Telegram Web Link
በቀጣይ አመታት የሻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ የት ይደረጋል ?

የአውሮፓ እግርኳስ ማህበር የሚያዘጋጃቸው የክለብ ውድድሮች በሚቀጥሉት አመታት የፍፃሜ ጨዋታቸው የሚደረግበትን ቦታ እና ስታዲየም ይፋ አድርጓል።

በዚህም መሰረት :-

- የ2026 ሻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ :- ቡዳፔሽት - ፑሽካሽ አሬና ስታዲየም

- የ2027 ሻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ :- ጣልያን - ሳን ሲሮ ስታዲየም

- የ2026 ዩሮፓ ሊግ ፍፃሜ :- ኢስታንቡል - ቤሺክታሽ ፓርክ

- የ2027 ዩሮፓ ሊግ ፍፃሜ :- ጀርመን ፍራክፈርት - ዶቸ ባንክ ፓርክ እንደሚደረጉ ተገልጿል።

የዘንድሮው የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ በዌምብሌይ ስታዲየም እንዲሁም የቀጣዩ የ2025 ፍፃሜ ጀርመን አሊያንዝ አሬና ስታዲየም እንደሚደረጉ ይታወቃል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ዋንጫ የማሸነፊያ ጥሩ እድል አግኝተናል " ማጓየር

እንግሊዛዊው የማንችስተር ዩናይትድ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ሀሪ ማጓየር አስቸጋሪ የውድድር አመት ያሳለፈው ቡድናቸው ዋንጫ የማሸነፊያ ጥሩ እድል እንዳለው ገልጿል።

" ለማንችስተር ዩናይትድ መጫወት ሁልጊዜ ዋንጫ ማሸነፍን ይጠይቃል " የሚለው ሀሪ ማጓየር ባለፈው አመት አድርገነዋል አሁንም አስቸጋሪ አመት ካሳለፍን በኋላ ዋንጫ የምናሸንፍበት ጥሩ አጋጣሚ አግኝተናል ብሏል።

ሀሪ ማጓየር ቀጥሎም በተደጋጋሚ የጡንቻ ጉዳት ሲያጋጥመው የዚህ አመቱ የመጀመሪያ መሆኑን የገለፀ ሲሆን ለኤፌ ካፑ ፍፃሜ ለመድረስ ተስፋ እንደሚያደርግ ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ኤፌ ካፑን ለማሸነፍ ሁሉንም እንሰጣለን " ጋርዲዮላ

የማንችስተር ሲቲው ዋና አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ቡድናቸው ቅዳሜ የኤፌ ካፕ ዋንጫውን በድጋሜ ለማሸነፍ ያለውን ሁሉ እንደሚሰጥ ገልጸዋል።

" የኤፌ ካፕ ዋንጫውን በድጋሜ በማሸነፍ የማንችስተር ሲቲ ደጋፊዎችን ለማኩራት ያለንን አቅም ሁሉ በጨዋታው እንደምንጠቀም ቃል እገባላችኋለሁ።"ሲሉ አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ተናግረዋል።

" በዚህ አመትም በኤፌ ካፕ ፍፃሜ ላይ በመሆናችን ትልቅ ክብር ነው ይህንን ውብ ዋንጫ የማሸነፍ እድል አግኝተናል ምን ያህል ወሳኝ እንደሆነ እናውቃለን ተጨዋቾቹ ዝግጁ ናቸው ጓጉተናል።" ጋርዲዮላ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የአሰልጣኝ ስቴፋኖ ፒዮሊ የኤሲ ሚላን ቆይታ ?

የጣልያን ሴርያው ክለብ ኤሲ ሚላን በውድድር አመቱ መጨረሻ አሰልጣኝ ስቴፋኖ ፒዮሊን ከሀላፊነታቸው ለማሰናበት በወሰነው ውሳኔ መፅናቱ ተገልጿል።

አሰልጣኝ ስቴፋኖ ፒዮሊ በቅርቡ ስለወደፊት ቆይታቸው ተጠይቀው " በውድድር አመቱ መጨረሻ ከክለቡ ጋር እነጋገራለሁ አሁን አስተያየት መስጠት አልፈልግም።" ብለው ነበር።

ኤሲ ሚላን አሁን ላይ አሰልጣኙን የማሰናበት ውሳኔውን እንደማይቀይር ሲገለፅ አዲስ ተተኪ አሰልጣኝ ለመሾም በማፈላለግ ላይ መሆናቸው ተነግሯል።

አሰልጣኝ ስቴፋኖ ፒዮሊ የፊታችን ቅዳሜ ኤሲ ሚላን በስታዲዮ ጁሴፔ ሜዛ ከሳለርኒታና ጋር በሚያደርገው የሊግ የመጨረሻ ሳምንት መርሐ ግብር ክለቡን ይሰናበታሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ኤሲ ሚላን በቀጣይ የአሰልጣኝ ስቴፋኖ ፒዮሊ ተተኪ ለማድረግ ፖርቹጋላዊውን የሊል አሰልጣኝ ፓውሎ ፎንሴካን ማነጋገራቸው ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የኤሪክ ቴንሀግ የዩናይትድ ቆይታ ?

