Telegram Web Link
አንዱ አምላክ እና በጉ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

5፥117 በእርሱ ያዘዝከኝን ቃል *”ጌታዬንና ጌታችሁን አላህን አምልኩ”* ማለትን እንጂ ለእነርሱ ሌላ አላልኩም፡፡ مَا قُلْتُ لَهُمْ إِلَّا مَآ أَمَرْتَنِى بِهِۦٓ أَنِ ٱعْبُدُوا۟ ٱللَّهَ رَبِّى وَرَبَّكُمْ

አንዱ አምላክ አላህ ኢየሱስን ሲልከው፦ “ጌታዬንና ጌታችሁን አላህን አምልኩ” እንዲል ነው፦
5፥117 በእርሱ ያዘዝከኝን ቃል *”ጌታዬንና ጌታችሁን አላህን አምልኩ”* ማለትን እንጂ ለእነርሱ ሌላ አላልኩም፡፡ مَا قُلْتُ لَهُمْ إِلَّا مَآ أَمَرْتَنِى بِهِۦٓ أَنِ ٱعْبُدُوا۟ ٱللَّهَ رَبِّى وَرَبَّكُمْ

ነገር ግን ሰዎች ዛሬ ፍጡር የሆነውን ኢየሱስን ሲያመልኩ ይታያል። ይህ ስህተት ቢሆንም ኢየሱስ አምልኮ ይገባዋል ብለው ድምዳሜ ላይ ከአደረሳቸው አናቅጽ መካከል አንዱ እንይ፦
ራእይ 5፥13 *”በሰማይና በምድርም ከምድርም በታች በባሕርም ላይ ያለ ፍጥረት ሁሉ በእነርሱም ውስጥ ያለ ሁሉ፦ በረከትና ክብር ምስጋናም ኃይልም ከዘላለም እስከ ዘላለም በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው እና ለበጉ ይሁን ሲሉ ሰማሁ። አራቱም እንስሶች፦ አሜን አሉ፥ ሽማግሌዎቹም ወድቀው ሰገዱለት”*።
καὶ πᾶν κτίσμα ὃ ἐν τῷοὐρανῷ καὶ ἐπὶ τῆςγῆς καὶ ὑποκάτω τῆςγῆς καὶ ἐπὶ τῆςθαλάσσης, καὶ τὰ ἐναὐτοῖς πάντα, ἤκουσαλέγοντας, Τῷκαθημένῳ ἐπὶ τῷθρόνῳ καὶ τῷ ἀρνίῳ ἡεὐλογία καὶ ἡ τιμὴ καὶἡ δόξα καὶ τὸ κράτοςεἰς τοὺς αἰῶνας τῶναἰώνων. καὶ τὰ τέσσαρα ζῷαἔλεγον, Ἀμήν: καὶ οἱπρεσβύτεροι ἔπεσανκαὶ προσεκύνησαν.

እዚህ አንቀጽ ላይ “በረከትና ክብር ምስጋናም ኃይልም” በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው ለአንድ አምላክ እና ለበጉ ቀርቧል። ግን “አምልኮ” ቀርቧል የሚል ሽታው የለም። ይልቁንም በዙፋኑ ላይ የተቀመጠው እና በጉን ለመለየት “ካይ” καὶ ማለትም “እና” የሚል መስተጻምር ይጠቀማል። ሲጀመር ምስጋና የተገባው ማንነት ሁሉ አምልኮ ቀረበለት ብሎ መደምደም ስህተት ነው፥ ምስጋና የሚገባው ያህዌህ ቢሆንም ለቅኖች እና በግፍ መከራን የሚቀበል ሰው እግዚአብሔርን እያሰበ ኃዘንን ቢታገሥ ምስጋና ይገባቸዋል፦
መዝሙር 18፥3 *”ምስጋና የሚገባውን ያህዌህ እጠራለሁ”*፥ ከጠላቶቼም እድናለሁ።
መዝሙር 33፥1 ጻድቃን ሆይ፥ በእግዚአብሔር ደስ ይበላችሁ፤ *”ለቅኖች ምስጋና ይገባል”*።
1ኛ ጴጥሮስ 2፥19 በግፍ መከራን የሚቀበል ሰው እግዚአብሔርን እያሰበ ኃዘንን ቢታገሥ *”ምስጋና ይገባዋልና”*።

በጉ ባለጠግነት ክብር ሕይወትም ተገባው ማለት ትህትና ተገባው ማለት ነው፥ ምክንያቱም ትሕትናና ባለጠግነት፣ ክብር፣ ሕይወትም ነው፦
ምሳሌ 22፥4 *”ትሕትና እና እግዚአብሔርን መፍራት ባለጠግነት ክብር ሕይወትም ነው*።

ክብር ለነገሥታት የሚሰጥ አንድ አምላክ ነው፥ ክብር ለሚገባው ክብርን ስጡ ተብሏል፦
ዳንኤል 2፥37 አንተ፥ ንጉሥ ሆይ፥ የሰማይ አምላክ መንግሥትንና *”ኃይልን፥ ብርታትንና ክብርን የሰጠህ”* የነገሥታት ንጉሥ አንተ ነህ።
ሮሜ 13፥7 ለሁሉ የሚገባውን አስረክቡ፤ ግብር ለሚገባው ግብርን፥ ቀረጥ ለሚገባው ቀረጥን፥ መፈራት ለሚገባው መፈራትን፥ *”ክብር ለሚገባው ክብርን ስጡ”*።

እንግዲህ ክብርና ምስጋና የሚገባቸው እነዚህ አካላት እየተመለኩ ነው ብሎ መደምደም ቂልነት ነው። ሲቀጥል አንድ ነቢይ ከአንዱ አምላክ ጋር ምስጋና ክብር ተቀበለ ማለት ያን ነቢይ መመለክ ይገባዋል ብሎ ድምዳሜ ላይ መድረስ ከተቻለ ዳዊት ተመላኪ ነበር ማለት ነው፦
1 ዜና 29፥20 ዳዊትም ጉባኤውን ሁሉ፦ አምላካችሁን ያህዌህን ባርኩ፡ አላቸው። ጉባኤውም ሁሉ የአባታቸውን አምላክ ያህዌህን ባረኩ፥ *”ራሳቸውንም አዘንብለው ለያህዌህ እና ለንጉሡ ሰገዱ”*።

ጉባኤውን ሁሉ ራሳቸውንም አዘንብለው ለያህዌህ እና ለንጉሡ ሰገዱ ማለት ዳዊት ከያህዌህ ጋር ተሰግዶለታል። እና ዳዊት አምልኮ ተቀብሏልን? አይ፦ “ስግደት የአምልኮ ክፍል እንጂ ስግደት በራሱ አምልኮ አይሆንም፥ ለያህዌህ የባሕርይ ሲሆን ለዳዊት የጸጋ ነው” ከተባለ እንግዲያውስ ምስጋና ክብር የአምልኮ ክፍል እንጂ ምስጋና ክብር በራሱ አምልኮ አይሆንም፥ ለያህዌህ የባሕርይ ምስጋና ክብር ሲሆን ለበጉ የጸጋ ምስጋና ክብር ነው።
ሢሰልስ “ሽማግሌዎቹም ወድቀው ሰገዱለት” ይላል፥ ሽማግሌዎቹም ወድቀው የሰገዱት ለአብና ለወልድ ቢሆን ኖሮ “ሰገዱላቸው” ይባል ነበር። ነገር ግን ሽማግሌዎቹም ወድቀው የሰገዱት ለበጉ ሳይሆን በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው ለእግዚአብሔር ነው፦
ራእይ 19፥4 ሀያ *”አራቱም ሽማግሌዎችና አራቱ እንስሶች በፊታቸው ተደፍተው በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው ለእግዚአብሔር፦ አሜን፥ ሃሌ ሉያ፡ እያሉ ሰገዱለት”*።
ራእይ 4፥10 *”ሀያ አራቱ ሽማግሌዎች በዙፋን ላይ በተቀመጠው ፊት ወድቀው፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም በሕይወት ለሚኖረው እየሰገዱ*።
ራእይ 11፥16 በእግዚአብሔርም ፊት በዙፋኖቻቸው የተቀመጡ *”ሀያ አራቱ ሽማግሌዎች በግምባራቸው ተደፍተው ለእግዚአብሔር እየሰገዱ”*፡

ሲያረብብ በጉ መጥቶ በዙፋኑ ላይ ከተቀመጠው ከእግዚአብሔር መጽሐፍ መቀበሉ በራሱ በጉ እና በዙፋኑ ላይ የተቀመጠው ሁለት የተለያዩ ምንነት እና ማንነት ናቸው፦
ራእይ 5፥7 *”መጥቶም በዙፋን ላይ ከተቀመጠ ከዚያ ከቀኝ እጁ መጽሐፉን ወሰደው”*።
ራእይ 5፥13 *”በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው እና καὶ ለበጉ”* ይሁን ሲሉ ሰማሁ።

“ካይ” καὶ ማለት “እና” ማለት ሲሆን ይህ መስተዋድድ በዙፋኑ ላይ የተቀመጠው እና በጉን ሁለት ማንነቶች እንደሆኑ የሚያሳይ ነው፦
ራእይ 6፥16 ተራራዎችንና ዓለቶችንም፦ በላያችን ውደቁ *”በዙፋንም “ከ”ተቀመጠው ፊት እና “ከ”በጉም ቍጣ ሰውሩን፤
ራእይ 7፥10 በታላቅም ድምፅ እየጮሁ፦ *”በዙፋኑ ላይ “ለ”ተቀመጠው ለአምላካችን እና “ለ”በጉ ማዳን ነው”* አሉ።

“ከ” እና “ለ” የሚለው መስተዋድድ በዙፋኑ ላይ ተቀመጠ በተባለው እና በጉ በሚለው መነሻ ቅጥያ ሆኖ ሁለቴ መምጣቱ በዙፋኑ ላይ የተቀመጠው እና በጉ ሁለት ማንነቶች መሆናቸውን ቁልጭ አርጎ ያሳያል። በዙፋኑ ላይ የተቀመጠው ምንነቱ ጌታ አምላክ መባሉ ኢየሱስ ደግሞ በግ መባሉ ሁለት ምነነቶች እንደሆኑ ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ነው፦
ራእይ 21፥22 *”ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ እና በጉ መቅደስዋ ናቸውና”* መቅደስ በእርስዋ ዘንድ አላየሁም።

ልብ አድርግ “ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ” እና “በጉ” ሁለት ማንነት እንደሆኑ ለማሳየት “ናቸው” በሚል የብዜት አያያዥ ግስ ተቀምጧል፥ በተጨማሪም “እና” በሚል መስተጻምር ተለይተዋል። ስለዚህ በዙፋኑ ላይ የተቀመጠው ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ” እና “በጉ” ሁለት ኑባሬ ናቸው። እንደ ባይብሉ በግ የሚታረድ ስጋ ስለሆነ ስጋ ደግሞ አምልኮ አይገባው። በነገራችን ላይ “በግ” የሚለውን ተርም እኛ ሙሥሊሞች አንቀበለም። ዋናው ነጥባችን ኢየሱስ አምልኮ አይገባውም ነው።

ወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም

Follow us on:
https://fb.me/tiriyachen
https://www.tg-me.com/tiriyachen
https://tiriyachen.org
https://bit.ly/3eVixKv
https://www.tiktok.com/@tiriyachen

ወሠላሙ ዐለይኩም
👍3
ፈጣሪ ፆታ አለውን?

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

42፥11 *የሚመስለው ምንም ነገር የለም*፡፡ እርሱም ሰሚው ተመልካቹ ነው፡፡ لَيْسَ كَمِثْلِهِۦ شَىْءٌۭ ۖ وَهُوَ ٱلسَّمِيعُ ٱلْبَصِيرُ

ፈጣሪአችን አላህ የሚመስለው ምንም ሆነ ማንም የለም፥ ፍጡራንም እርሱን አይመስሉትም፤ አላህም ከፍጡራን ጋር የማይመሳሰል የራሱ ስምና ባህርይ አለው፤ ይህንን ስምና ባህርይ ከፍጡራን ጋር ሳናመሳስልና ሳናወዳድር እራሱ ዕውቅና በመሰጠበት መሠረት እንቀበላለን፦
42፥11 *የሚመስለው ምንም ነገር የለም*፡፡ እርሱም ሰሚው ተመልካቹ ነው፡፡ لَيْسَ كَمِثْلِهِۦ شَىْءٌۭ ۖ وَهُوَ ٱلسَّمِيعُ ٱلْبَصِيرُ
112፤4 *ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም*፡፡ وَلَمْ يَكُن لَّهُۥ كُفُوًا أَحَدٌۢ

አላህ ፈጣሪ ነው ፍጡርን አይመስልም ከተባለ ታዲያ ለምንድን ነው በቁርአን እራሱ “እርሱ” እና “አንተ” በሚል ተባዕታይ ፆታ የሚጠራው? ለሚለው ጥያቄ መልሱ አምላካችን አላህ ቁርኣንን ዐረቢኛ በማድረግ በዐረቢኛ ሰዋስው አውርዶታል፦
43፥3 *እኛ ታውቁ ዘንድ ዐረብኛ ቁርኣን አደረግነው*፡፡ إِنَّا جَعَلْنَاهُ قُرْآنًا عَرَبِيًّا لَّعَلَّكُمْ تَعْقِلُونَ
12፥2 *እኛ ትገነዘቡ ዘንድ ዘንድ ዐረብኛ ቁርኣን ሲሆን በእርግጥ አወረድነው*። إِنَّا أَنزَلْنَاهُ قُرْآنًا عَرَبِيًّا لَّعَلَّكُمْ تَعْقِلُونَ

“ነሕው” نَحْو ማለት “ሰዋስው” ማለት ሲሆን “ጂንሥ” جِنْس ማለት ደግሞ “ፆታ”gender” ማለት ነው፥ የሰዋስው ፆታ በሁለት ይከፈላል፤ አንዱ “ሙዘከር” مُذَكَّر ማለትም “ተባዕታይ”masculine” ሲሆን ሁለተኛው “ሙአነስ” مُؤَنَّث ማለትም “አንስታይ”feminine” ነው፤ ከዚህ ውጪ ልክ እንደ ኢንዶ-ኤሮፕያን ሰዋስው ግዑዝ ፆታ”neutral gender” የሚባል ዐረብኛ ሰዋስው ውስጥ የለም። ታዲያ ፆታ የሌላቸው ማንነት ሆነ ምንነት ምን ብለን እንጠራቸዋለን? ከተባለ አሁንም ለዐረቢኛው ሰዋስው መድረኩን መልቀቅ ነው። አሁንም በዚሁ የሰዋስው ሙግት ስንሄድ ከሁለቱም ማለትም ከሴትና ወንድ ፆታ ውጪ ያለ ማንነት ሆነ ምንነት ሲሆን “ሙፍረድ” مُفْرَد ማለትም ነጠላ”singular” ከሆነ ተባታይ በሆነው በሦስተኛ መደብ “ሁወ” هُوَ ማለትም “እርሱ” የሚለውን እና በሁለተኛ መደብ “አንተ” أَنْتَ ማለትም “አንተ” የሚለውን ተውላጠ-ስም እንጠቀማለን።
ለምሳሌ “ዋሒድ” وَٰحِد ማለት “አንድ” ማለት ሲሆን ተዕባታይ መደብ ነው።
ከአንድ በላይ የሆነ ማንነት ሆነ ምንነት “ጀመዕ” جَمَع ማለትም “ብዜት”plurar” ከሆኑ አንስታይ በሆነው በሦስተኛ መደብ “ሂየ” هِيَ ማለትም “እርሷ” የሚለውን እና በሁለተኛ መደብ “አንቲ” أنتِ ማለትም “አንቺ” የሚለውን ተውላጠ-ስም እንጠቀማለን።
ለምሳሌ “ሰላሳህ” ثَلَٰثَة ማለትም “ሦስት” አንስታይ ናት፦
4፥171 *”እናንተ የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! በሃይማኖታችሁ ወሰንን አትለፉ፡፡ በአላህም ላይ እውነትን እንጅ አትናገሩ”*፡፡ .. *”«ሦስት ናቸው» አትበሉም”*፡፡ ተከልከሉ፤ ለእናንተ የተሻለ ይኾናልና፡፡ *”አላህ አንድ አምላክ ብቻ ነው”*፡፡ يَٰٓأَهْلَ ٱلْكِتَٰبِ لَا تَغْلُوا۟ فِى دِينِكُمْ وَلَا تَقُولُوا۟ عَلَى ٱللَّهِ إِلَّا ٱلْحَقَّ ۚ إِنَّمَا ٱلْمَسِيحُ عِيسَى ٱبْنُ مَرْيَمَ رَسُولُ ٱللَّهِ وَكَلِمَتُهُۥٓ أَلْقَىٰهَآ إِلَىٰ مَرْيَمَ وَرُوحٌۭ مِّنْهُ ۖ فَـَٔامِنُوا۟ بِٱللَّهِ وَرُسُلِهِۦ ۖ وَلَا تَقُولُوا۟ ثَلَٰثَةٌ ۚ ٱنتَهُوا۟ خَيْرًۭا لَّكُمْ ۚ إِنَّمَا ٱللَّهُ إِلَٰهٌۭ وَٰحِدٌۭ ۖ سُبْحَٰنَهُۥٓ أَن يَكُونَ لَهُۥ وَلَدٌۭ ۘ لَّهُۥ مَا فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِى ٱلْأَرْضِ ۗ وَكَفَىٰ بِٱللَّهِ وَكِيلًۭا

ልብ አድርግ አላህ አንድ ስለሆነ “ዋሒድ” ብለክ “ሁወ” እንጂ “ሂየ” አትልም። የሚያጅበው “ሰላሳ” ثَلَٰثَة በሚለው ቃል መጨረሻ ላይ “ታ” ة የሚባለው “ታእ-መርቡጧህ” መሆኑ በራሱ ቃሉን አንስታይ ያደርገዋል። ለምሳሌ “መለክ” مَلَك ማለትም “መልአክ” በነጠላ ሙዘከር ነው፥ ነገር ግን በብዜት “መላኢካ-ህ” مَلَائِكَة ማለትም “መላእክት” ሙዐነስ ነው። “መላኢካ” በሚለው መድረሻ ቅጥያ ላይ ያለች “ታ” ة የምትባለው “ታእ-መርቡጧህ” ሙአነስ ናት፥ ለዚያ ነው እዚህ አንቀጽ ላይ፦ “ናደት” نَادَتْ ማለትም “ጠራች” የሚል ያለው፦
3፥39 እርሱም በጸሎት ማድረሻው ክፍል ቆሞ ሲጸልይ መላእክት፦ «አላህ በየሕያ ከአላህ በኾነ ቃል የሚያረጋግጥ ጌታም ድንግልም ከደጋጎቹ ነቢይም ሲኾን ያበስርሃል» በማለት *”ጠሩት”*፡፡ فَنَادَتْهُ الْمَلَائِكَةُ وَهُوَ قَائِمٌ يُصَلِّي فِي الْمِحْرَابِ أَنَّ اللَّهَ يُبَشِّرُكَ بِيَحْيَىٰ مُصَدِّقًا بِكَلِمَةٍ مِّنَ اللَّهِ وَسَيِّدًا وَحَصُورًا وَنَبِيًّا مِّنَ الصَّالِحِينَ

“ጠሩት” ለሚለው ቃል “ናደት-ሁ” َنَادَتْهُ መሆኑን አንስታይ መሆኑን ያሳያል፥ “ቃለ” قَالَ ማለት “አለ” ማለት ሲሆን ተባዕታይ ነው፥ “ቃለት” قَالَت ደግሞ “አለች” ማለት ሲሆን አንስታይ ነው። ይህ ቃል ለመላእክት ጥቅም ላይ ውሏል፦
3፥42 *”መላእክትም ያሉትን”* አስታውስ፡፡ «መርየም ሆይ! አላህ በእርግጥ መረጠሸ፡፡ አነጻሽም፡፡ በዓለማት ሴቶችም ላይ መረጠሽ፡፡» وَإِذْ قَالَتِ الْمَلَائِكَةُ يَا مَرْيَمُ إِنَّ اللَّهَ اصْطَفَاكِ وَطَهَّرَكِ وَاصْطَفَاكِ عَلَىٰ نِسَاءِ الْعَالَمِينَ

“ያሉት” ለሚለው “ቃለት” قَالَت በሚል መምጥቷል፥ “ቃለ” በሚለው መድረሻ ቅጥያ ላይ ያለች “ታ” ت “ታእ-መፍቱሓህ” تَاء مَفْتُوحَة‎ የምትባለው ሙአነስ ናት፥ ስለዚህ “ቃለት” የሚለው “ቃሉ” قَالُوا ማለትም “አሉ” ለማለት ተፈልጎ ነው፦
2፥30 ጌታህ ለመላእክት፡- «እኔ በምድር ላይ ምትክን አድራጊ ነኝ፤» ባለ ጊዜ የኾነውን አስታውስ፤ *”እነርሱም”*፦ «እኛ ከማመስገን ጋር የምናጠራህ ላንተም የምንቀድስ ስንኾን በርሷ ውስጥ የሚያጠፋንና ደሞችንም የሚያፈስን ታደርጋለህን?» *”አሉ”*፡፡ አላህ «እኔ የማታውቁትን ነገር አውቃለሁ» አላቸው፡፡ وَإِذْ قَالَ رَبُّكَ لِلْمَلَائِكَةِ إِنِّي جَاعِلٌ فِي الْأَرْضِ خَلِيفَةً ۖ قَالُوا أَتَجْعَلُ فِيهَا مَن يُفْسِدُ فِيهَا وَيَسْفِكُ الدِّمَاءَ وَنَحْنُ نُسَبِّحُ بِحَمْدِكَ وَنُقَدِّسُ لَكَ ۖ قَالَ إِنِّي أَعْلَمُ مَا لَا تَعْلَمُون
👍2
እዚህ አንቀጽ ላይ “አሉ” ለሚለው “ቃሉ” قَالُوا ማለቱን አስተውል። መላእክት ፆታ የሌላቸው ሴትም ወንድም አይደሉም። ለምን በአንስታይ መደብ ተጠቀመ? ስልን መላእክት ብዙ ማንነቶች ስለሆኑ ሲሆን አላህ ደግሞ አንድ ማንነት ስለሆነ በተባታይ መደብ “እርሱ” “አንተ” “አለ” ተብሎ ተገልጿል። ልብ አድርግ ሂየ” هِيَ የሚለው አንስታይ መደብ “እነርሱ” የሚለውን ብዜት ለማመልከት ይመጣል፦
6፥78 ለእኛም ምሳሌን አደረገልን፡፡ መፈጠሩንም ረሳ፡፡ *«አጥንቶችን እነርሱ የበሰበሱ ሲኾኑ ሕያው የሚያደርጋቸው ማነው?»* አለ፡፡ وَضَرَبَ لَنَا مَثَلًا وَنَسِيَ خَلْقَهُ ۖ قَالَ مَن يُحْيِي الْعِظَامَ وَهِيَ رَمِيمٌ

“ዐዝም” عَظْم በነጠላ “አጥንት”bone” ማለት ነው፤ “ዒዛም” عِظَام ደግሞ የዐዝም ብዜት ሲሆን “አጥንቶች” ማለት ነው፤ እዚህ አንቀጽ ላይ አጥንቶች ለሚለው ስም ተክቶ የገባው ነጠላ አንስታይ ተውላጠ ስም በሙዐነስ “ሂየ” هِيَ ነው። በተጨማሪ፦
27፥88 *”ጋራዎችንም እርሷ” እንደ ደመና አስተላለፍ የምታልፍ ስትኾን የቆመች ናት ብለህ የምታስባት ሆና ታያታለህ*፡፡ የዚያን ነገሩን ሁሉ ያጠነከረውን የአላህን ጥበብ ተመልከት፡፡ እርሱ በምትሠሩት ሁሉ ውስጥ ዐዋቂ ነው፡፡ وَتَرَى الْجِبَالَ تَحْسَبُهَا جَامِدَةً وَهِيَ تَمُرُّ مَرَّ السَّحَابِ ۚ صُنْعَ اللَّهِ الَّذِي أَتْقَنَ كُلَّ شَيْءٍ ۚ إِنَّهُ خَبِيرٌ بِمَا تَفْعَلُونَ

“ጀበል” جَبَلْ በነጠላ “ጋራ” ማለት ነው፤ “ጂባል” جِبَالْ ደግሞ የጀበል ብዜት ሲሆን “ጋራዎች” ማለት ነው፤ እዚህ አንቀጽ ላይ ጋራዎች ለሚለው ስም ተክቶ የገባው ነጠላ አንስታይ ተውላጠ ስም አሁንም በሙዐነስ “ሂየ” هِيَ ነው።

እሩቅ ሳንሄድ በዐረቢኛ ድምጽ ያላቸው ተነባቢ ፊደላት”sound letters” 28 ሲሆኑ ከእነርሱ ውጥስ 14 ሐርፎች “ሑሩፉል ቀመሪያህ” حُرُوف القَمَرِيَّة ማለትም “የጨረቃ ፊደሎች”lunar letters” ተባታይ ናቸው፣ እነርሱም፦
ء ﺏ ﺝ ﺡ ﺥ ﻉ ﻍ ﻑ ﻕ ﻙ ﻡ ﻭ ﻱ ه
የቀሩት 14 ሐርፎች “ሁሩፉ አሽ-ሸምሢያህ” حُرُوف الشَمْسِيَّة ማለትም “የፀሐይ ፊደሎች”solar letters” አንስታይ ናቸው፣ እነርሱም፦
ﺕ ﺙ ﺩ ﺫ ﺭ ﺯ ﺱ ﺵ ﺹ ﺽ ﻁ ﻅ ﻝ ﻥ
ያ ማለት አስራ አራቱ ቀመሪያህ ሙዘከር ስለሆኑ ወንዶች ናቸውን? አስራ አራቱ ሸምሲያህ ሙዐነስ ስለሆኑ ሴቶች ናቸውን? መልሱ አይ ይህ የዐረቢኛ ሰዋስው ላይ የተለመደ ነው። ፀሐይ “ሂየ” هِيَ ትባላለች፥ ጨረቃ ደግሞ “ሁወ” هُوَ ይባላል፤ እና ፀሐይ ሴት ጨረቃ ወንድ ነውን? ፀሐይ በአንስታይ መደብ ነው የተጠራችው፦
81፥1 *”ፀሐይ “በተጠቀለለች” ጊዜ”*። إِذَا الشَّمْسُ كُوِّرَتْ

“ተጠቀለለች” ለሚለው ቃል የገባው “ከወረት” كُوِّرَتْ የሚለው ሙዐነስ እንጂ “ከወረ” كُوِّرَ የሚለው ሙዘከር አይደለም፦
75፥8 *”ጨረቃም “በጨለመ” ጊዜ”*፡፡ وَخَسَفَ الْقَمَر

“ጨለመ” ለሚለው ቃል የገባው “ኸሠፈ” خَسَفَ የሚለው ሙዘከር እንጂ “ኸሠፈት” خَسَفَتْ የሚለው ሙዐነስ አይደለም።
ስለዚህ አላህ “አንተ” እና “እርሱ” ስለተባለ ፈጣሪ ፆታ አለው ብሎ መደምደም ስህተት ነው። ባይሆን በባይብል እግዚአብሔር ፆታ ከሌለው ወንድም ሴትም ካልሆነ ለምን “አንተ” እና “እርሱ” እንደሚባል የቤት ሥራ ሰጥተናችኃል።

ከኡሥታዝ ወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም

Follow us on:
https://fb.me/tiriyachen
https://www.tg-me.com/tiriyachen
https://tiriyachen.org
https://bit.ly/3eVixKv
https://www.tiktok.com/@tiriyachen

ወሠላሙ ዐለይኩም
መርየም

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

5፥116 አላህም፡- «የመርየም ልጅ ዒሳ ሆይ! አንተ ለሰዎቹ፡- *እኔን እና እናቴን ከአላህ ሌላ አምላኮች አድርጋችሁ ያዙ ብለሃልን?*» በሚለው ጊዜ አስታውስ ፡፡ وَإِذْ قَالَ اللَّهُ يَا عِيسَى ابْنَ مَرْيَمَ أَأَنتَ قُلْتَ لِلنَّاسِ اتَّخِذُونِي وَأُمِّيَ إِلَـٰهَيْنِ مِن دُونِ اللَّهِ

አላህ ዒሳን እዲናገር ያዘዘው ቃል፦ “አላህ ጌታዬ ጌታችሁ ነው፤ በብቸኝነት አምልኩት” የሚል ሲሆን ነገር ግን ነሳራዎች እርሱ እና እናቱን ከአላህ ሌላ አምላክ አድርገው ይዘዋል፤ “አምላክ አድርጎ መያዝ” ምን ማለት ነው? አንድ ሰው አንድ ነገር አምላክ አርጎ ያዘ ማለት ለአምላክ የሚሰጠውን የአምልኮ ክፍል ለሌላ ማንነት ሆነ ምንነት መስጠትን ያመለክታል፤ ለምሳሌ አንድ ሰው ፍላጎቱን አምላኩ አድርጎ ያዘ ማለት ፍላጎቱን አምላኬ ብሎ ጠራ ማለት ሳይሆን ለአምላክ የሚሰጠውን የአምልኮ ክፍል ለፍላጎቱ ቅድሚያ ሰጠ ማለት ነው፦
25፥43 *ፍላጎቱን አምላኩ አድርጎ የያዘውን ሰው አየህን?* አንተ በእርሱ ላይ ጠባቂ ትሆናለህን? أَرَأَيْتَ مَنِ اتَّخَذَ إِلَـٰهَهُ هَوَاهُ أَفَأَنتَ تَكُونُ عَلَيْهِ وَكِيلًا

ሰዎች ከአላህ ሌላ አምላክ አድርገው የያዙት ዒሳን እና እናቱን ብቻ ሳይሆን የእርሱ ባሮች የሆኑትንም መላእክት እና ነብያትንም ጭምር ነው፦
18፥102 እነዚያ የካዱት *ባሮቼን ከእኔ ሌላ አማልክት አድርገው መያዛቸውን* የማያስቆጣኝ አድርገው አሰቡን? እኛ ገሀነምን ለከሓዲዎች መስተንግዶ አዘጋጅተናል أَفَحَسِبَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوٓا۟ أَن يَتَّخِذُوا۟ عِبَادِى مِن دُونِىٓ أَوْلِيَآءَ ۚ إِنَّآ أَعْتَدْنَا جَهَنَّمَ لِلْكَٰفِرِينَ نُزُلًۭا ፡፡
3:80 *መላእክትንና ነቢያትንም አማልክቶች አድርጋችሁ እንድትይዙ* ሊያዛችሁ አይገባዉም፤ እናንተ ሙስሊሞች ከሆናችሁ በኋላ በክሕደት ያዛችኋልን? وَلَا يَأْمُرَكُمْ أَن تَتَّخِذُوا الْمَلَائِكَةَ وَالنَّبِيِّينَ أَرْبَابًا ۗ أَيَأْمُرُكُم بِالْكُفْرِ بَعْدَ إِذْ أَنتُم مُّسْلِمُونَ

ይህንን ከተረዳን “ኢላሀይኒ” إِلَٰهَيْنِ ለኢሳ እና ለመርየም በሙተና የገባ ነው፤ በሙፍረድ ሲሆን ደግሞ “ኢላህ” إِلَٰه ማለትም “የሚመለክ” ማለት ነው፣ “አምልኮ” የሚለው ቃል “መለከ” ማለትም “ገዛ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ለምንነት መገዛት” ማለት ነው። ከሣቴ ብርሃን ተሰማ የአማርኛ መዝገበ ቃላት (2005) ገጽ 708)

አምልኮ በውስጡ ልመና፣ ስግደት፣ ስለት መሳል እጣን ማጨስ መስዋዕት ማቅረብ ይይዛል። “አምላክ” የሚለውም ቃል “መለከ” ከሚል ስርወ ቃል መምጣቱ አንባቢ ልብ ይለዋል። ሰውን በአካል ማየት፣ መስማት፣ መናገር እስከቻለ ድረስ ማነጋገሩ ተፈጥሯዊ ነው፣ ነገር ግን የሚያይበት አይን፣ የሚሰማበት ጆሮ፣ የሚናገርበት አፍ፣ የሚያውቅበት አንጎል በሞት ጊዜ ስለሚፈራርሱ አይሰማም፣ አይናገርም፣ አያይም፣ ዐያውቅም።
በክርስትና ማለትም ካቶሊክ፣ ኦርቶዶክስና አንግሊካል ወደ ማርያም ጥሪ፣ ልመና፣ መተናነስ፣ መጎባደድ ይደረጋል፣ ስለት መሳል፣ እጣን ማጨስ እና መስዋዕት ማቅረብ ይደረጋል፤ ታዲያ ማርያም በሌለችበት ይህን ማድረግ አምልኮ አይደለምን? አዎ ከተባለ እንግዲያውስ አግባብ አይደለም፤ አይ ከተባል ለምን ወደ ማርያም ይህ ሁሉ ይደረጋል? ማርያም በምኗ ትሰማለች? ታያለች? ታውቃለች? ሰውን የምትገናኝበት ህዋሳቷ አፈር ሆኖ የለ እንዴ? በሰው ልብ ያለውን መለኮት ካልሆነች እንዴት ታውቃለች? ከአላህ ሌላ ማንነት ሆነ ምንነት መለማመን፣ መጎባደድ፣ መተናነስ፣ መጥራት ሽርክ ነው፤ ምክንያቱም ሁሉንም ነገር በጊዜና በቦታ ሳይገደብ ማወቅ፣ ማየት እና መስማት የሚችል አንድ አምላክ ብቻ ነው፦
46:5 *እስከ ትንሣኤ ቀን ድረስም ለእርሱ የማይመልስለት ከአላህ ሌላ ከሚጠራ ሰው ይበልጥ የተሳሳተ ማነው? እነርሱም ከጥሪያቸው ዘንጊዎች ናቸው*። وَمَنْ أَضَلُّ مِمَّن يَدْعُوا۟ مِن دُونِ ٱللَّهِ مَن لَّا يَسْتَجِيبُ لَهُۥٓ إِلَىٰ يَوْمِ ٱلْقِيَٰمَةِ وَهُمْ عَن دُعَآئِهِمْ غَٰفِلُونَ

ማርያም በሌለችበት እንዲህ ጸሎት፣ ስግደት እና መገዛት ይቀርብላታል፦
ዚቅ ዘየካቲት ኪዳነ ምህረት ገፅ 144
“ብቻዋን ታላላቅ ብርሃናትን ለፈጠረች ለመድኃኒት ድንግል ማርያም ኑ እንስገድላት ለእርሷም እንገዛ”
መጽሐፈ ሰአታት ገፅ 31
፦ “በብርሃን ጌጥ ያጌጥሽ ወርቅ ዘቦ ግምጃን የተጎናፀፍሽ የዳዊት ልጅ እመቤታችን ተገዛንልሽ ለአንቺ እንገዛለን”
፦ “አደፍ ጉድፍ የሌለብሽ ብርሌ ካህናት የሚያሹትሽ የሽቱ ሙዳይ እመቤታችን ሆይ ተገዛንልሽ ለአንቺን ፈፅመን እንገዛለን”
፦ “የታተምሽ የውሃ ጉድጓድ የተዘጋሽ የተክል ቦታ የዳዊት ልጅ እመቤታችን ሆይ የነብያት ልጆቻቸው አንች ነሽና ተገዛንልሽ ለአንቺ ፈፅመን እንገዛለን”
፦ “በብርና በወርቅ የተሸለምሽ አዲስ የጣሪያ ዋልታ ሚስጥር ማደሪያ የዳዊት ልጅ እመቤታችን ሆይ ተገዛንልሽ ለአንቺ ፈፅመን እንሰግዳለን”

ይህ አምልኮ ካልሆነ ምን ይባላል? አላህ የትንሳኤ ቀን ከእርሱ ሌላ አምልኮ የሚደረግላቸውን አካላት እንዲህ በማለት እያወቀ ይጠይቃቸዋል፦
25፥17 *እነርሱን እና ከአላህ ሌላ የሚግገዟቸውንም የሚሰበስብባቸውን እና «እናንተ እነዚህን ባሮቼን አሳሳታችሁን ወይስ እነርሱው መንገድን ሳቱ?» የሚልበትን ቀን አስታውስ*፡፡ وَيَوْمَ يَحْشُرُهُمْ وَمَا يَعْبُدُونَ مِن دُونِ اللَّهِ فَيَقُولُ أَأَنتُمْ أَضْلَلْتُمْ عِبَادِي هَـٰؤُلَاءِ أَمْ هُمْ ضَلُّوا السَّبِيلَ

ነገር ግን እነዚያ ዱዓ ሲደረግላቸው የነበሩት አካላት ከአምላኪዎች ተቃራኒ በመሆን አምልኮ እንዳልተቀበሉ ይክዳሉ፦
19፥81-82 *ከአላህም ሌላ አማልክትን* ለእነርሱ መከበሪያ እንዲኾኑዋቸው *ያዙ* وَٱتَّخَذُوا۟ مِن دُونِ ٱللَّهِ ءَالِهَةًۭ لِّيَكُونُوا۟ لَهُمْ عِزًّۭا ፡፡
ይከልከሉ፤ *ማምለካቸውን በእርግጥ ይክዷቸዋል፡፡ በእነሱም ላይ ተቃራኒ ይኾኑባቸዋል* كَلَّا ۚ سَيَكْفُرُونَ بِعِبَادَتِهِمْ وَيَكُونُونَ عَلَيْهِمْ ضِدًّا ፡፡

በካቶሊክ ማርያም፦ “ሰማይ ላይ ኖራ በኃላ ስጋ የለበሰች አርያማዊት ማለትም ሰማያዊት ናት፤ ከዚያም ሞታ ሳትበሰብስ ተነስታ ወደ ሰማይ አርጋለች” ተብሎ ይታመናል፤ በኦርቶዶክስና በአንግሊካንም፦ “ሞታ ሳትበሰብስ ተነስታ ወደ ሰማይ አርጋለች” ተብሎ ይታመናል።
በ 375 AD የተነሱት ኮላደሪያን ክርስቲያኖች ማርያምን በግልጽ፦ “ቴአ” Θεία ማለትም “ሴት አምላክ” ብለው ይጥሩአት ነበር።
👍1
በ 431 AD የኤፌሶን ጉባኤ ማርያምን “ቴኦቶኮስ” Θεοτόκος ማለትም “የአምላክ እናት” ብለዋታል።
ካቶሊክ፣ ኦርቶዶስ፣ አንግሊካን ማርያምን በግሪክ “ኪርያ” κυρία ማለትም “ሴት ጌታ” ይሉአታል፣ “ኪርዮስ” κύριος ማለት “ወንድ ጌታ” ማለት ነው። በአገራችን ኦርቶዶክሶች ደግሞ “እግዚኢት” ትባላለች፤ “እግዚኢት” ማለት “ሴት ጌታ” ማለት ሲሆን “እግዚእ” ደግሞ “ወንዱ ጌታ” ማለት ነው፤ ኢየሱስን “እግዚኢነ” ማለትም “ጌታችን” እንደሚሉት ሁሉ ማርያም “እግዚኢትነ” ማለትም “ጌታችን” ይሉአታል። ከዚህ የበለጠ ማርያምን አምላክ አድርጎ መያዝ አለን? ነሳራዎች ሆይ! ዒሳን በቀጥታ መርየምን ደግሞ በተዘዋዋሪ እያመለካችሁ ትገኛላችሁ፤ እናማ በእኛ እና በእናንተ የጋራ የሆነው ቃል አንድ አምላክ ብቻ ማምለክ የሚል ነውና ከአንዱ አምላክ ሌላ ከፍጡራን ከፊላችንም ከፊሉን ከአላህ ሌላ አማልክት አድርጎ ላይይዝ ነው፦
3፥64 የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! *በእኛና በእናንተ መካከል ትክክል ወደ ኾነች ቃል ኑ፡፡ እርሷም አላህን እንጅ ሌላን ላንገዛ፣ በእርሱም ምንንም ላናጋራ፣ ከፊላችንም ከፊሉን ከአላህ ሌላ አማልክት አድርጎ ላይይዝ ነው*፤ በላቸው፡፡ قُلْ يَا أَهْلَ الْكِتَابِ تَعَالَوْا إِلَىٰ كَلِمَةٍ سَوَاءٍ بَيْنَنَا وَبَيْنَكُمْ أَلَّا نَعْبُدَ إِلَّا اللَّهَ وَلَا نُشْرِكَ بِهِ شَيْئًا وَلَا يَتَّخِذَ بَعْضُنَا بَعْضًا أَرْبَابًا مِّن دُونِ اللَّهِ ۚ

ኡሥታዝ ወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም

የበለጠ ለማወቅ
ጥሪያችን Tiriyachen
https://www.facebook.com/tiriyachen

ወሠላሙ ዐለይኩም
👍2
ሙሰዲቃን እና ሙሃይሚን

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

5፥48 *”ወደ አንተም መጽሐፉን ከበፊቱ ያለውን መጽሐፍ “አረጋጋጭ” እና በእርሱ ላይ “ተጠባባቂ” ሲሆን በእውነት አወረድን”*። وَأَنزَلْنَآ إِلَيْكَ ٱلْكِتَٰبَ بِٱلْحَقِّ مُصَدِّقًۭا لِّمَا بَيْنَ يَدَيْهِ مِنَ ٱلْكِتَٰبِ وَمُهَيْمِنًا عَلَيْهِ

አምላካችን አላህ በነቢያችን”ﷺ” ላይ ቁርኣንን በእውነት አወረደ፥ ከቁርኣን በፊት ተውራትንና ኢንጂልን ለሰዎች መሪ አድርጎ አወረዳቸው፦
3፥3 *”ከእርሱ በፊት ያሉትን የሚያረጋግጥ ሲኾን መጽሐፉን በአንተ ላይ ከፋፍሎ በእውነት አወረደ፡፡ ተውራትንና ኢንጂልንም አውርዷል”*፡፡ نَزَّلَ عَلَيْكَ ٱلْكِتَٰبَ بِٱلْحَقِّ مُصَدِّقًۭا لِّمَا بَيْنَ يَدَيْهِ وَأَنزَلَ ٱلتَّوْرَىٰةَ وَٱلْإِنجِيلَ
3፥4 *”ከእርሱ በፊት ለሰዎች መሪ አድርጎ አወረዳቸው”*፡፡ مِن قَبْلُ هُدًۭى لِّلنَّاسِ

“የደይ” يَدَيْ ማለት “ፊት” ማለት ሲሆን “ኃላ” ለሚል ተቃራኒ ሆኖ የመጣ ነው፥ “ቀብል” قَبْل ማለት “ፊት” ማለት ሲሆን የየደይ ተመሳሳይ ትርጉም ነው። “የደይ-ሂ” يَدَيْهِ ማለት እና “ቀብሉ” قَبْلُ ማለት “ከበፊቱ” ማለት ነው፥ “ሂ” هِ ወይም “ሁ” هُ የሚለው ተሳቢ ተውላጠ-ስም ቁርኣንን ያሳያል። ከቁርኣን በፊት የወረዱትን ተውራትና ኢንጅልን ሊያረጋግጥ ቁርኣን ወርዷል። “ተውራትንና ኢንጂልንም አውርዷል” የሚለው ሃይለ-ቃል ይሰመርበት። አምላካችን አላህ፦ “እመኑ” ያለን ከቁርኣን በፊት ባወረደው ወሕይ ነው፦
4፥136 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በአላህ እና በመልክተኛው፤ በዚያም በመልክተኛው ላይ ባወረደው መጽሐፍ፤ በዚያም *”ከበፊቱ ባወረደው መጽሐፍ እመኑ”*፡፡ يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ ءَامِنُوا۟ بِٱللَّهِ وَرَسُولِهِۦ وَٱلْكِتَٰبِ ٱلَّذِى نَزَّلَ عَلَىٰ رَسُولِهِۦ وَٱلْكِتَٰبِ ٱلَّذِىٓ أَنزَلَ مِن قَبْلُ

“ከበፊቱ ባወረደው መጽሐፍ እመኑ” የሚለው ሃይለ-ቃል ይሰመርበት። እንግዲህ አምላካችን አላህ ተውራትና ኢንጅል የሚላቸው ወደ ሙሳ እና ወደ ዒሣ የወረዱትን ወሕይ ብቻና ብቻ ነው። አምላካችን አላህ ከራሱ የሚያወርደው ወሕይ እውነት ይለዋል፦
34፥48 ፦ጌታዬ *“እውነትን ያወርዳል”*፤ ሩቅ የኾኑትን ሚስጢሮች ሁሉ ዐዋቂ ነው *በላቸው*። قُلْ إِنَّ رَبِّى يَقْذِفُ بِٱلْحَقِّ عَلَّٰمُ ٱلْغُيُوبِ

ይህ ከአላህ የወረደውን እውነት የመጽሐፉ ሰዎች ከውሸት ማለት ከሰው ንግግር ጋር ቀላቅለውታል፦
3፥71 የመጸሐፉ ሰዎች ሆይ! *“እዉነቱን በዉሸት” ለምን ትቀላቅላላችሁ*? እዉነቱንም እናንተ የምታወቁ ስትሆኑ ለምን ትደብቃላችሁ? يَٰٓأَهْلَ ٱلْكِتَٰبِ لِمَ تَلْبِسُونَ ٱلْحَقَّ بِٱلْبَٰطِلِ وَتَكْتُمُونَ ٱلْحَقَّ وَأَنتُمْ تَعْلَمُونَ

ይህ የሰው ንግግር “ውሸት” ለምን ተባለ? ምክንያቱም የሰው ንግግር በእጆቻቸው ፅፈው «ይህ ከአላህ ዘንድ ነው» ብለው የቀጠፉት ጭማሬ ስለሆነ ነው፦
2፥79 *ለነዚያም መጽሐፉን በእጆቻቸው ለሚጽፉና ከዚያም በርሱ ጥቂትን ዋጋ ሊገዙበት «ይህ ከአላህ ዘንድ ነው» ለሚሉ ወዮላቸው*፡፡ ለነርሱም ከዚያ እጆቻቸው ከጻፉት ወዮላቸው፡፡ ለነሱም ከዚያ ከሚያፈሩት ኃጢኣት ወዮላቸው፡፡ فَوَيْلٌۭ لِّلَّذِينَ يَكْتُبُونَ ٱلْكِتَٰبَ بِأَيْدِيهِمْ ثُمَّ يَقُولُونَ هَٰذَا مِنْ عِندِ ٱللَّهِ لِيَشْتَرُوا۟ بِهِۦ ثَمَنًۭا قَلِيلًۭا ۖ فَوَيْلٌۭ لَّهُم مِّمَّا كَتَبَتْ أَيْدِيهِمْ وَوَيْلٌۭ لَّهُم مِّمَّا يَكْسِبُونَ

እዚው ዐውድ ላይ ስንመለከት ከመጽሐፉ ሰዎች የአላህን ንግግር የሚሰሙ እና ከዚያም ከተረዱት በኋላ እነርሱ እያወቁ የሰው ንግግር በእጆቻቸው ፅፈው «ይህ ከአላህ ዘንድ ነው» ብለው በርዘውታል፦
2፥75 *ከእነርሱ የኾኑ ጭፍሮች የአላህን ንግግር የሚሰሙ እና ከዚያም ከተረዱት በኋላ እነርሱ እያወቁ “የሚለውጡት” ሲኾኑ ለእናንተ ማመናቸውን ትከጅላላችሁን?”* أَفَتَطْمَعُونَ أَن يُؤْمِنُوا لَكُمْ وَقَدْ كَانَ فَرِيقٌ مِّنْهُمْ يَسْمَعُونَ كَلَامَ اللَّهِ ثُمَّ يُحَرِّفُونَهُ مِن بَعْدِ مَا عَقَلُوهُ وَهُمْ يَعْلَمُون

“የሚለውጡት” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ዩሐረፉነሁ” يُحَرِّفُونَهُ ሲሆን “የሚበርዙት” ማለት ነው፤ “ዩሐረፉ” يُحَرِّفُ የሚለው አላፊ ግስ “ሐረፈ” حَرَفَ ማለትም “በረዘ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ እንደሆነ አንባቢ ልብ ይለዋል፤ የሚበርዙት ፊደሉ “ሐርፍ” حَرْف ሲባል፥ በራዡ “ሙተሐሪፍ” مُتَحَرِّف ሲልባ፥ የመበረዙ ድርጊቱ ደግሞ “ተሕሪፍ” تَحريف ይባላል፤ ይህ ሙግት የሥነ-ቋንቋ ሙግት ታሳቢና ዋቢ ያደረገ ነው።
በተጨማሪም ከቀደምት የነቢያችን”ﷺ” ቅርብ ባልደረባ ኢብኑ ዓባሥ”ረ.ዐ” የሱረቱል በቀራ 2፥79 አንቀጽን በሰሒሕ ሐዲስ ሲፈሥረው እንዲህ ይላል፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 52, ሐዲስ 46:
ኢብኑ ዐባሥ”ረ.ዐ” ሲናገር፦ *ሙስሊሞች ሆይ ለምን የመጽሐፉ ሰዎችን ትጠይቃላችሁ? በተመሳሳይ መጽሐፋችሁ ከአላህ ዘንድ ለነቢዩ”ﷺ” የተወረደው ወቅታቂ መረጃ እና የምትቀሩት እያለ? መጽሐፋ አልተበረዘምን? አላህ ለእናንተ የመጽሐፉ ሰዎች በእጆቻቸው በርዘው «ይህ ከአላህ ዘንድ ነው» እንደሚሉ አውርዷል*። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ ـ رضى الله عنهما ـ قَالَ يَا مَعْشَرَ الْمُسْلِمِينَ، كَيْفَ تَسْأَلُونَ أَهْلَ الْكِتَابِ، وَكِتَابُكُمُ الَّذِي أُنْزِلَ عَلَى نَبِيِّهِ صلى الله عليه وسلم أَحْدَثُ الأَخْبَارِ بِاللَّهِ، تَقْرَءُونَهُ لَمْ يُشَبْ، وَقَدْ حَدَّثَكُمُ اللَّهُ أَنَّ أَهْلَ الْكِتَابِ بَدَّلُوا مَا كَتَبَ اللَّهُ وَغَيَّرُوا بِأَيْدِيهِمُ الْكِتَابَ، فَقَالُوا هُوَ مِنْ عِنْدِ اللَّهِ، لِيَشْتَرُوا بِهِ ثَمَنًا قَلِيلاً أَفَلاَ يَنْهَاكُمْ مَا جَاءَكُمْ مِنَ الْعِلْمِ عَنْ مُسَاءَلَتِهِمْ، وَلاَ وَاللَّهِ مَا رَأَيْنَا مِنْهُمْ رَجُلاً قَطُّ يَسْأَلُكُمْ عَنِ الَّذِي أُنْزِلَ عَلَيْكُمْ

ተውራትንና ኢንጂልን ከቁርኣን በፊት ለሰዎች መሪ አድርጎ ቢያወርዳቸውም ቁርኣን ግን ከእርሱ በፊት ያሉትን ተውራትንና ኢንጂልን የሚያረጋግጥ እና የተቀላቀለው እውነት ከውሸት የሚለይ ነው፥ የመጽሐፉ ሰዎች እዉነቱን በዉሸት በመቀላቀል ሲበረዙት አምላካችን አላህ ቁርኣንን ፉርቃን በማድረግ አውርዷል። “ፉርቃን” فُرْقَان ማለት “እውነትን ከውሸት የሚለይ” ማለት ነው፦
👍1
25፥1 ያ *ፉርቃንን በባሪያው ላይ ለዓለማት አስጠንቃቂ ይኾን ዘንድ ያወረደው አምላክ ክብርና ጥራት ተገባው*፡፡ تَبَارَكَ ٱلَّذِى نَزَّلَ ٱلْفُرْقَانَ عَلَىٰ عَبْدِهِۦ لِيَكُونَ لِلْعَٰلَمِينَ نَذِيرًا
3፥4 ከእርሱ በፊት ለሰዎች መሪ አድርጎ አወረዳቸው፡፡ *”ፉርቃንንም አወረደ”*፡፡ مِن قَبْلُ هُدًى لِّلنَّاسِ وَأَنزَلَ الْفُرْقَان
5፥48 *”ወደ አንተም መጽሐፉን ከበፊቱ ያለውን መጽሐፍ “አረጋጋጭ” እና በእርሱ ላይ “ተጠባባቂ” ሲሆን በእውነት አወረድን”*። وَأَنزَلْنَآ إِلَيْكَ ٱلْكِتَٰبَ بِٱلْحَقِّ مُصَدِّقًۭا لِّمَا بَيْنَ يَدَيْهِ مِنَ ٱلْكِتَٰبِ وَمُهَيْمِنًا عَلَيْهِ

“ሙሰዲቃን” مُصَدِّقًا ማለት “አረጋጋጭ” ማለት ሲሆን ቁርኣን ከወረደበት አላማ እና ኢላማ አንዱ ከአላህ የወረደውን እውነት ለማረጋገጥ ነው፥ ከአላህ የወረደውን እውነት ስለሚያረጋግጥ “ሙሰዲቃን” ይባላል። “ሙሃይሚን” مُهَيْمِنًا ማለት ደግሞ “አራሚ” corrector” ወይም “ተቆጣጣሪ”supervisor” ማለት ነው፦
Arabic-English Lexicon volume 1 page 147 Edited by Edward William Lane.

በተወረደው ላይ ቀጥፈው የጨመሩትን ውሸት ስለሚያርም “ሙሃይሚን” ይባላል።
የመጽሐፉ ሰዎች ጋር ያለው የተበረዘ መፅሐፍ ነው ማለት ወተት ከቡና ጋር ሲቀላቀል ኦርጂናሉ ወተት ተበርዟል ማለት ነው። ነገር ግን የወተት ቅሪት በማኪያቶ ላይ አለ። በተመሳሳይ የአላህ ንግግር የወረደበት ቋንቋ ሥረ-መሠረቱና የቃሉ አንጓ ባይኖርም መልእክቱ እና ሃሳቡ በቅሪት ደረጃ አለ። የመጽሐፉ ሰዎች ጋር ያሉት መጽሐፍት ሙሉ ለሙሉ እውነትን ነው ብለን እንደማንቀበል ሁሉ ሙሉ ለሙሉ ሐሰት ነው ብለን አናስተባብልም። ዋናው ከአላህ የወረደውን እውነት ሰዎች ከጨመሩበት ሐሰት የምንለይበት ፉርቃን ቁርኣን ነው። ቁርኣን ያረጋገጠውን እሳቤ በማረጋገጥ ያረመውን ደግሞ በመተው እንመዝናለን። ለምሳሌ ቁርኣን ከበፊቱ የወረደውን በመግለጽ እና በመዘርዘር አረጋግጧል፦
16፥44 በግልጽ ማስረጃዎች እና በመጻሕፍት ላክናቸው፡፡ ወደ አንተም ለሰዎች *”ወደ እነርሱ የተወረደውን ልትገልጽላቸው”* እና ያስተነትኑም ዘንድ ቁርኣንን አወረድን፡፡ بِٱلْبَيِّنَٰتِ وَٱلزُّبُرِ ۗ وَأَنزَلْنَآ إِلَيْكَ ٱلذِّكْرَ لِتُبَيِّنَ لِلنَّاسِ مَا نُزِّلَ إِلَيْهِمْ وَلَعَلَّهُمْ يَتَفَكَّرُون
10፥37 ይህም ቁርኣን ከአላህ ሌላ ከሆነ ፍጡር የተቀጠፈ ሊሆን አይገባውም፡፡ ግን ያንን *”ከእርሱ በፊት ያለውን”* የሚያረጋግጥ እና *”በመጽሐፉ ውስጥ ያለውን የሚዘረዝር”* በእርሱ ጥርጣሬ የሌለበት ሲሆን ከዓለማት ጌታ የተወረደ ነው፡፡ وَمَا كَانَ هَٰذَا ٱلْقُرْءَانُ أَن يُفْتَرَىٰ مِن دُونِ ٱللَّهِ وَلَٰكِن تَصْدِيقَ ٱلَّذِى بَيْنَ يَدَيْهِ وَتَفْصِيلَ ٱلْكِتَٰبِ لَا رَيْبَ فِيهِ مِن رَّبِّ ٱلْعَٰلَمِينَ

ከገለጻቸውና ከዘረዘራቸው መካለል በዐቂዳህ ነጥብ፦ አላህ “እነሆ ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ የለም” በማለት ወደ ነቢያቱ ማውረዱ ነው፦
21፥25 ከአንተ በፊትም እነሆ *”ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና አምልኩኝ”* በማለት ወደ እርሱ *”የምናወርድለት”* ቢኾን እንጅ ከመልክተኛ አንድንም አልላክንም፡፡ وَمَآ أَرْسَلْنَا مِن قَبْلِكَ مِن رَّسُولٍ إِلَّا نُوحِىٓ إِلَيْهِ أَنَّهُۥ لَآ إِلَٰهَ إِلَّآ أَنَا۠ فَٱعْبُدُونِ
16፥2 ከባሮቹ በሚሻው ሰው ላይ መላእክትን ከራእይ ጋር በፈቃዱ ያወርዳል ከሓዲዎችን በቅጣት አስጠንቅቁ፤ *”እነሆ ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ የለም፤ ፍሩኝም”* ማለትን አስታውቁ በማለት ያወርዳል፡፡ يُنَزِّلُ ٱلْمَلَٰٓئِكَةَ بِٱلرُّوحِ مِنْ أَمْرِهِۦ عَلَىٰ مَن يَشَآءُ مِنْ عِبَادِهِۦٓ أَنْ أَنذِرُوٓا۟ أَنَّهُۥ لَآ إِلَٰهَ إِلَّآ أَنَا۠ فَٱتَّقُونِ

በፊቅህ ነጥብ ደግሞ አላህ ስለ “ጾምን፣ መልካም ሥራዎችን መሥራትን፣ ሶላትንም መስገድን፣ ዘካንም መስጠትን” ማውረዱን ነው፦
2፥183 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! *”ጾም በእነዚያ ከእናንተ በፊት በነበሩት ላይ እንደ ተጻፈ በእናንተም ላይ ተጻፈ፥ ልትጠነቀቁ ይከጀላልና”*፡፡ يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ كُتِبَ عَلَيْكُمُ ٱلصِّيَامُ كَمَا كُتِبَ عَلَى ٱلَّذِينَ مِن قَبْلِكُمْ لَعَلَّكُمْ تَتَّقُونَ
21፥73 *”ወደ እነርሱም መልካም ሥራዎችን መሥራትን፣ ሶላትንም መስገድን፣ ዘካንም መስጠትን አወረድን”*፡፡ وَأَوْحَيْنَآ إِلَيْهِمْ فِعْلَ ٱلْخَيْرَٰتِ وَإِقَامَ ٱلصَّلَوٰةِ وَإِيتَآءَ ٱلزَّكَوٰة

ከወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም

የበለጠ ለማወቅ
ጥሪያችን Tiriyachen
https://www.facebook.com/tiriyachen

ወሠላሙ ዐለይኩም
ልከውኛል ወይስ ልኮኛል?

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

4፥171 *”እናንተ የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! በሃይማኖታችሁ ወሰንን አትለፉ፡፡ በአላህም ላይ እውነትን እንጅ አትናገሩ”*፡፡ .. *”«ሦስት ናቸው» አትበሉም”*፡፡ ተከልከሉ፤ ለእናንተ የተሻለ ይኾናልና፡፡ *”አላህ አንድ አምላክ ብቻ ነው”*፡፡ يَٰٓأَهْلَ ٱلْكِتَٰبِ لَا تَغْلُوا۟ فِى دِينِكُمْ وَلَا تَقُولُوا۟ عَلَى ٱللَّهِ إِلَّا ٱلْحَقَّ ۚ إِنَّمَا ٱلْمَسِيحُ عِيسَى ٱبْنُ مَرْيَمَ رَسُولُ ٱللَّهِ وَكَلِمَتُهُۥٓ أَلْقَىٰهَآ إِلَىٰ مَرْيَمَ وَرُوحٌۭ مِّنْهُ ۖ فَـَٔامِنُوا۟ بِٱللَّهِ وَرُسُلِهِۦ ۖ وَلَا تَقُولُوا۟ ثَلَٰثَةٌ ۚ ٱنتَهُوا۟ خَيْرًۭا لَّكُمْ ۚ إِنَّمَا ٱللَّهُ إِلَٰهٌۭ وَٰحِدٌۭ ۖ سُبْحَٰنَهُۥٓ أَن يَكُونَ لَهُۥ وَلَدٌۭ ۘ لَّهُۥ مَا فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِى ٱلْأَرْضِ ۗ وَكَفَىٰ بِٱللَّهِ وَكِيلًۭا

የሥላሴ አማንያን ከባይብል የሥላሴ እሳቤ ለማግኘት የማይቆፍሩት ጉድጓድ፣ የማይፈነቅሉት ድንጋይ፣ የማይደረምሱት መሬት የለም። በተለይ የሥላሴ ሽታው እንኳን ከማይሸተው ከብሉይ ኪዳን ፍንጭ ለማግኘት ሲዳዱ ማየት ፈገግ ያሰኛል። የብሉይ ኪዳን ቀዳማይ ተዳራሲያን አይሁዳውያን እንጂ ክርስቲያኖች አይደሉም። ክርስቲያኖች ደኃራይ ተዳራሲያን እንደመሆናችሁ መጠን አይሁዳውያን ከሙሴ ጀምሮ ሥላሴ የሚባል አምላክ ሰብከው እንደማያውቁ ከባለቤቶቹ ቀረብ ብሎ መጠየቅ ነው። እስቲ ለዛሬ ሥላሴን ያሳያል ብለው ድምዳሜ ላይ አደረሰን ከሚሏቸው ጥቅሶች አንዱ እንይ፦
ኢሳይያስ 48፥16 ወደ እኔ ቅረቡ ይህንም ስሙ፤ እኔ ከጥንት ጀምሬ በስውር አልተናገርሁም፤ ከሆነበት ዘመን ጀምሮ እኔ በዚያ ነበርሁ፥ አሁንም *"አዶናይ ያህዌህ በመንፈሱ ልኮኛል"*። NET Bible
ዕብራይስጥ ማሶሬቲክ፦
אֲדֹנָי יְהוִה שְׁלָחַנִי--וְרוּחו
ግሪክ ሰፕቱጀንት፦
καὶ νῦν Κύριος ἀπέστειλέ με καὶ τὸ πνεῦμα αὐτοῦ.

የዕብራይስጡ ማሶሬቲክ እና ግሪክ ሰፕቱጀንት(LXX)፦ "አዶናይ ያህዌህ በመንፈሱ ልኮኛል" ብለው አስቀምጠውት ሳለ ሥላሴአውያን፦ "አዶናይ ያህዌህ እና መንፈሱ ልከውኛል" በማለት ሥላሴ ለመስራት ሞክረዋል።
"ሠላሐኒ" שְׁלָחַ֖נִי ማለት "ልኮኛል" ነው እንጂ "ልከውኛል" ማለት አይደለም። "ሠላሐ" שְׁלָחַ֖ ማለት "ላከ" ማለት ሲሆን ነጠላ ግስ ነው፥ ይህ ግስ በተመሳሳይ ነቢያት "ላከኝ" ላሉበት ግስ የተጠቀሙት ይህንን ግስ ነው፦
ዘፍጥረት 45፥5 አሁንም ወደዚህ ስለ ሸጣችሁኝ አትዘኑ፥ አትቈርቈሩም፤ እግዚአብሔር ሕይወትን ለማዳን ከእናንተ በፊት *"ልኮኛልና"* שְׁלָחַ֖נִי ።
2 ነገሥት 2፥2 ኤልያስም ኤልሳዕን፦ ያህዌህ ወደ ቤቴል *"ልኮኛልና"* שְׁלָחַ֖נִי በዚህ ቆይ፡ አለው።
ኤርምያስ 26፥12 ኤርምያስም ለአለቆችና ለሕዝቡ ሁሉ እንዲህ ብሎ ተናገረ፦ በሰማችሁት ቃል ሁሉ በዚህች ቤትና በዚህች ከተማ ላይ ትንቢት እናገር ዘንድ ያህዌህ *"ልኮኛልና"* שְׁלָחַ֖נִי ።

ብሉይ ላይ "ሠላሐኒ" שְׁלָחַ֖נִי የሚለው ቃል 26 ቦታ አለ፥ ሁሉም ጋር "ልኮኛል" ለማለት እንጂ "ልከውኛል" ለማለት በፍጹም አልተጠቀሙበት። ኢሳይያስ ላይ ግን የሥላሴ አማንያን ትርጉም ላይ ሆን ብለው የሥላሴን እሳቤ ለማዳበር የጨመሯት ነው። የላከ ለሚለው ነጠላ ቃል ብዜት "ላኩ" ነው፥ "ላኩ" ደግሞ "ሣላሁ" שָׁלְח֖וּ ነው፦
ኤርምያስ 14፥3 ታላላቆችም ብላቴኖቻቸውን ወደ ውኃ *"ላኩ"* שָׁלְח֖וּ ።

ኢሳይያስ "ልከውኛል" ለማለት ቢፈልግ ኖሮ "ሣላሁኒ" שָׁלְח֖וּנִי ይል ነበር፥ ቅሉ ግን አላለም። የያህዌህ መንፈሱ ከአፉ እና ከአፍንጫው የሚወጣ እስትንፋ ነው፦
ዘጸአት 15፥8 *”በአፍንጫህ እስትንፋስ”* ውኆች ተከመሩ፥ ፈሳሾችም እንደ ክምር ቆሙ፤ ሞገዱም በባሕር ውስጥ ረጋ፡፡
መዝሙር 33፥6 በእግዚአብሔር ቃል ሰማዮች ጸኑ፥ ሠራዊታቸውም ሁሉ *”በአፉ እስትንፋስ”*።

የያህዌህ እስትንፋስ ከያህዌህ በተለይ መልኩ እንደ ያህዌህ እራሱ የቻለ ማንነት"person" ከሆነ እርሱ ማን ነው? ያህዌህስ ከራሱ አፍ እና አፍንጫ ተሸንሽኖ የሚወጣ ሌላ ማንነት ካለው ያህዌህ አንድ ነው ከሚለው ትምህርት ጋር ይጣረሳል። ሲቀጥል አፍንጭ እና አፍ ሁለት ስለሆኑ ሁለት እስትንፋሶች ከወጡ በኃላ ተገጣጥመው ነው ወይስ ተለያይተው ነው ማንነት የሚሆኑት?
ሢሰልስ ኢሳይያስን የያህዌህ እስትንፋስ አላከውም፥ ግን ላከው ቢባል የሚያስደንቅ አይደለም። ምክንያቱም ከያህዌህ አፍ የምትወጣ ጥበብ ትልካለች፦
ምሳሌ 9፥1 *"ጥበብ ቤትዋን ሠራች"*፥ ሰባቱንም ምሰሶችዋን አቆመች።
ምሳሌ 9 3፤ *"ባሪያዎችዋን ልካ"* በከተማይቱ ከፍተኛ ስፍራ ላይ ጠራች።
ሉቃስ 11፥49 ስለዚህ ደግሞ *የእግዚአብሔር ጥበብ* እንዲህ አለች፦ ወደ እነርሱ ነቢያትንና ሐዋርያትን *እልካለሁ*፥ ከእነርሱም ይገድላሉ ያሳድዱማል፥

ያህዌህ መልእክቱን ለነቢያት የሚያስተላልፈው በመንፈሱ ነው፦
ዘካርያስ7፥12 የሠራዊትም ጌታ ያህዌህ *"በቀደሙት ነቢያት እጅ በመንፈሱ የላከውን ሕጉን እና ቃሉን"* እንዳይሰሙ ልባቸውን እንደ አልማዝ አጠነከሩ።

ላኪ ያህዌህ በመንፈሱ ከሆነ የተላከው ማን ነው? የተላከው ኢሳይያስ ነው። ዐውዱ ላይ፦ "ወደ እኔ ቅረቡ ይህንም ስሙ፤ እኔ ከጥንት ጀምሬ በስውር አልተናገርሁም፤ ከሆነበት ዘመን ጀምሮ እኔ በዚያ ነበርሁ" የሚለው ያህዌህ ነው። ከዚያ ኢሳይያስ፦ "አዶናይ ያህዌህ በመንፈሱ ልኮኛል" ይላል። ይህ የተለመደ አነጋገር በኢሳይያስ መጽሐፍ እንይ፦
ኢሳይያስ 50፥3-4 *"ሰማያትን ጥቍረት አለብሳቸዋለሁ፥ መጋረጃቸውንም ማቅ አደርጋለሁ። የደከመውን በቃል እንዴት እንደምደግፍ አውቅ ዘንድ አዶናይ ያህዌህ የተማሩትን ምላስ ሰጥቶኛል፥ ማለዳ ማለዳ ያነቃኛል፥ እንደ ተማሪዎችም ትሰማ ዘንድ ጆሮዬን ያነቃቃል"*።

"ሰማያትን ጥቍረት አለብሳቸዋለሁ፥ መጋረጃቸውንም ማቅ አደርጋለሁ" የሚለው ያህዌህ ሆኖ ሳለ እዛው ዐውድ ላይ፦ "የደከመውን በቃል እንዴት እንደምደግፍ አውቅ ዘንድ አዶናይ ያህዌህ የተማሩትን ምላስ ሰጥቶኛል፥ ማለዳ ማለዳ ያነቃኛል፥ እንደ ተማሪዎችም ትሰማ ዘንድ ጆሮዬን ያነቃቃል" የሚለው ኢሳይያስ ነው። መቼም፦ "አንዱ ያህዌህ ለሌላው ያህዌህ የተማረ ምላስ ሰጥቷል፣ ማለዳ ማለዳ ያነቃዋል፣ ጆሮውን ያነቃቃዋል" የሚል ቂል ያለ አይመስለኝም። ስለዚህ ከላይ ያለውን ጥቅስ በዚህ ስሌት ተረዱት። የሚያጅበው እኮ ኣ “አዶናይ” אֲדֹנָ֥י ማለት "ጌታዬ" ማለት ከሆነ ኢሳይያስ 48፥16 እና 50፥4 ላይ "ጌታዬ" የሚለው ኢሳይያስ እንጂ ሌላ ማንም አይደለም። ሲቀጥል “አዶኒም” אֲדֹנִ֣ים የብዙ ቁጥር ሆኖ ሲመጣ "ጌቶች" ማለት ከሆነ ሥላሴን ያሳያል ካላችሁ እንግዲያውስ መንፈሱ እና የተላከው ከሥላሴ ውጪ ነው። ቅሉ ግን "ጌታዬ" ያህዌህ ልኮኛል የሚለው ኢሳይያስ ሲሆን ላኪው ደግሞ ያህዌህ በመንፈሱ ነው።

በወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም

Follow us on:
https://fb.me/tiriyachen

ወሠላሙ ዐለይኩም
👍2
የሥላሴ አማንያን ከባይብል የሥላሴ እሳቤ ለማግኘት የማይቆፍሩት ጉድጓድ፣ የማይፈነቅሉት ድንጋይ፣ የማይደረምሱት መሬት የለም። በተለይ የሥላሴ ሽታው እንኳን ከማይሸተው ከብሉይ ኪዳን ፍንጭ ለማግኘት ሲዳዱ ማየት ፈገግ ያሰኛል። የብሉይ ኪዳን ቀዳማይ ተዳራሲያን አይሁዳውያን እንጂ ክርስቲያኖች አይደሉም። ክርስቲያኖች ደኃራይ ተዳራሲያን እንደመሆናችሁ መጠን አይሁዳውያን ከሙሴ ጀምሮ ሥላሴ የሚባል አምላክ ሰብከው እንደማያውቁ ከባለቤቶቹ ቀረብ ብሎ መጠየቅ ነው። እስቲ ለዛሬ ሥላሴን ያሳያል ብለው ድምዳሜ ላይ አደረሰን ከሚሏቸው ጥቅሶች አንዱ እንይ፦

... ይቀጥላል
====================
ሙሉ ጽሁፉን ጥሪያችን ድረገጽ ላይ ያገኙታል።
https://tiriyachen.org/ልከውኛል-ወይስ-ልኮኛል/
3
ይፍረዱ

አምላካችን አላህ ለዒሣ ወንጌልን ሰጠው፤ በዚያ ወንጌል ውስጥ፦ “የኢንጅልም ባለቤቶች በውስጡ አላህ ባወረደው ሕግ ይፍረዱ” የሚል መመሪያ አለ፦

5፥46 በፈለጎቻቸውም ላይ የመርየምን ልጅ ዒሳን ከተውራት በስተፊቱ ያለውን አረጋጋጭ ሲሆን *አስከተልን፤ ኢንጂልንም በውስጡ ቀጥታና ብርሃን ያለበት በስተፊቱ ያለችውን ተውራትንም የሚያረጋግጥ ለጥንቁቆችም መሪና ገሣጭ ሲሆን ሰጠነው*። وَقَفَّيْنَا عَلَىٰٓ ءَاثَٰرِهِم بِعِيسَى ٱبْنِ مَرْيَمَ مُصَدِّقًۭا لِّمَا بَيْنَ يَدَيْهِ مِنَ ٱلتَّوْرَىٰةِ ۖ وَءَاتَيْنَٰهُ ٱلْإِنجِيلَ فِيهِ هُدًۭى وَنُورٌۭ وَمُصَدِّقًۭا لِّمَا بَيْنَ يَدَيْهِ مِنَ ٱلتَّوْرَىٰةِ وَهُدًۭى وَمَوْعِظَةًۭ لِّلْمُتَّقِينَ

5፥47 የኢንጅልም ባለቤቶች በውስጡ *አላህ ባወረደው ሕግ ይፍረዱ*። وَلْيَحْكُمْ أَهْلُ ٱلْإِنجِيلِ بِمَآ أَنزَلَ ٱللَّهُ فِيهِ

... ይቀጥላል
====================
ሙሉ ጽሁፉን ጥሪያችን ድረገጽ ላይ ያገኙታል።
https://tiriyachen.org/ይፍረዱ/
አዲስ ዓመት
TIRIYACHEN
🎙 የድምፅ ትምህርት | 7.3 MB

አዲስ አመት

#Tiriyachen
#ንፅፅር_ሐይማኖት

ከዓቃቢ ኢስላም ወሒድ

የፈረንጆች አዲስ ዓመት ጃኑአርይ ነው። “ጃኑአርይ” ማለት “ጃኑስ” የተባለው ጣዖት የሚመለክበት ወር ነው። ይህ በዓል ጁለስ ቄሳር በ 46 ቅድመ-ልደት ስለጀመረው በዚህ ወር ዓመቱ ስለሚቀየር ጁሊያን የዘመን አቆጣጠር ይባላል።

መልካም ቆይታ ከጥሪያችን ጋር
‐‐‐
Follow us on:
‐‐‐
https://fb.me/tiriyachen
https://www.tg-me.com/tiriyachen
https://tiriyachen.org
https://bit.ly/3eVixKv
https://www.tiktok.com/@tiriyachen
ዒባዳህ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

51፥56 *ጂኒን እና ሰውንም ሊያመልኩኝ እንጅ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም*፡፡ وَمَا خَلَقْتُ الْجِنَّ وَالْإِنسَ إِلَّا لِيَعْبُدُونِ

“ዒባዳህ” عِبَادَة የሚለው ቃል “ዓበደ عَبَدَ ማለትም “አመለከ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "አምልኮ" ማለት ነው። ዒባዳህ ማለት በቀልብያ፣ በቀውልያ፣ በዐመልያ ለአንድ ምንነት እና ማንነት የሚደረግ ማጎብደድ፣ ማሸርገድ፣ መተናነስ ነው። የመስኩ ልሂቃን፦ "አምልኮ" ማለት "ለአንድ ምንነትና ማንነት በፍጹም ሁለንተናዊነት ማለትም በኃልዮ፣ በነቢብ፣ በገቢር መገዛት ነው" ይላሉ።
ዒባዳህ በተመላኪ እና በአምላኪ መካከል ያለ መርሕ ነው፥ "መዕቡድ" مَعْبُد ማለት "ተመላኪ" ማንነት ማለት ሲሆን “ዐብድ” عَبْد ወይም “ዐቢድ” عَابِد ደግሞ "አምላኪ" ማንነት ነው። አምላካችን አላህ በመጀመሪያ መደብ ብዙ ቦታ "አምልኩኝ" እያለ ይናገራል፦
29፥56 እናንተ ያመናችሁ ባሮቼ ሆይ! ምድሬ በእርግጥ ሰፊ ናት፤ ብትቸገሩ ተሰደዱ፡፡ *”እኔንም ብቻ አምልኩኝ”*፡፡ يَٰعِبَادِىَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ إِنَّ أَرْضِى وَٰسِ

... ይቀጥላል
====================
ሙሉ ጽሁፉን ጥሪያችን ድረገጽ ላይ ያገኙታል።
https://tiriyachen.org/ዒባዳህ/
👍2
ነጻ ፈቃድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

18፥29 *«እውነቱም ከጌታችሁ ነው፡፡ የሻም ሰው ይመን፤ የሻም ሰው ይካድ»* በላቸው፡፡ وَقُلِ الْحَقُّ مِن رَّبِّكُمْ فَمَن شَاءَ فَلْيُؤْمِن وَمَن شَاءَ فَلْيَكْفُر

“ሻእ” شَآء ማለት “ፈቃድ” ማለት ሲሆን አምላካችን አላህ በፍጥረተ-ዓለማት ውስጥ የሚሻውን ይፈጥራል፦
24፥45 *አላህ የሚሻውን ሁሉ ይፈጥራል፡፡ አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነውና*፡፡ يَخْلُقُ اللَّهُ مَا يَشَاءُ إِنَّ اللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِير
86፥16 *የሚሻውን ሁሉ ሠሪ ነው*፡፡ فَعَّالٌ لِّمَا يُرِيدُ
5፥17 *የሚሻውን ይፈጥራል፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው*፡፡ يَخْلُقُ مَا يَشَاءُ وَاللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ
3፥47 *አላህ የሚሻውን ይፈጥራል፡፡ አንዳችን በሻ ጊዜ ለርሱ ኹን ይለዋል፤ ወዲውኑም ይኾናል አላት*፡፡ قَالَ كَذَٰلِكِ اللَّهُ يَخْلُقُ مَا يَشَاءُ إِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ

"የሚሻውን" ለሚለው ቃል የገባው "የሻኡ" يَشَاءُ ማለትም "የሚፈቅደውን" ነው። ማንኛውም ነገር ሲከሰት፣ ሲከናወንና ሲሆን አላህ ፈቅዶ ነው፥ ያለ አላህ ፈቃድ ምንም እኩይ ወይም ሰናይ ነገር አይከሰትም፤ አይከናወንም፣ አይሆንም። የአላህ ፈቃድ በሁለት መልክ ለፍጡራን ሆኗል፥ አንዱ ያለፈቃዳቸው ሲሆን ሁለተኛው በተሰጣቸው ነጻ ፈቃድ ላይ ነው።

... ይቀጥላል
====================
ሙሉ ጽሁፉን ጥሪያችን ድረገጽ ላይ ያገኙታል።

https://tiriyachen.org/ነጻ-ፈቃድ/
2025/07/10 17:41:27
Back to Top
HTML Embed Code: