ሶማሊያ የስዋሂሊ ቋንቋን በትምህርት ስርዓቷ ለማካተት ማቀዷ ተነገረ።
ሶማሊያ ከምስራቅ አፍሪካ ማህበረሰብ አባል ሃገራት ጋር ያላትን ትስስር ለማሳደግ የስዋሂሊ ቋንቋን በትምህርት ስርዓቷ በማካተት ለማስተማር አቅዳለች።
ሶማሊያ በ2024 ኬንያ፣ ታንዛኒያ ፣ ኡጋንዳ፣ ሩዋንዳ፣ ቡሩንዲ፣ ደቡብ ሱዳንና ዲሞክራቲክ ኮንጎ ያሉበትን ይህንን ጥምረት መቀላቀሏ ይታወቃል።
የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሃሰን ሼህ መሐሙድ የሃገሪቱ ዩኒቨርሲቲዎች ቋንቋውን በማስተማር እና በመጠቀም ረገድ መሪ እንዲሆኑ ጠይቀዋል።
ይህ የተባለው በሞቃዲሾ በተዘጋጀ የምስራቅ አፍሪካ የትብብር እና የኢኮኖሚ ጉባኤ ሲሆን የሶማሊያው የትምህርት ሚኒስቴር ፋራህ ሼህ አብዱልቃዶር ስዋሂሊ በቀጣይ ጉባኤያቸው እንግሊዝኛን ሊተካ እንደሚችልም አንስተዋል።
ሶማሊያ የስዋሂሊ ቋንቋን በትምህርት ስርዓቷ ከማካተቷ በተጨማሪ ከሶማሊኛ፣ አረብኛ እና እንግሊዝኛ እኩል የስራ ቋንቋ የማድረግ እቅድም እንዳላት ተገልጿል።
መረጃው የTRT ነው።
@TikvahethMagazine

❤60👏6🤷♂2🙏1
ወጋገን ባንክ በጀት ዓመቱ በታሪኩ ከፍተኛውን ገቢ ማስመዝገቡን ገለጸ።
ባንኩ በ2017 በጀት ዓመት 13.5 ቢሊዮን ገቢ ያስመዘገበ ሲሆን የአንድ አክሲዮን ትርፉንም ወደ 46.10 በመቶ ማሳደጉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከው መግለጫ ገልጿል።
ባንኩ በመግለጫው ምነ አለ ?
በገቢ ደረጃ ካለፈው በጀት ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ38 በመቶ እድገት አሳይቷል።
- ከታክስ በፊት በታሪኩ ከፍተኛውን የ 3.85 ቢሊዮን ትርፍ አግኝቷል። ይህም ከባለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ73 በመቶ ብልጫ አለው።
- የባለአክሲዮኖች ብዛትን ወደ 14,871 አሳድጓል።
- የባንኩ የተከፈለ ካፒታል የ37 በመቶ ዓመታዊ እድገት በማሳየት በበጀት ዓመቱ መጨረሻ ብር 7 ቢሊዮን ደርሷል። ይህም ብሔራዊ ባንክ ካስቀመጠው የባንኮች ዝቅተኛ የተከፈለ ካፒታል መስፈርት በላይ ነው።
- የባንኩ ጠቅላላ ካፒታል በ39 በመቶ በማደግ 12.8 ቢሊዮን ብር ደርሷል።
- የባንኩ ጠቅላላ ሀብት ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ29 በመቶ ብልጫ በማሳየት በበጀት ዓመቱ መጨረሻ ወደ ብር 84.7 ቢሊዮን ማደግ ችሏል።
- በበጀት ዓመቱ የባንኩ ተቀማጭ ገንዘብ የ28 በመቶ እድገት በማስመዝገብ ብር 66.5 ቢሊዮን ደርሷል።
- የሰጠው ብድር መጠን 53.5 ቢሊዮን ብር ደርሷል። ይህም ከባለፈው በጀት ዓመት አንፃር የ18 በመቶ ጭማሪ አለው።

❤53👏7🔥2😢2👎1🙏1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ከአሜሪካ የመጡ ኦርጅናል የፉርማሲ ብራንድ የMakeUp እቃዋችን ለምትፈልጉ @smoochcosmo page አይታችሁታል??
በጅምላ ወስዳችሁ አትርፉችሁ ለምትሸጡ ሱቆች በሚገርም የwholesale ዋጋዋች አቅርበንላችሗል! ግለሰቦችንም ከmarket በደንብ ባነሰ ዋጋ እናስተናግዳለን!
መደወል እና ማዘዝ ለምትፈልጉ call/Text ☎️ 𝟎𝟗𝟕𝟑𝟏𝟓𝟕𝟕𝟕𝟕 @smoochcosmocontact ወይም በtelegram በ📱𝟎𝟗𝟐𝟏𝟔𝟐𝟑𝟕𝟑𝟕 @hilluuuu ጻፉልን! እናመሰግናለን!
https://www.tg-me.com/SmoochCosmo

❤18👍2
#ጥቆማ
የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ2018 የትምህርት ዓመት የቴአትር እና የፊልም ጥበባት ትምህርት ቤት በቅድመ ምረቃ በማታው መርሃ ግብር ገብተው መማር ለሚፈልጉ አመልካቾች ጥሪ አቅርቧል።
በማስታወቂያውም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አመልካቾች ከመስከረም 29 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 6 ቀን 2018 ዓ.ም በመደበኛ የስራ ቀናት OCR እንደኛ ፎቅ ቢሮ 224 በስራ ሰዓት ተገኝተው መመዝገብ ይችላሉ ብሏል።
ምን ያስፈልጋል ?
1. 2015፣ 2016 እና 2017 ዓ.ም የ2ኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና ተፈትናችሁ በወቅቱ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያላቸው፤
2. 2015፣ 2016 እና 2017 ዓ.ም የመልቀቂያ ፈተና ተፈትናችሁ ከመንግስት ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ውጤት ያላቸው፤
3. ከሙያ ትምህርት ቤቶች(TVET) ተመርቀው የአራተኛ (COC) ማስረጃ ያላቸው፤
4. ዲግሪ እና ዲፕሎማ ያላቸው፤
በዚህም ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች የምታሟሉ አመልካቾች
- የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት፤
- ከሙያ ትምህርት ቤቶች የጨረሳችሁ ከላይ ከተጠቀሱት የትምህርት ማስረጃዎች በተጨማሪ፣ የሙያ ዲፕሎማ ማስረጃ፣ COC አራተኛ እርከን ያለፋችሁበት ማስረጃ ይዛችሁ በመምጣት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን በዩኒቨእሲቲው የቴአትር እና የፊልም ጥበባት ትምህርት ቤት አስታውቋል።

❤58👎6👍5
"ቅዱስነታቸው ሐዋርያዊ ተግባራትን ለመምራትም ሆነ ለማከናወን የማያስችል ምንም ዓይነት የጤና እክል ያልገጠማቸው፤ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ያቀረቡት ጥያቄ የሌለ መሆኑን እንገልጻለን።" የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽሕፈት ቤት
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት "በጤና እክል ምክንያት እንደራሴ እንዲሾምላቸው ጠየቁ" መባሉን ተከትሎ ጽ/ቤታቸው መረጃው ሐሰተኛ ነው ሲል ገልጿል።
የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽሕፈት ቤት ባወጣው መግለጫ "ቤተ ክርስቲያናችን በየዕለቱ የምታከናውናቸው መንፈሳዊ፣ ማኅበራዊ እና ዓለም አቀፍ ተግባራትንም በጽሕፈት ቤታቸው ሆነው በአባትነት እየመሩ በተሟላ ጤንነት ላይ ይገኛሉ።" ሲል ገልጿል።
ጽ/ቤቱ ብፁዕነታቸው ላለፉት ተከታታይ ዓመታት ወደ ሰሜን አሜሪካ በማምራት የሕክምና ክትትል ሲያደርጉ መቆየታቸውን አስታውሶ በቅርቡም ተመሳሳይ ጉዞ አድርገው ጳጉሜን 1 ቀን 2017 መመለሳቸውን ጠቅሷል።
ከዚህም በተጨማሪ ለርእሰ ዐውደ ዓመት (አዲስ ዓመት) በመገናኛ ብዙኃን ቀርበው መልዕክት ማስተላለፋቸውንና በቅርቡም የመስቀል ደመራ በዓልንም በመስቀል አደባባይ ተገኝተው በማክበር ለመላው ሕዝበ ክርስቲያን አባታዊ ትምህርተ ወንጌል፣ ቃለ ምእዳንና ቡራኬ መስጠታቸውን አንስቷል።
ጽ/ቤቱ በመግለጫው "የቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊ ተልእኮ ማደናቀፍ ዓላማቸው ያደረጉ አካላት" ብሎ የጠራቸው አካላት ያሰራጩት መረጃ "ፍጹም ከእውነት የራቀ" ሲል ገልጾታል።
አክሎም፥ "ቅዱስነታቸው ሐዋርያዊ ተግባራትን ለመምራትም ሆነ ለማከናወን የማያስችል ምንም ዓይነት የጤና እክል ያልገጠማቸው፤ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ያቀረቡት ጥያቄ የሌለ መሆኑን እንገልጻለን" ሲል አስታውቋል።

❤121🕊4🤷♀3👍1
የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሃሰን ሼህ መሐሙድ የተለያዩ ጉዳዮችን ከተመለከተ ከአል አረቢያ ጋር ቃለ ምልልስ አድርገዋል።
በቃለ መጠይቃቸው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብንና የቀይ ባህር ጉዳይን በተመለከተ ጥያቄ ቀርቦላቸው ምላሽ ሰጥተዋል።
ፕሬዚዳንቱ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በተመለከተ ምን አሉ?
ፕሬዚዳንት ሃሰን ሼህ መሐሙድ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ትልቅ ፕሮጀክት መሆኑን አንስተው ለኢትዮጵያና ለቀጣናው የኤሌክትሪክ ኃይል የሚያቀርብ ፕሮጀክት መሆኑንም ገልፀዋል።
ፕሬዚዳንቱ አክለውም ግድቡ በኢትዮጵያ መንግስት የተሰራ ስኬታማ ፕሮጀክት ነው ብለዋል።
ለህዳሴ ግድቡ ምርቃት ወደ ኢትዮጵያ መምጣታቸው ከግብፅ ጋር ያላቸውን ግንኙነት እንዴት ያደርገዋል ተብለው የተጠየቁት ፕሬዚዳንቱ "ኢትዮጵያ ጎረቤታችን ነች፤ 2000 ኪሎሜትር ድንበር እንጋራለን" በማለት" ከኢትዮጵያ ጋር ያለን ግንኙነት ከግብፅ ጋር ያለንን ስትራቴጂካዊ ግንኙነት የሚሸረሽር አይደለም" ብለዋል።
ፕሬዚዳንቱ ሶማሊያ ሁለቱ ሃገራት ሱዳንን ጨምሮ አንዱ ሌላኛውን እንዲረዳ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኗንም ገልፀዋል።
የግብፅ ጦር በሶማሊያ ስመስፈሩ ምን አሉ?
ፕሬዚዳንት ሃሰን ሼህ መሐሙድ የግብፅ ጦር በአፍሪካ ህብረት ጥላ ስር እንደሚሰፍሩ ገልፀው የግብፅ የጦር መኮንኖች ጦሩ የሚሰፍርበትን ቦታ መጥተው መገምገማቸውንና የሚቀረው ነገር ጦሩን ማስፈር እንደሆነ ገልፀዋል።
ፕሬዚዳንቱ ግብፅ የሶማሊያ የደህንነት አካላትን ከስልጠና እስከ መሳሪያ ድረስ እየደገፈች መሆኑንም ተናግረዋል።
የግብፅ ጦርን መስፈር በተመለከተ ከኢትዮጵያ የቀረበላቸው ጥያቄ እንደሌለ ያነሱት ሃሰን ሼህ መሐሙድ በሶማሊያ የኢትዮጵያ አምባሳደር የግብፅ ጦርን መስፈር ተከትሎ ያነሱት ነገር ተገቢ አይደለም ብለዋል።
በተጨማሪ ፕሬዚዳንቱ "ሶማሊያ ሉዓላዊ ሃገር ነች፤ ውሳኔዋም ሉዓላዊ ነው" በማለት "ግብፅ ወደዚህ እንድትመጣ የመረጥነው እኛ ነን እና ይመጣሉም" ብለዋል።
ፕሬዚዳንቱ የቀይ ባህርን ጉዳይ በተመለከተ ምን አሉ?
የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ኢትዮጵያ ያጣችውን የባህር በር አማራጭ ለማስመለስ እንደሚሰሩ መናገራቸውን ሶማሊያ በስጋትነት ትመለከተዋለች ተብለው ተጠይቀው "ኢትዮጵያ ቀይ ባሀር መድረስ ከፈለገች መድረስ ትችላለች ነገር ግን ሁሌም ለመድረስ የሚኬዱ መንገዶች አሉ ያንን በአለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ያለው መንገድ ይከተላሉ ብዬ አስባለሁ" ብለዋል።
ፕሬዚዳንቱ "ኢትዮጵያና ኤርትራ በቀይ ባህር ጉዳይ ይዋጋሉ የሚል ወሬ እሰማለሁ፤ ነገር ግን በይፋ የሰማሁት ነገር የለም" ብለው" ሶማሊያ በመላው አለም ሉዓላዊነት ላይ የሚፈፀምን ጥሰት አትደግፍም" ሲሉ ተናግረዋል።
ፕሬዚዳንት ሃሰን ሼህ መሐሙድ" ከቀይ ባህር ጋር የሚዋሰኑና የደህንነት ስጋት ያላቸው ሃገራት አንዱ ሌላኛውን ለመረዳት መስማማት አለበት፤ የትኛውም ሃገር የሌላኛውን ሃገር ድንበር መጣስ የለበትም በተጨማሪ ጦርነት ይኖራል ብዬ አላስብም ጥያቄ ያለው ካለ በመነጋገር መፍታት ይቻላል" ብለዋል።
ፕሬዚዳንቱ አልሸባብ እየተዳከመ መሆኑን እና እርምጃ እየተወሰደበት መሆኑን እንደዚውም በቀጣይ ሊደረግ በታሰበው ምርጫ ዙሪያ ከፑንትላንድ እና ጁባላንድ የሚቀርቡ ቅሬታዎች ይፈታሉ ብለው እንደሚያስቡ ገልፀዋል።
ከሶማሊላንድ ጋር ያለውን ችግር ለመቅረፍ ከቀድሞ የሶማሊላንድ አስተዳደር ጋር በተደጋጋሚ ንግግር መደረጉንና አለመሳካቱን ገልፀው በቅርቡ ከሶማሊላንድ ጋር የሚጋጩበት አካባቢን አካቶ የተመሰረተው ክልል ወደ ሶማሊላንድ ዳግም የመመለሱ ነገር የማይሆን ነው ብለዋል።
@TikvahethMagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤134👎12👏9👍6🕊5
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#SamiTech
አዳዲስ ላፕቶፕች ከአንድ ዓመት ዋስትና ጋር!!
@samcomptech
በጥራት፣ በብራንድና በባትሪ ቆይታ አስተማማኝ የሆኑ የተለያዩ ሞዴል ላፕቶፖች በፈለጉት ስክሪን መጠን፣ ኮር አይ እና ጀነሬሽን አሉን።
ላፕቶፕ ከመገዛትዎ በፊት ማወቅ ያለባችሁን ወሳኝ ነገሮች እናስረዳለን። በላፕቶፖቻችን ጥራት ላይ አንደራደርም!
ለቢሮዎች፣ ለተማሪዎች፣ ለዲዛይን ባለሙያዎች፣ ለጌመሮች ወ.ዘ.ተ. ሁሉም አሉን።
የዕቃዎች ዋጋ፣ ዓይነት እና አድራሻ ለማግኘት 👉 @samcomptech
@sww2844
0928442662 / 0940141114
Telgram
👇
https://www.tg-me.com/samcomptech

❤18
🔥በመሀል ፒያሳ ከአራዳ ፓርክ ትይዩ ከወዳጅነት ፓርክ እንዲሁም አብርሆት ቤተ መፅሀፍት በቅርብ ርቀት ላይ
🌟ለ15 ቤቶች ብቻ በማስታወቅያ ዋጋ ቅንጡ አፓርትመንቶች ቀረበልዎት
🏡ከባለ አንድ እስከ ባለ ሶስት መኝታ በ 10% ቅድመ ክፍያ ብቻ
ቀሪውን ዘና ብለው የሚከፍሉት
💎 ባለ 1 መኝታ በ 441,000 ብር
💎ባለ 2 መኝታ በ 855,000 ሺ ብር
💎ባለ 3 መኝታ በ 1,170,000 ሺ ብር ቅድመ ክፍያ
ለ 15 ቤቶች ብቻ❗️
- ባሉት ውስን ቀናቶች ለሚመጡ ደንበኞች እስከ 30% የሚደርስ ታላቅ ቅናሽ አቅርበን እየጠበቅኖት ነው
ይደውሉልን
የዘመናዊ መንደራችን አካል ይሁኑ!
☎️0900025097
#telegram (@SamuelMERITRealtor)
#whatsapp

❤8
ዶናልድ ትራምፕ እስራኤልና ሃማስ በጋዛ የመጀመሪያ ዙር የሰላም ስምምነት ላይ መድረሳቸውን አስታወቁ።
ትራምፕ " ሁሉም ታጋቾች ይለቀቃሉ፤ እስራኤልም በስምምነቱ መሰረት ጦሯን ታስወጣለች" ብለዋል።
ሃማስ ስምምነቱ መፈፀሙን አስታውቆ እስራኤል የምትለቃቸውን እስረኞችን ዝርዝር አለማወቁን ገልጿል።
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታኔያሁ " ቀኑ ለእስራኤል ታላቅ ቀን ነው " ብለዋል።
የተኩስ አቁም የእስራኤል መንግስት ስምምነቱን ካፀደቀው በኋላ ወደ ተግባር ይገባል ሲባል ኔታኔያሁ መንግስታቸው ስምምነቱን እንዲያፀድቅ እንደሚሰሩ ገልፀዋል።
የእስራኤል ሃማስ ጦርነት ከተጀመረ ድፍን ሁለት አመት ሲያልፈው በጥቅምት 7, 2023 ሃማስ እስራኤል ላይ ጥቃት ፈፅሞ 1200 እስራኤላውያንን ከገደለ በኋላ ጦርነቱ ወደ ቀጣናው ሰፍቶ ነበር።
እስራኤል በጋዛ በፈፀመችው ጥቃት ከ67 ሺህ በላይ ሰዎችን ገድላለች።
ስምምነቱን ተከትሎ በጋዛ ደስታ ሞልቷል ሲባል እስራኤል ስምምነቱን ባፀደቀች በ24 ሰዓት ውስጥ ጦሯን ከጋዛ ታስወጣለች ተብሏል።
እስራኤል ጦሯን ባስወጣች በ72 ሰዓት ውስጥም ሃማስ የያዛቸውን ታጋቾች ይለቃል። በተጨማሪ ወደ ጋዛ እርዳታ እንዲገባ ይደረጋል ተብሏል።
በታጋቾቹ ምትክም እስራኤል የያዘቻቸውን የፍልስጤም ታሳሪዎችን ትለቃለች። የእስራኤል ጦርም ስምምነቱን በበጎ እንደሚቀበለው አስታውቋል።
በስምምነቱ የሃማስ ትጥቅ መፍታትን እና የጋዛ ቀጣይ አስተዳደርን በተመለከተ የተደረሰ ስምምነት ስለመኖሩ አልተገለፀም።
መረጃው የቢቢሲ እና አሶሼትድ ፕሬስ ነው።

❤73🕊11👍4🤔1
ኬንያ ክሪፕቶከረንሲን የተመለከተ ህግ ልታወጣ ነው።
የኬንያ ፓርላማ የቨርቹዋል ንብረት አገልግሎት ሰጪዎችን የሚመለከት የህግ ማዕቀፍ አፅድቋል።
ይህንንም ተከትሎ ክሪፕቶከረንሲን የተመለከተው ማዕቀፍ ህግ ሆኖ እንዲወጣ ለፊርማ ወደ ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ በመጪዎቹ ሳምንታት ይላካል።
በማዕቀፉ የኬንያ ማዕከላዊ ባንክና የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ዲጂታል ንብረቶችን የመቆጣጠር ኃላፊነት ሲሰጣቸው የገንዘብ ቢሮው የገንዘብ ማጭበርበር እንዳይፈጠር የሚረዱ መመሪያዎችንና አሰራሮችን ያወጣል።
ማዕቀፉ በዘርፉ የሚሰሩ የሃገር ውስጥና የውጪ ሃገር ተቋማት ፈቃድ የሚሰጥበትን አሰራር ሲያስቀምጥ ህግ ሆኖ ለመውጣት የፕሬዚዳንቱ ፊርማ ብቻ ቀርቶታል።
ህጉ ኬንያ በአፍሪካ ክሪፕቶከረንሲን የተመለከተ የተሟላ ህግ ካላቸው ሃገራት ውስጥ በቀዳሚነት ያስቀምጣታል ተብሎ ሲጠበቅ በዘርፉ ተፎካካሪ ያደርጋታልም ተብሏል።
የክሪፕቶከረንሲን መምጣት ተከትሎ በርካታ ሃገራት ነገሩን በበጎ ለመጠቀም የሚሆኑ መመሪያዎችን እያወጡ ሲሆን በአፍሪካ ናይጄሪያ እና ደቡብ አፍሪካ ጥሩ እየሄዱበት ያሉ ሃገራት ናቸው።
ክሪፕቶከረንሲን በኃላፊነት ለመጠቀም ህግ የሚያወጡ ሃገራት እንዳሉ ሁሉ ከነጭራሹ መጠቀምን የሚከለክሉ እንደ ሞሮኮ ያሉ ሃገራትም አልጠፉም።
ከብሎክቼይን ቴክኖሎጂ መምጣት ጋር ተያይዞ ብቅ ያለው ክሪፕቶከረንሲን በበጎ ለመጠቀም ጥናት እና ሳይንስን መሰረት ያደረጉ ውሳኔዎች መሰጠት ይኖርበታል።
መረጃው የተገኘው ከኦል አፍሪካና ከቴክ ዊዝ ነው።

❤64👍9
#SafaricomEthiopia
የሳፋሪኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ እና የቮዳኮም ከፍተኛ የቦርድ አመራሮች ከኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ አመራሮች ጋር ውይይት አድርገዋል።
በውይይቱ የገንዘብ ሚኒስቴር አህመድ ሺዴ፣ የብሔራዊ ባንክ ገዢ እዮብ ተካልኝ(ዶ/ር) እንደዚሁም የቴሌኮም ፈቃድ ሰጪ ከሆነው የኢትዮጵያ ቴሌኮሚዩኒኬሽን ባለስልጣን ዳይሬክተር ባልቻ ሬባ ተገኝተዋል።
ከሰሞኑ የአለም ባንክ የኢትዮጵያ የቴሌኮም ዘርፍን በተመለከተ ባወጣው ሪፖርት በመንግስታዊው ኢትዮ ቴሌኮም እና በሳፋሪኮም መካከል ፍትሃዊ ውድድር አለመኖሩን መግለፁ ይታወሳል።
በ2013 850 ሚሊየን ዶላር ክፍያ በመክፈል በመክፈል የኢትዮጵያን የቴሌኮም ገበያ የተቀላቀለው ሳፋሪኮም በየወሩ ከሞባይል ተርሚኔሽን ምጣኔ የተነሳ 1.6 ሚሊየን ዶላር እንደሚያጣ ሪፖርተ አሳይቷል።
በሪፖርቱ ኢትዮ ቴሌኮም በተቆጣጣሪ አካሉ ከተቀመጠው ምጣኔ በታች ለድምፅ ጥሪ እንደሚያስከፍል ያሳየው ሪፖርቱ ይህም ሳፋሪኮም ወደ ኢትዮ ቴሌኮም በሚደረጉ ጥሪዎች ላይ ኪሳራ እንዲገጥመው ማድረጉን አመላክቷል።
አለም ባንክ ይህንን ፍትሃዊ ያልሆነ ውድድር በተመለከተ ተቆጣጣሪ አካሉ እርምጃ እንዲወስድ ጠይቋል።
አለም ባንክ ባለፈው በጀት አመት ኢትዮ ቴሌኮም ከሳፋሪኮም 12 እጥፍ የበለጠ ትርፍ ማስመዝገቡን አስታውቋል።
እንደ ሪፖርቱ በ2024 ሳፋሪኮም 325 ሚሊየን ዶላር ማጣቱን የገለፀው ሪፖርቱ በዚሁ በጀት አመት ያገኘው አመታዊ ገቢ የፈቃድ ክፍያውን እንኳን አይሸፍንም ብሏል።
የሳፋሪኮም አመራሮች ከከፍተኛ ባለስልጣናቱ ጋር ባደረጉት ውይይት የቴሌኮም ቁጥጥር ምህዳርን በተመለከተ ውይይት ተደርጓል።
ውይይቱም የቴሌኮም ተቋሙ የኢትዮጵያን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ለመደገፍ ያለውን ቁርጠኝነት ያሳየ ነው።
መረጃው ከሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ገጽ እና ከሪፖርተር የተገኘ ነው።

❤74🤔10👍4🕊2🤬1🤝1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ከአሜሪካ የመጡ ኦርጅናል የፉርማሲ ብራንድ የMakeUp እቃዋችን ለምትፈልጉ @smoochcosmo page አይታችሁታል??
በጅምላ ወስዳችሁ አትርፉችሁ ለምትሸጡ ሱቆች በሚገርም የwholesale ዋጋዋች አቅርበንላችሗል! ግለሰቦችንም ከmarket በደንብ ባነሰ ዋጋ እናስተናግዳለን!
መደወል እና ማዘዝ ለምትፈልጉ call/Text ☎️ 𝟎𝟗𝟕𝟑𝟏𝟓𝟕𝟕𝟕𝟕 @smoochcosmocontact ወይም በtelegram በ📱𝟎𝟗𝟐𝟏𝟔𝟐𝟑𝟕𝟑𝟕 @hilluuuu ጻፉልን! እናመሰግናለን!
https://www.tg-me.com/SmoochCosmo
በጅምላ ወስዳችሁ አትርፉችሁ ለምትሸጡ ሱቆች በሚገርም የwholesale ዋጋዋች አቅርበንላችሗል! ግለሰቦችንም ከmarket በደንብ ባነሰ ዋጋ እናስተናግዳለን!
መደወል እና ማዘዝ ለምትፈልጉ call/Text ☎️ 𝟎𝟗𝟕𝟑𝟏𝟓𝟕𝟕𝟕𝟕 @smoochcosmocontact ወይም በtelegram በ📱𝟎𝟗𝟐𝟏𝟔𝟐𝟑𝟕𝟑𝟕 @hilluuuu ጻፉልን! እናመሰግናለን!
https://www.tg-me.com/SmoochCosmo
❤16👎3
#UN #AI
ተመድ የሰው ሰራሽ አስተውህሎትን በተመለከተ ያሉ ክፍተቶችን ለመሙላት ሁለት ዘርፉን የተመለከቱ የአስተዳደር አካላትን መስርቷል።
ሁለቱ አካላት "The Global Dialogue on AI Governance " እና "Independent International Scientific Panel on AI" ይሰኛሉ።
የሰው ሰራሽ አስተውህሎት በአሁኑ ጊዜ በእጅጉ ፈጣን ዕድገት እያመጣ ሲሆን ቴክኖሎጂውን በኃላፊነት እና አካታች በሆነ መልኩ ለመጠቀም የሚያስችሉ አለም አቀፍ ተቋማት ግን የሉም።
ተመድ 118 ሀገራት የሰው ሰራሽ አስተውህሎትን የተመለከቱ ምንም አይነት ኢንሼቲቭ ውስጥ የሉም ሲል ፥ ቴክኖሎጂውን ለማስተዳደር የሚሆን ዓለም አቀፍ ህግም የለም ብሏል።
የተመድ ዋና ፀሃፊ፥ ቴክኖሎጂው በብዙ ዘርፍ የሰዎችን ህይወት እየለወጠ መሆኑን ተናግረው በሃላፊነት በመጠቀም በኩል ግን ክፍተቶች እንዳሉ ተናግረዋል።
"The Global Dialogue on AI Governance" የተባለው የተመድ አካል የመንግስታት፣ የኢንዱስትሪዎች፣ የሲቪል ማህበረሰብና የሳይንቲስቶች ፎረም ይሆናል ሲባል የሰው ሰራሽ አስተውህሎትን ለማስተዳደር የሚሆኑ የጋራ መንገዶች ይጋሩበታል ተብሏል።
ሁለተኛው አካል "The Independent International Scientific Panel on AI" በበኩሉ የሰው ሰራሽ አስተውህሎት ስጋቶች እና ዕድሎችን የተመለከቱ ሃሳቦችን የሚያቀርቡ 40 ባለሙያዎችን ይይዛል።
ሁለቱ አካላት ቴክኖሎጂውን ሃገራት እና ተቋማት በሃላፊነት እንዲጠቀሙ ከማስቻል በተጨማሪ በዘርፉ ያለውን ክፍተት ይሞላሉ ተብሎ ተስፋ ተሰንቋል።
መረጃው ከወርልድ ኢኮኖሚክ ፎረም የተገኘ ነው
@Tikvahethmagazine

❤34👏4🤔2
ሆቴሎች ባህላዊ ምግቦችን በምግብ ዝርዝራቸው እንዲያቀርቡ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ።
በሀገራችን በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ ባህላዊ ምግቦችን በባለኮኮብ ሆቴሎች በምግብ ዝርዝር ላይ ለማቅረብ እየሰራው ነው ሲል የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት አስታወቀ።
ኢንስቲትዩቱ 205 የተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦች ባህላዊ ምግቦች እና ጠላ፣ ጠጅ እና አረቄን ሳይጨምር 15 ዓይነት ባህላዊ የመጠጥ አይነቶችን እንዳጠናም ገልጿል።
የማሰልጠኛ ኢንስቲትዩቱ የጥናትና ምርምር ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ይታሰብ ስዩም ባህላዊ ምግቦችና መጠጦች ሀገር በቀል በሆነ እውቀት ይዘታቸው ተጠብቆ ፣ ተመዝግቦ በባለሙያዎች ተደግፎ እንደተቋም እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

❤94👎33🤣22👍8🤔7