Telegram Web Link
መገለጥ


በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

«እኔ አላህ እኔ ነኝ ያለ እኔ አምላክ የለምና አምልከኝ፡፡ ሶላትንም በእርሷ እኔን ለማውሳት ስገድ፡፡

إِنَّنِىٓ أَنَا ٱللَّهُ لَآ إِلَٰهَ إِلَّآ أَنَا۠ فَٱعْبُدْنِى وَأَقِمِ ٱلصَّلَوٰةَ لِذِكْرِىٓ
ቁርኣን 20፥14

“ወሕይ” وَحْي የሚለው ቃል “አውሓ” أَوْحَىٰٓ ማለትም “ገለጠ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ግልጠተ-መለኮት” ወይም “ግህደተ-መለኮት” አሊያም "መለኮታዊ ራእይ"Revelation” ማለት ነው። አምላካችን አላህ ለነቢያት ግልጠት ይገልጥላቸዋል፦

"እኛ ወደ ኑሕና ከርሱ በኋላ ወደ ነበሩት ነቢያት እንዳወረድን ወደ አንተም "አወረድን"፡፡ ወደ ኢብራሂምም፣ ወደ ኢስማዒልም፣ ወደ ኢስሓቅም፣ ወደ ያዕቆብም፣ ወደ ነገዶቹም፣ ወደ ዒሳም፣ ወደ አዩብም፣ ወደ ዩኑስም፣ ወደ ሃሩንና፣ ወደ ሱለይማንም "አወረድን"፡፡ ለዳውድም ዘቡርን ሰጠነው፡፡

إِنَّا أَوْحَيْنَا إِلَيْكَ كَمَا أَوْحَيْنَا إِلَىٰ نُوحٍ وَالنَّبِيِّينَ مِن بَعْدِهِ ۚ وَأَوْحَيْنَا إِلَىٰ إِبْرَاهِيمَ وَإِسْمَاعِيلَ وَإِسْحَاقَ وَيَعْقُوبَ وَالْأَسْبَاطِ وَعِيسَىٰ وَأَيُّوبَ وَيُونُسَ وَهَارُونَ وَسُلَيْمَانَ ۚ وَآتَيْنَا دَاوُودَ زَبُورًا
ቁርኣን 4፥163

"አወረድን" ለሚለው ቃል የገባው "አውሐይና" أَوْحَيْنَا ሲሆን "አውሓ” أَوْحَىٰٓ ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ገለጥን" ማለት ነው። አላህ ለነቢያት ስለራሱ ማንነት የሚገልጠው ........

ሙሉውን ያንብቡ 👇🏻
https://tiriyachen.org/መገለጥ/
👍9
ኢሥቲሥላም


በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

"በሰማያትና በምድር ያሉ ሁሉ በውድም በግድም "ለእርሱ የታዘዙ" ወደ እርሱም የሚመለሱ ሲኾኑ ከሓዲዎች ከአላህ ሃይማኖት ሌላን ይፈልጋሉን?"

أَفَغَيْرَ دِينِ اللَّهِ يَبْغُونَ وَلَهُ أَسْلَمَ مَن فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ طَوْعًا وَكَرْهًا وَإِلَيْهِ يُرْجَعُونَ
📜 ቁርኣን 3፥83

"ኢሥቲሥላም" اِسْتِسْلَام የሚለው ቃል "ኢሥተሥለመ" اِسْتَسْلَمَ ማለትም "ታዘዘ" "ተገዛ" ለሚለው መስደር ሲሆን “መታዘዝ” “መገዛት” ማለት ነው። በሰማያት እና በምድር ያሉ ሁሉ በውድም በግድም ለአላህ የታዘዙ ናቸው፦

"በሰማያት እና በምድር ያሉ ሁሉ በውድም በግድም "ለእርሱ የታዘዙ" ወደ እርሱም የሚመለሱ ሲኾኑ ከሓዲዎች ከአላህ ሃይማኖት ሌላን ይፈልጋሉን?"

أَفَغَيْرَ دِينِ اللَّهِ يَبْغُونَ وَلَهُ أَسْلَمَ مَن فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ طَوْعًا وَكَرْهًا وَإِلَيْهِ يُرْجَعُونَ
📜 ቁርኣን 3፥83


ገበተው ሙሉውን ያንብቡት 👇🏻👇🏻👇🏻
https://tiriyachen.org/ኢሥቲሥላም/
6👍2
ሐዲስ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

መልክተኛውም የሰጣችሁን ማንኛውንም ነገር ያዙት፡፡ ከእርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና፡፡

وَمَا آتَاكُمُ الرَّسُولُ فَخُذُوهُ وَمَا نَهَاكُمْ عَنْهُ فَانتَهُوا ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۖ إِنَّ اللَّهَ شَدِيدُ الْعِقَابِ
📜ቁርኣን 59፥7

"ሐዲስ" حَدِيث የሚለው ቃል "ሐደሰ" حَدَّثَ‎ ማለትም "ተናገረ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ንግግር" ማለት ነው፦

"ከዚህ ንግግር ትደነቃላችሁን?"

أَفَمِنْ هَـٰذَا الْحَدِيثِ تَعْجَبُونَ
📜ቁርኣን 53፥59

እዚህ አንቀጽ ላይ "ንግግር" ለሚለው የተቀመጠው ቃል "ሐዲስ" حَدِيث መሆኑ ልብ በል። እዚህ ድረስ የሐዲስ ቃል ምን ማለት እንሆነ በግርድፉና በሌጣው ካየን ዘንዳ ነቢያችን"ﷺ" በዐቂዳህ እና በፊቅህ ነጥብ ላይ የሚናገሩት ንግግር ሁሉ ወሕይ ነው፦

ሙሉውን ያንብቡ
https://tiriyachen.org/ሐዲስ/
👍5
የቁርኣን አወራረድ


በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

ቁርአንንም በሰዎች ላይ ሆነህ ታነበው ዘንድ ከፋፈልነው፥ ቀስ በቀስ ማውረድንም አወረድነው።

وَقُرْآنًا فَرَقْنَاهُ لِتَقْرَأَهُ عَلَى النَّاسِ عَلَىٰ مُكْثٍ وَنَزَّلْنَاهُ تَنزِيلًا
📜 ቁርኣን 17፥106

“ኑዙል” نُزُل ማለት “አወራረድ” ማለት ሲሆን “ተንዚል” تَنزِيل ማለት ደግሞ “የተወረደ”Revelation” ማለት ነው፤ ሁለቱም ቃላት “አንዘለ” أَنْزَلَ ወይም “ነዝዘለ” نَزَّلَ ማለትም “አወረደ” ወይም “ገለጠ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጡ ናቸው። የቁርኣን አወራረዱ ሁለት አይነት ነው፤ አንዱ በጠቅላላ አንድ ጊዜ ከለውሐል መሕፉዝ ማለትም ከተጠበቀው ሰሌዳ ወደ ቅርቢቱ ሰማይ ሲሆን ሁለተኛው ከቅርቢቱ ሰማይ ወደ ነብያችን”ﷺ” ልብ ቀስ በቀስ ለ 23 ዓመት ወረደ፤ ይህንን ጥልልና ጥንፍፍ አርገን እንመልከት።
የተቆጠሩ ቀኖች የያዘው ረመዷን 9ኛው ወር ሲሆን ይህ ወር የሚጾምበት ምክንያት ቁርኣን ከጥብቁ ሰሌዳ ወደ ቅርቢቱ ሰማይ ወደ እልቅና ቤት የወረደበት ወር ስለሆነ ነው። ቁርኣን በዚህ ወር ውስጥ በአንድ በተባረከች ሌሊት በጠቅላላ አንድ ጊዜ ወርዷል፥ ይህም አወራረድ “ጁምለተን ዋሒዳህ” جُمْلَةً وَاحِدَةً ይባላል፦

ሙሉወን ያንብቡ ይማርበታል👇🏻👇🏻👇🏻
https://tiriyachen.org/የቁርኣን-አወራረድ/
👍4
የአላህ ባሕርይ


በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

የዐርሹ ጌታ አላህም "ከሚሉት" ሁሉ ጠራ።

فَسُبْحَانَ اللَّهِ رَبِّ الْعَرْشِ عَمَّا يَصِفُونَ
📜 ቁርኣን 21፥22

"ሲፋህ" صِفَة የሚለው ቃል "ወሰፈ" وَصَفَ‎ ማለትም "ገጠለ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ባሕርይ" ወይም "መገለጫ"description" ማለት ነው፥ የሲፋህ ብዙ ቁጥር "ሲፋት" صِفَات‎ ነው፦

የዐርሹ ጌታ አላህም "ከሚሉት" ሁሉ ጠራ።

فَسُبْحَانَ اللَّهِ رَبِّ الْعَرْشِ عَمَّا يَصِفُونَ
📜 ቁርኣን 21፥22

የሰማያትና ምድር ጌታ የዙፋኑ ጌታ ከሚሉት ነገር ሁሉ ጠራ።

سُبْحَانَ رَبِّ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ رَبِّ الْعَرْشِ عَمَّا يَصِفُونَ
📜 ቁርኣን 43፥82

የማሸነፍ ጌታ የሆነው ጌታህ "ከሚሉት" ሁሉ ጠራ።

سُبْحَانَ رَبِّكَ رَبِّ الْعِزَّةِ عَمَّا يَصِفُونَ
📜 ቁርኣን 37፥180

"ከሚሉት" ለሚለው ቃል የገባው “የሲፉነ” يَصِفُونَ ሲሆን “ባሕርይ ካደረጉለት”they attribute” ማለት ነው፥ ፍጡራን ከወሰፉት ሲፋህ ሁሉ የጠራ ነው። “ሡብሓን” سُبْحَٰن የሚለው ቃል “ሠበሐ” سَبَّحَ ማለትም “አጠራ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ስብሐት” ማለት ነው፥ “ተሥቢሕ” تَسْبِيح ማለት ደግሞ “ተስብሖት” ማለት ሲሆን አላህ ከወሰፉት የነውርና የጎደሎ ባሕርይ ማጥራት ነው። አላህ እራሱ በራሱ የእኔ ሲፋህ ይህ ነው ብሎ ከተናገረበት ውጪ ውድቅ ማድረግ ተስቢሕ ነው። እራሱን በራሱ ከገለጣቸው .....

ሊንኩን ተክተው ያንብቡ👇🏻👇🏻👇🏻
https://tiriyachen.org/የአላህ-ባሕርይ/
👍21
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦
”ከሰዎች ሁሉ ይልቅ ለዒሣ የመርየም ልጅ በዚህ ዓለም በመጨረሻይቱ ዓለም ቅርብ ነኝ። እነርሱም፦ "ይህ እንዴት ይሆናል? የአላህ መልእክተኛም፦ ሆይ!" አሉ። እርሳቸው፦ "ነቢያት ወንድማማቾች ናቸው፣ እናቶቻቸው ይለያያሉ፣ ነገር ግን ሃይማኖታቸው አንድ ነው። በእኔ እና በእርሱ መካከል አንድም ነቢይ የለም" አሉ"።

📚ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 43, ሐዲስ 190
---------------------------------------------------------------------
የበለጠ ለማወቅ
ጥሪያችን Tiriyachen
https://www.facebook.com/tiriyachen
ሦስቱ መልእክተኞች

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

ከአንተ በፊትም መልክተኞችን በእርግጥ ልከናል፡፡ ከእነርሱ በአንተ ላይ የተረክንልህ አለ፥ ከእነርሱም በአንተ ላይ ያልተረክነው አለ፡፡

وَلَقَدْ أَرْسَلْنَا رُسُلًا مِّن قَبْلِكَ مِنْهُم مَّن قَصَصْنَا عَلَيْكَ وَمِنْهُم مَّن لَّمْ نَقْصُصْ عَلَيْكَ
📜 ቁርኣን 40፥78

አምላካችን አላህ ከነቢያችን”ﷺ” በፊት መልእክተኞች ልኳል። ከእነርሱ ውስጥ በነቢያችን”ﷺ” ላይ ስማቸው የተተረኩ አሉ፥ ከእነርሱም ውስጥ ስማቸው ያልተተረኩ አሉ፦

ከአንተ በፊትም መልክተኞችን በእርግጥ ልከናል፡፡ ከእነርሱ በአንተ ላይ የተረክንልህ አለ፥ ከእነርሱም በአንተ ላይ ያልተረክነው አለ፡፡

وَلَقَدْ أَرْسَلْنَا رُسُلًا مِّن قَبْلِكَ مِنْهُم مَّن قَصَصْنَا عَلَيْكَ وَمِنْهُم مَّن لَّمْ نَقْصُصْ عَلَيْكَ
📜 ቁርኣን 40፥78

ስማቸው ካልተተረኩት መልእክተኞች መካከል ሦስት መልእክተኞች ወደ አንዲት ከተማ ልኳል፦

ሙሉውን ለማንበብ 👇🏻👇🏻👇🏻
https://tiriyachen.org/ሦስቱ-መልእክተኞች/
👍2
ከሺርክ በስተጀርባ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

36፥60 *"የአደም ልጆች ሆይ! ሰይጣንን አታምልኩ! እርሱ ለእናንተ ግልጽ ጠላት ነውና በማለት ወደ እናንተ አላዘዝኩምን?* أَلَمْ أَعْهَدْ إِلَيْكُمْ يَا بَنِي آدَمَ أَن لَّا تَعْبُدُوا الشَّيْطَانَ ۖ إِنَّهُ لَكُمْ عَدُوٌّ مُّبِينٌ

“ዒባዳህ” عِبَادَة የሚለው ቃል “ዓበደ عَبَدَ ማለትም “አመለከ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “አምልኮ” ማለት ነው። ዒባዳህ በሦስት ይከፈላል፥ እርሱም፦
1ኛ. "ዒባደቱል ቀልቢያ" عِبَادَة قَلْبِيَّة ማለት "የኃልዮ አምልኮ” ማለት ነው፥ "ቀልብ" قَلْب ማለት "ኃልዮ" ወይም "ልብ" ማለት ነው።
2ኛ. "ዒባደቱል ቀውልያ” عِبَادَة قَوْلِيَّة ማለት "የነቢብ አምልኮ" ማለት ነው፥ "ቀውል" قَوْل ማለት "ነቢብ" ወይም "አንደበት" ማለት ነው።
3ኛ. "ዒባደቱል ዐመልያ" عِبَادَة عَمَلِيَّة ማለት "የገቢር አምልኮ" ማለት ነው፥ "ዐመል" عَمَل ማለት "ገቢር" ወይም "ድርጊት" ማለት ነው።

"ዱዓ" ደግሞ በቀውል ከሚከናወን ዒባዳህ አንዱ ነው፥ “ዱዓእ” دُعَآء የሚለው ቃል "ደዓ" دَعَا ማለትም "ለመነ" "ጠራ" "ጸለየ" "ተማጸነ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ልመና" "ጥሪ" "ጸሎት" "ተማጽንዖ" ማለት ነው። ዱዓእ የአንድ አምላክ የአላህ ሐቅና ገንዘብ ነው፦
2፥186 *”ባሮቼም ከእኔ በጠየቁህ “እኔ ቅርብ ነኝ፥ የለማኝን ጸሎት በለመነኝ ጊዜ እቀበለዋለሁ*”፡፡ ስለዚህ ለእኔ ይታዘዙ፤ በእኔም ይመኑ፤ እነርሱ ሊመሩ ይከጀላልና፡፡ وَإِذَا سَأَلَكَ عِبَادِي عَنِّي فَإِنِّي قَرِيبٌ ۖ أُجِيبُ دَعْوَةَ الدَّاعِ إِذَا دَعَانِ ۖ فَلْيَسْتَجِيبُوا لِي وَلْيُؤْمِنُوا بِي لَعَلَّهُمْ يَرْشُدُونَ
40፥60 ጌታችሁም አለ *«ለምኑኝ እቀበላችኋለሁና፡፡ እነዚያ እኔን ከማምለክ የሚኮሩት ተዋራጆች ኾነው ገሀነምን በእርግጥ ይገባሉ"*፡፡ وَقَالَ رَبُّكُمُ ادْعُونِي أَسْتَجِبْ لَكُمْ ۚ إِنَّ الَّذِينَ يَسْتَكْبِرُونَ عَنْ عِبَادَتِي سَيَدْخُلُونَ جَهَنَّمَ دَاخِرِينَ
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 34, ሐዲስ 2
አን-ኑዕማን ኢብኑ በሺር እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛም"ﷺ" አሉ፦ *"ዱዓእ ዒባዳህ ነው፥ ከዚያም፦ "ጌታችሁም አለ *«ለምኑኝ እቀበላችኋለሁና" የሚለውን አንቀጽ ቀሩ"*። عَنِ النُّعْمَانِ بْنِ بَشِيرٍ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ ‏"‏ إِنَّ الدُّعَاءَ هُوَ الْعِبَادَةُ ‏"‏ ‏.‏ ثُمَّ قَرَأَ ‏{وَقَالَ رَبُّكُمُ ادْعُونِي أَسْتَجِبْ لَكُمْ}‏

ዱዓእ አምልኮ ከሆነ አምልኮ የአላህ ብቻ ሐቅ እና የባሕርይው ገንዘቡ ነው፥ አላህ ወደ እርሱ ዱዓእ ለሚያደርጉት ቅርብ ነው፥ አላህ መለኮት ነው። መለኮት በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው፣ ነገሩን ሁሉ ዐዋቂ ነው፣ ሁሉን ሰሚ ነው፣ ሁሉን ተመልካች ነው፣ በነገሩ ሁሉ ላይ ተቆጣጣሪ ነው፦
29፥20 አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው”*። إِنَّ اللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ
65፥11 *”አላህም ነገሩን ሁሉ ዐዋቂ ነው”*፡፡ وَاللَّهُ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمٌ
58፥1 *”አላህ ሰሚ ተመልካች ነው”*፡፡ إِنَّ اللَّهَ سَمِيعٌ بَصِير
2፥110 *”አላህ የምትሠሩትን ሁሉ ተመልካች ነው”*፡፡ إِنَّ اللَّهَ بِمَا تَعْمَلُونَ بَصِيرٌ
4፥86 *አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ተቆጣጣሪ ነውና*፡፡ إِنَّ اللَّهَ كَانَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ حَسِيبًا

ነገር ግን ሰዎች ከዚህ በተቃራኒው ወደ ፍጡራን ዱዓእ ያረጋሉ። ፍጡራን ሁሉን የማወቅ፣ የመስማት፣ የማየት፣ የመቆጣጠር ችሎታ ውስንነት አለባቸው፥ ስለዚህ ወደ እነርሱ የሚደረግ ዱዓእ አይመልሱም፦
7፥194 *"እነዚያ ከአላህ ሌላ የምትጠሯቸው እንደ እናንተ አምላኪዎች ናቸው፥ እውነተኞችም እንደሆናችሁ ጥሩዋቸው እና ለእናንተ ይመልሱላችሁ አይችሉም"*። إِنَّ ٱلَّذِينَ تَدْعُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ عِبَادٌ أَمْثَالُكُمْ ۖ فَٱدْعُوهُمْ فَلْيَسْتَجِيبُوا۟ لَكُمْ إِن كُنتُمْ صَٰدِقِينَ ።

እነርሱ እንደ ማንኛውም ፈጣሪን አምላኪ አምላኪዎች ናቸው እንጂ ተመላኪዎች አይደሉም። በክርስትና ዱዓእ ከሚደረግላቸው ፍጡራን መካከል መላእክት ናቸው፥ አላህ የትንሳኤ ቀን መላእክትን፦ "እነዚህ እናንተን ያመልኩ ነበሩን? ብሎ ይጠይቃቸዋል፤ እነርሱም በፍጹም፦ "ይልቁንም ጂንን ያመልኩ ነበሩ" ብለው ይመልሳሉ፦
34፥40 *"ሁሉንም በሚሰበስባቸው እና ከዚያም ለመላእክቶቹ፦ «እነዚህ እናንተን ያመልኩ ነበሩን?» በሚላቸው ቀን የሚኾነውን አስታውስ*፡፡ وَيَوْمَ يَحْشُرُهُمْ جَمِيعًا ثُمَّ يَقُولُ لِلْمَلَائِكَةِ أَهَـٰؤُلَاءِ إِيَّاكُمْ كَانُوا يَعْبُدُونَ
34፥41 *መላእክቶቹም፦ «ጥራት ይገባህ "ከእነርሱ ይልቅ ረዳታችን አንተ ብቻ ነህ፥ እንደሚሉት አይደለም፥ ይልቁንም ጂንን ያመልኩ ነበሩ፡፡ አብዛኞቻቸው በእነርሱ አማኞች ናቸው» ይላሉ*፡፡ قَالُوا سُبْحَانَكَ أَنتَ وَلِيُّنَا مِن دُونِهِم ۖ بَلْ كَانُوا يَعْبُدُونَ الْجِنَّ ۖ أَكْثَرُهُم بِهِم مُّؤْمِنُونَ

ልብ አድርግ አድርግ ሰዎች ወደ መላእክት በዱዓእ ዒባዳህ ቢጠቀሙም ግን ያንን ዒባዳህ የሚቀበሉት ጂኒዎች ናቸው። እዚህ ዐውድ ላይ ጂን የተባሉት ሸያጢን ናቸው፥ አንድ ሰው ጣዖት ሲያመልክ ከጣዖቱ በስተኃላ አምልኮ የሚቀበለው ሸይጧን ነው፦
19፥42 *"ለአባቱ «አባቴ ሆይ! የማይሰማንና የማያይን ከአንተም ምንንም የማይጠቅምህን ጣዖት ለምን ታመልካለህን? ባለ ጊዜ አስታውስ"*። إِذْ قَالَ لِأَبِيهِ يَا أَبَتِ لِمَ تَعْبُدُ مَا لَا يَسْمَعُ وَلَا يُبْصِرُ وَلَا يُغْنِي عَنكَ شَيْئًا
19፥44 *«አባቴ ሆይ! ሰይጣንን አታምልክ፡፡ ሰይጣን ለአልረሕማን አመጸኛ ነውና"*፡፡ يَا أَبَتِ لَا تَعْبُدِ الشَّيْطَانَ ۖ إِنَّ الشَّيْطَانَ كَانَ لِلرَّحْمَـٰنِ عَصِيًّا

የኢብራሂም አባት የማይሰማና የማያይ ጣዖት ሲለማመን ከዚያ በስተኃላ የሚመለከው ሸይጧን ስለነበር፦ "አባቴ ሆይ! ሰይጣንን አታምልክ" አለው። እንግዲህ አንድ ሰው ፍጡራንን ሲጠራ ከአላህ ሌላ እረዳት አድርጎ በአላህ ላይ የሚያሻርከው ኩ*ፋ*ሩ*ል ጂን የሆኑትን ሸያጢንን ነው፦
👍1
6፥100 *"ለአላህም ተጋሪዎች የፈጠራቸውን ጂንዎችን አደረጉ"*፡፡ ወንዶች ልጆችንና ሴቶች ልጆችንም ያለ ዕውቀት ለእርሱ ቀጠፉ፡፡ አላህ ጥራት የተገባው ከሚሉት ነገር የላቀ ነው፡፡ وَجَعَلُوا لِلَّهِ شُرَكَاءَ الْجِنَّ وَخَلَقَهُمْ ۖ وَخَرَقُوا لَهُ بَنِينَ وَبَنَاتٍ بِغَيْرِ عِلْمٍ ۚ سُبْحَانَهُ وَتَعَالَىٰ عَمَّا يَصِفُونَ
7፥30 ከፊሉን ወደ ቅን መንገድ መራ፡፡ ከፊሎቹም በእነሱ ላይ ጥመት ተረጋግጦባቸዋል፡፡ *እነርሱ ሰይጣናትን ከአላህ ሌላ ረዳቶች አድርገው ይዘዋልና"*፡፡ እነርሱም ቅኑን መንገድ የተመራን ነን ብለው ያስባሉ፡፡ فَرِيقًا هَدَىٰ وَفَرِيقًا حَقَّ عَلَيْهِمُ الضَّلَالَةُ ۗ إِنَّهُمُ اتَّخَذُوا الشَّيَاطِينَ أَوْلِيَاءَ مِن دُونِ اللَّهِ وَيَحْسَبُونَ أَنَّهُم مُّهْتَدُونَ

አላህ ሰዎችን በቀጥተኛው መንገድ በኢሥላም ላይ ፈጥሮ ሳለ ሸያጢን ግን ከዚህ ዲን በሺርክ ምክንያት ሰዎችን ያርቃሉ፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐግ 53, ሐዲስ 76
ዒያድ ኢብኑ ሒማር እንደተረከው፦ የአላህ መልእክተኛም"ﷺ" ኹጥባህ በሚደረግበት ቀን እንዲህ አሉ፦ *"ለእናንተ ያስተማርኩት ጌታዬ ያዘዘኝ፥ እናንተ የማታውቁትን እርሱ ዛሬ ያሳወቀኝን። አላህም አለ፦ "እኔ የሰጠኃቸውንና ሕጋዊ የሆነላቸው ያ ሁሉ ንብረት ነው። እኔ ሁሉንም ባሮቼን በቀጥተኛው መንገድ ላይ ፈጠርኳቸው፥ ሸያጢን መጥተው ከዲናቸው አራቋቸው"*። عَنْ عِيَاضِ بْنِ حِمَارٍ الْمُجَاشِعِيِّ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ذَاتَ يَوْمٍ فِي خُطْبَتِهِ ‏"‏ أَلاَ إِنَّ رَبِّي أَمَرَنِي أَنْ أُعَلِّمَكُمْ مَا جَهِلْتُمْ مِمَّا عَلَّمَنِي يَوْمِي هَذَا كُلُّ مَالٍ نَحَلْتُهُ عَبْدًا حَلاَلٌ وَإِنِّي خَلَقْتُ عِبَادِي حُنَفَاءَ كُلَّهُمْ وَإِنَّهُمْ أَتَتْهُمُ الشَّيَاطِينُ فَاجْتَالَتْهُمْ عَنْ دِينِهِم

እዚህ ሐዲስ ላይ "ሁነፋእ" حُنَفَاءَ የሚለው ቃል "ሐኒፍ" حَنِيف ለሚለው ብዙ ቁጥር ነው፥ አላህ ሰዎችን በእርስዋ ላይ የፈጠረባትን ሃይማኖት “ሐኒፋ” حَنِيفًا ናት፦
30፥30 *”ፊትህንም ወደ ቀጥተኛ ሃይማኖት ቀጥ አድርግ፡፡ የአላህን ፍጥረት ያችን አላህ ሰዎችን በእርስዋ ላይ የፈጠረባትን ሃይማኖት ያዟት፡፡ የአላህን ፍጥረት መለወጥ የለም፡፡ ይህ ቀጥተኛ ሃይማኖት ነው”*፡፡ ግን አብዛኛዎቹ ሰዎች አያውቁም፡፡ فَأَقِمْ وَجْهَكَ لِلدِّينِ حَنِيفًا ۚ فِطْرَتَ اللَّهِ الَّتِي فَطَرَ النَّاسَ عَلَيْهَا ۚ لَا تَبْدِيلَ لِخَلْقِ اللَّهِ ۚ ذَٰلِكَ الدِّينُ الْقَيِّمُ وَلَـٰكِنَّ أَكْثَرَ النَّاسِ لَا يَعْلَمُونَ

እዚህ አንቀጽ ላይ “ቀጥተኛ” ለሚለው ቃል የገባው “ሐኒፋ” حَنِيفًا ሲሆን አላህ ሰዎችን ሁሉ የፈጠረበት ሃይማኖት ኢሥላም “ሐኒፋ” መሆኑን ያሳያል። አንድ ሰው ፍጡርን በዱዓእ ከጠራ ከዱዓእ በስተኃላ ሸይጧን አምልኮ ስለሚቀበል አምላካችን አላህ በትንሳኤ ቀን፦ "ሸይጧንን አታምልኩ" "አምልኩኝ" ብሎ አዞ እንደነበር ይናገራል፦
36፥60 *የአደም ልጆች ሆይ! ሰይጣንን አታምልኩ! እርሱ ለእናንተ ግልጽ ጠላት ነውና በማለት ወደ እናንተ አላዘዝኩምን?* أَلَمْ أَعْهَدْ إِلَيْكُمْ يَا بَنِي آدَمَ أَن لَّا تَعْبُدُوا الشَّيْطَانَ ۖ إِنَّهُ لَكُمْ عَدُوٌّ مُّبِينٌ
36፥61 *"አምልኩኝ! ይህ ቀጥተኛ መንገድ ነው፤ በማለትም አላዘዝኩምን?"*፡፡ وَأَنِ اعْبُدُونِي ۚ هَـٰذَا صِرَاطٌ مُّسْتَقِيمٌ

ሺርክ በአላህ ላይ ሌሎች ማንነትንና ምንነትን በአምልኮ ማሻረክ ነው፥ ከሺርክ በስተጀርባ ይህንን አምልኮ የሚቀበሉት ሸያጢን ናቸው። ክርስቲያኖች ሆይ! ሳታውቁ የመስማት፣ የማየት፣ የማወቅ፣ የመቆጣጠር ውስንነት ባሕርይ ያለባቸውን ፍጡራንን ስትለማመኑ፣ ስትማጸኑ፣ ስትጠሩ ከነበረ እንግዲያውስ ባለማወቅ ነውና የተውበት በር ሳይዘጋ ወደ ዲኑል ኢሥላም ኑ እና የመስማት፣ የማየት፣ የማወቅ፣ የመቆጣጠር ውስንነት ባሕርይ የሌለበትን ፈጣሪን አላህን በብቸኝነት አብረን እናምልክ። ወደ ፍጡራን ዱዓእ በማድረግ በአላህ ላይ በማሻረክ ለሸያጢን አምልኮ ከመስጠት አላህ ይጠብቀን! አሚን።

ከኡሥታዝ ወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም

🔹🔹ጥሪያችን በሁሉም ቦታ🔹🔹

➡️Facebook ፦
🌐www.facebook.com/tiriyachen

➡️ telegram ፦ https://www.tg-me.com/tiriyachen

➡️YouTube:- youtube.com/@tiriyachen

ወሠላሙ ዐለይኩም
👍1
ከሁሉ በላይ የሆነ አምላክ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

87፥1 ከሁሉ በላይ የሆነዉን ጌታህን ስም አሞግሥ። سَبِّحِ ٱسْمَ رَبِّكَ ٱلْأَعْلَى

በክርስትና ስልታዊ ሥነ-መለኮት”systematic theology” የአምላክ ሰው መሆን አስተምህሮት “ተሰግዎት”Incarnation” ሲባል፥ በአገራችን “ሚስጥረ-ስጋዌ” ይሉታል። “ስጋዌ” የሚለው ቃል “ስግው” ማለትም “ስጋ” ከሚለው የመጣ ነው፥ መለኮት በትስብእት ተገለጠ ብለው ድምዳሜ ላይ ያደረሳቸው የጳውሎስ ንግግር ነው። ለእኛ ለሙሥሊሞች ጳውሎስ የኢየሱስ ሐዋርያ ሳይሆን የግሪክንና የሮምን ዶክትሪን ከኢየሱስ ደክትሪን ጋር ለማስማማት የታገለ ጥሩ ፈላስፋ ነው። ነገር ግን ለክርስቲያኖች እንደ ነብይ ስለሚታይ የእርሱ ትምህርት ለሙሥሊም ማስረጃ ባይሆንም ለእነርሱ ግን መረጃ አድርገን እናቀርባለን። ብዙ ጊዜ ጳውሎስ ኢየሱስን ቁጭ የሚያደርገው ከአንዱ አምላክ ከአብ ነጥሎ ነው፥ ነገር ግን ክርስቲያኖች በተቃራኒው "ጳውሎስ ስለ ኢየሱስ አምላክነት ተናግሯል" ይላሉ። እዚህ ድምዳሜ ላይ አደረሰን ከሚሏቸው አናቅጽ መካከል አንዱን ጥቅስ በአጽንዖትና በአንክሮት እንመልከት፦
ሮሜ 9፥5 አባቶችም ለእነርሱ ናቸውና፤ *"ከእነርሱም ክርስቶስ በሥጋ መጣ፥ ከሁሉ በላይ የሆነ አምላክ እርሱ ለዘላለም የተባረከ ይሁን! አሜን*"። καὶ ἐξ ὁ Χριστὸς τὸ κατὰ σάρκα ὁ ὢν ἐπὶ πάντων Θεὸς εὐλογητὸς εἰς τοὺς αἰῶνας ἀμήν.
Whose are the fathers, and of whom as concerning the flesh Christ came. God, who is over all be blessed for ever. Amen.” Reivised standard version 1971 ,

ግሪኩ ላይ "ኤስቲን" ἐστιν ማለትም "ነው" የሚል ቃል የለም። አዲሱ መደበኛ ትርጉም የግርጌ ማስታወሻ "ከሁሉ በላይ የሆነ አምላክ እርሱም ለዘላለም የተባረከ ይሁን" የሚል ፍቺ እንዳለው እሩቅ ሳንሄድ የዐማርኛ ምሁራን ይነግሩናል። በ 1971 ዕትም Reivised standard version "ይሁን"be" ብሎ አስቀምጦታል፥ "be blessed for ever"። "አሜን" የሚለው ቃል ለምስጋና የመጣ እስከሆነ ድረስ "ለዘላም የተባረከ ይሁን" ማለት ምስጋና ነው። ማነው ለዘላም የተባረከ ይሁን የተባለው? ስንል ለዘላም የተባረከ ይሁን የተባለው "ከሁሉ በላይ" የሆነ አምላክ ነው። እርሱም ከኢየሱስ እና ከመላው ፍጥረት ሁሉ በላይ የሆነው አብ ነው፦
ኤፌሶን 4፥6 ከሁሉ በላይ የሚሆን πάντων በሁሉም የሚሠራ በሁሉም የሚኖር አንድ አምላክ የሁሉም አባት አለ።
ዮሐንስ 10፥29 "የሰጠኝ አባቴ ከሁሉ πάντων ይበልጣል"።
ዮሐንስ 14፥28 የምትወዱኝስ ብትሆኑ *ከእኔ አብ ይበልጣልና ወደ አብ በመሄዴ ደስ ባላችሁ ነበር።

ኢየሱስን የሚበልጠው አብ "ፓንቶን" πάντων ማለትም "ከሁሉ በላይ" ተብሏል። ልብ አድርግ "ክርስቶስ በሥጋ መጣ" የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት። በስጋ የመጣው አምላክ ሳይሆን ክርስቶስ ኢየሱስ ነው። ክርስቶስን ከዳዊት ዘር ያመጣው አምጪ አምላክ ነው፦
የሐዋርያት ሥራ 13፥23 "ከዚህም ሰው ዘር "አምላክ" Θεὸς እንደ ተስፋው ቃል ለእስራኤል መድኃኒትን እርሱም ኢየሱስን አመጣ"*።

"አመጣ" የሚለው ቃል ይሰመርበት። አምጪው አምላክ መጪው ኢየሱስ ከሆነ፥ ክርስቶስን በስጋ ያመጣው አምጪው "ከሁሉ በላይ የሆነ አምላክ ለዘላለም የተባረከ ይሁን" መልእክቱ ይህ ነው። "ለዘላለም የተባረከ" ደግሞ የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እና አምላክ ነው፦
2ኛ ቆሮንቶስ 11፥31 "ለዘላም የተባረከ εὐλογητὸς εἰς τοὺς αἰῶνας ἀμήν የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት"* እንዳልዋሽ ያውቃል።

ጳውሎስ አይሁዳዊ ነው፥ የሚሞግተውም የአይሁድ ዳራ ይዞ ነው። "ቶዩስ አዩናስ" τοὺς αἰῶνας ማለት "ከዘላለም እስከ ዘላለም" ማለት ነው፦
መዝሙር 41፥13 "ከዘላለም እስከ ዘላለም የእስራኤል አምላክ ያህዌህ ይባረክ"። አሜን አሜን።
መዝሙር 106፥48 "ከዘላለም እስከ ዘላለም የእስራኤል አምላክ ያህዌህ ይባረክ፤ ሕዝብም ሁሉ አሜን ይበል"። ሃሌ ሉያ።

ከዘላለም እስከ ዘላለም የተባረከ የእስራኤል አምላክ ያህዌህ ከሆነ፥ እስራኤላውያን አምላካችን የሚሉት ያህዌህን ነው፥ አምላካችን የሚሉት ኢየሱስን ሳይሆን አባቱን እንደሆነ እራሱ ኢየሱስ ተናግሯል፦
ዘዳግም 6፥4 እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ አምላካችን ያህዌህ አንድ ያህዌህ ነው"።
ዮሐንስ 8፥54 "እናንተ አምላካችን የምትሉት አባቴ ነው"።

የሮሜ መልእክት ጸሐፊ ክርስቶስን ለአምላክ ተቀበላችሁት፣ አምላክ የክርስቶስ አባት ነው፣ የክርስቶስ ራስ አምላክ ነው፣ ክርስቶስ የአምላክ ነው፣ ክርስቶስ በአምላክ ፊት ይታያል ወዘተ እያለ ለማምታታት ተመልሶ ክርስቶስ አምላክ ነው አይልም፦
ሮሜ 15፥7 ስለዚህ "ክርስቶስ ለአምላክ Θεὸς ክብር እንደ ተቀበላችሁ"* እንዲሁ እርስ በርሳችሁ ተቀባበሉ።
ሮሜ 15፥6 በአንድ ልብ ሆናችሁ በአንድ አፍ "አምላክን Θεὸς፥ እርሱም የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት"፥ ታከብሩ ዘንድ፥
1ኛ ቆሮንቶስ 11፥3 ነገር ግን የወንድ ሁሉ ራስ ክርስቶስ፥ የሴትም ራስ ወንድ፥ የክርስቶስም ራስ አምላክ Θεὸς እንደ ሆነ ልታውቁ እወዳለሁ""
1ኛ ቆሮንቶስ 3፥23 "ሁሉ የእናንተ ነው፥ እናንተም የክርስቶስ ናችሁ ክርስቶስም የአምላክ Θεὸς ነው።
ዕብራውያን 9፥24 "ክርስቶስ በእጅ ወደ ተሰራች፥ የእውነተኛይቱ ምሳሌ ወደ ምትሆን ቅድስት አልገባምና፥ ነገር ግን በአምላክ Θεὸς *ፊት* ስለ እኛ አሁን ይታይ ዘንድ ወደ እርስዋ ወደ ሰማይ ገባ"።

ክርስቶስ አምላክ ሳይሆን የአምላክ ነው። አምላክ ክርስቶስ ሳይሆን የክርስቶስ አባት እና ራስ ነው። አምላክ በአምላክ ፊት ከታየ ሁለት አምላክ ሊሆን ነው፥ ቅሉ ግን በአምላክ ፊት ስለ አማንያን የሚታየው ክርስቶስ ነው። "ክርስቶስ" ማለት እራሱ "የተቀባ" ማለት ነው፥ ቀቢ አምላክ ተቀቢ ሰው ነው፦
የሐዋርያት ሥራ 10፥38 "አምላክ Θεὸς የናዝሬቱን ኢየሱስን በመንፈስ ቅዱስ በኃይልም ቀባው፥ እርሱም መልካም እያደረገ ለዲያብሎስም የተገዙትን ሁሉ እየፈወሰ ዞረ፥ አምላክ Θεὸς ከእርሱ ጋር ነበረና"።

ክርስቶስ አምላክ ሳይሆን አምላክ የቀባው እና አምላክ ከእርሱ ጋር የነበረ ሰው ነው። አምላክ አምላክን ለመርዳት አብሮት ነበር ማለት መድበለ-አማልክት ይሆናል። አይ አምላክ በክርስቶስ ሆኖ የዕርቅ ሥራ ሠራ እንጂ አምላክ ክርስቶስ አይደለም፦
2ኛ ቆሮንቶስ 5፥19 "አምላክ Θεὸς በክርስቶስ ሆኖ" ዓለሙን ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበርና።

"አምላክ በአምላክ ሆኖ" ትርጉም አይሰጥም፥ ሁለት አምላክ ይሆናል። "አንድ ሰው ከሌላ ሰው ጋር ነበረ" ብሎ ሁለቱም አንድ ሰው ሳይሆኑ ሁለት ሰዎች ናቸው።
ስለዚህ ጳውሎስ ለማለት የፈለገው "ክርስቶስን በስጋ ያመጣ ከሁሉ በላይ የሆነ አምላክ አብ ለዘላለም የተባረከ ይሁን! አሜን" የሚል ብቻ ነው። በኢሥላም ከሁሉ በላይ የሆነዉ ጌታ አምላክ አላህ ብቻ ነው፥ እነዚያ መሲሢሑን "አላህ ነው" ያሉ በእርግጥ ካዱ። ይህ በአላህ አምላክነትን ላይ ሰውን ማሻረክ ነው፥ እነሆ በአላህ ላይ የሚያጋራ ሰው አላህ በእርሱ ላይ ገነትን በእርግጥ እርም ስላደረገበት እና መኖሪያውም እሳት ስለሆነች መሲሢሑን "አላህ ነው" የምትሉ የተውበት በሩ ሳይዘጋ በተውበት ወደ አላህ ተመለሱ፦
👍1
87፥1 ከሁሉ በላይ የሆነዉን ጌታህን ስም አሞግሥ። سَبِّحِ ٱسْمَ رَبِّكَ ٱلْأَعْلَى
5፥72 " «አላህ እርሱ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ነው» ያሉ በእርግጥ ካዱ፡፡ አልመሲህም አለ፡- «የእስራኤል ልጆች ሆይ! ጌታዬንና ጌታችሁን አላህን ተገዙ፡፡» እነሆ! በአላህ የሚያጋራ ሰው አላህ በርሱ ላይ ገነትን በእርግጥ እርም አደረገ፡፡ መኖሪያውም እሳት ናት፡፡ ለበዳዮችም ምንም ረዳቶች የሏቸውም"፡፡ لَقَدْ كَفَرَ الَّذِينَ قَالُوا إِنَّ اللَّهَ هُوَ الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ ۖ وَقَالَ الْمَسِيحُ يَا بَنِي إِسْرَائِيلَ اعْبُدُوا اللَّهَ رَبِّي وَرَبَّكُمْ ۖ إِنَّهُ مَن يُشْرِكْ بِاللَّهِ فَقَدْ حَرَّمَ اللَّهُ عَلَيْهِ الْجَنَّةَ وَمَأْوَاهُ النَّارُ ۖ وَمَا لِلظَّالِمِينَ مِنْ أَنصَارٍ

✍️ከኡሥታዝ ወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም

🔹🔹ጥሪያችን በሁሉም ቦታ🔹🔹

➡️Facebook ፦
🌐www.facebook.com/tiriyachen

➡️ telegram ፦ https://www.tg-me.com/tiriyachen

➡️YouTube:- youtube.com/@tiriyachen

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሁለተኛው አጽናኝ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

የመርየም ልጅ ዒሳም፡- «የእስራኤል ልጆች ሆይ! እኔ ከተውራት በፊቴ ያለውን የማረጋግጥ እና ”ከእኔ በኋላ በሚመጣው መልክተኛ ስሙ አሕመድ በኾነው የማበስር” ስኾን ወደ እናንተ የተላክሁ የአላህ መልክተኛ ነኝ» ባለ ጊዜ አስታውስ፡፡ በግልጽ ተዓምራቶች በመጣቸውም ጊዜ «ይህ ግልጽ ድግምት ነው» አሉ፡፡
ቁርኣን 61፥6

መግቢያ
የመጽሐፉም ባለቤቶች ክርስቲያኖች እና አይሁዳውያን ከአላህ የወረደውን እውነት ከሰው ንግግር ቃል ቀላቅለዋል፤ በተጨማሪም ከአላህ የወረደውን እውነት ደብቀዋል፦

የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! እውነቱን በውሸት ለምን ትቀላቅላላችሁ ”እውነቱንም እናንተ የምታውቁ ስትኾኑ ለምን ትደብቃላችሁ”?፤
ቁርኣን 3፥71

በ 397 AD የተደረገው የካርቴጅ ጉባኤ ብዙ የወንጌል ቅሪት አፓክራፋ ብሎ ቀንሷል፤ “አፓክራፋ” ማለት “አፓክራፎስ” ἀπόκρυφος ከሚለው የግሪክ ቃል የተገኘ ሲሆን “ድብቅ” “ስውር” ማለት ነው፦

ገብታችህ አንብቡት ይጠቅማችኋል👇🏻👇🏻
https://tiriyachen.org/ሁለተኛው-አጽናኝ/
5👍1
አላህ ሁሉን ዐዋቂ ነው! | ዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ | ጥሪያችን

🔗 https://youtu.be/FIuKzn_KwTo

👆  አዲስ ቪድዮ በዩትዩብ ቻነላችን ላይ


መልካም ቆይታ ከጥሪያችን ጋር
‐‐‐
Follow us on:
https://fb.me/tiriyachen
https://www.tg-me.com/tiriyachen
https://tiriyachen.org
https://bit.ly/3eVixKv
https://www.tiktok.com/@tiriyachen
የጨረቃ አቆጣጠር

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

2፥189 *ከለጋ ጨረቃዎች ይጠየቁሃል፥ እነርሱ ለሰዎች ጥቅም ለሐጅም ማወቂያ ጊዜያቶች ምልክቶች ናቸው በላቸው*፡፡ يَسْأَلُونَكَ عَنِ الْأَهِلَّةِ ۖ قُلْ هِيَ مَوَاقِيتُ لِلنَّاسِ وَالْحَج

የተቆጠሩ ቀኖች የያዘው 9ኛው ወር ረመዷን በመጣ ቁጥር የጨረቃ መታየት እና አለመታየት በፆም መጀመር እና መጨረስ ላይ የሚኖረውም አውንታዊ ተፅዖኖ ብዙ የክርስትና ዘላፊያን ሆኑ ኀያሲያን እንደ በቀቀን እየደጋገሙ መዝለፍና ኂስ መስጠታቸው አይቀሬ ነው። ይህንን ታሳቢና ዋቢ ባደረገ መልኩ ይህንን መጣጥፍ ለዚያ ምላሽ አቅርቤአለው። ግብጻውያን፣ ባቢሎናውያን፣ ሰመርያን፣ ሄለናውያን(ግሪኮች)፣ ሮማውያን፣ ዞራስተሪያን፣ ሂንዱ የየራሳቸው "የዘመን አቆጣጠር"calendar" ነበራቸው።
ይህ አቆጣጠራቸው ምንጩ "አል-ቀመርያ" ማለትም "የጨረቃ አቆጣጠር"lunar calender" እና "አሽ-ሸምሲያህ" ማለትም "የፀሐይ አቆጣጠር"solar calended" ናቸው። አምላካችን አላህ በተከበረ ቃሉ ፀሐይን እና ጨረቃን ለሰው ልጆች የዓመታትን ቁጥርና ሒሳብን መቁጠሪያ እንዳደረገ ይናገራል፦
6፥96 እርሱም ጎህን ከሌሊት ጨለማ ፈልቃቂ ሌሊትንም ማረፊያ *"ፀሐይንና ጨረቃንም ለጊዜ መቁጠሪያ አድራጊ ነው"*፡፡ فَالِقُ الْإِصْبَاحِ وَجَعَلَ اللَّيْلَ سَكَنًا وَالشَّمْسَ وَالْقَمَرَ حُسْبَانًا ۚ ذَٰلِكَ تَقْدِيرُ الْعَزِيزِ الْعَلِيمِ
10፥5 እርሱ ያ ፀሐይን አንጻባራቂ ጨረቃንም አብሪ ያደረገ ነው፡፡ *የዓመታትን ቁጥርና ሒሳብን ታውቁ ዘንድም ለእርሱ መስፈሪያዎችን የለካ ነው*፡፡ አላህ ይህንን በእውነት እንጂ በከንቱ አልፈጠረውም፡፡ ለሚያውቁ ሕዝቦች አንቀጾችን ያብራራል፡፡ هُوَ الَّذِي جَعَلَ الشَّمْسَ ضِيَاءً وَالْقَمَرَ نُورًا وَقَدَّرَهُ مَنَازِلَ لِتَعْلَمُوا عَدَدَ السِّنِينَ وَالْحِسَابَ ۚ مَا خَلَقَ اللَّهُ ذَٰلِكَ إِلَّا بِالْحَقِّ ۚ يُفَصِّلُ الْآيَاتِ لِقَوْمٍ يَعْلَمُونَ

የሥነ-ተረት ጥናት"mythology" እንደሚያትተው በተለይ በባቢሎናውያን "ሲን" የተባለው የጨረቃ አምላክ እና "ሻም" የተባለው የፀሐይ አምላክ ባልና ሚስት ተደርገው ይመለኩ ነው፤ "ሲን" ማለት "ጨረቃ" ማለት ሲሆን "ሻም" ደግሞ "ፀሐይ" ማለት ነው። ይህንን እሳቤ ቁርአን መንግሎ ይጥለዋል፤ መመለክ የሚገባው ፀሐይና ጨረቃን የፈጠራቸው አላህ ብቻ ነው፦
41፥37 ሌሊትና ቀንም፣ *"ጸሐይና ጨረቃም ከምልክቶቹ ናቸው፤ ለፀሐይና ለጨረቃ አትስገዱ፤ ለዚያም ለፈጠራቸው አላህ ሰገዱ፤ እርሱን ብቻ የምታመልኩ እንደሆናችሁ ለሌላ አትስገዱ"*። وَمِنْ آيَاتِهِ اللَّيْلُ وَالنَّهَارُ وَالشَّمْسُ وَالْقَمَرُ ۚ لَا تَسْجُدُوا لِلشَّمْسِ وَلَا لِلْقَمَرِ وَاسْجُدُوا لِلَّهِ الَّذِي خَلَقَهُنَّ إِن كُنتُمْ إِيَّاهُ تَعْبُدُونَ

የዘመናችን የሥነ-ፈለክ ጥናት እንደሚያትተው የጨረቃ ፈለክ ምድራችንን በ 384,408 km በሆነ ዑደት”Revolution” ለመዞር የሚወስድባት ጊዜ 27 ቀናት ነው። አምላካችን አላህም በቁርኣን “ቀመር” قَمَر ማለትም “ጨረቃ” የሚለውን ቃል የተጠቀመው “27” ጊዜ ብቻ ነው። ጨረቃ ፕላኔታችንን በምእራባዊ አቅጣጭ 360 ድግሪ ለመዞር 19 ዓመት ይፈጅባታል።
የሚያስደምመው ነገር “ዓመት” የሚለው ቃል የተጠቀሰው “ሢኒን” سِنِين በብዜት 12 ጊዜ ወይም “ሠናህ” سَنَة በነጠላ 7 ጊዜ በጥቅሉ “19” ጊዜ ብቻ ነው። ይህ የሆነበት ምክንያት የዓለማቱ ጌታ ነገርን ሁሉ በቁጥር ያጠቃለለ ስለሆነ ነው፦
72፥28 እነርሱ ዘንድ ባለው ነገር እውቀቱ የከበበ እና * ነገሩንም ሁሉ “በቁጥር” ያጠቃለለ ሲሆን"* የጌታቸውን መልክቶች ያደረሱ መሆናቸውን ያውቅ ዘንድ ጠባቂ ያደርጋል። لِّيَعْلَمَ أَن قَدْ أَبْلَغُوا رِسَالَاتِ رَبِّهِمْ وَأَحَاطَ بِمَا لَدَيْهِمْ وَأَحْصَىٰ كُلَّ شَيْءٍ عَدَدًا

የእኛ አቆጣጠር የጨረቃ አቆጣጠር ነው፦
2፥189 *ከለጋ ጨረቃዎች ይጠየቁሃል፥ እነርሱ ለሰዎች ጥቅም ለሐጅም ማወቂያ ጊዜያቶች ምልክቶች ናቸው በላቸው*፡፡ يَسْأَلُونَكَ عَنِ الْأَهِلَّةِ ۖ قُلْ هِيَ مَوَاقِيتُ لِلنَّاسِ وَالْحَج

የለጋ ጨረቃ መታየት የጊዜ ማወቂያ ምልክት ነው። ነቢያችን”ﷺ” የአላህ ነብይ ስለሆኑ በዐቂዳህ እና በፊቅህ ጉዳይ ላይ የሚናገሩት ወሕይ ስለሆነ ስለ ጨረቃ እንዲህ ይሉናል፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 6, ሐዲስ 2378
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ.” እንደተረከው የአላህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"መቼም ቢሆን ለጋ ጨረቃ በረመዳን ወር ስታዩ ፆምን ጀምሩ፤ የሸዋል ለጋ ጨረቃ ስታዩ ፆማችሁን ጨርሱ፤ ሰማይ ደመናማ ሲሆንላችሁ ፆም ሰላሳ ቀን መሆኑን አጢኑ"*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، - رضى الله عنه - قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ إِذَا رَأَيْتُمُ الْهِلاَلَ فَصُومُوا وَإِذَا رَأَيْتُمُوهُ فَأَفْطِرُوا فَإِنْ غُمَّ عَلَيْكُمْ فَصُومُوا ثَلاَثِينَ يَوْمًا ‏"
የጨረቃ አቆጣጠር በኢሥላም በግርድፉና በሌጣው ይህ ያክል ካየን ዘንዳ የጨረቃ አቆጣጠር በባይብልና በትውፊት እናያለን። የጨረቃ መታየት ለጊዜ ማወቂያ እንደሆነ መዝሙረኛው ይናገራል፦
መዝሙረ ዳዊት 104፥19 *”ጨረቃን ለጊዜዎች አደረገ”* ፀሐይም መግቢያውን ያውቃል።

በተለይ አይሁዳውያን የወር መባቻ ጠብቀው በዓላቸውን የሚያውቁበት ነው፤ የወር መባቻ የሚለው የዕብራይስጥ ቃል “ቆደሽ” חֹ֫דֶשׁ ሲሆን ትርጉሙ “አዲስ ጨረቃ” ማለት ነው ፣ ይህም ቃል በባይብል 28 ጊዜ ተወስቷል፤ ዕብራውያን ወራቸውን ሆነ ዓመታቸውን የሚጀምሩ በለጋ ጨረቃ መታየት ነው፦
ዘኍልቍ 10፥10 ደግሞ በደስታችሁ ቀን፥ በበዓላታችሁም ዘመን፥ *”በአዲስ ጨረቃ” חָדְשֵׁיכֶם֒ ፥”* በሚቃጠል መሥዋዕታችሁና በደኅንነት መሥዋዕታችሁ ላይ መለከቶቹን ንፉ እነርሱም በአምላካችሁ ፊት ለመታሰቢያ ይሆኑላችኋል እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ። NIV Bible
መዝሙር 81፥3 *”በአዲስ ጨረቃ” חָדְשֵׁיכֶם֒ ቀን”* በከፍተኛው በዓላችን ቀን መለከትን ንፉ፤ NIV Bible

በክርስትና ቀዳማይ የዘመን አቆጣጠር ከ 180 –222 ድኅረ-ልደት”A.D” ድረስ ለ 42 ዓመት የአሌክሳንድርያ ፓትርያርክ የነበረው ድሜጥሮስ የቀመረው ነው። ይህም የዘመን ቀመር “አቡሻኽር” ወይም “ባሕረ-ሐሳብ” ይባላል። “ባሕር” ማለት “ዘመን” ማለት ሲሆን “ሐሳብ” ማለት ደግሞ “ሒሳብ” “ቁጥር” “ኍልቅ” ማለት ነው። በዚህ የዘመን ቀመር ላይ ስለ “አዕዋዳት” ይናገራል፥ “አዕዋድ” ማለት “ዖደ” ማለትም “ዞረ” ከሚል የግዕዝ ቃል የተገኘ ሲሆን “ዙረት” ማለት ሲሆን በየጊዜው እየዞረ የሚመጣ ማለት ነው።
1👍1
2025/07/08 22:18:05
Back to Top
HTML Embed Code: