑትአዎንታዊ ምላሽ አላገኙም።

ይህም ወደ ካናዳ ሄደው ለመማር ጥያቄ አቅርበው ፈቃድ ከማያገኙት መካከል ህንድን ቀዳሚዋ ሃገር እንዳደረጋት ተገልጿል።

ካናዳ በ2025 ለትምህርት ከሚቀርቡላት 3 ጥያቄዎች መካከል ሁለቱን አትቀበልም የተባለ ሲሆን ይህም ከ10 ዓመት በኋላ ከፍተኛው ነው ተብሏል።

2025 ከገባ ወዲህ ወደ ካናዳ የሚያመሩ ዓለም አቀፍ ተማሪዎች የቀነሰ ሲሆን በ2024 ከነበረው አንፃር ከጥር እስከ ሰኔ 2025 ድረስ ወደ ካናዳ ያመሩ የአለም አቀፍ ተማሪዎች ቁጥር በ214 ሺህ ያነሰ ነው።

ይህም የአለም አቀፍ ተማሪዎች ቁጥር በ70 በመቶ የቀነሰ እንዲሆን ሲያደርገው ጥቂት ተማሪዎች ብቻ ለትምህርት ወደ ካናዳ እየገቡ ይገኛሉ።

ካናዳ ወደ ሀገሯ መግባት በሚችሉ ዓለም አቀፍ ተማሪዎች ላይ በ2024 ገደብ አስቀምጣ እንደነበር ሲታወስ በ2025 የምትቀበለውን ዓለም አቀፍ ተማሪ ቁጥር በ10% ቀንሳለች።

ካናዳ የተማሪዎችን ቁጥር ከመቀነሷ በተጨማሪ ለማስረጃነት የሚቀርበው (Proof of evidence) የገንዘብ መጠንንም በሁለት እጥፍ ጨምራለች።

መረጃው የፋይናንሻል ኤክስፕረስ ነው።

@TikvahethMagazine
66👍6🔥1
#Kenya 🇰🇪

የኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ከመላው ሃገሪቱ ተውጣጡ ከተባሉ ከ10,000 በላይ መምህራን ጋር በደመወዝ እና ሌሎች ጉዳዮች ላይ መምከራቸው ተነግሯል።

በውይይቱ ወቅት መምህራኑ ደመወዛቸው በየ 4 አመቱ አንዴ ተገምግሞ እንደሚሻሻል አንስተው ይህ ጊዜ ወደ ሁለት አመት እንዲቀነስላቸው ጠይቀዋል ተብሏል።

ፕሬዚዳንት ሩቶም የመምህራኑን ጥያቄ የተቀበሉ ሲሆን የመምህራን ኮሚሽን፣ የአስተማሪዎች ህብረት እና የትምህርት ሚኒስቴር በጋራ ሆነው ተገቢ የሚሉትን ከአራት ዓመት ያነሰ ጊዜ እንዲያቀርቡ አዘዋል።

ሩቶ፥ ለአስተማሪዎች የተሻለ የህክምና ሽፋን እንደሚሰጥም ሲያነሱ "በንግግር መፈታት ለሚችል ጉዳይ አደባባይ መውጣት አይገባም" ብለዋል።

በተጨማሪ ተመጣጣኝ ሆነው እየተገነቡ ካሉ ቤቶች 20 በመቶው ለመምህራን እንዲሰጥም ተፈርሟል።

ፕሬዚዳንቱ መምሀራን በየወሩ ለቤት 900 ሚሊየን የኬንያ ሽልንግ በቤት ፈንድ በኩል አስተዋፅኦ ያደርጋሉ ሲሉ በማንሳትም "ተገቢው ቤት ይገባቸዋል" ብለዋል።

በተጨማሪ የልዩ ፍላጎት መምህራን አንድ የስራ ደረጃ ከፍ እንደሚሉና የፋይናንስ ድጋፍ እንደሚደረግላቸው ነው የጠቆሙት።

ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ በየአመቱ ዕድገት ያገኙ የነበሩ አስተማሪዎች ቁጥር 25,000 እንደነበር አንስተው ወደ 50,000 ለማሳደግ የሚያዘው በጀት በእጥፍ እንዲጨምር መደረጉን ተናግረዋል።

ባለፉት 3 ዓመታት ከ76,000 በላይ መምህራን መቀጠራቸውን ያነሱት ሩቶ በመጪው ጥር ተጨማሪ 24,000 መምህራን ይመለመላሉ ብለዋል።

በ3 አመት የትምህርት ዘርፉ በጀት ከ504 ቢሊየን ሽልንግ ወደ 702 ቢሊየን ሽልንግ ማደጉን ያነሱት ሩቶ  "መምህራን የኬንያ ጀግኖች ናቸውም" ሲሉ መግለጻቸው ተዘግቧል።

የመረጃው ምንጮች TUKO እና CAPITAL FM ናቸው።

@TikvahethMagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
201👍23👏19🤔4👎2
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#SamiTech

አዳዲስ ላፕቶፕች ከአንድ ዓመት ዋስትና ጋር!!
@samcomptech

በጥራት፣ በብራንድና በባትሪ ቆይታ አስተማማኝ የሆኑ የተለያዩ ሞዴል ላፕቶፖች በፈለጉት ስክሪን መጠን፣ ኮር አይ እና ጀነሬሽን አሉን።

ላፕቶፕ ከመገዛትዎ በፊት ማወቅ ያለባችሁን ወሳኝ ነገሮች እናስረዳለን። በላፕቶፖቻችን ጥራት ላይ አንደራደርም!

ለቢሮዎች፣ ለተማሪዎች፣ ለዲዛይን ባለሙያዎች፣ ለጌመሮች ወ.ዘ.ተ. ሁሉም አሉን።

የዕቃዎች ዋጋ፣ ዓይነት እና አድራሻ ለማግኘት 👉 @samcomptech

@sww2844

0928442662 / 0940141114

Telgram

      👇
https://www.tg-me.com/samcomptech
22👎4
"ቀጣዩ ትውልድ በደንብ የሚያስፈልገዉ  ክህሎት እንዴት መማር እንዳለበትን መማር ነው"- ደሚስ ሃሳቢስ

በሰው ሰራሽ አስተውህሎት ላይ የሚሰራው የጎግሉ ዲፕማይንድ ዋና ስራ አስፈፃሚ ደሚስ ሃሳቢስ ቀጣዩ ትውልድ የሚያስፈልገው ትልቁ ክህሎት እንዴት መማር እንዳለበት መማር ነው ብለዋል።

ስራ አስፈፃሚው ይህ ክህሎት ያስፈለገው የሰው ሰራሽ አስተውህሎት ሰዎች የሚማሩበትና የሚሰሩበትን መንገድ እየቀየረ በመሆኑ ስለመሆኑ ተናግረዋል።

የሰው ሰራሽ አስተውህሎት በየሳምንቱ እየተቀያየረ መሆኑን ያነሱት ዋና ስራ አስፈፃሚው ከ10 ዓመት በኋላ የሚሆነውን መገመት ከባድ መሆኑን ተናግረው በጣም ትልቅ ለውጥ የሚያመጣ ነው ሲሉ ነው የገለጹት።

በ2024 በኬሚስትሪ የኖቤል ሽልማትን ያሸነፉት ደሚስ ሃሳቢስ እንደ የሰው ልጅ የበሰሉ ወይም የሰው ልጅ ማከናወን የሚችለውን ነገር በብዛት መስራት የሚችል የሰው ሰራሽ አስተውህሎት በ10 አመት ውስጥ እንደሚመጣ አንስተው ሰዎች እንዴት መማር እንዳለባቸውና ከተለመዱት ትምህርቶች ውጪ ራሳቸውን ለአዲስ ነገር ማዘጋጀት እንደሚገባቸው አሳስበዋል።

የሰው ሰራሽ አስተውህሎት ከመጣ ወዲህ ዓለማችንን በእጅጉ እየቀየረ ሲሆን መጥፎም ጥሩ ጎኖችንም ይዞ ብቅ ብሏል።

የትምህርት ዘርፉን ጨምሮ በርከት ያሉ ዘርፎች ከቴክኖሎጂው መምጣት በኋላ ሲቀየሩ ተማሪዎች በቴክኖሎጂው ላይ ይበልጥ ጥገኛ መሆናቸው የማሰብ ችሎታቸውን እንደሚያዳክም ይነገራል።

አንዳንድ ስራዎችም በሰው ሰራሽ አስተውህሎት መተግበሪያዎች እየተተኩ ሲሆን ዘርፉ ግን ስራን ከመተካት በተጨማሪ በርከት ያሉ ሌሎች ስራዎችን እንደሚፈጥር የሚሟገቱ አሉ።

የሰው ሰራሽ አስተውህሎት ምድርን እየለወጠ ባለበት ሁኔታ ነገሩን እንዴት መያዝ አለብን የሚለው ትልቅ ጥያቄ ሲሆን እንደ ሃገር ከዘርፉ መጠቀም እንድንችል ምርምር እና ትምህርቶችም ያስፈልጋሉ።

መረጃው የMINT ነው።

@TikvahethMagazine
87👍10👎2
ኬንያ የ42 የቴሌቪዥን ጣቢያዎችን ፈቃድ ልትሰርዝ ነው።

የኬንያ የኮሚዩኒኬሽን ባለስልጣን በ7 ቀናት ውስጥ የ42 የቴሌቪዥን ጣቢያዎችን ፈቃድ ሊሰርዝ መሆኑ ተነግሯል።

ባለስልጣኑ ፈቃዳቸው ሊሰረዝ የሚችልን ጣቢያዎች ዝርዝር ይፋ ሲያደርግ ፈቃዳቸው ከተሰረዘ በኋላ ምንም ስራ ማከናወን እንደማይችሉ ገልጿል።

የኮሚዩኒኬሽን ባለስልጣኑ የኬንያን የመረጃ ህግ የሚጥሱ ተቋማት በጋዜጣ ከተነገረ በኋላ በ7 ቀናት ውስጥ ፈቃዳቸው ሊሰረዝ እንደሚችል ሲያነሳ በዋነኝነት ያልተገባ ይዘት ማሰራጨት፣ የማሰራጫ መሰረተ ልማት አለመኖርና የፈቃድ ክፍያ አለመክፈል ፈቃድ ሊያሰርዙ ይችላሉ።

ከወራት በፊት የቤቲንግ ቁጥጥር እና ፈቃድ ቦርድ 23 የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ከስፖርታዊ ውርርድ ጋር በተያያዘ የወጣውን የማስታወቂያ መመሪያ በመጣሳቸው ሊዘጉ እንደነበር አስጠንቅቆ ነበር።

ጣቢያዎቹ የስፖርት ውርርድ ማስታወቂያ እንዳይተወወቅ ቢታገድም ማስታወቂያዎችን ማሳየት መቀጠላቸውን ቦርዱ ገልፆ ነበር።

42 የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ፈቃድ መሰረዝ በባለፈው የፈረንጆቹ መስከረም 12 በጋዜጣ የወጣ ሲሆን በመጪዎቹ 7 ቀናት ውስጥ ይፈፀማል ተብሎ ይጠበቃል።

ጎረቤት ሃገር ኬንያ በ2023 በአጠቃላይ 135 የቴሌቪዥን ጣቢያዎችና 225 የሬዲዮ ጣቢያዎች የነበሯት ሲሆን በዋነኝነት መቀመጫቸውን በዋና ከተማዋ ናይሮቢ ያደረጉ ናቸው።

ዘገባው የKenyans ነው።

@TikvahethMagazine
116😢4👎1🕊1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#SamiTech

አዳዲስ ላፕቶፕች ከአንድ ዓመት ዋስትና ጋር!!
@samcomptech

በጥራት፣ በብራንድና በባትሪ ቆይታ አስተማማኝ የሆኑ የተለያዩ ሞዴል ላፕቶፖች በፈለጉት ስክሪን መጠን፣ ኮር አይ እና ጀነሬሽን አሉን።

ላፕቶፕ ከመገዛትዎ በፊት ማወቅ ያለባችሁን ወሳኝ ነገሮች እናስረዳለን። በላፕቶፖቻችን ጥራት ላይ አንደራደርም!

ለቢሮዎች፣ ለተማሪዎች፣ ለዲዛይን ባለሙያዎች፣ ለጌመሮች ወ.ዘ.ተ. ሁሉም አሉን።

የዕቃዎች ዋጋ፣ ዓይነት እና አድራሻ ለማግኘት 👉 @samcomptech

@sww2844

0928442662 / 0940141114

Telgram

      👇
https://www.tg-me.com/samcomptech
31👎2
ከክላሽና ታንክ ወደ ድሮን ጦርነት ያደገው የሱዳን ጦርነት

በሱዳን ከሁለት አመት በፊት በሁለቱ ጀነራሎች አለመስማማት የተጀመረው ጦርነት ሃገሪቷ የማትወጣበት ቅርቃር ውስጥ የከተታት ሲመስል ሁለቱም ተዋጊዎች በድሮን መዋጋት መጀመራቸው ስጋትን ፈጥሯል።

ከዚህ በፊት የሱዳን የፈጥኖ ደራሽ ኃይል ከተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በሚሰጠው ድጋፍ የድሮን ጥቃት ይፈፅማል ብሎ ሲከስ የቆየው የጀነራል አልቡርሃን ጦር ራሱም ድሮን ታጥቆ ውጊያ ከጀመረ ሰንብቷል።

የሱዳን ጦር ከሰሞኑ በኮርዶፋንና ዳርፉር ዘመናዊ የተባሉ ድሮኖችን መጠቀም ጀምሯል።

የሱዳን ጦር በሃገር ውስጥ የተሰራ "ሳፍሩቅ" የተሰኘ ድሮን ለውጊያ መጠቀም ጀምሯል ሲባል ተፋላሚው የፈጥኖ ደራሽ ኃይል ደግሞ አዳዲስ በታጠቃቸው ዘመናዊ ድሮኖች ጥቃቱን ማድረሱን ተያይዞታል።

በሰዓት እስከ 160 ኪሎሜትር መብረር ይችላል የተባለው የሳፍሩቅ ድሮን በባራ ከተማ ከፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ጋር በነበረው ውጊያ ውጤታማ ነበር ተብሏል።

በዚህ ውጊያ ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉን ኢላማ ያደረጉ 11 ድሮኖች ጥቅም ላይ ውለዋል ተብሎም ተነግሯል።

በአንፃሩ ተፋላሚው የፈጥኖ ደራሽ ኃይል ቻይና ሰራሽ ስትራቴጂክ ድሮኖችን መታጠቁ ሲነገር ባለፈው ሳምንትም ለዋና ከተማዋ ቅርብ በሆኑ አካባቢዎች ጥቃቶችን መፈፀሙ ይታወሳል።

በተጨማሪ የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ከሱዳን ጦር የበለጠ ርቀትን መሄድ የሚችሉ ድሮኖችን መታጠቁ ሲነገር የጦሩ ድርኖች 600 ኪሎ ሜትር ሲሄዱ የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ 2000 ኪሎ ሜትር መሄድ ይችላሉ። ይህም በሱዳን ውስጥ ያለን የትኛውንም ቦታ ማጥቃት እንዲችል ዕድል ይሰጠዋል።

የሱዳን ጦር በዳርፉር የሚገኘውን የድሮኖች መነሻ ሆኖ የሚያገለግል ኤርፖርት በተደጋጋሚ መምታቱን ቢገልፅም የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ በተደጋጋሚ በአየር መከላከያው ሲመክት ቆይቷል።

ይባስ ብሎ የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ባለፉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ የጦሩን 3 ቱርክ ሰራሽ ድሮኖች መትቼ ጥያለሁ ብሏል።

ሁለቱም ተፋላሚዎች ትኩረታቸውን ከመሬት ውጊያ ወደ አየር ውጊያ እያዞሩ ሲሆን እነዚህን የተወሳሰበ ቴክኖሎጂ የሚጠቀሙ ድሮኖች በደንብ ለውጊያ መጠቀም መጀመራቸው ጦርነቱን እንዳያባብስ ተሰግቷል።

የመረጃው ምንጭ ሱዳን ትሪቡን ነው።

@TikvahethMagazine
59🕊15😢6🤷‍♂3🤔2👍1💔1
#SouthSudan: ላልተሰራ መንገድ 1.7 ቢሊየን ዶላር ተከፍሏል!

የተመድ መርማሪዎች የደቡብ ሱዳን ዜጎች በተራቡበት ሁኔታ ውስጥ ባለስልጣናቱ ረብጣ ቢሊየኖችን በሚያወጡ የሙስና ወንጀሎች መዘፈቃቸውን አጋልጠዋል።

የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን "ደቡብ ሱዳን የግል ጥቅም ለማግኘት የሃገር ሃብትን በተቋማዊና ስርዓት መልኩ በሚሰርቁ በሊታ መሪዎች ተይዛለች" ብሏል።

የደቡብ ሱዳን አማካይ የነፍስ ወከፍ ገቢ በ2011 ነፃ ከወጣችበት አንፃር አሁን ላይ የሱን 1/4ኛ ሲሆን 2/3ኛ የሚሆነው ህዝቧም በረሃብ ይማቅቃል።

በምርመራው ከ2021-2024 የተደረገ ያልተገባ ክፍያ ሲጋለጥ በዚህ ዓመት የደቡብ ሱዳን ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው ከተሾሙት ቦል ሜል ጋር ዝምድና ላላቸው የመንገድ ገንቢዎች ላልተሰራ መንገድ 1.7 ቢሊየን ዶላር ተከፍሏል ተብሏል።

አሜሪካ ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ቦል ሜልና ሁለት ድርጅቶች ላይ ማዕቀብ ጥላ የነበረ ሲሆን በቅርቡ በነበሩ ውይይቶችም ይኸው ማዕቀብ እንዲነሳ የትራምፕ አስተዳደርን ጠይቀዋል ተብሏል።

ከ2021-2024 ባለው ጊዜ የደቡብ ሱዳን መንግስት ከቦል ሜል ጋር ግንኙነት አላቸው ለተባሉ ድርጅቶች ከ2.2 ቢሊየን ዶላር በላይ ክፍያንም ፈፅሟል ተብሏል።

"ነዳጅ ለመንገድ" ተብሎ ለተሰየመውና ከነዳጅ የሚገኘውን ገንዘብ ለመንገድ ግንባታ ለማዋል ለታሰበው ለዚህ ፕሮጀክትም በአንድ ወቅት ከመንግስት አጠቃላይ ክፍያዎች 60 በመቶው ይወጣ እንደነበር በሪፖርቱ ተገልጿል።

እነዚህ የቦል ሜል ድርጅቶች ከ500 ሚሊየን ዶላር ያልበለጡ መንገዶችን ሲሰሩ የመንገዱን እርዝማኔ በመጨመር ኮንትራቶችን ጨምረው ከፍተኛ ገንዘብ ያስከፍላሉ።

ደቡብ ሱዳን ከነፃነቷ ወዲህ ከነዳጅ ሽያጭ ካገኘችው 23 ቢሊየን ዶላር ለህብረተሰቡ በሚጠቅም መልኩ የዋለው ጥቂቱ ሲሆን ለማሳያነት በ2022/23 የበጀት ዓመት ለመላው ሃገሪቱ የጤና ስርዓት ከተያዘው በጀት በላይ ለፕሬዚዳንቱ የጤና ክፍል ብቻ የተያዘው ይበልጣል።

የደቡብ ሱዳን የፍትህ ሚኒስቴር ለተመድ በፃፉት ምላሽ የተጠቀሰው መንግስት ካለው መረጃ ጋር አይገናኝም እንደዚሁም ካለው የኢኮኖሚ ችግር እና የነዳጅ ሽያጭ መቀነስ ጋር አይገናኝም በማለት ሪፖርቱን አጣጥለዋል።

ሙስና ደቡብ ሱዳናውያንን እየገደለ ነው ያለው ሪፖርቱ እነዚህ ከ2021-2024 የተፈፀሙ ክፍያዎች ጥቂቱ ብቻ ናቸው ብሏል።

ከ79 አካባቢዎች 76ቱ በከባድ ረሃብ ባለበት ሁኔታ ጥቂት ገንዘብ ብቻ ይህንን ለመቅረፍ መዋሉን ያሳየው ሪፖርቱ ሙስና በደቡብ ሱዳን ተቋማዊ ሆኗል ብሏል።

ዘገባው የሮይተርስና አልጄዚራ ነው።

@TikvahethMagazine
396😢46🤣11🤬6👏4💔1
ዩቲዩብ ባለፉት አራት አመታት ለይዘት ፈጣሪዎች ከ100 ቢሊየን ዶላር በላይ መክፈሉን አስታወቀ።

የቪዲዮ ማሰራጫው ዩቲዩብ ከ2021 ወዲህ ለይዘት ፈጣሪዎቹ ከ100 ቢሊየን ዶላር በላይ ክፍያ መፈፀሙን አስታውቆ ከ100 ሺህ ዶላር በላይ የሚሰሩ የዪቲዩብ ቻናሎች ቁጥር በአመት በ45 በመቶ እየጨመረ ነው ብሏል።

የዩቲዩብ የፕሮዳክት ኦፊሰር የሆኑት ጆሃና ቮሊች የይዘት ፈጣሪዎች "ባህልና መዝናኛን አስበን በማናውቀው መንገድ ቅርፅ እያስያዙ ነው" ብለዋል።

ዩቲዩብ ከዚህ በተጨማሪ አዳዲስ አገልግልቶችን ለመጀመር ማቀዱን አስታውቋል።

ዩቲዩብ ከአጫጭር ቪዲዮዎቹ ጋር በተያያዘ አዲስ የሰው ሰራሽ አስተውህሎት መተግበሪያም ሲያመጣ ሰዎች በሰው ሰራሽ አስተውህሎት እገዛ የተቀረፀ ቪዲዮን ወደ ተቀነባበረ ቪዲዮ መቀየር ፣ ሙዚቃ መጨመርና ድምፅ መጨመር ይችላሉ ተብሏል።

በተጨማሪ ከተፈቀዱ ቪዲዮዎች የተወሰዱ ንግግሮችን ወደ ሙዚቃ ቀይረው መጠቀም ይችላሉ ተብሏል።

ዩቲዩብ አክሎም የጎግል VEO 3 ከዩቲዩብ የአጫጭር ቪዲዮዎቾ(Shorts) ጋር እንዲቀናጅ እንደሚደረግ ለተጠቃሚዎቹ አብስሯል።

በተጨማሪ ዩቲዩብ በአንድ ቪዲዮ በርካታ ሰዎች አንድ ላይ ሰርተው ቪዲዮ ለሁሉም ሰዎች ተመልካቾች የሚደርስበትን የ'YouTube collab' እንደሚጀምር ገልጿል።

የይዘት ፈጣሪዎች ስለ ተመልካቻቸው እንዲረዱ የሚያስችል የሰው ሰራሽ አስተውህሎት ቻትቦትም እንደሚጀምር ተገልጿል።

በመጪው ሚያዝያ ወር 20 ዓመት የሚሞላው ዩቲዩብ በመተግበሪያው ከ20 ቢሊየን በላይ ቪዲዮዎች ሲኖሩት ለበርካቶችም የገቢ ምንጭ ሆኗል።

በተለያየ መንገድ ራሱን እና ተጠቃሚዎችን ለመጥቀም እየሰራ ያለው ዩቲዩብም በ2026 ከሰፊ ማስፋፊያ ጋር እንደሚመጣ ተዘግቧል።

የመረጃው ምንጮች CNBC እና The Wrap ናቸው።

@TikvahethMagazine
153👏18👍6👎3
🖥 🖥   🖥 🖥 🖥 🖥 🖥 🖥 🖥
BK  C  O  M  P  U  T  E  R S

  ማንኛውንም አይነት  አዳዲስ ላፕቶፖች ዱባይ ዩዝድ ላፕቶፖች ዴስክ ቶፖችን ጨምሮ ከብዛት እና ከታላቅ ቅናሽ ጋር ያዘንላቹ መተናል

ለ ቢሮዎች ፣ ለተማሪዎች፣ለግሪፊክስ ዲዛይን ባለሙያዎች ፣ ለጌመሮች እንዲሁም ለጨረታ የሚሆኑ በጥራት እና በ ብዛት  ከ አንድ አመት ዋስትና ጋር እኛ ያገኛሉ

ለተጨማሪ  መረጃ እና የላፕቶፕ አማራጮችን ለማየት የቴሌግራም ፔጃችንን Join ያድርጉ።
Tg. https://www.tg-me.com/BKComputers
Inbox @bkcomputer27

አድራሻ አዲስ አበባ መገናኛ ሲቲ ሞል ከ መሰረት ደፋር ህንፃ አጠገብ 1 ፎቅ ላይ እንገኛለን
           ☎️ 0911448148. 0955413433
           we make IT easy!
30👍1
2025/10/24 07:45:49
Back to Top
HTML Embed Code: