Telegram Web Link
TIKVAH-SPORT
ዳርዊን ኑኔዝ ናፖሊን ለመቀላቀል ተስማማ ! ዩራጓዊው የፊት መስመር አጥቂ ዳርዊን ኑኔዝ በዚህ ክረምት ሊቨርፑልን ይለቃሉ ተብለው ከሚጠበቁ ተጨዋቾች መካከል ይጠቀሳል። አሁን ላይ ዳርዊን ኑኔዝ የጣሊያን ሴርያውን ክለብ ናፖሊ ለመቀላቀል መስማማቱ ተገልጿል። ይሁን እንጂ ለዝውውሩ እውን መሆን ናፖሊ በተጨዋቹ ዝውውር ሒሳብ ዙሪያ ከሊቨርፑል ጋር ከስምምነት መድረስ ይጠበቅባቸዋል። ኬቨን ዴብሮይንን…
ሊቨርፑል የናፖሊን ጥያቄ ውድቅ አደረገ !

ናፖሊ ዩራጓዊውን የፊት መስመር አጥቂ ዳርዊን ኑኔዝ ለማስፈረም ለሊቨርፑል ያቀረበው 50 ሚልዮን ዩሮ ውድቅ እንደተደረገበት ተገልጿል።

ናፖሊ በቀጣይ አዲስ የዝውውር ሒሳብ ያቀርባሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተነግሯል።

ዳርዊን ኑኔዝ የጣሊያን ሴርያውን ክለብ ናፖሊ ለመቀላቀል ቀደም ብሎ መስማማቱ አይዘነጋም።

ኬቨን ዴብሮይንን በነፃ ዝውውር ያስፈረሙት አሰልጣኝ አንቶኒዮ ኮንቴ በቀጣይ ቡድናቸውን ለማጠናከር ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛሉ።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
135😁33👍13👏3🙏2
ፒኤስጂ ተከላካዩ ሁለት ጨዋታ ይቀጣል !

ፊፋ የፒኤስጂውን የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ዊሊያን ፓቾ ሁለት ጨዋታዎች ለመቅጣት መወሰኑ ተገልጿል።

ተጨዋቹ ፒኤስጂ ባየር ሙኒክን ባሸነፈበት የሩብ ፍፃሜ ጨዋታ ቀይ ካርድ መመልከቱ አይዘነጋም።

ዊሊያን ፓቾ የሪያል ማድሪድን ጨዋታ ጨምሮ ፒኤስጂ ለፍፃሜ ከደረሰ የፍፃሜ ጨዋታው እንደሚያልፈው ተገልጿል።

በተጨማሪም ሌላኛው ተጨዋች ሉካስ ሄርናንዴዝ በተመሳሳይ ሁለት ጨዋታዎች እንደሚቀጣ ይፋ ተደርጓል።

የሪያል ማድሪዱ የመሐል ተከላካይ ዲን ሁይሰን በበኩሉ የአንድ ጨዋታ ቅጣት ተጥሎበታል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
114👍23😱17🔥2
የኒኮ ጎንዛሌዝ የማንችስተር ሲቲ ቆይታ ?

የማንችስተር ሲቲው የመሐል ሜዳ ተጨዋች ኒኮ ጎንዛሌዝ በቀጣይ ክለቡን ሊለቅ ይችላል መባሉ ሀሰተኛ መሆኑ ተገልጿል።

ተጨዋቹ በማንችስተር ሲቲ የሚቀጥለው የውድድር አመት እቅድ ውስጥ መሆኑን ለክለቡ ቅርብ የሆኑ ምንጮች አስነብበዋል።

ስፔናዊው አማካይ ኒኮ ጎንዛሌዝ ከአምስት ወራት በፊት ጥር ወር ላይ ከፖርቶ ማንችስተር ሲቲን መቀላቀሉ አይዘነጋም።

ተጨዋቹ ለማንችስተር ሲቲ 17 ጨዋታዎችን አድርጎ ሁለት ጎሎችን አስቆጥሯል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
137😁18👍14🔥2👏1
በፊፋ የክለቦች ዓለም ዋንጫ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ቼልሲ ፍሉሚንሴን ይገጥማል።

ቲያጎ ሲልቫ ከቀድሞ ቡድኑ ጋር ይጫወታል⚔️

⚽️ አንድም የጨዋታውን ደቂቃ እንዳያመልጥዎ ሁሉንም ጨዋታዎች በጎጆ ፓኬጅ ላይ በቻናል 223 ይመልከቱ! 📺

📣 አዲሱን የዲኤሲቲቪ ስጦታ እየተጠቀማችሁ ነው?

🎊 እስከ ሐምሌ 24 ድረስ ባሉት ቀናት በመረጡት የዲኤስቲቪ ፓኬጅ የአንድ ወር ሙሉ ክፍያ ሲከፍሉ ዲኤስቲቪ ያለተጨማሪ ክፍያ ከፍ ወዳለው ፓኬጅ ከተጨማሪ ቻናሎች ጋር በስጦታ ያገኛሉ!

ደንበኝነትዎን አሁኑኑ አራዝሙ ስጦታ ያግኙ!
⬇️
https://mydstv.onelink.me/vGln/xepsjmo7

ደንብና ሁኔታዎች ተፈፃሚነት አላቸው!

#ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia #FIFACWC
42👍2
#Wanawsportswear✔️

5ኛው አቃቂ ቃሊቲ ሰመር ካፕ በ40 የጤና ስፖርት ማህበራት ውድድር መካከል በድምቀት ተጀምሯል።

የመክፈቻ መርሀ ግብሩ ትእይንቶች
🟡የቀድሞ ብሄራዊ ቡድን ተጫዋች ዮርዳኖስ አባይ እና የግብጹ ዜድ ኢ ዲ ተጫዋች አቤል ያለው በክብር እንግዳነት ተገኝተዋል።
🟡አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ስፖርት ለሁሉም ኮሚቴ አዘጋጅንነት በ40 ጤና ስፖርት ማህበራት መካከል በሁለት ምድብ ተከፍሎ ተጀምሯል።
🟡08 ማዞሪያ 3ለ0 በሆነ ውጤት ውድድሩን ጀምሮታል።

⭐️ ዋናው የስፖርት አልባሳት ብራንድ የአቃቂ ቃሊቲ ሰመር ካፕ የጤና ስፖርት ማህበራት ውድድር ይፋዊ የስፖርት ትጥቅ አቅራቢ እና ስፖንሰር እንደምሆኑ ማህበሩ የሰነቀውን አላማ በመደገፍ የዚህ ዝግጅት ተሳታፊ ስለሆነ ኩራት ይሰማዋል።
🗓የአቃቂ ቃሊቲ ሰመር ካፕ እስከ ጥቅምት 2 /2018 ዓ.ም የሚቀጥል ይሆናል።

ለበለጠ መረጃ
8️⃣2️⃣8️⃣9️⃣

🔗 ማህበራዊ ገጾቻችን🔗
Instagram|Facebook |TikTok |X|Youtube
🔥🔥🔥🔥በኢትዮጵያ የተመረተ🔥🔥🔥🔥
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
34👎6🔥1
TIKVAH-SPORT
ዲያጎ ጆታ ህይወቱ ማለፉ ተገለፀ ! የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል የመስመር ተጫዋች ዲያጎ ጆታ በስፔን በደረሰበት የመኪና አደጋ ህይወቱ ማለፉን “ማርካ” አስነብቧል። መረጃውን የስፔኑ ማርካ ከደቂቃዎች በፊት ቢያወጣውም ክለቡ መረጃውን እስከ አሁን ይፋ አላደረገውም። ዛሞራ በተሰኘ አካባቢ ዲያጎ ጆታ በመኪና አደጋ ህይወቱ ማለፉ ሲገለፅ በመኪና ውስጥ የነበረው ወንድሙም ህይወቱ አልፏል። በደረሰው…
የመኪና አደጋው ምክንያት ምን ነበር ?

ከሳምንት በፊት የዲያጎ ጆታ እና ወንድሙን ህይወት የቀጠፈው የመኪና አደጋ የተፈጠረበትን ምክንያት የስፔን መንግሥት አስታውቋል።

የመኪና አደጋው የተፈጠረው ከተፈቀደው የፍጥነት መጠን በላይ በማሽከርከር ምክንያት መሆኑን የስፔን ሲቪል ጠባቂ ማረጋገጡን " AFP " አስነብቧል።

አደጋው በተከሰተበት ወቅት የሊቨርፑሉ የፊት መስመር ተጨዋች ዲያጎ ጆታ መኪናውን ሲያሽከረክር እንደነበር ተገልጿል።

ዲያጎ ጆታ ባደረገው ቀዶ ጥገና ምክንያት ከአየር ይልቅ የየብስ ትራንስፖርት እንዲጠቀም በሀኪሞች መነገሩን ተከትሎ ከስፔን በመኪና እየተጓዘ ነበር።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
😢34778😱10👍8🔥3😁2
“ ጨዋታው ለእኔ የተለየ ነው “ ቲያጎ ሲልቫ

የፍሉሚኔንሱ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ቲያጎ ሲልቫ ለእሱ የቀድሞ ክለቡ ቼልሲን መግጠም የተለየ መሆኑን ተናግሯል።

“ በጨዋታው ደስተኛ ነኝ “ ያለው ቲያጎ ሲልቫ ለእኔ የተለየ ቀን ይሆናል ነገርግን እነሱን ጥለን ካለፍን የበለጠ የተለየ ቀን ይሆናል “ ሲል ተደምጧል።

አክሎም “ ቼልሲ በህይወቴ በጣም ልዩ ክለብ ነው ላሳለፍኩት ነገር አመስጋኝ ነኝ እዛ ከትልቅ ዋንጫዎች አንዱን አሸንፌያለሁ “ ብሏል።

“ አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካን በደንብ አላውቃቸውም ነገርግን ብዙ የማውቃቸው ተጨዋቾች አሉ በየሳምንቱ እናወራለን የተወሰኑት ለእኔ ቅርብ ናቸው “ ቲያጎ ሲልቫ

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
🥰13590👍25😁11🔥4
የቪክቶር ዮኬሬሽ ዝውውር ለምን ዘገየ ?

መድፈኞቹ ስዊድናዊውን የፊት መስመር አጥቂ ቪክቶር ዮኬሬሽ ዝውውር በ 65 ሚልዮን ዩሮ እሁድ ያጠናቅቃሉ ተብሎ ሲጠበቅ ነበር።

ሆኖም ስፖርቲንግ ሊዝበን ለዝውውር 70 ሚልዮን ዩሮ መፈለግ ስምምነቱን ሊያዘገየው ምክንያት ሆኗል።

ሁለቱ ክለቦች በትላንትናው ዕለት ድርድራቸውን እንደቀጠሉ ሲገለፅ በዛሬው ዕለትም ከስምምነት ለመድረስ በስራ ላይ መሆናቸው ተዘግቧል።

ስምምነቱ ለመጠናቀቀ የተቃረበ መሆኑ ሲገለፅ በቀጣይ ሰዓታት አልያም በጥቂት ቀናት ውስጥ ይፋ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።

መድፈኞቹ ዝውውሩን እንደሚያጠናቅቁ እርገጠኞች ሲሆኑ ቪክቶር ዮኬሬሽ በግሉ ክለቡን የመቀላቀል ከፍተኛ ፍላጎት አለው።

ዮኬሬሽ ዝውውሩ እንዲሳካ እና ክለቡን ለመቀላቀል ከክለቡ ሀላፊዎች ጋር በግል የፅሁፍ መልዕክት እየተለዋወጠ እንደሚገኝ ተነግሯል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
444👍49👎39😁22🔥8💯8🙏2
TIKVAH-SPORT
አርሰናል የአሰልጣኝ ክፍሉን ሊያጠናክር ነው ! የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል የሚኬል አርቴን የአሰልጣኝ ቡድን አባላት ለማጠናከር አዲስ ሀላፊዎችን ሊሾም መሆኑ ታውቋል። ክለቡ ካርሎስ ኩዌታን ማጣቱን ተከትሎ በምትኩ የቀድሞ የማንችስተር ዩናይትድን ተጫዋቹን ጋብሬል ሄይንዜን ሊሾም መሆኑ ተዘግቧል። ሚኬል አርቴታ እና ጋብሬል ሄይንዜ ከዚህ ቀደም በ 2001/02 የውድድር ዘመን በፒኤስጂ ቤት አብረው…
ጋብሬል ሄይንዜ አርሰናልን ተቀላቀለ!

የቀድሞው የማንችስተር ዩናይትድ ተጫዋች ጋብሬል ሄይንዜ የአርሰናልን አሰልጣኝ ቡድን አባላት መቀላቀሉን ክለቡ ይፋ አድርጓል።

የ 47 አመቱ ጋብሬል ሄይንዜ የአርቴታን የአሰልጣኝ ቡድን አባላት በይፋ መቀላቀሉን መድፈኞቹ አስታውቀዋል።

አርሰናል ከወራት በፊት ላጡት ካርሎስ ኩዌስታ ሁነኛ ተተኪ ብለው ያሰቡትን ጋብሬል ሄዬንዜን የግላቸው ማድረግ ችለዋል።

አርጀንቲናዊው ጋብሬል ሄይንዜም በቀጣይ የተለያዩ የአጨዋወት ስልቶችንና በአሰልጣኝነቱም ዘርፍ ያላቸውን ልምድ በማካፈል ለቡድኑ መሻሻል ጉልህ ሚና እንደሚያበረክቱ ይጠበቃል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
242👏25😁22👎7👍5🔥1
TIKVAH-SPORT
ጇ ፔድሮ ምን አይነት ተጨዋች ነው ? የለንደኑ ክለብ ቼልሲ ብራዚላዊውን የፊት መስመር አጥቂ ጇ ፔድሮ ከ 50 ሚልዮን ፓውንድ በላይ በማውጣት ወደ ስብሰባቸው ቀላቅለዋል። ተጨዋቹ በእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ጨዋታዎች ጥሩ የሚባል ግብ የማስቆጠር እና አመቻችቶ የማቀበል ቁጥር ይዟል። ፔድሮ በፕርሚየር ሊጉ በአማካይ በ 90 ደቂቃ 0.35 ጎል የማስቆጠር እና 0.16 ለግብ የሆነ ኳስ አመቻችቶ የማቀበል…
" ወደ ቼልሲ ያመራሁት ዋንጫ ለማሸነፍ ነው " ፔድሮ

አዲሱ የቼልሲ ፈራሚ ጇ ፔድሮ ለትልቅ ክለብ የመጫወት ህልም ነበረኝ ሲል ክለቡን ስለተቀላቀለበት ምክንያት ተናግሯል።

“ ቼልሲ ትልቅ ክለብ ነው “ ያለው ጇ ፔድሮ " እኔ ደግሞ ህልሜ ለትልቅ ክለብ መጫወት እና ዋንጫዎችን ማሸነፍ ነው ብሏል።

“ ቼልሲ ወጣት እና ምርጥ ቡድን አለው ወደዚህ የመጣሁበት ምክንያት ይህ ነው ለአዲስ ፈተና ዝግጁ ነኝ “ ፔድሮ

ብራዚላዊው የፊት መስመር ተጨዋች ጇ ፔድሮ በምሽቱ ጨዋታ የልጅነት ክለቡ ፍሉሚኔንስን በተቃራኒው ሊግጥም ይችላል።

ጇ ፔድሮ በፍሉሚኔስ ዋናው ቡድን አንድ የውድድር አመት ሲያሳልፍ በ 36 ጨዋታዎች 10 ጎሎችን አስቆጥሯል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
😁129113👏14👍13👌3👎1🔥1
#ClubWorldCup 🇺🇸

አዲሱ የቼልሲ ፈራሚ ጇ ፔድሮ የቀድሞ ክለቡን ፍሉሚኔንሴ ዛሬ ምሽት ሊገጥም ይችላል።

ጇ ፔድሮ ከ ፍሉሚኔንሴ አካዳሚ የተገኘ ሲሆን በተከላካይ አማካይ ሚና ቡድኑን በ 2011 ተቀላቅሎ ነበር።

ጇ ፔድሮ ከስምንት አመታት ቆይታ በኃላ የመጀመሪያ ጨዋታውን በአስራ ሰባት አመቱ ለክለቡ ማድረግ ችሏል።

በሰላሳ ስድስት ጨዋታዎች ለፍሉሚኔንሴ ተሰልፎ የተጫወተው ጇ ፔድፎ አስር ግቦችንም ማስቆጠር ችሎ ነበር።

ከ ጇ ፔድሮ በተጨማሪም ቲያጎ ሲልቫ የቀድሞ ቡድኑን ቼልሲ ምሽቱን በተቃራኒ የሚገጥም ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
126👍25😱9🔥8😁5🤬5👏2
#ClubWorldCup 🇺🇸

አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ በምሽቱ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ የሁለት ተጨዋቾች ቅያሬ አድርገው ወደ ሜዳ ለመግባት ይገደዳሉ።

ሰማያዊዎቹ በሩብ ፍፃሜው ሁለት ተጨዋቾቻው በውድድሩ ሁለተኛ ቢጫ ካርድ መመልከታቸውን ተከትሎ የዛሬው ጨዋታ በቅጣት ያመልጣቸዋል።

ሊያም ዴላፕ እና ሌቪ ኮልዊል የዛሬው ጨዋታ ሲያመልጣቸው ቼልሲ በቋሚ አሰላለፉ ላይ በምትኩ ሌሎች ተጨዋቾችን ማሰለፍ ያስፈልገዋል።

የቡድኑ ቁልፍ ተጨዋች ሞይሰስ ካይሴዶ ቅጣቱን ጨርሶ ለጨዋታው ዝግጁ መሆኑ ለሰማያዊዎቹ መልካሙ ዜና ነው።

የሊያም ዴላፕን መቀጣት ተከትሎ ጇ ፔድሮ  የመጀመሪያ ጨዋታውን በቋሚነት ተሰልፎ ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
135👍11😢2
TIKVAH-SPORT
ቦታፎጎ ዴቪድ አንቾሎቲን እያነጋገሩ ነው ! ከቀናት በፊት አሰልጣኙን ያሰናበተው የብራዚሉ ክለብ ቦታፎጎ አሰልጣኝ ዴቪድ አንቾሎቲን ለመሾም ንግግር ላይ መሆናቸው ተገልጿል። የአሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ ልጅ ዴቪድ አንቾሎቲ በቅርቡ የብራዚል ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ቡድንን መቀላቀሉ አይዘነጋም። የ 35ዓመቱ አሰልጣኝ ዴቪድ አንቾሎቲ አሁን ላይ ቦታፎጎን ሊረከቡ እንደሚችሉ የብራዚል መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።…
ዴቪድ አንቾሎቲ በሀላፊነት ተሾሟል !

አሰልጣኝ ዴቪድ አንቾሎቲ ከቀናት በፊት አሰልጣኙን ያሰናበተውን የብራዚሉ ክለብ ቦታፎጎ በሀላፊነት መረከቡ ይፋ ተደርጓል።

የአሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ ልጅ ዴቪድ አንቾሎቲ በቅርቡ የብራዚል ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ቡድንን መቀላቀሉ አይዘነጋም።

የ 35ዓመቱ አሰልጣኝ ዴቪድ አንቾሎቲ እስከ 2026 ውድድር አመት መጨረሻ ቦታፎጎን ለመምራት ፊርማውን አኑሯል።

አሰልጣኙ በቀጣዩ የ 2026 አለም ዋንጫ ውድድር ወደ ብራዚል ብሔራዊ ቡድን በመመለስ ከአባቱ ጋር እንደሚሰራ ተገልጿል።

ዴቪድ አንቾሎቲ ከ 2011 ጀምሮ ከአባቱ ጋር የሰራ ሲሆን ባለፉት አመታት ሪያል ማድሪድ ሁለት የላሊጋ እና ሁለት የሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ ሲያሳካ ጉልህ ሚና ነበረው።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
102👍46🔥3😁1
“ ዮከሬሽ ገና በትልቅ ሊግ አልታየም “ ፈርዲናንድ

የቀድሞ እንግሊዛዊ ተጨዋች ሪዮ ፈርዲናንድ አርሰናልን ለመቀላቀል የተቃረበው ቪክቶር ዮኬሬሽ በትልቅ ሊግ ራሱን አላሳየም በማለት ገልጿል።

" ለፖርቹጋል ሊግ ክብር አለኝ በጣም ጥሩ ሊግ ነው ነገርግን ትልቅ አይደለም “ ሲል ፈርዲናንድ ተናግሯል።

አክሎም “ ስለዚህ ዮኬሬሽ ለፕርሚየር ሊግ ክለብ ከፈረም ማን እንደሆነ ማሳየት ይጠበቅበታል እስካሁን በትልቅ ሊግ ስኬት አላሳየም “ሲል ተደምጧል።

ስዊድናዊው የፊት መስመር አጥቂ ቪክቶር ዮከሬሽ አርሰናልን ለመቀላቀል ከጫፍ መድረሱ አይዘነጋም።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
😁266154👍82👎11💯8👏4🤬3🤔1
2025/07/09 23:34:03
Back to Top
HTML Embed Code: