TIKVAH-SPORT
ፔድሮ ኔቶ ልምምድ አልሰራም ! በክለቦች አለም ዋንጫ ውድድር እየተሳተፈ የሚገኘው ቼልሲ የዛሬ ልምምዱን ለዲያጎ ጆታ የህሊና ፀሎት በማድረግ ጀምሯል። በቡድኑ ልምምድ ላይ ፖርቹጋላዊው የቡድኑ የፊት መስመር ተጨዋች ፔድሮ ኔቶ አለመሳተፉ ተገልጿል። ተጨዋቹ የቅርብ ጓደኛው ዲያጎ ጆታን ህይወት ማለፍ ተከትሎ በልምምድ እንዳልተሳተፈ ተዘግቧል። ፔድሮ ኔቶ በስነልቦና ዝግጁ ላይሆን ስለሚችል በነገው…
ፔድሮ ኔቶ በጣም አዝኗል “

የለንደኑ ክለብ ቼልሲ ዋና አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ የቡድናቸው ተጫዋች ፔድሮ ኔቶ በቅርብ ጓደኛው ዶያጎ ጆታ ድንገተኛ ህልፈት ማዘኑን ገልፀዋል።

በዛሬው ጨዋታ ስለ መጫወቱ ሲጠየቁ “ ሙሉ ለሙሉ ውሳኔው የፔድሮ ኔቶ ነው “ በማለት ለተጫዋቹ ቅድሚያ እንደሚሰጡ ገልፀዋል።

ትላንት ረፋድ ላይ ከፔድሮ ኔቶ ጋር ማውራታቸውን የገለፁት ማሬስካ “ ምንም አይነት ውሳኔ ቢወስን ልክ ነው ፣ እኛ ከጎኑ ነን “ የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

“ በጣም አዝኗል “ በማለት አሁን ላይ የሚገኝበትን ሁኔታ የገለፁት ማሬስካ “ ከማዘንም በላይ ተጎድቷል ፣ ነገር ግን በዚህ አሳዛኝ ወቅት ከጎኑ ነን “ ብለዋል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
አሮን ራምሴይ ወደ ሜክሲኮ ሊያመራ ነው ! የቀድሞ የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል እና ጁቬንቱስ አማካይ አሮን ራምሴ የሜክሲኮውን ክለብ ፑማስ ለመቀላቀል ከስምምነት መድረሱ ተገልጿል። ክለቡን ለመቀላቀል የህክምና ምርመራውን ያደረገው አሮን ራምሴይ ቀጣዩን የውድድር አመት በቡድኑ የሚያቆየውን ውል ለመፈረም ወደ ሜክሲኮ ለማምራት መዘጋጀቱ ተነግሯል። ተጨዋቹ ከሳውዲ አረቢያ እና ዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ…
አሮን ራምሴይ የሜክሲኮውን ክለብ ተቀላቀለ !

የቀድሞ የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል እና ጁቬንቱስ አማካይ አሮን ራምሴ የሜክሲኮውን ክለብ ፑማስ በነፃ ዝውውር ተቀላቅሏል።

ክለቡን በአንድ አመት ውል የተቀላቀለው አሮን ራምሴይ “ እዚህ በመሆኔ ደስተኛ ነኝ ብዙ ልምድ አለኝ ቡድኑን ስኬታማ ለማድረግ ማገዝ እፈልጋለሁ " ብሏል።

ተጨዋቹ ከሳውዲ አረቢያ እና ዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ የቀረበለትን ጥያቄ ውድቅ በማድረግ ፑማስን ለመቀላቀል መወሰኑ ተነግሯል።

የ 34ዓመቱ አሮን ራምሴይ በውድድር አመቱ መጨረሻ በሶስት ጨዋታዎች ካርዲፍ ሲቲን በጊዜያዊነት አሰልጣኝነት መርቶ ነበር።

በክለቡ ያለው ውል በአመቱ መጨረሻ ያበቃው አሮን ራምሴይ ባለፈው አመት ለካርዲፍ ሲቲ አስር ጨዋታዎችን ማድረግ ችሏል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
“ አሜሪካዊያን የነፃነት በዓላችሁን እኛን በመደገፍ አክብሩ “

የብራዚሉ ክለብ ፓልሜራስ አሰልጣኝ አቤል ፌሬራ አሜሪካዊያን ገለልተኛ ደጋፊዎች እኛን በመቀላቀል ከእንግሊዝ በተቃራኒ ቁሙ ሲሉ ጠይቀዋል።

አሜሪካ ዛሬ " June 4 " ከታላቋ ብሪቴን ነፃ መውጣቷን የሚዘክር ብሔራዊ በዓል ታከብራለች።

የፓልሜራስ እና ቼልሲ ጨዋታ በተመሳሳይ ቀን መደረጉን ተከትሎ አሰልጣኙ አሜሪካውያን የሀገር ፍቅራችሁን አሳዩ በማለት አስታውሰዋል።

“ እኛን መደገፍ ለአሜሪካውያን መልካም አጋጣሚ ነው “ ያሉት አሰልጣኝ አቤል ፌሬራ “ ምክንያቱም ቀኑ ከእንግሊዝ በተቃራኒ የምትቆሙበት የነፃነት ቀን ነው “ ብለዋል።

“ ስለዚህ ከእኛ ጋር በመምጣት ተቀላቀሉን ምክንያቱም የእናንተ ድጋፍ ያስፈልገናል “ሲሉ  አሰልጣኝ አቤል ፌሬራ ጥሪ አቅርበዋል።

“ በጨዋታው ያለንን እንሰጣለን ቼልሲ ጠንካራ መሆኑን እናውቃለን ነገርግን እኛ አንድ ህልም ነው ያለን ለዚህ ህልም እንፋለማለን “ አሰልጣኝ አቤል ፌሬራ

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኒኮ ዊሊያምስ በይፋ ውሉን አራዘመ!

ስፔናዊው የአትሌቲክ ቢልባኦ የፊት መስመር ተጫዋች ኒኮ ዊልያምስ ውሉን ለተጨማሪ ስምንት አመታት ማራዘሙን ክለቡ ይፋ አድርጓል።

ተጫዋቹ በአትሌቲክ ቢልባኦ ቤት እስከ 2035 ድረስ የሚያቆየውን የረዥም አመት ውል መፈረሙ ይፋ ተደርጓል።

ምንም እንኳ ባርሴሎና በተጫዋቹ ላይ ከፍተኛ ፍላጎት ቢኖረውም ተጫዋቹ ግን በአትሌቲክ ቢልባኦ ለመቆየት መወሰኑ ተገልጿል።

ኒኮ ዊሊያምስ አዲስ በፈረመው ኮንትራት ላይ የውል ማፍረሻው 96 ሚልየን ዩሮ መሆኑ ተነግሯል።

ተጫዋቹም በይፋ ፊርማውን ካኖረ በኋላ " አትሌቲክ ቢልባኦ ቤቴ ነው “ ሲል ተደምጧል።

“ ውሳኔ ለመወሰን ስትፈልግ መጀመሪያ ማድረግ ያለብህ ልብህን ማድመጥ ነው ፣ እኔ መቆየት የምፈልገው በዚሁ ነው “ ኒኮ ዊሊያም

@tikvahethsport @kidusyoftahe
አርሰናል ከተጨዋቹ ጋር ሊለያይ ነው !

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል የመስመር ተጨዋች ታኬሂሮ ቶሚያሱ ከክለቡ ሊለያይ መሆኑ ተገልጿል።

አርሰናል ከተጨዋቹ ጋር በጋራ ስምምነት ያላቸውን ኮንትራት ለማፍረስ መወሰናቸው ተነግሯል።

በተደጋጋሚ ጉዳት ምክንያት ቡድኑን በሚገባው ልክ ያላገለገለው ቶሚያሱ በተጠናቀቀው የውድድር አመት ለአርሰናል አንድ ጨዋታ ነው ያደረገው።

የተጨዋቹ ኮንትራት በሚቀጥለው አመት 2026 የሚጠናቀቅ ቢሆንም በስምምነት መለያየታቸው ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት በቀን 24/10/2017 ዓ/ም ባካሄዱት ስብሰባ ላይ የተወሰኑ አበይት ጉዳዮች @tikvahethsport @kidusyoftahe
#Ethiopia

የኢትዮጵያ ፕ/ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንባስተላለፈው ውሳኔ መሰረት በሲዳማ ፣ በመቻል እና በሀዋሳ ከተማ ስፖርት ቡድኖች ላይ አስተላልፏል።

ክለቦቹ የታገዱ ተጫዋቾቹን በመጠቀም ያደረጓቸውን ጨዋታዎችን በፎርፌ እንዲሸነፉ የውድድርና ስነ ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።

በተሰጡት የፎርፌ ውሳኔዎች መሰረት  የ2017 የፕሪሚየር ሊግ ደረጃና ግብ አግቢዎች ተስተካክሏል።

ይህንንም ተከትሎ ቅጣቱ የተላለፈባቸው ክለቦች :-

1️⃣5️⃣ኛ - መቻል
1️⃣7️⃣ኛ - ሲዳማ ቡና በመሆን የዘንድሮው ውድድር ዓመት አጠናቀዋል።

በተቃራኒው በወራጅ ቀጠናው ይገኙ የነበሩት :-

1️⃣3️⃣ኛ አዳማ ከተማ
1️⃣4️⃣ኛ መቐለ 70 እንደርታ ደረጃ ላይ ለመቀመጥ ችለዋል።

❗️የአክስዮን ማህበሩ ሙሉ የውድድር ዘመኑ መግለጫ ከላይ በምስሉ ላይ ተያይዟል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
አርሰናል ከተጨዋቹ ጋር ሊለያይ ነው ! የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል የመስመር ተጨዋች ታኬሂሮ ቶሚያሱ ከክለቡ ሊለያይ መሆኑ ተገልጿል። አርሰናል ከተጨዋቹ ጋር በጋራ ስምምነት ያላቸውን ኮንትራት ለማፍረስ መወሰናቸው ተነግሯል። በተደጋጋሚ ጉዳት ምክንያት ቡድኑን በሚገባው ልክ ያላገለገለው ቶሚያሱ በተጠናቀቀው የውድድር አመት ለአርሰናል አንድ ጨዋታ ነው ያደረገው። የተጨዋቹ ኮንትራት በሚቀጥለው…
“ የአርሰናል በመሆኔ ሁልጊዜም እኮራለሁ “ ቶሚያሱ

ጃፓናዊው የመስመር ተጨዋች ታኬሂሮ ቶሚያሱ ከአርሰናል ጋር መለያየቱን በማህበራዊ ትስስር ገፁ አረጋግጧል።

“ በዚህ ታላቅ ክለብ ከነበሩን አራት የማይረሱ አመታት በኋላ የመሰነባበቻ ጊዜው አሁን ነው ስለሰጣችሁኝ ህይወት አመሰግናለሁ “ ሲል ቶሚያሱ ተናግሯል።

“ በአርሰናል ቤት ከቡድን አጋሮቼ ፣ ከሚኬል አርቴታ ከአሰልጣኝ ቡድኑ እና ሁሉም ሰው ጋር በማሳለፌ በጣም ደስተኛ ነበርኩ “ ቶሚያሱ

ቶሚያሱ አክሎም ደጋፊዎች ሜዳ ላይ እና ከሜዳ ውጪ ላሳያችሁኝ ነገር አመሰግናለሁ በቼም አልረሳውም በማለት ተናግሯል።

“ ጊዜው የአዲስ ምዕራፍ ነው ነገርግን የአርሰናል ሰው በመሆኔ ሁልጊዜም እኮራለሁ " ቶሚያሱ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ወደ ሊቨርፑል መመለስ አስፈርቶኛል “ ሳላህ

ግብፃዊው የሊቨርፑል ኮከብ ሞሀመድ ሳላህ በቡድን አጋሩ ዲያጎ ጆታ ድንገተኛ ህልፈት የተሰማውን ሀዘን ገልጿል።

ወደ መርሲሳይድ መመለስ እንዳስፈራው የገለፀው ሳላህ “ ከ እረፍት ስመለስ ዲያጎ ጆታን እንደማላገኘው ራሴን ማሳመን እና መቀበል ከብዶኛል “ ብሏል።

“ የቡድን አጋሮች ይመጣሉ ይሄዳሉ በዚህ መንገድ ግን አይደለም ፣ እስከ ትላንት ድረስ የትኛውም ነገር ወደ ሊቨርፑል ለመመለስ ያስፈረኛል ብዬ አላስብም ነበር “ ሞሀመድ ሳላህ

ሳላህ ለዲያጎ ጆታ ቤተሰቦች እና አድናቂዎቹ በሀዘን መግለጫው መፅናናትን ተመኝቷል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ሩበን አሞሪም ወደ ካሪንግተን ተመልሰዋል !

የማንችስተር ዩናይትዱ ዋና አሰልጣኝ ሩበን አምሪም ዛሬ ጠዋት ወደ ካሪንግተን ልምምድ ማዕከል መመለሳቸው ተገልጿል።

አሰልጣኙ ለቅድመ ውድድር ዝግጅት ከአሰልጣኝ ቡድን አባላቶቻቸው ጋር ካሪንግተን ልምምድ ማዕከል ተገኝተዋል።

የክለቡ ተጨዋቾች ከቀናት በኋላ ሰኞ ወደ ካሪንግተን በመመለስ የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን ይጀምራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሊቨርፑል የዝግጅት መጀመሪያ ቀኑን ሊያራዝም ነው !

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል በዲያጎ ጆታ ህልፈት ምክንያት የቅድመ ውድድር ዝግጅት መጀመሪያ ቀናቸውን ሊያራዝሙ እንደሚችሉ ተገልጿል።

ሊቨርፑል የቅድመ ውድድር ዝግጅቱን መቼ ለመጀመር እንዳሰበ በግልጽ እንዳልታወቀ ተነግሯል።

በተጨማሪም ሊቨርፑል ከዘጠኝ ቀናት በኋላ ከ ፕሪስተን ጋር የሚያደርገው የመጀመሪያ የወዳጅነት ጨዋታ መደረግ አለመደረጉ አልተወሰነም።

ሊቨርፑል የክለቡ አገልግሎት መስጫ ተቋማት እስከ ሰኞ ዝግ ሆነው እንዲቆዩ መወሰኑን ማስታወቁ አይዘነጋም።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Wanawsportswear✔️

ዋናው ፕሪምየም ማሊያ በቁምጣ | ገደቡ ለማይበግራቸው ለታላላቅ ቡድኖች ትክክለኛው ምርጫ
⚡️ጥንቅቅ ያለ
🫶 የአንድነት ስሜትን የሚሰጥ
👏 የምርት ጥራቱን ኢትዮጵያን ጨምሮ የላይቤሪያ ብሄራዊ ቡድን የመሰከረለት

ዋናው ፕሪምየም (No Socks Edition) በያዛቸው
🤔ዘመናዊ የቦዲ ማፒንግ ቴክኖሎጂ
🤔ፈጣን ሞቃት አየርን ከሰውነት ወደ ውስጥ እና ወደ ውጭ መውጣት የሚያስችል
🤔2024/25 ኤክስፖርት ስታንዳርድ ተጨማሪ አቅምን ያጎናጽፍዎታል

💰በ1700ብር | ማሊያ እና ቁምጣ
🔥 ብዛት 50 በላይ ለምታዙ ከዋናው ስፖርት 1ኛ ደረጃ ኳስ(professional Football) ስጦታ ይኖራችኋል!

📞ለማዘዝ
8️⃣2️⃣8️⃣9️⃣
➡️+251901138283
➡️+251910851535
➡️+251913586742

🔗 ማህበራዊ ገጾቻችን🔗
Instagram|Facebook |TikTok |X|Youtube
🔥🔥🔥🔥በኢትዩጵያ የተመረተ🔥🔥🔥🔥
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የየእለቱን ዜናዎችን በSMS እናግኝ! 🗞📲

ከሳፋሪኮም ቁጥራችን 'A’ ብለን ወደ 30000 SMS አሁኑኑ በመላክ ወይም ወደ *799# በመደወል የቲክቫህ ትኩስ መረጃዎችን እናግኝ! በቀን 1ብር ብቻ! ከሳፋሪኮም ጋር አንድ ወደፊት ⚡️

#SafaricomEthiopia
#1Wedefit
#Furtheraheadtogether
“ አጨዋወቴ እንደ ሜሲ ነው “ እስቴቫኦ

የወደፊቱ የቼልሲ የፊት መስመር ተጨዋች እስቴቫኦ የአጨዋወት ዘይቤው ከሊዮኔል ሜሲ ጋር እንደሚመሳሰል ተናግሯል።

ዛሬ ምሽት ከፓልሜራስ ጋር ቼልሲን የሚገጥመው ተጨዋቹ " አጨዋወቴ ከሊዮኔል ሜሲ ጋር ተመሳሳይ ሆኖ ነው የምመለከተው “ ብሏል።

ስለወደፊት ህልሙ ያነሳው ተጨዋቹ “ ከአለም ዋንጫ ቀጥሎ ሁለተኛ ህልሜ ባሎን ዶር ማሸነፍ ነው በማለት ተናግሯል።

ሰማያዊዎቹ 34 ሚልዮን ዩሮ በማውጣት ያስፈረሙት እስቴቫኦ ከክለቦች አለም ዋንጫ በኋላ ቡድኑን ይቀላቀላል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቶማስ ፓርቴ ክስ እንደተመሰረተበት ተገለጸ !

ጋናዊው የቀድሞ የአርሰናል የመሐል ሜዳ ተጨዋች ቶማስ ፓርቴ በአስገድዶ መድፈር እና ፆታዊ ጥቃት ክስ እንደተመሰረተበት ተገልጿል።

ተጨዋቹ አምስት የአስገድዶ መድፈር እና አንድ የፆታዊ ጥቃት ወንጀል በመፈጸም ክስ እንደተመሰረተበት ተነግሯል።

ፓርቴ የቀረበበት ክስ ሶስት የተለያዩ ሴቶች ሪፖርት ያደረጉት በ 2021 እና 2022 መካከል የተፈጠረ ክስተት መሆኑ ተገልጿል።

ተጨዋቹ ከ 2022 ጀምሮ ምርመራ ላይ እንደነበር ሲገለፅ ውሉ እስከሚጠናቀቅ ለአርሰናል መጫወቱን እንደቀጠለ ተዘግቧል።

በቅርቡ ከአርሰናል ጋር የተለያየው ቶማስ ፓርቴ በቀጣይ ነሐሴ ወር ውስጥ ፍርድ ቤት እንደሚቀርብ ተገልጿል።

ተጨዋቹ ጥፋተኛ ሆኖ ከተገኘ እስከ 25 አመት እስራት ሊጠብቀው እንደሚችል ተነግሯል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
ዩናይትድ የ 1️⃣0️⃣ ቁጥር ማልያን ለኩንሀ ሰጠ !

አዲሱ የማንችስተር ዩናይትድ ፈራሚ ማቲውስ ኩንሀ በቀጣይ በማንችስተር ዩናይትድ የ 1️⃣0️⃣ ቀጥር ማልያ ተሰጥቶታል።

1️⃣0️⃣ ቁጥር ማልያ ከዚህ በፊት በማርከስ ራሽፍርድ ይለበስ እንደነበር ይታወሳል።

ማርከስ ራሽፎርድ ማንችስተር ዩናይትድን መልቀቅ እንደሚፈልግ ለክለቡ ማሳወቁ ተነግሯል።

በተጨማሪም አንቶኒ ፣ አሌሀንድሮ ጋርናቾ ፣ ጄደን ሳንቾ እና ማላሽያ ክለቡን ለመልቀቅ ጥያቄ ማቅረባቸው ተዘግቧል።

ይህንንም ተከትሎ ተጨዋቾቹ ዘግይተው ወደ ክለቡ እንዲመለሱ ፍቃድ እንደተሰጣቸው ተዘግቧል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ቶማስ ፓርቴ ክስ እንደተመሰረተበት ተገለጸ ! ጋናዊው የቀድሞ የአርሰናል የመሐል ሜዳ ተጨዋች ቶማስ ፓርቴ በአስገድዶ መድፈር እና ፆታዊ ጥቃት ክስ እንደተመሰረተበት ተገልጿል። ተጨዋቹ አምስት የአስገድዶ መድፈር እና አንድ የፆታዊ ጥቃት ወንጀል በመፈጸም ክስ እንደተመሰረተበት ተነግሯል። ፓርቴ የቀረበበት ክስ ሶስት የተለያዩ ሴቶች ሪፖርት ያደረጉት በ 2021 እና 2022 መካከል የተፈጠረ ክስተት…
“ ቶማስ ፓርቴ እንዲከሰስ ፈቅደናል “ ፖሊስ

የእንግሊዝ የህግ አካል የሆነው " CPS " የቶማስ ፓርቴን ጉዳይ ከመረመረ በኋላ ተጨዋቹ ክስ እንዲመሰረትበት መፍቀዱን አስታውቋል።

" CPS " በእንግሊዝ ፖሊስ እና ሌሎች የህግ አካላት የመረመሯቸውን የወንጀል ጉዳዮች ወደ ክስ የሚወስድ ገለልተኛ ተቋም መሆኑ ተገልጿል።

የህግ ተቋሙ ከዚህ በፊት ከሜትሮፖሊታን ፖሊስ የተላከለትን ማስረጃ እየገመገመ መሆኑን ገልፆ ነበር።

አሁን ላይ " CPS " የምርመራ ማስረጃውን በጥንቃቄ ከመረመረ በኋላ ቶማስ ፓርቴ በአስገድዶ መድፈር ክስ እንዲመሰረትበት ፍቃድ መስጠቱን አስታውቋል።

ምርመራውን የመሩት የፖሊስ ሀላፊ በበኩላቸው በሰጡት አስተያየት “ ትኩረታችን ወደፊት መጥተው ጉዳታቸውን የተናገሩ ሴቶችን መርዳት ላይ ነው " ብለዋል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
2025/07/04 15:30:01
Back to Top
HTML Embed Code: