Telegram Web Link
"የእንጀራ ምጣድ እና ማብሰያ ምድጃ ዝቅተኛ ኢነርጅ አጠቃቀም ብቃት ደረጃን ለማሻሻል በተለያዩ ምርቶች ላይ ልኬት እያከናወንኩ ነው" - የነዳጅና ኢነርጂ ባለሥልጣን

በኃይል አጠቃቀም ብቃታቸው ከፍተኛ ኃይል አባካኝ ተብለው በጥናት ከተለዩ ምርቶች መካከል በሀገር ውስጥ የሚመረቱ እንጀራ ምጣዶችና የማብሰያ ምድጃ ቀዳሚዎቹ ናቸው፡፡

በሀገር ውስጥ የሚመረቱ የእንጀራ ምጣድ እና ማብሰያ ምድጃ ዝቅተኛ ኢነርጅ አጠቃቀም ብቃት ደረጃን ለመሻሻል በተለያዩ ምርቶች ላይ ልኬት የመውሰድ ሥራ እየተሠራ ይገኛል ሲል የነዳጅና ኢነርጂ ባለሥልጣን አስታውቋል።

ብሔራዊ ኢነርጂ ብቃት ስትራቴጂን ለማስፈጸም በባለስልጣን መ/ቤቱ ከተቀረጹ ፕሮግራሞች መካከል የተለጣፊ ምልክት ፕሮግራም (labeling program) ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል ተብሏል።

በዚህም፥ የምርት ስታንዳርድ እና ዝቅተኛ ኢነርጂ አጠቃቀም ብቃት በደረጃዎች ኢንስቲትዊት በ2009 ዓ.ም እና በ2011 ዓ.ም እንዲጸድቅ ተደርጓል፡፡

የደረጃዎቹን መጽደቅ ተከትሎም ሳይንሣዊ አመራረት ዘዴን በልኬት ላይ በተመሠረተ ለመስራት እንዲቻል ከአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ጋር በመተባበር የምጣድ ማሳያ (Prototype) በማስመረት አምራቾች ተደጋጋሚ ስልጠና እንዲያገኙ ተደርጓል ሲል ገልጿል።

ስልጠናውን መሠረት በማድረግ የተመረቱ ምርቶችን በባለስልጣን መ/ቤቱ ላብራቶሪ በማስፈተሸ የተለጣፊ ምልክት የመስጠት ሥራ እየተከናወነ ይገኛል፡፡

አሁን ላይ የተቀመጡ ስታንዳርዶችን በድጋሚ ማየትና መፈተሸ አስፈላጊ በመሆኑ የምርቱን ዝቅተኛ ኢነርጂ አጠቃቀም ደረጃ ለማሻሻል በመስራት ላይ ይገኛል ተብሏል፡፡

@TikvahethMagazine
71🤣26👎2🤬2👍1
ጥቂት ቤቶች የቀሩት!
ሳርቤት ከመቻሬ ሜዳ ፊት ለፊት የሚገኘውን ሆራ አፓርትመንት በ35% ጥሬ ገንዘብ እና 65% የባንክ ፋይናንስ እጅዎ ያስገቡ።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥሮቻችን 0984676767 ወይም 0984767676 በመደወል መረጃዋችን ማግኘት ይችላሉ!!!
8
ሶማሊያ ገለልተኛ የሆነ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን መስርታለች።

በ1993 የሶማሊያ ማዕከላዊ መንግስትን መፍረስ ተከትሎ የሃገሪቱ የሰብዓዊ መብት ሁኔታ በውጪ ገለልተኛ አካላት እና በአለም አቀፍ ተቋማት ቁጥጥር ስር ነበረ።

በዚህ ሳምንት የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ካውንስል ይህንን የመቆጣጣር ኃላፊነቱን ባለማራዘሙ ሶማሊያ የራሷን ብሔራዊ ገለልተኛ ብሔራዊ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን መስርታለች።

ምሰረታው የሶማሊያ ራስን የመቻል ምልክት ተደርጎ ሲወሰድ ፓርላማው የኮሚሽኑን 9 አባላትንም መምረጡና አባላቱ ደግሞ ኮሚሽነር እንደሚመርጡ ተነግሯል።

ዘገባው የዳዋን አፍሪካ ነው።

@TikvahethMagazine
36🙏4🕊4🤔2🤣2
TIKVAH-MAGAZINE
🔈 #የነዋሪዎችድምጽ " መታወቂያ ለማውጣትም ሆነ ለማደስ ከ6 ወር በላይ እየወሰደብን ነው፣ ሌሊት ወረፋ ለመያዝ ስንሄድ በዘራፊዎች እየተደበደብን ነው፣ ጉቦ የሰጠ ግን በደቂቃ ይሰጠዋል " የቦሌ ወረዳ 12 ነዋሪዎች " ወረፋ አለ የሚታይ ነገር ነው፣ ወረፋ ለመያዝ ሌሊት እንዳይመጡ ከልክለናል፣ ችግሩ ይቀረፋል ወይ ስንል ግን አስቸጋሪ ነው " ቦሌ ወረዳ 12 አስተዳደር የቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12…
#Update

በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 የነዋሪዎች ቡድን መሪ የሆኑትን  ጨምሮ አገልግሎቶችን በገንዘብ ሲሸጡ እና ህብረተሰቡን ሲያንገላቱ የነበሩ  ባለሙያዎች ከመንግስት ስራ እንዲሰናበቱ ዉሳኔ መተላለፉን የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ አስታውቋል።

ኤጀንሲው ደረሰኝ ያለውን የተገልጋይ ጥቆማ መሰረት አድርጎ የቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 12 የነዋሪዎች አገልግሎት  ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ክብረት ቦጋለ እንዲሁም የነዋሪዎች አገልግሎት ባለሙያ የሆኑት አቶ ሞላ ልንገረዉ ላይ ነው እርምጃ የወሰደው።

ግለሰቦቹ በተለያዩ ግዜያት ተገልጋዮችን ማንገላታትና  አገልግሎትን ያለአግባብ በገንዘብ ሲሸጡ የነበረ መሆኑን በማስረጃ በማረጋገጥ በአዋጅ 87/2017 ዓ.ም ላይ በተቀመጠዉ አሰራር መሰረት ከስራ እንዲሰናበቱ ዉሳኔ መሰጠቱን ነው የገለጸው።

ኤጀንሲው ከህገ-ወጥ ደላሎች እና አገልግሎትን በገንዘብ ከሚሸጡ ህብረተሰቡ ራሱን እንዲጠብቅ አሳስቦ ተመሳሳይ አይነት ነገር ሲገጥም በ7533 የነፃ የስልክ መስመር እንዲሰጡ ጥሪ አስተላልፏል።

ከዚህ ቀደም ቲክቫህ ኢትዮጵያ በጉዳዩ ላይ የሰራው ዘገባ ከላይ ተያይዟል።

@TikvahethMagazine
83👏30👍7🤣5👎1🕊1
በሱዳን ጦርነት ለሚዋጉ የኮሎምቢያ ተዋጊዎች የቦሳሶ ወደብ መሸጋገሪያ መሆኑ ተነገረ።

የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የምታስተዳድረው በቦሳሶ የሚገኝ ወታደራዊ ማዘዣ ለተዋጊዎቹ መሸጋገሪያ መሆኑ ተገልጿል።

የቀድሞ የኮሎምቢያ ጦር አባላት ለግለሰባዊ ደህንነት ከተመለመሉ በኋላ ለሱዳን የፈጥኖ ደራሽ ኃይል እንዲዋጉ ይደረጋሉ ተብሏል።

አንድ የኮሎምቢያ ተዋጊ 2600 ዶላር በወር የሚያስገኝለትን ኮንትራት መፈረሙን ገልፆ #በኢትዮጵያ በኩል አድርጎ ወደ ፑንትላንድ ቦሳሶ ወደብ መወሰዱን በኋላም በዳርፉር መስፈሩን ገልጿል።

የቦሳሶ ወደብ መጀመሪያ በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ሲሰራ የፑንትላንድ የባህር ኃይልን ለማሰልጠን ነበር ሲባል አሁን ሙሉ ለሙሉ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የምትቆጣጠረው ማዘዣ ነው ተብሏል።

ምንም እንኳን የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በሱዳን ጦርነት ያላትን ተሳተፎ ብትክድም ከሰሞኑ የቦሳሶ ወደብ እንዴት የኮሎምቢያ ተዋጊዎች መሸጋገሪያ እንደሆነና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች እየተጠቀመች እንደሆነ የሚያሳይ የምርመራ ዘገባ ወጥቷል።

ዘ ጋርዲያንና La Silla Vacia የተሰኘ የኮሎምቢያ ጋዜጣ በጉዳዩ ላይ የሰሩትን የምርመራ ሪፖርት ከዚህ ማንበብ ይችላሉ።

@TikvahethMagazine
86😢9🕊9👎4👍3
🤙 ኑሮዎን ፒያሳ ላይ ያድርጉ

➣ ውብ አፓርትመንቶቻችን ለኑሮ ምቹ በሆነችው አዲሲቷ ፒያሳ ላይ እርሰዎን ይጠብቃል

   
     66 ካሬ ባለ 1 መኝታ
                 
➣  40% ሲከፍሉ 20% ቅናሽ  6,072,000 ብር ጠቅላላ ዋጋ

100% ለከፈለ 30% ቅናሽ 5,313,000 ብር ጠቅላላ ዋጋ
      
              2 መኝታ 75 ካሬ
  
➣ 40% ሲከፍሉ 20% ቅናሽ
6,900,000 ብር ጠቅላላ ዋጋ

100% ለከፈለ 30% ቅናሽ 6,037,500 ብር ጠቅላላ ዋጋ

          3 መኝታ 106 ካሬ

➣ 40% ሲከፍሉ 20% ቅናሽ 9,752,000 ብር ጠቅላላ ዋጋ

➣100% ለከፈለ  30% ቅናሽ 8,533,000 ብር ጠቅላላ ዋጋ

❗️ልብ ይበሉ ከላይ የተፃፉት አነስተኛ ካሬዎች ለ ምሳሌ ሲሆኑ ከፍ ያለ ካሬ ማግኜት ትችላላችሁ

ለበለጠ መረጃ
         👇
☎️
+251986687513

WhatsApp:- +251986687513
Email:-
[email protected]
16🤔1
የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ፓትርያርክ  መታሰቢያ ሐውልት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ጥቅምት 9 ቀን  2018 ዓ.ም ይመረቃል።

ምንጭ : EOTC

@TikvahethMagazine
185🤣13😢5👍4
በጠለፋና በአስገድዶ መድፈር የተከሰሰው ግለሰብ በ15 አመት ጽኑ እስራት ተቀጣ።

በካፋ ዞን በቢጣ ወረዳ ኦጊ ዳኪቲ ቀበሌ የካቲት 16 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 7:00 ሰዓት ላይ ገበያ ለመገበያየት እየሄደች ያለች የግል ተበዳይን ጠልፎ በመድፈር ወንጀል ተከሶ በ15 ዓመት እስራት መቀጣቱን ወረዳው አስታውቋል።

ተከሳሽ ለጊዜው እጃቸውን ለፖሊስ ካልሰጡ ግብራበሮቹ ጋር በመሆንና ስለታማ ቁስ በእጁ ይዞ በማስፈራራት የጠለፋ ወንጀል በመፈፀም ወደ ጌሻ ወረዳ ሀነቶ ቀበሌ አስገድዶ ስለመውሰዱ ነው ፖሊስ ያስረዳው።

በዚሁ መሠረት የቢጣ ወረዳ ፍርድ ቤት  ጥቅምት 3 ቀን 2018 ዓ.ም በዋለው የወንጀል ችሎት ተከሳሹ ኤልያስ ቆጭቶ በሁለት ወንጀሎች ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ በ15 አመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል።

@TikvahethMagazine
👎4424😢17👏7🤔1🤬1
#Oromia: በኦሮሚያ ክልል በአዲስ መልክ ለተደራጁ የቀበሌ መዋቅሮች 6 ሺህ 800 የሞተር ብስክሌቶች ተከፋፍሏል።

የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ሽመልስ አብዲሳ የሞተር ብስክሌቶቹ በቀበሌ መዋቅር የመንግሥት አገልግሎት ፈጣን፣ ቀልጣፋና ውጤታማ ለማድረግ የሚሰራውን ሥራ የሚያግዙ በመሆኑ በአግባቡ ለተፈለገው ዓላማ እንዲውሉ አስገንዝበዋል። [OBN]

@TikvahethMagazine
👍66👎6418🤔11
#እንድታውቁት

ከዚህ ቀደም የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ሳይኖራችሁ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላችሁ ግብር ከፋዮች ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥራችሁን ከፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ጋር በአካል መሔድ ሳይጠበቅባችሁ https://mor-migration.fayda.et  በመጠቀም ማያያዝ የሚቻል መሆኑን የብሔራዊ መታወቂያ አስታውቋል።

እስካሁን በኢትዮጵያ ከ25 ሚሊዮን በላይ ዜጎችን በፋይዳ አገልግሎት መመዝገብ ተችሏል ሲባል ከ91 በላይ ተቋማት ጋርም ትስስር ተፈጥሯል።

@TikvahethMagazine
24👎12👍3😢1
2025/10/21 10:08:05
Back to Top
HTML Embed Code: