Telegram Web Link
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ልዩ የእግር ኳስ ጥቅል ለክለቦች ዋንጫ ሩብ ፍጻሜ!⚽️

አጓጊውን የፒኤስጂ እና ባየርን ሙኒክ ጨዋታ ለ3 ሰአታት በሚቆይ ልዩ 2.5ጊባ ጥቅል ከዳር እስከ ዳር በሚገኘው በሳፋሪኮም ኔትወርክ ላይ በDSTV በቀጥታ እንከታተል!

#SafaricomEthiopia  #1Wedefit
#Furtheraheadtogether
ባየር ሙኒክ ተጨዋቾቹ ለቅጣት ተቃርበዋል !

ዛሬ ምሽት ከፒኤስጂ ወሳኝ ጨዋታ ያለበት የጀርመኑ ክለብ ባየር ሙኒክ በርካታ ተጨዋቾቹ ለቅጣት ተቃርበዋል።

ባየር ሙኒክ ስድስት ተጨዋቾቹ ዛሬ የማስጠንቀቂያ ካርድ የሚመለከቱ ከሆነ ቡድኑ ለግማሽ ፍፃሜው ካለፈ አንድ ጨዋታ የሚቀጡ ይሆናል።

ሀሪ ኬን ፣ ጀማል ሙሲያላ ፣ ጆሽዋ ኪሚች ፣ ጆናታን ታህ ፣ ጎሬዝካ እና ኮንራድ ላይመር ለቅጣት የተቃረቡ ተጨዋቾች ናቸው።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
2'

ፒኤስጂ 0 - 0 ባየር ሙኒክ

@Tikvahethsport       @kidusyoftahe
14'

ፒኤስጂ 0 - 0 ባየር ሙኒክ

@Tikvahethsport       @kidusyoftahe
33 '

ፒኤስጂ 0 - 0 ባየር ሙኒክ

@Tikvahethsport       @kidusyoftahe
እረፍት

ፒኤስጂ 0 - 0 ባየር ሙኒክ

@Tikvahethsport       @kidusyoftahe
60 '

ፒኤስጂ 0 - 0 ባየር ሙኒክ

@Tikvahethsport       @kidusyoftahe
70 '

ፒኤስጂ 0 - 0 ባየር ሙኒክ

@Tikvahethsport       @kidusyoftahe
“ ፌነርባቼ አበረታች ንጥረነገር ሊሰጠኝ ሞክሯል “ አለን ሴንት ማክስሚን

ፈረንሳዊው የፊት መስመር ተጨዋች አለን ሴንት ማክስሚን ባለፈው አመት በፌነርባቼ በውሰት ያሳለፈው አስቸጋሪ ጊዜ እንደነበር ገልጿል።

ተጨዋቹ ባደረገው ቃለምልልሱ ላይ ፌነርባቼ አበረታች ንጥረ ነገር ሊሰጠው መሞከሩን ተናግሯል።

አለን ሴንት ማክስሚን በንግግሩም “ በታመምኩበት ወቅት ፌነርባቼ እንደ አበረታች ንጥረነገር የሚቆጠር መድኃኒት ሰጥተውኛል  " ብሏል።

የ 28ዓመቱ አለን ሴንት ማክስሚን ባለፈው አመት ከአል አህሊ በውሰት ፌነርባቼን ተቀላቅሎ አራት ጎሎችን ማስቆጠር ችሏል።

ቡድኑ የሊጉን ዋንጫ ለምን እንዳላሸነፈ ያስረዳው ተጨዋቹ “ ሞሪንሆ ዋንጫውን ለመውሰድ ሁሉንም ሰጥተዋል ነገርግን በክለቡ ዙሪያ ነው ችግሩ ውስብስብ ጉዳይ አለ " ብሏል።

“ ችግሩ የከፋ መሆኑን ማረጋገጫ ለእኔ ' ዶፒንግ ' ሊሰጡኝ መሞከራቸው ነው እንዳትናገር ከኋላ መጥቶ የሚያስፈራራህ ሰው አለ።" አለን ሴንት ማክስሚን

ፌነርባቼ በበኩሉ ባወጣው መግለጫ " ተጨዋቹ በአደባባይ ስማችንን እያጠለሸ ነው በማለት “ የቀረበበትን ውንጀላ ውድቅ አድርጓል።

ክለቡ አክሎም ተጨዋቹ ስሜን አጥፍቷል በሚል ህጋዊ እርምጃ ለመውሰድ ስራ መጀመሩን አስታውቋል።

@Tikvahethsport       @kidusyoftahe
80 '

ፒኤስጂ 1 - 0 ባየር ሙኒክ

ዱዌ

@Tikvahethsport       @kidusyoftahe
90+6'

ፒኤስጂ 2 - 0 ባየር ሙኒክ

ዱዌ
ዴምቤሌ

@Tikvahethsport       @kidusyoftahe
ፒኤስጂ ግማሽ ፍፃሜውን ተቀላቀለ !

በክለቦች አለም ዋንጫ ሩብ ፍፃሜ ፒኤስጂ ከባየር ሙኒክ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የፒኤስጂን የማሸነፊያ ግብ ወጣቱ ተጨዋች ዲዚሬ ዱዌ እና ኦስማን ዴምቤሌ ማስቆጠር ችለዋል።

በጨዋታው የባየር ሙኒክ ወሳኝ አማካይ ጀማል ሙሲያላ ምናልባት ለረጅም ጊዜ ከሜዳ የሚያርቀው ከባድ ጉዳት አጋጥሞታል።

ፒኤስጂ ማሸነፉን ተከትሎ ግማሽ ፍፃሜውን የተቀላቀለ ሶስተኛው ክለብ ሆኗል።

የፒኤስጂው ተከላካይ ዊሊያን ፓቾ እና ሉካስ ሄርናንዴዝ ቀይ ካርድ መመልከታቸውን ተከትሎ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታው ያመልጣቸዋል።

በግማሽ ፍፃሜው ፒኤስጂ የሪያል ማድሪድ እና ቦርስያ ዶርትመንድን አሸናፊ የሚገጥሙ ይሆናል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ለሙሲያላ በጣም አዝነናል " ኑኖ ሜንዴዝ

የፒኤስጂው የመስመር ተጨዋች ኑኖ ሜንዴዝ ጀማል ሙሲያላ ባጋጠመው ከባድ ጉዳት ቡድናቸው እንዳዘነ ገልጿል።

“ በጣም ከባድ ጉዳት ነበር የገጠመው ለእሱ በጣም አዝነናል “ ሲል ኑኖ ሜንዴዝ ከጨዋታው በኋላ አስተያየቱን ሰጥቷል።

" እሱ ከምርጥ ተጨዋቾች መካከል አንዱ ነው ጠንካራ ሆኖ እንደሚመለስ ተስፋ እናደርጋለን “ ኑኖ ሜንዴዝ

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
የጨዋታ አሰላለፍ !

5:00 ሪያል ማድሪድ ከ ዶርትመንድ

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
" የከፋ እንደማይሆን ተስፋ አደርጋለሁ " ኮምፓኒ

የባየር ሙኒኩ ዋና አሰልጣኝ ቪንሴንት ኮምፓኒ የጀማል ሙሲያላ ጉዳት ከባድ እንደሚመስል ከጨዋታው በኋላ ተናግረዋል።

ጉዳቱን " አሳዛኝ " ሲሉ የገለፁት አሰልጣኙ “ ስመለከተው ጥሩ አይመስልም በጣም የከፋ እንደማይሆን እና በቶሎ እንደሚያገግም ተስፋ አደርጋለሁ ብለዋል።

አሽራፍ ሀኪሚ በበኩሉ “ የሙሲያላ ጉዳት ይመስለኛል ከጎኑ መሆኔን መናገር እወዳለሁ በቅርቡ አገግሞ ሜዳ ላይ እንደምናየው ተስፋ አለኝ "ሲል ተደምጧል።

የባየር ሙኒኩ ተጨዋች ጀማል ሙሲያላ ካጋጠመው ከባድ ጉዳት በኋላ ወደ ሆስፒታል መወሰዱ ተዘግቧል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
#ClubWorldCup 🇺🇸

ስፔናዊው የሪያል ማድሪድ አካዳሚ ውጤት ጎንዛሎ ጋርሺያ በክለቦች አለም ዋንጫ ውድድር የሪያል ማድሪድ ቁልፍ ተጨዋች ነው።

ተጨዋቹ ከክለቦች አለም ዋንጫ ውድድር በፊት በዚህ የውድድር አመት ለዋናው ቡድን ተሰልፎ የተጫወተው ለ 61 ደቂቃዎች ነበር።

ይሁን እንጂ በኪሊያን ምባፔ መታመም እና በኤንድሪክ መጎዳት ምክንያት የተሰጠውን እድል በአግባቡ በመጠቀም በብቃቱ አለምን ማስደመም ችሏል።

ተጨዋቹ በውድድሩ ሶስት ግቦችን አስቆጥሮ አንድ ለግብ የሆነ ኳስ በማመቻቸት ጥሩ ጊዜ እያሳለፈ ይገኛል።

በአሰልጣኝ ዣቢ አሎንሶ ከክለቡ ታሪካዊ ተጨዋች ራውል ጋር የተነፃፀረው ጎንዛሎ ጋርሺያ ዛሬ ምሽትም ከሚጠበቁ ተጨዋቾች አንዱ ነው።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
ተጀመረ

ሪያል ማድሪድ 0 - 0 ዶርትመንድ

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ፖርቹጋላዊ ተጨዋቾችን ማስደሰት ፈልገን ነበር "

የፒኤስጂው ተጨዋች ማርኩኒሆስ በዛሬው ጨዋታ በዲያጎ ጆታ ህልፈት ምክንያት ጥሩ ስሜት ላይ ላልነበሩት ፖርቹጋላዊ ተጨዋቾች ድጋፍ ለማሳየት መሞከራቸውን ገልጿል።

በጨዋታው ኦስማን ዴምቤሌ ባየር ሙኒክ ላይ ግብ ካስቆጠረ በኋላ የዲያጎ ጆታን ደስታ አገላለጽ በመጠቀም ተጫዋቹን አስቦ ነበር።

ከጨዋታው በኋላ ስለ ሁነቱ የተጠየቀው ማርኩኒሆስ “ ዜናውን መስማት በጣም አስቸጋሪ ነበር “ ሲል ተናግሯል።

" መልበሻ ቤት ውስጥ ፖርቹጋላዊ ተጨዋቾች አሉ ከቅርብ ጊዜ በፊት አብረውት ሲጫወቱ ነበር “ ሲል ማርኩኒሆስ ገልጿል።

“ ስለዚህ በጨዋታው ከጎናቸው መሆናችንን ለማሳየት እና ልናስደስታቸው ፈልገን ነበር ፤ ጆታ ትልቅ ክብር ይገባዋል እንደዚህ አይነት አደጋዎች ማየት ማንም አይፈልግም።"ማርኩኒሆስ

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
2025/07/07 03:26:13
Back to Top
HTML Embed Code: