Telegram Web Link
“ ራሽፎርድ ዩናይትድ እንዲቆይ እፈልጋለሁ “ ሁዋን ማታ

የቀድሞ የቀያይ ሴጣኖቹ አማካይ ሁዋን ማታ ማርከስ ራሽፎርድ በማንችስተር ዩናይትድ ቢቆይ ለሁለቱም ጥሩ መሆኑን ተናግሯል።

ሁዋን ማታ በሰጠው አስተያየት አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ውሳኔያቸውን አጢነው ራሽፎርድን እንዲያቆዩት ጠይቋል።

ማታ በማንችስተር ዩናይትድ በነበረው ቆይታ ከማርከስ ራሽፎርድ ጋር ከ 100 በላይ ጨዋታዎች አንድላይ ተጫውተዋል።

ራሽፎርድ ከዋናው ቡድን ጋር ልምምድ ሲጀምር ለእሱ የተለየ ፍቅር እንደነበረው የገለፀው ማታ “ እሱ ያለፍርሀት ነበር የሚጫወተው ድንቅ ነበር " ብሏል።

አክሎም " እንደ ማንችስተር ዩናይትድ ደጋፊ እና ራሽፎርድ ጓደኛ እሱ እዛው ቆይቶ እንዲሳካለት እፈልጋለሁ ምክንያቱም የልጅነት ክለቡ ነው " ሲል ተደምጧል።

“ አሁን ምን እየተፈጠረ እንዳለ አላውቅም ነገርግን እሱ ቢቆይ እና ደስተኛ መሆን ከቻለ ለሁለቱም ጥሩ ጥቅም ይመስለኛል “ ሁዋን ማታ

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
የዌስትሀም ደጋፊዎች አድማ ጠሩ !

የዌስትሀም ዩናይትድ ደጋፊዎች ማህበር ክለቡ የፊት መስመር ተጨዋቹ መሐመድ ኩዱስን ለቶተንሀም እንዳይሸጥ ጠይቋል።

ደጋፊዎቹ ክለቡ ተጫዋቹን ለቶተንሀም አሳልፎ የሚሰጥ ከሆነ አድማ ለመጥራት እና ተቃዋሞ ለመቀስቀስ በዝግጅት ላይ መሆናቸውን አስታውቀዋል።

ቶተንሀም ሆትስፐርስ መሐመድ ኩዱስን ከዌስትሀም ለማስፈረም በንግግር ላይ መሆናቸው ይታወቃል።

መሐመድ ኩዱስ በበኩሉ ቶተንሀም ያቀረበለትን ጥያቄ በመቀበል ይሁንታውን መስጠቱ ተዘግቧል።

ለተጨዋቹ ያቀረበው 50 ሚልዮን ፓውንድ ውድቅ የሆነበት ቶተንሀም በዚህ ሳምንት አዲስ የዝውውር ሒሳብ ያቀርባል ተብሎ ይጠበቃል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
ኢቫን ራኪቲች ጫማውን ሰቀለ !

የቀድሞ የባርሴሎና ታሪካዊ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ኢቫን ራኪቲች በ 37ዓመቱ ራሱን ከ ፕሮፌሽናል እግርኳስ ማግለሉን በይፋ አስታውቋል።

ክሮሽያዊው አማካይ ራኪቲች በእግርኳስ ህይወቱ 17 ዋንጫዎችን በማሳካት ስኬታማ የተጫዋችነት ጊዜን ማሳለፍ ችሏል።

ተጨዋቹ 993 ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ መጫወት የቻለ ሲሆን 297 የግብ ተሳትፎ ማድረግም ችሏል።

ኢቫን ራኪቲች አሁን ላይ ጫማውን መስቀሉን በኢንስታግራም የማህበራዊ ትስስር ገፁ አስታውቋል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
ኒውካስል ዩናይትድ ከተጨዋቹ ጋር ተለያየ !

ኒውካስል ዩናይትድ ኮንትራቱ ከተጠናቀቀው እንግሊዛዊ የፊት መስመር ተጨዋች ካሉም ዊልሰን ጋር መለያየቱ ይፋ ተደርጓል።

እንግሊዛዊው የፊት መስመር ተጨዋች ካሉም ዊልሰን ከአምስት አመታት በኋላ ከኒውካስል ዩናይትድ ጋር ተለያይቷል።

ተጨዋቹ በኒውካስል በነበረው ቆይታ 113 የፕርሚየር ሊግ ጨዋታዎች አድርጎ 47 ጎሎችን ማስቆጠር ችሏል።

የ 33ዓመቱ ካሉም ዊልሰን በቀጣይ አዲስ ክለብ በነፃ ዝውውር ይቀላቀላል ተብሎ ይጠበቃል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
ሞድሪች ኤሲ ሚላንን መቼ ይቀላቀላል ?

የጣልያን ሴርያው ክለብ ኤሲ ሚላን ክሮሽያዊውን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ሉካ ሞድሪች ለማስፈረም ከስምምነት መድረሳቸው ይታወሳል።

ሉካ ሞድሪች በቀጣይ ከክለቦች አለም ዋንጫ ውድድር በኋላ ኤሲ ሚላንን እንደሚቀላቀል አሰልጣኝ ማሲሚሊያኖ አሌግሪ አረጋግጠዋል።

የ 39ዓመቱ አማካይ ሉካ ሞድሪች ከክለቦች አለም ዋንጫ በኋላ ሪያል ማድሪድን በነፃ እንደሚለቅ ማሳወቁ አይዘነጋም።

አሰልጣኙ በተጨማሪም ቲኦ ሄርናንዴዝ የሳውዲ አረቢያውን ክለብ አል ሂላል ለመቀላቀል ከስምምነት መድረሱን አስታውቀዋል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
አርኔ ስሎት ቡድኑን መርዳት ላይ ያተኩራሉ !

አሰልጣኝ አርኔ ስሎት ባለፈው ሳምንት ሶስቱን አዳዲስ ፈራሚዎች ከቡድናቸው ጋር የማዋሀድ ስራ ቀዳሚው ተግባራቸው አድርገው አንደነበር ተገልጿል።

ከቡድኑ ተጨዋች ዲያጎ ጆታ ድንገተኛ ህልፈት በኋላ አሁን ላይ የአሰልጣኙ ቀዳሚ እቅድ አስፈላጊ ነገር ተደርጎ አይታይም።

አሰልጣኝ አርኔ ስሎት በቀጣይ ቀዳሚው ፈታኝ ተግባራቸው በቡድን አጋራቸው አሳዛኝ ህልፈት ልባቸው የተሰበረ የቡድኑ ተጨዋቾችን መርዳት እንደሚሆን ተገልጿል።

የቅድመ ውድድር ዝግጅት መጀመሪያ ቀኑን ያራዘመው ሊቨርፑል በዚህ ሳምንት ወደ ልምምድ ሊመለስ እንደሚችል ተዘግቧል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ኦሲሜን በጋላታሳራይ መቆየት ይፈልጋል !

ናይጄሪያዊው የፊት መስመር አጥቂ ቪክቶር ኦሲሜን ስኬታማ የውሰት አመት ባሳለፈበት ጋላታሳራይ ለመቀጠል ማሰቡ ተገልጿል።

ተጨዋቹ በክለቡ በቋሚነት ለመቀጠል ከስምምነት መድረሱን የቱርክ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

ቪክቶር ኦሲሜን ከሳውዲ አረቢያው ክለብ አል ሂላል የቀረበለትን አመታዊ 40 ሚልዮን ዩሮ ክፍያ ውድቅ ማድረጉ አይዘነጋም።

ጋላታሳራይ በቀጣይ ከናፖሊ ጋር ከስምምነት ለመድረስ ጥረት እንደሚጀምሩ ሲገለፅ ከውል ማፍረሻው ባነሰ ዋጋ ይሸጣል የሚል እምነት አላቸው ተብሏል። 

ጋላታሳራይ የተጨዋቾች የዝውውር መስኮቱ ቀን እየተጠናቀቀ ሲሄድ ናፖሊ የሚጠይቀው ክፍያ ዝቅ ያደርጋል የሚል እምነት እንዳላቸው ተገልጿል።

ቪክቶር ኦሲሜን ባለፈው አመት በውሰት ከናፖሊ ጋላታሳራይን ተቀላቅሎ በ 41 ጨዋታዎች 37 ጎሎችን ማስቆጠር ችሏል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ሼዝኒ አዲስ ኮንትራት ቀረበለት ! ፖላንዳዊው ግብ ጠባቂ ሼዝኒ ከባርሴሎና አዲስ ኮንትራት እንደቀረበለት ተናግሯል። “ ባርሴሎና አዲስ የሁለት አመት ኮንትራት አቅርቦልኛል “ ሲል ሼዝኒ አስተያየቱን ሰጥቷል። አክሎም " አሁን በተጨዋችነት ልቀጥል ወይስ ጓንቴን ልስቀል የሚለውን ከቤተሰቤ ጋር ተነጋግሬ እወስናለሁ “ ሲል ተናግሯል። ከአመት በፊት ጓንቱን ሰቅሎ የነበረው ሼዝኒ ባለፈው አመት ለባርሴሎና…
ባርሴሎና የሼዝኒን ውል አራዘመ !

የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና የፖላንዳዊውን ግብ ጠባቂ ሼዝኒ ኮንትራት ለተጨማሪ አመታት ማራዘማቸውን በይፋ አስታውቀዋል።

የ 35ዓመቱ ሼዝኒ በባርሴሎና እስከ 2027 የሚያቆየውን የሁለት አመታት ውል መፈረሙ ይፋ ሆኗል።

ከአመት በፊት ጓንቱን ሰቅሎ የነበረው ሼዝኒ ባለፈው አመት ለባርሴሎና ፈርሞ ድንቅ የሚባል ጊዜ ማሳለፉ አይዘነጋም።

ባርሴሎና በቀጣይ የቡድኑ አምበል ቴር ስቴገን ክለቡን እንዲለቅ እንደሚፈልጉ ተገልጿል።

ባርሴሎና በዚህ አመት የእስፓኞሉን ግብ ጠባቂ ሁዋን ጋርሺያ ለቡድኑ ቁጥር አንድ ግብ ጠባቂነት ማስፈረማቸው አይዘነጋም።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ኤዱ ጋስፐር ለምን ከአርሰናል ጋር ይለያያሉ ? የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ብሬዚላዊ ስፖርቲንግ ዳይሬክተር ኤዱ ጋስፐር ከክለቡ ጋር ለመለያየት መወሰናቸውን ዘ አትሌቲክ አረጋግጧል። ስፖርቲንግ ዳይሬክተሩ ከአምስት አመታት በላይ ከቆዩበት አርሰናል ለመልቀቅ የወሰኑት አዲስ ሀላፊነት በማግኘታቸው መሆኑ ተገልጿል። ኤዱ ጋስፐር መድፈኞቹን የሚለቁት በኖቲንግሀም ፎረስት ባለቤት ኢቫንጄሎስ ማሪናኪስ…
ኤዱ ጋስፐር በሀላፊነት ተሾመዋል !

የቀድሞ የአርሰናል ስፖርቲንግ ዳይሬክተር ኤዱ ጋስፐር በኖቲንግሀም ፎረስት በሀላፊነት መሾማቸው ተገልጿል።

ኤዱ ጋስፐር በኖቲንግሀም ፎረስት የክለቡ ዋና የእግርኳስ የበላይ ሀላፊ በመሆን መሾማቸው ተገልጿል።

ኤዱ ጋስፐር በቀጣይ በኖቲንግሀም የዝውውር ጉዳይ ፣ የቡድኑን አቋም እና ተጨዋቾችን እድገት ጨምሮ ሁሉንም የእግርኳስ ነክ ስራ እንደሚቆጣጠሩ ተነግሯል።

“ በዚህ አዲስ ምዕራፍ ደስተኛ ነኝ እኔ ላይ በተጣለው እምነት ኮርቻለሁ ፤ የፕሬዝዳንቱን ምኞት ለመገንባት እና ለማሳካት ጓጉቻለሁ “ ሲሉ ኤዱ ተናግረዋል።

ኤዱ ጋስፐር ከወራት በፊት አርሰናልን ከአምስት አመታት በኋላ መልቀቃቸው አይዘነጋም።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የአርሰናል የዮከሬሽ ዝውውር ምን ላይ ደረሰ ?

አርሰናል ቪክቶር ዮከሬሽን ለማስፈረም ከስፖርቲንግ ሊስበን ጋር እስካሁን ከስምምነት እንዳልደረሱ ተገልጿል።

አሁንም የሚቀሩ ስራዎች ይኑሩ እንጂ አርሰናል ተጫዋቹን ለማስፈረም የሚያደርገው ንግግር ለስምምነት የቀረበ ደረጃ ላይ መድረሱ ተነግሯል።

መድፈኞቹ ተጫዋቹን በአምስት አመት ኮንትራት ለማስፈረም ከወዲሁ በግል ከስምምነት መድረሳቸው ታውቋል።

ስዊድናዊ አጥቂ ቪክቶር ዮከሬሽ በበኩሉ አርሰናልን ለመቀላቀል ዝግጁ መሆኑ ሲገለፅ ሚኬል አርቴታ ዝውውሩ በቶሎ እንዲፈፀም ግፊት እያደረጉ መሆኑ ተዘግቧል።

የአርሰናል ሌሎች ዝውውሮች ምን ይመስላሉ ?

አርሰናል ኖኒ ማዱኬን ለማስፈረም እስካሁን በይፋ ከቼልሲ ጋር ለንግግር አለመቀመጣቸው ተገልጿል።

ኖኒ ማዱኬ በበኩሉ ወደ አርሰናል ለመዘዋወር እንደሚፈልግ እና በቀረበለት ጥያቄ መደሰቱ ተነግሯል።

መድፈኞቹ አሁንም በኦሊ ዋትኪንስ ላይ ያላቸው ፍላጎት እንዳለ እና ሁኔታውን እንደሚከታተሉ ተጠቁሟል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
“ የክለቦች አለም ዋንጫ ምርጥ ውድድር ነው “ ካይሴዶ

የሰማያዊዎቹ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ሞይሰስ ካይሴዶ የክለቦች አለም ዋንጫ ውድድርን “ ድንቅ ውድድር “ ሲል ገልፆታል።

“ እውነታው የክለቦች አለም ዋንጫ ምርጥ ውድድር መሆኑ ነው “ ሲል ሞይሰስ ካይሴዶ ቅሬታ የለኝም ብሏል።

አክሎም “ ግማሽ ፍፃሜ ደርሰናል እዚህ በመሆናችን እና ባሳካነው ነገር ደስተኞች ነን። “ ብሏል።

“ ለመሻሻል ያስቀመጥኩት ገደብ የለም ከአለም ምርጥ ተጨዋቾች አንዱ መሆን እፈልጋለሁ “ ሞይሰስ ካይሴዶ

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
“ በትክክለኛው መንገድ ላይ ነን “ ማሬስካ

የለንደኑ ክለብ ቼልሲ ዋና አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ ቡድናቸው በትክክለኛው መንገድ ላይ እየተጓዘ መሆኑን ገልጸዋል።

“ ለመሻሻል ሁልጊዜም ቦታ አለ “ ያሉት ማሬስካ “ በትክክለኛው መንገድ ላይ ነን ነገርግን ብዙ ነገሮችን የተሻለ ማድረግ እንችላለን “ ብለዋል።

“ በጨዋታዎች ላይ የበለጠ ማጥቃት እና የበለጠ መከላከል ይኖርብናል “ ማሬስካ

የነገው የፍሉሚኔንስ ጨዋታ " አስቸጋሪ ይሆናል " ያሉት አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ አሰልጣኛቸውን አውቀዋለሁ የተለየ አሰልጣኝ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ በንግግራቸው ወቅት ሮሚዮ ላቪያ ለነገው ጨዋታ ዝግጁ አይደለም በማለት ገልጸዋል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ኒውካስል የዝውውር ጥያቄ አቀረበ ! ኒውካስል ዩናይትድ የኖቲንግሀም ፎረስቱን የፊት መስመር ተጨዋች አንቶኒ ኢላንጋ ለማስፈረም 55 ሚልዮን ፓውንድ ማቅረባቸው ተገልጿል። ኖቲንግሀም ፎረስት በቅርቡ ኒውካስል ዩናይትድ ያቀረበውን 45 ሚልዮን ፓውንድ ውድቅ ማድረጉ አይዘነጋም። ኒውካስል አሁን ላይ ዝውውሩን እውን ለማድረግ ከኖቲንግሀም ፎረስት ጋር ንግግር ላይ መሆናቸው ተዘግቧል። የ 23ዓመቱ አንቶኒ…
ኒውካስል ኢላንጋን ለማስፈረም ተስማማ !

ኒውካስል ዩናይትድ የኖቲንግሀም ፎረስቱን የፊት መስመር ተጨዋች አንቶኒ ኢላንጋ ለማስፈረም ከስምምነት ደርሰዋል።

ኒውካስል ተጫዋቹን 55 ሚልዮን ፓውንድ በሚደርስ የዝውውር ሒሳብ ለማስፈረም ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል።

አንቶኒ ኢላንጋ በኒውካስል ዩናይትድ ቤት የረጅም ጊዜ ውል እንደሚፈርም ፋብሪዝዮ ሮማኖ ዘግቧል።

የ 23ዓመቱ አንቶኒ ኢላንጋ ባለፈው አመት በሁሉም የፕርሚየር ሊግ ጨዋታዎች ለኖቲንግሀም ግልጋሎት ሰጥቷል።

ተጨዋቹ በጨዋታዎቹ ስድስት ጎሎች አስቆጥሮ 11 አመቻችቶ ማቀበልም ችሏል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሩበን አሞሪም የክለቡን ውሳኔ ውድቅ አደረጉ !

ማንችስተር ዩናይትድ ዘጋቢ ፊልም ለማዘጋጀት ከአሜሪካው ግዙፉ መዝናኛ ተቋም አማዞን ጋር ሲያደርገው የነበረውን ንግግር ማቋረጡ ተገልጿል።

ማንችስተር ዩናይትድ በሚቀጥለው የውድድር አመት ቡድኑ ከመጋረጃ ጀርባ የሚኖረውን ሁነት ዘጋቢ ፊልም ለማዘጋጀት ከአማዞን ጋር ንግግር ላይ ነበር።

አማዞን የቡድኑን ያልታዩ የመጋረጃ ጀርባ ሁነቶች ቀርፆ ለማቅረብ ለማንችስተር ዩናይትድ 10 ሚልዮን ፓውንድ ክፍያ አቅርበው እንደነበር ተገልጿል።

የክለቡ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኦማር ቤራዳ በሀሳቡ ተስማምተው የነበረ ቢሆንም አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ውድቅ ማድረጋቸው ተነግሯል።

ስምምነቱ ቢፈፀም አማዞን ማንችስተር ዩናይትድ ውስጥ ሁሉንም ቦታዎች የሚያካልል ያልተገደበ መዳረሻ ይኖረው እንደነበር ተዘግቧል።

ሩበን አሞሪም በበኩላቸው ቀድሞውን ችግር ውስጥ በሚገኘው መልበሻ ቤት ይህንን ማድረግ አላስፈላጊ ትኩረት ይስባል ማለታቸው ተገልጿል።

በተጨማሪም አሰልጣኙ መልበሻ ቤት ውስጥ የሚያሳዩት ባህሪ ተቀርጾ እንዳይወጣ መስጋታቸው ተነግሯል።

አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ባለፈው አመት በቡድኑ አቋም በመበሳጨት የመልበሻ ቤቱን ስክሪን መስበራቸው አይዘነጋም።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
ክረምትን በምን ሊያሳልፋ አስበዋል?

Can PlayStation 🎮 መፍትሄ ይዞ ብቅ ብሎሎታል🫴

-Sony
PlayStation 2
PlayStation 3
PlayStation 4
PlayStation 5

-Microsoft
Xbox 360
Xbox one
Xbox one s
Xbox Series

ምርቶችን አዘጋጅቶ እናንተን በመጠበቅ ላይ ነን
እንግዲያውስ እርሶ በተመቻቹ ሰአት ብቅ በማለት ሱቃችን መጎብኘት ይችላሉ

እቃዎቻችን 6 ወር ዋስትና ስላለው የለ ሀሳብ ይዝናኑ

ለልጅም ለአዋቂ የሚሆኑ PlayStation Cidi Game ስላሉን ይደውሉልን

Tv በተለያየ Brand እና Size እኛ ዘንድ ያገኛሉ

ባሎት ማንኛውም እቃ መቀያየር ይቻላል

ለክፍለ ሀገር እናቀርባለን ይደውሉ

🤝Tanks for choice

አድራሻ፡፦
ቁጥር 1፦  መገናኛ
ቁጥር  2፦  ቦሌ

ስልክ፦ 0904658609 ወይም                  0910529770
0977349492  ይደውሉ

ለአዳዲስ መረጃ Telegram channel join ይበሉ ፦
https://www.tg-me.com/CanPlaystation

                       👍Update Your Life

    Can PlayStation እና Tv Market
ኦዶች ዛሬም ከፍ ብለዋል!
ታዲያ ምን ይጠብቃሉ? ለማሸነፍ በተመቻቹ ኦዶች ይወራረዱ!
አሁኑኑ Betika.et ላይ ብቻ!
ቤቲካ የአሸናፊዎች ቤት!
የሊዮኔል ሜሲ ቀጣይ ማረፊያ የት ይሆናል ?

የ 38ዓመቱ ሊዮኔል ሜሲ ከ ኢንተር ሚያሚ ጋር ያለው ኮንትራት በ 2025 የውድድር ዘመን መጨረሻ የሚጠናቀቅ ይሆናል።

አርጀንቲናዊውን ኮከብ ለማስፈረም የሳውዲ አረቢያው የ እስያ ሻምፒየንስ ሊግ አሸናፊ አል አህሊ ከፍተኛ ፍላጎት ማሳየታቸው ታውቋል።

ኢንተር ሚያሚ ሊዮኔል ሜሲ በክለቡ ለማቆየት ቆየት ብለው ድርድር የጀመሩ ሲሆን በሚያሚ የሚያቆየውን ኮንትራት እንደሚፈርም እርግጠኞች ናቸው።

ኢንተር ሚያሚ ከዛሬ ጀምሮ በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት የሊዮኔል ሜሲን ውል ማራዘም ይፋ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ሊዮኔል ሜሲ ክለቡን ከተቀላቀለ በኃላ በ 42 የሊግ ጨዋታዎች 34 ጎሎችን ማስቆጠር ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
አርሰናል ተጨዋች ማስፈረም ተቃረበ ! የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል የብሬንትፎርዱን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ክርስቲያን ኖርጋርድ ለማስፈረም ከጫፍ መድረሳቸው ተገልጿል። መድፈኞቹ የ 31ዓመቱን አማካይ ክርስቲያን ኖርጋርድ በ 11 ሚልዮን ፓውንድ ለማስፈረም ከብሬንትፎርድ ጋር ለስምምነት መቃረባቸው ተነግሯል። አርሰናል ከተጨዋቹ በኩል በግል ጥቅማጥቅም ዙሪያ ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል። ዴንማርካዊው…
አርሰናል የኖርጋርድን ዝውውር አጠናቀቀ !

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል የብሬንትፎርዱን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ክርስቲያን ኖርጋርድ ዝውውር ማጠናቀቃቸው ተገልጿል።

መድፈኞቹ ለ 31ዓመቱ አማካይ ክርስቲያን ኖርጋርድ ዝውውር 10 ሚልዮን ፓውንድ እና ተጨማሪ ሁለት ሚልዮን ማውጣታቸው ተነግሯል።

ተጨዋቹ የህክምና ምርመራውን በማጠናቀቅ የአርሰናል ተጨዋች መሆኑ መረጋገጡን ለክለቡ ቅርብ የሆኑ ምንጮች አሳውቋል።

አርሰናል በሚቀጥሉት 48 ሰዓት የተጫዋቹን ፊርማ በይፋ ያሳውቃል ተብሎ ይጠበቃል።

ዴንማርካዊው አማካይ ክርስቲያን ኖርጋርድ ለብሬንትፎርድ በሁሉም ውድድሮች 192 ጨዋታዎች ሲያደርግ 13 ግቦችን ማስቆጠር ችሏል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
ባየር ሙኒክ ንኩንኩን ማስፈረም ይፈልጋል !

የጀርመን ቡንደስሊጋ ክለብ ባየር ሙኒክ ፈረንሳዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ክርስቶፈር ንኩንኩ ለማስፈርም በድጋሜ ኢላማ ማድረጋቸው ተገልጿል።

የቡንደስሊጋው አሸናፊ ባየር ሙኒክ ባለፈው አመት ተጫዋቹን ለማስፈረም እንቅስቃሴ አድርገው እንዳልተሳካላቸው ይታወሳል።

በዚህ ክረምት ኢላማ ያደረጓቸውን ፍሎሪያን ቨርትዝ እና ኒኮ ዊሊያምስ ያጡት ባየር ሙኒኮች ንኩንኩን ወደ ጀርመን ለመመለስ እንደሚፈልጉ ተዘግቧል።

ቼልሲዎች በበኩላቸው ተጨዋቹን መሸጥ የሚፈልጉት በቋሚ ዝውውር ብቻ መሆኑ ተገልጿል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
2025/07/08 08:03:30
Back to Top
HTML Embed Code: