Telegram Web Link
29 '

ሪያል ማድሪድ 0 - 0 ጁቬንቱስ

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት በቀን 24/10/2017 ዓ/ም ባካሄዱት ስብሰባ ላይ የተወሰኑ አበይት ጉዳዮች @tikvahethsport @kidusyoftahe
#Update

ሲዳማ ቡና ስፖርት ክለብ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴን ውሳኔ " ተገቢና ህግን ያልተከተለ ውሳኔ " ሲል ተቃወመ።

የሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብ ቦርድ ውሳኔውን " ተገቢነት የሌለው ውሳኔ ነው። ውሳኔው እጅግ አሳዝኖናል " ብሏል።

" ብርቅዬ የክለባችን ተጫዋቾች በጨዋታ ሜዳ የገጠሙትን ሁሉንም ከጨዋታ ብልጫ ጋር በማሸነፍ የ2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ዋንጫ ማሸነፉ የአደባባይ ምስጥር ነዉ " ሲል ገልጿል።

" ይሁን እንጂ ' የሊግ ካምፓኒ ያወጣውን የፋይናንስ ደንብ አላከበራችሁም ' በሚል በክለቡና በተጫዋቾች ላይ ቅጣት ተጥሎባቸዋል ቢባልም ክለቡ  ያነሳዉ ዋንጫ የኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ በ48 ክለቦች መካከል የተደረገው መሆኑ ዕሙን ነው " ብሏል።

" የሲዳማ ቡና ስፖርት ክለብ የታገዱ ተጫዋቾችን አሰልፎ ከሆነ በጥሎ ማለፉ ያሸነፋቸው ክለቦች በሙሉ ፎርፌ አግኝተው ጉዳያቸው እንደገና መታየት አለበት እንደ ማለትም ይሆናል " ብሏል።

" እርስ በርስ የሚጣረሱ ሀሳቦችን በማገናኘት ውጤቱን ለመቀማት መሞከር  ተገቢና ህግን የተከተለ ውሳኔ ነው ብለን አናምንም " ሲል ቦርዱ አሳውቋል።

" ፌዴሬሽኑ ዉሳኔውን ከህግጋቱ ጋር በማገናዘብ እንደገና እንዲያጠነዉ ቅሬታችንን እናሰማለን " ብሏል።

" ህዝባችን በፌደሬሽኑ ውሳኔ የተከፋ ቢሆንም የአፊኒ ባህል ያለው ታላቅ ህዝብ ስለሆነ ክስተቶችን በመረጋጋት መርምሮ በተገቢው እንዲያጠነውና  ሂደቱን  በትዕግሥት እንዲጠባበቅ በአክብሮት እየጠይቃል " ሲል ገልጿል።

" የተነፈግነው ፍትህ እስኪረጋገጥ ድረስ ጉዳዩን እስከ ፊፋ ገላጋይ ፍርድ ቤት ድረስ በይግባኝ ወስደን ለጉዳዩ  ተገቢው እልባት እስኪሰጥ ድረስ የክለቡ ቦርድ ቁርጠኛ መሆኑን እናረጋግጣለን " ሲል አሳውቋል።

@tikvahethiopia
እረፍት

ሪያል ማድሪድ 0 - 0 ጁቬንቱስ

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
53 '

ሪያል ማድሪድ 1 - 0 ጁቬንቱስ

ጋርሺያ

- አሌክሳንደር አርኖልድ ለሪያል ማድሪድ የመጀመሪያውን ለግብ የሆነ ኳስ አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
የላሊጋ መርሐ ግብር ይፋ ሆነ !

የስፔን ላሊጋ የ 2025/26 የውድድር አመት የጨዋታ መርሐ ግብሮች በይፋ ተገልጸዋል።

የወቅቱ የላሊጋው አሸናፊ ባርሴሎና የመጀመሪያ ጨዋታውን ከማዮርካ ጋር የሚያደርግ ይሆናል።

ሪያል ማድሪድ በበኩሉ የመጀመሪያ ጨዋታውን በሜዳው ከኦሳሱና ጋር የሚያደርግ ይሆናል።

የመጀመሪያው የኤል ክላሲኮ ጨዋታ ጥቅምት ወር መጨረሻ ሳንቲያጎ በርናቦ ስታዲየም ላይ የሚደረግ ይሆናል።

የመጀመሪያው የማድሪድ ደርቢ ጨዋታ መስከረም ወር ውስጥ በሪያል ማድሪድ ስታዲየም ላይ የሚካሄድ ይሆናል።
78 '

ሪያል ማድሪድ 1 - 0 ጁቬንቱስ

ጋርሺያ

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት በቀን 24/10/2017 ዓ/ም ባካሄዱት ስብሰባ ላይ የተወሰኑ አበይት ጉዳዮች @tikvahethsport @kidusyoftahe
" ተክሰናል ፤ ሕዝቡ በልዩ ልዩ መንገዶች ደስታዉን እየገለፀ ነዉ " - የወላይታ ዲቻ እግር ኳስ ክለብ

ዛሬ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ያስተላለፈዉን ዉሳኔ ተከትሎ የሲዳማ ቡና ስፖርት ክለብ " የኢትዮጵያ ዋንጫን " ለወላይታ ዲቻ ይመልሳል ወላይታ ዲቻ እግር ኳስ ቡድንም በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ #ኢትዮጵያን የሚወክል ይሆናል።

ይህን የፌደሬሽኑን ዉሳኔ ተከትሎ የወላይታ ዲቻ ደጋፊዎች በአደባባይ ደስታቸዉን የገለፁ ሲሆን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላላ ከበደን ጨምሮ የክልሉና የወላይታ ዞን አመራሮች " የእንኳን ደስ ያላችሁ " መልዕክት አስተላልፈዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ያነጋገርናቸው የወላይታ ዲቻ እግር ኳስ ክለብ ስራ አስኪያጅ አቶ አሰፋ ሆሲሶ " ዉሳኔዉ በእግር ኳሱ ዘርፍ ተስፋ ሰጪና ለወላይታ ዲቻ እግር ኳስ ቡድን ደጋፊዎች ትልቅ ደስታን የፈጠረ ተገቢ ዉሳኔ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

" ተክሰናል " ያሉት ስራ አስኪያጁ " የዉሳኔዉን አፈጻጸም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን በሚያስቀሚጠዉ ዕቅድ መሰረት ተፈፃሚ እናደርጋለን " ብለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia
ሪያል ማድሪድ ሩብ ፍፃሜ ተቀላቀለ !

በክለቦች አለም ዋንጫ ውድድር ጥሎ ማለፍ ሪያል ማድሪድ ከጁቬንቱስ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 1ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

የሎስ ብላንኮዎቹን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ጎንዛሎ ጋርሺያ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

እንግሊዛዊው የመስመር ተጨዋች አሌክሳንደር አርኖልድ በሪያል ማድሪድ ማልያ የመጀመሪያውን ለግብ የሆነ ኳስ አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።

ስፔናዊው የፊት መስመር ተጨዋች ጎንዛሎ ጋርሺያ በክለቦች አለም ዋንጫ ባደረጋቸው አራት ጨዋታዎች ሶስት ግቦችን አስቆጥሯል።

ሪያል ማድሪድ በሩብ ፍፃሜው የቦርስያ ዶርትመንድ እና ሞንቴሬይን አሸናፊ የሚገጥሙ ይሆናል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ኦሊቬ ጅሩ ወደ አውሮፓ ሊመለስ ነው ! ፈረንሳዊው የፊት መስመር አጥቂ ኦሊቬ ጅሩ የፈረንሳዩን ክለብ ሊል ለመቀላቀል ከስምምነት መድረሱ ተገልጿል። የቀድሞ የአርሰናል እና ቼልሲ አጥቂ ኦሊቬ ጅሩ ባለፈው አመት ኤሲ ሚላንን በመልቀቅ የአሜሪካውን ክለብ ሎስአንጀለስ ተቀላቅሎ እንደነበር ይታወሳል። በአሜሪካ ጥሩ የሚባል ጊዜ ማሳለፍ ያልቻለው ኦሊቬ ጅሩ ለክለቡ ባደረጋቸው 37 ጨዋታዎች አምስት ግቦችን…
ኦሊቬ ጅሩ ሊልን ተቀላቀለ !

ፈረንሳዊው የፊት መስመር አጥቂ ኦሊቬ ጅሩ የፈረንሳዩን ክለብ ሊል መቃላቀሉ ይፋ ተደርጓል።

ኦሊቬ ጅሩ የአሜሪካውን ክለብ ሎስ አንጀለስ በመልቀቅ ሊልን ለአንድ ተጨማሪ አመት የመቆየት አማራጭ ባካተተ የአንድ አመት ኮንትራት ተቀላቅሏል።

በአሜሪካ ጥሩ የሚባል ጊዜ ማሳለፍ ያልቻለው ኦሊቬ ጅሩ ለክለቡ ባደረጋቸው 37 ጨዋታዎች አምስት ግቦችን ነው ማስቆጠር የቻለው።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ክረምትን በምን ሊያሳል አስበዋል?

Can PlayStation 🎮 መፍትሄ ይዞ ብቅ ብሏል🫴

-Sony
PlayStation 2
PlayStation 3
PlayStation 4
PlayStation 5

-Microsoft
Xbox 360
Xbox one
Xbox one s
Xbox Series

ምርቶችን አዘጋጅቶ እናንተን በመጠበቅ ላይ ነን! እንግዲያውስ እርሶ በተመችዎት ሰዓት ብቅ በማለት ሱቃችን መጎብኘት ይችላሉ።

እቃዎቻችን 6 ወር ዋስትና ስላለው ያለ ሀሳብ ይዝናኑ።

ለልጅም ሆነ ለአዋቂ የሚሆኑ PlayStation Cidi Game ስላሉን ይደውሉልን።

Tv በተለያየ Brand እና Size እኛ ዘንድ ያገኛሉ።

ባሎት ማንኛውም እቃ መቀያየር ይቻላል።

ለክፍለ ሀገር እናቀርባለን ይደውሉ።

🤝Thanks for choice!

አድራሻ፡፦
ቁጥር 1፦  መገናኛ
ቁጥር  2፦  ቦሌ

ስልክ፦ 0904658609 ወይም                  0910529770
0977349492  ይደውሉ

ለአዳዲስ መረጃ Telegram channel join ይበሉ ፦
https://www.tg-me.com/CanPlaystation

                       👍Update Your Life

    Can PlayStation እና Tv Market
አሸናፊዎች እነሆ!
እንደተለመደው ደንበኞቻችን ማሸነፋቸውን ቀጥለዋል።
በየቀኑ ለአምስት እድለኞችም 500 ብር እየሸለምንም ነው
ተራው የእርስዎ ነው !
አሁኑኑ Betika.et ላይ ይወራረዱ!
ቤቲካ የአሸናፊዎች ቤት!
TIKVAH-SPORT
በሩብ ፍፃሜው ምን ልንመለከት እንችላለን ? ሪያል ማድሪድ ዛሬ ምሽት ጁቬንቱስን የሚያሸንፍ ከሆነ በውድድሩ ሩብ ፍፃሜ ታሪካዊ ጨዋታ ልንመለከት እንችላለን። የሪያል ማድሪድ እና ጁቬንቱስ አሸናፊ በሩብ ፍፃሜው የቦርስያ ዶርትመንድ እና ሞንቴሬይን አሸናፊ ይገጥማሉ። ሪያል ማድሪድ ጁቬንቱስን አሸንፎ ዶርትመንድ የሚያልፍ ከሆን ሁለቱ ወንድማማቾች ጁድ ቤሊንግሀም እና ጆቤ ቤሊንግሀም ለመጀመሪያ ጊዜ…
#ClubWorldCup 🇺🇸

ቦርስያ ዶርትመንድ ሞንቴሬይን በሴርሁ ጉራሲ ግቦች 2ለ1 በማሸነፍ የክለቦች አለም ዋንጫ ሩብ ፍፃሜ የተቀላቀለ የመጨረሻው ቡድን ሆኗል።

ዶርትመንድ በሩብ ፍፃሜው ከሪያል ማድሪድ ጋር የሚገናኙ ይሆናል።

በጨዋታው የዶርትመንዱ ጁቤ ቤሊንግሀም የውድድሩን ሁለተኛ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል።

ይህም ማለት ጁቤ ቤሊንግሀም በቅጣት ምክንያት ከታላቅ ወንድሙ ጋር በተቃራኒው የሚጫወትበትን እድል አጥቷል።

በሌላ በኩል ሰርጅዮ ራሞስ ከውድድር መሰንበቱን ተከትሎ የቀድሞ ክለቡን ሪያል ማድሪድ የማይገጥም ይሆናል።

የሩብ ፍፃሜ ጨዋታዎች ምን ይመስላሉ ?

አርብ ( 4:00 ) - ፍሉሚኔንስ ከ አል ሂላል

አርብ ሌሊት ( 10:00 ) - ፓልሜራስ ከ ቼልሲ

ቅዳሜ ( 1:00 ) - ፒኤስጂ ከ ባየር ሙኒክ

ቅዳሜ ( 4:00 ) - ሪያል ማድሪድ ከ ዶርትመንድ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ታሚ አብረሀም ወደ ቱርክ ለማምራት ተስማማ !

የቱርኩ ክለብ ቤሺክታሽ እንግሊዛዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ታሚ አብረሀም ለማስፈረም ከሮማ ጋር ንግግር ላይ መሆናቸውን አስታውቋል።

ታሚ አብረሀም በሮማ ቤት ቀሪ የሁለት የውድድር አመት ኮንትራት አለው።

ያለፈውን የውድድር አመት በውሰት በኤሲ ሚላን ያሳለፈው ታሚ አብረሀም ለክለቡ በሁሉም ውድድሮች 45 ጨዋታዎች አድርጎ 10 ግቦችን አስቆጥሯል።

ኤሲ ሚላን ዝውውሩን በቋሚነት ማድረግ ባለመፈለጉ የ 27ዓመቱ ታሚ አብረሀም ወደ ክለቡ ሮማ ተመልሶ ነበር።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ኳንሳህ ለጤና ምርመራ ጀርመን ይገኛል ! የሊቨርፑሉን የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ጃሬል ኳንሳ ባየር ሌቨርኩሰንን ለመቀላቀል ዛሬ የጤና ምርመራውን ያደርጋል። ተጨዋቹ አሁን ጀርመን መድረሱ ሲገለፅ በቀጣይ የአሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀጉን ስብስብ ይቀላቀላል። ባየር ሌቨርኩሰን ተጨዋቹን 40 ሚልዮን ዩሮ በሚደርስ የዝውውር ሒሳብ ለማስፈረም ከሊቨርፑል ጋር ተስማምተዋል። ሊቨርፑል ከአንድ አመት በኋላ ተጫዋቹን…
ኳንሳህ በይፋ ባየር ሌቨርኩሰንን ተቀላቀለ !

የጀርመን ቡንደስሊጋው ክለብ ባየር ሌቨርኩሰን የሊቨርፑሉን የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ጃሬል ኳንሳህ ማስፈረማቸውን ይፋ አድርገዋል።

ሊቨርፑል በበኩሉ ተጨዋቹ ቡድኑን መልቀቁን በማረጋገጥ መልካም ምኞቱን በማህበራዊ ትስስር ገፁ ገልፆለታል።

በአሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ የሚመራው ባየር ሌቨርኩሰን ተጨዋቹን 35 ሚልዮን ፓውንድ በሚደርስ የዝውውር ሒሳብ አስፈርሟል።

ሊቨርፑል ከአንድ አመት በኋላ ተጫዋቹን 70 ሚልዮን ዩሮ በሚጠጋ ክፍያ መልሰው መግዛት የሚያስችላቸው አንቀጽ አካተዋል።

የ 22ዓመቱ ተከላካይ ጃሬል ኳንሳህ በሚቀጥለው የውድድር አመት በቂ የጨዋታ ሰዓት ያገኛል ተብሎ ይጠበቃል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ጃራድ ብራንዝዌት ውሉን ሊያራዝም ነው ! የመርሲሳይዱ ክለብ ኤቨርተን የመሐል ተከላካይ ጃራድ ብራንዝዌት ኮንትራቱን ለተጨማሪ አመታት ለማራዘም መቃረቡ ተገልጿል። በክለቡ እስከ 2027 የሚያቆይ ውል ያለው ተጨዋቹ አዲስ የረጅም ጊዜ ኮንትራት ለመፈረም መቃረቡ ተነግሯል። የ 23ዓመቱ ተጨዋች ብራንዝዌት ባለፈው አመት ከማንችስተር ዩናይትድ ጥያቄ ቀርቦለት ኤቨርተን ውድቅ ማድረጉ አይዘነጋም። ተጨዋቹ…
ኤቨርተን የቁልፍ ተጫዋቹን ውል አራዘመ !

የመርሲሳይዱ ክለብ ኤቨርተን የመሐል ተከላካያቸው ጃራድ ብራንዝዌትን ኮንትራት ማራዘማቸውን በይፋ አስታውቀዋል።

የ 23ዓመቱ ተጨዋች ብራንዝዌት በኤቨርተን ቤት ከፍተኛ ተከፋይ የሚያደርገውን የአምስት አመት ውል መፈረሙ በይፋ ተገልጿል።

ተጨዋቹ ከአምስት አመታት በፊት ቡድኑን ከተቀላቀለ ወዲህ በ 88 ጨዋታዎች ተሰልፎ ቡድኑን ማገልገል ችሏል።

ኤቨርተን በተጨማሪም የሚሼል ኪን እና እና ጉዬን ኮንትራት ለተጨማሪ አመታት ለማራዘም መቃረባቸው ተገልጿል።

በሌላ በኩል ኤቨርተን የቪያሪያሉን የፊት መስመር ተጨዋች ቴርኖ ባሪ በ 32 ሚልዮን ዩሮ ለማስፈረም የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ ይገኛሉ።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሉዊስ ዲያዝ ወደ ባየር ሙኒክ ?

የቡንደስሊጋው ክለብ ባየር ሙኒክ የሊቨርፑልን የፊት መስመር ተጨዋች ሉዊስ ዲያዝ ለማስፈረም ፍላጎት አሳይተው እንደነበር ተገልጿል።

ይሁን እንጂ ሊቨርፑል ከባየር ሙኒክ የቀረበለትን የእንነጋገር ጥያቄ ውድቅ ማድረጉ ተነግሯል።

ሊቨርፑል ሉዊስ ዲያዝን በዚህ ክረምት በየትኛውም የዝውውር ሒሳብ የመሸጥ ፍላጎት እንደሌላቸው ለባየር ሙኒክ ሀላፊዎች ማሳወቃቸው ተዘግቧል።

በቅርቡ የላሊጋው አሸናፊ ባርሴሎና በተመሳሳይ በተጨዋቹ ላይ ፍላጎት አሳይቶ እንደነበር አይዘነጋም።

ሊቨርፑል ባለፈው አመት ሊጉን ሲያሸንፍ ሉዊስ ዲያዝ 13 ጎሎችን አስቆጥሮ ሰባት አመቻችቶ በማቀበል ጥሩ ጊዜ አሳልፏል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
ጁቬንቱስ ተጨዋች ለማስፈረም ተቃረበ !

የሴርያው ክለብ ጁቬንቱስ ካናዳዊውን የሊል የፊት መስመር ተጨዋች ጆናታን ዴቪድ ለማስፈረም ከስምምነት መድረሱ ተገልጿል።

ጁቬንቱስ ተጫዋቹን በነፃ ዝውውር የመጀመሪያ የክረምቱ ፈራሚው ለማድረግ ከጫፍ መድረሳቸው ተነግሯል።

ተጨዋቹ በጁቬንቱስ ቤት አመታዊ ስድስት ሚልዮን ዩሮ እና ጉርሻ ሁለት ሚልዮን ዩሮ ክፍያ እንደሚያገኝ ተዘግቧል።

የተጨዋቹ ፊርማ ጁቬንቱስ የፊት መስመሩን ለማጠናከር ተጨማሪ ተጨዋች ከመመልከት የሚከለክለው አለመሆኑ ተገልጿል።

ጆናታን ዴቪድ ባለፈው አመት ለሊል ባደረጋቸው 49 ጨዋታዎች 25 ጎሎችን አስቆጥሮ 12 ለግብ የሆነ ኳስ አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
አንድን ክለብ ለመጥቀም ሌላውን ለመጉዳት የተደረገ ውሳኔ አይደለም “ አቶ ኢሳያስ ጅራ

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በፌዴሬሽኑ ዋና ጽ/ቤት ጋዜጣዊ መግለጫ በመስጠት ላይ ይገኛል።

የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ በሰጡት መግለጫ “ ግልፅ መሆን የሚገባው ነገር ውሳኔው በፍትህ አካል የተሰጠ ነው “ ብለዋል።

ቀሪ መመርመር የሚገባቸው 14 ክለቦች እንዳሉ የገለፁት ፕሬዝዳንቱ “ የፍትሐዊነት ጥያቄ “ መኖሩን ገልፀዋል።

አስራ አራቱን ክለቦች አሰመልክቶ “ በአጭር ጊዜ ተግባራዊ ለማድረግ ከሚመለከተው አካል ጋር እየሰራን ነው “ ብለዋል።

“ የሶስተኛ ወገን ጣልቃ ገብነት ተቀባይነት እንደሌለው ልንገነዘብ ይገባል ፣ አንድን ክለብ ለመጥቀም ሌላውን ለመጉዳት የተደረገ ውሳኔ አይደለም “ አቶ ኢሳያስ ጅራ

@tikvahethsport @kidusyoftahe
2025/07/05 15:45:09
Back to Top
HTML Embed Code: