Telegram Web Link
የራሽፎርድ የማንችስተር ዩናይትድ ቆይታ ?

ማርከስ ራሽፎርድ ማንችስተር ዩናይትድ የሚለቅ ከሆነ ከእንግሊዝ ውጪ ወደሆነ ሊግ ማምራት እንደሚፈልግ ተገልጿል።

ማንችስተር ዩናይትድ ተጫዋቹን መሸጥ የሚፈልጉ ሲሆን ራሽፎርድ በበኩሉ በውሰት ወይም በተጨዋች ቅያሬ አካል በመሆን ለመልቀቅ ዝግጁ ነው ተብሏል።

የ 27ዓመቱ ማርከስ ራሽፎርድ ዋንጫ ለመፎካከር የሚያስችለውን ክለብ መቀላቀል እንደሚፈልግ ተነግሯል።

አሁን ላይ ለማርከስ ራሽፎርድ እየቀረበ የሚገኘው ጥያቄ ከግዢ ይልቅ የውሰት ጥያቄ መሆኑ ተጠቁሟል።

ማንችስተር ዩናይትድ በቀጣይ ተጨማሪ አጥቂ ለማስፈረም ከተጨዋቾች ሽያጭ ገንዘብ ማሰባሰብ እንደሚያስፈልገው ተነግሯል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
የሮድሪጎ የሪያል ማድሪድ ሁኔታ ?

ብራዚላዊው ተጨዋች ሮድሪጎ የክለቦች አለም ዋንጫ የመጀመሪያ ጨዋታዎች ላይ ባለመሳተፉ ደስተኛ ስላለመሆኑ በቅርቡ ያሉ ሰዎች ተናግረዋል።

የተጨዋቹ የሪያል ማድሪድ ሁኔታ በቀጣይ የዝውውር መስኮቱ መነጋገሪያ ርዕሰ ሊሆን እንደሚችል ተገልጿል።

ሎስ ብላንኮዎቹ ማስታንቱኖን ከሪቨር ፕሌት ማስፈረማቸው የሮድሪጎን ሚና ሊቀንሰው እንደሚችል ተሰግቷል።

በሌላ በኩል የቡድኑ የኋላ መስመር ተጨዋቹ ዴቪድ አላባ በሪያል ማድሪድ ያለው ውል እስከሚጠናቀቅ በክለቡ መቆየት እንደሚፈልግ ተነግሯል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
“ ለቡድኑ መፋለም የማይፈልግ መልቀቅ አለበት “ ማርቲኔዝ የኢንተር ሚላኑ የፊት መስመር ተጨዋች ላውታሮ ማርቲኔዝ ለቡድናቸው መፋለም የማይፈልግ ክለቡን መልቀቅ አለበት በማለት ተናግሯል። ኢንተር ሚላን ትላንት ምሽት ከፍሉሚኔንስ ተሸንፎ ከውድድሩ ውጪ ከሆነ በኋላ አስተያየቱን የሰጠው ማርቲኔዝ በሽንፈቱ ማዘኑን ገልጿል። " ለቡድኑ በሁሉም ልምምድ ጊዜያት ያለኝን ሁሉ ሰጥቻለሁ መሸነፍ አልፈልግም…
“ እኔ ኢንተር ሚላንን አልካድኩም " ካልሀኖግሉ

“ ትክክለኛ መሪ ተጠያቂ አያፈላልግም “

የኢንተር ሚላኑ አማካይ ካልሀኖግሉ “ እኔ ኢንተር ሚላንን አልካድኩም እዚህ ደስተኛ አይደለሁም ብዬ አላውቅም " ሲል ምላሽ ሰጥቷል።

የቡድኑ አምበል ላውታሮ ማርቲኔዝ ከትላንቱ ሽንፈት በኋላ “ ቡድኑ ውስጥ መሆን ያልፈለገ መልቀቅ ይችላል “ ብሎ ነበር።

የክለቡ ፕሬዝዳንት ማሮታ በበኩላቸው “ ማርቴኔዝ ስም ባይጠቀስም የተናገረው ካልሀኖግሉን ነው “ ብለው ነገሩን አባብሰውታል።

ለሁነቱ ምላሽ የሰጠው ካልሀኖግሉ “ መሸነፋችን ያሳምማል ከሽንፈቱ በላይ የጎዱኝ የተነገሩ ቃላቶች ናቸው “ ብሏል።

ከቡድኑ የተገለለው መጫወት ባለመፈለጉ ሳይሆን በጉዳት ምክንያት መሆኑን እና በአሜሪካ ቢያቀናም አዲስ ጉዳት እንደገጠመው ተጨዋቹ ተናግሯል።

አክሎም “ ትክክለኛ መሪ ተጠያቂ አያፈላልግም “ ያለው ተጨዋቹ " የሚያወጣቸው ቃላቶች ብቻ ለውጥ ያመጣሉ " ሲል ገልጿል።

“ ከቡድን አጋሮቼ ወይም ከፕሬዝዳንቱ ቢመጡም ሁሉንም አስተያየቶች እቀበላለሁ ነገርግን መከባበር ከአንድ ወገን ብቻ አይደለም “ ካልሀኖግሉ

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት በቀን 24/10/2017 ዓ/ም ባካሄዱት ስብሰባ ላይ የተወሰኑ አበይት ጉዳዮች

@tikvahethsport @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
አንሱ ፋቲ በውሰት ሞናኮን ሊቀላቀል ነው ! ስፔናዊው የባርሴሎና የፊት መስመር ተጨዋች አንሱ ፋቲ በረጅም ጊዜ ውሰት ውል የፈረንሳዩን ክለብ ሞናኮ ለመቀላቀል ተስማምቷል። በተጠናቀቀው የውድድር አመት ለባርሴሎና 11 ጨዋታዎች ብቻ ያደረገው አንሱ ፋቲ ነገ በሞናኮ የህክምና ምርመራውን ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል። ተጨዋቹ ወደ ሞናኮ ከማቅናቱ በፊት ለባርሴሎና የተጨማሪ አንድ አመት ውል ያራዝማል ተብሎ…
አንሱ ፋቲ በውሰት ሞናኮን ተቀላቀለ !

ስፔናዊው የፊት መስመር ተጨዋች አንሱ ፋቲ በረጅም ጊዜ ውሰት ውል የፈረንሳዩን ክለብ ሞናኮ መቀላቀሉ በይፋ ተገልጿል።

በተጨዋቹ የውሰት ውል ውስጥ ባርሴሎና መጥራት ቢፈልግ 11 ሚልዮን ዩሮ መክፈል የሚያስገድድ አንቀጽ ተካቷል።

በተጠናቀቀው የውድድር አመት ለባርሴሎና 11 ጨዋታዎች ያደረገው አንሱ ፋቲ በቅድሚያ በባርሴሎና እስከ 2028 ውሉን አራዝሟል።

ሞናኮ በዝውውር መስኮቱ ፖል ፖግባ እና ኤሪክ ዳየርን በነፃ ዝውውር እንዲሁም አንሱ ፋቲን በውሰት በማስፈረም ቡድናቸውን አጠናክረዋል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
ጆን ዱራን ወደ ፌነርባቼ ለማምራት ተስማማ !

ኮሎምቢያዊው የፊት መስመር አጥቂ ጆን ዱራን የቱርኩን ክለብ ፌነርባቼ ለመቀላቀል ከስምምነት ደርሷል።

ተጨዋቹ ከአል ነስር ወደ ፌነርባቼ በውሰት የሚያደርገውን ዝውውር ለማጠናቀቅ ከኮሎምቢያ ወደ ቱርክ ለመብረር መዘጋጀቱ ተገልጿል።

ጆን ዱራን ባለፈው ክረምት ከአስቶን ቪላ በ 77 ሚልዮን ዩሮ በአምስት አመት ኮንትራት አል ነስርን መቀላቀሉ ይታወሳል።

የ 22ዓመቱ ጆን ዱራን በሳውዲ አረቢያ ሊግ ባደረጋቸው 18 ጨዋታዎች 12 ጎሎችን ማስቆጠር ችሏል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሎሬንዞ ኢንሲኜ ከክለቡ ጋር ተለያየ !

ሎሬንዞ ኢንሲኜ እና ፌዴሪኮ ቤርናዴቺ ከአሜሪካ ሜጀር ሊግ ሶከሩ ክለብ ቶሮንቶ ጋር ያላቸው ኮንትራት መቋረጡ ተገልጿል።

ሁለቱም ተጨዋቾች ከክለቡ ጋር ያላቸውን ውል በስምምነት በማቋረጥ አሁን ላይ ከኮንትራት ነፃ መሆናቸው ተነግሯል።

የ 34ዓመቱ ኢንሲኜ በ 2025 ለቶሮንቶ 13 ጨዋታዎች ሲያደርግ አንድ ጎል ሲያስቆጥር ሶስት አመቻችቶ አቀብሏል።

ሎሬንዞ ኢንሲኜ በአሜሪካ ሜጀር ሊግ ሶከር ከሊዮኔል ሜሲ በመቀጠል ከፍተኛ ተከፋይ እግርኳስ ተጨዋች ነበር።

በጉዳት እና ቅጣት ያለፉት አራት ጨዋታዎች ያመለጡት ቤርናዴቺ በበኩሉ በ 2025 15 ጨዋታዎች ሲያደርግ አራት ጨዋታዎች አድርጎ ሶስት አመቻችቶ አቀብሏል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
አርሰናል ኬፓን ለማስፈረም ተቃርቧል ! የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል የቼልሲውን ግብ ጠባቂ ኬፓ አሪዛባላጋን ዝውውር ለማጠናቀቅ ከጫፍ መድረሳቸው ተገልጿል። መድፈኞቹ ኬፓ አሪዛባላጋን የቡድኑ ቁጥር ሁለት ግብ ጠባቂ አድርገው ለማስፈረም እየሰሩ መሆኑ ተዘግቦ እንደነበር ይታወሳል። አርሰናል አሁን ላይ የ 30ዓመቱ ኬፓ አሪዛባላጋ በቼልሲ ያለውን ኮንትራት ማፍረሻ 5 ሚልዮን ፓውንድ በመክፈል ለማስፈረም…
አርሰናል በይፋ ግብ ጠባቂ አስፈረመ !

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል የቼልሲውን ግብ ጠባቂ ኬፓ አሪዛባላጋ ማስፈረማቸውን በይፋ አስታውቀዋል።

መድፈኞቹ ኬፓ አሪዛባላጋን የቡድኑ ቁጥር ሁለት ግብ ጠባቂ አድርገው በሶስት አመት ኮንትራት ማስፈረማቸው ተገልጿል።

አርሰናል የ 30ዓመቱ ኬፓ አሪዛባላጋ በቼልሲ ያለውን ኮንትራት ማፍረሻ 5 ሚልዮን ፓውንድ በመክፈል አስፈርመዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
አርሰናል በይፋ ግብ ጠባቂ አስፈረመ ! የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል የቼልሲውን ግብ ጠባቂ ኬፓ አሪዛባላጋ ማስፈረማቸውን በይፋ አስታውቀዋል። መድፈኞቹ ኬፓ አሪዛባላጋን የቡድኑ ቁጥር ሁለት ግብ ጠባቂ አድርገው በሶስት አመት ኮንትራት ማስፈረማቸው ተገልጿል። አርሰናል የ 30ዓመቱ ኬፓ አሪዛባላጋ በቼልሲ ያለውን ኮንትራት ማፍረሻ 5 ሚልዮን ፓውንድ በመክፈል አስፈርመዋል። @tikvahethsport    …
“ አርሰናል ዋንጫ ለማሸነፍ ተቃርቧል “ ኬፓ አሪዛባላጋ

አርሰናልን የተቀላቀለው ስፔናዊ ግብ ጠባቂ ኬፓ አሪዛባላጋ በክለቡ ለመስራት መጓጓቱን ከፊርማው በኋላ ተናግሯል።

“ እዚህ በመሆኔ በጣም ደስተኛ ነኝ " ያለው ኬፓ አሪዛባላጋ በቀጣይ በክለቡ ለመስራት ጓጉቻለሁ ቡድኑ ለማሸነፍ ያለውን ምኞት ሰምቻለሁ ብሏል።

አክሎም " አርሰናል ዋንጫ ለማሸነፍ ተቃርቧል " ያለው ኬፓ አሪዛባላጋ በጋራ እንደምናሳካው ባለሙሉ ተስፋ ነኝ ሲል ተደምጧል።

ኬፓ አሪዛባላጋ በአርሰናል ቤት የ 13 ቁጥር ማልያ የማለብስ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ኤደርሰን ከደጋፊዎች ተቃውሞ ቀረበበት !

ብራዚላዊው የማንችስተር ሲቲ ቁጥር አንድ ግብ ጠባቂ ኤደርሰን ከክለቡ ደጋፊዎች ተቃውሞ እየቀረበበት ይገኛል።

ግብ ጠባቂው ትላንት ምሽት በአል ሂላል ጨዋታ ያሳየውን አቋም ተከትሎ ደጋፊዎቹ መልቀቅ አለበት በማለት ተቃውመዋል።

የክለቡ ደጋፊዎች አሁን ላይ በማህበራዊ ሚዲያዎች “#EdersonOut “ የሚል ዘመቻ ከፍተዋል።

ኤደርሰን በቅርቡ በሚቀጥለው የውድድር ዘመን በማንችስተር ሲቲ ቤት እንደሚቆይ ማረጋገጡ አይዘነጋም።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#ClubWorldCup 🇺🇸

ሪያል ማድሪድ ዛሬ ምሽት ከጁቬንቱስ ጋር በሚያደርገው ጨዋታ ወሳኝ ተጨዋቾቹ ወደ ሜዳ እንደሚመለሱ ተገልጿል።

በጨዋታው በህመም ያለፉት ጨዋታዎች ያመለጡት የቡድኑ ቁልፍ ተጨዋች ኪሊያን ምባፔ ወደ ሜዳ እንደሚመለስ ይጠበቃል።

የቡድኑ ዋና አሰልጣኝ ዣቢ አሎንሶ ኪሊያን ምባፔ “ ጥሩ ጤንነት ላይ ነው " ያሉ ሲሆን ወደ አሰላለፍ የሚመለስበት እድል ሰፊ ነው ብለዋል።

ሎስ ብላንኮዎቹ በውድድሩ ወሳኝ ወቅት ኪሊያን ምባፔ ብቻ ሳይሆን ሌሎች ሁለት የኋላ መስመር ተጨዋቾቻቸው ይመለሳሉ።

ለተጨዋቾች ጠንቅ ከሆነው የ " ACL " ጉዳት የተመለሱት ዳኒ ካርቫል እና ኤደር ሚሊታኦ ከጥሎ ማለፉ በኋላ ቡድኑን ማገልገል ይጀምራሉ ተብሎ ይጠበቃሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
በሩብ ፍፃሜው ምን ልንመለከት እንችላለን ?

ሪያል ማድሪድ ዛሬ ምሽት ጁቬንቱስን የሚያሸንፍ ከሆነ በውድድሩ ሩብ ፍፃሜ ታሪካዊ ጨዋታ ልንመለከት እንችላለን።

የሪያል ማድሪድ እና ጁቬንቱስ አሸናፊ በሩብ ፍፃሜው የቦርስያ ዶርትመንድ እና ሞንቴሬይን አሸናፊ ይገጥማሉ።

ሪያል ማድሪድ ጁቬንቱስን አሸንፎ ዶርትመንድ የሚያልፍ ከሆን ሁለቱ ወንድማማቾች ጁድ ቤሊንግሀም እና ጆቤ ቤሊንግሀም ለመጀመሪያ ጊዜ በተቃራኒው ይፋለማሉ።

በሌላ በኩል ሪያል ማድሪድ ጁቬንቱስን አሸንፎ ሞንቴሬይ የሚያልፍ ከሆነ ሰርጂዮ ራሞስ የቀድሞ ክለቡን በተቃራኒው ይገጥማል።

ለሪያል ማድሪድ በወሳኝ ቅፅብት ግብ በማስቆጠር የሚታወቀው ራሞስ የቀድሞ ክለቡን ከውድድሩ ለማሰናበት የሚፋለም ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የጨዋታ አሰላለፍ !

4:00 ሪያል ማድሪድ ከ ጁቬንቱስ

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
#ClubWorldCup 🇺🇸

ጁቬንቱስ ማንችስተር ሲቲን ከገጠመው የቡድን ስብስብ የስድስት ተጨዋቾች ቅያሬ አድርገው ወደ ሜዳ ይገባሉ።

አሰልጣኝ ኢጎር ቱዶር በማንችስተር ሲቲ ጨዋታ በተመለከቱት ነገር ደስተኛ አለመሆናቸውን ተናግረው ነበር።

አሰልጣኙ ከጨዋታው በፊት በሰጡት አስተያየት " ሁሉም ሰው ሪያል ማድሪድን ማሸነፍ ይፈልጋል ማለፍ እንፈልጋለን እምነት አለኝ " ብለዋል።

በሪያል ማድሪድ በኩል ኪሊያን ምባፔ የውድድሩ የመጀመሪያ ጨዋታውን ለማድረግ ተጠባባቂ ወንበር ላይ ተቀምጧል።

በሌላ በኩል ሩዲገር በቋሚነት ሲሰለፍ ዳኒ ካርቫል ከዘጠኝ ወራት በኋላ ቡድኑን ለማገልገል ተጠባባቂ ሆኖ ይጀመራል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
" ሁሉም ጨዋታ እንደ ፍፃሜ ነው " አሎንሶ

የሎስ ብላንኮዎቹ አሰልጣኝ ዣቢ አሎንሶ ጁቬንቱስ በማንችስተር ሲቲ ቢሸነፍም ቀላል ግምት እንደማይሰጡ ገልጸዋል።

“ ሁሉም ጨዋታዎች እንደ ፍፃሜ ነው ስሜታቸው " ያሉት ዣቢ አሎንሶ " ጁቬንቱስ ያው ጁቬንቱስ ነው የአውሮፓ ታሪካዊ ክለብ ነው " ብለዋል።

የጁቬንቱሱ አሰልጣኝ ኢጎር ቱዶር በበኩላቸው “ ብዙ መሮጥ አለብን ምንም ስህተት መስራት የለብንም በራሳችን ማመን አለብን “ ብለዋል።

“ ጨዋታው ከባድ ነው ሪያል ማድሪድ በዚህ ውድድር ሁልጊዜም ጠንካራ ነው ማለፍ ስለምንፈልግ የቻልነውን እናደርጋለን “ ኢጎር ቱዶር

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
#ClubWorldCup 🇺🇸

ሪያል ማድሪድ እና ጁቬንቱ ከዚህ በፊት በ 21 አጋጣሚዎች እርስበርስ ጨዋታቸውን አድርገዋል።

ሪያል ማድሪድ በእርስበርስ ግንኙነታቸው የበላይነቱን ቢወስድም ተቀራራቢ ውጤት ነው ያስመዘገቡት።

በእርስበርስ ግንኙነታቸው ሪያል ማድሪድ አስር ጊዜ ሲያሸንፍ ጁቬንቱስ ዘጠኙን አሸንፏል በቀሪዎቹ አቻ ተለያይተዋል።

ሁለቱ ክለቦች እርስበርስ ለመጨረሻ ጊዜ የተገናኙት 2018 በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ሩብ ፍፃሜ አቻ በተለያዩበት ጨዋታ ነበር።

ከእርስበርስ ግንኙነታቸው ትልቅ የሚባለው ጨዋታ ሪያል ማድሪድ አሸናፊ የነበረበት የ 2016/17 ሻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ ነው።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
7 '

ሪያል ማድሪድ 0 - 0 ጁቬንቱስ

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
2025/07/05 20:32:18
Back to Top
HTML Embed Code: