የዲያጎ ጆታ ቀብር መቼ ይፈፀማል ?
በድንገተኛ አደጋ ህይወታቸው ያለፈው ዲያጎ ጆታ እና ወንድሙ አስከሬን በትውልድ መንደራቸው ፖርቹጋል ጎንዶማር በሚገኝ የእምነት ተቋም ይገኛል።
የተጨዋቾቹ አስከሬን ትላንት ከስፔን ወደ ፖርቹጋል መወሰዱ ተገልጿል።
የፖርቹጋሉ ጠቅላይ ሚኒስቴር ሉዊስ ሞንቴኔግሮ ዛሬ ከሰዓት በኋላ በስፍራው ተግኝተው ሀዘናቸውን መግለፃቸው ተገልጿል።
የተጨዋቾቹ ስርዓተ ቀብር በነገው ዕለት ቅዳሜ እንደሚፈፀም ተነግሯል።
በነገው ስረዓተ ቀብር በርካታ የሊቨርፑል ተጨዋቾች እንዲሁም የቡድን አባላት ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የቀድሞ የሊቨርፑል ተጨዋች ጆርዳን ሄንደርሰን በዛሬው ዕለት አንፊልድ ተገኝቶ ሀዘኑን በመግለፅ አበባ አስቀምጧል።
@Tikvahethsport @kidusyoftahe

TIKVAH-SPORT
“ ቶማስ ፓርቴ እንዲከሰስ ፈቅደናል “ ፖሊስ የእንግሊዝ የህግ አካል የሆነው " CPS " የቶማስ ፓርቴን ጉዳይ ከመረመረ በኋላ ተጨዋቹ ክስ እንዲመሰረትበት መፍቀዱን አስታውቋል። " CPS " በእንግሊዝ ፖሊስ እና ሌሎች የህግ አካላት የመረመሯቸውን የወንጀል ጉዳዮች ወደ ክስ የሚወስድ ገለልተኛ ተቋም መሆኑ ተገልጿል። የህግ ተቋሙ ከዚህ በፊት ከሜትሮፖሊታን ፖሊስ የተላከለትን ማስረጃ እየገመገመ…
“ ቶማስ ፓርቴ ክሱን አይቀበልም “ ጠበቃው
የአስገድዶ መድፈር እና ፆታዊ ጥቃት ክስ የቀረበበት ቶማስ ፓርቴ ክሱን ውድቅ እንዳደረገ የህግ ጠበቃው ተናግረዋል።
“ ቶማስ ፓርቴ ክሱን ውድቅ አድርጓል “ ያሉት ጠበቃው በሶስት አመቱ ምርመራ ከፖሊስ እና አቃቢ ህግ ጋር ተባብሮ ሰርቷል ብለዋል።
“ አሁን ላይ ቶማስ ፓርቴ በመጨረሻም ስሙን ለማንፃት እድሉን በደስታ ይቀበላል “ ጠበቃው
አክለውም “ እየተካሄደ በሚገኘው የህግ ሂደት ምክንያት ደንበኛዬ ተጨማሪ አስተያየት መስጠት አይችልም " ብለዋል።

ቼልሲ ከፍተኛ የገንዘብ ቅጣት ተጣለበት !
የአውሮፓ እግርኳስ ማህበር የፋይናንሻል ፌር ፕሊይ ህጉን አላከበሩም ባላቸው ክለቦች ላይ የቅጣት ውሳኔ ማስተላለፉን አስታውቋል።
ቼልሲ ቅጣት ከተጣለባቸው ክለቦች መካከል አንዱ ሲሆን 20 ሚልዮን ዩሮ ቅጣት እንዲከፍል ተወስኖበታል።
በድጋሜ ህጉን የሚጥሱ ከሆነ 60 ሚልዮን ዩሮ እንደሚቀጡ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው ተጠቁሟል።
በተጨማሪም ኦሎምፒክ ሊዮን 12.5 ሚልዮን ዩሮ መቀጣታቸው ተነግሯል።
በሌላ በኩል ህጉን ጥሰዋል የተባሉት ባርሴሎና 15 ሚልዮን ዩሮ እንዲሁም አስቶንቪላ 5 ሚልዮን ዩሮ ቅጣት ተጥሎባቸዋል።

ኒኮ ዊሊያምስ በይፋ ውሉን አራዘመ! ስፔናዊው የአትሌቲክ ቢልባኦ የፊት መስመር ተጫዋች ኒኮ ዊልያምስ ውሉን ለተጨማሪ ስምንት አመታት ማራዘሙን ክለቡ ይፋ አድርጓል። ተጫዋቹ በአትሌቲክ ቢልባኦ ቤት እስከ 2035 ድረስ የሚያቆየውን የረዥም አመት ውል መፈረሙ ይፋ ተደርጓል። ምንም እንኳ ባርሴሎና በተጫዋቹ ላይ ከፍተኛ ፍላጎት ቢኖረውም ተጫዋቹ ግን በአትሌቲክ ቢልባኦ ለመቆየት መወሰኑ ተገልጿል። ኒኮ…
የኒኮ ዊሊያምስ የባርሴሎና ዝውውር ለምን ቀረ ?
ባርሴሎና ስፔናዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ኒኮ ዊሊያምስ ለማስፈረም ከጫፍ ደርሰው በግልም ከስምምነት ደርሰው ነበር።
ይሁን እንጂ ኒኮ ዊሊያምስ በዛሬው ዕለት በአትሌቲክ ቢልባኦ ለአስር አመታት ለመቆየት ውሉን አራዝሟል።
የባርሴሎና ዝውውር ምን ገጠመው ?
ኒኮ ዊሊያምስ ባርሴሎና ባለበት የፋይናንስ ችግር ምክንያት ማስመዝገብ ካልቻለ ክለቡን መልቀቅ የሚያስችለው አንቀጽ በውሉ እንዲካተት መጠየቁ ተገልጿል።
ባርሴሎና በበኩሉ ኒኮ ዊሊያምስ የጠየቀውን የመልቀቅ መብት አንቀጽ ጥያቄ ውድቅ ማድረጉ ተነግሯል።
የኒኮ ዊሊያምስ ተወካዮች ተጨዋቹ ከላሊጋው የመጀመሪያ ጨዋታ ጀምሮ እንደሚመዘገብ ማረጋገጫ ፈልገው እንደነበር ተገልጿል።
የኒኮ ዊሊያምስ በአትሊቲክ ቢልባኦ ከፍተኛ ውል ማፍረሻ ያለው ውል መፈረሙ ዜና ከተጨዋቹ ጋር የተጫወቱ የባርሴሎናን ተጨዋቾችንም ማስደንገጡ ተነግሯል።
በተጨማሪም የባርሴሎና ሀላፊዎች የተጫዋቹን ውል ማራዘም ውሳኔ ከማህበራዊ ሚዲያ ማየታቸው ተዘግቧል።

“ ቤተሰቦችህ ምንም እንደማይጎልባቸው አረጋግጥልሀለው “ ሩብን ኔቬስ
የዲያጎ ጆታ የቅርብ ጓደኛ እና የቀድሞ የቡድን አጋር ሩብን ኔቬስ የተሰማውን ሀዘን ሲገልፅ “ አንተን ማጣቴ ደካማ ሰው አድርጎኛል “ ብሏል።
በብሔራዊ ቡድን ቆይታቸው በምግብ ቤት ፣ በክፍል ውስጥ እና በፕሌን ጉዟቸው የማይለያዩት ጆታ እና ኔቬስ “ በህይወት ባለመኖርህ ለአንተ ያለኝ ነገር አይቀየርም “ ሲል ተናግሯል።
“ሁሌም ከጎኔ መሆንህን ትቀጥላለህ “ ያለው ኔቬስ “ቤተሰቦችህ እና የምትወዳቸው ግለሰቦች ፍላጎታቸው እንደማይጓደልባቸው ላረጋግጥልህ እወዳለሁ “ የሚል መልዕክቱን አጋርቷል።
“ ህይወት አንድ አድርጋናለች አሁንም ቢሆን ልትነጥልን አትችልም ፣ አንድ መሆናችንን እንቀጥላለን “ ሩብን ኔቬስ
ሩብን ኔቬስ በመጨረሻም “ ከዛሬ ጀምሮ ወደ ሜዳ አብረሀኝ ትገባለህ ፣ ለመጀመሪያ ጊዜ በተዋወቅንበት የሜዳ መድረክ ጉዟችንን እንቀጥላለን “ ሲል የሀዘን መልዕክቱን አስፍሯል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe

ካይል ዎከር በርንሌይን ለመቀላቀል ተቃርቧል !
እንግሊዛዊው የመስመር ተጨዋች ካይል ዎከር አዲስ አዳጊውን በርንሌይ ለመቀላቀል ከጫፍ መድረሱ ተገልጿል።
በርንሌይ የ 35ዓመቱን ተጨዋች ካይል ዎከር በቋሚነት ለማስፈረም የጤና ምርመራውን ለማድረግ መዘጋጀታቸው ተነግሯል።
ተጨዋቹ በበርንሌይ የሁለት አመት ኮንትራት ይፈርማል ተብሎ ሲጠበቅ በርንሌይ በበኩሉ ለቡድኑ የረጅም ጊዜ ልምድ ባለቤት ተጨዋች ያገኛል።
ካይል ዎከር በቶተንሀም ቆይታው ከአሁኑ የበርንሌይ አሰልጣኝ ስኮት ፓርከር ጋር ለሁለት አመታት ተጫውተዋል።
ማንችስተር ሲቲ በበኩሉ በሚቀጥለው አመት ውሉ ከሚጠናቀቀው ተጨዋቹ ዝውውር አምስት ሚልዮን ፓውንድ እንደሚያገኙ ተነግሯል።

ጁቬንቱስ ተጨዋች ለማስፈረም ተቃረበ ! የሴርያው ክለብ ጁቬንቱስ ካናዳዊውን የሊል የፊት መስመር ተጨዋች ጆናታን ዴቪድ ለማስፈረም ከስምምነት መድረሱ ተገልጿል። ጁቬንቱስ ተጫዋቹን በነፃ ዝውውር የመጀመሪያ የክረምቱ ፈራሚው ለማድረግ ከጫፍ መድረሳቸው ተነግሯል። ተጨዋቹ በጁቬንቱስ ቤት አመታዊ ስድስት ሚልዮን ዩሮ እና ጉርሻ ሁለት ሚልዮን ዩሮ ክፍያ እንደሚያገኝ ተዘግቧል። የተጨዋቹ ፊርማ ጁቬንቱስ…
ጁቬንቱስ በይፋ ተጨዋች አስፈረመ !
የሴርያው ክለብ ጁቬንቱስ ካናዳዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ጆናታን ዴቪድ በአምስት አመት ኮንትራት ማስፈረማቸውን በይፋ አስታውቀዋል።
ጁቬንቱስ ተጫዋቹን በነፃ ዝውውር የመጀመሪያ የክረምቱ ፈራሚው በማድረግ ወደ ስብሰባቸው ቀላቅለዋል።
ተጨዋቹ በጁቬንቱስ ቤት አመታዊ ስድስት ሚልዮን ዩሮ እና ጉርሻ ሁለት ሚልዮን ዩሮ ክፍያ እንደሚያገኝ ተዘግቧል።
ጆናታን ዴቪድ ባለፈው አመት ለሊል ባደረጋቸው 49 ጨዋታዎች 25 ጎሎችን አስቆጥሮ 12 ለግብ የሆነ ኳስ አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።

የእረፍት ሰዓት !
በክለቦች አለም ዋንጫ ሩብ ፍፃሜ ፍሉሚኔንስ ከአል ሂላል ጋር እያደረጉ የሚገኙትን ጨዋታ 1ለ0 እየመሩ ወደ መልበሻ ቤት አምርተዋል።
- የፍሉሚኔንስን የመሪነት ግብ ማርቲኔሊ አስቆጥሯል።
🟨 የቢጫ ካርድ የተመለከቱ ተጫዋቾች እነማን ናቸው ?
- በመጀመሪያው አጋማሽ በአል ሂላል በኩል ረናን ሎዲ እና ሚሊንኮቪች ሳቪች በፍሉሚኔንስ በኩል ፍሬይቴስ እና ማርቲኔሊ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክተዋል።
- አል ሂላል ግማሽ ፍፃሜውን የሚቀላቀል ከሆነ ቢጫ ያየው ተከላካዩ ሬናን ሎዲ በቅጣት ጨዋታው የሚያመልጠው ይሆናል።
- ፍሉሚኔንስ ግማሽ ፍፃሜውን የሚቀላቀል ከሆነ ቢጫ ያየው ተከላካዩ ሁዋን ፍሬይቴስ በቅጣት ጨዋታው ያመልጠዋል።
⚽ የጨዋታው የኳስ ቁጥጥር ምን ይመስላል ?
- በመጀመሪያው አጋማሽ አል ሂላል 52% - 48% የኳስ ቁጥጥር ብልጫ ነበራቸው።

“ ጆታ የእውነትም ጥሩ ሰው ነበር “ ሞሪንሆ
ፖርቹጋላዊው አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ በዲያጎ ጆታ ድንገተኛ ሞት የተሰማቸውን ሀዘን በሰጡት አስተያየት ገልጸዋል።
“ ሰው ሲሞት ጥሩ ሰው ነበር ማለት የተለመደ ነው “ ያሉት ሞሪንሆ “ ነገርግን ዲያጎ ጆታ የእውነትም ጥሩ ሰው ነበር “ ሲሉ ተናግረዋል።
“ ጆታ የዚህ ዘመን ትውልድ ተከታይ አይመስልም ነበር ፤ ምንም እንኳን እሱ ለሊቨርፑል እና ፖርቹጋል እየተጫወተ እያሸነፈ ቢሆንም ትኩረት ማግኘት አይፈልግም ነበር “ ሲሉ ሞሪንሆ ተናግረዋል።
አክለውም " አሁን ያለ አባት ማደግ ያለባቸው ሶስት ልጆች እና ሁልጊዜ ፍቅሩ የነበረች ሴት እና ሁለት ልጆች ያጡ ቤተሰቦች አሉ “ ብለዋል።
“ ምናልባት አንድ ቀን ህልፈቱን ተረድተን እንቀበለው ይሆናል አሁን ግን ለመቀበል ከባድ ነው " ጆዜ ሞሪንሆ

ፍሉሚኔንስ ግማሽ ፍፃሜውን ተቀላቀለ !
በክለቦች አለም ዋንጫ ሩብ ፍፃሜ ፍሉሚኔንስ ከአል ሂላል ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።
የፍሉሚኔንስን የማሸነፊያ ግቦች ማርቲኔሊ እና ሄርኩለስ ሲያስቆጥሩ ለአል ሂላል ሊዮናርዶ ከመረብ አሳርፏል።
የብራዚሉ ክለብ ፍሉሚኔንስ ማሸነፉን ተከትሎ ግማሽ ፍፃሜውን የተቀላቀለ የመጀመሪያው ክለብ ሆኗል።
የፍሉሚኔንሱ ተከላካይ ሁዋን ፍሬይቴስ የማስጠንቀቂያ ካርድ መመልከቱን ተከትሎ በቅጣት የግማሽ ፍፃሜው ጨዋታ ያመልጠዋል።
በግማሽ ፍፃሜው ፍሉሚኔንስ የቼልሲ እና ፓልሜራስን አሸናፊ የሚገጥሙ ይሆናል።

ቼልሲ ተጫዋቾቹን በቅጣት ያጣል !
በክለቦች የአለም ዋንጫ ፓልሜራስን 2ለ1 በማሸነፍ ግማሽ ፍፃሜ የደረሱት ቼለሲ የሁለት ተጫዋቾቻቸውን ግልጋሎት አያገኙም።
በምሽቱ ጨዋታ የቢጫ ካርድ የተመለከቱት ሊያም ዴላፕ እና ሌቪ ኮልዊልን በቅጣት የሚያጡ ይሆናል።
በምሽቱ ጨዋታ በቅጣት ጨዋታው ያመለጠው ሞይሰስ ካይሴዶ በግማሽ ፍፃሜው ጨዋታ ይመለሳል።
ቼልሲ በቀጣይ ማክሰኞ በግማሽ ፍፃሜው ሌላኛው የብራዚል ተወካይ ፍሉሚኔንሴ በኒው ጀርሲ የሚገጥሙ ይሆናል።
“ በማሸነፋችን ደስተኛ ነኝ ፣ ልዩ ምሽት ነበር “ ሲሉ አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ ከምሽቱ ድል በኃላ ተናግረዋል።

ሊቨርፑል ለዲያጎ ጆታ ቤተሰብ ድጋፍ ያደርጋል !
ያለፉትን አምስት አመታት ሊቨርፑል ያገለገለው ዲያጎ ጆታ ህልፈት ህይወት ተከትሎ ክለቡ ለቤተሰቦቹ ድጋፍ እንደሚያደርግ ተነግሯል።
የፖርቹጋል መገናኛ ብዙሀን እንደዘገቡት የተጫዋቹን ቀሪ የሁለት አመት ክፍያ ለዲያጎ ጆታ ቤተሰቦች እንደሚከፍሉ ዘግበዋል።
የሊቨርፑል በርካታ ተጫዋቾች የቡድን አጋራቸውን በክብር ለመሸኘት በሳን ኮስሜ ከትላንትናው ዕለት ጀምሮ ተገኝተዋል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
ያለፉትን አምስት አመታት ሊቨርፑል ያገለገለው ዲያጎ ጆታ ህልፈት ህይወት ተከትሎ ክለቡ ለቤተሰቦቹ ድጋፍ እንደሚያደርግ ተነግሯል።
የፖርቹጋል መገናኛ ብዙሀን እንደዘገቡት የተጫዋቹን ቀሪ የሁለት አመት ክፍያ ለዲያጎ ጆታ ቤተሰቦች እንደሚከፍሉ ዘግበዋል።
የሊቨርፑል በርካታ ተጫዋቾች የቡድን አጋራቸውን በክብር ለመሸኘት በሳን ኮስሜ ከትላንትናው ዕለት ጀምሮ ተገኝተዋል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
“ ይህ ድል ለዲያጎ ጆታ ነው “ ኢንዞ ማሬስካ
የለንደኑ ክለብ ቼልሲ ዋና አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ የቡድናቸው ተጫዋች ፔድሮ ኔቶ ስለሚገኝበት ወቅታዊ ሁኔታ ከጨዋታው በኃላ ተናግረዋል።
“ ያደረገውን ነገር እናበረታታለን “ ያሉት ማሬስካ “ በቡድኑ ፊት የፓልሜራስ ድል ለዲያጎ ጆታ እንደሆነ ነግሬዋለሁ “ ብለዋል።
አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ ፔድሮ ኔቶ እና ዲያጎ ጆታ ያላቸውን ቅርበት በደንብ እንደሚያውቁም ገልፀዋል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
የለንደኑ ክለብ ቼልሲ ዋና አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ የቡድናቸው ተጫዋች ፔድሮ ኔቶ ስለሚገኝበት ወቅታዊ ሁኔታ ከጨዋታው በኃላ ተናግረዋል።
“ ያደረገውን ነገር እናበረታታለን “ ያሉት ማሬስካ “ በቡድኑ ፊት የፓልሜራስ ድል ለዲያጎ ጆታ እንደሆነ ነግሬዋለሁ “ ብለዋል።
አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ ፔድሮ ኔቶ እና ዲያጎ ጆታ ያላቸውን ቅርበት በደንብ እንደሚያውቁም ገልፀዋል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
“ ባሎን ዶር ለዴምቤሌ ካልተሰጠ ችግር አለ “ ናስር አል ካሊፋ
የፈረንሳዩ ክለብ ፒኤስጂ ፕሬዝዳንት ናስር አል ካሊፊ የባሎን ዶር ሽልማት ለኦስማን ዴምቤሌ እንደሚገባው ገልጸዋል።
“ ካሳለፈው ጥሩ አመት አንፃር የባሎን ዶር ሽልማቱን ዴምቤሌ እንደሚወስደው ምንም ጥርጥር የለኝም “ ሲሉ ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል።
አክለውም “ ይህ የማይሆን እና ባሎን ዶር የማያገኝ ከሆነ ግን ችግር አለ “ ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
“ አላማችን ውድድሩን በጥሩ ሁኔታ መጨረስ ላይ ነው ከውድድሩ በኋላ ስለ ዝውውር ማውራት እንጀምራለን “ ናስር አል ካሊፊ

“ ሻምፒዮን ለመሆን ዝግጁ ነን “ ኤንሪኬ
የፒኤስጂው ዋና አሰልጣኝ ሉዊስ ኤንሪኬ የምሽቱ የባየር ሙኒክ ጨዋታ አስቸጋሪ እንደሚሆን ገልጸዋል።
“ ቡድኑ ለዛሬው ጨዋታ ዝግጁ ነው " ያሉት ኤንሪኬ አስቸጋሪ ጨዋታ ይሆናል የምንገጥመው ከአውሮፓ ምርጥ ቡድኖች አንዱን ነው ብለዋል።
አክለውም " በውድድሩ የቻልነውን ያህል መጓዝ እንፈልጋለን ፤ ዋንጫ ማሸነፍ በሚያስችል ሁኔታ ላይ ነን ዝግጁ ነን " ሲሉ ገልጸዋል።
" ጨዋታው ክፍት ጨዋታ ይሆናል ስለ በቀል አላስብም አዝናኝ ጨዋታ ማድረግ ነው የምፈልገው " ሲሉ አሰልጣኙ ተናግረዋል።
የፒኤስጂ እና ባየር ሙኒክ ሩብ ፍፃሜ ጨዋታ ምሽት 1:00 ይካሄዳል።

ኢንተር ሚላን ተጨዋች አስፈረመ !
የጣልያን ሴርያው ክለብ ኢንተር ሚላን ፈረንሳዊውን ተጨዋች ዮን ቦኒ ከፓርማ ማስፈረማቸውን አስታውቀዋል።
ኢንተር ሚላን ተጫዋቹን 24 ሚልዮን ዩሮ በማውጣት በአምስት አመት ኮንትራት ማስፈረማቸው ተገልጿል።
የ 22ዓመቱ የፊት መስመር ተጨዋች ቦኒ በኢንተር ሚላን ቤት አመታዊ ሁለት ሚልዮን ዩሮ የሚከፈለው ይሆናል።

የዲያጎ ጆታ እና ወንድሙ ቀብር እየተካሄደ ነው !
በድንገተኛ አደጋ ህይወታቸው ያለፈው የሊቨርፑሉ ተጨዋች ዲያጎ ጆታ እና ወንድሙ ስርዓተ ቀብር እየተካሄደ ነው።
በስርዓተ ቀብሩ ላይ የሊቨርፑሉ አሰልጣኝ አርኔ ስሎትን ጨምሮ በርካታ የሊቨርፑል ተጨዋቾች ተገኝተዋል።
እንዲሁም የዲያጎ ጆታ የቅርብ ጓደኛ ሩበን ኔቬዝ እና ካንሴሎ ከአሜሪካ ወደ ፖርቹጋል በማቅናት በቀብር ስነ-ስርዓቱ ተገኝተዋል።
የማንችስተር ዩናይትዱ ተጨዋች ብሩኖ ፈርናንዴዝ የፖርቹጋል አሰልጣኝ ሮቤርቶ ማርቲኔዝ በስፍራው ተገኝተዋል።