Telegram Web Link
አዲስ ዓመት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

7፥3 *ከጌታችሁ ወደ እናንተ የተወረደውን ተከተሉ*። اتَّبِعُوا مَا أُنزِلَ إِلَيْكُم مِّن رَّبِّكُمْ

የፈረንጆች አዲስ ዓመት ጃኑአርይ ነው። “ጃኑአርይ” ማለት “ጃኑስ” የተባለው ጣዖት የሚመለክበት ወር ነው። ይህ በዓል ጁለስ ቄሳር በ 46 ቅድመ-ልደት ስለጀመረው በዚህ ወር ዓመቱ ስለሚቀየር ጁሊያን የዘመን አቆጣጠር ይባላል። ቁጥሩ ደግሞ ኢየሱስ ከተወለደበት ጀምሮ የሚቆጠር የክርስትና በዓል ያደረገው በ 1582 ድኅረ-ልደት ግሪጎሪ ወይም ጎርጎርዮስ የተባለው ጳጳስ ነው፥ በዚህም የጎርጎሮሳውያን አቆጣጠር ይባላል። ይህ ዓመታዊ በዓል ዓረማዊ እና ክርስትናን ቀላቅሎ የያዘ በዓል ነው፥ በዚህ ጊዜ "እንኳን አደረስን" ወይም "እንኳን አደረሳችሁ" ስንል ይህንን በዓል ታሳቢ እና ዋቢ ያደረገ ነው። ሙሥሊም ያሉት ዓመታዊ በዓል ሁለት ብቻ ናቸው፥ እነርሱም ዒዱል ፊጥር እና ዒዱል አድሓ ናቸው፦
ሡነን አቢ ዳዉድ መጽሐፍ 2, ሐዲስ 745
አነሥ ኢብኑ ማሊክ እንደተረከው፤ የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” መዲና ሲገቡ የመዲና ሠዎች የሚደሰቱባቸው ሁለት በዓላት እንዳሏቸው አወቁ። እርሳቸውም እነዚህ ሁለቱ ቀናት ምንድን ናቸው? በማለት ጠየቁ፤ ሰዎችም በጃሂሊያ ጊዜ እንጫወትባቸው የነበሩ በዓላት ናቸው አሏቸው። የአላህ መልእክተኛም”ﷺ”፦ *”አላህ ከእነርሱ የተሻሉ ሁለት ዒዶችን ሠጥቷችኋል፤ እነርሱም፦ ዒዱል ፊጥር እና ዒዱል አድሓን። አሏቸው”*። عَنْ أَنَسٍ، قَالَ قَدِمَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم الْمَدِينَةَ وَلَهُمْ يَوْمَانِ يَلْعَبُونَ فِيهِمَا فَقَالَ ‏”‏ مَا هَذَانِ الْيَوْمَانِ ‏”‏ ‏.‏ قَالُوا كُنَّا نَلْعَبُ فِيهِمَا فِي الْجَاهِلِيَّةِ ‏.‏ فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ إِنَّ اللَّهَ قَدْ أَبْدَلَكُمْ بِهِمَا خَيْرًا مِنْهُمَا يَوْمَ الأَضْحَى وَيَوْمَ الْفِطْرِ ‏”‏ ‏.‏
ጃሚዒ አት-ቲርሚዚህ መጽሐፍ 8, ሐዲስ 121
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *“ዒዱል ፈጥር ሰዎች ጾም የሚፈቱበት ነው፤ ዒዱል አደሐ ደግሞ መስዋዕት የሚያቀርቡበት ቀን ነው”*። عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ الْفِطْرُ يَوْمَ يُفْطِرُ النَّاسُ وَالأَضْحَى يَوْمَ يُضَحِّي النَّاسُ ‏”‏
ጃሚዒ አት-ቲርሚዚህ መጽሐፍ 8, ሐዲስ 91
አቡ ሰዒደል ኹድሪይ እንደተረከው፥ የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” *”በሁለቱ በዓል በዒደል አደሐ እና ዒደል ፈጥር መጾም ከልክለዋል”*። عَنْ أَبِي سَعِيدٍ الْخُدْرِيِّ، قَالَ نَهَى رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم عَنْ صِيَامَيْنِ يَوْمِ الأَضْحَى وَيَوْمِ الْفِطْرِ ‏.

“ዒድ” عِيد የሚለው ቃል “ዓደ” عَادَ ማለትም “ተመላለሰ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ምልሰት” ማለት ነው፥ ይህ “መደሰቻ” ወይም “በዓል” በየዓመቱ ስለሚመላለስ ይህንን ስያሜ አግኝቷል። ስለዚህ ከአላህ የወረዱትን ቁርኣን እና ሐዲስ ብቻ መከተል አለብን፦
7፥3 *ከጌታችሁ ወደ እናንተ የተወረደውን ተከተሉ*። اتَّبِعُوا مَا أُنزِلَ إِلَيْكُم مِّن رَّبِّكُمْ

“ተከተሉ” የሚለው ቃል “ኢተቢዑ” اتَّبِعُوا ሲሆን “ኢትባዕ” إِتْبَاع‎ ማለት ከአላህ ወደ ነቢያችን”ﷺ” የተወረደውን ብቻ መከተል ማለት ነው። ሙሥሊም የተወረደውን ብቻ ሲከተል ሁለት ብቻ ዒድ ያከብራል።

ከኡሥታዝ ወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም

Follow us on:
https://fb.me/tiriyachen
https://www.tg-me.com/tiriyachen
https://tiriyachen.org
https://bit.ly/3eVixKv
https://www.tiktok.com/@tiriyachen

ወሠላሙ ዐለይኩም
👍1
የስቅለት ውዝግብ

የአዲስ ኪዳን ምሁር ሄርማን ቻርለስ በ 1890 AD ሲናገሩ፦ 5,800 የሚደርሱ የአዲስ ኪዳን ግሪክ እደ-ክታባት ይገኛሉ፤ እነዚህ እደ-ክታባት እርስ በእርሳቸው የቃላት ሆነ የትርጉም ልዩነት አላቸው፤ ለምሳሌ በሳይናቲከስና በቫቲካነስ እደ-ክታባት መካከል የ 3,036 የቃላትና የትርጉም ልዩነት አላቸው ብለዋል፤ ይህ ልዩነት የመጣው የአዲስ ኪዳን ስረ-መሰረት”orgion” ስለሌለና አሁን ያለት እደ-ክታባት የቅጂዎች ቅጂ ስለሆነ እንደሆነ ምሁራን ይናገራሉ፤ ይህ ልዩነት ጤናማ አለመሆን ብቻ ሳይሆን የክርስትናን ዶግማ ክፉኛ ይፈታተናል፤ ምክንያቱም እነዚህን አራት ወንጌላት ሃዋርያት አለመፃፋቸው ብቻ ሳይሆን በእነርሱ የዳቦ ስም የገለበጡት ፅሁፍም ችግር ስላለበት ነው፤ እስቲ ይህንን ልዩነት ዛሬ በስቅለቱ ዙሪያ ያሉትን ዘገባዎች እንመልከት፦

ነጥብ አንድ
“የቤተ መቅደስም መጋረጃ”
የሉቃስ ዘጋቢ ኢየሱስም በታላቅ ድምፅ ጮኾ ህይወቱን የሰጠው የቤተ መቅደስም መጋረጃ ከመካከሉ ከላይ እስከ ታች ለሁለት ከተቀደደ በኃላ እንደሆነ ይተርካል፦
ሉቃስ 23፥45-46 “የቤተ መቅደስም መጋረጃ ከመካከሉ ተቀደደ”። ኢየሱስም በታላቅ ድምፅ ጮኾ፦ አባት ሆይ፥ ነፍሴን በእጅህ አደራ እሰጣለሁ አለ። ይህንም ብሎ ነፍሱን ሰጠ።

የማቴዎስ ዘገቢ ኢየሱስም በታላቅ ድምፅ ጮኾ ህይወቱን የሰጠው የቤተ መቅደስም መጋረጃ ከመካከሉ ከላይ እስከ ታች ለሁለት ከመቀደዱ በፊት እንደሆነ ይተርካል፦
ማቴዎስ 27፥ 50-51 ኢየሱስም ሁለተኛ በታላቅ ድምፅ ጮኾ ነፍሱን ተወ። እነሆም፥ “የቤተ መቅደስ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ከሁለት ተቀደደ”፥ ምድርም ተናወጠች፥ ዓለቶችም ተሰነጠቁ፤

ጥያቄአችን፦ የቱ ትረካ ነው ትክክል? ኢየሱስም በታላቅ ድምፅ ጮኾ ህይወቱን የሰጠው የቤተ መቅደስም መጋረጃ ከመካከሉ ከላይ እስከ ታች ለሁለት ከተቀደደ በኃላ እንደሆነ የሚተርክልን የሉቃስ ዘጋቢ ወይስ ኢየሱስም በታላቅ ድምፅ ጮኾ ህይወቱን የሰጠው የቤተ መቅደስም መጋረጃ ከመካከሉ ከላይ እስከ ታች ለሁለት ከመቀደዱ በፊት እንደሆነ የሚተርክልን የማቴዎስ ዘጋቢ?

ነጥብ ሁለት
“በሰቀሉትም ጊዜ”
ቅድሚያ የአራቱ ወንጌላት ተራኪዎች ጊዜን የሚቆጥሩት በዕብራውያን አቆጣጠር ብቻ መሆኑ ሊጤን የሚገባው ጉዳይ ነው፤ የሮማውያን አቆጣጠር አንዳንዶች ይጠቀሙ ነበር የሚለው ቅጥፈት የታሪክ፣ የአውድና የባህል ማስረጃ የለውም፤ ይህ ቅጥፈት ግጭትን ለመደበቅ ሆን ብሎ ግምታዊ ነው፤ ለምሳሌ ማርቆስ የዕብራዊያን አቆጣጠሩ ኢየሱስ ተሰቀለ የተባለበት በዕብራውያን 3 ሰአት ነው ይለናል፦
ማርቆስ 15፥25 “”በሰቀሉትም ጊዜ” “”ሦስት ሰዓት”” ነበረ።
ማርቆስ 15፥33 “ስድስት ሰዓትም”” በሆነ ጊዜ፥ እስከ “”ዘጠኝ ሰዓት”” በምድር ሁሉ ላይ ጨለማ ሆነ።
34 “”በዘጠኝ ሰዓትም”” ኢየሱስ፦ ኤሎሄ፥ ኤሎሄ፥ ላማ ሰበቅታኒ? ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ፤

በዚህ ሁለም ይስማማል፤ ኢየሱስ ተሰቀለ የተባለው ከ ቀኑ ጠዋት 3 ሰአት ነው፤ ከዮሃንስ ዘገባ ጋር ፍጭቱን ከማየታችን በፊት ዮሃንስ የሚጠቀመው የዕብራውያን አቆጣጠር መሆኑን በአፅንኦትና በአንክሮት እንመልከት፦
ዮሐንስ 1፥40 መጥታችሁ እዩ አላቸው። መጥተው የሚኖርበትን አዩ፥ በዚያም ቀን በእርሱ ዘንድ ዋሉ፤ “አሥር ሰዓት” ያህል ነበረ።
ዮሐንስ 4፥6 በዚያም የያዕቆብ ጕድጓድ ነበረ። ኢየሱስም መንገድ ከመሄድ ደክሞ በጕድጓድ አጠገብ እንዲህ ተቀመጠ፤ “”ጊዜውም ስድስት ሰዓት”” ያህል ነበረ።

ድካም ያለበት ቀትር ስድስት ሰአት የዕብራውያን አቆጣጠር እንጂ የሮማውያን አቆጣጠር አይደለም፤ ምክንያቱም የሮማውያን ስድስት ሰአት የዕብራውያን ከምሽቱ 12 ሰአት አሊያም ከጎህ 12 ሰአት ነው፤ ይህን ሃቅ ይዘን የዮሃንስ ዘጋቢ ጋር ኢየሱስ ስድስት ሰአት ላይ እንኳን ሊሰቀል ይቅርና ገና ህዝቡ ስቀለው እያሉ ይጮኹ እንደነበር ይተርካል፦
ዮሃንስ 19፥14-15 ለፋሲካም የማዘጋጀት ቀን ነበረ፤ “ስድስት ሰዓትም” የሚያህል ነበረ፤ አይሁድንም፦ እነሆ ንጉሣችሁ አላቸው። እነርሱ ግን፦ አስወግደው፥ አስወግደው፥ “”ስቀለው”” እያሉ ጮኹ።

ጥያቄአችን፦ የቱ ትረካ ነው ትክክል? በሰቀሉት ጊዜ 3 ሰአት ነበረ ብሎ የሚተርከው የማርቆስ ዘጋቢ ወይስ 6 ሰአት ላይ ገና አልተሰቀለም ብሎ የሚተርከው የዮሃንስ ዘጋቢ?

ነጥብ ሶስት
“ሶስት ቀን”
ኢየሱስ የአላህ ነብይ ነው አይዋሽም፤ መቼም አራቱ ወንጌላት ላይ ያሉት ቃላት አይደለም የኢየሱስ ይቅርና የመጀመሪያዎቹ ፀሃፊያን ያልሆኑ ንግግሮች በእማኝነትና በአስረኝነት ማቅረብ ይቻላል፤ ነገር ግን ነጥባችን እርሱ አይደለም፤ ኢየሱስ ተናገረ ተብሎ የተቀጠፈበት ነገር እርስ በእርሱ ይጋጫል፤ እንደ ማርቆስ ዘጋቢ ኢየሱስ ይነሳል የተባለው “ከሦስት ቀንም “”በኋላ”” ተብሎ ነው፤ ልብ አድርጉ “በኃላ” የሚለው መስተዋድድ በአራተኛው ቀን አሊያም በአምስተኛው ቀን ሊሆን ይችላል፤ ግን ሶስኛውን ቀን አይጨምርም፦
ማርቆስ 8፥31 የሰው ልጅ ብዙ መከራ ሊቀበል፥ ከሽማግሌዎችም ከካህናት አለቆችም ከጻፎችም ሊጣል፥ ሊገደልም “ከሦስት ቀንም “”በኋላ”” ሊነሣ” እንዲገባው ያስተምራቸው ጀመር፤ ቃሉንም ገልጦ ይናገር ነበር።

የማቴዎ ዘጋቢ ደግሞ ኢየሱስ ይነሳል የተባለው “በ”ሦስተኛውም ቀን”” ተብሎ ነው፤ ልብ አድርጉ “በ” የሚለው መስተዋድድ ሶስተኛውን ቀን ብቻ የሚያመለክት ነው፦
ማቴዎስ 16፥21 ከዚያን ቀን ጀምሮ ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም ይሄድ ዘንድ ከሽማግሎችና ከካህናት አለቆች ከጻፎችም ብዙ መከራ ይቀበልና ይገደል ዘንድ “”በሦስተኛውም ቀን” ይነሣ ዘንድ እንዲገባው ለደቀ መዛሙርቱ ይገልጥላቸው ጀመር።

ጥያቄአችን፦ የቱ ትረካ ነው ትክክል? ኢየሱስ ይነሳል የተባለው “ከሦስት ቀንም “”በኋላ”” ነው ብሎ የሚተርከው የማርቆስ ዘጋቢ ወይስ ኢየሱስ ይነሳል የተባለው “በ”ሦስተኛውም ቀን”” ነው ብሎ የሚተርከው የማቴዎስ ዘጋቢ?

ኡሥታዝ ወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም

ጥሪያችን Tiriyachen
https://fb.me/tiriyachen
ኢብሊሥ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

18፥50 ለመላእክትም ለአደም ስገዱ፥ ባልናቸው ጊዜ የሆነውን አስታውስ ። ወዲያውም ሰገዱ፤ *ኢብሊስ ብቻ ሲቀር ከጂን ነበር፤ ከጌታውም ትእዛዝ ወጣ"*፡፡ وَإِذْ قُلْنَا لِلْمَلَائِكَةِ اسْجُدُوا لِآدَمَ فَسَجَدُوا إِلَّا إِبْلِيسَ كَانَ مِنَ الْجِنِّ فَفَسَقَ عَنْ أَمْرِ رَبِّهِ

“ጂን” جِنّ የሚለው ቃል “ጀንነ” جَنَّ ማለትም “ተሰወረ” ወይም “ተደበቀ” ከሚል ግስ የመጣ ሲሆን “ስውር” ወይም “ድብቅ” ማለት ነው፤ “ጅኒ” جني ደግሞ የጂን ብዙ ቁጥር ነው፤ ጂኒዎች የተፈጠሩት ከሰው በፊት ነው፤ ሰው የተፈጠረበት ንጥረ-ነገር ዐፈር እንደሆነ፤ መልአክ የተፈጠረበት ንጥረ-ነገር ብርሃን እንደሆነ ሁሉ ጂን የተፈጠረበት ንጥረ-ነገር ደግሞ እሳት ነው፦
15፥27 *ጃንንም ከሰው በፊት ከእሳት ነበልባል ፈጠርነው*፡፡ وَالْجَانَّ خَلَقْنَاهُ مِن قَبْلُ مِن نَّارِ السَّمُومِ
ኢማም ሙስሊም መጽሐፍ 55, ሐዲስ 78
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”መላእክት ከብርሃን ተፈጥረዋል፤ ጂንዎች ከእሳት ነበልባል ተፈጥረዋል፤ አደም ለእናንተ እንደተገለጸላችሁ ከሚጭለቀለቅ ሸክላ ተፈጥሯል”*፡፡ عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم‏ خُلِقَتِ الْمَلاَئِكَةُ مِنْ نُورٍ وَخُلِقَ الْجَانُّ مِنْ مَارِجٍ مِنْ نَارٍ وَخُلِقَ آدَمُ مِمَّا وُصِفَ لَكُمْ ‏.‏

ጂኒዎች የተፈጠሩበት አላማ የፈጠራቸው አላህ እንዲያመልኩ ነው፦
51፥56 *ጂኒን እና ሰውንም ሊያመልኩኝ እንጅ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም*፡፡ وَمَا خَلَقْتُ الْجِنَّ وَالْإِنسَ إِلَّا لِيَعْبُدُونِ

“ኢብሊሥ” إِبْلِيس በተፈጥሮው ከሰው ወይም ከመልአክ ሳይሆን ከጂን ሲሆን በመጥፎ ባህርይው ደግሞ “ሸይጧን” ነው፤ ለአደም አልሰግድም ብሎ በአላህ ላይ ያመጸው እርሱ ነው፦
18፥50 ለመላእክትም ለአደም ስገዱ፥ ባልናቸው ጊዜ የሆነውን አስታውስ ። ወዲያውም ሰገዱ፤ *ኢብሊስ ብቻ ሲቀር ከጂን ነበር፤ ከጌታውም ትእዛዝ ወጣ"*፡፡ وَإِذْ قُلْنَا لِلْمَلَائِكَةِ اسْجُدُوا لِآدَمَ فَسَجَدُوا إِلَّا إِبْلِيسَ كَانَ مِنَ الْجِنِّ فَفَسَقَ عَنْ أَمْرِ رَبِّهِ

"ከጂን ነበር" የሚለው ሃይለ-ቃል ይሰመርበት። አምላካችን አላህ "ለመላእክትም ለአደም ስገዱ" ብቻ ሳይሆን ለኢብሊስም ስገድ ብሎታል፥ ይህንን ማለቱ እዚሁ አንቀጽ ላይ፦ "ከጌታውም ትእዛዝ ወጣ" በማለት አላህ አዞት እንደነበር ይናገራል፦
አላህ፦ *«ባዘዝኩህ ጊዜ ከመስገድ ምን ከለከለህ?» አለው"*፡፡ «እኔ ከእርሱ የበለጥኩ ነኝ፡፡ ከእሳት ፈጠርከኝ፡፡ እርሱን ግን ከጭቃ ፈጠርከው» አለ፡፡ قَالَ مَا مَنَعَكَ أَلَّا تَسْجُدَ إِذْ أَمَرْتُكَ ۖ قَالَ أَنَا خَيْرٌ مِّنْهُ خَلَقْتَنِي مِن نَّارٍ وَخَلَقْتَهُ مِن طِينٍ

"ባዘዝኳችሁ ጊዜ ከመስገድ ምን ከለከለህ? ሳይሆን "ባዘዝኩህ ጊዜ ከመስገድ ምን ከለከለህ? አለው፥ "ባዘዝኩህ" የሚለው ሃይለ-ቃል ለአደም ስገድ ብሎ አዞት እንደነበር ቁልጭና ፍንትው አድርጎ ያሳይል። "ለመላእክትም ብቻ ለአደም ስገዱ" ቢል ኖሮ "ብቻ" የሚለው ገላጭ ቅጽል ስላለ አደም ከመላእክት ነበር ብለን እንደመድም ነበር። ነገር ግን "ለ" የሚለው መስተዋድድ መኖሩ በራሱ ለመላእክት ብቻ የሚለውን አያሲዝም። ለምሳሌ፦
7፥179 ከጂኒም ከሰዎችም ብዙዎችን ለገሀነም በእርግጥ ፈጠርን፡፡ *"ለ"እነርሱ ልቦች አሏቸው፥ ግን አይገነዘቡበትም፡፡ "ለ"እነርሱም ዓይኖች አሉዋቸው፥ ግን ዐያዩበትም፡፡ "ለ"እነርሱም ጆሮዎች አሉዋቸው ግን አይሰሙበትም"*፡፡ ይልቁንም እነርሱ በጣም የተሳሳቱ ናቸው፡፡ እነዚያ ዘንጊዎቹ እነርሱ ናቸው። وَلَقَدْ ذَرَأْنَا لِجَهَنَّمَ كَثِيرًا مِّنَ الْجِنِّ وَالْإِنسِ ۖ لَهُمْ قُلُوبٌ لَّا يَفْقَهُونَ بِهَا وَلَهُمْ أَعْيُنٌ لَّا يُبْصِرُونَ بِهَا وَلَهُمْ آذَانٌ لَّا يَسْمَعُونَ بِهَا ۚ أُولَـٰئِكَ كَالْأَنْعَامِ بَلْ هُمْ أَضَلُّ ۚ أُولَـٰئِكَ هُمُ الْغَافِلُون

"ለሁም ቁሉብ" لَهُمْ قُلُوب "ለሁም አዕዩን" لَهُمْ أَعْيُن "ለሁም አዛን" آذَانٌ የሚሉትን ቁልፍ ቃላት አስምሩበት። "ለ"ዘንጊዎች ልቦች፣ ዓይኖች እና ጆሮዎች አሉዋቸው ማለት ሌላው ልቦች፣ ዓይኖች እና ጆሮዎች የለውም የሚለውን እንደማያሲዝ ሁሉ ለመላእክት ስገዱ ማለቱ ለኢብሊስ ስገድ አለማለቱን አያሲዝም። "ለ" የሚለው መስተዋድድ በመነሻ ቅጥያ መምጣቱ "ብቻ" የሚለውን መደምደሚያ አያስደርስም። ሲቀጥል "ኢብሊስ ብቻ ሲቀር" በሚለው ሃይለ-ቃል ላይ "ሲቀር" የምትለዋን ይዘን ኢብሊስ ከመላእክት ነበር ማለት አሁንም የቁርኣንን ሰዋስው ካለመረዳት የሚመጣ ጥራዝ-ነጠቅ ዕውቀት ነው፦
26፥77 *"«እነርሱም ለእኔ ጠላቶች ናቸው፡፡ ግን የዓለማት ጌታ ሲቀር እርሱ ወዳጄ ነው"*፡፡ فَإِنَّهُمْ عَدُوٌّ لِّي إِلَّا رَبَّ الْعَالَمِينَ

ኢብራሂም፦ "ለእኔ ጠላቶች ናቸው። ግን የዓለማት ጌታ ሲቀር" ማለቱን አስተውል። "ሲቀር" የሚለውን አፍራሽ ቃል ይዘን ከዓለማቱ ጌታ ውጪ ለኢብራሂም ሁሉም ጠላት ነውን? አማንያን፣ ነቢያት፣ መላእክት፣ እንስሳትስ ጠላት ናቸውን? አይ "በቀር" የሚለው የአላህን ወዳጅ ለመሆን የገባ እንጂ "ሁሉን ጠላት ናቸው ከአላህ በቀር" ማለቱን አያሳይም ከተባለ እንግዲያውስ "በቀር" የሚለው ኢብሊስ ብቻ አለመታዘዙን እንጂ መላእክት ውስጥ መካተቱን አያሳይም።
ከመነሻው መላእክት በባሕያቸው ውስጥ ኩራትና አመጽ የለም፦
16፥49 ለአላህም በሰማያት ያለው ከተንቀሳቃሽም በምድር ያለው ሁሉ፣ *"መላእክትም ይሰግዳሉ፡፡ እነርሱም አይኮሩም"*፡፡ وَلِلَّهِ يَسْجُدُ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ مِن دَابَّةٍ وَالْمَلَائِكَةُ وَهُمْ لَا يَسْتَكْبِرُونَ
21፥19 በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉም የእርሱ ነው፡፡ *"እርሱ ዘንድ ያሉትም መላእክት እርሱን ከመገዛት አይኮሩም"*፡፡ አይሰለቹምም፡፡ وَلَهُ مَن فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۚ وَمَنْ عِندَهُ لَا يَسْتَكْبِرُونَ عَنْ عِبَادَتِهِ وَلَا يَسْتَحْسِرُونَ
66፥6 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ነፍሶቻችሁንና ቤተሰቦቻችሁን መቀጣጠያዋ ሰዎችና ደንጋዮች ከኾነች እሳት ጠብቁ፡፡ በእርሷ ላይ ጨካኞች፣ ኀይለኞች የኾኑ መላእክት አሉ፡፡ *"አላህ ያዘዛቸውን ነገር በመጣስ አያምጹም፤ የሚታዘዙትንም ሁሉ ይሠራሉ"*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا قُوا أَنفُسَكُمْ وَأَهْلِيكُمْ نَارًا وَقُودُهَا النَّاسُ وَالْحِجَارَةُ عَلَيْهَا مَلَائِكَةٌ غِلَاظٌ شِدَادٌ لَّا يَعْصُونَ اللَّهَ مَا أَمَرَهُمْ
👍1
وَيَفْعَلُونَ مَا يُؤْمَرُونَ

መላእክት አላህ ያዘዛቸውን ነገር በመጣስ አያምጹም፤ የሚታዘዙትንም ሁሉ ይሠራሉ። ኢብሊስ ግን ከመላእክት ስልላሆነ ኮራ፥ በጌታውም ትእዛዝ አመጸ፦
38፥74 ኢብሊስ ብቻ ሲቀር፡፡ *"ኮራ"*፤ ከከ-ሓ-ዲ-ዎ-ቹ-ም ነበር፡፡ إِلَّا إِبْلِيسَ اسْتَكْبَرَ وَكَانَ مِنَ الْكَافِرِينَ
18፥50 ለመላእክትም ለአደም ስገዱ፥ ባልናቸው ጊዜ የሆነውን አስታውስ ። ወዲያውም ሰገዱ፤ *ኢብሊስ ብቻ ሲቀር ከጂን ነበር፤ ከጌታውም ትእዛዝ ወጣ"*፡፡ وَإِذْ قُلْنَا لِلْمَلَائِكَةِ اسْجُدُوا لِآدَمَ فَسَجَدُوا إِلَّا إِبْلِيسَ كَانَ مِنَ الْجِنِّ فَفَسَقَ عَنْ أَمْرِ رَبِّهِ

ይህንን ሊገባችሁ በሚችለው መልኩ ከራሳችሁ ባይብል ላሳያችሁ፦
ዘፍጥረት 2፥16-18 *"እግዚአብሔር አምላክም ሰውን እንዲህ ብሎ አዘዘው፦ ከገነት ዛፍ ሁሉ ትበላለህ፤ ነገር ግን መልካምንና ክፉን ከሚያስታውቀው ዛፍ አትብላ፤ ከእርሱ በበላህ ቀን ሞትን ትሞታለህና"*። እግዚአብሔር አምላክም አለ፦ ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም፤ የሚመቸውን ረዳት እንፍጠርለት።

እግዚአብሔር አደምን መልካምንና ክፉን ከሚያስታውቀው ዛፍ "አትብላ" ብሎ ሲያዘው ሔዋን አልተፈጠረችም። ነገር ግን ሔዋን "አትብሉ" ብሎናል ብላለች፦
ዘፍጥረት 3፥2 ሴቲቱም ለእባቡ አለችው፦ በገነት ካለው ከዛፍ ፍሬ እንበላለን፤ ነገር ግን በገነት መካከል ካለው ከዛፉ ፍሬ፥ *"እግዚአብሔር አለ፦ "እንዳትሞቱ ከእርሱ አትብሉ አትንኩትም"*።

"አትብላ" ብሎ ያዘዘው አዳምን ብቻ ሆኖ ሳለ "አትብላ" የሚለውን "አትብሉ" በሚል ስላስቀመጠች ሁለቱንም አዟቸው ነበር ይባላል እንጂ ሔዋን አዳም ናት ይባላልን? ሔዋንን ሲያዛት የሚያሳይ ጥቅስ አለመኖሩ ሔዋንን አለማዘዙን ያሳያልን? በፍጹም! እንግዲያውስ ከላይ ያለውን የቁርኣን አንቀጽ በዚህ ሒሳብ ተረዱት። ኢብሊስ በፍጹም መልአክ አልነበረም።
በተጨማሪም በአሌክሳድሪየስ ኮዴክስ በሚገኘው በሮሙ ክሌመንት ማለትም በቀለሚንጦስ ደግሞ የሰገዱት እግዚአብሔር የፈጠረው ሁሉ እንደሆነ ተገልጿል፦
ክሌመንት 1፥41 አራዊት፣ እንስሳት ወፎች *”እግዚአብሔር የፈጠረው ሁሉ"* ወደ አዳም ተሰበሰቡ ከፊቱ ቁመው ራሳቸውን አዘነበሉ፤ *ለአዳምም ሰገዱ"*።

ሰይጣን ለአዳም ከእግዚአብሔር የተሰጠውን ኃብተ ፀጋ ማለትም “ሁሉም ፍጥረት መስገዳቸው” ባየ ጊዜ ከዚያ ሰአት ጀምሮ ቅንአት አደረበት፤ እግዚአብሔር በሰይጣን ላይ የነበረውን የምስጋና ልብስ እና የግርማ ልዕልና አስወገደ፤ ሰይጣን ብሎ ሰየመው፦
ክሌመንት 1፥46 *"ሰይጣን ለአዳም ከእግዚአብሔር የተሰጠውን ኃብተ ፀጋ ባየ ጊዜ ከዚያ ሰአት ጀምሮ ቅንአት አደረበት"*።
ክሌመንት 1፥47 *"በዚህ ጊዜ እግዚአብሔር በሰይጣን ላይ የነበረውን የምስጋና ልብስ እና የግርማ ልዕልና አስወገደ፤ ሰይጣን ብሎ ሰየመው፤ በእግዚአብሔር ላይ ታብዮአልና፤ በእግዚአብሔር መንገድ አልሄደምና ለራሱ ክብር ወዷልና"*።

በተጨማሪም በመቃብያን ላይ ዲያቢሎስ የወደቀበት ለአደም አልሰግድ በማለቱ እንደሆነ ተገልጿል፦
3ኛ መቃብያን 1፥6 *ለሚዋረድልኝ ለአዳም አልሰግድም በማለቴ እግዚአብሔር ስለአባታቸው ስለአዳም ከማዕረጌ አዋርዶኛልና*።

ኡሥታዝ ወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም

የበለጠ ለማወቅ
ጥሪያችን Tiriyachen
https://fb.me/tiriyachen

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሣሚሪይ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

20:85 አላህም እኛም ከአንተ በኋላ ሰዎችህን በእርግጥ ፈትተን፤ *ሳምራዊውም* አሳሳታቸው አለው። قَالَ فَإِنَّا قَدْ فَتَنَّا قَوْمَكَ مِن بَعْدِكَ وَأَضَلَّهُمُ السَّامِرِيُّ

"ሣሚሪይ" سَّامِرِىّ በሙሳ ዘመን ለእስራኢል ልጆች በእሳት አቅልጦ ወይፈን የሰራላቸው ሰው ነው፦
20:85 አላህም እኛም ከአንተ በኋላ ሰዎችህን በእርግጥ ፈትተን፤ *ሳምራዊውም* አሳሳታቸው አለው። قَالَ فَإِنَّا قَدْ فَتَنَّا قَوْمَكَ مِن بَعْدِكَ وَأَضَلَّهُمُ السَّامِرِيُّ
20:87 ቀጠሮህን በፈቃዳችን አልጣስንም፤ ግን እኛ ከሕዝቦቹ ጌጥ፣ ሸክሞችን ተጫን በእሳት ላይ ጣልናትም፤ *ሳምራዊውም* እንደዚሁ ጣለ አሉት። قَالُوا مَا أَخْلَفْنَا مَوْعِدَكَ بِمَلْكِنَا وَلَـٰكِنَّا حُمِّلْنَا أَوْزَارًا مِّن زِينَةِ الْقَوْمِ فَقَذَفْنَاهَا فَكَذَٰلِكَ أَلْقَى السَّامِرِيُّ
20:95 ሙሳ *ሳምራዊው* ሆይ ነገርህም ምንድነው? አለ። قَالَ فَمَا خَطْبُكَ يَا سَامِرِيُّ

እሱም የሰራላቸው አንድ ወይፈን የሆነ ጥጃ ነው፦
20፥88 ለእነሱም አካል የኾነ *ጥጃን* ለእርሱ መጓጎር ያለውን አወጣላቸው፡፡ ተከታዮቹ «ይህ አምላካችሁ የሙሳም አምላክ ነው ግን ረሳው» አሉም፡፡ فَأَخْرَجَ لَهُمْ عِجْلًا جَسَدًا لَّهُ خُوَارٌ فَقَالُوا هَـٰذَا إِلَـٰهُكُمْ وَإِلَـٰهُ مُوسَىٰ فَنَسِيَ
7፥148 የሙሳም ሕዝቦች ከእርሱ መኼድ በኋላ ከጌጦቻቸው *ወይፈንን አካልን ለእርሱ ማግሳት ያለውን አምላክ አድርገው ያዙ፡፡ እርሱ የማያናግራቸው መንገድንም የማይመራቸው መኾኑን አይመለከቱምን?* አምላክ አድርገው ያዙት፡፡ በዳዮችም ኾኑ፡፡ وَاتَّخَذَ قَوْمُ مُوسَىٰ مِن بَعْدِهِ مِنْ حُلِيِّهِمْ عِجْلًا جَسَدًا لَّهُ خُوَارٌ ۚ أَلَمْ يَرَوْا أَنَّهُ لَا يُكَلِّمُهُمْ وَلَا يَهْدِيهِمْ سَبِيلًا ۘ اتَّخَذُوهُ وَكَانُوا ظَالِمِينَ

ይህን ትረካ በመጠኑም ቢሆን ከፔንታተች ጋር ይመሳሰላል፦
ዘጸአት 32፥7-8 ያህዌህም ሙሴን፦ ከግብፅ ምድር ያወጣኸው ሕዝብህ ኃጢአት ሠርተዋልና ሂድ፥ ውረድ። ካዘዝኋቸው መንገድ ፈጥነው ፈቀቅ አሉ፤ *ቀልጦ የተሠራ የጥጃ ምስል ለራሳቸው አደረጉ፥ ሰገዱለትም፥ ሠዉለትም*፤፦ እስራኤል ሆይ፥ እነዚህ *ከግብፅ ምድር ያወጡህ አማልክትህ ናቸው አሉ* ሲል ተናገረው።
ዘጸአት 32፥20 *የሠሩትንም ጥጃ ወስዶ በእሳት አቀለጠው፥ እንደ ትቢያም እስኪሆን ድረስ ፈጨው፥ በውኃውም ላይ በተነው*፥ ለእስራኤልም ልጆች አጠጣው።

እዚህ ጋር የተሰራው ጥጃ አንድ ጥጃ እንደሆነ ይናገራል፤ ሰሪውም አሮን ነው ብሎ ያስቀምጣል፤ "ሣሚሪይ" سَّامِرِىّ በዕብራይስጥ "ሳንበርይ" זִמְרִי በአማርኛ "ዘንበሪ" የተባለው ሰው ነው፦
ዘኍልቍ 25፥14 ከምድያማዊቱም ጋር የተገደለው የእስራኤላዊው ሰው ስም *ዘንበሪ* ነበረ፤

ይህ ሆኖ ሳለ ሚሽነሪዎች ሁለት የተለያዩ ታሪኮችን በማታታት ቁርአን የታሪክ ግድፈት እንዳለበት ለማሳየት ሲያምታቱ ይገኛሉ። "ሳንበርይ" זִמְרִי ማለትም "ዘንበሪ" የተባለውን ስም "ሰማሪይ" שומרון‎ ማለትም "ሰማሪያ" ጋር ደባልቀው ቁርኣን፦ "በሙሳ ዘመን ጥጃ ሰራ የሚለው ግለሰብ የሰማሪያ ሰዎችን ነው" ብለው ለመጠምዘዝ ይሞክራሉ፤ በ 930 BC በአስሩ ነገድ ይኖር የነበረው ዘንበሪ የተባለው ንጉሥ ሳምርም ከሚባል ሰው በሁለት መክሊት ብር የሰማርያን ተራራ ገዛ፤ በተራራውም ላይ ሠራ፥ የሠራውንም ከተማ በተራራው ባለቤት በሳምር ስም ሰማርያ ብሎ ጠራው፦
1ኛ ነገሥት 16፥24 *ከሳምርም* በሁለት መክሊት ብር የሰማርያን ተራራ ገዛ፤ በተራራውም ላይ ሠራ፥ የሠራውንም ከተማ በተራራው ባለቤት *በሳምር* ስም *ሰማርያ* ብሎ ጠራው።

ከዚያ በኃላ ያሉ ሕዝቦች "ሳምራውያን" ሲባሉ ወንዱ "ሳምራዊ" ሴቷ "ሳምራዊት" ይባላሉ፦
ሉቃስ10፥33 አንድ *ሳምራዊ* ግን ሲሄድ ወደ እርሱ መጣ አይቶትም አዘነለት፥
ሉቃስ 17፥16 እያመሰገነውም በእግሩ ፊት በግንባሩ ወደቀ፤ እርሱም *ሳምራዊ* ነበረ።
ዮሐንስ 4፥9 ስለዚህ *ሳምራዊቲቱ*፦ አንተ የይሁዳ ሰው ስትሆን *ሳምራዊት* ሴት ከምሆን ከእኔ መጠጥ እንዴት ትለምናለህ? አለችው፤ አይሁድ *ከሳምራውያን* ጋር አይተባበሩም ነበርና።
ዮሐንስ 8፥48 አይሁድ መልሰው፦ *ሳምራዊ* እንደ ሆንህ ጋኔንም እንዳለብህ በማለታችን እኛ መልካም እንል የለምን? አሉት።

ይህንን እሳቤ ከያዝን ሳምራውያን ከጊዜ በኃላ የአስሩ ነገዶች መጠሪያ ሆነ፤ ሳምራውያን ቀልጠው የተሠሩትንም የሁለቱን እንቦሶች ምስሎች አደረጉ፥ የማምለኪያ ዐፀድንም ተከሉ፥ ለሰማይም ሠራዊት ሁሉ ሰገዱ፥ በኣልንም አመለኩ፤ የሰሯቸው አማልክት ብዙ ናቸው፦
2 ነገሥት 17፥16 የአምላካቸውንም የያህዌን ትእዛዝ ሁሉ ተዉ፥ *ቀልጠው የተሠሩትንም የሁለቱን እንቦሶች ምስሎች አደረጉ*፥ የማምለኪያ ዐፀድንም ተከሉ፥ ለሰማይም ሠራዊት ሁሉ ሰገዱ፥ *በኣልንም አመለኩ*።
2 ነገሥት 17፥29 *በየሕዝባቸውም አምላካቸውን አደረጉ፥ ሰምራውያንም በሠሩት በኮረብታው መስገጃዎች ሕዝቡ ሁሉ በሚኖሩበት ከተሞቻቸው አኖሩአቸው*።

ታዲያ ይህ ታሪክ በየትኛው ቀመርና ስሌት ነው ከቁርአን ጋር የሚመሳሰለው? ሲጀመር ከመነሻው "ሳንበርይ" זִמְרִי የተባለውን ስም እና "ሰማሪይ" שומרון‎ የተባለው ስም አንድ ነውን? ሲቀጥል በሙሳ ጊዜ የነበረው ሳንበርይ አንድ ግለሰብ ሲሆን ከይሁዳ ንጉሥ ከአሳ በኃላ አማልክት የሰሩት ሳምራውያን ደግሞ ሕዝብ ናቸው፤ ሲሠልስ ቁርኣን ልክ እንደ ዘጸአት በሙሴ ጊዜ ተሰራ የሚለን አንድ ጥጃ ነው፤ ነገር ግን በተቃራኒው ሳምራውያን የሰሩት የሁለቱን እንቦሶች ምስሎች ናቸው።

ጥያቄ፦ እስራኤላውያው በምድረ በዳ ያሉት የቱን ነው? "ከግብፅ ያወጣህ አምላክህ ይህ ነው" ወይስ "ከግብፅ ምድር ያወጡህ አማልክትህ ናቸው" ?
ነህምያ 9፥18 ቀልጦ የተሠራውንም እምቦሳ አድርገው፡— *ከግብፅ ያወጣህ አምላክህ ይህ ነው* ባሉ ጊዜ፥ እጅግም ባስቈጡህ ጊዜ፥
ዘጸአት 32፥4 ከእጃቸውም ተቀብሎ በመቅረጫ ቀረጸው፥ ቀልጦ የተሠራ ጥጃም አደረገው፤ እርሱም፡— እስራኤል ሆይ፥ እነዚህ *ከግብፅ ምድር ያወጡህ አማልክትህ ናቸው*፡ አላቸው።

ዘንበሪ ይኖር የነበረው በማን ዘመን ነው? በሙሴ ወይስ በይሁዳ ንጉሥ በአሳ?
ዘኍልቍ 25፥14 ከምድያማዊቱም ጋር የተገደለው የእስራኤላዊው ሰው ስም *ዘንበሪ* ነበረ፤
1ኛ ነገሥት 16፥23 በይሁዳ ንጉሥ በአሳ በሠላሳ አንደኛው ዓመት *ዘንበሪ* በእስራኤል ላይ አሥራ ሁለት ዓመት ነገሠ። በቴርሳም ስድስት ዓመት ነገሠ።
አይ ሁለቱ የተለያዩ ሰዎች ናቸው ካላችሁ እንግዲያውስ ቁርአን እየነገረን ያለው በሙሳ ጊዜ ስለነበረ ክስተት እንጂ በሰማርያውን ስለተከሰተው ክስተት አይደለም።
ሁለት ክስተት በተለያዩ ጊዜ ሲከናወኑ ታሪኩ አንድ ነው ብሎ መደምደም ቂልነት ነው። ለምሳሌ በሉጥ ዘመን የነበሩ ሰዎች ወንድ ለወንድ ለተራክቦ ፍላጎት እንዳላቸው ተዘግቧል፦
ዘፍጥረት 19፥5-9 *ሎጥንም ጠርተው እንዲህ አሉት፤ በዚህ ሌሊት ወደ ቤትህ የገቡት ሰዎች ወዴት ናቸው? እናውቃቸው ዘንድ ወደ እኛ አውጣቸው*። *ሎጥም ወደ እነርሱ ወደ ደጅ ወጣ መዝጊያውንም በኋላው ዘጋው*፤
እንዲህም አለ፦ ወንድሞቼ ሆይ፥ *ይህን ክፉ ነገር አታድርጉ፤ እነሆ፥ ወንድን ያላወቁ ሁለት ሴቶች ልጆች አሉኝ፤ እነርሱን ላውጣላችሁ፥ እንደ ወደዳችሁም አድርጓቸው*፤ በእነዚህ ሰዎች ብቻ ምንም አታድርጉ፥ እነርሱ በጣራዬ ጥላ ሥር ገብተዋልና።

ይህ ድርጊት በመሳፍንቱ ዘመን የነበሩ ሰዎች ወንድ ለወንድ ለተራክቦ ፍላጎት እንዳላቸው ተዘግቧል፦
መሣፍንት 19፥22-25 ሰውነታቸውንም ደስ ባሰኙ ጊዜ ወስላቶች የሆኑ *የከተማው ሰዎች ቤቱን ከበቡ በሩንም ይደበድቡ ነበር፤ ባለቤቱንም ሽማግሌውን፦ ወደ ቤትህ የገባውን ሰው እንድንደርስበት አውጣልን፡ አሉት። ባለቤቱም ሽማግሌው ወደ እነርሱ ወጥቶ፦ ወንድሞቼ ሆይ፥ ይህን ክፉ ነገር፥ እባካችሁ፥ አታድርጉ፤ ይህ ሰው ወደ ቤቴ ገብቶአልና እንደዚህ ያለ ኃጢአት አትሥሩ። ድንግል ልጄና የእርሱም ቁባት፥ እነሆ፥ አሉ፥ አሁንም አወጣቸዋለሁ፤ አዋርዱአቸው እንደ ወደዳችሁም አድርጉባቸው፤ ነገር ግን በዚህ ሰው ላይ እንደዚህ ያለ ኃጢአት አታድርጉ፡ አላቸው። ሰዎቹ ግን ነገሩን አልሰሙም፤ ሰውዮውም ቁባቱን ይዞ አወጣላቸው፤ ደረሱባትም፥ ሌሊቱንም ሁሉ እስኪነጋ ድረስ አመነዘሩባት፤ ጎህ በቀደደም ጊዜ ለቀቁአት*።

ያ ማለት ሁለት ተመሳሳይ ክስተት ግን በተለያየ ጊዜ የሆኑ ክንውኖች ናቸው ካላችሁ እንግዲያውስ ከላይ ያለውን እሳቤ በዚህ መልክና ልክ ተረዱት።

ኡሥታዝ ወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም

የበለጠ ለማወቅ
ጥሪያችን Tiriyachen
https://www.facebook.com/tiriyachen

ወሰላሙ አለይኩም
👍1
የኢብራሂም መንገድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው።

16፥123 *ከዚያም ወደ አንተ፦ “የኢብራሂምን መንገድ ቀጥተኛ ሲኾን ተከተል! ከአጋሪዎቹም አልነበረም” ማለት አወረድን*፡፡ ثُمَّ أَوْحَيْنَا إِلَيْكَ أَنِ اتَّبِعْ مِلَّةَ إِبْرَاهِيمَ حَنِيفًا ۖ وَمَا كَانَ مِنَ الْمُشْرِكِين

“ኢሥላም” إِسْلَٰم ማለትም “መታዘዝ” ወይም “መገዛት” ማለት ሲሆን አላህ ዘንድ ዕውቅና ያለ ሃይማኖት ኢሥላም ብቻ ነው፦
3፥19 *”አላህ ዘንድ የተወደደ ሃይማኖት “ኢሥላም” ብቻ ነው”*፡፡ إِنَّ ٱلدِّينَ عِندَ ٱللَّهِ ٱلْإِسْلَٰمُ

አላህ ሰዎችን ሁሉ የፈጠረበት ሃይማኖት ኢሥላም ነው፦
30፥30 *”ፊትህንም ወደ ቀጥተኛ ሃይማኖት ቀጥ አድርግ፡፡ የአላህን ፍጥረት ያችን አላህ ሰዎችን በእርስዋ ላይ የፈጠረባትን ሃይማኖት ያዟት፡፡ የአላህን ፍጥረት መለወጥ የለም፡፡ ይህ ቀጥተኛ ሃይማኖት ነው”*፡፡ ግን አብዛኛዎቹ ሰዎች አያውቁም፡፡ فَأَقِمْ وَجْهَكَ لِلدِّينِ حَنِيفًا ۚ فِطْرَتَ اللَّهِ الَّتِي فَطَرَ النَّاسَ عَلَيْهَا ۚ لَا تَبْدِيلَ لِخَلْقِ اللَّهِ ۚ ذَٰلِكَ الدِّينُ الْقَيِّمُ وَلَـٰكِنَّ أَكْثَرَ النَّاسِ لَا يَعْلَمُونَ

እዚህ አንቀጽ ላይ “ቀጥተኛ” ለሚለው ቃል የገባው “ሐኒፋ” حَنِيفًا ሲሆን አላህ ሰዎችን ሁሉ የፈጠረበት ሃይማኖት ኢሥላም “ሐኒፋ” መሆኑን ያሳያል። አምላካችን አላህ ለኢብራሂም “አሥሊም” أَسْلِمْ ማለትም “ታዘዝ” ብሎ ሲለው እርሱም ለዓለማት ጌታ “አሥለምቱ” أَسْلَمْتُ ማለትም “ታዘዝኩ” አለ፥ ኢብራሂም ወደ ቀጥተኛው የተዘነበለ ሙሥሊም ነበረ፦
2፥131 *”ጌታው ለእርሱ “ታዘዝ” ባለው ጊዜ መረጠው፡፡ ለዓለማት ጌታ ”ታዘዝኩ” አለ”*፡፡ إِذْ قَالَ لَهُۥ رَبُّهُۥٓ أَسْلِمْ ۖ قَالَ أَسْلَمْتُ لِرَبِّ ٱلْعَٰلَمِينَ
3፥67 *”ኢብራሂም ይሁዳዊም ክርስቲያንም አልነበረም፡፡ ግን “ወደ ቀጥተኛው የተዘነበለ ሙሥሊም ነበረ”፡፡ ከአጋሪዎችም አልነበረም”*፡፡ مَا كَانَ إِبْرَاهِيمُ يَهُودِيًّا وَلَا نَصْرَانِيًّا وَلَـٰكِن كَانَ حَنِيفًا مُّسْلِمًا وَمَا كَانَ مِنَ الْمُشْرِكِينَ

“ሙሥሊም” مُسْلِم የሚለው ቃል “አሥለመ” أَسْلَمَ ማለትም “ታዘዘ” ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ታዛዥ” ማለት ነው፥ አሁንም እዚህ አንቀጽ ላይ “ቀጥተኛ” ለሚለው ቃል የገባው “ሐኒፋ” حَنِيفًا ነው። “ሐኒፍ” حَنِيف ማለት “ቀጥተኛ” ማለት ሲሆን ለአላህ ቀጥ ያሉ “ቀጥተኞች” ደግሞ “ሑነፋ” حُنَفَاءَ ይባላሉ፦
22፥31 *”ለአላህ ቀጥተኞች በእርሱ የማታገሩ ሆናችሁ ከሐሰት ራቁ”*፡፡ በአላህም የሚያጋራ ሰው ከሰማይ እንደ ወደቀና በራሪ እንደምትነጥቀው ወይም ነፋስ እርሱን በሩቅ ስፍራ እንደምትጥለው ብጤ ነው፡፡ حُنَفَاءَ لِلَّهِ غَيْرَ مُشْرِكِينَ بِهِ ۚ وَمَن يُشْرِكْ بِاللَّهِ فَكَأَنَّمَا خَرَّ مِنَ السَّمَاءِ فَتَخْطَفُهُ الطَّيْرُ أَوْ تَهْوِي بِهِ الرِّيحُ فِي مَكَانٍ سَحِيقٍ
98፥5 አላህን ሃይማኖትን ለእርሱ ብቻ አጥሪዎች፣ *”ቀጥተኞች ኾነው ሊያመልኩት”*፣ ሶላትንም አስተካክለው ሊሰግዱ ዘካንም ሊሰጡ እንጂ ያልታዘዙ ሲኾኑ ተለያዩ፡፡ ይህም የቀጥተኛይቱ ሃይማኖት ድንጋጌ ነው፡፡ وَمَا أُمِرُوا إِلَّا لِيَعْبُدُوا اللَّهَ مُخْلِصِينَ لَهُ الدِّينَ حُنَفَاءَ وَيُقِيمُوا الصَّلَاةَ وَيُؤْتُوا الزَّكَاةَ ۚ وَذَٰلِكَ دِينُ الْقَيِّمَة

ኢብራሂም እራሱ ሐኒፍ ሲሆን እርሱ የተጓዘበት መንገድ ደግሞ ሐኒፋ ነው፦
2፥135 አይሁድን ወይም ክርስቲያኖችን ኹኑ! ቅኑን መንገድ ትመራላችሁና» አሉም፡፡ «አይደለም *”የኢብራሂምን መንገድ ቀጥተኛ ሲኾን እንከተላለን”*፤ ከአጋሪዎችም አልነበረም» በላቸው፡፡ وَقَالُوا كُونُوا هُودًا أَوْ نَصَارَىٰ تَهْتَدُوا ۗ قُلْ بَلْ مِلَّةَ إِبْرَاهِيمَ حَنِيفًا ۖ وَمَا كَانَ مِنَ الْمُشْرِكِينَ

“ሚላህ” مِلَّة ማለት “መንገድ” ማለት ነው፥ ይህም የኢብራሂም መንገድ ሐኒፋ ነው፦
3፥95 «አላህ እውነትን ተናገረ፡፡ *”የኢብራሂምንም መንገድ ቀጥተኛ ሲኾን ተከተሉ”*፡፡ ከአጋሪዎቹም አልነበረም» በላቸው፡፡ قُلْ صَدَقَ اللَّهُ ۗ فَاتَّبِعُوا مِلَّةَ إِبْرَاهِيمَ حَنِيفًا وَمَا كَانَ مِنَ الْمُشْرِكِين
4፥125 *”እርሱ መልካም ሠሪ ኾኖ ፊቱን ለአላህ ከሰጠና የኢብራሂምንም መንገድ ቀጥተኛ ሲኾን ከተከተለ ሰው ይበልጥ ሃይማኖቱ ያማረ ማን ነው? አላህም ኢብራሂምን ፍጹም ወዳጅ አድርጐ ያዘው”*፡፡ وَمَنْ أَحْسَنُ دِينًا مِّمَّنْ أَسْلَمَ وَجْهَهُ لِلَّهِ وَهُوَ مُحْسِنٌ وَاتَّبَعَ مِلَّةَ إِبْرَاهِيمَ حَنِيفًا ۗ وَاتَّخَذَ اللَّهُ إِبْرَاهِيمَ خَلِيلًا
6፥79 *«እኔ ለእዚያ ሰማያትንና ምድርን ለፈጠረው አምላክ ቀጥተኛ ስኾን ፊቴን አዞርኩ፡፡ እኔም ከአጋሪዎቹ አይደለሁም» አለ*፡፡ إِنِّي وَجَّهْتُ وَجْهِيَ لِلَّذِي فَطَرَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ حَنِيفًا ۖ وَمَا أَنَا مِنَ الْمُشْرِكِينَ

የኢብራሂም መንገድ ሐኒፋ ሲሆን አላማው ሁለንተናን ለአላህ መስጠት ነው፥ “የሰጠ” ለሚለው ቃል የገባው “አሥለመ” أَسْلَمَ ነው።
ነቢያችን”ﷺ” ወደ እርሳቸው ወሕይ ከመውረዱ ይህንን የኢብራሂም መንገድ ይተገብሩ ነበር፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 1 ሐዲስ 3
የምዕመናን እናት ዓኢሻህ እንደተረከችው፦ *”ከወሕይ ጅማሬ ለአላህ መልእክተኛ”ﷺ” ልክ እንደ ጎህ ንጋት ደማቅ ሆኖ በሰናይ ህልም ሁኔታ ነበር። ከዚያም የተማልሎ ውዴታ በእርሷቸው ላይ ነበር። በሒራእ ዋሻ ውስጥ ይገለሉ እና “ቀጥ ይሉ ነበር”። እርሳቸውም ቤተሰባቸውን ለማየት ከመፈለጋቸው በፊት ለብዙ ቀናት በተከታታይ አላህ ያመልኩ ነበር”*። عَنْ عَائِشَةَ أُمِّ الْمُؤْمِنِينَ، أَنَّهَا قَالَتْ أَوَّلُ مَا بُدِئَ بِهِ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم مِنَ الْوَحْىِ الرُّؤْيَا الصَّالِحَةُ فِي النَّوْمِ، فَكَانَ لاَ يَرَى رُؤْيَا إِلاَّ جَاءَتْ مِثْلَ فَلَقِ الصُّبْحِ، ثُمَّ حُبِّبَ إِلَيْهِ الْخَلاَءُ، وَكَانَ يَخْلُو بِغَارِ حِرَاءٍ فَيَتَحَنَّثُ فِيهِ ـ وَهُوَ التَّعَبُّدُ ـ اللَّيَالِيَ ذَوَاتِ الْعَدَدِ قَبْلَ أَنْ يَنْزِعَ إِلَى أَهْلِهِ
“ቀጥ ይሉ ነበር” ለሚለው የግስ መደብ የገባው “የተሐነሱ” يَتَحَنَّثُ ሲሆን ኢብኑ ሐጀሩል አሥቀላኒ በፈተሑል ባሪ ፊ ሸርህ ሰሒሑል ቡኻርይ ሐዲስ 3 ላይ፦ “የተሐነሱ” يَتَحَنَّثُ ማለት “የተሐነፉ” يَتَحَنَّفُ ማለት ነው ብለው አስቀምጠዋል፦
قوله : ( فيتحنث ) ‏
‏هي بمعنى يتحنف ، أي : يتبع الحنفية وهي دين إبراهيم ، والفاء تبدل ثاء في كثير من كلامهم . وقد وقع في رواية ابن هشام في السيرة ” يتحنف ” بالفاء أو التحنث إلقاء الحنث وهو الإثم ، كما قيل يتأثم ويتحرج ونحوهما .

ልብ አድርግ የኢብራሂም መንገድ አላህ ሰዎችን ሁሉ የፈጠረበት ኢሥላም ነው፥ ሲቀጥል አላህ በኢብራሂም ዝርዮች ውስጥ ይመለሱ ዘንድ በአንድ አምላክ የማመን ቀሪ ቃል አድርጓል፦
43፥28 *”በዝርዮቹም ውስጥ ይመለሱ ዘንድ ቀሪ ቃል አደረጋት”*፡፡ وَجَعَلَهَا كَلِمَةً بَاقِيَةً فِي عَقِبِهِ لَعَلَّهُمْ يَرْجِعُونَ

ነቢያችን”ﷺ” ደግሞ የኢብራሂም ዝርያ ናቸው። ከዚያ በኃላ አላህ ቁርኣንን በማውረድ “ቁል” قُلْ በሚል ትእዛዝ የኢብራሂምን መንገድ ቀጥተኛ ሲሆን መራቸው፦
6፥161 *«እኔ ጌታዬ ወደ ቀጥተኛው መንገድ ትክክለኛን ሃይማኖት “ቀጥተኛ” ሲኾን የኢብራሂምን መንገድ መራኝ፡፡ እርሱም ከአጋሪዎቹ አልነበረም» በል”*፡፡ قُلْ إِنَّنِي هَدَانِي رَبِّي إِلَىٰ صِرَاطٍ مُّسْتَقِيمٍ دِينًا قِيَمًا مِّلَّةَ إِبْرَاهِيمَ حَنِيفًا ۚ وَمَا كَانَ مِنَ الْمُشْرِكِينَ
10፥105 *”ፊትህንም ወደ ቀጥተኛ ሃይማኖት ቀጥ አድርግ”*፡፡ ከአጋሪዎቹም አትሁን፡፡ وَأَنْ أَقِمْ وَجْهَكَ لِلدِّينِ حَنِيفًا وَلَا تَكُونَنَّ مِنَ الْمُشْرِكِينَ

ይህ ዲን ሐኒፋ የሆነው ኢሥላም እንደሆነ እና ኢሥላም ማለት መታዘዝ ማለት እንደሆነ ከላይ አይተናል፥ ቁርኣን ደግሞ “ትእዛዝ” ሆኖ ወደ እርሳቸው ወርዷል፦
65፥5 *”ይህ “የአላህ ትእዛዝ ነው”። ወደ እናንተም አወረደው”*። ذَٰلِكَ أَمْرُ ٱللَّهِ أَنزَلَهُۥٓ إِلَيْكُمْ

ይህንን ትእዛዝ ተቀብለው የታዘዙ የመጀመሪያው ታዛዥ እርሳቸው ናቸው፦
6፥14 *«እኔ መጀመሪያ ትእዛዝን ከተቀበለ ሰው ልኾን ታዘዝኩ*”፡፡ ከአጋሪዎችም ፈጽሞ አትኹን ተብያለሁ» በላቸው፡፡ قُلْ إِنِّىٓ أُمِرْتُ أَنْ أَكُونَ أَوَّلَ مَنْ أَسْلَمَ ۖ وَلَا تَكُونَنَّ مِنَ ٱلْمُشْرِكِينَ

“ትእዛዝን ከተቀበለ” የሚለው ይሰመርበት። “ትእዛዝን የተቀበለ” ለሚለው ቃል የገባው “አሥለመ” أَسْلَمَ መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል፥ “አወል” أَوَّل ማለትም “መጀመሪያ” በአንጻራዊነት ደረጃ የመጣ ገላጭ ነው። እንግዲህ ቁርኣንን ተቀብሎ ከሠለሙት ሙሥሊሞች መጀመሪያ ነቢያችን”ﷺ” ናቸው ማለት ነው፦
6፥163 *”«ለእርሱ ተጋሪ የለውም፡፡ በዚህም በማጥራት ታዘዝኩ፡፡ እኔም የሙስሊሞች መጀመሪያ ነኝ» በል”*፡፡ لَا شَرِيكَ لَهُۥ ۖ وَبِذَٰلِكَ أُمِرْتُ وَأَنَا۠ أَوَّلُ ٱلْمُسْلِمِينَ
3፥20 ቢከራከሩህም፡- *”«ፊቴን ለአላህ ሰጠሁ፤ የተከተሉኝም ሰዎች እንደዚሁ ለአላህ ሰጡ»* በላቸው፡፡ فَإِنْ حَاجُّوكَ فَقُلْ أَسْلَمْتُ وَجْهِيَ لِلَّهِ وَمَنِ اتَّبَعَنِ

“ሰጠሁ” ለሚለው ቃል የገባው “አሥለምቱ” أَسْلَمْتُ ሲሆን እርሳቸው ቀጥሎ ተከታዮቻቸው ሁለንተናቸውን ለአላህ ያሠለሙ መሆናቸውን ፍንትው አርጎ ያሳያል። ነቢያችን”ﷺ” ከአላህ ወደ እርሳቸው በተወረደው ቁርኣን አምነዋል፥ ተከታዮቻቸውም እንደዚሁ አመኑ፦
2፥285 *”መልክተኛው ከጌታው ወደ እርሱ በተወረደው አመነ፡፡ ምእምኖቹም እንደዚሁ አመኑ”*፡፡ آمَنَ الرَّسُولُ بِمَا أُنزِلَ إِلَيْهِ مِن رَّبِّهِ وَالْمُؤْمِنُون

“ሙዕሚኑን” مُؤْمِنُون ማለት አማኞች ማለት ነው። “ኢማን” إِيمَان ማለት “አመነ” آمَنَ ማለትም “አመነ” ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “እምነት” ማለት ነው። ቁርኣን ትእዛዝ ሆኖ ወደ ነቢያችን”ﷺ” ከመውረዱ በፊት ቁርኣንን ሆነ በቁርኣን ላይ እምነቱ ምን እንደሆነ ዐያውቁም ነበር፦
42፥52 እንደዚሁም *”ወደ አንተ ከትእዛዛችን ሲኾን መንፈስን (ቁርኣንን) አወረድን፡፡ መጽሐፉም እምነቱም ምን እንደኾነ የምታውቅ አልነበርክም”*፡፡ ግን መንፈሱን ከባሮቻችን የምንሻውን ሰው በእርሱ የምንመራበት ብርሃን አደረግነው፡፡ አንተም ወደ ቀጥተኛው መንገድ በእርግጥ ትመራለህ፡፡ وَكَذَٰلِكَ أَوْحَيْنَا إِلَيْكَ رُوحًا مِّنْ أَمْرِنَا ۚ مَا كُنتَ تَدْرِي مَا الْكِتَابُ وَلَا الْإِيمَانُ وَلَـٰكِن جَعَلْنَاهُ نُورًا نَّهْدِي بِهِ مَن نَّشَاءُ مِنْ عِبَادِنَا ۚ وَإِنَّكَ لَتَهْدِي إِلَىٰ صِرَاطٍ مُّسْتَقِيم

ከኡሥታዝ ወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም

የበለጠ ለማወቅ
ጥሪያችን Tiriyachen
https://www.facebook.com/tiriyachen

ወሰላሙ አለይኩም
👍1
አንዱ ተመላኪ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

5፥117 በእርሱ ያዘዝከኝን ቃል *”ጌታዬንና ጌታችሁን አላህን አምልኩ”* ማለትን እንጂ ለእነርሱ ሌላ አላልኩም፡፡ مَا قُلْتُ لَهُمْ إِلَّا مَآ أَمَرْتَنِى بِهِۦٓ أَنِ ٱعْبُدُوا۟ ٱللَّهَ رَبِّى وَرَبَّكُمْ

ኢየሱስ ለሰይጣን፦ "ለጌታህ ለአምላክህ ስገድ እርሱንም ብቻ አምልክ ተብሎ ተጽፎአልና" ብሎታል፦
ማቴዎስ 4፥10 ያን ጊዜ ኢየሱስ፦ ሂድ፥ አንተ ሰይጣን ለጌታህ ለአምላክህ ስገድ *እርሱንም ብቻ አምልክ* αὐτῷ μόνῳ λατρεύσεις ተብሎ ተጽፎአልና አለው።

"አውቶ" αὐτῷ ማለት "እርሱ"him" ማለት ሲሆን ነጠላ ተውላጠ-ስም መሆኑ አንድ ነጠላ ማንነት ብቻ እንደሚመለክ ያሳያል፥ ከአንድ በላይ የሚመለኩ ማንነት ቢሆን ኖሮ "አውቶኢስ" αὐτοῖς ማለትም "እነርሱ"them" ይሆን ነበር። ይህ ጌታ አምላክ ለኢየሱስ የዳዊትን ዙፋን የሰጠው አብ ነው፦
ሉቃስ 1፥32 እርሱ ታላቅ ይሆናል የልዑል ልጅም ይባላል፥ *ጌታ አምላክም የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል*።

ይህ ጌታ አምላክ ከበጉ ማንነት በሰዋስው ተነጥሎ ተቀምጧል፦
ራእይ 21፥22 *"ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ እና በጉ መቅደስዋ ናቸውና"* መቅደስ በእርስዋ ዘንድ አላየሁም።

ልብ አድርግ "ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ" እና "በጉ" ሁለት ማንነት እንደሆኑ ለማሳየት "ናቸው" በሚል የብዜት አያያዥ ግስ ተቀምጧል፥ በተጨማሪም "እና" በሚል መስተጻምር ተለይተዋል። ስለዚህ "ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ" እና "በጉ" ሁለት ማንነት ናቸው፥ ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ አብ ከሆነ "በጉ" ደግሞ ኢየሱስ ነው። በጉ የሚታረድ ማንነት ስለሆነ ፍጡር ነው፦
ራእይ 5፥12 በታላቅም ድምፅ፦ *"የታረደው በግ"* ኃይልና ባለ ጠግነት ጥበብም ብርታትም ክብርም ምስጋናም በረከትም ሊቀበል ይገባዋል፥ አሉ።

መለኮት የሆነው ጌታ አምላክ ስጋ ስላልሆነ መቼም አይታረድም። እንደ ባይብሉ የታረደው በግ ሰው የሆነው ኢየሱስ ከሆነ ሰው አይመለክም፦
ራእይ 22፥3 *"የእግዚአብሔር እና የበጉም ዙፋን በእርስዋ ውስጥ ይሆናል፥ ባሪያዎቹም ያመልኩታል"*፥ λατρεύσουσιν αὐτῷ ፊቱንም ያያሉ።

እግዚአብሔር እና በጉ ሁለት ማንነት መሆናቸው ለማሳየት አሁንም "እና" በሚል መስተጻምር ተለይተዋል። አሁንም "አውቶ" αὐτῷ ማለት "እርሱ"him" ማለት ሲሆን ነጠላ ተውላጠ-ስም መሆኑ አንድ ነጠላ ማንነት ብቻ እንደሚመለክ ያሳያል፥ ከአንድ በላይ የሚመለኩ ማንነት ቢሆን ኖሮ "አውቶኢስ" αὐτοῖς ማለትም "እነርሱ"them" ይሆን ነበር። "ያመልኩታል" እንጂ "ያመልኳቸዋል" አላለም፥ ይህ የሚመለክ እግዚአብሔር እንጂ በጉ አይደለም፦
ራእይ 7፥15 ስለዚህ *"በእግዚአብሔር ዙፋን ፊት አሉ፥ ሌሊትና ቀንም በመቅደሱ ያመልኩታል"*።
ራእይ 7፥17 በዙፋኑ መካከል ያለው *"በጉ እረኛቸው ይሆናልና"*።

ልብ አድርግ "አውቶ" αὐτῷ ማለትም "እርሱ"him" የሚለው ተክቶ የመጣው "እግዚአብሔር" የሚለውን ቃል ነው፥ "ያመልኩታል" የተባለው በግልጽና በማያሻማ "እግዚአብሔርን" ነው። በጉ ከእግዚአብሔር በሰዋሰው አቀማመጥ ተነጥሎ "እረኛቸው ይሆናልና" የተባለው።
አንዳንድ ቂሎች፦ "የእግዚአብሔር እና የበጉ ዙፋን አንድ ዙፋን ነው፥ ስለዚህ በጉ ይመለካል" ይላሉ፥ ለመሆኑ ሰለሞን የተቀመጠበት ዙፋን የማን ነው የእግዚአብሔር ወይስ የዳዊት? እስቲ እንመልከት፦
1ኛ ዜና 28፥5 *በእግዚአብሔር መንግሥት ዙፋን* ላይ ተቀምጦ በእስራኤል ላይ ይነግሥ ዘንድ ልጄን ሰሎሞንን መርጦታል።
1ኛ ዜና 29፥23 *"ሰሎሞንም በአባቱ በዳዊት ዙፋን ላይ ተቀመጠ"*፥ ተከናወነለትም፤ እስራኤልም ሁሉ ታዘዙለት።

የዳዊት ዙፋን የእግዚአብሔር ዙፋን ነው፥ ዳዊትም ሆነ ሰለሞን የተቀመጡት በእግዚአብሔር ዙፋን ላይ ነው። ታዲያ የእግዚአብሔር እና የዳዊት ዙፋን አንድ ስለሆነ ዳዊት ይመለካልን? እንደ ባይብሉ ኢየሱስም የተሰጠው ዙፋን የዳዊት ዙፋን ነው፦
ሉቃስ 1፥32 እርሱ ታላቅ ይሆናል የልዑል ልጅም ይባላል፥ *ጌታ አምላክም የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል*።

በእግዚአብሔር እና በበጉ ዙፋን ላይ ከኢየሱስ ጋር የሚቀመጡ አማንያንም ጭምር ናቸው፦
ራእይ 3፥21 እኔ ደግሞ ድል እንደ ነሣሁ *"ከአባቴም ጋር በዙፋኑ ላይ እንደተቀመጥሁ"*፥ ድል ለነሣው *"ከእኔ ጋር በዙፋኔ ላይ ይቀመጥ"* ዘንድ እሰጠዋለሁ።

በዙፋኑ ላይ የሚቀመጡት አማንያንስ ይመለካሉን? ሲጀመር ኢየሱስ ዙፋኑን ከጌታ አምላክ በስጦታ ያገኘው ነው፥ ሲቀጥል እግዚአብሔር ለኢየሱስ የሰጠውን ነገር ሁሉ ለአማንያንም ይሰጣል፦
ሮሜ 8፥32 *"ከእርሱ ጋር ደግሞ "ሁሉን ነገር" እንዲያው እንዴት አይሰጠንም?*

"ሁሉን ነገር" የሚለው ይሰመርበት። ለወልድ የተሰጠው "ሁሉ ነገር" እግዚአብሔር ከኢየሱስ ጋር ሁሉን ነገር ለአማንያን ይሰጣል። ለምሳሌ ሥልጣን፣ ፍርድ፣ ንግሥና፣ ዙፋን ወዘተ። ኢየሱስ ምንም የራሱ ነገር የለውም። ሁሉንም በስጦታ ያገኘው ነው፦
ሉቃስ 10፥22 *"ሁሉ ከአባቴ ዘንድ ተሰጥቶኛል"*።
ዮሐንስ 17፥10 *"የእኔም የሆነ ሁሉ የአንተ ነው፥ የአንተውም የእኔ ነው"*፤ እኔም ስለ እነርሱ ከብሬአለሁ።

የኢየሱስ የሆነ ሁሉ ከአብ የተሰጠው ስለሆነ "የእኔም የሆነ ሁሉ የአንተ ነው" አለ፥ ግን የእግዚአብሔር የሆነ ሁሉ የኢየሱስ ስላልሆነ "የአንተውም የእኔ ነው" አለ እንጂ "የአንተ "ሁሉ" የእኔ ነው" አላለም። የአንተ ዙፋን የእኔ ነው ማለቱ ነው፥ የእግዚአብሔር ዙፋን የዳዊት ዙፋን ነው እንደማለት ነው። ከሌላ ማንነት ሥልጣን፣ ፍርድ፣ ንግሥና፣ ዙፋን እረ ሕይወትም ሳይቀር የተሰጠው ማንነት በፍጹም አይመለክም፦
ዮሐንስ 5፥26 አብ በራሱ ሕይወት እንዳለው እንዲሁ ደግሞ *"ለወልድ በራሱ ሕይወት እንዲኖረው ሰጥቶታልና"*።

ሕይወት አልባ የነበረውን የኢየሱስን ማንነት ሕይወት በመስጠት ወደ ህልውና ያመጣ ማንነት በእውነት ሊመለክ ይገባዋል።
ኢየሱስ የትምህርቱ ጭብጥ፦ “አላህ ጌታዬና ጌታችሁ ነው፤ ስለዚህ አምልኩት” የሚል ነው፤ አምላካችን አላህም ኢየሱስ ተናገር ብሎ ያዘዘው ቃል “ጌታዬንና ጌታችሁን አላህን አምልኩ” ማለትን ነው፦
5፥117 በእርሱ ያዘዝከኝን ቃል *”ጌታዬንና ጌታችሁን አላህን አምልኩ”* ማለትን እንጂ ለእነርሱ ሌላ አላልኩም፡፡ مَا قُلْتُ لَهُمْ إِلَّا مَآ أَمَرْتَنِى بِهِۦٓ أَنِ ٱعْبُدُوا۟ ٱللَّهَ رَبِّى وَرَبَّكُمْ
3፥51 *”አላህ ጌታዬና ጌታችሁ ነው፤ ስለዚህ አምልኩት”* ፤ ይህ ቀጥተኛ መንገድ ነው» አላቸው፡፡ إِنَّ ٱللَّهَ رَبِّى وَرَبُّكُمْ فَٱعْبُدُوهُ ۗ هَٰذَا صِرَٰطٌۭ مُّسْتَقِيمٌۭ

ስለዚህ አንድ ተመላኪ አለ እርሱም ኢየሱስን መልእክተኛ አድርጎ የላከ አላህ ብቻ ነው። እርሱም፦ "እኔን ብቻ አምልኩኝ" ይላል፦
29፥56 እናንተ ያመናችሁ ባሮቼ ሆይ! ምድሬ በእርግጥ ሰፊ ናት፤ ብትቸገሩ ተሰደዱ፡፡ *”እኔንም ብቻ አምልኩኝ”*፡፡ يَٰعِبَادِىَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ إِنَّ أَرْضِى وَٰسِعَةٌۭ فَإِيَّٰىَ فَٱعْبُدُونِ

ከኡሥታዝ ወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም
2025/07/10 10:29:09
Back to Top
HTML Embed Code: