Telegram Web Link
የማውሪዝዮ ሳሪ የላዚዮ ቆይታ ?

ጣልያናዊው አሰልጣኝ ማውሪዝዮ ሳሪ ከ 25 ቀናት በፊት ላዚዮን ከአንድ አመት በኋላ በድጋሜ መረከባቸው ይታወሳል።

አሰልጣኙ አሁን ላይ ክለቡን ለቀው ለመሄድ በማሰብ ላይ መሆናቸውን የጣልያን መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

አሰልጣኝ ማውሪዝዮ ሳሪ ከአንድ አመት በፊት ላዚዮን በገዛ ፍቃዳቸው ለቀው የነበረ ቢሆንም ከሳምንታት በፊት ክለቡ በድጋሜ ጠርቶ ሾሟቸዋል።

ክለቡ እስከ ጥር ወር ተጨዋች እንዳያስፈርም መታገዱን ዘግይተው የሰሙት ማውሪዝዮ ሳሪ በዚህ ሁኔታ አልቀጥልም ማለታቸው ተነግሯል።

አሰልጣኙ ዛሬ ከክለቡ ጋር ለንግግር መቀመጣቸው የተዘገበ ሲሆን በክለቡ ለመቀጠል ሳይስማሙ እንዳልቀሩ ተገልጿል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
😁8668👍7😢5👏3
ዴቪድ አላባ በድጋሜ ጉዳት አጋጠመው !

በቅርቡ ከረጅም ጊዜ ጉዳት ወደ ሜዳ የተመለሰው የሪያል ማድሪዱ የመስመር ተጨዋች ዴቪድ አላባ ሌላ ጉዳት እንዳጋጠመው ተገልጿል።

ተጨዋቹ በግራ እግሩ ላይ አዲስ የጡንቻ ጉዳት እንዳጋጠመው ተነግሯል።

ይህንንም ተከትሎ ዴቪድ አላባ ለአንድ ወር ከሜዳ ከሜዳ እንደሚርቅ ሲገለፅ ቀሪው የክለቦች አለም ዋንጫ ውድድርም ያመልጠዋል።

በዘንድሮው የውድድር ዘመን ጉዳት ያላጋጠማቸው የሪያል ማድሪድ ተጨዋቾች ሉካ ሞድሪች እና አርዳ ጉለር ብቻ መሆናቸው ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
😢11765😁32👎10👍6🤩5🥰4👏3😱2
የብሪያን ምቤሞ የዩናይትድ ዝውውር ?

ካሜሮናዊው ተጨዋች ብሪያን ምቤሞ ብሬንትፎርድን የሚለቅ ከሆነ ማንችስተር ዩናይትድን ብቻ መቀላቀል እንደሚፈልግ ለክለቡ እና ቶተንሀም ማሳወቁ ተገልጿል።

ማንችስተር ዩናይትዶች በበኩላቸው ለተጨዋቹ ሁለተኛ የዝውውር ሒሳብ አቅርበው የነበረ ቢሆንም ውድቅ እንደተደረገባቸው ተነግሯል።

ማንችስተር ዩናይትድ ለሁለተኛ ጊዜ አቅርቦ የነበረው የዝውውር ሒሳብ ተጨማሪ ክፍያን ጨምሮ 62.5 ሚልዮን ፓውንድ እንደነበር ተገልጿል።

ሁለቱ ክለቦች በተጨዋቹ ዝውውር ላይ ከስምምነት ለመድረስ የሚያደርጉትን ንግግር አጠናክረው መቀጠላቸው ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
252😁47👍24👎18🔥7🤔3🤬2
ቪንሰስ ጁኒየር ሪያል ማድሪድን ስንት ጠየቀ ?

ብራዚላዊው የፊት መስመር ተጨዋች ቪንሰስ ጁኒየር በሪያል ማድሪድ ቤት ውሉን ለማራዘም በንግግር ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል።

ቪንሰስ ጁኒየር ሪያል ማድሪድ በአዲሱ ኮንትራት መሰረት በአመት 30 ሚልዮን ዩሮ ክፍያ መጠየቁን ለተጨዋቹ ቅርብ የሆኑ ምንጮች ገልጸዋል።

ቪንሰስ ጁኒየር ባለፈው አመት የፊፋ የአመቱ ምርጥ ሽልማት ማሸነፉን ተከትሎ አመታዊ ክፍያው ወደ 15 ሚልዮን ዩሮ ማደጉ ይታወቃል።

ተጨዋቹ ኮንትራቱን ለማራዘም ከክለቡ ጋር የሚያደርገው ንግግር አሁንም በሂደት ላይ መሆኑ ተገልጿል።

ቪንሰስ ጁኒየር ስለ ኮንትራቱ ተጠይቆ “ ሁለት ቀሪ አመታት አሉኝ ነገርግን ሙሉ የእግርኳስ ህይወቴን እዚህ መቀጠል እፈልጋለሁ “ ሲል ምላሽ ሰጥቷል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
266😁115👍36👎9👏2🤬2
#WanawSportswear ✔️

ዋናው ስፖርት X Esfna 2025
ነገ ሰኔ 21 የሀበሻውያን አንድነት,ኩራት አና ታሪክ በሲያትል ሜዳ ላይ ዋናውን ተጎናፅፈው ዙፋናቸውን ይይዛሉ::
ESFNA | ⭐️ ከዋናው ጋር ወድፊት


📍ሲያትል፣ ሰሜን አሜሪካ🇺🇸
🤝ዋናው ስፖርት የሲልቨር ደረጃ ስፖንሰር
🗓ሰኔ 21| june 28 በይፋ ይጀመራል

ለበለጠ መረጃ
8️⃣2️⃣8️⃣9️⃣

🔗 ማህበራዊ ገጾቻችን🔗
Instagram|Facebook |TikTok |X|Youtub
🔥🔥🔥🔥በኢትዮጵያ የተመረተ🔥🔥🔥🔥
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
33🥰2
"የአቪዬተር ቻሌንጅ ቀጥሏል!
ደንበኞች እያሸነፉ ነው! እርስዎስ?
በአቪዬተር የከፍታ ተልእኮዎች ይሳተፉ ፣ ከመሪዎቹ አንዱ ይሁኑ ፣ እስከ 7500 ብር ያሸንፉ!
ከፍተኛውን የማባዣ ድምር በመሰብሰብ ወደ መሪነት ሰሌዳው ላይ ይውጡ፣ነጻ በረራዎችን ያግኙ።
ከፍታውን ይቀዳጃሉ? አሁኑኑ መብረር ይጀምሩ!
https://www.betika.com/et/mobile/#/crash-games
ቤቲካ - የአሸናፊዎች ቤት"
17🤬2😁1
የክለቦች አለም ዋንጫ ተመልካች ቁጥር ምን ይመስላል ?

በአሜሪካ እየተካሄደ የሚገኘው የክለቦች አለም ዋንጫ ውድድር  የምድብ ጨዋታዎች ተደርገው ተጠናቀዋል።

ውድድሩ ከሚያካሂዳቸው 63 ጨዋታዎች 48 ጨዋታዎች ሲደረጉ በቀጣይ እስከ ፍፃሜው 15 ጨዋታዎች ይቀራሉ።

ፒኤስጂ ከአትሌቲኮ ማድሪድ ያደረጉት ጨዋታ 80,619 ተመልካቾችን በማስመዝገብ እስካሁን የውድድሩ ሪከርድ የተመልካች ቁጥር ሆኗል።

በተጨማሪም ጨዋታው በክለቦች አለም ዋንጫ ውድድር ታሪክ በርካታ ተመልካቾች የታደሙት ጨዋታ በመሆን ሪከርድ ሆኖ ተመዝግቧል።

በውድድሩ አነስተኛ ቁጥር ያለው ተመልካች የተገኘበት ጨዋታ የማሜሎዲ ሰንዳውንስ እና ኡልሳን ኤችዲ ጨዋታ ሲሆን 3,412 ተመልካቾች ተገኝተዋል።

በውድድሩ አንስተኛ ቁጥር ይሆን እንጂ በውድድሩ ታሪክ አነስተኛ ተመልካች የተመዘገበበት ጨዋታ በ 2023 ክለብ ሊዮን እና ኡራዋ ሬድ ዳይመንድስ ጨዋታ ሲሆን 2,525 ተመልካቾች ተገኝተው ነበር።

የ 2025 ክለቦች አለም ዋንጫ አማካይ የተመልካች ቁጥር 34,759 ሆኖ መመዝገቡን የፊፋ መረጃ ያሳያል።

በውድድሩ በተመሳሳይ ቀን የተደረገው የሰንዳውንስ እና ፍሉሚኔንስ እንዲሁም ሞንቴሬይ እና ኡራዋ ሬድ ዳይመንድስ ጨዋታ እንደ አጋጣሚ ተመሳሳይ 14,312 ተመልካቾች ተከታትለውታል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
154😁23👏11👎9👍3
“ ስህተት ከሰራን በማግስቱ ወደ ቤታችን ነን “ ማሬስካ

የሰማያዊዎቹ ዋና አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ ዛሬ ምሽት ከቤኔፊካ ጋር የሚያደርጉት የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ከባድ እንደሚሆን ገልጸዋል።

“ እነሱ ባየር ሙኒክን አሸንፈዋል “ ያሉት ማሬስካ “ በጨዋታው ላይ ምን ያህል ጥሩ እንደሆኑ እና ምን ማድረግ እንደሚችሉ አሳይተዋል “ ብለዋል።

“ ተመጣጣኝ ጨዋታ እንደሚሆን እርግጠኛ ነኝ ጨዋታዎች ከባድ ነው “ ሲሉ አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ ጨምረው ተናግረዋል።

“ አሁን ያለነው ጥሎ ማለፍ ላይ ነው ምንም ሊፈጠር ይችላል ፤ ተጨዋቾቹ በዚህ ሰዓት ስህተት የሚሰራው ቡድን በጨዋታው ማግስት ወደ ቤቱ የሚሸኘው ቡድን መሆኑን ያውቃል። “ ኢንዞ ማሬስካ


ቼልሲ ዛሬ ከምሽቱ 5:00 ሰዓት የክለቦች አለም ዋንጫ ጥሎ ማለፍ ጨዋታውን ከቤኔፊካ ጋር ያደርጋል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
182😁44👏22👍8🙏2
የጆሽ አቻምፖንግ የቼልሲ ቆይታ ?

የሰማያዊዎቹ ዋና አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ ለወጣቱ ተከላካይ ጆሽ አቻምፖንግ የሚበጀው በክለቡ ቢቆይ መሆኑን ገልጸዋል።

ተጨዋቹ በዚህ ክረምት ቼልሲን ሊለቅ እንደሚችል ሲዘገብ የነበረ ሲሆን ኒውካስል ዩናይትድ እና ቦርስያ ዶርትመንድ ሊያስፈርሙት ይፈልጋሉ።

ሁለገቡ ተከላካይ ጆሽ አቻምፖንግ ባለፈው አመት ለቼልሲ በሁሉም ውድድሮች 12 ጨዋታዎች ማድረግ ችሏል።

ሰማያዊዎቹ በዚህ ክረምት ወጣቱን ተከላካይ የመሸጥ ፍላጎት እንደሌላቸው ለክለቡ ቅርብ ምንጮች አረጋግጠዋል።

የ 19ዓመቱ ተከላካይ ጆሽ አቻምፖንግ በቼልሲ የወደፊት አቅድ ውስጥ ትልቅ ቦታ የተሰጠው ተጨዋች መሆኑ ተገልጿል።

ኢንዞ ማሬስካ በሰጡት አስተያየት “ አቻምፖንግን እወደዋለሁ ባለው አቅም የክለቡ ምርጥ ተከላካይ መሆን ይችላል ለእሱ ቢቆይ ጥሩ ነው “ ብለዋል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
162👍18🔥2👏1😁1🤔1
በሳምንታዊ ጥቅሎች ፈታ ብለን ዳታ እንጠቀም! ከጉርሻ የሳፋሪኮም ደቂቃ ጋር 🎁

በልዩ ልዩ አማራጮች የቀረበልንን የሳፋሪኮም የኢንተርኔት ጥቅል የM-PESA Appን በመጠቀም አሁኑኑ እንግዛ! በፈጣን ዳታ እንንበሽበሽ!

#SafaricomEthiopia
#1wedefit
#Furtheraheadtogether
34👎3👍1
“ ጨዋታው ቀላል አይሆንም “ ሩበን ኔቬዝ

የአል ሂላሉ ተጨዋች ሩበን ኔቬዝ ከ ማንችስተር ሲቲ ጋር የሚያደርጉት ጨዋታ ቀላል እንደማይሆን ተናግሯል።

“ ከአለም ምርጥ ሶስት ቡድኖች መካከል አንዱን ነው የምንገጥመው “ ያለው ተጨዋቹ ማንችስተር ሲቲን በደንብ እናውቀዋለን ብሏል።

“ ብዙ ተጨዋቾች ቀያይረዋል ፤ ጋርዲዮላን አውቀዋለሁ እንግሊዝ ስጫወት ብዙ ግዜ በተቃራኒ ተጫውተናል ፤ ቀላል አይሆንም ነገርግን የቻልነውን ሁሉ እናደርጋለን።"ሩበን ኔቬስ

አል ሂላል በጨዋታው የሚትሮቪችን ግልጋሎት የማያገኝ ሲሆን አምበሉ ሳሌም አል ሳውዳሪ ለጨዋታው የመድረስ እድሉ ጠባብ መሆኑ ተነግሯል።

የማንችስተር ሲቲ እና አል ሂላል ጥሎ ማለፍ ጨዋታ ሰኞ ሌሊት 10:00 ሰዓት ይደረጋል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
140👍26😁11
ክረምትን በምን ሊያሳል አስበዋል?

Can PlayStation 🎮 መፍትሄ ይዞ ብቅ ብሏል🫴

-Sony
PlayStation 2
PlayStation 3
PlayStation 4
PlayStation 5

-Microsoft
Xbox 360
Xbox one
Xbox one s
Xbox Series

ምርቶችን አዘጋጅቶ እናንተን በመጠበቅ ላይ ነን! እንግዲያውስ እርሶ በተመችዎት ሰዓት ብቅ በማለት ሱቃችን መጎብኘት ይችላሉ።

እቃዎቻችን 6 ወር ዋስትና ስላለው ያለ ሀሳብ ይዝናኑ።

ለልጅም ሆነ ለአዋቂ የሚሆኑ PlayStation Cidi Game ስላሉን ይደውሉልን።

Tv በተለያየ Brand እና Size እኛ ዘንድ ያገኛሉ።

ባሎት ማንኛውም እቃ መቀያየር ይቻላል።

ለክፍለ ሀገር እናቀርባለን ይደውሉ።

🤝Thanks for choice!

አድራሻ፡፦
ቁጥር 1፦  መገናኛ
ቁጥር  2፦  ቦሌ

ስልክ፦ 0904658609 ወይም                  0910529770
0977349492  ይደውሉ

ለአዳዲስ መረጃ Telegram channel join ይበሉ ፦
https://www.tg-me.com/CanPlaystation

                       👍Update Your Life

    Can PlayStation እና Tv Market
25👎3
“ የክለቦች አለም ዋንጫ የደከመ ሀሳብ ነው “ ክሎፕ

ጀርመናዊው አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ አዲሱን የክለቦች አለም ዋንጫ ውድድር መጀመር ሀሳብ “ የማይረባ ሀሳብ “ ሲሉ ተችተዋል።

“ የክለቦች አለም ዋንጫን የመጀመር ሀሳብ በእግርኳስ ከተተገበሩ ጥሩ ያልሆኑ ውሳኔዎች መካከል የከፋው ነው “ ሲሉ የርገን ክሎፕ ተናግረዋል።

ውድድሩ በሚቀጥለው የውድድር አመት “ ተጨዋቾች ገጥሟቸው የማያውቀው ጉዳት “ ይገጥማቸዋል የሚል ፍራቻ እንዳላቸው የርገን ክሎፕ ገልጸዋል።

አክለውም ተጨዋቾች በውድድር አመቱ በጉዳት ባይሰቃዩ እንኳን በሚቀጥለው አለም ዋንጫ አስቸጋሪ ጊዜ ይጠብቃቸዋል በማለት ተናግረዋል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
338👍78😁28👎19🔥3👏1
ቼልሲ ተጨዋች ለማስፈረም እየጣሩ ነው !

የለንደኑ ክለብ ቼልሲ እና ኒውካስል ዩናይትድ የብራይተኑን የፊት መስመር ተጨዋች ጇ ፔድሮ ለማስፈረም ፉክክር ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

ብራይተን ለ 23ዓመቱ ብራዚላዊ የፊት መስመር ተጨዋች ጇ ፔድሮ እስካሁን የቀረበ ጥያቄ አለመቀበሉ ተነግሯል።

ሁለቱ ክለቦች ተጫዋቹን ወደ ስብሰባቸው ለመቀላቀል ከብራይተን ጋር በንግግር ላይ መሆናቸው ተዘግቧል።

ተጨዋቹ በውድድር አመቱ ለብራይተን 30 ጨዋታዎች ሲያደርግ 10 የፕርሚየር ሊግ ግቦችን አስቆጥሮ ስድስት አመቻች አቀብሏል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
156😁49👎8🔥4😱4🤬4🥰1
TIKVAH-SPORT
ፖል ፖግባ የጤና ምርመራውን ያደርጋል ! ፈረንሳዊው የመሐል ሜዳ ተጨዋች ፖል ፖግባ ከፈረንሳዩ ክለብ ሞናኮ ለመቀላቀል ዛሬ የጤና ምርመራውን እንደሚያደርግ ተገልጿል። ከአንድ አመት በላይ ከሜዳ ርቆ የቆየው ፖል ፖግባ ከጁቬንቱስ ጋር ያለውን ኮንትራት ማቋረጡን ተከትሎ ሞናኮን በነፃ ዝውውር ይቀላቀላል። ፖል ፖግባ በታዳጊነቱ ሌ ሀቭሬን በመልቀቅ የማንችስተር ዩናይትድን አካዳሚ ከተቀላቀለ ወዲህ ለመጀመሪያ…
ፖል ፖግባ በይፋ ሞናኮን ተቀላቀለ !

ፈረንሳዊው የመሐል ሜዳ ተጨዋች ፖል ፖግባ የፈረንሳዩን ክለብ ሞናኮ መቀላቀሉ ይፋ ተደርጓል።

ሞናኮ የ 32ዓመቱን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ፖል ፖግባ በነፃ ዝውውር በሁለት አመት ኮንትራት አስፈርመዋል።

ፖል ፖግባ በእግርኳስ ህይወቱ ለመጀመሪያ ጊዜ በፈረንሳይ ሊግ የሚጫወት ይሆናል።

ፖግባ በሞናኮ የስምንት ቁጥር ማልያ እንደሚለብስ ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
389👍71🔥40👎4😁2
አል ነስር አሰልጣኝ ሊሾም ነው !

የሳውዲ አረቢያው ክለብ አል ነስር ፖርቹጋላዊውን አሰልጣኝ ጆርጅ ጄሱስ በሀላፊነት ለመሾም ከስምምነት መድረሱ ተገልጿል።

የቀድሞ የአል ሂላል አሰልጣኝ ጆርጅ ጄሱስ በቅርቡ ሀላፊነቱን ተረክበው ስራቸውን እንደሚጀምሩ ተዘግቧል።

የቡድኑ አምበል ክርስቲያኖ ሮናልዶ አሰልጣኙ ቡድኑን እንዲረከቡ ፍቃደኛ መሆኑን ማረጋገጫ መስጠቱ ተገልጿል።

አል ነስር ከቀናት በፊት ከጣልያናዊው አሰልጣኝ ስቴፋኖ ፒዮሊ ጋር መለያየታቸው አይዘነጋም።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
👍9862😁40
ፍሌቸር የዩናይትድን ወጣት ቡድን ሊረከብ ነው !

ማንችስተር ዩናይትድ ዳረን ፍሌቸርን የክለቡ ከ 18ዓመት በታች ቡድን ዋና አሰልጣኝ አድርገው ለመሾም ማሰባቸው ተነግሯል።

ዳረን ፍሌቸር በማንችስተር ዩናይትድ ያለውን ሚና ለመቀየር በንግግር ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል።

የ 41ዓመቱ ዳረን ፍሌቸር አሁን ላይ የማንችስተር ዩናይትድ ዋናው ቡድን አሰልጣኝ አባል በመሆን እያገለገለ ይገኛል።

የክለቡ እግርኳስ ዳይሬክተር ጄሰን ዊሎክስ እና የአካዳሚው ዳይሬክተር ዳረን ፍሌቸር ለቦታው ትክክለኛ ሰው ነው በሚል እምነት ሀላፊነቱን እንዳቀርቡለት ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
172👍36😁14👎6
ፓልሜራስ ሩብ ፍፃሜውን ተቀላቀለ !

በክለቦች አለም ዋንጫ ጥሎ ማለፍ ፓልሜራስ ከቦታፎጎ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1ለ0 ማሸነፍ ችለዋል።

የፓልሜራስን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ፓውሊንሆ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ውጤቱን ተከትሎ ፓልሜራስ ቦታፎጎን በመጣል ለውድድሩ ሩብ ፍፃሜ ማለፋቸውን አረጋግጠዋል።

ፓልሜራስ በሩብ ፍፃሜው የቼልሲ እና ቤኔፊካን አሸናፊ የሚገጥሙ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
🔥6149👍20😁2
የጨዋታ አሰላለፍ !

5:00 ቤኔፊካ ከ ቼልሲ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
🔥2621
2025/07/13 20:22:20
Back to Top
HTML Embed Code: