Telegram Web Link
🔥በመሀል ፒያሳ ከአራዳ ፓርክ ትይዩ ከወዳጅነት ፓርክ እንዲሁም አብርሆት ቤተ መፅሀፍት በቅርብ ርቀት ላይ

🌟ለ15 ቤቶች ብቻ በማስታወቅያ ዋጋ ቅንጡ አፓርትመንቶች ቀረበልዎት

🏡ከባለ አንድ እስከ ባለ ሶስት መኝታ በ 10% ቅድመ ክፍያ ብቻ
ቀሪውን ዘና ብለው የሚከፍሉት

💎 ባለ 1 መኝታ በ 441,000 ብር
💎ባለ 2 መኝታ በ 855,000 ሺ ብር
💎ባለ 3 መኝታ በ 1,170,000 ሺ ብር ቅድመ ክፍያ

ለ 15 ቤቶች ብቻ❗️

- ባሉት ውስን ቀናቶች ለሚመጡ ደንበኞች እስከ 30% የሚደርስ ታላቅ ቅናሽ አቅርበን እየጠበቅኖት ነው

ይደውሉልን
የዘመናዊ መንደራችን አካል ይሁኑ!

☎️0900025097

#telegram (@SamuelMERITRealtor)
#whatsapp
8
ዶናልድ ትራምፕ እስራኤልና ሃማስ በጋዛ የመጀመሪያ ዙር የሰላም ስምምነት ላይ መድረሳቸውን አስታወቁ።

ትራምፕ " ሁሉም ታጋቾች ይለቀቃሉ፤ እስራኤልም በስምምነቱ  መሰረት ጦሯን ታስወጣለች" ብለዋል።

ሃማስ ስምምነቱ መፈፀሙን አስታውቆ እስራኤል የምትለቃቸውን እስረኞችን ዝርዝር አለማወቁን ገልጿል።

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታኔያሁ " ቀኑ ለእስራኤል ታላቅ ቀን ነው " ብለዋል።

የተኩስ አቁም የእስራኤል መንግስት ስምምነቱን ካፀደቀው በኋላ ወደ ተግባር ይገባል ሲባል ኔታኔያሁ መንግስታቸው ስምምነቱን እንዲያፀድቅ እንደሚሰሩ ገልፀዋል።

የእስራኤል ሃማስ ጦርነት ከተጀመረ ድፍን ሁለት አመት ሲያልፈው በጥቅምት 7, 2023 ሃማስ እስራኤል ላይ ጥቃት ፈፅሞ 1200 እስራኤላውያንን ከገደለ በኋላ ጦርነቱ ወደ ቀጣናው ሰፍቶ ነበር።

እስራኤል በጋዛ በፈፀመችው ጥቃት ከ67 ሺህ በላይ ሰዎችን ገድላለች።

ስምምነቱን ተከትሎ በጋዛ ደስታ ሞልቷል ሲባል እስራኤል ስምምነቱን ባፀደቀች በ24 ሰዓት ውስጥ ጦሯን ከጋዛ ታስወጣለች ተብሏል።

እስራኤል ጦሯን ባስወጣች በ72 ሰዓት ውስጥም ሃማስ የያዛቸውን ታጋቾች ይለቃል። በተጨማሪ ወደ ጋዛ እርዳታ እንዲገባ ይደረጋል ተብሏል።

በታጋቾቹ ምትክም እስራኤል የያዘቻቸውን የፍልስጤም ታሳሪዎችን ትለቃለች። የእስራኤል ጦርም ስምምነቱን በበጎ እንደሚቀበለው አስታውቋል።

በስምምነቱ የሃማስ ትጥቅ መፍታትን እና የጋዛ ቀጣይ አስተዳደርን በተመለከተ የተደረሰ ስምምነት ስለመኖሩ አልተገለፀም።

መረጃው የቢቢሲ እና አሶሼትድ ፕሬስ ነው።

@TikvahethMagazine
73🕊11👍4🤔1
ኬንያ ክሪፕቶከረንሲን የተመለከተ ህግ ልታወጣ ነው።

የኬንያ ፓርላማ የቨርቹዋል ንብረት አገልግሎት ሰጪዎችን የሚመለከት የህግ ማዕቀፍ አፅድቋል።

ይህንንም ተከትሎ ክሪፕቶከረንሲን የተመለከተው ማዕቀፍ ህግ ሆኖ እንዲወጣ ለፊርማ ወደ ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ በመጪዎቹ ሳምንታት ይላካል።

በማዕቀፉ የኬንያ ማዕከላዊ ባንክና የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ዲጂታል ንብረቶችን የመቆጣጠር ኃላፊነት ሲሰጣቸው የገንዘብ ቢሮው የገንዘብ ማጭበርበር እንዳይፈጠር የሚረዱ መመሪያዎችንና አሰራሮችን ያወጣል።

ማዕቀፉ በዘርፉ የሚሰሩ የሃገር ውስጥና የውጪ ሃገር ተቋማት ፈቃድ የሚሰጥበትን አሰራር ሲያስቀምጥ ህግ ሆኖ ለመውጣት የፕሬዚዳንቱ ፊርማ ብቻ ቀርቶታል።

ህጉ ኬንያ በአፍሪካ ክሪፕቶከረንሲን የተመለከተ የተሟላ ህግ ካላቸው ሃገራት ውስጥ በቀዳሚነት ያስቀምጣታል ተብሎ ሲጠበቅ በዘርፉ ተፎካካሪ ያደርጋታልም ተብሏል።

የክሪፕቶከረንሲን መምጣት ተከትሎ በርካታ ሃገራት ነገሩን በበጎ ለመጠቀም የሚሆኑ መመሪያዎችን እያወጡ ሲሆን በአፍሪካ ናይጄሪያ እና ደቡብ አፍሪካ ጥሩ እየሄዱበት ያሉ ሃገራት ናቸው።

ክሪፕቶከረንሲን በኃላፊነት ለመጠቀም ህግ የሚያወጡ ሃገራት እንዳሉ ሁሉ ከነጭራሹ መጠቀምን የሚከለክሉ እንደ ሞሮኮ ያሉ ሃገራትም አልጠፉም።

ከብሎክቼይን ቴክኖሎጂ መምጣት ጋር ተያይዞ ብቅ ያለው ክሪፕቶከረንሲን በበጎ ለመጠቀም ጥናት እና ሳይንስን መሰረት ያደረጉ ውሳኔዎች መሰጠት ይኖርበታል።

መረጃው የተገኘው ከኦል አፍሪካና ከቴክ ዊዝ ነው።

@TikvahethMagazine
64👍9
#SafaricomEthiopia

የሳፋሪኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ እና የቮዳኮም ከፍተኛ የቦርድ አመራሮች ከኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ አመራሮች ጋር ውይይት አድርገዋል።

በውይይቱ የገንዘብ ሚኒስቴር አህመድ ሺዴ፣ የብሔራዊ ባንክ ገዢ እዮብ ተካልኝ(ዶ/ር) እንደዚሁም የቴሌኮም ፈቃድ ሰጪ ከሆነው የኢትዮጵያ ቴሌኮሚዩኒኬሽን ባለስልጣን ዳይሬክተር ባልቻ ሬባ ተገኝተዋል።

ከሰሞኑ የአለም ባንክ የኢትዮጵያ የቴሌኮም ዘርፍን በተመለከተ ባወጣው ሪፖርት በመንግስታዊው ኢትዮ ቴሌኮም እና በሳፋሪኮም መካከል ፍትሃዊ ውድድር አለመኖሩን መግለፁ ይታወሳል።

በ2013 850 ሚሊየን ዶላር ክፍያ በመክፈል በመክፈል የኢትዮጵያን የቴሌኮም ገበያ የተቀላቀለው ሳፋሪኮም በየወሩ ከሞባይል ተርሚኔሽን ምጣኔ የተነሳ 1.6 ሚሊየን ዶላር እንደሚያጣ ሪፖርተ አሳይቷል።

በሪፖርቱ ኢትዮ ቴሌኮም በተቆጣጣሪ አካሉ ከተቀመጠው ምጣኔ በታች ለድምፅ ጥሪ እንደሚያስከፍል ያሳየው ሪፖርቱ ይህም ሳፋሪኮም ወደ ኢትዮ ቴሌኮም በሚደረጉ ጥሪዎች ላይ ኪሳራ እንዲገጥመው ማድረጉን አመላክቷል።

አለም ባንክ ይህንን ፍትሃዊ ያልሆነ ውድድር በተመለከተ ተቆጣጣሪ አካሉ እርምጃ እንዲወስድ ጠይቋል።

አለም ባንክ ባለፈው በጀት አመት ኢትዮ ቴሌኮም ከሳፋሪኮም 12 እጥፍ የበለጠ ትርፍ ማስመዝገቡን አስታውቋል።

እንደ ሪፖርቱ በ2024 ሳፋሪኮም 325 ሚሊየን ዶላር ማጣቱን የገለፀው ሪፖርቱ በዚሁ በጀት አመት ያገኘው አመታዊ ገቢ የፈቃድ ክፍያውን እንኳን አይሸፍንም ብሏል።

የሳፋሪኮም አመራሮች ከከፍተኛ ባለስልጣናቱ ጋር ባደረጉት ውይይት የቴሌኮም ቁጥጥር ምህዳርን በተመለከተ ውይይት ተደርጓል።

ውይይቱም የቴሌኮም ተቋሙ የኢትዮጵያን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ለመደገፍ ያለውን ቁርጠኝነት ያሳየ ነው።

መረጃው ከሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ገጽ እና ከሪፖርተር የተገኘ ነው።

@TikvahethMagazine
74🤔10👍4🕊2🤬1🤝1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ከአሜሪካ የመጡ ኦርጅናል የፉርማሲ ብራንድ የMakeUp እቃዋችን ለምትፈልጉ @smoochcosmo page አይታችሁታል??
በጅምላ ወስዳችሁ አትርፉችሁ ለምትሸጡ ሱቆች በሚገርም የwholesale ዋጋዋች አቅርበንላችሗል! ግለሰቦችንም ከmarket በደንብ ባነሰ ዋጋ እናስተናግዳለን!
መደወል እና ማዘዝ ለምትፈልጉ call/Text ☎️ 𝟎𝟗𝟕𝟑𝟏𝟓𝟕𝟕𝟕𝟕
@smoochcosmocontact ወይም በtelegram በ📱𝟎𝟗𝟐𝟏𝟔𝟐𝟑𝟕𝟑𝟕 @hilluuuu ጻፉልን! እናመሰግናለን!
https://www.tg-me.com/SmoochCosmo
16👎3
#UN #AI

ተመድ የሰው ሰራሽ አስተውህሎትን በተመለከተ ያሉ ክፍተቶችን ለመሙላት ሁለት ዘርፉን የተመለከቱ የአስተዳደር አካላትን መስርቷል።

ሁለቱ አካላት "The Global Dialogue on AI Governance " እና "Independent International Scientific Panel on AI" ይሰኛሉ።

የሰው ሰራሽ አስተውህሎት በአሁኑ ጊዜ በእጅጉ ፈጣን ዕድገት እያመጣ ሲሆን ቴክኖሎጂውን በኃላፊነት እና አካታች በሆነ መልኩ ለመጠቀም የሚያስችሉ አለም አቀፍ ተቋማት ግን የሉም።

ተመድ 118 ሀገራት የሰው ሰራሽ አስተውህሎትን የተመለከቱ ምንም አይነት ኢንሼቲቭ ውስጥ የሉም ሲል ፥ ቴክኖሎጂውን ለማስተዳደር የሚሆን ዓለም አቀፍ ህግም የለም ብሏል።

የተመድ ዋና ፀሃፊ፥ ቴክኖሎጂው በብዙ ዘርፍ የሰዎችን ህይወት እየለወጠ መሆኑን ተናግረው በሃላፊነት በመጠቀም በኩል ግን ክፍተቶች እንዳሉ ተናግረዋል።

"The Global Dialogue on AI Governance" የተባለው የተመድ አካል የመንግስታት፣ የኢንዱስትሪዎች፣ የሲቪል ማህበረሰብና የሳይንቲስቶች ፎረም ይሆናል ሲባል የሰው ሰራሽ አስተውህሎትን ለማስተዳደር የሚሆኑ የጋራ መንገዶች ይጋሩበታል ተብሏል።

ሁለተኛው አካል "The Independent International Scientific Panel on AI" በበኩሉ የሰው ሰራሽ አስተውህሎት ስጋቶች እና ዕድሎችን የተመለከቱ ሃሳቦችን የሚያቀርቡ 40 ባለሙያዎችን ይይዛል።

ሁለቱ አካላት ቴክኖሎጂውን ሃገራት እና ተቋማት በሃላፊነት እንዲጠቀሙ ከማስቻል በተጨማሪ በዘርፉ ያለውን ክፍተት ይሞላሉ ተብሎ ተስፋ ተሰንቋል።

መረጃው ከወርልድ ኢኮኖሚክ ፎረም የተገኘ ነው

@Tikvahethmagazine
34👏4🤔2
ሆቴሎች ባህላዊ ምግቦችን በምግብ ዝርዝራቸው እንዲያቀርቡ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ።

በሀገራችን በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ ባህላዊ ምግቦችን በባለኮኮብ ሆቴሎች በምግብ ዝርዝር ላይ ለማቅረብ እየሰራው ነው ሲል የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት አስታወቀ።

ኢንስቲትዩቱ  205 የተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦች ባህላዊ ምግቦች  እና  ጠላ፣ ጠጅ እና አረቄን ሳይጨምር 15 ዓይነት ባህላዊ የመጠጥ አይነቶችን እንዳጠናም ገልጿል።

የማሰልጠኛ ኢንስቲትዩቱ የጥናትና ምርምር ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ይታሰብ ስዩም ባህላዊ ምግቦችና መጠጦች ሀገር በቀል በሆነ እውቀት ይዘታቸው ተጠብቆ ፣ ተመዝግቦ በባለሙያዎች ተደግፎ  እንደተቋም  እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። 

@TikvahethMagazine
94👎33🤣22👍8🤔7
በዓመት ከሚያስፈልገው የኮንዶም መጠን ወደ ሀገር እየገባ ያለው 40 በመቶው ብቻ መሆኑ ተገለጸ።

በኢትዮጵያ በዓመት ከ270 እስከ 300 ሚሊየን ኮንዶም ያስፈልጋል ቢባልም ወደ አገር ውስጥ የሚገባው ከ1መቶ ሚሊየን በታች ወይም 40 በመቶ ብቻ መሆኑ ተገልጿል።

ከዚህ ቀደም ወደ አገር ውስጥ በሚገባ የኮንዶም ምርት ላይ የሚጣሉ የቀረጥ፤ የኤክሳይዝም ሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ አሁን ላይ በመነሳታቸው የግል አስመጪዎች በዘርፉ እንዲሳተፉ አበታች ነው ተብሏል።

ይህ የተገለጸው ይህ የተባለው ኤ ኤች ኤፍ ኢትዮጵያ ከጤና ሚኒስቴር ፣ ከህክምና ግብዓት አምራቾች፣ አከፋፋዮች፣ እንዲሁም ከሌሎች ተቋማት ጋር በመሆን ባዘጋጀው ስለ ኮንዶም ፖሊሲ ፣ጥራት እና የገበያ ስርዓት ላይ ትኩረት ያደረገ ውይይት ላይ ነው።

በመድረኩ የተመዘገቡ የኮንዶም አስመጪዎች እና የህክምና ግብዓት አምራች እና አስመጪዎች ወደ አገር ውስጥ ለሚያስገቡት የኮንዶም ምርት ተጥሎ የነበረው የ35 በመቶ ቀረጥ መነሳቱ ነው የተገለጸው።

በተጨማሪም በሀገር ውስጥ ኮንዶም የሚያመርቱ ፋብሪካዎች ለ5 ዓመት የገቢ ግብር ታክስ እንደማይጠየቁ እና የኮንስትራክሽን ዕቃዎች፣ ስፔር ፓርት እና ሌላ ወደ አገር ውስጥ ማስገባት የሚፈልጉትን ግብዓት ማስገባት ይችላሉ ተብሏል።

ከጊዜ ወደ ጊዜ የኤች አይ ቪ ሥርጭት በሀገራችን እየጨመረ መምጣቱ ሲገለጽ ይህም በአገራችን በየዓመቱ ወደ 8 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች በቫይረሱ እንደሚያዙ መረጃዎች ያሳያሉ።

ዘገባው የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ነው

@TikvahethMagazine
🤣16053👎6😢4🙏1
ሚኒስትሩ ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ እንዳቀረቡ ዘገባ ከተሰራባቸው በኋላ ከኃላፊነታቸው ለቀዋል።

ኡቼ ንናጂ የናይጄሪያ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ሚኒስቴር ሆነው በ2023 የተሾሙ ሹመኛ ነበሩ።

ፕሪሚየም በተባለ ጋዜጣ የሁለት ዓመት ፈጀ በተባለ ምርምራው ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ እንዳቀረቡ በጋዜጣው ከዘገበ በኋላ ከኃላፊነታቸው በገዛ ፈቃዳቸው ለቀዋል።

ሚኒስትሩ፥ በ2023 ሹመት ሲሰጣቸው ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃቸውን ማስገባታቸው ሲነገር እሳቸው ግን በማይክሮባዮሎጂ የመጀመሪያ ድግሪ አለኝ በማለት የምርመራ ዘገባውን አጣጥለዋል።

ሚኒስትሩ ተማርኩ ያሉበት ዩኒቨርሲቲ እሳቸው የመጀመሪያ ድግሪዬን ተመረቅኩ ባሉበት በ1985 ስለመመረቃቸው ምንም ማስረጃ እንደሌለ ለጋዜጣው አሳውቋል ተብሏል።

በዩኒቨርሲቲው ውስጥ ያለ አመራር ንናጂ ወደ ዩኒቨርሲቲው በ1981 እንደገባ ግን ትምህርቱን እንዳልጨረሰ ተናግረዋል።

በናይጄሪያ ሚኒስትሮች መባረራቸውና ከኃላፊነት መልቀቅ ያልተለመደ ነው ሲባል የአሁኑ ፕሬዚዳንት ቦላ ቲኑቡ በ2023 ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ ባለፈው አመት ከሙስና ጋር በተያያዘ ከተነሱት የሰብዓዊ ጉዳዮችና ድህነት ቅነሳ ሚኒስትር ቀጥሎ ንናጂ ከኃላፊነታቸው የለቀቁ ሁለተኛ ሚኒስተር ሆነዋል።

ከቲኑቡ በፊት የነበሩት መሐመዱ ቡሃሪም በ8 አመት የስልጣን ቆይታ ወቅት ያባረሩት ሁለት ሚኒስትሮችን ብቻ ነበር።

የሃሰተኛ የትምህርት ማስረጃውን በተመለከተ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ገለልተኛ ምርመራ እንዲደረግ ጠይቀዋል።

ዘገባው የቢቢሲ ነው።

@TikvahethMagazine
57🤣26👏4👍3💔2🔥1🤔1🕊1
የጃፖን መንግስት በ3.5 ሚልዮን ዶላር የተገዙ 13 ተንቀሳቃሽ ክሊኒክ ያላቸው አምቡላንሶችን በድጋፍ መልክ ማበርከቱን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

@TikvahethMagazine
143🙏29👏6🤔6🤷‍♂5👍3
📍 ፒያሳ ላይ የንግድ ሱቅ
   
    
                  3ኛ ፎቅ
➣  ቅድመ ክፍያ ሲከፍሉ 15% ቅናሽ 3,570,000 ብር ጠቅላላ ዋጋ

100% ለከፈለ 25% ቅናሽ 3,150,000 ብር ጠቅላላ ዋጋ
      
                     2ኛ ፎቅ
➣ ቅድመ ክፍያ ሲከፍሉ 15% ቅናሽ
4,080,000 ብር ጠቅላላ ዋጋ

100% ለከፈለ 25% ቅናሽ 3,600,000 ብር ጠቅላላ ዋጋ

                 1ኛ ፎቅ
➣ ቅድመ ክፍያ ሲከፍሉ 15% ቅናሽ 4,675,000 ብር ጠቅላላ ዋጋ

➣100% ለከፈለ  25% ቅናሽ 4,125,000 ብር ጠቅላላ ዋጋ

                ግራውንድ

➣ቅድመ ክፍያ ሲከፍሉ 15% ቅናሽ 5,950,000 ብር ጠቅላላ ዋጋ

100% ለከፈለ 25% ቅናሽ 5,250,000 ብር ጠቅላላ ዋጋ

ለበለጠ መረጃ
         👇
☎️
+251986687513

WhatsApp:- +251986687513
Email:-
[email protected]
22
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#SamiTech

አዳዲስ ላፕቶፕች ከአንድ ዓመት ዋስትና ጋር!!
@samcomptech

በጥራት፣ በብራንድና በባትሪ ቆይታ አስተማማኝ የሆኑ የተለያዩ ሞዴል ላፕቶፖች በፈለጉት ስክሪን መጠን፣ ኮር አይ እና ጀነሬሽን አሉን።

ላፕቶፕ ከመገዛትዎ በፊት ማወቅ ያለባችሁን ወሳኝ ነገሮች እናስረዳለን። በላፕቶፖቻችን ጥራት ላይ አንደራደርም!

ለቢሮዎች፣ ለተማሪዎች፣ ለዲዛይን ባለሙያዎች፣ ለጌመሮች ወ.ዘ.ተ. ሁሉም አሉን።

የዕቃዎች ዋጋ፣ ዓይነት እና አድራሻ ለማግኘት 👉 @samcomptech

@sww2844

0928442662 / 0940141114

Telgram

      👇
https://www.tg-me.com/samcomptech
9
TIKVAH-MAGAZINE
ዶናልድ ትራምፕ እስራኤልና ሃማስ በጋዛ የመጀመሪያ ዙር የሰላም ስምምነት ላይ መድረሳቸውን አስታወቁ። ትራምፕ " ሁሉም ታጋቾች ይለቀቃሉ፤ እስራኤልም በስምምነቱ  መሰረት ጦሯን ታስወጣለች" ብለዋል። ሃማስ ስምምነቱ መፈፀሙን አስታውቆ እስራኤል የምትለቃቸውን እስረኞችን ዝርዝር አለማወቁን ገልጿል። የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታኔያሁ " ቀኑ ለእስራኤል ታላቅ ቀን ነው " ብለዋል። የተኩስ…
#Update

የእስራኤል መንግሥት የተኩስ ማቆም እና ታጋቾችን እና እስረኞችን ወደ መፍታት የሚያመራውን የጋዛ ስምምነት የመጀመሪያ ምዕራፍ አጽድቋል።

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ አርብ ዕለት በኤክስ ገጻቸው ላይ "መንግሥት አሁን ሁሉንም ታጋቾች (በሕይወት ያሉትን እና የሞቱትን) የሚፈቱበትን ማዕቀፍ አጽድቋል" ሲሉ ጽፈዋል።

የእስራኤል ጦር 53 በመቶ ጋዛን ወደ ሚቆጣጠርበት መስመር ይወጣል።
ሐማስ በሕይወት ያሉ 20 ታጋቾችን በ72 ሰዓታት ውስጥ መልቀቅ አለበት። በመቀጠልም የሞቱትን የ28 ታጋቾች አስከሬን መመለስ ይጠበቅበታል።

እስራኤል በበኩሏ 250 የሚጠጉ ፍልስጤማውያን የዕድሜ ልክ እስረኞችን እና ከጋዛ የተያዙ አንድ ሺህ 700 እስረኞችን እንደምትለቅ የፍልስጤም ምንጭ መግለጹን ቢቢሲ ዘግቧል።

@TikvahethMagazine
56👏10🕊7
የ2025 የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸናፊ ዛሬ ይፋ ይሆናል።

ከ1901 ጀምሮ ለ105 ጊዜ የተሰጠው የኖቤል የሰላም ሽልማት እስካሁን 92 ወንዶች፣ 19 ሴቶችና 28 ተቋማት አሸንፈዋል።

ሽልማቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰጠው ለፍሬድሪክ ፓሲና ለቀይ መስቀል መስራቹ ሄነሪ ዱራንት ነበር።

በተደጋጋሚ የኖቤል የሰላም ሽልማት ላቋምኳቸው ጦርነቶች ይገባኛል ሲሉ የቆዩት ፕሬዚዳንት ትራምፕ ለሽልማቱ በእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታኔያሁና በፓኪስታን መታጨታቸው ይታወሳል።

በዚህ አመት 338 እጩዎች ለሽልማቱ ሲቀርቡ 94 ያህሉ ተቋማት መሆናቸው ተገልጿል።

በኖቤል የሰላም ሽልማት ኮሚቴ በኩል እጩዎቹ እነማን እንደሆኑ ያልተገለፀ ሲሆን አሸናፊው ዕውቅናን ጨምሮ ከ1 ሚሊየን ዶላር በላይ የገንዘብ ሽልማትም ይሰጠዋል።

የኖቤል የሰላም ሽልማት ከተጀመረ ወዲህ እንደ ባራክ ኦባማ ያሉ የአሜሪካ መሪዎች ሲያሸንፉ ከአፍሪካ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ፣ ኤለን ጆንሰን ሰርሊፍ ከላይቤሪያ፣ ዋንጋሪ ማታይ ከኬንያ ፣ ኮፊ አናን ከጋና፣ አንዋር ሳዳት ከግብፅና ማንዴላ ከደቡብ አፍሪካ ማሸነፋቸው ይታወሳል።

ከግለሰቦች በተጨማሪ ሽልማቱን እንደ የቀይ መስቀል፣ የተመድ የስደተኞች ኮሚሽን፣ የአለም ምግብ ፕሮግራምና የኒውኪሊየር መሳሪያን የማጥፋት ዘመቻ ያሉ ተቋማት አሸንፈዋል።

የዘንድሮው የኖቤል ሽልማት በተለያዩ ዘርፎች አሸናፊዎችን እያሳወቀ ሲሆን በህክምና፣ በፊዚክስና ኬሚስትሪ ዘርፍ ያሸነፉ ተመራማሪዎችም ታውቀዋል።

ዘገባው የCBS ነው።

@TikvahethMagazine
110👎27🕊5👍4😢1
2025/10/22 11:23:15
Back to Top
HTML Embed Code: