Telegram Web Link
ሊቨርፑል የዝግጅት መጀመሪያ ቀኑን ሊያራዝም ነው !

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል በዲያጎ ጆታ ህልፈት ምክንያት የቅድመ ውድድር ዝግጅት መጀመሪያ ቀናቸውን ሊያራዝሙ እንደሚችሉ ተገልጿል።

ሊቨርፑል የቅድመ ውድድር ዝግጅቱን መቼ ለመጀመር እንዳሰበ በግልጽ እንዳልታወቀ ተነግሯል።

በተጨማሪም ሊቨርፑል ከዘጠኝ ቀናት በኋላ ከ ፕሪስተን ጋር የሚያደርገው የመጀመሪያ የወዳጅነት ጨዋታ መደረግ አለመደረጉ አልተወሰነም።

ሊቨርፑል የክለቡ አገልግሎት መስጫ ተቋማት እስከ ሰኞ ዝግ ሆነው እንዲቆዩ መወሰኑን ማስታወቁ አይዘነጋም።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Wanawsportswear✔️

ዋናው ፕሪምየም ማሊያ በቁምጣ | ገደቡ ለማይበግራቸው ለታላላቅ ቡድኖች ትክክለኛው ምርጫ
⚡️ጥንቅቅ ያለ
🫶 የአንድነት ስሜትን የሚሰጥ
👏 የምርት ጥራቱን ኢትዮጵያን ጨምሮ የላይቤሪያ ብሄራዊ ቡድን የመሰከረለት

ዋናው ፕሪምየም (No Socks Edition) በያዛቸው
🤔ዘመናዊ የቦዲ ማፒንግ ቴክኖሎጂ
🤔ፈጣን ሞቃት አየርን ከሰውነት ወደ ውስጥ እና ወደ ውጭ መውጣት የሚያስችል
🤔2024/25 ኤክስፖርት ስታንዳርድ ተጨማሪ አቅምን ያጎናጽፍዎታል

💰በ1700ብር | ማሊያ እና ቁምጣ
🔥 ብዛት 50 በላይ ለምታዙ ከዋናው ስፖርት 1ኛ ደረጃ ኳስ(professional Football) ስጦታ ይኖራችኋል!

📞ለማዘዝ
8️⃣2️⃣8️⃣9️⃣
➡️+251901138283
➡️+251910851535
➡️+251913586742

🔗 ማህበራዊ ገጾቻችን🔗
Instagram|Facebook |TikTok |X|Youtube
🔥🔥🔥🔥በኢትዩጵያ የተመረተ🔥🔥🔥🔥
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የየእለቱን ዜናዎችን በSMS እናግኝ! 🗞📲

ከሳፋሪኮም ቁጥራችን 'A’ ብለን ወደ 30000 SMS አሁኑኑ በመላክ ወይም ወደ *799# በመደወል የቲክቫህ ትኩስ መረጃዎችን እናግኝ! በቀን 1ብር ብቻ! ከሳፋሪኮም ጋር አንድ ወደፊት ⚡️

#SafaricomEthiopia
#1Wedefit
#Furtheraheadtogether
“ አጨዋወቴ እንደ ሜሲ ነው “ እስቴቫኦ

የወደፊቱ የቼልሲ የፊት መስመር ተጨዋች እስቴቫኦ የአጨዋወት ዘይቤው ከሊዮኔል ሜሲ ጋር እንደሚመሳሰል ተናግሯል።

ዛሬ ምሽት ከፓልሜራስ ጋር ቼልሲን የሚገጥመው ተጨዋቹ " አጨዋወቴ ከሊዮኔል ሜሲ ጋር ተመሳሳይ ሆኖ ነው የምመለከተው “ ብሏል።

ስለወደፊት ህልሙ ያነሳው ተጨዋቹ “ ከአለም ዋንጫ ቀጥሎ ሁለተኛ ህልሜ ባሎን ዶር ማሸነፍ ነው በማለት ተናግሯል።

ሰማያዊዎቹ 34 ሚልዮን ዩሮ በማውጣት ያስፈረሙት እስቴቫኦ ከክለቦች አለም ዋንጫ በኋላ ቡድኑን ይቀላቀላል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቶማስ ፓርቴ ክስ እንደተመሰረተበት ተገለጸ !

ጋናዊው የቀድሞ የአርሰናል የመሐል ሜዳ ተጨዋች ቶማስ ፓርቴ በአስገድዶ መድፈር እና ፆታዊ ጥቃት ክስ እንደተመሰረተበት ተገልጿል።

ተጨዋቹ አምስት የአስገድዶ መድፈር እና አንድ የፆታዊ ጥቃት ወንጀል በመፈጸም ክስ እንደተመሰረተበት ተነግሯል።

ፓርቴ የቀረበበት ክስ ሶስት የተለያዩ ሴቶች ሪፖርት ያደረጉት በ 2021 እና 2022 መካከል የተፈጠረ ክስተት መሆኑ ተገልጿል።

ተጨዋቹ ከ 2022 ጀምሮ ምርመራ ላይ እንደነበር ሲገለፅ ውሉ እስከሚጠናቀቅ ለአርሰናል መጫወቱን እንደቀጠለ ተዘግቧል።

በቅርቡ ከአርሰናል ጋር የተለያየው ቶማስ ፓርቴ በቀጣይ ነሐሴ ወር ውስጥ ፍርድ ቤት እንደሚቀርብ ተገልጿል።

ተጨዋቹ ጥፋተኛ ሆኖ ከተገኘ እስከ 25 አመት እስራት ሊጠብቀው እንደሚችል ተነግሯል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
ዩናይትድ የ 1️⃣0️⃣ ቁጥር ማልያን ለኩንሀ ሰጠ !

አዲሱ የማንችስተር ዩናይትድ ፈራሚ ማቲውስ ኩንሀ በቀጣይ በማንችስተር ዩናይትድ የ 1️⃣0️⃣ ቀጥር ማልያ ተሰጥቶታል።

1️⃣0️⃣ ቁጥር ማልያ ከዚህ በፊት በማርከስ ራሽፍርድ ይለበስ እንደነበር ይታወሳል።

ማርከስ ራሽፎርድ ማንችስተር ዩናይትድን መልቀቅ እንደሚፈልግ ለክለቡ ማሳወቁ ተነግሯል።

በተጨማሪም አንቶኒ ፣ አሌሀንድሮ ጋርናቾ ፣ ጄደን ሳንቾ እና ማላሽያ ክለቡን ለመልቀቅ ጥያቄ ማቅረባቸው ተዘግቧል።

ይህንንም ተከትሎ ተጨዋቾቹ ዘግይተው ወደ ክለቡ እንዲመለሱ ፍቃድ እንደተሰጣቸው ተዘግቧል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ቶማስ ፓርቴ ክስ እንደተመሰረተበት ተገለጸ ! ጋናዊው የቀድሞ የአርሰናል የመሐል ሜዳ ተጨዋች ቶማስ ፓርቴ በአስገድዶ መድፈር እና ፆታዊ ጥቃት ክስ እንደተመሰረተበት ተገልጿል። ተጨዋቹ አምስት የአስገድዶ መድፈር እና አንድ የፆታዊ ጥቃት ወንጀል በመፈጸም ክስ እንደተመሰረተበት ተነግሯል። ፓርቴ የቀረበበት ክስ ሶስት የተለያዩ ሴቶች ሪፖርት ያደረጉት በ 2021 እና 2022 መካከል የተፈጠረ ክስተት…
“ ቶማስ ፓርቴ እንዲከሰስ ፈቅደናል “ ፖሊስ

የእንግሊዝ የህግ አካል የሆነው " CPS " የቶማስ ፓርቴን ጉዳይ ከመረመረ በኋላ ተጨዋቹ ክስ እንዲመሰረትበት መፍቀዱን አስታውቋል።

" CPS " በእንግሊዝ ፖሊስ እና ሌሎች የህግ አካላት የመረመሯቸውን የወንጀል ጉዳዮች ወደ ክስ የሚወስድ ገለልተኛ ተቋም መሆኑ ተገልጿል።

የህግ ተቋሙ ከዚህ በፊት ከሜትሮፖሊታን ፖሊስ የተላከለትን ማስረጃ እየገመገመ መሆኑን ገልፆ ነበር።

አሁን ላይ " CPS " የምርመራ ማስረጃውን በጥንቃቄ ከመረመረ በኋላ ቶማስ ፓርቴ በአስገድዶ መድፈር ክስ እንዲመሰረትበት ፍቃድ መስጠቱን አስታውቋል።

ምርመራውን የመሩት የፖሊስ ሀላፊ በበኩላቸው በሰጡት አስተያየት “ ትኩረታችን ወደፊት መጥተው ጉዳታቸውን የተናገሩ ሴቶችን መርዳት ላይ ነው " ብለዋል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
የዲያጎ ጆታ ቀብር መቼ ይፈፀማል ?

በድንገተኛ አደጋ ህይወታቸው ያለፈው ዲያጎ ጆታ እና ወንድሙ አስከሬን በትውልድ መንደራቸው ፖርቹጋል ጎንዶማር በሚገኝ የእምነት ተቋም ይገኛል።

የተጨዋቾቹ አስከሬን ትላንት ከስፔን ወደ ፖርቹጋል መወሰዱ ተገልጿል።

የፖርቹጋሉ ጠቅላይ ሚኒስቴር ሉዊስ ሞንቴኔግሮ ዛሬ ከሰዓት በኋላ በስፍራው ተግኝተው ሀዘናቸውን መግለፃቸው ተገልጿል።

የተጨዋቾቹ ስርዓተ ቀብር በነገው ዕለት ቅዳሜ እንደሚፈፀም ተነግሯል።

በነገው ስረዓተ ቀብር በርካታ የሊቨርፑል ተጨዋቾች እንዲሁም የቡድን አባላት ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የቀድሞ የሊቨርፑል ተጨዋች ጆርዳን ሄንደርሰን በዛሬው ዕለት አንፊልድ ተገኝቶ ሀዘኑን በመግለፅ አበባ አስቀምጧል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
“ ቶማስ ፓርቴ እንዲከሰስ ፈቅደናል “ ፖሊስ የእንግሊዝ የህግ አካል የሆነው " CPS " የቶማስ ፓርቴን ጉዳይ ከመረመረ በኋላ ተጨዋቹ ክስ እንዲመሰረትበት መፍቀዱን አስታውቋል። " CPS " በእንግሊዝ ፖሊስ እና ሌሎች የህግ አካላት የመረመሯቸውን የወንጀል ጉዳዮች ወደ ክስ የሚወስድ ገለልተኛ ተቋም መሆኑ ተገልጿል። የህግ ተቋሙ ከዚህ በፊት ከሜትሮፖሊታን ፖሊስ የተላከለትን ማስረጃ እየገመገመ…
“ ቶማስ ፓርቴ ክሱን አይቀበልም “ ጠበቃው

የአስገድዶ መድፈር እና ፆታዊ ጥቃት ክስ የቀረበበት ቶማስ ፓርቴ ክሱን ውድቅ እንዳደረገ የህግ ጠበቃው ተናግረዋል።

“ ቶማስ ፓርቴ ክሱን ውድቅ አድርጓል “ ያሉት ጠበቃው በሶስት አመቱ ምርመራ ከፖሊስ እና አቃቢ ህግ ጋር ተባብሮ ሰርቷል ብለዋል።

“ አሁን ላይ ቶማስ ፓርቴ በመጨረሻም ስሙን ለማንፃት እድሉን በደስታ ይቀበላል “ ጠበቃው

አክለውም “ እየተካሄደ በሚገኘው የህግ ሂደት ምክንያት ደንበኛዬ ተጨማሪ አስተያየት መስጠት አይችልም " ብለዋል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቼልሲ ከፍተኛ የገንዘብ ቅጣት ተጣለበት !

የአውሮፓ እግርኳስ ማህበር የፋይናንሻል ፌር ፕሊይ ህጉን አላከበሩም ባላቸው ክለቦች ላይ የቅጣት ውሳኔ ማስተላለፉን አስታውቋል።

ቼልሲ ቅጣት ከተጣለባቸው ክለቦች መካከል አንዱ ሲሆን 20 ሚልዮን ዩሮ ቅጣት እንዲከፍል ተወስኖበታል።

በድጋሜ ህጉን የሚጥሱ ከሆነ 60 ሚልዮን ዩሮ እንደሚቀጡ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው ተጠቁሟል።

በተጨማሪም ኦሎምፒክ ሊዮን 12.5 ሚልዮን ዩሮ መቀጣታቸው ተነግሯል።

በሌላ በኩል ህጉን ጥሰዋል የተባሉት ባርሴሎና 15 ሚልዮን ዩሮ እንዲሁም አስቶንቪላ 5 ሚልዮን ዩሮ ቅጣት ተጥሎባቸዋል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ኒኮ ዊሊያምስ በይፋ ውሉን አራዘመ! ስፔናዊው የአትሌቲክ ቢልባኦ የፊት መስመር ተጫዋች ኒኮ ዊልያምስ ውሉን ለተጨማሪ ስምንት አመታት ማራዘሙን ክለቡ ይፋ አድርጓል። ተጫዋቹ በአትሌቲክ ቢልባኦ ቤት እስከ 2035 ድረስ የሚያቆየውን የረዥም አመት ውል መፈረሙ ይፋ ተደርጓል። ምንም እንኳ ባርሴሎና በተጫዋቹ ላይ ከፍተኛ ፍላጎት ቢኖረውም ተጫዋቹ ግን በአትሌቲክ ቢልባኦ ለመቆየት መወሰኑ ተገልጿል። ኒኮ…
የኒኮ ዊሊያምስ የባርሴሎና ዝውውር ለምን ቀረ ?

ባርሴሎና ስፔናዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ኒኮ ዊሊያምስ ለማስፈረም ከጫፍ ደርሰው በግልም ከስምምነት ደርሰው ነበር።

ይሁን እንጂ ኒኮ ዊሊያምስ በዛሬው ዕለት በአትሌቲክ ቢልባኦ ለአስር አመታት ለመቆየት ውሉን አራዝሟል።

የባርሴሎና ዝውውር ምን ገጠመው ?

ኒኮ ዊሊያምስ ባርሴሎና ባለበት የፋይናንስ ችግር ምክንያት ማስመዝገብ ካልቻለ ክለቡን መልቀቅ የሚያስችለው አንቀጽ በውሉ እንዲካተት መጠየቁ ተገልጿል።

ባርሴሎና በበኩሉ ኒኮ ዊሊያምስ የጠየቀውን የመልቀቅ መብት አንቀጽ ጥያቄ ውድቅ ማድረጉ ተነግሯል።

የኒኮ ዊሊያምስ ተወካዮች ተጨዋቹ ከላሊጋው የመጀመሪያ ጨዋታ ጀምሮ እንደሚመዘገብ ማረጋገጫ ፈልገው እንደነበር ተገልጿል።

የኒኮ ዊሊያምስ በአትሊቲክ ቢልባኦ ከፍተኛ ውል ማፍረሻ ያለው ውል መፈረሙ ዜና ከተጨዋቹ ጋር የተጫወቱ የባርሴሎናን ተጨዋቾችንም ማስደንገጡ ተነግሯል።

በተጨማሪም የባርሴሎና ሀላፊዎች የተጫዋቹን ውል ማራዘም ውሳኔ ከማህበራዊ ሚዲያ ማየታቸው ተዘግቧል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቤተሰቦችህ ምንም እንደማይጎልባቸው አረጋግጥልሀለው “ ሩብን ኔቬስ

የዲያጎ ጆታ የቅርብ ጓደኛ እና የቀድሞ የቡድን አጋር ሩብን ኔቬስ የተሰማውን ሀዘን ሲገልፅ “ አንተን ማጣቴ ደካማ ሰው አድርጎኛል “ ብሏል።

በብሔራዊ ቡድን ቆይታቸው በምግብ ቤት ፣ በክፍል ውስጥ እና በፕሌን ጉዟቸው የማይለያዩት ጆታ እና ኔቬስ “ በህይወት ባለመኖርህ ለአንተ ያለኝ ነገር አይቀየርም “ ሲል ተናግሯል።

“ሁሌም ከጎኔ መሆንህን ትቀጥላለህ “ ያለው ኔቬስ “ቤተሰቦችህ እና የምትወዳቸው ግለሰቦች ፍላጎታቸው እንደማይጓደልባቸው ላረጋግጥልህ እወዳለሁ “ የሚል መልዕክቱን አጋርቷል።

“ ህይወት አንድ አድርጋናለች አሁንም ቢሆን ልትነጥልን አትችልም ፣ አንድ መሆናችንን እንቀጥላለን “ ሩብን ኔቬስ

ሩብን ኔቬስ በመጨረሻም “ ከዛሬ ጀምሮ ወደ ሜዳ አብረሀኝ ትገባለህ ፣ ለመጀመሪያ ጊዜ በተዋወቅንበት የሜዳ መድረክ ጉዟችንን እንቀጥላለን “ ሲል የሀዘን መልዕክቱን አስፍሯል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ካይል ዎከር በርንሌይን ለመቀላቀል ተቃርቧል !

እንግሊዛዊው የመስመር ተጨዋች ካይል ዎከር አዲስ አዳጊውን በርንሌይ ለመቀላቀል ከጫፍ መድረሱ ተገልጿል።

በርንሌይ የ 35ዓመቱን ተጨዋች ካይል ዎከር በቋሚነት ለማስፈረም የጤና ምርመራውን ለማድረግ መዘጋጀታቸው ተነግሯል።

ተጨዋቹ በበርንሌይ የሁለት አመት ኮንትራት ይፈርማል ተብሎ ሲጠበቅ በርንሌይ በበኩሉ ለቡድኑ የረጅም ጊዜ ልምድ ባለቤት ተጨዋች ያገኛል።

ካይል ዎከር በቶተንሀም ቆይታው ከአሁኑ የበርንሌይ አሰልጣኝ ስኮት ፓርከር ጋር ለሁለት አመታት ተጫውተዋል።

ማንችስተር ሲቲ በበኩሉ በሚቀጥለው አመት ውሉ ከሚጠናቀቀው ተጨዋቹ ዝውውር አምስት ሚልዮን ፓውንድ እንደሚያገኙ ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ጁቬንቱስ ተጨዋች ለማስፈረም ተቃረበ ! የሴርያው ክለብ ጁቬንቱስ ካናዳዊውን የሊል የፊት መስመር ተጨዋች ጆናታን ዴቪድ ለማስፈረም ከስምምነት መድረሱ ተገልጿል። ጁቬንቱስ ተጫዋቹን በነፃ ዝውውር የመጀመሪያ የክረምቱ ፈራሚው ለማድረግ ከጫፍ መድረሳቸው ተነግሯል። ተጨዋቹ በጁቬንቱስ ቤት አመታዊ ስድስት ሚልዮን ዩሮ እና ጉርሻ ሁለት ሚልዮን ዩሮ ክፍያ እንደሚያገኝ ተዘግቧል። የተጨዋቹ ፊርማ ጁቬንቱስ…
ጁቬንቱስ በይፋ ተጨዋች አስፈረመ !

የሴርያው ክለብ ጁቬንቱስ ካናዳዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ጆናታን ዴቪድ በአምስት አመት ኮንትራት ማስፈረማቸውን በይፋ አስታውቀዋል።

ጁቬንቱስ ተጫዋቹን በነፃ ዝውውር የመጀመሪያ የክረምቱ ፈራሚው በማድረግ ወደ ስብሰባቸው ቀላቅለዋል።

ተጨዋቹ በጁቬንቱስ ቤት አመታዊ ስድስት ሚልዮን ዩሮ እና ጉርሻ ሁለት ሚልዮን ዩሮ ክፍያ እንደሚያገኝ ተዘግቧል።

ጆናታን ዴቪድ ባለፈው አመት ለሊል ባደረጋቸው 49 ጨዋታዎች 25 ጎሎችን አስቆጥሮ 12 ለግብ የሆነ ኳስ አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
የእረፍት ሰዓት !

በክለቦች አለም ዋንጫ ሩብ ፍፃሜ ፍሉሚኔንስ ከአል ሂላል ጋር እያደረጉ የሚገኙትን ጨዋታ 1ለ0 እየመሩ ወደ መልበሻ ቤት አምርተዋል።

- የፍሉሚኔንስን የመሪነት ግብ ማርቲኔሊ አስቆጥሯል።

🟨 የቢጫ ካርድ የተመለከቱ ተጫዋቾች እነማን ናቸው ?

- በመጀመሪያው አጋማሽ በአል ሂላል በኩል ረናን ሎዲ እና ሚሊንኮቪች ሳቪች በፍሉሚኔንስ በኩል ፍሬይቴስ እና ማርቲኔሊ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክተዋል።

- አል ሂላል ግማሽ ፍፃሜውን የሚቀላቀል ከሆነ ቢጫ ያየው ተከላካዩ ሬናን ሎዲ በቅጣት ጨዋታው የሚያመልጠው ይሆናል።

- ፍሉሚኔንስ ግማሽ ፍፃሜውን የሚቀላቀል ከሆነ ቢጫ ያየው ተከላካዩ ሁዋን ፍሬይቴስ በቅጣት ጨዋታው ያመልጠዋል።

የጨዋታው የኳስ ቁጥጥር ምን ይመስላል ?

- በመጀመሪያው አጋማሽ አል ሂላል 52% - 48% የኳስ ቁጥጥር ብልጫ ነበራቸው።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ጆታ የእውነትም ጥሩ ሰው ነበር “ ሞሪንሆ

ፖርቹጋላዊው አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ በዲያጎ ጆታ ድንገተኛ ሞት የተሰማቸውን ሀዘን በሰጡት አስተያየት ገልጸዋል።

“  ሰው ሲሞት ጥሩ ሰው ነበር ማለት የተለመደ ነው “ ያሉት ሞሪንሆ “  ነገርግን ዲያጎ ጆታ የእውነትም ጥሩ ሰው ነበር “ ሲሉ ተናግረዋል።

“ ጆታ የዚህ ዘመን ትውልድ ተከታይ አይመስልም ነበር ፤ ምንም እንኳን እሱ ለሊቨርፑል እና ፖርቹጋል እየተጫወተ እያሸነፈ ቢሆንም ትኩረት ማግኘት አይፈልግም ነበር “ ሲሉ ሞሪንሆ ተናግረዋል።

አክለውም " አሁን ያለ አባት ማደግ ያለባቸው ሶስት ልጆች እና ሁልጊዜ ፍቅሩ የነበረች ሴት እና ሁለት ልጆች ያጡ ቤተሰቦች አሉ “ ብለዋል።

“ ምናልባት አንድ ቀን ህልፈቱን ተረድተን እንቀበለው ይሆናል አሁን ግን ለመቀበል ከባድ ነው " ጆዜ ሞሪንሆ

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
ፍሉሚኔንስ ግማሽ ፍፃሜውን ተቀላቀለ !

በክለቦች አለም ዋንጫ ሩብ ፍፃሜ ፍሉሚኔንስ ከአል ሂላል ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የፍሉሚኔንስን የማሸነፊያ ግቦች ማርቲኔሊ እና ሄርኩለስ ሲያስቆጥሩ ለአል ሂላል ሊዮናርዶ ከመረብ አሳርፏል።

የብራዚሉ ክለብ ፍሉሚኔንስ ማሸነፉን ተከትሎ ግማሽ ፍፃሜውን የተቀላቀለ የመጀመሪያው ክለብ ሆኗል።

የፍሉሚኔንሱ ተከላካይ ሁዋን ፍሬይቴስ የማስጠንቀቂያ ካርድ መመልከቱን ተከትሎ በቅጣት የግማሽ ፍፃሜው ጨዋታ ያመልጠዋል።

በግማሽ ፍፃሜው ፍሉሚኔንስ የቼልሲ እና ፓልሜራስን አሸናፊ የሚገጥሙ ይሆናል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
2025/07/05 00:46:43
Back to Top
HTML Embed Code: