Telegram Web Link
ወርቃማው ሕግ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

4፥36 አላህንም አምልኩ፡፡ በእርሱም ምንንም አታጋሩ፡፡ *"በወላጆችና በቅርብ ዝምድና ባለቤትም፣ በየቲሞችም፣ በምስኪኖችም፣ በቅርብ ጎረቤትም፣ በሩቅ ጎረቤትም፣ በጎን ባልደረባም፣ በመንገደኛም፣ እጆቻችሁም ንብረት ባደረጓቸው፣ መልካምን ሥሩ"*። አላህ ኩራተኛ ጉረኛ የኾነን ሰው አይወድም፡፡ وَاعْبُدُوا اللَّهَ وَلَا تُشْرِكُوا بِهِ شَيْئًا ۖ وَبِالْوَالِدَيْنِ إِحْسَانًا وَبِذِي الْقُرْبَىٰ وَالْيَتَامَىٰ وَالْمَسَاكِينِ وَالْجَارِ ذِي الْقُرْبَىٰ وَالْجَارِ الْجُنُبِ وَالصَّاحِبِ بِالْجَنبِ وَابْنِ السَّبِيلِ وَمَا مَلَكَتْ أَيْمَانُكُمْ ۗ إِنَّ اللَّهَ لَا يُحِبُّ مَن كَانَ مُخْتَالًا فَخُورًا

ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ያለ አብላጫውን ሾላ በድፍኑ ሆኖ፦ "እኔ ከሞትኩኝ ሰርዶ በእኔ ላይ አይብቀል" እንዳለችው አህያ ሆኗል ብዬ ብናገር እብለት ወይም ቅጥፈት አሊያም ግነት አይሆንብኝም። አበው፦ "እፍ ብለህ ታነዳነህ እፍ ብለህ ታጠፋለህ አጠቃቀምህ ነው" ይላሉ። መገናኛ ብዙኃንን ለአውንታዊ ማሕበረሰብ ግንባታ አሊያም ለአውንታዊ ማኅበረሰብ ውድቀት ሊውል ይችላል፥ አጠቃቀማችን ነው። ለአሉታዊ ከተጠቀምንበት በለስ የቀናው ያጠፋበታል እድል የጎደለው ይጠፋበታል። ማኅበራዊ ሚድያ ላይ ያለው አብዛኛውን ማለት ይቻላል የሌላን ሰው ስሜት፣ ፍላጎት፣ አስተሳሰብ፣ አመለካከት ማንቋሸሽ ሥራዬ ብሎ ተያይዞታል። ይህ የሆነው ወርቃማውን ሕግ ስለረሳን ነው። ይህ ወርቃማው ሕግ ምንድን ነው?
አምላካችን አላህ ስለ ሥነ-ምግባር መርኆ ሲናገር፦ "በወላጆችና በቅርብ ዝምድና ባለቤትም፣ በየቲሞችም፣ በምስኪኖችም፣ በቅርብ ጎረቤትም፣ በሩቅ ጎረቤትም፣ በጎን ባልደረባም፣ በመንገደኛም፣ እጆቻችሁም ንብረት ባደረጓቸው፣ መልካምን ሥሩ" ነው፦
4፥36 አላህንም አምልኩ፡፡ በእርሱም ምንንም አታጋሩ፡፡ *"በወላጆችና በቅርብ ዝምድና ባለቤትም፣ በየቲሞችም፣ በምስኪኖችም፣ በቅርብ ጎረቤትም፣ በሩቅ ጎረቤትም፣ በጎን ባልደረባም፣ በመንገደኛም፣ እጆቻችሁም ንብረት ባደረጓቸው፣ መልካምን ሥሩ"*። አላህ ኩራተኛ ጉረኛ የኾነን ሰው አይወድም፡፡ وَاعْبُدُوا اللَّهَ وَلَا تُشْرِكُوا بِهِ شَيْئًا ۖ وَبِالْوَالِدَيْنِ إِحْسَانًا وَبِذِي الْقُرْبَىٰ وَالْيَتَامَىٰ وَالْمَسَاكِينِ وَالْجَارِ ذِي الْقُرْبَىٰ وَالْجَارِ الْجُنُبِ وَالصَّاحِبِ بِالْجَنبِ وَابْنِ السَّبِيلِ وَمَا مَلَكَتْ أَيْمَانُكُمْ ۗ إِنَّ اللَّهَ لَا يُحِبُّ مَن كَانَ مُخْتَالًا فَخُورًا

ለሰዎች በጎ ማድረግ ካልተቻለ ሰዎች እኛ ላይ ሊያደርጉብህ የማንፈልገውን ነገር በሌላው ላይ አለማድረግ ነው። ይህ ወርቃማ ሕግ ይባላል። ነቢያችን"ﷺ" ስለዚህ ወርቃማ ሕግ ሲናገሩ፦ "ከእናንተ አንድም አላመነም ለራሱ የሚወደውን ለወንድሙ እስካልወደደ ድረስ ወይም ለራሱ የሚወደውን ለጎረቤቱ እስካልወደደ ድረስ" ብለዋል፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 1, ሐዲስ 77
አነሥ ኢብኑ ማሊክ"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ ነቢዩም"ﷺ" አሉ፦ *"ከእናንተ አንድም አላመነም ለራሱ የሚወደውን ለወንድሙ እስካልወደደ ድረስ ወይም ለራሱ የሚወደውን ለጎረቤቱ እስካልወደደ ድረስ"*፡፡ يُحَدِّثُ عَنْ أَنَسِ بْنِ مَالِكٍ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ لاَ يُؤْمِنُ أَحَدُكُمْ حَتَّى يُحِبَّ لأَخِيهِ - أَوْ قَالَ لِجَارِهِ - مَا يُحِبُّ لِنَفْسِه
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 2, ሐዲስ 6
አነሥ"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ ነቢዩም"ﷺ" አሉ፦ *"ከእናንተ አንድም አላመነም ለራሱ የሚወደውን ለወንድሙ እስካልወደደ ድረስ"*፡፡ عَنْ أَنَسٍ ـ رضى الله عنه ـ عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم‏.‏
وَعَنْ حُسَيْنٍ الْمُعَلِّمِ، قَالَ حَدَّثَنَا قَتَادَةُ، عَنْ أَنَسٍ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ لا يُؤْمِنُ أَحَدُكُمْ حَتَّى يُحِبَّ لأَخِيهِ مَا يُحِبُّ لِنَفْسِهِ

ኢማም ነወዊይ ይህንን ሐዲስ ሲያብራሩ፦
ሸርሑል አርበዒን 13
*"እዚህ ንግግር ላይ "ወንድሙ" የተባለው በጥቅሉ ሙሥሊሙንም ካ/ም ነው"*።
የራሱ ስሜት፣ ፍላጎት፣ አስተሳሰብ፣ አመለካከት እንዲነካበት የማይፈልግ የሌላው ሰው ስሜት፣ ፍላጎት፣ አስተሳሰብ፣ አመለካከት አይነካም። ይህ ወርቃማ የሥነ-ምግባር ሕግ የነቢያት ሁሉ አስተምህሮት ነው፦
ማቴዎስ 7፥12 እንግዲህ *"ሰዎች ሊያደርጉላችሁ የምትወዱትን ሁሉ እናንተ ደግሞ እንዲሁ አድርጉላቸው፤ ሕግም ነቢያትም ይህ ነውና"*።

ኡሥታዝ ወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም
የበለጠ ለማወቅ
ጥሪያችን Tiriyachen
https://fb.me/tiriyachen

ወሰላሙ አለይኩም
👍3
መተት

ክፍል አንድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

17፥47 እኛ ወደ አንተ በሚያዳምጡ ጊዜ እነርሱም በሚንሾካሾኩ ጊዜ በዳዮች እርስ በርሳቸው *"የተደገመበትን ሰው እንጂ አትከተሉም በሚሉጊዜ"* በእርሱ የሚያዳምጡበትን ምክንያት ዐዋቂ ነን፡፡ نَّحْنُ أَعْلَمُ بِمَا يَسْتَمِعُونَ بِهِۦٓ إِذْ يَسْتَمِعُونَ إِلَيْكَ وَإِذْ هُمْ نَجْوَىٰٓ إِذْ يَقُولُ ٱلظَّٰلِمُونَ إِن تَتَّبِعُونَ إِلَّا رَجُلًۭا مَّسْحُورًا

መግቢያ
"ዒስማ" عِصْمَة‌‎ ማለት ከኃጢያት "ጥበቃ"protection" ማለት ሲሆን "ማዕሱም" معصوم‌‎ ደግሞ ከኃጢያት የሚጠበቀው ነብይ ነው፤ ኃጢያት በሁለት ይከፈላል፦
"ከባኢር" كبائر ማለት "አበይት ኃጢያት"ሲሆን እነርሱም፦ ሺርክ፣ ዝሙት፣ አራጣ፣ ቁማር፣ ቅጥፈት፣ ሌብነት ወዘተ..ናቸው።
"ሰጋኢር" صغائر ማለት "ንዑሳን ኃጢያት" ሲሆኑ በአለማወቅ አሊያም በአለፍፅምና የሚመጡ ስህተት ናቸው፤ ለምሳሌ መናደድ፣ መቆጣት፣ ማዘን፣ መበሳጨት ወዘተ፦
53፥32 እነዚያ የኃጢያትን “ታላላቆችና” አስጠያፊዎቹን የሚርቁ ናቸው፤ ግን "ትናንሾቹ" የሚማሩ ናቸው። ጌታህ ምሕረተ ሰፊ ነውና፤ ٱلَّذِينَ يَجْتَنِبُونَ كَبَٰٓئِرَ ٱلْإِثْمِ وَٱلْفَوَٰحِشَ إِلَّا ٱللَّمَمَ ۚ إِنَّ رَبَّكَ وَٰسِعُ ٱلْمَغْفِرَةِ
4፥31 ከእርሱ ከተከለከላችሁት “ታላላቆቹን” ብትርቁ “ትናንሾቹን ኃጢአቶቻችሁን” ከእናንተ እናብሳለን፤ የተከበረንም ስፍራ እናገባችኋለን፡፡ إِن تَجْتَنِبُوا۟ كَبَآئِرَ مَا تُنْهَوْنَ عَنْهُ نُكَفِّرْ عَنكُمْ سَيِّـَٔاتِكُمْ وَنُدْخِلْكُم مُّدْخَلًۭا كَرِيمًۭا
42፥37 ለእነዚያም “የኀጢያትን ታላላቆችና” ጠያፎችን የሚርቁ በተቆጡም ጊዜ እነርሱ የሚምሩ ለሆኑት። وَٱلَّذِينَ يَجْتَنِبُونَ كَبَٰٓئِرَ ٱلْإِثْمِ وَٱلْفَوَٰحِشَ وَإِذَا مَا غَضِبُوا۟ هُمْ يَغْفِرُونَ

እንግዲያውስ በኢስላም ነብያት የሚጠበቁት ከአበይት ኃጢያት ነው፤ ከንዑሳን ኃጢያት እንደማንኛውም ሰው አለፍፅምና ስላለባቸው በራሳቸው ሆነ በሰይጣን ሊሳሳቱ ይችላሉ፤ ለምሳሌ አደም ነብይ ነው፤ ግን ሰይጣን ወደ እርሱ ጎትጉቶት የጌታውን ትእዛዝ ጣሰ፤ ተሳሳተም፦
20፥120 ሰይጣንም ወደ እርሱ ጎተጎተ «አደም ሆይ! በመዘውተሪያ ዛፍ በማይጠፋ ንግሥናም ላይ ላመላክትህን አለው፡፡ فَوَسْوَسَ إِلَيْهِ ٱلشَّيْطَٰنُ قَالَ يَٰٓـَٔادَمُ هَلْ أَدُلُّكَ عَلَىٰ شَجَرَةِ ٱلْخُلْدِ وَمُلْكٍۢ لَّا يَبْلَىٰ
20፥121 ከእርሷም በሉ፡፡ ለእነርሱም ኀፍረተ ገላቸው ተገለጸች፡፡ ከገነትም ቅጠል በላያቸው ላይ ይለጥፉ ጀመር፡፡ *"አደምም የጌታውን ትእዛዝ ጣሰ፤ ተሳሳተም"*፡፡ فَأَكَلَا مِنْهَا فَبَدَتْ لَهُمَا سَوْءَٰتُهُمَا وَطَفِقَا يَخْصِفَانِ عَلَيْهِمَا مِن وَرَقِ ٱلْجَنَّةِ ۚ وَعَصَىٰٓ ءَادَمُ رَبَّهُۥ فَغَوَىٰ

በተመሳሳይ ሰይጣን ኢዮብን በጉዳትና በስቃይ ጎድቶታል፤ እንደ ባይብሉም ከእግሩ ጫማ ጀምሮ እስከ አናቱ ድረስ በክፉ ቍስል መቶታል፤ ይህ ሲደረግ ሰይጣንን እግዚአብሔርም ሕይወቱን ተወው እንጂ እርሱ በእጅህ ነው አለው፦
38፥41 ባሪያችንን አዩብንም አውሳላቸው፡፡ *«እኔ ሰይጣን በጉዳትና በስቃይ ነካኝ»* ሲል ጌታውን በተጣራ ጊዜ፡፡ وَٱذْكُرْ عَبْدَنَآ أَيُّوبَ إِذْ نَادَىٰ رَبَّهُۥٓ أَنِّى مَسَّنِىَ ٱلشَّيْطَٰنُ بِنُصْبٍۢ وَعَذَابٍ
ኢዮብ 2፥6-7 እግዚአብሔርም ሰይጣንን ሕይወቱን ተወው እንጂ እነሆ፥ እርሱ በእጅህ ነው አለው። ሰይጣንም ከእግዚአብሔር ፊት ወጣ፥ ኢዮብንም ከእግሩ ጫማ ጀምሮ እስከ አናቱ ድረስ በክፉ ቍስል መታው።

እንዲሁ ሰይጣን ዳዊትን፦ "ሂድ፥ እስራኤልንና ይሁዳን ቍጠር" ብሎ አዞት ቆጥሯል፦
2ኛ ሳሙኤል 24.1 ደግሞም የእግዚአብሔር ቍጣ በእስራኤል ላይ ነደደ፥ ዳዊትንም፦ *ሂድ፥ እስራኤልንና ይሁዳን ቍጠር* ብሎ በላያቸው አስነሣው።
1ኛ ዜና መዋዕል 21፥1 ሰይጣንም በእስራኤል ላይ ተነሣ፥ እስራኤልንም ይቈጥር ዘንድ ዳዊትን “አንቀሳቀሰው”።

በተመሳሳይ ሰይጣን ኢየሱስን ወደ ከተማና ወደ ተራራ እየወሰደ የዓለምንም መንግሥታት ሁሉ ክብራቸውንም ያሳየው ነበር፦
ማቴዎስ 4፥5 ከዚህ በኋላ *"ዲያቢሎስ ወደ ቅድስት ከተማ ወሰደው"* እና እርሱን በመቅደስ ጫፍ ላይ አቁሞ።
ማቴዎስ 4፥8 ደግሞ *"ዲያቢሎስ እጅግ ረጅም ወደ ሆነ ተራራ ወሰደው"*፥ የዓለምንም መንግሥታት ሁሉ ክብራቸውንም አሳይቶ።
ሉቃስ 4:13 ዲያቢሎስም ፈተናውን ሁሉ ከጨረሰ በኋላ *"እስከ ጊዜው ከእርሱ ተለየ"*።

"እስከ ጊዜው ከእርሱ ተለየ" የሚለው ይሰመርበት፤ ሰይጣን ከኢየሱስ ከመለየቱ በፊት ከኢየሱስ ጋር ነበር ማለት ነው፤ የተለየውም ለጊዜው እንደሆነ ተጽፏል፤ ሰይጣን ይህ ሁሉ ነገር በነብያቱ ላይ ሲፈፀም አምላክ እንዴት ዝም አለ? አይ ፈጣሪ ዝም የሚልበት የራሱ ጥበብ አለው ከሆነ መልሱ እንግዲያውስ ነብያችን"ﷺ" በድግምት ተፅእኖ ቢደርስባቸው ምኑ ያስደንቃል? እስቲ ስለ መተት ተፅዕኖ በሁለቱም መጽሐፍት እንመልከት፦

ነጥብ አንድ
"መተት በቁርአን"
ስለ መተት በቁርአን ያለው እሳቤ እንመልከት፤ “ሲሕር” سِحْر የሚለው ቃል “ሰሐረ” سحر ማለትም “ደገመ” ከሚል ስርወ-ግንድ የረባ ሲሆን “ድግምት” "መተት" "አስማት" ማለት ነው፤ ድግምቱን የሚሰራው ሰው ደግሞ “ሳሒር” سَٰحِر ይባላል፤ “ሱሑር” سحور ማለትም በረመዳን ፆም ለመያዝ ከሌሊቱ መጨረሻ የሚመገቡት ምግብ እና “ሰሐር” سَحَر ማለትም “የሌሊት መጨረሻ”before down” የሚሉት ሁለቱ ቃላት ልክ እንደ ሲሕር “ሰሐረ” سحر ከሚለው ስርወ-ግንድ የመጡ ናቸው።
በባቢሎት በሚገኙት በሀሩትና በማሩት ላይ የተወረደው የሲሕር ትምህርት ሰዎችን እንዴት እንደሚጎዳ ማስጠንቀቂያ ሆኖ ነው፤ ነገር ግን ሰይጣናትም በሱለይማን ዘመነ መንግስት ሰዎችን የሚያስተምሩት ለአሉታዊ ነገር ነበር፦
2፥102 ሰይጣናትም በሱለይማን ዘመነ መንግስት የሚያነቡትን ተከተሉ፡፡ ሱለይማንም አልካደም፤ ግን ሰይጣናት ሰዎችን ድግምትን የሚያስተምሩ ሲኾኑ ካዱ፡፡ ያንንም በባቢል በሁለቱ መላእክት በሃሩትና ማሩት ላይ የተወረደውን ነገር ያስተምሩዋቸዋል፡፡ «እኛ መፈተኛ ነንና አትካድ» እስከሚሉም ድረስ አንድንም አያስተምሩም፡፡ ከእነሱም በሰውየውና በሚስቱ መካከል በርሱ የሚለዩበትን ነገር ይማራሉ፡፡ وَٱتَّبَعُوا۟ مَا تَتْلُوا۟ ٱلشَّيَٰطِينُ عَلَىٰ مُلْكِ سُلَيْمَٰنَ ۖ وَمَا كَفَرَ سُلَيْمَٰنُ وَلَٰكِنَّ ٱلشَّيَٰطِينَ كَفَرُوا۟ يُعَلِّمُونَ ٱلنَّاسَ ٱلسِّحْرَ وَمَآ أُنزِلَ عَلَى ٱلْمَلَكَيْنِ بِبَابِلَ هَٰرُوتَ وَمَٰرُوتَ ۚ وَمَا يُعَلِّمَانِ مِنْ أَحَدٍ حَتَّىٰ يَقُولَآ إِنَّمَا نَحْنُ فِتْنَةٌۭ فَلَا تَكْفُرْ ۖ فَيَتَعَلَّمُونَ مِنْهُمَا مَا يُفَرِّقُونَ بِهِۦ
1
بَيْنَ ٱلْمَرْءِ وَزَوْجِهِۦ

ሲሕር በግብጻውያን ዘንድ በጣም የታወቀ ስራ ነው፤ የግብጻውያን ሳሒሪን ዘንጎቻቸውን ወደ እባብ በመቀየት የሰዎች ዓይኖች ላይ ደግመውባቸው ነበር፦
20፥66 «አይደለም ጣሉ» አላቸው፡፡ ወዲያውም ገመዶቻቸውና ዘንጎቻቸው *"ከድግምታቸው የተነሳ እነርሱ የሚሮጡ እባቦች ኾነው ወደ እርሱ ተመለሱ"*፡፡ قَالَ بَلْ أَلْقُوا۟ ۖ فَإِذَا حِبَالُهُمْ وَعِصِيُّهُمْ يُخَيَّلُ إِلَيْهِ مِن سِحْرِهِمْ أَنَّهَا تَسْعَىٰ
7፥116 «ጣሉ» አላቸው፡፡ በጣሉም ጊዜ *"የሰዎቹን ዓይኖች ደገሙባቸው"*፡፡ አስፈራሩዋቸውም፡፡ *ትልቅ ድግምትንም"* አመጡ፡፡ قَالَ أَلْقُوا۟ ۖ فَلَمَّآ أَلْقَوْا۟ سَحَرُوٓا۟ أَعْيُنَ ٱلنَّاسِ وَٱسْتَرْهَبُوهُمْ وَجَآءُو بِسِحْرٍ عَظِيمٍۢ

ትእይንቱን ከሚከታተሉት እና አይኖቻቸው የሚቀጣጥፉትን የድግምተኛ ተንኮል ካዩት መካከል ሙሳ በነፍሱ ውስጥ ፍርሃትን አሳደረ፦
20፥67 ሙሳም *"በነፍሱ ውስጥ ፍርሃትን አሳደረ"*፡፡ فَأَوْجَسَ فِى نَفْسِهِۦ خِيفَةًۭ مُّوسَىٰ

ነገር ግን አላህ ሲሕር ሲሰራ ዝም ማለቱ ለሲሕሩ ማክሸፈያ ሊያመጣ መሆኑን ያሳያል፤ የሙሳ በትር የሚቀጣጥፉትን ዘንግ ውጣዋለች፦
20፤69 «በቀኝ እጅህ ያለቸውንም በትር ጣል፡፡ ያንን የሠሩትን ትውጣለችና፡፡ *"ያ የሠሩት ሁሉ የድግምተኛ ተንኮል ነውና"*፡፡ ድግምተኛም በመጣበት ስፍራ ሁሉ አይቀናውም» አልን፡፡ وَأَلْقِ مَا فِى يَمِينِكَ تَلْقَفْ مَا صَنَعُوٓا۟ ۖ إِنَّمَا صَنَعُوا۟ كَيْدُ سَٰحِرٍۢ ۖ وَلَا يُفْلِحُ ٱلسَّاحِرُ حَيْثُ أَتَىٰ
7፥117 ወደ ሙሳም፡- «በትርህን ጣል» ስንል ላክን፡፡ ጣላትም ወዲያውኑም *"የሚቀጣጥፉትን ትውጣለች"*፡፡ وَأَوْحَيْنَآ إِلَىٰ مُوسَىٰٓ أَنْ أَلْقِ عَصَاكَ ۖ فَإِذَا هِىَ تَلْقَفُ مَا يَأْفِكُونَ

በተመሳሳይ ነብያችን"ﷺ" ላይ ሲሕር ተደርጎባቸው ነበር፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 80 , ሐዲስ 86:
ዓኢሻ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው፦ የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” በድግምት ተፅእኖ ደርሶባቸው ነበር፤ ያላደረጉትን እንዳደረጉ ያስቡ ነበር፤ عَنْ عَائِشَةَ ـ رضى الله عنها أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم طُبَّ حَتَّى إِنَّهُ لَيُخَيَّلُ إِلَيْهِ قَدْ صَنَعَ الشَّىْءَ وَمَا صَنَعَهُ،

አላህም ለሲሕሩ ማክሸፈያ "አል-ሙዐወዘተይን" الْمُعَوِّذَتَيْن የሚባሉት ሁለቱ ሱራዎች ሱረቱል ፈለቅ እና ሱረቱ አን-ናስ አውርዷል፦
ኢማም ሙስሊም መጽሐፍ 6 , ሐዲስ 319:
የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” አሉ፦ ዛሬ ምን አስደናቂ አንቀጾች ዛሬ ወርደዋል፤ ይህም ብጤአቸው ታይቶ አያውቅም! እነርሱም፦ "በል «በተፈልቃቂው ጎህ ጌታ እጠበቃለሁ" እና በል «በሰዎች ፈጣሪ እጠበቃለሁ» ናቸው። قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏"‏ أَلَمْ تَرَ آيَاتٍ أُنْزِلَتِ اللَّيْلَةَ لَمْ يُرَ مِثْلُهُنَّ قَطُّ ‏{‏ قُلْ أَعُوذُ بِرَبِّ الْفَلَقِ‏}‏ وَ ‏{‏ قُلْ أَعُوذُ بِرَبِّ النَّاسِ‏}‏ ‏"‏

ታላቁ ሙፈሲር ኢብኑ ከሲር ስለ "አል-ሙዐወዘተይን" ሲናገር፦ "በሌላ ሐዲስ እንደተዘገበው፦ "ጂብሪል ወደ ነብዩ”ﷺ” መጥቶ እንዲህ አላቸው፦ "ሙሐመድ”ﷺ” ሆይ በማንኛውም ህመም እየተሰቃየህ ነውን? ነብዩም”ﷺ” ነዐም ብለው መለሱ፤ ጂብሪልም በአላህ ስም ሩቂያ እቀራብሃለው፤ ከማንኛውም በሽታ አንተን የጎዳህን፤ ከእያንዳንዱ ሸረኛ እና ክፉ ዓይን፤ አላህ ይፈውስሃል"።
ጃምዒ አት-ተርሚዚ መጽሐፍ 10 , ሐዲስ 8:
"ጂብሪል ወደ ነብዩ”ﷺ” መጥቶ እንዲህ አላቸው፦ "ሙሐመድ”ﷺ” ሆይ በማንኛውም ህመም እየተሰቃየህ ነውን? ነብዩም”ﷺ” ነዐም ብለው መለሱ፤ ጂብሪልም በአላህ ስም ሩቂያ እቀራብሃለው፤ ከማንኛውም በሽታ አንተን የጎዳህን፤ ከእያንዳንዱ ሸረኛ እና ክፉ ዓይን፤ አላህ ይፈውስሃል"። أَنَّ جِبْرِيلَ، أَتَى النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم فَقَالَ يَا مُحَمَّدُ اشْتَكَيْتَ قَالَ ‏ "‏ نَعَمْ ‏"‏ ‏.‏ قَالَ بِاسْمِ اللَّهِ أَرْقِيكَ مِنْ كُلِّ شَيْءٍ يُؤْذِيكَ مِنْ شَرِّ كُلِّ نَفْسٍ وَعَيْنِ حَاسِدٍ بِاسْمِ اللَّهِ أَرْقِيكَ وَاللَّهُ يَشْفِيكَ ‏.‏
.
"አል-ሙዐወዘተይን" እራሱ ለሲሕር "ሩቂያ" رقيّة ነው፤ ሩቂያ ማለት "ፈውስ" ማለት ሲሆን የቁርአን አናቅፅ መድሃኒት ነው፦
17:82 “ከቁርአንም” ለምእመናን ”መድኀኒት” እና እዝነት የሆነን ”እናወርዳለን”፤በዳዮችንም ከሳራን እንጂ ሌላን አይጨምርላቸውም። وَنُنَزِّلُ مِنَ ٱلْقُرْءَانِ مَا هُوَ شِفَآءٌۭ وَرَحْمَةٌۭ لِّلْمُؤْمِنِينَ ۙ وَلَا يَزِيدُ ٱلظَّٰلِمِينَ إِلَّا خَسَارًۭا
10:57 እናንተ ሰዎች ሆይ! ከጌታችሁ ግሳጼ ”በደረቶች” ውስጥም ላለው በሽታ “”መድኃኒት”” ለምእምናንም ብርሃንና እዝነት በእርግጥ “መጣችላችሁ”፡፡ يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّاسُ قَدْ جَآءَتْكُم مَّوْعِظَةٌۭ مِّن رَّبِّكُمْ وَشِفَآءٌۭ لِّمَا فِى ٱلصُّدُورِ وَهُدًۭى وَرَحْمَةٌۭ لِّلْمُؤْمِنِينَ

የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” የሲሕር በሽታ ፈውስ ካገኙ በኃላ ይህ በቅጠላ-ቅጠል እና የዕፅ ስር በመበጠስ ሰው ላይ ለሚተበተብ በሽታ ጠዋት ጠዋት ሰባት የዘንባባ ተምር መብላት መድሃኒት እንደሆነ ነግረውናል፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 70 , ሐዲስ 74:
የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” አሉ፦ ማንኛውም ሰው ጠዋት ጠዋት ሰባት የዘንባባ ተምር የሚበላ በበላበት ቀን በመርዝ እና በመተት አይጠቃም። حَدَّثَنَا جُمْعَةُ بْنُ عَبْدِ اللَّهِ، حَدَّثَنَا مَرْوَانُ، أَخْبَرَنَا هَاشِمُ بْنُ هَاشِمٍ، أَخْبَرَنَا عَامِرُ بْنُ سَعْدٍ، عَنْ أَبِيهِ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ مَنْ تَصَبَّحَ كُلَّ يَوْمٍ سَبْعَ تَمَرَاتٍ عَجْوَةً لَمْ يَضُرُّهُ فِي ذَلِكَ الْيَوْمِ سُمٌّ وَلاَ سِحْرٌ ‏"‌‏.‏

በኢስላም ወንጀለኛ ሲሕር የተደረገበት ሰው ሳይሆን ድግምተኛ ሰው ነው፤ በነብያችን”ﷺ” ወቅት የነበሩ በዳዮች ነብያችንን”ﷺ” የተደገመበትን ሰው ይሉ ነበር፤ ይህ የከንቱዎች መሳለቂያ ነበር፦
2
17፥47 እኛ ወደ አንተ በሚያዳምጡ ጊዜ እነርሱም በሚንሾካሾኩ ጊዜ በዳዮች እርስ በርሳቸው *"የተደገመበትን ሰው እንጂ አትከተሉም በሚሉ ጊዜ"* በእርሱ የሚያዳምጡበትን ምክንያት ዐዋቂ ነን፡፡ نَّحْنُ أَعْلَمُ بِمَا يَسْتَمِعُونَ بِهِۦٓ إِذْ يَسْتَمِعُونَ إِلَيْكَ وَإِذْ هُمْ نَجْوَىٰٓ إِذْ يَقُولُ ٱلظَّٰلِمُونَ إِن تَتَّبِعُونَ إِلَّا رَجُلًۭا مَّسْحُورًا
25፥8 «ወይም ወደ እርሱ ድልብ አይጣልለትምን ወይም ከእርሷ የሚበላላት አትክልት ለእርሱ አትኖረውምን» አሉ፡፡ *በዳዮቹም ለአመኑት «የተደገመበትን ሰው እንጂ ሌላ አትከተሉም» አሉ*፡፡ أَوْ يُلْقَىٰٓ إِلَيْهِ كَنزٌ أَوْ تَكُونُ لَهُۥ جَنَّةٌۭ يَأْكُلُ مِنْهَا ۚ وَقَالَ ٱلظَّٰلِمُونَ إِن تَتَّبِعُونَ إِلَّا رَجُلًۭا مَّسْحُورًا

ለተሳላቂዎች ደግሞ አላህ በቂ ምላሽ ሰጥቷል፦
25፥41 ባዩህም ጊዜ ያ አላህ መልእክተኛ አድርጎ የላከው ይህ ነውን እያሉ *" መሳለቂያ እንጂ ሌላ አያደርጉህም"*፡፡ وَإِذَا رَأَوْكَ إِن يَتَّخِذُونَكَ إِلَّا هُزُوًا أَهَٰذَا ٱلَّذِى بَعَثَ ٱللَّهُ رَسُولًا
15፥95 *"ተሳላቂዎችን ሁሉ እኛ በቅተንሃል"*፡፡ إِنَّا كَفَيْنَٰكَ ٱلْمُسْتَهْزِءِينَ

ኢንሻላህ ስለ መተት በባይብል በክፍል ሁለት ይቀጥላል....

ኡሥታዝ ወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም

የበለጠ ለማወቅ
ጥሪያችን Tiriyachen
https://fb.me/tiriyachen

ወሰላሙ አለይኩም
👍41
1👍1😢1
የመተት ተፅዕኖ

ክፍል ሁለት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

ነጥብ ሁለት
"መተት በባይብል"
ስለ መተት በባይብል ያለው እሳቤ ደግሞ እስቲ በመጠኑን ቢሆን እንመልከት፤ "ፋርማሲይ"pharmacy" የሚለውም ቃል "ፋርማኮን" φάρμακον ከሚለው የግሪኩ ቃል የመጣ ሲሆን "ዕፅ"drug" ማለት ነው፤ ጥንት ግብፃውያን መተት፣ አስማት እና ድግምት የሚሰሩት በዕፅዋት ቅመማ ነው፤ በአገራችን "ዕፀ-መሰውር" ይሉታል፤ ይህ የዕፅ ሥራ በግሪክ ኮይኔ "ፋርማኮስ" φαρμάκων ሲባል ቃሉ አዲስ ኪዳን እንዲህ ሰፍሯል፦
ራእይ 18:23 የመብራትም ብርሃን ከእንግዲህ ወዲህ በአንቺ ውስየምድር አይበራም፥ የሙሽራና የሙሽራይቱም ድምጽ ከእንግዲህ ወዲህ በአንቺ ውስጥ ከቶ አይሰማም፤ ነጋዴዎችሽ የምድር መኳንንት ነበሩና፥ *በአስማትሽም* φαρμακείᾳ አሕዛብ ሁሉ ስተዋልና።"
ራእይ 9:21 ስለ መግደላቸውም ቢሆን ወይም ስለ *"አስማታቸው"* φαρμάκων ወይም ስለ ዝሙታቸው ወይም ስለ ስርቆታቸው ንስሐ አልገቡም።
ራእይ 21:8 ዳሩ ግን የሚፈሩና የማያምኑ የርኵሳንም የነፍሰ ገዳዮችም የሴሰኛዎችም *"የአስማተኛዎችም"* φαρμακοῖς ጣዖትንም የሚያመልኩ የሐሰተኛዎችም ሁሉ ዕድላቸው በዲንና በእሳት በሚቃጠል ባሕር ነው፤ ይኸውም ሁለተኛው ሞት ነው።"
ራእይ 22:15 ውሻዎችና *"አስማተኞች"* φαρμακοὶ ሴሰኛዎችም ነፍሰ ገዳዮችም ጣዖትንም የሚያመልኩት ውሸትንም የሚወዱና የሚያደርጉ ሁሉ በውጭ አሉ።"

"ምዋርት" ወይም "አስማት" ለሚለው ቃል የተጠቀመበት "ፋርማኮስ" φαρμάκων መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል፤ በብሉይ ኪዳን ግሪክ ሰፕቱጀንት"LXX" ላይም ይህ ቃል ነው የሰፈረው፤ በዕብራይስጡ ደግሞ "ከሻፍ" כָּשַׁף ሲሆን ግብጻውያን በሙሴ ዘመን የሰሩትት መተት ለማመልከት ተጠቅሞበታል፦
ዘጸአት 7:11 ፈርዖንም ጠቢባንን እና *"መተተኞችን" לָטִים ጠራ፤ የግብፅም ጠንቋዮች በአስማታቸው"* እንዲሁ ደግሞ አደረጉ።

ይህ ካየን ስለ በለዓም እንይ፤ በለዓም እግዚአብሔር የሚያናግረው የእግዚአብሔር ነብይ ነው፦
2ኛ የጴጥሮስ 2፥16 ነገር ግን ስለ መተላለፉ ተዘለፈ፤ ቃል የሌለው አህያ በሰው ቃል ተናግሮ *"የነቢዩን እብድነት"* አገደ።
ዘኍልቍ 23፥16 *እግዚአብሔርም በለዓምን ተገናኘ፥ ቃልንም በአፉ አድርጎ፦ ወደ ባላቅ ተመለስ፥ እንዲህም በል አለው*።

ይህ ነብይ አስማተኛ እና ምዋርተኛ ነበር፦
ዘኍልቍ 24፥1 በለዓምም እግዚአብሔር እስራኤልን ይባርክ ዘንድ እንዲወድድ ባየ ጊዜ፥ *"አስቀድሞ ያደርግ የነበረውን አስማት ይሻ ዘንድ አልሄደም"*፤ ነገር ግን ወደ ምድረ በዳ ፊቱን አቀና።
ኢያሱ 13፥22 ከገደሉአቸውም ሰዎች ጋር የእስራኤል ልጆች *"ምዋርተኛውን የቢዖርን ልጅ በለዓምን በሰይፍ ገደሉት"*።

የእስራኤል ልጆች ብዔልፌጎርን የተባለውን ጣዖት እንዲያመልኩ እና ከሞዓብ ልጆች ጋር ያመነዝሩ ያደረገው ይህ ነብይ ነው፦
ራእይ 2፥14 ዳሩ ግን *"ለጣዖት የታረደውን እንዲበሉ እና እንዲሴስኑ በእስራኤል ልጆች ፊት ማሰናከያን ሊያኖርባቸው ባላቅን ያስተማረ የበልዓምን ትምህርት"* የሚጠብቁ በዚያ ከአንተ ጋር ስላሉ ፥ የምነቅፍህ ጥቂት ነገር አለኝ ።
ዘኍልቍ 31:16 እነሆ፥ እነዚህ በፌጎር ምክንያት *"በበለዓም ምክር"* እግዚአብሔርን *"ይበድሉ ዘንድ ለእስራኤል ልጆች ዕንቅፋት ሆኑ"*፤ ስለዚህም በእግዚአብሔር ማኅበር ላይ መቅሠፍት ሆነ።
ዘኍልቍ 25፥1-3 እስራኤልም በሰጢም ተቀመጡ፤ *ሕዝቡም ከሞዓብ ልጆች ጋር ያመነዝሩ ጀመር። ሕዝቡንም ወደ አምላኮቻቸው መሥዋዕት ጠሩ፤ ሕዝቡም በሉ፥ ወደ አምላኮቻቸውም ሰገዱ። እስራኤልም ብዔልፌጎርን ተከተለ*፤ የእግዚአብሔርም ቍጣ በእስራኤል ላይ ነደደ።
ይሁዳ 1፥11 ወዮላቸው፥ በቃየል መንገድ ሄደዋልና ስለ ደመወዝም *"ለበለዓም ስሕተት"* ራሳቸውን አሳልፈው ሰጥተዋል በቆሬም መቃወም ጠፍተዋል።

ምዋርተኛውና አስማተኛው የአምላክ ነብይ በለዓም "በያዕቆብ ላይ አስማት የለም፥ በእስራኤልም ላይ ምዋርት የለም" ይበል እንጂ ድብን አድርጎ በእስራኤል ላይ "አስማት" ነበረ፦
ዘኍልቍ 23፥23 በያዕቆብ ላይ "አስማት" כְּשָׁפַ֔יִךְ የለም፥ በእስራኤልም ላይ "ምዋርት" የለም፤
2ኛ ነገሥት 21፥6 ልጁንም በእሳት አሳለፈ፥ ሞራ ገላጭም ሆነ፥ *"አስማትም" כְּשָׁפַ֔יִךְ አደረገ"*፥ መናፍስት ጠሪዎችንና ጠንቋዮችንም ሰበሰበ፤ ያስቈጣውም ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት እጅግ ክፉ ነገር አደረገ።
ኢሳይያስ 47፥9 አሁን ግን በአንድ ቀን እነዚህ ሁለት ነገሮች፥ የወላድ መካንነትና መበለትነት፥ በድንገት ይመጡብሻል፤ *ስለ "መተቶችሽ" כְּשָׁפַ֔יִךְ ብዛትና ስለ "አስማቶችሽ" ጽናት ፈጽመው ይመጡብሻል*።
ኢሳይያስ 47:12 ምናልባትም መጠቀም ትችዪ ወይም ታስደነግጪ እንደ ሆነ፥ *"ከአስማቶችሽ" כְּשָׁפַ֔יִךְ እና ከሕፃንነትሽ ጀምረሽ ከደከምሽበት ከመተቶችሽ ብዛት ጋር ቁሚ*።

ታዲያ የቱ ይከብዳል መተት የተደረገበት ነብይ ወይስ መተት አድራጊ ነብይ? ለጣዖት የታረደውን እንዲበሉና እንዲሴስኑ በእስራኤል ልጆች ፊት ማሰናከያን ያደረገ ነብይ ወይስ ተውሒድን ያስተማሪ ነብይ? ሰው ላይ አስማት ማድረግስ ወንጀል አይደለምን?፦
ዘዳግም 18፥11 *"አስማተኛም፥ መተተኛም"፥ በድግምት የሚጠነቍልም፥ መናፍስትንም የሚጠራ፥ ጠንቋይም፥ ሙታን ሳቢም በአንተ ዘንድ አይገኝ*።
ዘሌዋውያን 19፥26 ከደሙ ጋር ምንም አትብሉ፤ *"አስማትም አታድርጉ"*፥ ሞራ ገላጭም አትሁኑ።

መደምደሚያ
ሲጀመር ሲሕር በነብያችን"ﷺ" ላይ ተፅዕኖ ያሳደረባቸው በድርጊታቸው ላይ እንጂ በወሕይ ላይ አይደለም፤ ሲቀጥል ሲሕሩ በቅጠላ-ቅጠል ብጠሳ የሚደረግ በሽታ ነው፤ ሲሰልስ አላህ ነብያችን"ﷺ" ላይ ሲሕር ተፅዕኖ ሲያሳድር ዝም ያለበት ጥበብ ሰዎች ሲሕር ሲደርግባቸው እንዴት ማክሸፍ እንዳለባቸው ለማስተማር ነው እንጂ የተሳሳተ ሰው የተመራን ሰው አይጎዳም፦
5፥105 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! እራሳችሁን ከእሳት ጠብቁ፤ *"በተመራችሁ ጊዜ የተሳሳተ ሰው አይጎዳችሁም"*፡፡ የሁላችሁም መመለሻ ወደ አላህ ብቻ ነው፡፡ ትሠሩትም የነበራችሁትን ሁሉ ይነግራችኋል፡፡ يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ عَلَيْكُمْ أَنفُسَكُمْ ۖ لَا يَضُرُّكُم مَّن ضَلَّ إِذَا ٱهْتَدَيْتُمْ ۚ إِلَى ٱللَّهِ مَرْجِعُكُمْ جَمِيعًۭا فَيُنَبِّئُكُم بِمَا كُنتُمْ تَعْمَلُونَ

ሲያረብብ ከምንም በላይ ሰይጣን ሙኽሊሲን በሚባሉት የአላህ ባሮች ላይ ስልጣን የለውም፤ "ሙኽሊስ" مُخْلِص ማለት "አጥሪ" ማለት ሲሆን አምልኮቱ "ኢኽላስ" ያለው ማለት ነው፤ "ኢኽላስ" إخلاص ማለት እዩልኝና ስሙልኝ ያልታከለበት፣ ከሙገሳና ከወቀሳ ነጻ የሆነ፣ ለአላህ ውዴታ ተብሎ የሚደረግ ማጥራት፣ ፍጽምና፣ መተናነስ፣ መጎባደድ ማለት ነው፤ ሰይጣን ቃል የገባው ሙኽሊስ የተባሉትን የአላህ ባሮች እንደማይነካ ነው፦
👍31
38፥83 «ከእነርሱ *"ምርጥ የኾኑት ባሮችህ"* ብቻ ሲቀሩ፡፡» إِلَّا عِبَادَكَ مِنْهُمُ ٱلْمُخْلَصِينَ
15:40 «ከእነርሱ *"ፍጹሞቹ ባሮችህ"* ብቻ ሲቀሩ፡፡» إِلَّا عِبَادَكَ مِنْهُمُ ٱلْمُخْلَصِينَ
15፥42 «እነሆ *ባሮቼ በእነርሱ ላይ ለአንተ ስልጣን የለህም*፡፡ ከጠማሞቹ የተከተለህ ሰው ብቻ ሲቀር፡፡» إِنَّ عِبَادِى لَيْسَ لَكَ عَلَيْهِمْ سُلْطَٰنٌ إِلَّا مَنِ ٱتَّبَعَكَ مِنَ ٱلْغَاوِينَ
16፥109 እርሱ በእነዚያ ባመኑት እና በጌታቸው ላይ *"በሚጠጉት ላይ ለእርሱ ስልጣን የለውምና"*፡፡ إِنَّهُۥ لَيْسَ لَهُۥ سُلْطَٰنٌ عَلَى ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَعَلَىٰ رَبِّهِمْ يَتَوَكَّلُونَ
16፥100 *"ስልጣኑ በእነዚያ በሚታዘዙት ላይ እና በእነዚያም እነርሱ በእርሱ ምክንያት አጋሪዎች በኾኑት ላይ ብቻ ነው"*፡፡ إِنَّمَا سُلْطَٰنُهُۥ عَلَى ٱلَّذِينَ يَتَوَلَّوْنَهُۥ وَٱلَّذِينَ هُم بِهِۦ مُشْرِكُونَ

አላህ ሙኽሊሲን ከሚላቸው ባሮቹ ያርገን አሚን።

ከኡሥታዝ ወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም

Follow us on:
https://fb.me/tiriyachen
https://www.tg-me.com/tiriyachen
https://tiriyachen.org
https://bit.ly/3eVixKv
https://www.tiktok.com/@tiriyachen

ወሰላሙ አለይኩም
ጅኒ እና ሸያጢን

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡

2፥208 *እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ሁላችሁም በመታዘዝ ውስጥ ግቡ፡፡ የሰይጣንንም እርምጃዎች አትከተሉ፤ እርሱ ለእናንተ ግልጽ ጠላት ነውና*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا ادْخُلُوا فِي السِّلْمِ كَافَّةً وَلَا تَتَّبِعُوا خُطُوَاتِ الشَّيْطَانِ ۚ إِنَّهُ لَكُمْ عَدُوٌّ مُّبِينٌ

“ጂን” جِنّ የሚለው ቃል “ጀንነ” جَنَّ ማለትም “ተሰወረ” ወይም “ተደበቀ” ከሚል ግስ የመጣ ሲሆን “ስውር” ወይም “ድብቅ” ማለት ነው፤ “ጅኒ” جني ደግሞ የጂን ብዙ ቁጥር ነው፤ ጂኒዎች የተፈጠሩት ከሰው በፊት ነው፤ ሰው የተፈጠረበት ንጥረ-ነገር ዐፈር እንደሆነ፤ መልአክ የተፈጠረበት ንጥረ-ነገር ብርሃን እንደሆነ ሁሉ ጂን የተፈጠረበት ንጥረ-ነገር ደግሞ እሳት ነው፦
15፥27 *ጃንንም ከሰው በፊት ከእሳት ነበልባል ፈጠርነው*፡፡ وَالْجَانَّ خَلَقْنَاهُ مِن قَبْلُ مِن نَّارِ السَّمُومِ
ኢማም ሙስሊም መጽሐፍ 55, ሐዲስ 78
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”መላእክት ከብርሃን ተፈጥረዋል፤ ጂንዎች ከእሳት ነበልባል ተፈጥረዋል፤ አደም ለእናንተ እንደተገለጸላችሁ ከሚጭለቀለቅ ሸክላ ተፈጥሯል”*፡፡ عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم‏ خُلِقَتِ الْمَلاَئِكَةُ مِنْ نُورٍ وَخُلِقَ الْجَانُّ مِنْ مَارِجٍ مِنْ نَارٍ وَخُلِقَ آدَمُ مِمَّا وُصِفَ لَكُمْ ‏.‏

ጂኒዎች የተፈጠሩበት አላማ የፈጠራቸው አላህ እንዲያመልኩ ነው፦
51፥56 *ጂኒን እና ሰውንም ሊያመልኩኝ እንጅ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም*፡፡ وَمَا خَلَقْتُ الْجِنَّ وَالْإِنسَ إِلَّا لِيَعْبُدُونِ

ጂኒዎች እንደ ሰው ወንድና ሴት ሆነው የሚወለዱና የሚወልዱ፣ የሚኖሩና የሚሞቱ፤ የሚበሉና የሚጠጡ ፍጡሮች ናቸው፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 87, ሐዲስ 13
ኢብኑ ዐባስ”ረ.ዐ.” እንደተረከው ነብዩም”ﷺ” እንዲህ ይሉ ነበር፦ *”በሃያልነትህ እጠበቃለው፤ በእውነት የሚመለክ ከአንተ ከማትሞተው ሌላ የለም፤ ጂን እና ሰው ግን ይሞታል”*። أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم كَانَ يَقُولُ ‏ أَعُوذُ بِعِزَّتِكَ الَّذِي لاَ إِلَهَ إِلاَّ أَنْتَ، الَّذِي لاَ يَمُوتُ وَالْجِنُّ وَالإِنْسُ يَمُوتُونَ
ሱነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 1, ሐዲስ 312
ዘይድ ኢብኑ አርቀም እንደተረከው የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” አሉ፦ “ቆሻሻ ቦታዎች በሰይጣናት ይጎበኛሉ፤ ከእናንተም ወደዚያ ሲገባ፦ *”አላህ ሆይ! ከወንድ እና ከሴት ሰይጣናት በአንተ እጠበቃለው”* ይበል። عَنْ زَيْدِ بْنِ أَرْقَمَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ ‏ “‏ إِنَّ هَذِهِ الْحُشُوشَ مُحْتَضَرَةٌ فَإِذَا دَخَلَ أَحَدُكُمْ فَلْيَقُلِ اللَّهُمَّ إِنِّي أَعُوذُ بِكَ مِنَ الْخُبُثِ وَالْخَبَائِثِ ‏”‏ ‏.‏

ጂኒዎች እንደ ሰው ነጻ ምርጫ ያላቸው ፍጡሮች ናቸው፤ በምርጫቸው ጀነት ወይም ጀሃነም መግባት ይችላሉ፦
11፥119 የጌታህም ቃል፣ *ገሀነምን ከጂኒዎ እና ከሰዎች ከሁሉም በእርግጥ እሞላታለሁ* በማለት ተፈጸመች። وَتَمَّتْ كَلِمَةُ رَبِّكَ لَأَمْلَأَنَّ جَهَنَّمَ مِنَ الْجِنَّةِ وَالنَّاسِ أَجْمَعِينَ
55፥45 *ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?* فَبِأَيِّ آلَاءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَان
55፥46 *በጌታውም ፊት መቆምን ለፈራ ሁለት ገነቶች አሉት*፡፡ وَلِمَنْ خَافَ مَقَامَ رَبِّهِ جَنَّتَانِ

በተለይ “ጌታችሁ” የሚለው ቃል “ረቢኩማ” رَبِّكُمَا ሲሆን ሁለተኛ መደብ ሙተና”dual” ነው፤ ይህም ሁለቱንም ማለትም ሰውንና ጃንን ያመለክታል፤ “ታስተባብላላችሁ” የሚለው ቃል “ቱከዚባኒ” تُكَذِّبَانِ ሲሆን ሁለተኛ መደብ ሙተና”dual” ነው፤ ይህም ሁለቱንም ማለትም ሰውንና ጃንን ያመለክታል፤ የትንሳኤ ቀን ለሁለቱም የተቀጠረ ቀጠሮ ነው፦
55፥39 *በዚያም ቀን ሰውም ጃንም ከኃጢኣቱ ገና አይጠየቅም*፡፡ فَيَوْمَئِذٍ لَّا يُسْأَلُ عَن ذَنبِهِ إِنسٌ وَلَا جَانٌّ
44፥40 *የመለያው ቀን ለሁሉም ቀጠሯቸው ነው*፡፡ إِنَّ يَوْمَ الْفَصْلِ مِيقَاتُهُمْ أَجْمَعِينَ
6፥130 *የጂኒዎች እና የሰዎች ጭፍሮች ሆይ! አንቀጾቼን በእናንተ ላይ የሚተርኩ የዚህንም ቀናችሁን ቅጣት ማግኘትን የሚያስጠነቅቋችሁ ከእናንተው የኾኑ መልክተኞች አልመጧችሁምን? ይባላሉ*፡፡ يَا مَعْشَرَ الْجِنِّ وَالْإِنسِ أَلَمْ يَأْتِكُمْ رُسُلٌ مِّنكُمْ يَقُصُّونَ عَلَيْكُمْ آيَاتِي وَيُنذِرُونَكُمْ لِقَاءَ يَوْمِكُمْ هَـٰذَا
6፥128 *ሁሉንም የሚሰበስብባቸውንም ቀን አስታውስ፡፡ የጂኒዎች ጭፍሮች ሆይ! ከሰዎች ጭፍራን በማጥመም በእርግጥ አበዛችሁ* ይባላሉ፡፡ وَيَوْمَ يَحْشُرُهُمْ جَمِيعًا يَا مَعْشَرَ الْجِنِّ قَدِ اسْتَكْثَرْتُم مِّنَ الْإِن

ለጂኒዎች ጀነት እና ጀሃነም እንዲሁ የትንሳኤ ቀን ቀጠሮ እንዳላቸው እና የተፈጠሩበት አላማ ካየን ዘንዳ በነጻ ምርጫቸው ሙሥሊም አልያም ካ/ር የመሆን ምርጫ አላቸው፦
72፥14 *«እኛም ከእኛ ውስጥ ሙስሊሞች አሉ፡፡ ከእኛም ውስጥ በዳዮች አሉ፡፡ የሰለሙም ሰዎች እነዚያ ቅንን መንገድ መረጡ፡፡»* وَأَنَّا مِنَّا الْمُسْلِمُونَ وَمِنَّا الْقَاسِطُونَ ۖ فَمَنْ أَسْلَمَ فَأُولَـٰئِكَ تَحَرَّوْا رَشَدًا

ከጂኒዎች መካከል አማንያን እንዳሉ ሁሉ ከሃድያንም አሉ፤ ከሃድያኑ ሰይጣናት ይባላሉ። “ኢብሊስ” إِبْلِيس በተፈጥሮው ከሰው ወይም ከመልአክ ሳይሆን ከጂን ሲሆን በመጥፎ ባህርይው ደግሞ “ሸይጧን” ነው፤ ለአደም አልሰግድም ብሎ ያመጸ እና አደም እና ሐዋን ያሳሳተ እርሱ ነው፦
18፥50 ለመላእክትም ለአደም ስገዱ፥ ባልናቸው ጊዜ የሆነውን አስታውስ ። ወዲያውም ሰገዱ፤ *ኢብሊስ ብቻ ሲቀር ከጂን ነበር*፤ ከጌታውም ትእዛዝ ወጣ፡፡ وَإِذْ قُلْنَا لِلْمَلَائِكَةِ اسْجُدُوا لِآدَمَ فَسَجَدُوا إِلَّا إِبْلِيسَ كَانَ مِنَ الْجِنِّ فَفَسَقَ عَنْ أَمْرِ رَبِّهِ
2፥36 *ከእርሷም ሰይጣን አዳለጣቸው በውስጡም ከነበሩበት ድሎት አወጣቸው*፡፡فَأَزَلَّهُمَا الشَّيْطَانُ عَنْهَا فَأَخْرَجَهُمَا مِمَّا كَانَا فِيه
“ሸይጧን” شَّيْطَان የሚለው ቃል “ሸጠነ” شطن ማለትም “ራቀ” ወይም “ተገለለ” ከሚል ግስ የመጣ ሲሆን “የተገለለ” ወይም “የራቀ” ማለት ነው፤ “ሸያጢን” شَيَاطِين ደግሞ የሽይጧን ብዙ ቁጥር ሲሆን “ሰይጣናት” ማለት ነው፤ “ሸይጧን” ልክ እንደ “ሌባ” “ውሸታም” “ባለጌ” የባህርይ ስም እንጂ የተፀውኦ ስም አይደለም፤ ሸይጧን የሰውም የጂኒም አለ፦
6፥112 እንደዚሁም ለነቢያት ሁሉ *ከሰው እና ከጂን የኾኑን ሰይጣናት ጠላት* አደረግን፡፡ وَكَذَٰلِكَ جَعَلْنَا لِكُلِّ نَبِيٍّ عَدُوًّا شَيَاطِينَ الْإِنسِ وَالْجِن
114፥6 *«ከጂኒዎችም ከሰዎችም ሰይጣናት እጠበቃለሁ»* በል። مِنَ الْجِنَّةِ وَالنَّاسِ
23፥97 በልም *«ጌታዬ ሆ! ከሰይጣናት ጉትተጎታዎች በአንተ እጠበቃለሁ»* ፡፡ وَقُل رَّبِّ أَعُوذُ بِكَ مِنْ هَمَزَاتِ الشَّيَاطِينِ
7፥200 *ከሰይጣንም በኩል ጉትጎታ ቢያገኝህ በአላህ ተጠበቅ፡፡ እርሱ ሰሚው ዐዋቂው ነውና*፡፡ وَإِمَّا يَنزَغَنَّكَ مِنَ الشَّيْطَانِ نَزْغٌ فَاسْتَعِذْ بِاللَّهِ ۚ إِنَّهُ سَمِيعٌ عَلِيمٌ

“ወሥዋሥ” وَسْوَاس ማለት “ጉትጎታ” ማለት ሲሆን ይህ ጉትጎታ የሚመጣው ከጂኒ ሰይጣናት ብቻ ሳይሆን ከሰውም ሰይጣናት ነው፤ ከዚህ ውስዋስ የምንጠበቀው በተዐዉዝ ነው፤ አላህ የሙናፊቂን መሪዎቻቸውን ፦ “ሰይጣኖቻቸው” ብሏል፤ ይህ የሚያሳየው የሰው ሸይጧን እንዳለ ነው፤ ሸይጧን ከአላህ ራህመት የተገለለ የራቀ ማለት መሆኑ ልብ በል፦
2፥14 እነዚያንም ያመኑትን በተገናኙ ጊዜ «አምነናል» ይላሉ፡፡ *ወደ ሰይጣኖቻቸውም* ባገለሉ ጊዜ «እኛ ከእናንተ ጋር ነን፤ እኛ በእነርሱ ተሳላቂዎች ብቻ ነን» ይላሉ፡፡ وَإِذَا لَقُوا الَّذِينَ آمَنُوا قَالُوا آمَنَّا وَإِذَا خَلَوْا إِلَىٰ شَيَاطِينِهِمْ قَالُوا إِنَّا مَعَكُمْ إِنَّمَا نَحْنُ مُسْتَهْزِئُونَ

እዚህ ድረስ ስለ ሸይጧን እሳቤ ከተረዳን ዘንዳ ረመዷን ላይ የሚታሰሩት ሸያጢን ከኩ*ፋ*ሩ*ል ጂን ሲሆኑ ከእነርሱም የሚታሰሩት መሪዎቻቸው ናቸው፦
ኢማም ቡኻርይ: መጽሐፍ 30, ሐዲስ 9
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ” እንደተረከው የአላህም መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”የረመዷን ወር ሲጀመር የሰማይ ደጆች ይከፈታሉ፤ የጀሃነም ደጆች ይዘጋሉ፤ ሰይጣናትም ይታሰራሉ”* سَمِعَ أَبَا هُرَيْرَةَ ـ رضى الله عنه ـ يَقُولُ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ إِذَا دَخَلَ شَهْرُ رَمَضَانَ فُتِّحَتْ أَبْوَابُ السَّمَاءِ، وَغُلِّقَتْ أَبْوَابُ جَهَنَّمَ، وَسُلْسِلَتِ الشَّيَاطِينُ ‏”‌‏
ኢማም አብኑ ኹዘይማህ: መጽሐፍ 3, ቁጥር 188
ነብዩም”ﷺ”፦ *”ሰይጣናት ይታሰራሉ” ያሉት ከእነርሱ አመጸኞቹ እንጂ ሁሉም ሰይጣናት አይደለም*። باب ذكر البيان أن النبي – صلى الله عليه وسلم – إنما أراد بقوله : ” وصفدت الشياطين ” مردة الجن منهم ، لا جميع الشياطين ”

ሚሽነሪዎች፦ “ሰይጣናት ከታሰሩ ሰው እንዴት በረመዷን ወር ይሳሳታል?” ብለው ይጠይቃሉ፤ ጥሩ ጥያቄ ነው። ሲጀመር በረመዷን ወር ሁሉም ሰይጣናት አይታሰሩም። ሲቀጥል የታሰሩት በሁለተኛ ደረጃ ያሉትን “ማሪድ” مَّارِد የተባሉትን መሪዎች ናቸው፤ የመጀመሪያ ደረጃ ያለው ዋናው ሸይጧን ኢብሊስ ነውና። ሲሰልስ ሰውን የሚወሰውሱ የሰው ሰይጣናት እራሳቸው አልታሰሩም፤ እነርሱን በረመዳን ወር ሊወሰውሱ ይችላሉ። ሲያረብብም ሰይጣን ቢታሰርም እርምጃዎቹ አልታሰሩም፤ አላህ አትከተሉ ያለው ሰይጣንን ብቻ ሳይሆን የሰይጣንን እርምጃዎች ጭምር ነው፦
2፥208 *እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ሁላችሁም በመታዘዝ ውስጥ ግቡ፡፡ የሰይጣንንም እርምጃዎች አትከተሉ፤ እርሱ ለእናንተ ግልጽ ጠላት ነውና*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا ادْخُلُوا فِي السِّلْمِ كَافَّةً وَلَا تَتَّبِعُوا خُطُوَاتِ الشَّيْطَانِ ۚ إِنَّهُ لَكُمْ عَدُوٌّ مُّبِينٌ

የሰይጣን እርምጃዎች “አህዋዕ” أَهْوَآء ማለት “ዝንባሌ”inclination” እና “ነፍሢያህ” نفسيه ናቸው፤ አህዋዕ ሊመለክ የሚችል ክፉ አዛዥ ነው፤ በጌታው ፊት መቆምን የፈራ ሰውማ ነፍሱንም ከዝንባሌዋ የከለከለ ገነት እርሷ በእርግጥ መኖሪያው ናት፦
25፥43 *ዝንባሌውን አምላኩ አድርጎ የያዘውን ሰው አየህን አንተ በእርሱ ላይ ጠባቂ ትኾናለህን?* أَرَأَيْتَ مَنِ اتَّخَذَ إِلَـٰهَهُ هَوَاهُ أَفَأَنتَ تَكُونُ عَلَيْهِ وَكِيلًا
79፥40 *በጌታው ፊት መቆምን የፈራ ሰውማ ነፍሱንም ከዝንባሌዋ የከለከለ* وَأَمَّا مَنْ خَافَ مَقَامَ رَبِّهِ وَنَهَى النَّفْسَ عَنِ الْهَوَى
79፥41 *ገነት እርሷ በእርግጥ መኖሪያው ናት*፡፡ فَإِنَّ الْجَنَّةَ هِيَ الْمَأْوَىٰ

ነፍሢያ አላህ የጠበቃት ካልሆነች በስተቀር በመጥፎ ነገር በእርግጥ አዛዥ ናትና፤ ነፍሲያ በራሷ ላይ እንጅ ክፉን አትሠራም፦
12፥53 «ነፍሴንም ከስሕተት አላጠራም፡፡ *ነፍስ ሁሉ ጌታዬ የጠበቃት ካልሆነች በስተቀር *”በመጥፎ ነገር በእርግጥ አዛዥ ናትና*፡፡ ጌታዬ በጣም መሓሪ አዛኝ ነው» አለ፡፡ وَمَا أُبَرِّئُ نَفْسِي ۚ إِنَّ النَّفْسَ لَأَمَّارَةٌ بِالسُّوءِ إِلَّا مَا رَحِمَ رَبِّي ۚ إِنَّ رَبِّي غَفُورٌ رَّحِيمٌ
6፥164 በላቸው «እርሱ የሁሉ ጌታ ሲኾን ከአላህ በቀር ሌላን ጌታ እፈልጋለሁን *ነፍስም ሁሉ በራሷ ላይ እንጅ ክፉን አትሠራም*፡፡ قُلْ أَغَيْرَ ٱللَّهِ أَبْغِى رَبًّۭا وَهُوَ رَبُّ كُلِّ شَىْءٍۢ ۚ وَلَا تَكْسِبُ كُلُّ نَفْسٍ إِلَّا عَلَيْهَا

ሰይጣን የትንሳኤ ቀን፦ “ለእኔም በእናንተ ላይ ምንም ስልጣን አልበረኝም፤ ግን ጠራኋችሁ፡፡ ለእኔም ታዘዛችሁ፤ ስለዚህ አትውቀሱኝ፤ ነፍሶቻችሁንም ውቀሱ” ይላል፦
14፥22 ነገሩም በተፈጸመ ጊዜ ሰይጣን ይላቸዋል፦ *«አላህ እውነተኛውን ቃል ኪዳን ገባላችሁ፡፡ ቃል ኪዳንም ገባሁላችሁ፤ አፈረስኩባችሁም፡፡ ለእኔም በእናንተ ላይ ምንም ስልጣን አልበረኝም፡፡ ግን ጠራኋችሁ፡፡ ለእኔም ታዘዛችሁ፡፡ ስለዚህ አትውቀሱኝ፤ ነፍሶቻችሁንም ውቀሱ፡፡ እኔ የምረዳችሁ አይደለሁም፡፡ እናንተም የምትረዱኝ አይደላችሁም፡፡ እኔ ከአሁን በፊት ለአላህ ተጋሪ በአደረጋችሁት ነገር ካድኩ፡፡ በዳዮቹ ለእነርሱ በእርግጥ አሳማሚ ቅጣት አላቸው»*። وَقَالَ الشَّيْطَانُ لَمَّا قُضِيَ الْأَمْرُ إِنَّ اللَّهَ وَعَدَكُمْ وَعْدَ الْحَقِّ وَوَعَدتُّكُمْ فَأَخْلَفْتُكُمْ ۖ وَمَا كَانَ لِيَ عَلَيْكُم مِّن سُلْطَانٍ إِلَّا أَن دَعَوْتُكُمْ فَاسْتَجَبْتُمْ لِي ۖ فَلَا تَلُومُونِي وَلُومُوا أَنفُسَكُم ۖ مَّا أَنَا بِمُصْرِخِكُمْ وَمَا أَنتُم بِمُصْرِخِيَّ ۖ
إِنِّي كَفَرْتُ بِمَا أَشْرَكْتُمُونِ مِن قَبْلُ ۗ إِنَّ الظَّالِمِينَ لَهُمْ عَذَابٌ أَلِيمٌ

ስለዚህ ለምንሰራው መጥፎ ሥራ ሰይጣንን ተጠያቂ ማድረግ አንችልም፤ ሰይጧን ለእኛ ግልጽ ጠላት ነው፤ እርሱ የሚያጠቃን በእርምጃዎቹ ነው። አላህ ከሸይጧን እና ከእርምጃዎቹ ይጠብቀን።

ኡሥታዝ ወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም

የበለጠ ለማወቅ
ጥሪያችን Tiriyachen
https://fb.me/tiriyachen

ወሰላሙ አለይኩም
ሒጃብ

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

24፥31 ለምእምናትም ንገራቸው፡- ዓይኖቻቸውን ይከልክሉ፡፡ ብልቶቻቸውንም ይጠብቁ፡፡ ጌጣቸውንም ከእርሷ ግልጽ ከኾነው በስተቀር አይግለጡ፡፡ ጉፍታዎቻቸውንም በአንገትጌዎቻቸው ላይ ያጣፉ፡፡ وَقُل لِّلْمُؤْمِنَاتِ يَغْضُضْنَ مِنْ أَبْصَارِهِنَّ وَيَحْفَظْنَ فُرُوجَهُنَّ وَلَا يُبْدِينَ زِينَتَهُنَّ إِلَّا مَا ظَهَرَ مِنْهَا ۖ وَلْيَضْرِبْنَ بِخُمُرِهِنَّ عَلَىٰ جُيُوبِهِنَّ

"ሒጃብ" حِجَاب የሚለው ቃል "ሐጀበ" حَجَبَ ማለትም "ጋረደ" "ሸፈነ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "መሸፈኛ" "መሸፋፈኛ" "መጋረጃ" "ግርዶ" ማለት ነው፦
19፥17 ከእነርሱም መጋረጃን አደረገች፡፡ فَاتَّخَذَتْ مِن دُونِهِمْ حِجَابًا

እዚህ አንቀጽ ላይ መርየም እንዳያዩአት ያደረገችው መጋረጃ "ሒጃብ" حِجَاب ተብሎ ተቀምጧል። ሒጃብ ሙሥሊም ሴት የምትሰተርበት ኺማር እና ጂልባብ ነው፦
24፥31 ለምእምናትም ንገራቸው፡- ዓይኖቻቸውን ይከልክሉ፡፡ ብልቶቻቸውንም ይጠብቁ፡፡ ጌጣቸውንም ከእርሷ ግልጽ ከኾነው በስተቀር አይግለጡ፡፡ ጉፍታዎቻቸውንም በአንገትጌዎቻቸው ላይ ያጣፉ፡፡ وَقُل لِّلْمُؤْمِنَاتِ يَغْضُضْنَ مِنْ أَبْصَارِهِنَّ وَيَحْفَظْنَ فُرُوجَهُنَّ وَلَا يُبْدِينَ زِينَتَهُنَّ إِلَّا مَا ظَهَرَ مِنْهَا ۖ وَلْيَضْرِبْنَ بِخُمُرِهِنَّ عَلَىٰ جُيُوبِهِنَّ

"ጉፍታዎች" ለሚለው በብዜት የገባው ቃል "ኹሙር" خُمُر ሲሆን በነጠላ ደግሞ "ኺማር" خِمَار ነው። ይህ አንቀጽ ሲወርድ ሴቶች በኒቃብ ተሰትረዋል፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 65, ሐዲስ 4759
ሶፊያህ ቢንት ሸይባህ እንደተረከችው፦ "ዓኢሻህ"ረ.ዐ." እንዲህ ትል ነበር፦ "ጉፍታዎቻቸውንም በአንገትጌዎቻቸው ላይ ያጣፉ" የሚለው አንቀጽ በወረደች ጊዜ ሴቶቹ ከወገቦቻቸውን ጨርቆች በኩል ይቆርጡና ጭንቅላታቸውን እና ፊታቸውን በተቆረጡት የጨርቅ ቁርጥራጮች ይሸፍኑ ነበር"። عَنْ صَفِيَّةَ بِنْتِ شَيْبَةَ، أَنَّ عَائِشَةَ ـ رضى الله عنها ـ كَانَتْ تَقُولُ لَمَّا نَزَلَتْ هَذِهِ الآيَةُ ‏{‏وَلْيَضْرِبْنَ بِخُمُرِهِنَّ عَلَى جُيُوبِهِنَّ‏}‏ أَخَذْنَ أُزْرَهُنَّ فَشَقَّقْنَهَا مِنْ قِبَلِ الْحَوَاشِي فَاخْتَمَرْنَ بِهَا‏.‏

"ኒቃብ" نِقَاب ማለት "መሸፈኛ" ማለት ሲሆን "ጉፍታዎች" በሌላ አንቀጽ "መከናነቢያዎች" በሚል ተለዋዋጭ ቃል መጥቷል፦
33፥59 አንተ ነቢዩ ሆይ! ለሚስቶቸህ፣ ለሴቶች ልጆችህም፣ ለምእምናን ሚስቶችም ከመከናነቢያዎቻቸው በላያቸው ላይ እንዲለቁ ንገራቸው፡፡ ይህ እንዲታወቁ እና በባለጌዎች እንዳይደፈሩ ለመኾን በጣም የቀረበ ነው፡፡ አላህም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡ يَا أَيُّهَا النَّبِيُّ قُل لِّأَزْوَاجِكَ وَبَنَاتِكَ وَنِسَاءِ الْمُؤْمِنِينَ يُدْنِينَ عَلَيْهِنَّ مِن جَلَابِيبِهِنَّ ۚ ذَٰلِكَ أَدْنَىٰ أَن يُعْرَفْنَ فَلَا يُؤْذَيْنَ ۗ وَكَانَ اللَّهُ غَفُورًا رَّحِيمًا

እዚህ አንቀጽ ላይ "መከናነቢያዎች" ለሚለው በብዜት የገባው ቃል "ጀላቢብ" جَلَٰبِيب ሲሆን በነጠላ ደግሞ "ጂልባብ" جِلْبَاب‎ ነው።
በባይብል ውስጥ ይስሐቅም ርብቃን ከማግባቱ በፊት አጅነቢይ ስለነበረ እንዳያያት ኺማር ወስዳ ተከናነበች፦
ዘፍጥረት 24፥65 "እርስዋም መሸፈኛ ወስዳ ተከናነበች"። فَأخَذَتْ رِفقَةُ الخِمارَ وَغَطَّتْ وَجهَها

እዚህ አንቀጽ ላይ "መሸፈኛ" ለሚለው ቃል የገባው "ኺማር" خِمارَ ሲሆን "ፊቷን" ለሚለው የገባው ቃል "ወጀሀሃ" وَجهَها ነው፥ ርብቃ በሒጃብ የተሰተረችው ፊቷን ነው። በእስራኤል ሴቶቹ ዓይናቸውን በኒቃብ ይሸፈኑ ነበር፥ ንጉሥ ሰለሞን የሱላማጢስ ልጃገረድን በዓይነ ርግብ መሸፈኛሽ ውስጥ ዓይኖች እና ጕንጭና ጕንጯ እንዳሉ መናገሩ በኒቃብ ፊታቸው እና ዓይናቸው ይሰተሩ እንደነበር አመላካች ነው፦
መኃልይ 4፥1 በዓይነ ርግብ መሸፈኛሽ ውስጥ ዓይኖችሽ እንደ ርግቦች ናቸው። عَيْنَاكِ حَمَامَتَانِ مِنْ تَحْتِ نَقَابِكِ

አንቀጹ ላይ "መሸፈኛሽ" ለሚለው ቃል የገባው "ነቃቢኪ" نَقَابِكِ ሲሆን "ኒቃብ" نِقَاب በጥንትም ፊትን መሸፈኛ ነው፥ እዚሁ ዐውድ ላይ "መሸፈኛሽ" ለሚለው ቃል የገባው "ሒማሪኪ" خِمارِكِ ነው፦
መኃልይ 4፥3 በዓይነ ርግብ መሸፈኛሽ ውስጥ ጕንጭና ጕንጭሽ እንደ ተከፈለ ሮማን ናቸው። كَفَلَقَةِ رُمّانَةٍ هُوَ خَدُّكِ تَحتَ خِمارِكِ

የሱላማጢስ ልጃገረድን ሒጃቧትን ልክ እንደ ኢትዮጵያዊያን ሴት ሙሥሊሞች ቅጥር ጠባቂዎች እንደወሰዱባት መናገሯ በራሱ ሒጃብ ታደርግ እንደነበር ማሳያ ነው፦
መኃልይ 5፥7 ቅጥር ጠባቂዎችም የዓይነ ርግብ መሸፈኛዬን ወሰዱት። وَنَزَعَ حُرّاسُ الأسوارِ خِمارِي عَنِّي

እዚህ አንቀጽ ላይ "መሸፈኛ" ለሚለው የገባው ቃል "ኺማር" خِمَار እንደሆነ ልብ አድርግ! ሴት ራስዋን በኺማር ሳትሸፍን ወደ ፈጣሪ ልትጸልይ አይገባትም፥ ሴት አማኝ ሁሉም ቦታ እንድትከናነብ ወፍራም ትእዛዝ አለ፦
1ኛ ቆሮንቶስ 11፥13 በእናንተ በራሳችሁ መካከል ፍረዱ፤ ሴት "ራስዋን ሳትሸፍን" ወደ አምላክ ልትጸልይ ይገባታልን?
ዲድስቅልያ 3፥32 ነገር ግን ላመኑ ሴቶች ራሳቸውን በንጽህና “ሊከናነቡ” ይገባል። እነርሱ “ተከናንበው” በጎዳና ራሳቸውን ዝቅ አድርገው ይሂዱ!።

በግዕዝ "ዲድስቅሊያ" በውጪው ዓለም "ዲዳኬ"Didache" ከ 60-85 ድኅረ ልደት የተዘጋጀ የሐዋርያት ትምህርት ነው፥ ይህ መጽሐፍ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ የአዲስ ኪዳን 35 ከምትላቸው የቀኖና መጻሕፍት አንዱ ነው። "እነርሱ “ተከናንበው” በጎዳና ራሳቸውን ዝቅ አድርገው ይሂዱ" የሚለው ይሰመርበት! ታዲያ ለምን ይሆን ክርስቲያን ሴት ተገላልጣ በጎዳና ላይ የምትሄደው? መልሱ መጽሐፉን ለትራስነት እንጂ አያነቡትም፥ ያነበቡትም የሚከተሉት መጽሐፉን ሳይሆን የምዕራቡን ርዕዮት እና እሳቦት ነው። መራቆትን እንደ መሰልጠን መሰተርን እንደ ኃላ ቀርነት ለሚቆጥሩት አሏህ ቀልብ ይስጣቸው! ለእኛም ጽናቱን ይወፍቀን! አሚን።

ኡሥታዝ ወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም

የበለጠ ለማወቅ
ጥሪያችን Tiriyachen
https://fb.me/tiriyachen

ወሠላሙ ዐለይኩም
👌2
2025/07/10 17:56:01
Back to Top
HTML Embed Code: