Telegram Web Link
#ClubWorldCup

በመጀመሪያው አጋማሽ ኢንተር ሚያሚ በተጋጣሚው ፒኤስጂ የሜዳ ክልል ማድረግ የቻለው ቅብብል 25 ነው።

ፒኤስጂ በአንፃሩ 257 ኮሶችን በተጋጣሚያቸው የሜዳ ክልል መቀባበል ችለዋል።

ፒኤስጂ በመጀመሪያው አጋማሽ ያስቆጥረው ግብ ኢንተር ሚያሚ በሶስተኛ የሜዳ ክፍል ካደረጉት ቅብብል ( 3 ) የበለጠ ነው።

ኢንተር ሚያሚ በጨዋታው ከዚህም የከፋ ውጤት ይዘው ላለመውጣት በሁለተኛው አጋማሽ የተሻለ የኳስ ቁጥጥር ማድረግ ያስፈልጋቸዋል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
😁14647🔥2👍1
57 '

ፒኤስጂ 4 - 0 ኢንተር ሚያሚ

ጇ ኔቬዝ
አቪሌስ ( በራስ ላይ )
ሀኪሚ

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
😁8924😢10🔥8👎7🥰3👌3
68 '

ፒኤስጂ 4 - 0 ኢንተር ሚያሚ

ጇ ኔቬዝ
አቪሌስ ( በራስ ላይ )
ሀኪሚ

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
43😁21👍5
80 '

ፒኤስጂ 4 - 0 ኢንተር ሚያሚ

ጇ ኔቬዝ
አቪሌስ ( በራስ ላይ )
ሀኪሚ

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
46😁22
90 '

ፒኤስጂ 4 - 0 ኢንተር ሚያሚ

ጇ ኔቬዝ
አቪሌስ ( በራስ ላይ )
ሀኪሚ

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
😁4830👎4🤬4🥰1
ፒኤስጂ ሩብ ፍፃሜውን ተቀላቅለዋል !

በክለቦች አለም ዋንጫ ጥሎ ማለፍ ፒኤስጂ ከኢንተር ሚያሚ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 4ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የፒኤስጂን የማሸነፊያ ግብ ጇ ኔቬዝ 2x ፣ አሽራፍ ሀኪሚ እና አቪሌስ በራሱ መረብ ላይ አስቆጥረዋል።

ውጤቱን ተከትሎ ፒኤስጂ ሩብ ፍፃሜውን ሲቀላቀል ኢንተር ሚያሚ ከውድድሩ ተሰናብተዋል።

በጨዋታው የፒኤስጂን ሁለት ግቦች ያስቆጠረው ጇ ኔቬዝ የጨዋታው ኮከብ በመባል መመረጥ ችሏል።

ፒኤስጂ በሩብ ፍፃሜው የባየር ሙኒክ እና ፍላሚንጎን አሸናፊ የሚገጥሙ ይሆናል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
😁16899👍30👎15😢10🔥7🥰1
TIKVAH-SPORT
ቼልሲ ተጨዋች ለማስፈረም እየጣሩ ነው ! የለንደኑ ክለብ ቼልሲ እና ኒውካስል ዩናይትድ የብራይተኑን የፊት መስመር ተጨዋች ጇ ፔድሮ ለማስፈረም ፉክክር ላይ መሆናቸው ተገልጿል። ብራይተን ለ 23ዓመቱ ብራዚላዊ የፊት መስመር ተጨዋች ጇ ፔድሮ እስካሁን የቀረበ ጥያቄ አለመቀበሉ ተነግሯል። ሁለቱ ክለቦች ተጫዋቹን ወደ ስብሰባቸው ለመቀላቀል ከብራይተን ጋር በንግግር ላይ መሆናቸው ተዘግቧል። ተጨዋቹ…
ቼልሲ ተጨዋች ለማስፈረም ተስማማ !

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ብራዚላዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ጇ ፔድሮ ለማስፈረም ከብራይተን ጋር ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል።

የ 23ዓመቱ የፊት መስመር ተጨዋች ጇ ፔድሮ በቼልሲ እና ኒውካስል ዩናይትድ ቢፈለግም ሰማያዊዎቹን ምርጫው ማድረጉ ተነግሯል።

ቼልሲ ለጇ ፔድሮ ዝውውር 50 ሚልዮን ፓውንድ እንደሚያወጡ ሲገለፅ ተጨዋቹ የስድስት አመት ውል እንደሚፈርም ተዘግቧል።

ተጨዋቹ በውድድር አመቱ ለብራይተን 30 ጨዋታዎች ሲያደርግ 10 የፕርሚየር ሊግ ግቦችን አስቆጥሮ ስድስት አመቻች አቀብሏል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
188😁71👍25👎10😱8👏2🔥1
“ የአለም ምርጥ ቡድን ነው የገጠምነው “ ማሼራኖ

የኢንተር ሚያሚው አሰልጣኝ ዣቪየር ማሼራኖ ቡድናቸው ከፒኤስጂ ትልቅ ልዩነት ቢኖረውም ለመፎካከር መሞከሩን ገልጸዋል።

“ የገጠምነው የአለም ምርጡን ቡድን ነው “ ያሉት ማሼራኖ “ አውሮፓ ላይ እነሱን ማቆም የቻለ ክለብ የለም እዚህም የአሸናፊነት ግምቱ የእነሱ ነው “ ብለዋል።

አክለውም “ በሁለቱ ክለቦች መካከል ትልቅ ልዩነት አለ ቢሆንም ለመፎካከር ሞክረናል በተጨዋቾቼ ኮርቻለሁ “ ብለዋል።

ከውድድሩ ምን እንደተማሩ ጥያቄ የቀረበላቸው አሰልጣኝ ማሼራኖ “ ምንም አላውቅም “ ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።

“ በሁለተኛው አጋማሽ ትንሽ ጥሩ ተጫውተን በምድቡ ሁለት ትልቅ ቡድኖች ጥለናል አሁን ወደፊት እንቀጥላለን “ ማሼራኖ

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
215😁152👍10👏10👎4🥰2💯2
“ ጥሩ ጨዋታ አድርገናል “ ኤንሪኬ

የፒኤስጂው ዋና አሰልጣኝ ሉዊስ ኤንሪኬ ቡድናቸው ባስመዘገበው ድል ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸዋል።

“ ጨዋታውን በጥሩ ሁኔታ ነው የጀመርነው " ያሉት ኤንሪኬ ኳስ ተቆጣጥረናል በቂ የግብ አድልም ፈጥረናል ብለዋል።

አክለውም “ በሁለተኛው አጋማሽ ተቀዛቅዘን ነበር ግብ ሊያስቆጥሩ ይችሉም ነበር ነገርግን ደስተኛ ነኝ “ ሲሉ ተደምጠዋል።

“ በሁሉም ተጨዋቾች ደስተኛ ነኝ ይህ እግርኳስ ነው እንደሁልጊዜው ራሳችንን ማሻሻል አለብን “ ኤንሪኬ

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
225👍46🔥11👏2😁2
" ሜሲ ድንቅ ጨዋታ ነው ያደረገው “

የኢንተር ሚያሚው ዋና አሰልጣኝ ዣቪየር ማሼራኖ ሊዮኔል ሜሲ በምሽቱ ጨዋታ ማድረግ የሚችለውን ምርጥ ነገር ማሳየቱን ገልጸዋል።

“ ሊዮኔል ሜሲ አስደናቂ ጨዋታ ነው ያደረገው “ ያሉት አሰልጣኙ በሁለተኛው አጋማሽ በነበሩን አጋጣሚዎች እሱ ሊያደርገው የሚችለውን ምርጥ ነገር አይተናል ብለዋል።

“ እሱ አሁን 38 ዓመቱ ነው ነገርግን ሰዎች አሁንም እሱን ለማየት ትኬት መቁረጣቸውን ቀጥለዋል ፤ ይህ እሱ ሊሰጠን የሚችለው ትልቅ ዋጋ ያለው ነገር ነው “ ማሼራኖ

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
😁420352👍41🔥12👎9🥰9💯5
ባየር ሙኒክ ሩብ ፍፃሜውን ተቀላቅለዋል !

በክለቦች አለም ዋንጫ ጥሎ ማለፍ ባየር ሙኒክ ከፍላሚንጎ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 4ለ2 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የባየር ሙኒክን የማሸነፊያ ግቦች ሀሪ ኬን 2x ፣ ጎሬዝካ እና ፑልጋር ማስቆጠር ችለዋል።

የፍላሚንጎን ግቦች ጆርጂንሆ እና ጌርሰን ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

ውጤቱን ተከትሎ ባየር ሙኒክ ሩብ ፍፃሜውን ሲቀላቀል ፍላሚንጎ ከውድድሩ ተሰናብተዋል።

በሩብ ፍፃሜው ባየር ሙኒክ የፈረንሳዩን ክለብ ፒኤስጂ  ከአምስት ቀናት በኋላ የሚገጥሙ ይሆናል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
👏14796👍18🔥10👎3
ክረምትን በምን ሊያሳል አስበዋል?

Can PlayStation 🎮 መፍትሄ ይዞ ብቅ ብሏል🫴

-Sony
PlayStation 2
PlayStation 3
PlayStation 4
PlayStation 5

-Microsoft
Xbox 360
Xbox one
Xbox one s
Xbox Series

ምርቶችን አዘጋጅቶ እናንተን በመጠበቅ ላይ ነን! እንግዲያውስ እርሶ በተመችዎት ሰዓት ብቅ በማለት ሱቃችን መጎብኘት ይችላሉ።

እቃዎቻችን 6 ወር ዋስትና ስላለው ያለ ሀሳብ ይዝናኑ።

ለልጅም ሆነ ለአዋቂ የሚሆኑ PlayStation Cidi Game ስላሉን ይደውሉልን።

Tv በተለያየ Brand እና Size እኛ ዘንድ ያገኛሉ።

ባሎት ማንኛውም እቃ መቀያየር ይቻላል።

ለክፍለ ሀገር እናቀርባለን ይደውሉ።

🤝Thanks for choice!

አድራሻ፡፦
ቁጥር 1፦  መገናኛ
ቁጥር  2፦  ቦሌ

ስልክ፦ 0904658609 ወይም                  0910529770
0977349492  ይደውሉ

ለአዳዲስ መረጃ Telegram channel join ይበሉ ፦
https://www.tg-me.com/CanPlaystation

                       👍Update Your Life

    Can PlayStation እና Tv Market
25
ተመላሽ እያደረግን ነው! 🔥
ሽንፈት? አይታሰብም!!!!!
በየቀኑ ለአምስት እድለኞች 500 ብር እየሸለምን ነው።
ውርርዱ ባይሳካም አምስት መቶ ብር የግልዎ ይሆናል። ይወራረዱ!
ቢሸነፉም በተመላሽ ያሸንፉ!
24😁7👍2
ጋቶች ፓኖም በግብ አግቢነቱ ቀጥሏል !

የዋልያዎቹ የመሐል ሜዳ ተጫዋች ጋቶች ፓኖም በ ኢራቅ ሊግ ተከታታተይ ጨዋታዎች ግብ ማስቆጠሩን ቀጥሏል።

ሁሉንም ጨዋታዎች ተሰልፎ እየተጫወተ የሚገኘው ጋቶች አራተኛ የሊግ ጎሉን ለኒው ሮዝ ስፖርት ክለብ አስቆጥሯል።

ጋቶች ፓኖም ትላንት ምሽት ቡድኑን መሪ ያደረገች ግብ ሲያስቆጥር የጨዋታው ኮከብ በመባልም ተመርጧል።

ኒውሮዝ ክለብ ትላንት ምሽት ተጋጣሚውን 4ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

ጋቶች ከትላንቱ የሊግ ጨዋታ አስቀድሞ በነበረ የሊግ መርሐ ግብር ቡድኑን አሸናፊ ያደረገ ግብ ሲያስቆጥር በሊጉ የሳምንቱ ምርጥ አስራ አንድ ውስጥ መካተት ችሎ ነበር።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
👍316108👏19🔥16😁12👎2🙏1
“ ሜሲ ከእሱ ጋር የሚሄዱ አጋሮች አላገኘም “ ኢብራሂሞቪች

ስዊድናዊው የቀድሞ ተጨዋች ዝላታን ኢብራሂሞቪች ሊዮኔል ሜሲ በትላንቱ ጨዋታ “ የማውቀው ሜሲ አልነበረም “ ሲል ገልጿል።

ሜሲ የማውቀው አልነበረም " ያለው ኢብራሂሞቪች ትክክለኛ ቡድን ብትሰጠው እሱ ያለውን ነገር ጨምሮ ጠንካራ ያደርገዋል ብሏል።

“ ኢንተር ሚያሚ ከሜሲ ጋር ከኳስ ውጪ እንዴት መንቀሳቀስ እንዳለባቸው እንኳን የማይረዱ ተጨዋቾች እና አሰልጣኞች ነው ያለው “ ሲል ዝላታን ተናግሯል።

አክሎም " የተሸነፈው ሜሲ ሳይሆን ኢንተር ሚያሚ ነው እሱ ከሀውልት ጋር ነው የተጫወተው እውነተኛ የቡድን አጋር ቢያገኝ አንበሳውን ታዩት ነበር።"ብሏል።

" ሜሲ እስካሁን የሚጫወተው እግርኳስ ስለሚወድ ነው እሱ አሁንም 99% የአሁን ተጨዋቾች ማድረግ የማይችሉትን ነገር እያደረገ ነው።" ኢብራሂሞቪች

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
575😁141💯23👍13👎3🔥3🤔3🤬3
የቪክቶር ዮከሬሽ የስፖርቲንግ ሊስበን ቆይታ ?

የስፖርቲንግ ሊስበኑ ፕሬዝዳንት ፍሬዴሪኮ ቫራንዳዝ ቪክቶር ዮከሬሽ በዚህ ክረምት ክለቡን የሚለቅበት እድል ከፍተኛ መሆኑን ገልፀዋል።

ስፖርቲንግ ሊስበን አሁን ላይ ተጫዋቹን በውሉ ካለው 100 ሚልዮን ዩሮ ውል ማፍረሻ በታች በሆነ የዝውውር ገንዘብ ለመሸጥ ማሰቡን ፕሬዝዳንቱ ጠቁመዋል።

“ ይሁን እንጂ በ 60 ሚልዮን ዩሮ እና ተጨማሪ 10 ሚልዮን ክለቡን እንደማይለቅ አረጋግጣለሁ “ ሲሉ ፕሬዚዳንቱ ተናግረዋል።

ፕሬዝዳንቱ ማንችስተር ዩናይትድ ለማቲውስ ኩንሀ ያወጣውን 73 ሚልዮን ዩሮ እና ለምቤሞ ያቀረበውን ገንዘብ በመጥቀስ አነፃፅረዋል።

አክለውም “ እነዚህ ሁለት ተጨዋቾች የዮከሬሽን ያህል የገበያ ዋጋም ሆነ ብቃት የላቸውም ብዬ አስባለሁ " ሲሉ ተደምጠዋል።

ቪክቶር ዮከሬሽ የፊት መስመር አጥቂ ለማስፈረም በማፈላለግ ላይ በሚገኘው አርሰናል እየተፈለገ ይገኛል።

በሌላ በኩል ተጨዋቹ የሻምፒየንስ ሊግ ቡድን መቀላቀል ቢፈልግም የማንችስተር ዩናይትዱ አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ሊያስፈርሙት ይፈልጋሉ።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
156😁49🔥10👎6👍5🥰2
TIKVAH-SPORT
ኳንሳህ ባየር ሌቨርኩሰንን ሊቀላቀል ነው ! የጀርመን ቡንደስሊጋው ክለብ ባየር ሌቨርኩሰን የሊቨርፑሉን የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ጃሬል ኳንሳህ ለማስፈረም ከስምምነት ደርሰዋል። ባየር ሌቨርኩሰን ተጨዋቹን 40 ሚልዮን ዩሮ በሚደርስ የዝውውር ሒሳብ ለማስፈረም ከሊቨርፑል ጋር መስማማታቸው ተገልጿል። ሊቨርፑል በተጨዋቹ ኮንትራት ውስጥ መልሶ መግዛት የሚያስችላቸው አንቀጽ ማካተታቸው ተነግሯል። የ…
ኳንሳህ ለጤና ምርመራ ጀርመን ይገኛል !

የሊቨርፑሉን የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ጃሬል ኳንሳ ባየር ሌቨርኩሰንን ለመቀላቀል ዛሬ የጤና ምርመራውን ያደርጋል።

ተጨዋቹ አሁን ጀርመን መድረሱ ሲገለፅ በቀጣይ የአሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀጉን ስብስብ ይቀላቀላል።

ባየር ሌቨርኩሰን ተጨዋቹን 40 ሚልዮን ዩሮ በሚደርስ የዝውውር ሒሳብ ለማስፈረም ከሊቨርፑል ጋር ተስማምተዋል።

ሊቨርፑል ከአንድ አመት በኋላ ተጫዋቹን 70 ሚልዮን ዩሮ በሚጠጋ ክፍያ መልሰው መግዛት የሚያስችላቸው አንቀጽ ያካትታሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
91👍28👏6😢3😁1
ቦታፎጎ አሰልጣኙን አሰናበተ !

ከክለቦች አለም ዋንጫ የተሰናበተው የብራዚሉ ክለብ ቦታፎጎ የቡድኑን ዋና አሰልጣኝ ሬናቶ ፓይቫ ማሰናበታቸውን አስታውቀዋል።

አሰልጣኙ ቦታፎጎን እየመሩ በክለቦች አለም ዋንጫው የሻምፒየንስ ሊግ አሸናፊውን ፒኤስጂ ማሸነፍ ችለዋል።

ቡድኑ በፓልሜራስ ተሸንፎ ከውድድሩ ውጪ መሆኑን ተከትሎ የክለቡ ባለቤት ጆን ቴክስተር አሰልጣኙን አሰናብተዋል።

አሰልጣኙ በተጨማሪም ቦታፎጎ በኮፓ ሊበርታዶሬስ እና ኮፓ ዶ ብራዚል ቡድናቸው አስራ ስድስት ውስጥ እንዲቀላቀል ረድተዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
👎10964👍13
2025/07/12 19:46:19
Back to Top
HTML Embed Code: