TIKVAH-SPORT
ማድሪድ ሮድሪጎን ለመሸጥ ዝግጁ መሆኑ ተገለጸ ! ሪያል ማድሪድ እና አሰልጣኝ ዣቢ አሎንሶ ብራዚላዊውን ተጨዋች ሮድሪጎን በዚህ ክረምት ለመሸጥ ዝግጁ መሆናቸው ተገልጿል። ትክክለኛው የዝውውር ሒሳብ የሚቀርብ ከሆነ ክለቡ በተጨዋቹ መንገድ ላይ ላለመቆም ከስምምነት መደረሱ ተዘግቧል። የ 24ዓመቱ ሮድሪጎ ሪያል ማድሪድ በክለቦች አለም ዋንጫ የመክፈቻ ጨዋታ ሲያደርግ ከ 53 ቀናት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ…
የሮድሪጎ የሪያል ማድሪድ ቆይታ ?
ሪያል ማድሪድ ብራዚላዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ሮድሪጎ በዚህ ክረምት ለመሸጥ ዝግጁ መሆኑ መገለፁ አይዘነጋም።
ሎስ ብላንኮዎቹ አሁን ላይ የሮድሪጎን የወደፊት ቆይታ ለመወሰን በሚቀጥለው ሳምንት ከተጨዋቹ ጋር ለንግግር እንደሚቀመጡ ተገልጿል።
ሪያል ማድሪድ ሮድሪጎንን ለመልቀቅ ዝግጁ መሆኑ ሲገለፅ ውሳኔው ለተጨዋቹ እንደሚሰጥ ተነግሯል።
ሮድሪጎ በቀጣይ ወደ ሳውዲ አረቢያ ማምራት እንደማይፈልግ እና በአውሮፓ መቆየት እንደሚፈልግ ተዘግቧል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe

❤194👍16😁8🤬6😢4
የሚላን ጨዋታ በሌላ ሀገር ሊደረግ ይችላል !
ኤሲ ሚላን እና ኮሞ በ 2026 የካቲት ወር ውስጥ የሚያደርጉት የጣልያን ሴርያ ጨዋታ ከሀገር ውጪ ሊደረግ መሆኑ ተገልጿል።
ጨዋታው ከሀገር ውጪ የሚደረገው ጨዋታው በሚደረግበት ዕለት ባለው የመርሐግብር መደራረብ ምክንያት መሆኑ ተገልጿል።
ጨዋታው በሚካሄድበት ዕለት በሳን ሲሮ የ 2026 ኦሎምፒክ ጨዋታዎች መክፈቻ ስነስርዓት እንደሚካሄድ ተነግሯል።
አሁን ላይ የጣልያን እግርኳስ ፌዴሬሽን ክለቦቹ ጨዋታውን ከሀገር ውጫ ለማድረግ ያቀረቡትን ጥያቄ ማፅደቁ ተገልጿል።
ጨዋታው አውስትራሊያ የሚካሄድ ከሆነ ከአውሮፓ ውጪ የተካሄደ በታሪክ የመጀመሪያው የአውሮፓ ሊግ ጨዋታ ይሆናል።
በቀጣይ የፊፋ እና አውሮፓ እግርኳስ ማህበር ፍቃድ እንደሚጠበቅ ተነግሯል።
@Tikvahethsport @kidusyoftahe

❤104👍19
ቶተንሀም ጊቢስ ዋይትን ማስፈረም ይፈልጋል !
የሰሜን ለንደኑ ክለብ ቶተንሀም ሞርጋን ጊብስ ዋይትን ከኖቲንግሀም ፎረስት ማስፈረም እንደሚፈልጉ ዘ አትሌቲክ ዘግቧል።
አዲሱ የቶተንሀም አለቃ ቶማስ ፍራንክ የእንግሊዛዊው አማካይ ሞርጋን ጊብስ ዋይት የረጅም ጊዜ አድናቂ መሆናቸው ተገልጿል።
ቶተንሀም አሁን ላይ በሌሎች ክለቦች የሚፈለገው ሞርጋን ጊብስ ዋይት እንዲቀላቀላቸው ለማሳመን እየሰሩ መሆኑ ተነግሯል።
የ 25ዓመቱ ሞርጋን ጊብስ ዋይት ከሶስት አመታት በፊት ከዎልቭስ ኖቲንግሀምን በመቀላቀል ባለፉት አመታት ጎልተው መውጣት ከቻሉ የሊጉ ተጨዋቾች መካከል አንዱ ሆኗል።
ሞርጋን ጊብስ ዋይት በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኖቲንግሀም ቀልፍ ተጨዋቾች መካከል አንዱ ሲሆን ሰባት ጎሎችን አስቆጥሮ 10 አመቻችቶ አቀብሏል።

❤163😱16👍12👎2🥰1😁1
TIKVAH-SPORT
አርሰናል ከቼልሲ ጋር ንግግር ጀመረ ! የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል እንግሊዛዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ኖኒ ማዱኬ ለማስፈረም ከቼልሲ ጋር ንግግር መጀመራቸው ተገልጿል። ሁለቱ ክለቦች በአሁን ሰዓት ዝውውሩን እውን ለማድረግ በድርድር ላይ ሲገኙ ተጨዋቹ አርሰናልን ለመቀላቀል መስማማቱ ይታወሳል። የ 23ዓመቱ የፊት መስመር ተጨዋች ኖኒ ማዱኬ ለአርሰናል የአምስት አመት ኮንትራት ለመፈረም ቃሉን…
የአርሰናል ደጋፊዎች ማዱኬን ለምን ተቃወሙ ?
አርሰናል ኖኒ ማዱኬን ከቼልሲ ለማስፈረም የሚያደርገው ጥረት የክለቡን ደጋፊዎች እንዳላስደሰተ ተገልጿል።
ደጋፊዎቹ ተጨዋቹ እንዳይፈርም በማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ የጀመሩ ሲሆን ድምፅ ማሰባሰብም ጀምረዋል።
ዝውውሩ ለቼልሲ ጥቅም ይኖረዋል ?
ሰማያዊዎቹ ኖኒ ማዱኬን በዚህ ክረምት ለአርሰናል መሸጥ የቡድናቸውን ሚዛን ለመጠበቅ ይረዳቸዋል።
ፔድሮ ኔቶ በቀኝ ተሰልፎ በክለቦች አለም ዋንጫ ኢንዞ ማሬስካን ማሳመኑ እንዲሁም ፓልመር በቦታው ተስቦ እንዲጫወት መደረጉ ቦታውን አስተማማኝ አድርጎታል።
በተጨማሪም በቅርቡ ቡድኑን የሚቀላቀለው እስቴቫኦ ፣ ጇ ፔድሮ እና ታይሪክ ጆርጅ በቀኝ ተሰልፈው መጫወት የሚችሉ ተጨዋቾች ናቸው።
እንዲሁም ቼልሲ የዩኤፋን የፋይናንስ ደንብ ለማስተካከል የማዱኬን ሽያጭ ጥሩ እድል አድርገው መመልከታቸው ተገልጿል።
አርሰናል ከዝውውሩ ምን ይጠቀማል ?
ኖኒ ማዱኬ ለአርሰናል መፈረም የፊት መስመራቸው እንዲጠናከር እንዲሁም በቀኝ መስመር ቡካዩ ሳካን ለማገዝ ይረዳቸዋል።
ተጨዋቹ በግራ በኩል መጫወት መቻሉ ለአርሰናል ሌላኛው ጥቅም ቢሆንም አርቴታ በቦታው የግራ እግር ተጨዋች ማሰለፍ ይመርጣሉ።
የአርሰናል ደጋፊዎች ለምን ተቃወሙ ?
የአርሰናል ደጋፊዎች ዝውውሩን የተቃወሙት ከዚህ በፊት ከተደረጉ ሌሎች ዝውውሮች ጋር በማነፃፀር መሆኑ ተገልጿል።
ደጋፊዎቹ የማዱኬ ዝውውር ከአጥቂ ፊርማ በኋላ ቢነገር ምናልባት አስተሳሰባቸው ይቀየር ነበር ተብሏል።
ሌላኛው ደጋፊዎቹን ያስቆጣው ዋነኛው ምክንያት ኖኒ ማዱኬ ሌላ የቼልሲ ተጨዋች መሆኑ እንደሆነ ተነግሯል።
ከዚህ በፊት ከቼልሲ አርሰናልን የተቀላቀሉ አብዛኞቹ ተጨዋቾች ስኬታማ ጊዜ ሳያሳልፉ ነበር ክለቡን የለቀቁት።

❤366😁117👍27👎6🔥2🎉1
ኖቲንግሀም ዊሳን ለማስፈረም ሥራ ጀምሯል !
ኖቲንግሃም ፎረስት ዮአን ዊሳን ከብራንትፎርድ ለማስፈረም በድጋሜ እንቅስቃሴ መጀመራቸው ተገልጿል።
ኖቲንግሃም ፎረስት ባለፈው ጥር ተጫዋቹን ለማስፈረም እስከ 25 ሚልዮን ፓውንድ አቅርበው ሳይሳካለችው መቅረቱ አይዘነጋም።
ኖቲንግሀም አሁን ላይ ተጫዋቹን ለማስፈረም ከበፊቱ ያነሰ የዝውውር ሒሳብ ያቀረቡ ሲሆን ብሬንትፎርድ ውድቅ ማድረጉ ተነግሯል።
ብሬንትፎርድ ለ 28 ዓመቱ ኮንጓዊ የፊት መስመር ተጨዋች ከ 50 ሚልዮን ፓውንድ በላይ እንደሚፈልግ ተዘግቧል።
ዊሳ ባለፈው የውድድር አመት ለብሬንትፎርድ 19 የፕርሚየር ሊግ ግቦችን አስቆጥሯል።

❤147🤔28🤬10👍6👎6👏1😁1
የዮኬሬሽ ዝውውር በምን ሁኔታ ላይ ነው ?
አርሰናል የስፖርቲን ሊዝበኑን የፊት መስመር አጥቂ ቪክቶር ዮኬሬሽ ለማስፈረም አሁንም በንግግር ላይ መሆናቸው ተገልጿል።
የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ዛሬ የቪክቶር ዮኬሬሽን ዝውውር ሊያቋርጥ መሆኑ ተዘግቦ ነበር።
ይሁን እንጂ አርሰናሎች አሁንም ዝውውሩን ለማጠናቀቅ በመስራት ላይ መሆናቸው እና ዝውውሩ እንዳልተቋረጠ ተገልጿል።
አርሰናል ተጫዋቹን እነሱ በፈለጉት መንገድ ለማስፈረም በጥረት ላይ ሲሆኑ ስፖርቲንግ ሊዝበን ከሚፈልገው ጋር የተወሰነ ክፍተት እንዳለ ተዘግቧል።
ቪክቶር ዮኬሬሽ በበኩሉ ክለቡን መልቀቅ እንደሚፈልግ በግልጽ ለክለቡ ፕሬዝዳንት በማሳወቅ ነገ ልምምድ ላይ አልገኝም ማለቱ ተነግሯል።
ተጨዋቹ በዝውውር ሒሳቡ ላይ ያለውን ክፍተት ለማስተካከል እንዲረዳ ከደሞዙ ላይ ሁለት ሚልዮን ዩሮ እንደተወ ተነግሯል።

❤407😁92👏26👎22🔥20👍5🤔2
ኦባሚያንግ ወደ ማርሴይ ሊመለስ ይችላል !
ጋቦናዊው የፊት መስመር ተጨዋች ፔር ኤምሪክ ኦባሚያንግ ከሳውዲ አረቢያ ሊግ ለመልቀቅ መቃረቡ ተገልጿል።
ፔር ኤምሪክ ኦባሚያንግ ከሳውዲ አረቢያው ክለብ አል ቃዲሲያ ጋር ያለውን ኮንትራት እንደሚያቋርጥ ተዘግቧል።
የፈረንሳዩ ክለብ ማርሴይ በበኩሉ ዛሬ የቀደሞ ተጨዋቹ ፔር ኤምሪክ ኦባምያንግን ወደ ቡድኑ ለመመለስ ማነጋገራቸው ተነግሯል።
ማርሴይ ተጫዋቹን የሚያስፈርሙት ከደሞዝ ክፍያውን የሚቀንስ ከሆነ መሆኑ ተዘግቧል።

❤139👍26😁18
ክርስቲያን ኖርጋርድ ምን አይነት ተጨዋች ነው ?
አርሰናሎች የ 31ዓመቱን አማካይ ክርስቲያን ኖርጋርድ ከብሬንትፎርድ በማስፈረም የመሐል ክፍሉን አጠናክረዋል።
መድፈኞቹ በመከላከል ረገድ ልምድ ያካበተ እና ጥሩ ብቃት ያለው እንዲሁም ጠንካራ አማካይ ወደ ስብሰባቸው ቀላቅለዋል።
ኖርጋርድ ሙከራዎችን ተደርቦ በማውጣት እንዲሁም ተጋጣሚ ሲያጠቃ በማደናቀፍ እና በሚያደርጋቸው ስኬታማ ሸርተቴዎች ይታወቃል።
በተጨማሪም ኖርጋርድ የአየር ላይ ኳሶችን የመቆጣጠር ብቃት ያለው የተከላካይ አማካይ ነው።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ተጨዋቹ አሁን ላይ የማጥቃት አቅሙን ቢያሻሽልም በቀጣይ በማጥቃቱ ረገድ አስተዋጽኦ ያደርጋል ተብሎ አይጠበቅም።
ባለፈው የውድድር አመት አምስት ጎሎችን አስቆጥሮ አራት አመቻችቶ ያቀበለው ተጨዋቹ በግልጽ የሚታየው ጥንካሬው መከላከሉ ላይ እንደሆነ ተገልጿል።
ተጨዋቹ በማጥቃት እንቅስቃሴ ውስጥ በሚያቀብላቸው ኳሶች ቡድኑን በመርዳት ተፅዕኖ መፍጠር ይችላል።
ኖርጋርድ በአርሰናል የሚኖረው ሚና ኳስ በፍጥነት በማንቀሳቀስ የኦዴጋርድ እና ዴክላን ራይስን ኳስ የማግኘት አቅም መጨመር እንደሚሆን ተነግሯል።

❤213😁36👍26👌4👎3
ሪያል ማድሪድ ተጫዋች ለማስፈረም ተስማማ !
የላሊጋው ክለብ ሪያል ማድሪድ የግራ መስመር ተጫዋቹን አልቫሮ ካሬራስ ለማስፈረም ከቤንፊካ ጋር መስማማታቸው ተገልጿል።
ሪያል ማድሪድ ካሬራስ በቤንፊካ ቤት ያለውን 5️⃣0️⃣ ሚልዮን ዩሮ የውል ማፍራሻ በመክፈል ለማስፈረም ተስማምተዋል።
አልቫሮ ካሬራስ በሪያል ማድሪድ አካዳሚ የነበረ ሲሆን በፈረንጆቹ ከ 2017 እስከ 2020 ለዋናው ቡድን ምንም አይነት ግልጋሎት ሳይሰጥ ማንችስተር ዩናይትድን ተቀላቅሎም ነበር።
ማንችስተር ዩናይትዶች ከዝውውሩ ባላቸው ኮንትራት መሰረት 7.6 ሚልዮን ፓውንድ ክፍያ የሚያገኙ ይሆናል።
ካሬራስ በቤንፊካ ቤት 6️⃣5️⃣ ጨዋታዎችን አድርጎ 5️⃣ ጎሎችን ሲያስቆጥር 6️⃣ ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።

❤155👍21🤔10
“ ለማድሪድ ሁሉንም እንደሰጠ ተጨዋች መታወስ እፈልጋለሁ “ ሞድሪች
የሪያል ማድሪዱ ታሪካዊ ተጨዋች ሉካ ሞድሪች " አሁንም በሪያል ማድሪድ ደጋፊነቴ እቀጥላለሁ " ሲል ከስንብቱ በኋላ ተናግሯል።
“ የሪያል ማድሪድ ደጋፊዎች ለእኔ ያላቸውን ፍቅር መቼም አልረሳውም " ያለው ሞድሪች አሁንም ማድሪዲስታ መሆኔ ለዘለዓለም ይቀጥላል ብሏል።
“ የማይረሳ ረጅም ጉዞ ነበር ሪያል ማድሪድ ቤቴ ነው ሁሉንም ነገር ሰጥቶኛል በቀሪው ህይወቴ ሳመሰግነው እኖራለሁ “ ሲል ሞድሪች ተናግሯል።
“ ሰዎች እኔን እንደ ጥሩ ሰው እና ሁልጊዜም ለሪያል ማድሪድ ያለውን ሁሉ የሰጠ ተጨዋች አድርገው እንዲያስታውሱኝ እፈልጋለሁ።“ ሉካ ሞድሪች
ሉካ ሞድሪች በቀጣይ የጣልያን ሴርያውን ክለብ ኤሲ ሚላን የመቀላቀል ይሆናል።

❤398👏52🥰10👍2
TIKVAH-SPORT
ቶተንሀም ተጨዋች ለማስፈረም ተስማማ ! የሰሜን ለንደኑ ክለብ ቶተንሀም ጋናዊውን የፊት መስመር ተጨዋች መሐመድ ኩዱስ ለማስፈረም ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል። ቶተንሀም ተጫዋቹን በ 55 ሚልዮን ፓውንድ ለማስፈረም ከስምምነት መድረሱ ተዘግቧል። መሐመድ ኩዱስ ነገ ሐሙስ የህክምና ምርመራውን በማድረግ ለቶተንሀም የስድስት አመት ኮንትራት እንደሚፈርም ተነግሯል። ተጨዋቹ ዌስትሀም ዩናይትድን ከለቀቀ…
ቶተንሀም በይፋ ተጨዋች አስፈረመ !
የሰሜን ለንደኑ ክለብ ቶተንሀም ጋናዊውን የፊት መስመር ተጨዋች መሐመድ ኩዱስ ከዌስትሀም ማስፈረማቸውን ይፋ አድርገዋል።
ቶተንሀም ተጫዋቹን በ 55 ሚልዮን ፓውንድ የዝውውር ሒሳብ በማውጣት ማስፈረማቸው ተገልጿል።
" ቶተንሀምን ብቻ ነበር መቀላቀል የፈለኩት “ ሲል መሐመድ ኩዱስ ለቶተንሀም የስድስት አመት ኮንትራት ከፈረመ በኋላ ተናግሯል።
ባለፈው የውድድር አመት መሐመድ ኩዱስ በ 35 የፕርሚየር ሊግ ጨዋታዎች አምስት ጎሎችን ሲያስቆጥር አራት አመቻችቶ አቀብሏል።

❤127😁59👍32😱9🔥5🤔3👎2
TIKVAH-SPORT
የአርሰናል ደጋፊዎች ማዱኬን ለምን ተቃወሙ ? አርሰናል ኖኒ ማዱኬን ከቼልሲ ለማስፈረም የሚያደርገው ጥረት የክለቡን ደጋፊዎች እንዳላስደሰተ ተገልጿል። ደጋፊዎቹ ተጨዋቹ እንዳይፈርም በማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ የጀመሩ ሲሆን ድምፅ ማሰባሰብም ጀምረዋል። ዝውውሩ ለቼልሲ ጥቅም ይኖረዋል ? ሰማያዊዎቹ ኖኒ ማዱኬን በዚህ ክረምት ለአርሰናል መሸጥ የቡድናቸውን ሚዛን ለመጠበቅ ይረዳቸዋል። ፔድሮ ኔቶ በቀኝ…
አርሰናል ማዱኬን ለማስፈረም ተስማማ !
የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል እንግሊዛዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ኖኒ ማዱኬ ለማስፈረም ከቼልሲ ጋር ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል።
አርሰናል ተጫዋቹን 50 ሚልዮን ፓውንድ በሚደርስ የዝውውር ሒሳብ ለማስፈረም ከቼልሲ ጋር ከስምምነት ደርሰዋል።
ተጨዋቹ ከዚህ በፊት በአርሰናል ቤት የአምስት አመት ውል ለመፈረም መስማማቱ የሚታወስ ሲሆን አሁን ዝውውሩን እንዲያጠናቅቅ ከቼልሲ ፍቃድ አግኝቷል።
ኖኒ ማዱኬ በዚህ አመት ለቼልሲ 45 ጨዋታዎች ሲያደርግ 11 ግቦችን አስቆጥሮ አምስት አመቻችቶ አቀብሏል።
ቼልሲ ኖኒ ማዱኬን ከሁለት አመታት በፊት ከፒኤስቪ በ 29 ሚልዮን ፓውንድ ማስፈረማቸው አይዘነጋም።

😁475👎171❤153👍66🔥13😢9🤬5👏1
ክረምትን በምን ሊያሳልፋ አስበዋል?
Can PlayStation 🎮 መፍትሄ ይዞ ብቅ ብሎሎታል🫴
-Sony
PlayStation 2
PlayStation 3
PlayStation 4
PlayStation 5
-Microsoft
Xbox 360
Xbox one
Xbox one s
Xbox Series
ምርቶችን አዘጋጅቶ እናንተን በመጠበቅ ላይ ነን
እንግዲያውስ እርሶ በተመቻቹ ሰአት ብቅ በማለት ሱቃችን መጎብኘት ይችላሉ
እቃዎቻችን 6 ወር ዋስትና ስላለው የለ ሀሳብ ይዝናኑ
ለልጅም ለአዋቂ የሚሆኑ PlayStation Cidi Game ስላሉን ይደውሉልን
Tv በተለያየ Brand እና Size እኛ ዘንድ ያገኛሉ
ባሎት ማንኛውም እቃ መቀያየር ይቻላል
ለክፍለ ሀገር እናቀርባለን ይደውሉ
🤝Tanks for choice
ስልክ፦ 0904658609 ወይም
0977349492 ይደውሉ
ለአዳዲስ መረጃ Telegram channel join ይበሉ ፦
https://www.tg-me.com/CanPlaystation
👍Update Your Life
Can PlayStation እና Tv Market

❤39🥰2😁1
TIKVAH-SPORT
“ የክለቦች አለም ዋንጫ የደከመ ሀሳብ ነው “ ክሎፕ ጀርመናዊው አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ አዲሱን የክለቦች አለም ዋንጫ ውድድር መጀመር ሀሳብ “ የማይረባ ሀሳብ “ ሲሉ ተችተዋል። “ የክለቦች አለም ዋንጫን የመጀመር ሀሳብ በእግርኳስ ከተተገበሩ ጥሩ ያልሆኑ ውሳኔዎች መካከል የከፋው ነው “ ሲሉ የርገን ክሎፕ ተናግረዋል። ውድድሩ በሚቀጥለው የውድድር አመት “ ተጨዋቾች ገጥሟቸው የማያውቀው ጉዳት…
“ የክለቦች አለም ዋንጫ ያስፈልጋል “ ቬንገር
የቀድሞ ፈረንሳዊ አሰልጣኝ አርሴን ቬንገር የክለቦች አለም ዋንጫ ውድድር አስፈላጊ ነው የሚል እምነት እንዳላቸው ገልጸዋል።
በቅርቡ አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ የውድድሩ መጀመር ላይ ላቀረቡት ትችት ምላሽ የሰጡት አርሴን ቬንገር " የውድድሩ ሀሳብ ደጋፊ ነኝ " ብለዋል።
የቀድሞ የአርሰናል ታሪካዊ አሰልጣኝ አርሴን ቬንገር አሁን ላይ በፊፋ አለምአቀፍ የእግርኳስ እድገት ሀላፊ በመሆን እያገለገሉ ይገኛሉ።
" የክለቦች አለም ዋንጫ ውድድር ያስፈልጋል “ ያሉት አርሴን ቬንገር እዚህ የነበሩትን ሁሉንም ክለቦች ብትጠይቁ በድጋሜ መወዳደር ይፈልጋሉ ብለዋል።
ውድድሩ በደጋፊዎች ስለመወደዱ ያነሱት አርሴን ቬንገር “ የተመልካች ቁጥር ዝቅተኛ ነው ተብሎ ቢገመትም ከፍ ብሎ ታይቷል ምላሹ ይሄ ነው " ሲሉ ተደምጠዋል።
የ 2025 የ ክለቦች አለም ዋንጫ ውድድር ዕሁድ ቼልሲ ከፒኤስጂ ጋር በሚያደርጉት የፍፃሜ ጨዋታ ይጠናቀቃል።

👍164❤91😁52👎30👏6🤔2🔥1
ሄንደርሰን ብሬንትፎርድን ለመቀላቀል ተስማማ !
እንግሊዛዊው አማካይ ጆርዳን ሄንደርሰን የፕርሚየር ሊጉን ክለብ ብሬንትፎርድ ለመቀላቀል ከስምምነት መድረሱ ተገልጿል።
ሄንደርሰን ከአያክስ ጋር መለያየቱን ተከትሎ ከኮንትራት ነፃ ሲሆን በቀጣይ ብሬንትፎርድን በነፃ ዝውውር የሚቀላቀል ይሆናል።
የ 35ዓመቱ አማካይ ጆርዳን ሄንደርሰን ወደ እንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ በመመለስ የሁለት አመት ውል እንደሚፈርም ተነግሯል።
ጆርዳን ሄንደርሰን ሌሎች ዝውውሮች ቢቀርቡለትም ወደ እንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ለመመለስ መወሰኑን ተከትሎ ብሬንትፎርድ ዝውውሩን ለማጠናቀቅ መቃረባቸው ተዘግቧል።
የዝውውር ሂደቱ ቢጠናቀቅም ጆርዳን ሄንደርሰን ለቀድሞ የቡድን አጋሩ ዲያጎ ጆታ ክብር ዝውውሩ በሚቀጥለው ሳምንት ይፋ እንዲደረግ መጠየቁ ተነግሯል።

❤200👍18😁11
TIKVAH-SPORT
የአርሰናል ደጋፊዎች ማዱኬን ለምን ተቃወሙ ? አርሰናል ኖኒ ማዱኬን ከቼልሲ ለማስፈረም የሚያደርገው ጥረት የክለቡን ደጋፊዎች እንዳላስደሰተ ተገልጿል። ደጋፊዎቹ ተጨዋቹ እንዳይፈርም በማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ የጀመሩ ሲሆን ድምፅ ማሰባሰብም ጀምረዋል። ዝውውሩ ለቼልሲ ጥቅም ይኖረዋል ? ሰማያዊዎቹ ኖኒ ማዱኬን በዚህ ክረምት ለአርሰናል መሸጥ የቡድናቸውን ሚዛን ለመጠበቅ ይረዳቸዋል። ፔድሮ ኔቶ በቀኝ…
የአርሰናል ደጋፊዎች ተቃውሞ ቀጥሏል !
የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ደጋፊዎች የኖኒ ማዱኬ ዝውውር እንዳይፈፀም የሚያደርጉትን ተቃውሞ መቀጠላቸው ተገልጿል።
ደጋፊዎቹ ዝውውሩን በመቃወም ዛሬ በክለቡ ስታዲየም ኤምሬትስ ውጪ የሚገኙ በርካታ ምስሎችን አበላሽተው ማደራቸው ተነግሯል።
ደጋፊዎቹ በስታዲየሙ ውጪ " Arteta Out " የሚል ፅሁፍ አስፍረውም ታይቷል።
በሌላ በኩል ደጋፊዎቹ ተጨዋቹ ወደ አርሰናል የሚያደርገው ዝውውር ለማስቆም በጥቂት ሰዓታት ውስጥ 4,000 የሚጠጋ ድምፅ አሰባስበዋል።
አርሰናል ተጫዋቹን ለማስፈረም ከቼልሲ ጋር ከስምምነት መድረሳቸው መዘገቡ አይዘነጋም።

❤284😁215👍37👎30🥰2👏1😱1
TIKVAH-SPORT
ክሪስታል ፓላስ ተጨዋች ሊያስፈርም ነው ! የፕርሚየር ሊጉ ክለብ ክሪስታል ፓላስ የአያክሱን የግራ መስመር ተጨዋች ቦርና ሶሳ ለማስፈረም ከጫፍ መድረሳቸው ተገልጿል። አያክስ ተጨዋቹ ወደ እንግሊዝ እንዲያመራ ፍቃድ መስጠቱ የተገለፀ ሲሆነ የህክምና ምርመራው በነገው ዕለት እንደሚደረግ ተዘግቧል። የ 27ዓመቱ የግራ መስመር ተጨዋች ቦርና ሶሳ ባለፈው አመት በውሰት ወደ ቶሪኖ አምርቶ 20 ጨዋታዎች ላይ…
ክሪስታል ፓላስ ተጨዋች አስፈረመ !
የፕርሚየር ሊጉ ክለብ ክሪስታል ፓላስ ከአያክስ የግራ መስመር ተጨዋች ማስፈረማቸውን በይፋ አስታውቀዋል።
ክሪስታል ፓላስ የ 27ዓመቱን ክሮሽያዊ የግራ መስመር ተጨዋች ቦርና ሶሳ ማስፈረማቸው ይፋ ሆኗል።
ተጨዋቹ ከፊርማው በኋላ “ ክሪስታል ፓላስን በመቀላቀሌ ተደስቻለሁ ስለ ክለቡ በርካታ ጥሩ ነገሮችን ሰምቻለሁ " ሲል ተደምጧል።
ተጨዋቹ ባለፈው አመት በውሰት ወደ ቶሪኖ አምርቶ 20 ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ መጫወት ችሏል።
ክሪስታል ፓላስ ታይሪክ ሚቼልን የመጀመሪያ ተመራጭ የግራ ተመላላሽ አድርጎ ቢመለከትም ቡድኑን ለማጠናከር እና የተጨዋቹ ተፎካካሪ ለማድረግ ቦርና ሶሳን አስፈርሟል።
የ ክሮሽያዊው ተጨዋች ቦርና ሶሳ ዝውውር ሒሳብ ሁለት ሚልዮን ፓውንድ መሆኑ ተዘግቧል።

❤81👍8👎4
TIKVAH-SPORT
ሊቨርፑል የወዳጅነት ጨዋታውን ያደርጋል ? ሊቨርፑል ከ ፕሪስተን ጋር ለማድረግ ያቀደው የቅድመ ዝግጅት የወዳጅነት ጨዋታ በተያዘለት መርሐግብር መሰረት እንደሚደረግ ታውቋል። ባለፈው ሳምንት ተጫዋቻቸውን በድንገተኛ አደጋ ያጡት ሊቨርፑሎች በጨዋታው ዙሪያ ከፕሪስተን ሀላፊዎች ጋር መወያየታቸው ተገልጿል። የፕሪስተን ሀላፊዎች ከጨዋታው በፊት ዲያጎ ጆታን እንዴት በጥሩ ሁኔታ እናስበው በማለት ከሊቨርፑል…
ተጨዋቾች ጥቁር ጨርቅ አስረው ይገባሉ !
ሊቨርፑል እሁድ ከፕሬስተን ጋር በሚያደርገው የወዳጅነት ጨዋታ ዲያጎ ጆታ እና ወንድሙ እንደሚታሰቡ ተገልጿል።
ጨዋታው ከመጀመሩ በፊት የአንድ ደቂቃ የህሊና ፀሎት እንደሚደረግ እና የደጋፊዎች መልዕክት በስታዲየሙ ስክሪን እንደሚታይ ተነግሯል።
በተጨማሪም በስታዲየሙ ታዋቂው የሊቨርፑል ክለብ መዝሙር “ You'll Never Walk Alone “ እንደሚደመጥ ተገልጿል።
እንዲሁም ተጨዋቾቹ በክንዳቸው ላይ ጥቁር ጨርቅ በማሰር ወደ ሜዳ የሚገቡ ይሆናል።
ጨዋታው እሁድ ከቀኑ 11:00 በፕሬስተን ስታዲየም የሚደረግ ይሆናል።

❤268👍28👏8
ቪክቶር ዮኬሬሽ ወደ ልምምድ አይመለስም !
ስዊድናዊው የፊት መስመር አጥቂ ቪክቶር ዮኬሬሽ ወደ ስፖርቲንግ ሊዝበን ልምምድ ተመልሶ ሪፖርት ለማድረግ እንዳላሰበ ተገልጿል።
ተጨዋቹ በነገው ዕለት ወደ ልምምድ መመለስ የሚጠበቅበት ቢሆንም በድጋሜ የክለቡን ማልያ መልበስ እንደማይፈልግ ለክለቡ ማሳወቁ ተነግሯል።
ተጨዋቹ አርሰናልን ለመቀላቀል በንግግር ላይ እንደሚገኝ የሚታወቅ ሲሆን መድፈኞቹ ለማስፈረም በጥረት ላይ ናቸው።
ቪክቶር ዮኬሬሽ ለአርሰናል የአምስት አመት ኮንትራት ለመፈረም ከስምምነት መድረሱ ተነግሯል።
አርሰናል በበኩሉ የተጫዋቹን ዝውውር ለማጠናቀቅ በሒሳቡ ዙሪያ ለመስማማት በሂደት ላይ እንደሚገኙ ተዘግቧል።

❤358👏59👎39😁24👍19🤩4🔥2🥰2🙏2