የማንችስተር ዩናይትዱ ዋና አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ክለቡ በአመቱ ውስጥ ባሳየው ደካማ እንቅስቃሴ ምክንያት በቀጣይ አመት በክለቡ የሚኖራቸው ቆይታ አጠራጣሪ ሆኗል።

አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ በማንችስተር ዩናይትድ ቤት የሚኖራቸው የወደፊት ቆይታ አስተማማኝ እንዳልሆነ የተገለፀ ሲሆን ሁኔታው 50/50 መሆኑ ተዘግቧል።

አሰልጣኙ የመሰናበት አደጋ ውስጥ መውደቃቸው እርግጥ ቢሆንም በክለቡ በኩል እስካሁን በግልጽ የተነገረ ውሳኔ #እንደሌለ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ታማኝ የመረጃ ምንጮች ገልጸዋል።

ማንችስተር ዩናይትድ ቅዳሜ በኤፌ ካፑ የሚያስመዘግበው ውጤት ክለቡ በአሰልጣኙ ዙሪያ የሚያሳልፈው ውሳኔ ላይ ለውጥ እንደማያመጣ ተጠቁሟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የጨዋታ አሰላለፍ !

4:00 አታላንታ ከ ባየር ሊቨርኩሰን ( ዩሮፓ ሊግ ፍፃሜ )

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ዋልያዎቹ ስብስባቸውን አሳውቀዋል !

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በቀጣይ ላሉበት ሁለት የአለም ዋንጫ ማጣርያ የምድብ ጨዋታዎች የሚጠቀመውን የቡድን ስብስብ አሳውቋል።

በአሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ የሚመራው ብሔራዊ ቡድኑ ለሀያ ስድስት ተጫዋቾች የመጀመርያ ጥሪ ማድረጉን የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ይፋ አድርጓል።

ብሔራዊ ቡድኑ ግንቦት 29/2016 ዓ.ም ከጊኒ ቢሳው እንዲሁም ሰኔ 2/2016 ዓ.ም ከጅቡቲ ጋር ከሜዳው ውጪ ጨዋታውን ያደርጋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ታሪክ መፃፍ እንፈልጋለን " ዣቢ

ከደቂቃዎች በኋላ የዩሮፓ ሊግ ፍፃሜ ጨዋታቸውን ከአታላንታ ጋር የሚያደርጉት ባየር ሌቨርኩሰን አሰልጣኝ ዣቢ አሎንሶ ቡድናቸው ታሪክ መፃፍ እንደሚፈልግ ተናግረዋል።

ከጨዋታው በፊት አስተያየታቸውን የሰጡት አሰልጣኝ ዣቢ አሎንሶ " አታላንታ ጨዋታውን ከባድ እንደሚያደርጉብን እናውቃለን ነገርግን ለእሱ ጓጉተናል ፣ ታሪክ መፃፍ እንፈልጋለን።"ሲሉ ተደምጠዋል።

ግራኒት ዣካ በበኩሉ " ማመናችንን መቀጠል አለብን አሰልጣኛችን ሁልጊዜም ያለንን ሁሉ እንድንሰጥ ይፈልጋል ።"በማለት ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
12 ' አታላንታ 1 - 0 ባየር ሊቨርኩሰን ( ዩሮፓ ሊግ ፍፃሜ )

ሉክማን

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
25 ' አታላንታ 2 - 0 ባየር ሊቨርኩሰን ( ዩሮፓ ሊግ ፍፃሜ )

ሉክማን

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#እረፍት

አታላንታ ከባየር ሌቨርኩሰን ጋር እያደረጉ የሚገኙትን የዩሮፓ ሊግ ፍፃሜ ጨዋታ 2ለ0 በሆነ ውጤት እየመሩ ወደ መልበሻ ቤት አምርተዋል።

የአታላንታን የመሪነት ግቦች ሉክማን 2x ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

የጨዋታው የኳስ ቁጥጥር ምን ይመስላል ?

በመጀመሪያው አጋማሽ ባየር ሌቨርኩሰን 66% - 34% የኳስ ቁጥጥር ብልጫ ነበራቸው።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አዴሞላ ሉክማን አዲስ ታሪክ ፅፏል !

ናይጄሪያዊው የአታላንታ የፊት መስመር ተጨዋች አዴሞላ ሉክማን በአውሮፓ መድረክ ውድድሮች ፍፃሜ ጨዋታ ላይ ሁለት ግቦችን ማስቆጠር የቻለ የመጀመሪያው አፍሪካዊ ተጨዋች መሆን ችሏል።

አታላንታ የመጀመሪያ የአውሮፓ መድረክ ፍፃሜ ጨዋታ ግቡን በሉክማን አማካኝነት ዛሬ ምሽት አስቆጥሯል።

ሉክማን በዘንድሮው የውድድር አመት ለአታላንታ በሁሉም ውድድሮች አስራ አራተኛ ግቡን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
76 ' አታላንታ 3 - 0 ባየር ሊቨርኩሰን ( ዩሮፓ ሊግ ፍፃሜ )

         ሉክማን

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አታላንታ የዩሮፓ ሊግ ሻምፒዮን ሆነ !

የጣልያኑ ክለብ አታላንታ ከጀርመኑ ክለብ ባየር ሊቨርኩሰን ጋር ያደረገውን የዩሮፓ ሊግ ፍፃሜ ጨዋታ 3ለ0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ሻምፒዮን መሆን ችለዋል።

የአታላንታን የማሸነፊያ ግቦች ናይጄሪያዊው ተጨዋች አዴሞላ ሉክማን 3x ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

የጣልያኑ ክለብ አታላንታ በታሪኩ የመጀመሪያ የዩሮፓ ሊግ ዋንጫውን በማሳካት አዲስ ታሪክ አስመዝግበዋል።

ናይጄሪያዊው የአታላንታ የፊት መስመር ተጨዋች አዴሞላ ሉክማን በዩሮፓ ሊግ ፍፃሜ ሀትሪክ መስራት የቻለ የመጀመሪያው ተጨዋች በመሆን አዲስ ታሪክ ፅፏል።

የጀርመኑ ክለብ ባየር ሊቨርኩሰን በዘንድሮው የውድድር አመት በሁሉም ውድድሮች የመጀመሪያ ሽንፈታቸውን አስተናግደዋል።

ባየር ሊቨርኩሰን ከሀምሳ አንድ ጨዋታዎች ያለመሸነፍ ጉዞ በኋላ የመጀመሪያ ሽንፈታቸውን አስተናግደዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ያሸነፍንበት መንገድ የማይታመን ነው " ጋስፔሪኒ

አትላንታን እየመሩ በአሰልጣኝነት ህይወታቸው የመጀመሪያ ዋንጫቸውን ያሳኩት አሰልጣኝ ጂያን ፔሮ ጋስፔሪኒ ድሉን " የማይታመን እና የማይረሳ " ሲሉ ገልፀውታል።

" የዩሮፓ ሊግ ዋንጫን ማሸነፍ ትልቅ ስኬት ነው " ያሉት አሰልጣኙ ባየር ሊቨርኩሰንን ያሸነፍንበት መንገድ የማይታመን እና የማይረስ ነው ፣ እኛ ብቻ ሳንሆን ደጋፊዎችም ታሪክ ሰርተዋል በማለት ተናግረዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from HEY Online Market
Affordable Gaming PC

•HP Pavilion
•HP Victus

•HP Omen 15
•HP Omen 16

Contact Us
0953964175 @heymobile

@heyonlinemarket
ሽመልስ በቀለ 1⃣8⃣ ገስት ሀውስ

በውቢቷ ሀዋሳ ቆይታዎ የት ለማረፍ አስበዋል ? ንፁህ እና በደንበኞቻችን ተወዳጅ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን መጥተው የእረፍት ጊዜውን ያሳልፉ።

እንግዶቻችንን ተቀበልን ለእይታ ሳቢ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን ማስተናገድ ከጀመርን አመታትን አስቆጥረናል።

አድራሻችን :- ሀዋሳ አርቴፍሻል ስታዲየም መንገድ ላይ ያገኙናል።

ለተጨማሪ መረጃ እና ለትዕዛዝዎ ይደውሉልን :- 0928684848

#ShemelesBekele18
" ይህንን ሽንፈት መቼም አልረሳውም " ዣቢ

ትላንት ምሽት በአታላንታ ተሸንፈው የዩሮፓ ሊግ ዋንጫን ያጡት ባየር ሌቨርኩሰን ዋና አሰልጣኝ ዣቢ አሎንሶ የምሽቱ ሽንፈት ሊረሱት የማይችሉት መሆኑን ገልጸዋል።

" ይህንን ሽንፈት መቼም አልረሳውም " ያሉት አሰልጣኝ ዣቢ አሎንሶ " ጥሩ ነበርን ነገርግን የአታላንታ ጥንካሬ ትልቅ ነበር ቡድኑ ያለውን ሁሉ ሰጥቶ ተጫውቷል ለተጨዋቾቹ ያለኝን ፍቅር አይለውጠውም " ብለዋል።

ባየር ሌቨርኩሰን ከሀምሳ አንድ ጨዋታዎች በኋላ የመጀመሪያ ሽንፈቱ ሲሆን በአመቱ ውስጥ የሶስትዮሽ ዋንጫ የማሳካት ህልሙንም ሳያሳካ ቀርቷል።

ያለፉትን አምስት የፍፃሜ ጨዋታዎች ማሸነፍ ያልቻለው የዣቢ አሎንሶው ቡድን ባየር ሌቨርኩሰን የአመቱ ሁለተኛ ዋንጫውን ለማሳካት የጀርመን ፖካል ፍፃሜ ጨዋታውን ከካይሴርስላውቴርን ጋር የፊታችን ቅዳሜ ያደርጋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/05/23 06:09:38
Back to Top
HTML Embed Code: