ሪያል ማድሪድ ግማሽ ፍፃሜውን ተቀላቀለ !
በክለቦች አለም ዋንጫ ሩብ ፍፃሜ ሪያል ማድሪድ ከዶርትመንድ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 3ለ2 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ግማሽ ፍፃሜውን ተቀላቅለዋል።።
የሎስ ብላንኮዎቹን የማሸነፊያ ግቦች ኪሊያን ምባፔ ፣ ጎንዛሎ ጋርሺያ እና ፍራንሲስኮ ጋርሺያ ሲያስቆጥሩ ለዶርትመንድ ቤር እና ጉራሲ ከመረብ አሳርፈዋል።
ወጣቱ የፊት መስመር ተጨዋች ጎንዛሎ ጋርሺያ በውድድሩ አራተኛ ግቡን በማስቆጠር ኮከብ ግብ አግቢነቱን እየመራ ይገኛል
የሪያል ማድሪዱ ተከላካይ ዲን ሁይሰን ቀይ ካርድ መመልከቱን ተከትሎ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታው ያመልጠዋል።
በግማሽ ፍፃሜው ሪያል ማድሪድ ከ ፒኤስጂ ጋር የሚጫወቱ ይሆናል።
@Tikvahethsport @kidusyoftahe

የጉዳፍ ፀጋይ የአለም ሪከርድ ተሰበረ !
በኢትዮጵያዊቷ አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ተይዞ የነበረው የአለም የሴቶች የ 5000 ሜትር ሪከርድ በኬንያዊቷ አትሌት ቼቤት ተሰብሯል።
አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ከሁለት አመታት በፊት በተመሳሳይ ቦታ የሴቶች 5000 ማትር ሪከርድን 14:00.21 በሆነ ሰዓት ይዛ እንደነበር ይታወሳል።
ኬንያዊቷ አትሌት ፓትሪስ ቼቤት ዛሬ በተደረገው ዩጂን ዳይመንድ ሊግ ውድድር 13:58.06 በመግባት የአትሌት ጉዳፍ ፀጋይን ሪከርድ ማሻሻል ችላለች።
የኦሎምፒክ ሻምፒዮኗ አትሌት ፓትሪስ ቼቤት የ 5000 ሜትር ውድድርን ከ 14 ደቂቃዎች በታች የጨረሰች የመጀመሪያዋ ሴት አትሌት በመሆን ታሪክ ፅፋለች።
በውድድሩ የተካፈለችው ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቃለች።
በሌላ ውድድር ኬንያዊቷ የ 1500 ማትር የአለም ሪከርድ ባለቤቷ ፌዝ ኪፕዬጎን የራሷን ሪከርድ በድጋሜ በ 36 ሰከንድ በማሻሻል አዲስ ታሪክ ሰርታለች።
@tikvahethsport @kidusyoftahe

#WAFCON2024
የ 2024 የሞሮኮ ሴቶች አፍሪካ ዋንጫ ውድድር በዛሬው ዕለት በሞሮኮ ራባት መካሄዱን ጀምሯል።
በውድድሩ መክፈቻ ጨዋታ አዘጋጇ ሀገር ሞሮኮ ከዛምቢያ ጋር ጨዋታዋን አድርጋ 2ለ2 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቃለች።
የወቅቱ የአፍሪካ ዋንጫው አሸናፊ ደቡብ አፍሪካ በምድብ ሶስት ከጋና ፣ ማሊ እና ታንዛኒያ ጋር ተደልድላለች።
በመድረኩ በርካታ ጊዜ በማሸነፍ ባለክብር የሆነችው ናይጄሪያ የመጀመሪያ ጨዋታዋን ቱኒዚያ ጋር ታደርጋለች።
የአፍሪካ እግርኳስ የበላይ ካፍ በዘንድሮው የሴቶች አፍሪካ ዋንጫ ውድድር ላይ የሚሰጠውን ሽልማት መጠን ከፍ አድርጓል።
አሸናፊዎች ስንት ያገኛሉ ?
- የዋንጫው አሸናፊ :- አንድ ሚልዮን ዶላር
- የፍፃሜ ተፋላሚ :- 500,000 ዶላር
- ሶስተኛ ደረጃ :- 350,000 ዶላር
አራተኛ ደረጃ :- 300,000 ዶላር ሽልማት እንደሚቀበሉ ተነግሯል።
ካፍ በተጨማሪም በዘንድሮው ውድድር ለአሸናፊው ሽልማት የሚቀርብ አዲስ ዋንጫ አዘጋጅቶ አስተዋውቋል።
በውድድሩ 12 ብሔራዊ ቡድኖች በሶስት ምድብ ተከፍለው ለሚቀጥሉት ሀያ ቀናት ውድድራቸውን የሚያደርጉ ይሆናል።

ክረምትን በምን ሊያሳልፋ አስበዋል?
Can PlayStation 🎮 መፍትሄ ይዞ ብቅ ብሎሎታል🫴
-Sony
PlayStation 2
PlayStation 3
PlayStation 4
PlayStation 5
-Microsoft
Xbox 360
Xbox one
Xbox one s
Xbox Series
ምርቶችን አዘጋጅቶ እናንተን በመጠበቅ ላይ ነን
እንግዲያውስ እርሶ በተመቻቹ ሰአት ብቅ በማለት ሱቃችን መጎብኘት ይችላሉ
እቃዎቻችን 6 ወር ዋስትና ስላለው የለ ሀሳብ ይዝናኑ
ለልጅም ለአዋቂ የሚሆኑ PlayStation Cidi Game ስላሉን ይደውሉልን
Tv በተለያየ Brand እና Size እኛ ዘንድ ያገኛሉ
ባሎት ማንኛውም እቃ መቀያየር ይቻላል
ለክፍለ ሀገር እናቀርባለን ይደውሉ
🤝Tanks for choice
አድራሻ፡፦
ቁጥር 1፦ መገናኛ
ቁጥር 2፦ ቦሌ
ስልክ፦ 0904658609 ወይም 0910529770
0977349492 ይደውሉ
ለአዳዲስ መረጃ Telegram channel join ይበሉ ፦
https://www.tg-me.com/CanPlaystation
👍Update Your Life
Can PlayStation እና Tv Market

Forwarded from Betika Ethiopia Official Channel
ቀመረኛው!!
ዛሬም የሚያሸንፉባቸው የእለቱ የውርርድ ጥቆማዎች እነሆ!
አሁን ነው ማሸነፍ እድሜ ለቀመረኛው!!
ቀመረኛው - በቤቲካ ብቻ!
ዛሬም የሚያሸንፉባቸው የእለቱ የውርርድ ጥቆማዎች እነሆ!
አሁን ነው ማሸነፍ እድሜ ለቀመረኛው!!
ቀመረኛው - በቤቲካ ብቻ!
“ ለእኛ ትልቅ ፈተና ይሆናል “ ዣቢ አሎንሶ
የሎስ ብላንኮዎቹ ዋና አሰልጣኝ ዣቢ አሎንሶ የፒኤስጂ ግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ለቡድናቸው ትልቅ ፈተና እንደሚሆን ገልጸዋል።
“ ፒኤስጂን መግጠም ለእኛ ጥሩ ፈተና ይሆናል ከዶርትመንድ ጨዋታ ጥሩ ነገሮችን ይዘን ለጨዋታው እንቀርባለን “ ሲሉ ዣቢ አሎንሶ ተናግረዋል።
ቡድናቸው ትላንት ምሽት እስከ መጨረሻ ደቂቃ ጥሩ መጫወቱን የገለፁት አሰልጣኙ " በመጨረሻ ደቂቃ አቋማችን እና ጥንካሬያችን ጠፍቶ ነበር እንደ እድል መጥፎ ነገር አልተፈጠረም ብለዋል።
" ጎንዛሎ ጋርሺያ ትክክለኛ አጥቂ ነው ለቡድኑ ብዙ ስራ በመስራት እየረዳን ነው በሚያደርገው ነገር ደስተኛ ነኝ። " ዣቢ አሎንሶ