ሜሲ ለመጀመሪያ ጊዜ ከቀድሞ ክለቡ ይጫወታል !
አርጀንቲናዊው ተጨዋች ሊዮኔል ሜሲ በእግርኳስ ህይወቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የቀድሞ ክለቡን በተቃራኒው ሆኖ የሚገጥም ይሆናል።
በእግርኳስ ህይወቱ ለሶስት ክለቦች የተጫወተው ሊዮኔል ሜሲ በፒኤስጂ በነበረው ቆይታ ባርሴሎናን በተቃራኒው አልገጠመም።
ፔኤስጂ ታሪክ በማይዘነጋው የሻምፒየንስ ሊግ ምሽት በባርሴሎና ውጤት ሲቀለበስበት የነበረውን የተወሰነ ስብስብ ዛሬ በተቃራኒው ይገጥማል።
ሊዮኔል ሜሲ ፣ ሉዊስ ሱዋሬዝ ፣ ሰርጂዮ ቡስኬት ፣ አሰልጣኙ ዣቪየር ማሼራኖ እና ጆርዲ አልባ በውጤት ቀልባሹ የባርሴሎና ስብስብ ነበሩ።
@Tikvahethsport @kidusyoftahe

❤153😁13👎10👍1
TIKVAH-SPORT
“ የሳውዲ ሊግ ከምርጥ አምስት ሊጎች አንዱ ሆኗል “ ሮናልዶ “ ቀጣይ አመት ዋንጫ ማሸነፍ እፈልጋለሁ “ በአል ነስር ለተጨማሪ አመታት ለመቆየት የወሰነው ክርስቲያኖ ሮናልዶ በሳውዲ አረቢያ ቆይታው ዙሪያ ቃለምልልስ አድርጎ ነበር። ክርስቲያኖ ሮናልዶ በቃለ ምልልሱ “ የሳውዲ አረቢያ ሊግ አሁን ላይ ከአለም ምርጥ አምስት ሊጎች አንዱ ሆኗል “ ብሏል። ሮናልዶ ምን ጉዳዮችን አነሳ ? - "…
“ ሜጀር ሊግ ሶከር ትልቅ ደረጃ ደርሷል “ ዴቪድ ቤካም
የኢንተር ሚያሚው ጥምር ባለቤት ሰር ዴቪድ ቤካም የአሜሪካ ሜጀር ሊግ ሶከር አስደናቂ ደረጃ ላይ መድረሱን ተናግሯል።
“ ሊጉ አሁን ላይ በሚደንቅ ደረጃ ላይ ይገኛል " ያለው ዴቪድ ቤካም ባለፉት አስር አሰራ አምስት አመታት የተለየ ለውጥ መጥቷል ብሏል።
አክሎም " እኔ ወደዚህ ሴመጣ 15 ቡድኖች ነበሩ አሁን 30 ቡድኖች አሉን ሁሉም ስታዲየም አላቸው ገንዘብም ያገኛሉ " በማለት አስረድቷል።
" በሊጉ ውስጥ እና ባሉት ህጎች ላይ የተወሰነ ለውጥ መደረግ አለበት ነገርግን ሊጉ ያረጀ አይደለም፤ ብዙ ስራዎች ተሰርተዋል ወደፊትም መሰራት ያለባቸው አሉ።" ቤካም
ዴቪድ ቤካም በእጁ ላይ ጉዳት አጋጥሞት የነበረ ቢሆንም ሙሉ ለሙሉ ሳያገግም ጨዋታውን ለመታደም ስታዲየም ተገኝቷል።

❤109😁78👍13👎3🙏2👏1
ቶማስ ፓርቴይ ከአርሰናል ጋር ይለያያል !
የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ከጋናዊው የመሐል ሜዳ ተጨዋች ቶማስ ፓርቴይ ጋር ለመለያየት መወሰናቸው ተገልጿል።
ቶማስ ፓርቴ ነገ ከአርሰናል ጋር ያለው ኮንትራት ሲጠናቀቅ በነፃ ዝውውር ክለቡን እንደሚለቅ ተረጋግጧል።
አርሰናል ለወራት የቶማስ ፓርቴን ኮንትራት ለማራዘም ቢነጋገሩም ሊሳካ ባለመቻሉ ለመለያየት መወሰናቸው ተዘግቧል።
የ 32ዓመቱ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ቶማስ ፓርቴይ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ስለ ቀጣይ ማረፍያው እንደሚወስን ተነግሯል።

❤134😢71👍28😁22👎9🤬5🤩3
#ClubWorldCup
በመጀመሪያው አጋማሽ ኢንተር ሚያሚ በተጋጣሚው ፒኤስጂ የሜዳ ክልል ማድረግ የቻለው ቅብብል 25 ነው።
ፒኤስጂ በአንፃሩ 257 ኮሶችን በተጋጣሚያቸው የሜዳ ክልል መቀባበል ችለዋል።
ፒኤስጂ በመጀመሪያው አጋማሽ ያስቆጥረው ግብ ኢንተር ሚያሚ በሶስተኛ የሜዳ ክፍል ካደረጉት ቅብብል ( 3 ) የበለጠ ነው።
ኢንተር ሚያሚ በጨዋታው ከዚህም የከፋ ውጤት ይዘው ላለመውጣት በሁለተኛው አጋማሽ የተሻለ የኳስ ቁጥጥር ማድረግ ያስፈልጋቸዋል።

😁146❤47🔥2👍1
ፒኤስጂ ሩብ ፍፃሜውን ተቀላቅለዋል !
በክለቦች አለም ዋንጫ ጥሎ ማለፍ ፒኤስጂ ከኢንተር ሚያሚ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 4ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።
የፒኤስጂን የማሸነፊያ ግብ ጇ ኔቬዝ 2x ፣ አሽራፍ ሀኪሚ እና አቪሌስ በራሱ መረብ ላይ አስቆጥረዋል።
ውጤቱን ተከትሎ ፒኤስጂ ሩብ ፍፃሜውን ሲቀላቀል ኢንተር ሚያሚ ከውድድሩ ተሰናብተዋል።
በጨዋታው የፒኤስጂን ሁለት ግቦች ያስቆጠረው ጇ ኔቬዝ የጨዋታው ኮከብ በመባል መመረጥ ችሏል።
ፒኤስጂ በሩብ ፍፃሜው የባየር ሙኒክ እና ፍላሚንጎን አሸናፊ የሚገጥሙ ይሆናል።

😁168❤99👍30👎15😢10🔥7🥰1
TIKVAH-SPORT
ቼልሲ ተጨዋች ለማስፈረም እየጣሩ ነው ! የለንደኑ ክለብ ቼልሲ እና ኒውካስል ዩናይትድ የብራይተኑን የፊት መስመር ተጨዋች ጇ ፔድሮ ለማስፈረም ፉክክር ላይ መሆናቸው ተገልጿል። ብራይተን ለ 23ዓመቱ ብራዚላዊ የፊት መስመር ተጨዋች ጇ ፔድሮ እስካሁን የቀረበ ጥያቄ አለመቀበሉ ተነግሯል። ሁለቱ ክለቦች ተጫዋቹን ወደ ስብሰባቸው ለመቀላቀል ከብራይተን ጋር በንግግር ላይ መሆናቸው ተዘግቧል። ተጨዋቹ…
ቼልሲ ተጨዋች ለማስፈረም ተስማማ !
የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ብራዚላዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ጇ ፔድሮ ለማስፈረም ከብራይተን ጋር ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል።
የ 23ዓመቱ የፊት መስመር ተጨዋች ጇ ፔድሮ በቼልሲ እና ኒውካስል ዩናይትድ ቢፈለግም ሰማያዊዎቹን ምርጫው ማድረጉ ተነግሯል።
ቼልሲ ለጇ ፔድሮ ዝውውር 50 ሚልዮን ፓውንድ እንደሚያወጡ ሲገለፅ ተጨዋቹ የስድስት አመት ውል እንደሚፈርም ተዘግቧል።
ተጨዋቹ በውድድር አመቱ ለብራይተን 30 ጨዋታዎች ሲያደርግ 10 የፕርሚየር ሊግ ግቦችን አስቆጥሮ ስድስት አመቻች አቀብሏል።

❤188😁71👍25👎10😱8👏2🔥1
“ የአለም ምርጥ ቡድን ነው የገጠምነው “ ማሼራኖ
የኢንተር ሚያሚው አሰልጣኝ ዣቪየር ማሼራኖ ቡድናቸው ከፒኤስጂ ትልቅ ልዩነት ቢኖረውም ለመፎካከር መሞከሩን ገልጸዋል።
“ የገጠምነው የአለም ምርጡን ቡድን ነው “ ያሉት ማሼራኖ “ አውሮፓ ላይ እነሱን ማቆም የቻለ ክለብ የለም እዚህም የአሸናፊነት ግምቱ የእነሱ ነው “ ብለዋል።
አክለውም “ በሁለቱ ክለቦች መካከል ትልቅ ልዩነት አለ ቢሆንም ለመፎካከር ሞክረናል በተጨዋቾቼ ኮርቻለሁ “ ብለዋል።
ከውድድሩ ምን እንደተማሩ ጥያቄ የቀረበላቸው አሰልጣኝ ማሼራኖ “ ምንም አላውቅም “ ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።
“ በሁለተኛው አጋማሽ ትንሽ ጥሩ ተጫውተን በምድቡ ሁለት ትልቅ ቡድኖች ጥለናል አሁን ወደፊት እንቀጥላለን “ ማሼራኖ

❤215😁152👍10👏10👎4🥰2💯2