Telegram Web Link
ውሳኔውን አልቀበልም ያለ ክለብ ሊጉን ለቆ መውጣት ይችላል “

“ ውሳኔዎቻችን እግርኳሳዊ ናቸው ፣ የቢዝነስ ውሳኔ አልወሰንም “ አቶ ኢሳያስ ጅራ

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳይስ ጅራ ከጋዜጠኞች ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በዚህም መሰረት :-

- “ ከአራቱ ክለቦች ሶስቱ የታገዱት መደበኛ ፍርድ ቤት ስለወሰዱት ነው ፣ ትክከለኛውን መንገድ ተከትሎ የሄደው ( ወደ ካስ ) መቐለ 70 እንደርታ ነው።

- የኮከብ ግብ አግቢ ደረጃ ሊጉ በሚያወጣው ሰንጠረዥ ይሆናል ፣ የተቀጣ ክለብ ተጫዋች ኮከብ ግብ አግቢ ይሆናል የሚል እምነት የለኝም።

- ውሳኔውን አልቀበልም ያለ ክለብ ሊጉን ለቆ መውጣት ይችላል ፣ የክለቦች መብት ነው።

- ውሳኔዎቻችን እግርኳሳዊ ናቸው ፣ የቢዝነስ ውሳኔ አልወሰንም። ተጫዋቾች ብሩን ካልመለሱ ህጉ ተግባራዊ ይሆናል።

- ፊፋ ለምን ሀያ ተሳታፊ ክለብ አደረጋችሁ አይልም ፣ በዚህ ጉዳይ መወሰን አይችልም። ምክረ ሀሳብ ከመስጠት ውጪ አስገዳጅ ህግ የለውም “ ሲሉ በጋዜጣዊ መግለጫው ተናግረዋል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ቼልሲ ተጨዋች ለማስፈረም ተስማማ ! የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ብራዚላዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ጇ ፔድሮ ለማስፈረም ከብራይተን ጋር ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል። የ 23ዓመቱ የፊት መስመር ተጨዋች ጇ ፔድሮ በቼልሲ እና ኒውካስል ዩናይትድ ቢፈለግም ሰማያዊዎቹን ምርጫው ማድረጉ ተነግሯል። ቼልሲ ለጇ ፔድሮ ዝውውር 50 ሚልዮን ፓውንድ እንደሚያወጡ ሲገለፅ ተጨዋቹ የስድስት አመት ውል እንደሚፈርም…
ቼልሲ በይፋ ተጨዋች አስፈረመ !

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ብራዚላዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ጇ ፔድሮ ማስፈረሙን በይፋ አስታውቋል።

ቼልሲ የ 23ዓመቱን የፊት መስመር ተጨዋች ጇ ፔድሮ እስከ 2032 በሚቆይ የሰባት አመት ኮንትራት አስፈርመዋል።

ሰማያዊዎቹ ለጇ ፔድሮ ዝውውር 60 ሚልዮን ፓውንድ የሚደርስ ዋጋ ማውጣታቸው ተገልጿል።

ቼልሲ የፊት መስመሩን ማጠናከር ሲቀጥል በአጥቂ ቦታ ኒኮላስ ጃክሰን ፣ ንኩንኩ እና ሊያም ዴላፕን ጨምሮ አራተኛ ተጨዋቻቸውን አግኝተዋል።

ተጨዋቹ በውድድር አመቱ ለብራይተን 30 ጨዋታዎች ሲያደርግ 10 የፕርሚየር ሊግ ግቦችን አስቆጥሮ ስድስት አመቻች አቀብሏል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ቼልሲ በይፋ ተጨዋች አስፈረመ ! የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ብራዚላዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ጇ ፔድሮ ማስፈረሙን በይፋ አስታውቋል። ቼልሲ የ 23ዓመቱን የፊት መስመር ተጨዋች ጇ ፔድሮ እስከ 2032 በሚቆይ የሰባት አመት ኮንትራት አስፈርመዋል። ሰማያዊዎቹ ለጇ ፔድሮ ዝውውር 60 ሚልዮን ፓውንድ የሚደርስ ዋጋ ማውጣታቸው ተገልጿል። ቼልሲ የፊት መስመሩን ማጠናከር ሲቀጥል በአጥቂ ቦታ ኒኮላስ…
“ ቼልሲን ከተቀላቀልክ ሀሳብህ ዋንጫ ማሸነፍ ነው “ ፔድሮ

ሰማያዊዎቹን የተቀላቀለው ጇ ፔድሮ ከቼልሲ ጋር በቀጣይ ዋንጫዎችን ማሸነፍ እንደሚፈልግ ከፊርማው በኋላ ተናግሯል።

" ከልጅነቴ ፕርሚየር ሊግ ሳይ ነው ያደኩት " ያለው ጇ ፔድሮ ቼልሲ ዋንጫዎችን የሚያሸንፍ ክለብ ነው ብሏል።

“ ስለዚህ ቼልሲን ከተቀላቀልክ የምታስበው ስለአንድ ነገር ብቻ ነው ዋንጫዎችን ማሸነፍ ነው “ ሲል ተናግሯል።

ስለ ቼልሲ አንድሬ ሳንቶስን ጠይቆ እንደነበር የገለፀው ተጨዋቹ “ ስለ ቡድኑ ጥሩ ነገሮችን ነግሮኛል “በማለት ገልጿል።

ተጨዋቹ ቼልሲ አርብ ከፓልሜራስ ጋር በሚያደርገው የክለቦች አለም ዋንጫ ሩብ ፍፃሜ ጨዋታ ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Wanawsportswear✔️

⭐️ዋናው የስፖርት አልባሳት ብራንድ ከDHL express ጋር በመተባበር  ያለምንም ተጨማሪ ክፍያ ሰሜን አሜሪካ እና ካናዳ ላላችሁ ትውልደ ኢትዩጵያውያን የስፖርት ትጥቅዎትን በራስዎት የዲዛይን ምርጫ በ13,99 ዶላር ከበርዎት በ10 የስራ ቀናት ያደርስልዎታል ከእርሶ የሚጠበውቀው ዋትሳፕ ላይ ማዘዝ ነው‼️

2️⃣0️⃣ ብዛት ጀምሮ
በፈለጉት ዲዛይን!
📦 ዛሬውኑ ይዘዙ

📞ለማዘዝ
+251996648121

🔗 ማህበራዊ ገጾቻችን🔗
Instagram|Facebook |TikTok |X|Youtube
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
“ እኛ ከሮናልዶ ተፅዕኖ ጥገኝነት ተላቀናል “

የሳውዲ አረቢያው ክለብ አል ሂላል ሀላፊ እስቲቭ ካልዛዳ ክርስቲያኖ ሮናልዶ አሁን ላይ በሳውዲ አረቢያ ሊግ ተፅዕኖው እንደቀነሰ ተናግረዋል።

“ መጀመሪያ ላይ የሮናልዶ ተፅዕኖ ትልቅ ነበር “ ያሉት ሀላፊው በርካታ ተጨዋቾች ወደዚህ እንዲመጡ ረድቷል ብለዋል።

አክለውም “ አሁን ላይ ግን ለእኛ ሁሉም ነገር የተለመደ እና የተለየ ሆኗል “ ሲሉ ገልጸዋል።

“ ማንችስተር ሲቲን ያለ ወሳኝ ተጫዋቾቻችን ማንበርከክ ችለናል አል ሂላል በሳውዲ አረቢያ ሊግ ትልቁ ክለብ ነው “ ሲሉ ሀላፊው ተናግረዋል።

" የማንችስተር ሲቲ ድል የሳውዲ አረቢያ ብሔራዊ ቡድን አርጀንቲናን ካሸነፈበት ጋር አይወዳደርም ግን ይቀራረባል።“ እስቲቭ ካልዛዳ

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ቼልሲ በይፋ ተጨዋች አስፈረመ ! የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ብራዚላዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ጇ ፔድሮ ማስፈረሙን በይፋ አስታውቋል። ቼልሲ የ 23ዓመቱን የፊት መስመር ተጨዋች ጇ ፔድሮ እስከ 2032 በሚቆይ የሰባት አመት ኮንትራት አስፈርመዋል። ሰማያዊዎቹ ለጇ ፔድሮ ዝውውር 60 ሚልዮን ፓውንድ የሚደርስ ዋጋ ማውጣታቸው ተገልጿል። ቼልሲ የፊት መስመሩን ማጠናከር ሲቀጥል በአጥቂ ቦታ ኒኮላስ…
ጇ ፔድሮ ምን አይነት ተጨዋች ነው ?

የለንደኑ ክለብ ቼልሲ ብራዚላዊውን የፊት መስመር አጥቂ ጇ ፔድሮ ከ 50 ሚልዮን ፓውንድ በላይ በማውጣት ወደ ስብሰባቸው ቀላቅለዋል።

ተጨዋቹ በእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ጨዋታዎች ጥሩ የሚባል ግብ የማስቆጠር እና አመቻችቶ የማቀበል ቁጥር ይዟል።

ፔድሮ በፕርሚየር ሊጉ በአማካይ በ 90 ደቂቃ 0.35 ጎል የማስቆጠር እና 0.16 ለግብ የሆነ ኳስ አመቻችቶ የማቀበል ሪከርድ አለው።

ይሁን እንጂ ጇ ፔድሮ በቀጣይነት ግብ የሚያስቆጥር እና የሚያገኛቸውን የግብ እድሎች በተከታታይ ወደ ግብነት የሚቀይር አይነት አጥቂ ተደርጎ አይታሰብም።

ይህንንም ተከትሎ የቼልሲ ደጋፊዎች በቀጣይ ጇ ፔድሮ በቡድናቸው በቋሚነት ግብ ሲያስቆጥር ላይመለከቱ ይችላሉ።

ጇ ፔድሮ ወደ ኳስ ለመቅረብ ንቁ ሆኖ በሚያደርገው እንቅስቃሴ እና ከፊት መስመር ተጨዋቾች ጋር በሚፈጥረው ውጤታማ ጥምረት ይታወቃል።

ይህንንም ተከትሎ ተጨዋቹ የቡድኑ የፊት መስመር የበለጠ ስኬታማ እንዲሆን ለመርዳት የበኩሉን ሚና እንደሚወጣ ይጠበቃል።

ኢንዞ ማሬስካ በቡድናቸው ውስጥ የጇ ፔድሮ አይነት የአጨዋወት ባህሪ ያለው ተጨዋች ባለመኖሩ ተጨዋቹ በቀጣይ በቼልሲ ፊት መስመር ወሳኝ ሚና ይኖረዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የራስሙስ ሆይሉንድ የዩናይትድ ቆይታ ?

ራስሙስ ሆይሉንድ በክረምቱ የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት ማንችስተር ዩናይትድን የሚለቅበት እድል ሰፊ መሆኑ ተገልጿል።

ዴንማርካዊው የፊት መስመር ተጨዋች ራስሙስ ሆይሉንድ ክለቡን ከለቀቀ በቋሚነት የሚለቅበት እድል ሰፊ መሆኑ ተጠቁሟል።

ተጫዋቹን ለማስፈረም የሴርያው ክለብ ኢንተር ሚላን ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላቸው ተነግሯል።

ሆይሉንድ በቅርቡ “ በማንችስተር ዩናይትድ ቤት የመቀጠል ሀሳብ አለኝ " ሲል ተናግሮ ነበር።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
ክረምትን በምን ሊያሳልፋ አስበዋል?

Can PlayStation 🎮 መፍትሄ ይዞ ብቅ ብሎሎታል🫴

-Sony
PlayStation 2
PlayStation 3
PlayStation 4
PlayStation 5

-Microsoft
Xbox 360
Xbox one
Xbox one s
Xbox Series

ምርቶችን አዘጋጅቶ እናንተን በመጠበቅ ላይ ነን
እንግዲያውስ እርሶ በተመቻቹ ሰአት ብቅ በማለት ሱቃችን መጎብኘት ይችላሉ

እቃዎቻችን 6 ወር ዋስትና ስላለው የለ ሀሳብ ይዝናኑ

ለልጅም ለአዋቂ የሚሆኑ PlayStation Cidi Game ስላሉን ይደውሉልን

Tv በተለያየ Brand እና Size እኛ ዘንድ ያገኛሉ

ባሎት ማንኛውም እቃ መቀያየር ይቻላል

ለክፍለ ሀገር እናቀርባለን ይደውሉ

🤝Tanks for choice

አድራሻ፡፦
ቁጥር 1፦  መገናኛ
ቁጥር  2፦  ቦሌ

ስልክ፦ 0904658609 ወይም                  0910529770
0977349492  ይደውሉ

ለአዳዲስ መረጃ Telegram channel join ይበሉ ፦
https://www.tg-me.com/CanPlaystation

                       👍Update Your Life

    Can PlayStation እና Tv Market
ተወዳጁን ክራሽ ሮያል ጨዋታ እንዴት መጫወት እና ማሸነፍ እንዳለብዎ ያውቃሉ?
ቀላል እና ፈጣኑን መንገድ እናሳይዎ፡

ወደhttps://www.betika.com/et/ ይሂዱ እና 'Crash games' የሚለውን አማራጭ ይምረጡ።

ከጨዋታ ምርጫዎች ውስጥ ክራሽ ሮያልን ይምረጡ።
ቅጽል ስምዎን ያስገቡ
የዚህ ጨዋታ አላማ ኳሱ ሳይፈነዳ ካሽ አውት ማድረግ ነው።
የሚፈልጉት የገንዘብ መጠን ካስገቡ በኋላ ውርርድዎን ለማስያዝ "Place bet " የሚለውን ይጫኑ።
ኳሱ ረዥም ርቀት በሄደ ቁጥር የሚያሸንፉበት ማባዣ ከፍ እያለ ይሄዳል።
በማንኛውም ጊዜ ካሽ አውት ማድረግ ከፈለጉ የሚከፈሎትን ክፍያ ማየት ይችላሉ ።
እያንዳንዱ ዙር ልዩ ቁጥር ያለው ሲሆን ውጤቱም በስክሪኑ ላይ ለተጨዋቹ ይታያል። በተጨማሪም ሁሉም ውጤቶች እንዲሁ በ "Bet history" ስርላይ ሊገኙ ይችላሉ።
በቀላሉ ከላይ የተቀመጡትን በመከተል ይጫወቱ፣ ይወራረዱ፣ በትልቁ ያሸንፉ!
ቤቲካ - የአሸናፊዎች ቤት!
“ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ኪሳራ ነው “

የሊጉ አክስዮን ማህበር የቦርድ ሰብሳቢ መቶ አለቃ ፈቃደ ማሞ በወቅታዊ ጉዳዩ ላይ ከ EBC ጋር ባደረጉት ቆይታ እግር ኳሱ “ ትርፍ “ የለውም ሲሉ ተናግረዋል።

የ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ “ በክፍያ ከአፍሪካ አራተኛ ነው “ ያሉት መቶ አለቃ ሆኖም ግን የወጣበትን ያህል ውጤት የማይገኝበት መሆኑን ገልፀዋል።

“ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ኪሳራ ነው ትርፍ የለውም ፣ ከዚህ ተነስተን የፋይናንስ መመሪያ አውጥተናል። ይህን መመሪያ ሁሉም የክለቦች አባላት አጨብጭበው ነበር የተቀበሉት “ መቶ አለቃ ፈቃደ ማሞ

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ዲያጎ ጆታ ህይወቱ ማለፉ ተገለፀ !

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል የመስመር ተጫዋች ዲያጎ ጆታ በስፔን በደረሰበት የመኪና አደጋ ህይወቱ ማለፉን “ማርካ” አስነብቧል።

መረጃውን የስፔኑ ማርካ ከደቂቃዎች በፊት ቢያወጣውም ክለቡ መረጃውን እስከ አሁን ይፋ አላደረገውም።

ዛሞራ በተሰኘ አካባቢ ዲያጎ ጆታ በመኪና አደጋ ህይወቱ ማለፉ ሲገለፅ በመኪና ውስጥ የነበረው ወንድሙም ህይወቱ አልፏል።

በደረሰው አደጋ መኪናው የእሳት አደጋ እንደደረሰበት ሲገለፅ ከባድ ያለ እንደነበረም ተዘግቧል።

የዛሞራ ከተማ አስተዳደር አደጋ መድረሱን ቢያሳውቅም አደጋ የደረሰባቸውን ስም ከመግለፅ ተቆጥቧል።

አደጋውን ይፋ ሲያደርጉም የ 28 እና 26 ባለ እድሜ በአደጋው ህይወታቸው አልፏል ብሏል።

ዲያጎ ጆታ ከአምስት ቀናት በፊት የሰርግ ስነ-ስርዓቱን በስፔን ማከናወኑ ተገልጿል።

❗️መረጃውን የስፔኑ ማርካ ብቻ ያወጣው ሲሆን ክለቡ ማረጋገጫ አልሰጠም።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ዲያጎ ጆታ ህይወቱ ማለፉ ተገለፀ ! የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል የመስመር ተጫዋች ዲያጎ ጆታ በስፔን በደረሰበት የመኪና አደጋ ህይወቱ ማለፉን “ማርካ” አስነብቧል። መረጃውን የስፔኑ ማርካ ከደቂቃዎች በፊት ቢያወጣውም ክለቡ መረጃውን እስከ አሁን ይፋ አላደረገውም። ዛሞራ በተሰኘ አካባቢ ዲያጎ ጆታ በመኪና አደጋ ህይወቱ ማለፉ ሲገለፅ በመኪና ውስጥ የነበረው ወንድሙም ህይወቱ አልፏል። በደረሰው…
ዲያጎ ጆታ የተወደደ እና የተከበረ ተጫዋች ነበር “ የፖርቹጋል እግር ኳስ ፌዴሬሽን

ዲያጎ ጆታ እና ወንድሙ አንድሬያ ሲልቫ ህይወታቸው ዛሬ ንጋት ላይ ማለፉን የስፔን መገናኛ ብዙሀን አስነብበዋል።

የትራፊክ አደጋው መኪናው መንገድ ስቶ በመውጣት የእሳት አደጋ እንዳጋጠመው ተገልጿል።

የፖርቹጋል እግር ኳስ ፌዴሬሽን በዜናው ማዘኑን በመግለፅ “ ሁለት ሻምፒዮኖችን አጥተናል “ ሲል ባወጣው መግለጫ አስነብቧል።

ዲያጎ ጆታ “ ከተጫዋችም በላይ “ በማለት የገለፀው ፌዴሬሽኑ “ በተቃራኒ ቡድን ሳይቀር የተወደደ እና የተከበረ ተጫዋች ነው “ ብሏል።

የፖርቹጋል እግር ኳስ ፌዴሬሽን በሴቶች የአውሮፓ ዋንጫ ፖርቹጋል ከ ስፔን ሐሙስ ስትጫወት የአንድ ደቂቃ የህሊና ፀሎት እንዲኖር ዩፋን መጠየቃቸውን አሳውቀዋል።

ከአምስት ቀናት በፊት የጋብቻ ስነ-ስርዓቱን ያደረገው ዲያጎ ጆታ የሶስት ልጆች አባት ነበር።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
Photo
#Update

የመኪናው አደጋ ከጠዋቱ 12:30 ላይ መደረሱን የከተማው ፖሊስ ሲያረጋግጡ የሁለቱም ህይወት ማለፉን አሳውቋል።

ጆታ እና ሲልቫ በማድሪድ ግዛት በሰሜናዊ ፖርቹጋል ወደምትገኘው ጋላሲያ ከተማ እያቀኑ እንደነበረ ገልጿል።

በዲያጎ ጆታ ስም የምትገኘው መኪና መንገድ በመሳት አደጋውን ስታደርስ የእሳት አደጋም እንዲፈጠር ምክንያት መሆኑን ፖሊስ አሳውቋል።

ዶያጎ ጆታ በዘንድሮው የውድድር ዘመን የፕርሚየር ሊግ እና ኔሽን ሊግ ዋንጫ ማሸነፍ ችሎ ነበር።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
በዲያጎ ጆታ አሳዛኝ ህልፈት አዝነናል “ ሊቨርፑል እግር ኳስ ክለብ

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል የተጫዋቻቸውን ህልፈተ ህይወት ባወጡት አጭር መግለጫ ይፋ አድርገዋል።

የ 28ዓመቱ ዲያጎ ጆታ እና ወንድሙ ህይወት በመኪና አደጋ ማለፉን ክለቡ ማወቁን ገልጿል።

ሊቨርፑል እግር ኳስ ክለብ ለተጫዋቹ እና ለቤተሰቡ ደህንነት ሲል ተጨማሪ መረጃን ለጊዜው እንደማይሰጥ አሳውቋል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
“ አንተን በጭራሽ አልረሳህም “ ሩበን ኔቬዝ

ፖርቹጋላዊው ተጨዋች ሩበን ኔቬዝ በዲያጎ ጆታ ህልፈት የተሰማውን ሀዘን በማህበራዊ ትስስር ገፁ ገልጿል።

“ ሰውን የምታጣው ስትረሳው ብቻ ነው ይባላል “ ሲል መልዕክቱን ያጋራው ሩበን ኔቬዝ “ አንተን በጭራሽ አልረሳህም “ በማለት ተናግሯል።

ዲያጎ ጆታ በእግርኳስ ውስጥ የቅርብ ጓደኛው ሩበን ኔቬዝ መሆኑን ከዚህ በፊት በሰጠው አስተያየት ተናግሮ ነበር።

የቀድሞ የቡድን አጋሩ ስቴፋን ባቼቲች በበኩሉ “ ሁልጊዜም እናስታውስሀለን ጓደኛዬ “ ሲል ሀዘኑን ገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ አደጋው የደረሰው ጎማው ፈንድቶ ነው “

ዲያጎ ጆታ እና ወንድሙ ያጋጠማቸው የመኪና አደጋ መንስኤው የመኪናው ጎማ መፈንዳቱ መሆኑን የአካባቢው ፖሊስ አስታውቋል።

ሁለቱ ተጨዋቾች ሲጓዙበት የነበረው ላምበርጊኒ መኪና ሌላ መኪና ለማለፍ በሚሞክርበት ወቅት የጎማ መፈንዳት አደጋ እንዳጋጠመው ፖሊስ ገልጿል።

ይህንንም ተከትሎ መኪናው ጎማው በመፈንዳቱ መንገድ ስቶ በመውጣት አደጋው እንደደረሰበት ተገልጿል።

መኪናው በአደጋው ሙሉ ለሙሉ በእሳት በመቃጠሉ ምክንያት የተጨዋቾቹ ህይወት ሊያልፍ እንደቻለ ተነግሯል።

በስፍራው የነበሩ ሰዎች ለፖሊስ ማሳወቃቸው ሲገለፅ በወቅቱ መኪናው በእሳት ጋይቶ እንደነበር ምስክርነት መስጠታቸው ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" የተፈጠረውን ማመን አልቻልኩም " ክርስቲያኖ ሮናልዶ

የፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን አምበል ክርስቲያኖ ሮናልዶ የዲያጎ ጆታን ህልፈት " ማመን አልቻልኩም “ ሲል ሀዘኑን ገልጿል።

" የተፈጠረውን ማመን አልቻልኩም በብሔራዊ ቡድኑ አብረን ነበርን የትዳር ህይወትህን ገና መጀመርህ ነው “ ሲል ሮናልዶ ተናግሯል።

“ ለቤተሰቡ እና ለሚወዱህ ሁሉ መፅናናትን እመኛለሁ በእነሱ እና በእኛ ልብ ውስጥ ለዘለዓለም እንደምትኖር አውቃለሁ ሁለታችሁንም ነብስ ይማር “ ሮናልዶ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Update

የዲያጎ ጆታ የቅርብ ጓደኛ እና የቀድሞ የቡድን አጋር ሩብን ኔቬስ በከፍተኛ ሀዘን ውስጥ እንደሚገኝ የሳውዲ አረቢያ የመገናኛ ብዙሀን እየዘገቡ ይገኛሉ።

የአል ሂላል ክለብ አመራሮች ተጫዋቹ በወሳኙ የነገው የክለቦች አለም ዋንጫ ጨዋታ ላይ በነፃነት ውሳኔው እንዲያሳውቅ መፍቀዳቸው ተገልጿል።

ሩብን ኔቬስ በጥሩ የአዕምሮ ጥንካሬ ላይ እንደማይገኝ ሲገለፅ በቅርብ ጓደኛው ስርዓተ ቀብር ላይ እንደሚገኝ መረጃው አስነብቧል።

አል ሂላል በነገው ዕለት በክለቦች የአለም ዋንጫ በሩብ ፍፃሜ መርሐ ግብር ፍሉሚኔንሴን የሚገጥሙ ይሆናል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
2025/07/05 11:45:08
Back to Top
HTML Embed Code: