Telegram Web Link
የዘንድሮዋ የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸናፊ ማሪያ ማቻዶ ማናት?

ኒኮላስ ማዱሮ በሚያስተዳድሯት በነዳጅ በበለፀገችው ቬንዙዌላ አሉ ከሚባሉ ዋነኛ ተቃዋሚዎች መካከል ማሪያ ኮሪና ማቻዶ ቀዳሚዋ ነች።

ማቻዶ በሃገሯ ዲምክራሲያዊ መብቶች እንዲከበሩ እና ወደ ዲሞክራሲ የሚደረግ ሽግግር ላይ ላደረጉት ትግልም የዘንድሮው የኖቤል የሰላም ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

የ58 ዓመቷ ማቻዶ ውልደቷ በቬንዙዌላ ዋና ከተማ ካራካስ ሲሆን በሙያዋ ኢንዱስትሪያል ኢንጂነር ነች።

በ2023 በነበረው ቅድመ ምርጫ ወቅት ድጋፍ እያገኘች የነበረ ቢሆንም ቢሮ እንዲኖራት ስላልተፈቀደላት በ2024 ምርጫ መሳተፍ አልቻለችም።

ከምርጫው በኋላ ተደብቃ የነበረችው ማቻዶ በኋላ ላይ ተቃውሞ በመጥራቷ ታስራ የነበረ ሲሆን ከዛ በኋላ ተፈትታለች።

በኢኮኖሚው ማቻዶ የቬንዙዌላ የመንግስት ተቋማት ወደ ግል እንዲዞሩ የምትሟገት ስትሆን ይህም የቬኔዙዌላ ዋነኛ የገቢ ምንጭ የሆነው የነዳጅ ተቋምንም ይጨምራል።

ማቻዶ የፖለቲካ ህይወቷን በ2002 ከጀመረች በኋላ በ2014 በነበረው ተቃውሞ ስትሳተፍ ታስራ በሃገር ክህደት ወንጀልም ተከሳ ነበር።

በተደጋጋሚ ስትታሰር የቆየችው ማቻዶ አሁንም በተደጋጋሚ ከማዱሮ አገዛዝ ማስፈራሪያ ቢገጥማትም ሃገሯን ለቃ ሳትሄድ ቆይታለች።

የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸናፊ መሆኗ ከታወቀ በኋላ ማቻዶ በሰጠችው አሰተያየት በደስታ መደንገጧን ተናግራለች።

በርካታ የሰብዓዊ መብት ተቋማትና መንግስታትም ማቻዶ በቬኔዙዌላ እያደረገች ላለችው ትግል ሽልማቱ ይገባታል ብለዋል።

ዘገባው ከሮይተርስ የተወሰደ ነው።

@TikvahethMagazine
140👎21👍1🤬1
"የኖቤል ኮሚቴ ከሰላም በላይ ፖለቲካን እንደሚያስቀድም አሳይቷል"- የኋይት ሃውስ ቃለ አቀባይ

የኋይት ሃውስ ቃለ አቀባይ ስቴቨን ቼኡንግ ዶናልድ ትራምፕ የኖቤል የሰላም ሽልማትን አለማሸነፋቸውን ተከትሎ ባስተላለፉት መልዕክት ኮሚቴው ከሰላም በላይ ፖለቲካን ማስበለጡን አሳይቷል ብለዋል።

ቃለ አቀባዩ " ትራምፕ የሰብዓዊነት ማዕከል ናቸው" በማለት ሌሎች ሊሞክሩ የማይደፍሩትን ነገር አሳክተዋል ሲሉ ገልፀዋል።

ትራምፕ በተደጋጋሚ ላቆምኳቸው ጦርነቶች የሰላም ሽልማት አልተሰጠኝም ሲሉ ዘንድሮ በተለይ የእስራኤል እና ኢራንን ጦርነት በማስቆም እንደዚሁም ደግሞ ከሰሞኑ በጋዛ ለተፈፀመው የሰላም ስምምነት በነበራቸው ሚና ሽልማቱን ይገባኛል ሲሉ በተደጋጋሚ በግልጽ ተናግረው ነበር።

ትራምፕ ኢትዮጵያ እና ግብፅ ያልተዋጉትን ጦርነት ጨምሮ የሰርቢያና ኮሶቮ፣ የአርሜኒያ እና አዘርባጃን እንደዚሁም የህንድ እና ፓኪስታንን ግጭቶች አስቁሜያለሁ ብለው መናገራቸው ይታወሳል።

ዘገባው የአልጄዚራ ነው።

@TikvahethMagazine
🤣25161👎21🤔6👍2
ቡርኪናፋሶ ሲሰልሉ ነበር ያለቻቸውን 8 የሰብዓዊ ተቋም ሰራተኞች ማሰሯን ገለፀች።

ተቋሙ መቀመጫውን በኔዘርላንድስ ያደረገ ነው ሲባል ተይዘው ከታሰሩት ውስጥ የተቋሙ የቡርኪናፋሶ ዳይሬክተርና ምክትሉ እንዳሉበት ተገልጿል።

የሃገሪቱ የደህንነት ሚኒስቴር የግብረ ሰናይ ድርጅቱ " ለብሔራዊ ደህንነታችን ስጋት የሆኑ ወሳኝ የደህንነት መረጃዎችን ሰብስቦ ለውጪ አካላት ሲሰጥ ነበር" ብለዋል።

ከ2019 ጀምሮ በቡርኪናፋሶ ሲሰራ የነበረው ተቋሙ ከሐምሌ ወር ጀምሮ "ያለፈቃድ መረጃ በመሰብሰብ" በሚል የ3 ወር እገዳ እንደጣለበትም ተዘግቧል።

የደህንነት ሚኒስትሩ ተቋሙ ቢታገድም አሁን የተያዙት ሰዎች በድብቅ ስብሰባ ያደርጉ እንደነበርና መረጃ እንደሚሰበስቡ ተናግረዋል።

ተቋሙ በበኩሉ ይሰበሰብ የነበረው መረጃ ሚስጥራዊ እንዳልሆነና ለሰራተኞቹ ደህንነት ተብሎ እንደሚሰበሰብ አስታውቋል።

መረጃው የቢቢሲ ነው።

@TikvahethMagazine
126👏24👍7👎4🤔4😢2🕊2
📍 ፒያሳ ላይ የንግድ ሱቅ
   
    
                  3ኛ ፎቅ
➣  ቅድመ ክፍያ ሲከፍሉ 15% ቅናሽ 3,570,000 ብር ጠቅላላ ዋጋ

100% ለከፈለ 25% ቅናሽ 3,150,000 ብር ጠቅላላ ዋጋ
      
                     2ኛ ፎቅ
➣ ቅድመ ክፍያ ሲከፍሉ 15% ቅናሽ
4,080,000 ብር ጠቅላላ ዋጋ

100% ለከፈለ 25% ቅናሽ 3,600,000 ብር ጠቅላላ ዋጋ

                 1ኛ ፎቅ
➣ ቅድመ ክፍያ ሲከፍሉ 15% ቅናሽ 4,675,000 ብር ጠቅላላ ዋጋ

➣100% ለከፈለ  25% ቅናሽ 4,125,000 ብር ጠቅላላ ዋጋ

                ግራውንድ

➣ቅድመ ክፍያ ሲከፍሉ 15% ቅናሽ 5,950,000 ብር ጠቅላላ ዋጋ

100% ለከፈለ 25% ቅናሽ 5,250,000 ብር ጠቅላላ ዋጋ

ለበለጠ መረጃ
         👇
☎️
+251986687513

WhatsApp:- +251986687513
Email:-
[email protected]
24😢2🤔1
ሹመት እየተሰጠው ያለው የሰው ሰራሽ አስተውህሎት (AI) !

ከሰሞኑ የካዛኪስታን የመንግስት ፈንድ በማዕከላዊ እስያ የመጀመሪያ ነው የተባለለትን የሰው ሰራሽ አስተውህሎት ገለልተኛ የቦርድ ዳይሬክተር አስተዋውቋል።

ሥርዓቱ "SKAI" የሚባል ሲሆን እንደ ፋይናንስ እና አስተዳደር ያሉ የፈንዱ ተግባራት ውሳኔ ላይም ድምፅ መስጠት ይችላል።

ከ2008 ጀምሮ ባሉ የውስጥ ዶክመንቶች መሰልጠኑ ደግሞ ሚዛናዊ ውሳኔ እንዲሰጥ ያደርገዋል ተብሏል።

ካዛኪስታን በሰው ሰራሽ አስተውሎት ላይ ሰፊ ሥራዎችን እየሰራች የምትገኝ ሲሆን የሰው ሰራሽም አስተውህሎት ምርምር ላይ የሚሰራ ዩኒቨርሲቲ መመስረቷም ተገልጿል።

በተመሳሳይ ዜና ከዚህ በፊት አልባኒያ በዓለማችን የመጀመሪያውን የሰው ሰራሽ አስተውህሎት የሆነች ሚኒስትር መሾሟ ይታወሳል።

የሰው ሰራሽ አስተውሎት ሚኒስትር በጠቅላይ ሚኒስትሩ በተሾማበት ወቀትም ሙሉ ለሙሉ ከሙስና ነፃ መሆኑ ተገልፆ ነበር።

የሰው ሰራሽ አስተውሎት ሚኒስትሯ በፓርላማ ንግግር ባደረገችበት ወቅትም " ሰዎችን ለመተካት ሳይሆን ለመርዳት ነው የመጣውት" ብላለች።

ዲዬላ የሚል ስያሜ የተሰጣት ይቺ በሰው ሰራሽ አስተውህሎት የለማች ሚኒስትር  የተሾመችው የሰው ሰራሽ አስተውህሎት ሚኒስትር ተደረጋ ነው።

ፈጣን ለውጥን እያመጣ ያለው የሰው ሰራሽ አስተውህሎት አሁን አሁን በከፍተኛ ውሳኔ ሰጪ ቦታዎች ላይም ጭምር እየገባ ሲሆን አንዳንዶች ነገሩን ከጥቅሙ ይልቅ በስጋትነት እያነሱት ይገኛሉ።

መረጃው የተገኘው ከዩሮ ኒውስ እና ከኤቢሲ ነው።

@TikvahethMagazine
50👎7👍3🤔2😢2🕊1
ተመድ በመላው አለም ያለውን የሰላም ጠባቂ ኃይሉን ቁጥር በ25 በመቶ ሊቀንስ ነው።

ተመድ በመላው አለም ካሰማራቸው የሰላም ጠባቂ ኃይሎች ውስጥ 25 በመቶውን ከአሜሪካ የድጋፍ መቀነስ ጋር በተያያዘ ይቀንሳል ተብሏል።

በ9 አለም አቀፍ ተልዕኮዎች በተመድ ስር ከተሰማሩ 50 ሺህ የፀጥታ ኃይሎች መካከል 14 ሺህ ያህሉ በመጪዎቹ ወራት ወደመጡበት ሃገር ይመለሳሉ ተብሏል።

በሶማሊያ ያለው ተልዕኮ ተጠቂ ነው ሲባል ተመድ በዚህ አመት የተልዕኮው በጀት በ15% ይቀነሳል ተብሏል።

አሜሪካ ባለፈው አመት ለነዚህ ተልዕኮዎች ከ1 ቢሊየን ዶላር በላይ ድጋፍ ስትሰጥ ዘንድሮ 680 ሚሊየን ዶላር ብቻ ለመስጠት ፈቃደኝነቷን መግለጿ ተልዕኮውን እንደጎዳው ተገልጿል።

ተመድ የአሜሪካ ድጋፍ መቀነስን ተከትሎም የ20 በመቶ የስራ ቅነሳ ለማድረግ ማቀዱ ተዘግቧል።

ዘገባው የፍራንስ 24 ነው።

@TikvahethMagazine
28👍3🕊1🤣1
#SocialMedia

የአሜሪካዋ ኒውዮርክ ከተማ ታላላቅ የሚባሉ የማህበራዊ ሚዲያዎችን ህፃናትን ሱስ በማስያዝ ከሳለች።

ከተማዋ ፌስቡክ፣ ጎግል፣ ስናፕቻትና እንደ ቲክቶክ ያሉ የማህበራዊ ሚዲያዎች ህፃናትን ሱስ በማስያዝ አዕምሯዊ ጤናቸውን እየጎዱ ነው በማለት 327 ገፅ ያለው ክስ በፍርድ ቤት አቅርባለች።

በኒውዮርክ ከተማ ከሚኖሩ 8 ሚሊየን ሰዎች ውስጥ 1.8 ሚሊየኑ ህፃናት ናቸው።

የጎግል ቃለ አቀባይ በዩቲዩብ ላይ የተከፈተው ክስ ትክክል አይደለም ሲሉ ዩቲዩብ ሰዎች ቪዲዮ የሚያዩበት እንጂ ከጓደኞቻቸው ጋር የሚገናኙበት የማህበራዊ ሚዲያ አይደለም ብለዋል።

በክሱ 77.3% የሚሆኑት በኒውዮርክ የሚኖሩ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች በቀን ከሶስት ሰዓት በላይ በስክሪን ላይ እንደሚያጠፉ ተገልፆ ይህም የተማሪዎቹን ጤና እየጎዳ ነው ተብሏል።

ከዚሁ ከማህበራዊ ሚዲያ ጋር በተያያዘ ዜና ዴንማርክ ከ15 ዓመት በታች ያሉ ህፃናት ማህበራዊ ሚዲያዎችን እንዳይጠቀሙ እገዳ ለማስቀመጥ እየሰራች ነው።

የዴንማርክ ጠቅላይ ሚኒስትር ሜት ፍሬድሪክሰን ማህበራዊ ሚዲያዎች" የልጆቻችንን ህፃንነት እየሰረቁ" ነው ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሯ የሃገሪቱ ህግ አውጪዎች ከ15 አመት በታች ያሉ ህፃናት ማህበራዊ ሚዲያን እንዳይጠቀሙ እንዲከለክሉ ጠይቀዋል።

በአውሮፓ ህብረት ሃገራት ህፃናት 13 አመት ሳይሞላቸው የማህበራዊ ሚዲያ አካውንት መክፈት እንደማይችሉ ቢቀመጥም ጠቅላይ ሚኒስትሯ 94 በመቶ የዴንማርክ ህፃናት እዚህ ዕድሜ ላይ ሳይደርሱ ይከፍታሉ ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሯ " ህፃናት ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ማየት የሌለባቸውን ነገሮች ያያሉ" ያሉ ሲሆን ይህም ጭንቀትና ድብርትን ጨምሮ ሌሎቸ መዘዞችን እያዋለደ ነው ብለዋል።

ዘገባዎቹ የተገኙት ከዩሮ ኒውስና ከአሌጄዘራ ነው።

@TikvahethMagazine
86👏21👍6🤣6🕊4😢2👎1
ዶናልድ ትራምፕ ከዘንድሮዋ የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸናፊ ማሪያ ማቻዶ ስልክ እንደተደወለላቸው ተናገሩ።

ትራምፕ " የኖቤል ሽልማትን ዛሬ ያሸነፈችው ሰው ደውላልኝ ሽልማቱ ለአንተ ይገባካል ብላኛለች" ሲሉ ተናግረዋል።

ትራምፕ እንደዛ ማድረጓ ጥሩ ነገር ነው ብለው " እንደዛ ከሆነ ስጪኝ ግን አላልኳትም" ሲሉ አዝናኝ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

ትራምፕ ትናንት ምሽት ባደረጉትም ንግግር አመታትን የፈጁ ጦርነቶችን ጨምሮ 8 ጦርነቶችን ማስቆማቸውን ዳግም ተናግረዋል።

ምንም እንኳን ማሪያ ማቻዶን ለሽልማቱ ዕጩ አድርገው ያቀረቡት የወቅቱ የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ መስሪያ ቤት ኃላፊ ማርክ ሩቢዮ ያሉበት የህግ ቡድን ቢሆንም ኋይት ሃውስ የሽልማቱን ውጤት መኮነኑ ይታወሳል።

የሩሲያው ፕሬዚዳንት ፑቲን ሽልማቱ ላይ ጥያቄያቸውን ያነሱ ሲሆን ሽልማቱ ለሰላም ምንም አስተዋፅኦ ያላደረጉ ሰዎች እያሸነፉትም ነው ብለዋል።

ፑቲን "የወቅቱ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት የኖቤል ሽልማት ይገባቸው አይገባቸው አላውቅም፤ ነገር ግን አመታት የፈጁ የተወሳሰቡ ግጭቶችን ፈትተዋል" በማለት በተዘዋዋሪ ሽልማቱ ለትራምፕ እንደሚገባ አንስተዋል።

ትራምፕ የፑቲንን ንግግር ተከትሎም በማህበራዊ ሚዲያቸው " አመሰግናለሁ ፕሬዚዳንት ፑቲን" ብለዋል።

ዘገባው የሲኤንኤን ነው።

@TikvahethMagazine
🤣264111
ሩሲያ በአዘርባጃን ተከስቶ ለነበረው አውሮፕላን አደጋ ምክንያት መሆኗን አመነች።

ባለፈው ዓመት ታህሳስ ወር ከባኩ ተነስቶ ወደ ግሮዝኒ በረራ ላይ የነበረ የአዘርባጃን አየር መንገድ አውሮፕላን ተከስክሶ 38 ሰዎች መሞታቸው ይታወሳል።

ከሰሞኑ ፕሬዚዳንት ፑቲ፥ የአዘርባጃንን ፕሬዚዳንት ኢልሀም አሊዬቭ ባገኙበት ወቅት የአውሮፕላኑ መከስከስ ሀገራቸው የዩክሬን ድሮንን ኢላማ አድርጎ በተኮሰው ሚሳኤል ምክንያት የተከሰተ መሆኑን አምነዋል።

ፑቲን ለተፈጠረው ነገር ይቅርታ ጠይቀው ነገሩ በደንብ እንደሚጣራና አስፈላጊው ማከካሻ እንደሚደረግ አስታውቀዋል።

@TikvaethMagazine
156😢55👍22👏9🕊9👎1🤔1
🤙 ኑሮዎን ፒያሳ ላይ ያድርጉ

➣ ውብ አፓርትመንቶቻችን ለኑሮ ምቹ በሆነችው አዲሲቷ ፒያሳ ላይ እርሰዎን ይጠብቃል

   
     66 ካሬ ባለ 1 መኝታ
                 
➣  40% ሲከፍሉ 20% ቅናሽ  6,072,000 ብር ጠቅላላ ዋጋ

100% ለከፈለ 30% ቅናሽ 5,313,000 ብር ጠቅላላ ዋጋ
      
              2 መኝታ 75 ካሬ
  
➣ 40% ሲከፍሉ 20% ቅናሽ
6,900,000 ብር ጠቅላላ ዋጋ

100% ለከፈለ 30% ቅናሽ 6,037,500 ብር ጠቅላላ ዋጋ

          3 መኝታ 106 ካሬ

➣ 40% ሲከፍሉ 20% ቅናሽ 9,752,000 ብር ጠቅላላ ዋጋ

➣100% ለከፈለ  30% ቅናሽ 8,533,000 ብር ጠቅላላ ዋጋ

❗️ልብ ይበሉ ከላይ የተፃፉት አነስተኛ ካሬዎች ለ ምሳሌ ሲሆኑ ከፍ ያለ ካሬ ማግኜት ትችላላችሁ

ለበለጠ መረጃ
         👇
☎️
+251986687513

WhatsApp:- +251986687513
Email:-
[email protected]
22
ከአሳማ የተወሰደ ጉበት በንቅለ ተከላ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰጠው ግለሰብ ለወራት በህይወት መቆየቱ ተነገረ።

በካንሰርና በሄፓታይተስ ቢ በሽታ የተነሳ ጉበቱ የታመመው ግለሰብ ከሰው መቀበል እንደማይችል ሲታወቅ በተወሰነ መልኩ የዘረ መል ለውጥ የተደረገበት የአሳማ ጉበት በንቅለ ተከላ ተሰጥቶት ነበር።

ሁነቱም በህይወት ያለ ሰው ከአሳማ የተወሰደ ጉበት በንቅለ ተከላ  ሲሰጠው ለመጀመሪያ ጊዜ እንዲሆን አድርጎታል።

በመጀመሪያው ወር ጉበቱ በተገቢው መንገድ ሰርቷል ሲባል በ38ኛው ቀን ግን ከንቅለ ተከላ ጋር በተያያዘ ባጋጠመ ችግር እንዲወጣ ተደርጎ ነበር።

ችግሩ ከተፈታ በኋላ ታማሚው ከንቅለ ተከላው በኋላ በ171ኛ ቀኑ ህይወቱ አልፏል።

የአሳማ አካላት ከሰው ልጅ አካላት ጋር ተቀራራቢ መሆናቸውና የዘረ መል ለውጥ ማድረግ ስለሚቻልባቸውና በብዛት መገኘታቸው ለንቅለ ተከላ አመቺ ናቸው ሲባል በህክምናው አዲስ ተስፋን የፈጠረ ጉዳይም ሆኗል።

ከዚህ በፊትም ከአሳማ ልብ በንቅለ ተከላ የተሰጠው ግለሰብ ከቀዶ ጥገናው 2 ወር በኋላ መሞቱ ይታወሳል።

መረጃው የዘ ኢንዲፔንደንት ነው።

@TikvahethMagazine
40👎12🤔10🤣5👍2
TIKVAH-MAGAZINE
#SIT በሸገር ከተማ እየተገነባ ያለውና ትኩረቱን የህዋ ሳይንስ፣ ኒውኪሊየር ሳይንስና ሰው ሰራሽ አስተውህሎት ላይ ያደረገው ሸገር የቴክኖሎጂ ኢንስቲቲዩት ከዚህ ወር ጀምሮ ተማሪዎችን መቀበል ይጀምራል። ይህ ተቋም የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ብዙ ቢሊየኖችን መድቦ እያስገነባው ያለው ሲሆን በ50 ሄክታር ላይ ያረፈው ተቋም ግንባታውም በኮዬ ፈጬ ክፍለ ከተማ እየተከናወነ ነው። በዚህ ተቋም በልዩ ልዩ…
#Update

የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ የሸገር የቴክኖሎጂ ኢንስቲቲዩትን መርቀው ከፍተዋል።

በሸገር ከተማ ኮዬ ፈጬ ክፍለ ከተማ የተገነባው ኢንስቲቲዩቱ ትኩረቱን የህዋ ሳይንስ፣ የኑውኪሊየር ሳይንስና የሰው ሰራሽ አስተውህሎት ላይ እንደሚያደርግ መነገሩ ይታወሳል።

መረጃው የተገኘው ከኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት ነው።

@TikvahethMagazine
76👎41🤣16👍11
አፍጋኒስታን እና ፓኪስታን በድንበር አካባቢያቸው ግጭት ውስጥ ገብተዋል።

ሁለቱ ሃገራት ግጭት ውስጥ የገቡት ታሊባን ፓኪስታን የአየር ክልሌን ጥሳ ጥቃት ፈፅማለች ካለ በኋላ በወሰደው እርምጃ ነው።

ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ፓኪስታን በአፍጋኒስታን ዋና ከተማ ካቡልና በድንበር ከተማ የአየር ጥቃት የፈፀመች ሲሆን ፓኪስታን የካቡሉ ጥቃት የፓኪስታኑ ታሊባን(TTP) ተብሎ የሚታወቀውን ታጣቂ መሪ ኑር ዋሊ መስሁድን ለመግደል ኢላሚ ያደረገ ነበር ብለዋል።

ታጣቂው በዚህ አመት ብቻ በፓኪስታን በፈፀመው ጥቃት ከ2400 በላይ ሰዎችን ሲገድል ፓኪስታን ታሊባን ለዚህ ታጣቂ ምሽግ ሆኗል ብላ በተደጋጋሚ ስትከስ ነበር።

በድንበር አካባቢ በነበረው ግጭት 58 የፓኪስታን ታጣቂዎች መገደላቸውን ታሊባን ሲገልፅ ፓኪስታን በበኩሏ የሞቱት 23 መሆናቸውን ገልፃ በበኩሏ ከ200 በላይ የታሊባን ጦርና ታጣቂዎችን ገድያለሁ ብላለች።

የሁለቱም ሃገራት ከፍተኛ ባለስልጣናት አንዱ ለሌላኛው ማስጠንቀቂያ እየሰጡ ሲሆን የቀጣናው ሃገራት ወደባሰ ግጭት እንዳይገቡ አስጠንቅቀዋል።

ፓኪስታን ከ1996-2001 ለነበረው የታሊባን መንግስት ዕውቅና ከሰጡ ሶስት ሃገራት አንዷ ስትሆን ከአሜሪካ ጋር በነበራቸው ውጊያም ድጋፍ ለታሊባን አድርጋለች።

በ2021 ታሊባን ወደ ስልጣን ከተመለሰ በኋላ ፓኪስታን TTP ለተሰኘው ታጣቂ መደበቂያ ሰጥታለች በሚልም ፓኪስታን ግንኙነቷን አሻክራለች።

ፓኪስታን ከወራት በፊትም በህንድ ካሽሚር ግዛት ጥቃት ፈፅማ ከህንድ ጋር ግጭት ውስጥ እንደገባች ይታወሳል።

መረጃው የተሰባሰበው ከቢቢሲና አልጄዚራ ነው።

@TikvahethMagazine
28🕊10
2025/10/21 19:50:13
Back to Top
HTML Embed Code: