ሰኔ 21 የሴጅ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት የምስረታ ቀን!
በማኅበራዊ ገጾቻችን በሙሉ እየተከታተላችሁን ለዘለቃችሁ ቤተሰቦቻችን በሙሉ ምስጋናችን ከልብ ነው።
የምስረታ በዓላችንን ምክንያት በማድረግ እስከ ሰኔ 21/2017 ዓ.ም ድረስ በሁሉም ስልጠናዎቻችን ላይ አድርገን የነበረው የ25% ቅናሽ ዛሬ ይጠናቀቃል። በየጊዜው እያሳየን የመጣናቸውን ለውጦች አስጠብቀን ለመቀጠል እንጥራለን።
Instagram: https://www.instagram.com/sage_training_institute/
Telegram: https://www.tg-me.com/sagetraininginstitute
TikTok: https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ
ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ
የበለጠ ይጠብቁ ...

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ከ19 ሺህ በላይ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ይወስዳሉ። - የክልሉ ትምህርት ቢሮ
በክልሉ 19,127 ተማሪዎች ሀገር አቀፍ ፈተናውን የሚወስዱ ሲሆን፤ ከነዚህ ውስጥ 2,690 ተማሪዎች ፈተናውን በበየነ መረብ እንደሚወስዱ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አልማው ዘውዴ ተናግረዋል።
የተቀሩት ተፈታኞች በተዘጋጁ የፈተና ማዕከላት ተገኝተው ፈተናውን በወረቀት ይወስዳሉ ብለዋል።
ዘንድሮ ተማሪዎች የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ ዝግጅት መደረጉን የገለፁት ኃላፊው፤ የማጠናከሪያ ትምህርት፣ የስነ-ልቦና ግንባታ እንዲሁም ለበየነ መረብ ተፈታኞች ተከታታይ ልምምድ እንደተሰጠ ገልፀዋል።
በየደረጃው የተዋቀረ የፈተና ግብረኃይል ተፈታኝ ተማሪዎችን ከዛሬ ጀምሮ ወደ ፈተና ጣቢያዎች እንደሚያጓጓዝ ተገልጿል።
@tikvahuniversity

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በመጀመሪያ ዙር የሚወስዱ የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች እሑድ ሰኔ 22/2017 ዓ.ም ጠዋት 2፡30 በኦንላይን ፈተና መስጫ ጣቢያዎች በመገኘት የፈተና ገለጻ (Orientation) መከታተል አለባቸው ተብሏል።
በተጨማሪም ተፈታኞች የሚፈተኑበትን ቦታ እና የመፈተኛ ክፍሎችን ማየት እንደሚገባቸው የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ዲናኦል ጫላ አሳስበዋል፡፡
ፈተናውን በኦንላይን ለመስጠት ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውን የገለፁት ኃላፊው፤ ተፈታኞች ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ በፈተና መስጫ ጣቢያዎች በመገኘት ፈተናቸውን ይወስዳሉ ብለዋል፡፡
(በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ የኦንላይን ፈተና መርሐግብር ከላይ ተያይዟል።)

#KabridaharUniversity
ቀብሪደሃር ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን ከ1,100 በላይ ተማሪዎች አስመረቀ።
የዩኒቨርሲቲው 5ኛ ባች ተመራቂዎች፤ በመጀመሪያ ዲግሪ እና በሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራም ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቀቁ ናቸው፡፡
ዩኒቨርሲቲው በሁለተኛ ዲግሪ (71)፣ በመጀመሪያ ዲግሪ (1,054)፣ በHDP (34) እንዲሁም በELIP (25) በጠቅላላው 1,184 ተማሪዎችን በዛሩው ዕለት አስመርቋል፡፡

#JigjigaUniversity
ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን ከ1,500 በላይ ተማሪዎች አስመርቋል።
የዩኒቨርሲቲው 17ኛ ባች ተመራቂዎች፤ በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራሞች በሕግ፣ በግብርና፣ በጤና፣ በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ እንዲሁም ሌሎች የትምህርት ዘርፎች ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቀቁ ናቸው፡፡
ከዩኒቨርሲቲው የዛሬ ተመራቂዎች መካከል ከጎረቤት ሀገር ሶማሊያ የመጡ 13 ተማሪዎች ይገኙበታል፡፡

#AddisAbabaUniversity
#ClassOf2025
#CommencementPhotos
አንጋፋው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 75ኛ የተማሪዎች የምርቃት ስነ-ስርዓት እና የዩኒቨርሲቲው የአልማዝ ኢዮቤልዩ በዓል ማስጀመሪያ መርሐግብር ዛሬ አከናውኗል፡፡
ዩኒቨርሲቲው ከመጀመሪያ እስከ ሦስተኛ ዲግሪ ፕሮግራሞች ያስተማራቸውን ከ6,800 በላይ ተማሪዎች አስመርቋል፡፡ ከተመራቂዎቹ መካከል 304 ምሩቃን በሦስተኛ ዲግሪ (PhD) ፕሮግራም ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቀቁ ናቸው፡፡
352 በስፔሻሊቲ እና ሰብ-ስፔሻሊቲ ፕሮግራሞች እንዲሁም 2,859 በሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራም የተመረ ሲሆን፤ ቀሪዎቹ 3,334 በመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም የተመረቁ መሆናቸው ተገልጿል፡፡
ዩኒቨርሲቲው ባለፉት 75 ዓመታት በትምህርት ልህቀት፣ በአመራር ልማት እንዲሁም በሀገር ግንባታ ያደረገው ዘላቂ እና ዘርፈ ብዙ አበርክቶ በምርቃት ስነ-ስርዓቱ ላይ ተዘክሯል፡፡
ዩኒቨርሲቲው ከ75 ዓመታት በፊት ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ፤ የፈጠራ፣ ምርምር እና የዕውቀት መፍለቂያ በመሆን በርካታ መሪዎች፣ ባለሙያዎች እና ምሁራንን ማፍራቱ ይታወቃል።
በሀገሪቱ የመጀመሪያው ራስገዝ ዩኒቨርሲቲ የሆነው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፤ ከ2017 ዓ.ም ጀምሮ በራሱ መመዘኛና መስፈርት ተማሪዎችን ተቀብሎ በማስተማር ላይ ይገኛል፡፡

በሶማሌ ክልል ከ16 ሺህ በላይ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ይወስዳሉ። የክልሉ ትምህርት ቢሮ
በሶማሌ ክልል 16,779 ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ሲሆን፤ ከእነዚህ መካከል 2,983 ተማሪዎች በኦንላይን እንደሚፈተኑ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ መሀመድ ሼክ አደን ተናግረዋል።
በክልሉ እና በሌሎች ክልሎች በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች እና ለኦንላይን ፈተና በተዘጋጁ ቦታዎች ፈተናው ይሰጣል ብለዋል።
ተፈታኞች በጅግጅጋ እና ቀብሪደሃር ዩኒቨርሲቲዎች እንዲሁም በዲላ፣ በሀዋሳ፣ በመደ ወላቡ እና በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲዎች እና በሌሎች የኦንላይን መፈተኛ ማዕከላት እንደሚፈተኑ ገልፀዋል።
የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ሰኔ 21 እና 22/2017 ዓ.ም ወደመፈተኛ ማዕከላት ተጠናቀው እንደሚገቡ ተገልጿል።
የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ከሰኔ 23 እስከ ሐምሌ 08/2017 ዓ.ም እንደሚሰጥ ይታወቃል።
@tikvahuniveristy