Telegram Web Link
የተሳከረ ምልከታ

ክፍል አንድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

10፥68 በአላህ ላይ የማታውቁትን ትናገራላችሁን? ۚ أَتَقُولُونَ عَلَى اللَّهِ مَا لَا تَعْلَمُونَ

መግቢያ
ትጉሃን ሃያሲ በስሙር ሙግት ሂስ ሲሰጡ ማዳመጥ አስተማሪ ከመሆን ባሻገር ያለንበትን እውነት እንድናጠናክር ያበረታታል፤ በተቃራኒው ሚሽነሪዎች ቧጠውና ሟጠው በጥላቻ ለሚያጠለሹአቸው ጥላሸት ኢስላማዊ አቃቤ-እምነት መሰረት አድርገን ድባቅ ማስገባት ግድ ይላል፤ የተሳከረ፣ የተውረገረገ፣ የደፈረሰና የተንሸዋረረ ምልክታ የሚመጣው ከእጥረተ-ንባብ እና ከጥራዝ ነጠቅ ዕውቀት ነው፤ በተለይ በአላህ ላይ የማያውቁትን መናገር ከሸይጧን ነው፤ ሰይጣን ወዳጆቹን የሚያዛቸው በኃጢኣትና በጸያፍ ነገር በአላህም ላይ የማያውቁትን እንዲናገሩ ነው፦
2፥169 እርሱ(ሰይጣን) የሚያዛችሁ በኃጢኣትና በጸያፍ ነገር *"በአላህም ላይ የማታውቁትን እንድትናገሩ ብቻ ነው"*፡፡ إِنَّمَا يَأْمُرُكُم بِٱلسُّوٓءِ وَٱلْفَحْشَآءِ وَأَن تَقُولُوا۟ عَلَى ٱللَّهِ مَا لَا تَعْلَمُونَ
10፥68 *"በአላህ ላይ የማታውቁትን"* ትናገራላችሁን? ۚ أَتَقُولُونَ عَلَى اللَّهِ مَا لَا تَعْلَمُونَ

ሆን ተብሎ በአላህ ላይ ውሸትን ቀጣጥፎ አንቀጾቹን ማስተባበል ትልቅ በደል ነው፤ በደለኞች ደግሞ ከጀሃነም መዘውተር አይድኑም፦
6፥21 *በአላህም ላይ ውሸትን ከቀጣጠፈ ወይም በአንቀጾቹ ካስተባበለ ሰው ይበልጥ በደለኛ ማነው?"* እነሆ *"በደለኞች አይድኑም"*፡፡ وَمَنْ أَظْلَمُ مِمَّنِ ٱفْتَرَىٰ عَلَى ٱللَّهِ كَذِبًا أَوْ كَذَّبَ بِـَٔايَٰتِهِۦٓ ۗ إِنَّهُۥ لَا يُفْلِحُ ٱلظَّٰلِمُونَ
10፥17 *በአላህም ላይ እብለትን ከቀጣጠፈ ወይም በአንቀጾቹ ከአስተባበለ ይበልጥ በዳይ ማን ነው?"* እነሆ አመጸኞች አይድኑም፡፡ فَمَنْ أَظْلَمُ مِمَّنِ ٱفْتَرَىٰ عَلَى ٱللَّهِ كَذِبًا أَوْ كَذَّبَ بِـَٔايَٰتِهِۦٓ ۚ إِنَّهُۥ لَا يُفْلِحُ ٱلْمُجْرِمُونَ
29፥68 *"በአላህ ላይም ውሸትን ከቀጣጠፈ ሰው ወይም እውነቱ በመጣለት ጊዜ ከአስዋሸ ይበልጥ በዳይ ማነው?* በገሀነም ውስጥ ለከሓዲዎች መኖሪያ የለምን? وَمَنْ أَظْلَمُ مِمَّنِ ٱفْتَرَىٰ عَلَى ٱللَّهِ كَذِبًا أَوْ كَذَّبَ بِٱلْحَقِّ لَمَّا جَآءَهُۥٓ ۚ أَلَيْسَ فِى جَهَنَّمَ مَثْوًۭى لِّلْكَٰفِرِينَ

እንግዲህ እውነቱን እንገልጣለን ቅጥፈቱን እናጋልጣለን፤ አንድ ሰው ይህ እውነት በመጣለት ጊዜ ከአስዋሸ በደለኛ ከሃጂ ነው፤ ለከሓዲዎች ደግሞ መኖሪያ ገሀነም ነው፤ እስቲ ይህንን አለሌ እና ቅሪላ ምልከታ አንኮላ እና እንኩቶ መሆኑን እናሳያለን፦

ነጥብ አንድ
"ኢላህ"
“አሏህ” ٱللَّه የሚለው ስም 2699 ጊዜ በቁርአን የመጣ ሲሆን ትርጉሙ “የሚመለክ” ወይም “አምልኮ የሚገባው”"the Being Who worshiped" ማለት ነው፤ Lane's Arabic-English Lexicon by Edward William Lane (London: Willams & Norgate 1863) ይመልከቱ።
"አሏህ" ኢስሙል ዛት” ማለትም “የህላዌው ስም” ነው፤ “ዛት” ذات ማለት “ምንነት” ሲሆን አላህ በምንነቱ የሚመለክ ነው፤ ማንነት እከሌ የሚባል ነው፤ ፈጣሪ ማን ነው? ጌታ ማን ነው? አስተናባሪ ማን ነው? ተብሎ ሲጠየቅ አላህ ነው፦
10:31 «ከሰማይና ከምድር ሲሳይን የሚሰጣችሁ ማን ነው መስሚያዎችንና ማያዎችንስ የፈጠረ ማን ነው ከሙትም ሕያውን የሚያወጣ ከሕያውም ሙትን የሚያወጣስ ማን ነው ነገሩን ሁሉ የሚያስተናብርስ ማን ነው» በላቸው፡፡ «በእርግጥም አላህ ነው» ይሉሃል፡፡ «ታዲያ ለምን ታጋራላችሁ አትፈሩትምን» በላቸው፡፡

አላህ ማንነት ሲሆን የህላዌ ስሙ ነው፤ የተጸውዖ ስም በየትኛውም ቋንቋ እራሱን ነው እንጂ በትርጉም አይጠራም፤ ለምሳሌ "ወሒድ" ስሜ ነው፤ ትርጉሙ "ብቸኛ" ማለት ነው፤ ኢትዮጵያ "ብቸኛ" ኢንግላንድ "only" ስውዲን "bara" ግሪክ "ሞኖ" እስራኤል "ኢኻድ" እባላለውን? በፍፁም ይህ የተጸውዖ ስም የትም አገር አይቀየርም። እዚህ ድረስ ካየን አላህ የስሙን ትርጉሙ ከላይ እንዳየነው “የሚመለክ” ወይም “አምልኮ የሚገባው” ማለት ሲሆን አንዳንድ ጥራዝ ነጠቅ ተቺዎች ጎግል ላይ በሚቃርሟት የለበጣ መረጃ አሏህ "አል" ال እና "ኢላህ" إِلَٰه ከሚል ቃላት የተዋቀረ ነው ይላሉ፤ ይህ ትልቅ ስህተት ነው፤ “ኢላህ” إِلَٰه ትርጉሙ “አምላክ” ማለት ነው፤ "አል" የሚል አመልካች መስተአምር"definite article" ሲገባበት "አል-ኢላህ" الإِلَٰه "አምላክ"the-God" ይሆናል እንጂ ትርጉሙ "አሏህ" ٱللَّه ማለት አይደለም፤ ምክንያቱም አሏህ ላይ ላም ተሽዲድ ሆና ትመጣለችና፤ “ኢላህ” ላይ ግን ሸዳህ የለውም። “ኢላህ” 147 ጊዜ በቁርአን የመጣ ሲሆን የኢላህ ብዙ ቁጥር ደግሞ “አሊሀህ” آلِهَةٌ ማለትም "አማልክት" ነው፤ “ኢላህ” ማለት “አምላክ”God" ተብሎ በትርጉም መጠቀም ይቻላል፤ ግን “አላህ” የተፀውዖ ስም ስለሆነ እራሱ ነው የሚቀመጠው፦
17:22 “ከአላህ” ጋር ሌላን “አምላክ” አታድርግ፤ የተወቀስክ ረዳት የሌለህ ትሆናለህና لَّا تَجْعَلْ مَعَ ٱللَّهِ إِلَٰهًا ءَاخَرَ فَتَقْعُدَ مَذْمُومًۭا مَّخْذُولًۭا ፤
28:88 “ከአላህም” ጋር ሌላን “አምላክ” አትጥራ وَلَا تَدْعُ مَعَ ٱللَّهِ إِلَٰهًا ءَاخَرَ ۘ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ ۚ كُلُّ شَىْءٍ هَالِكٌ إِلَّا وَجْهَهُۥ ۚ لَهُ ٱلْحُكْمُ وَإِلَيْهِ تُرْجَعُونَ ፡፡
26:213 “ከአላህም” ጋር ሌላን “አምላክ” አትጥራ፤ ከሚቀጡት ትኾናለህና فَلَا تَدْعُ مَعَ ٱللَّهِ إِلَٰهًا ءَاخَرَ فَتَكُونَ مِنَ ٱلْمُعَذَّبِينَ ፡፡

በሰዋስው ሕግ "ያ" يا ማለት "ሆይ"O" ማለት ሲሆን "Vocative particle" ነው፤ በዚህ ሕግ "ያ ረብ" يا رَبِّ "ያ ኢላህ" يا إِلَٰه "ያ ረህማን" يا رَّحْمَٰنِ "ያ ረሂም" يا رَّحِيمِ ወዘተ ማለት እንችላለን፤ ነገር ግን አመልካች መስተአምር የሆኑትን ቀመርያህ እና ሸምሲያህ ጨምረን "ያ አር-ረብ" "ያ አል-ኢላህ" "ያ አር-ረህማን" "ያ አር-ረሂም" ወዘተ ማለት አይቻልም። አሏህ ቃሉ አል-ኢላህ ቢሆን ኖሮ "ያ አሏህ" يا ٱللَّه የሚለው አይመጣም ነበር፤ አሏህ ላይ ግን "Vocative particle" በመነሻ "ያ አሏህ" يا ٱللَّه አሊያም በመዳረሻ “አሏሁ-ማ” ٱللَّهُمَّ ሆኖ ይመጣል፦
3:26 በል- የንግሥና ባለቤት የሆንክ *"አላህ ሆይ"*! ለምትሻዉ ሰዉ ንግሥናን ትሰጣለህ፤ ከምትሻዉም ሰዉ ንግስናን ትገፍፋለህ፤ የምትሻዉንም ሰዉ ታልቃለህ፤ የምትሻዉንም ሰዉ ታዋርዳለህ። መልካም ነገር ሁሉ በእጅህ በችሎታህ ነው፤ አንተ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነህና። قُلِ ٱللَّهُمَّ مَٰلِكَ ٱلْمُلْكِ تُؤْتِى ٱلْمُلْكَ مَن تَشَآءُ وَتَنزِعُ ٱلْمُلْكَ مِمَّن تَشَآءُ وَتُعِزُّ مَن تَشَآءُ وَتُذِلُّ مَن تَشَآءُ ۖ بِيَدِكَ ٱلْخَيْرُ ۖ إِنَّكَ عَلَىٰ كُلِّ شَىْءٍۢ قَدِيرٌۭ

ሌላው በቋንቋ ሕግ ያለው የሙህራን አቅዋል አንድ ቃል ከግስ መደብ እና ከስም መደብ ሲረባ "ሙሽተቅ" مُشتَق ማለትም "ሥርወ-ግንዳዊ ቃል"derivative word" ሲባል ነገር ግን አንድ ቃል ከግስ መደብ እና ከስም መደብ የማይረባ ከሆነ "ጃሚድ" جامِد ማለትም "ሥርወ-ግንድ አልባ"un-derivative word" ይባላል፤ በዐረቢኛ ቋንቋ ሕግ የአሏህ ስም ጃሚድ ነው። ስለዚህ አሏህ ከአል-ኢላህ ሥርወ-ግንድ የተገኘ ነው ማለት የተሳከረ፣ የተውረገረገ፣ የደፈረሰና የተንሸዋረረ ምልክታ ነው። ኢንሻላህ ሌላውን የተሳከረውን ምልከታ በክፍል ሁለት እናየዋለን።

ኡሥታዝ ወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም

ለመከታተል፦ ጥሪያችን Tiriyachen
Follow as :- https://www.facebook.com/tiriyachen

ወሰላሙ አለይኩም
የአሏህ ስም

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

በአረቢኛ ድምጽ ያላቸው "ተነባቢ ፊደላት”sound letters” 28 ሲሆኑ "አጫዋች ፊደል”stretch letter” ደግሞ 1 ሲሆን እርሱም "አሊፍ" ا ነው። በመካከላቸው ስናነባቸው የሚቀጥን ፊደል 19 ሲሆን “ተርቂቅ” ይባላል፣ የሚወፍር ፊደል ደግሞ 7 ሲሆን “ተፍሂም” ይባላል፣ ነገር ግን ተርቂቅና ተፍሂም የሆኑ ሁለት ሃርፎች “ራ” ر እና “ላም”ل ናቸው፤ "ራ" ر በፈትሃና በደማ ይወፍራል በከስራ ይቀጥናል፣ "ላም" ل ደግሞ በለፍዙል ጀላላ ማለትም በአላህ ስም ላይ ትወፍራለች። ይህንን እሳቤ ይዘን የአላህ ስምን ስናጠና "አሏህ" ٱللَّه የሚለው ስም 2699 ጊዜ በቁርአን የመጣ ሲሆን ትርጉሙ "የሚመለክ" ወይም "አምልኮ የሚገባው" ማለት ነው፤ አላህ ኢስሙል ዛት" ማለትም "የህላዌው ስም" ነው፤ "ዛት" ذات ማለት "ምንነት" ሲሆን አላህ በምንነቱ የሚመለክ ነው፤ ይህ ስም በሙያ እንዲህ ተቀምጧል፤ “ኢዕራብ” إﻋﺮﺍﺏ ማለት “ሙያ”case” ማለት ሲሆን ይህ ሙያ “ፈትሐ” فَتْحَة “ከስራ” كَسْرَة “ደማ” ضَمَّة በሚባሉ አጭር አናባቢ ሃርፎች ላይ ያገለግላሉ፦
“መንሱብ”፦ በፈትሐ የሚያገለግለው ሙያ “መንሱብ” المنصوب ማለትም ተሳቢ ሙያ”accusative case” ሲሆን አሏህ በፈትሐ ስንጠቀም "አሏሀ" اللَّهَ ይሆናል።
“መጅሩር”፦ በከስራ የሚያገለግለው ሙያ “መጅሩር” المجرور ማለትም አገናዛቢ ሙያ”genitive case” ሲሆን አሏህ በከስራ ስንጠቀም "ሊሏሂ" اللَّهِ ይሆናል።
“መርፉዕ”፦ በደማ የሚያገለግለው ሙያ ደግሞ “መርፉዕ” المرفوع ማለትም ባለቤት ሙያ”nominative case” ሲሆን አሏህ በደማ ስንጠቀም "አሏሁ" اللَّهُ ይሆናል። ለምሳሌ፦ "አሏሁ-ማ" ٱللَّهُمَّ ማለት "ያ-አሏህ" ማለት ነው።

ይህ ስም የፈለግነውን ሃርፍ ከላዩ ላይ ቢቀነስ ትርጉም አለው፦
@ አሏህ በሚለው መነሻ የመጀመሪያውን አንድ ሀርፍ ስንቀንሰው "ሊሏህ" لله የሚል ይሆናል፡፡ ትርጉሙም "የአላህ" ማለት ነው።
@ አሏህ በሚለው የመጀመሪያዎቹን ሁለት ሃርፎች ስንቀንሰው ደግሞ ውጤቱ "ለሁ" لَهُ የሚል ይሆናል፡፡ ትርጉሙም "የእርሱ" የሚል ነው፡፡
@ አሏህ በሚለው የመጀመሪያዎቹን ሶስት ሃርፎች ስንቀንሰው ደግሞ ውጤቱ "ሁ" هُ የሚለው ይሆናል፡፡ ትርጉሙም "እርሱ" የሚል ነው፡፡
@ አሏህ በሚለው ሀርፎች ከመሀል ከሁለቱ የላም ሃርፎች አንዱን ስንቀንሰው ውጤቱ "ኢላህ" إِلَٰه የሚለው ይሆናል፤ ትርጉሙ "አምላክ" ማለት ነው፤ "ኢላህ" የሚለው ቃል 147 ጊዜ በቁርአን የመጣ ሲሆን ተባታይ ነው፤ አንስታይ ሲሆን ደግሞ "ኢላሃህ" إلاهة ነው፤ የኢላህ ብዙ ቁጥር ደግሞ "አሊሀህ" آلِهَةٌ ነው፤ "ኢላህ" በተለያየ አገናዛቢ ተውላጠ ስም ላይ ሲመጣ፦
"ኢላሂ" إِلَٰهي "አምላኬ"
"ኢላሁና" إِلَٰهُنَا "አምላካችን"
"ኢላሀከ" إِلَٰهَكَ "አምላክህ"
"ኢላሀኩም" إِلَٰهُكُمْ "አምላካችሁ"
"ኢላሀሁ" إِلَٰهَهُ "አምላኩ"
"ኢላሀሁም" إِلَٰهَهُمْ "አምላካቸው" ይሆናል።
"ኢላህ" ማለት "አምላክ" ተብሎ በትርጉም መጠቀም ይቻላል፤ ግን "አላህ" የተፀውዖ ስም ስለሆነ እራሱ ነው የሚቀመጠው፦
17:22 "ከአላህ" ጋር ሌላን "አምላክ" አታድርግ፤ የተወቀስክ ረዳት የሌለህ ትሆናለህና لَّا تَجْعَلْ مَعَ ٱللَّهِ إِلَٰهًا ءَاخَرَ فَتَقْعُدَ مَذْمُومًۭا مَّخْذُولًۭا ፤
28:88 "ከአላህም" ጋር ሌላን "አምላክ" አትጥራ وَلَا تَدْعُ مَعَ ٱللَّهِ إِلَٰهًا ءَاخَرَ ۘ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ ۚ كُلُّ شَىْءٍ هَالِكٌ إِلَّا وَجْهَهُۥ ۚ لَهُ ٱلْحُكْمُ وَإِلَيْهِ تُرْجَعُونَ ፡፡
26:213 "ከአላህም" ጋር ሌላን "አምላክ" አትጥራ፤ ከሚቀጡት ትኾናለህና فَلَا تَدْعُ مَعَ ٱللَّهِ إِلَٰهًا ءَاخَرَ فَتَكُونَ مِنَ ٱلْمُعَذَّبِينَ ፡፡

ነጥብ አንድ
"አሏህ እና ሴማዊ ዳራ"
አሏህ በዕብራይስ አሁንም "ላሜድን" א ተሽዲድ ስናደርገው "አሏህ" אללה‌‎ ሲሆን ከውስጡ ሁለት "ላሜድ" א ሲኖረው አንዱን ስንቀንስ "ኤሎሃ" אלוהּ ይሆናል፤ ትርጉሙም "አምላክ" ማለት ነው፤ የኤሎሃ ብዜት ደግሞ "ኤሎሂም" אלהים ነው፤ "ኤል" אֵל የኤሎሃ ምፃረ-ቃል ሲሆን የኤል ብዜት ደግሞ "ኤሊም" אֵלִ֑ים ነው።
አሏህ በአረማይክ አሁንም "አሏህ" ܐܲܠܵܗܵܐ
ሲሆን ከውስጡ "ኤላህ"ܐܠܗܐ ማለትም "አምላክ" የሚል ቃል አለ፤ ዋቢ መጽሐፍት፦
➊ . Bergsträsser, Gotthelf. 1995. Introduction to the Semitic Languages: Text Specimens and Grammatical Sketches.
➋. Fitzmyer, J. (1997), The Semitic Background of the New Testament, Eerdmans Publishing.
➌. Bennett, Patrick R. 1998. Comparative Semitic Linguistics:
➍. Moscati, Sabatino. 1969. An introduction to the comparative grammar of the Semitic languages: phonology and morphology.

እንግዲህ ኢየሱስ፣ ሔኖክ፣ ኖህ እና አብርሐም የሚጠቀሙበት ዘዬ አረማይክ ከነበረ እና ሌሎች የእስራኤል ነብያት የዕብራይስጥ ዘዬ ሲጠቀሙ ከነበረ "አሏህ" የሚለውን ስም መጠቀማቸው ግድ ይላል፤ ነገር ግን አሁን በዘመናችን የአላህ ጥንታዊ ነቢያት የተሰጣቸው ኪታባት የተዋቀረበት አንጓ፣ የተናገሩበት ቋንቋ፣ የመልዕክቱ ምጥቀት ሆነ የቃላቱ ልቀት በዘመናችን እንደሌሉ የታሪክ ምሁራን ያትታሉ፣ ለምሳሌ የእስራኤል ልጆች ውስጥ የነበሩት ነቢያት ሲናገሩበት የነበረው ቋንቋ ዕብራይስጥ ሲሆን እነርሱ የተናገሩበት መጽሐፍት የሉም፣ በጣም ቀደምትነት አለው የሚባለው የነቢያት መጽሐፍት ግልባጭ በግሪክ ሰፕቱአጀንት የተዘጋጀው ሲሆን ከሰፕቱአጀንት በኋላ የተዘጋጁት የሙት ባህር ጥቅል፣ ማሶሬቲክ፣ ሰመሪያን ይህንኑ የግሪኩን መሰረት አድርገው ነው የተተረጎሙት፣ ከሰፕቱአጀንት በፊት የነበረው የነቢያት መጽሐፍት ዛሬ የለም፣ ከሌለ አላህ የሚለው ቃል ይጠቀሙ አይጠቀሙ ምንም ምንጭ የለም ማለት ነው፣ ወደ ኢየሱስም ስንመጣ ኢየሱስ ሲናገርበት የነበረ ቋንቋ አረማይክ ሲሆን ሃዋርያቱም ሲናገሩበት የነበረው ይህን ቋንቋ ነው፣ ነገር ግን ወደ ሁለተኛው ትውልድ ይህ የኢየሱስ ትምህርት ሲገባ የተጻፈው ኮይኔ በሚባል የግሪክ ቋንቋ ነው፣ ስለዚህ ነቢያት አምላካቸውን ማን ብለው እንደነበር የሚያሳይ የቋንቋ መረጃ በዛሬ ጊዜ የለም። አላህ የሚለውን ስም ነቢያቶች ተናግረውት አያውቁም የሚለው አሉባልታ ምንጭ አልባና ሰነድ አልባ ነው፣ ይህን ደፍሮ ለመናገር ስረ-መስረት ያለው አንጓ፣ ቋንቋ፣ ምጥቀት ሆነ ልቀት ያስፈልጋል፣ በተረፈ ""እግዚአብሔር፣ ቴኦስ፣ ጋድ፣ ጉድ"" የሚሉት ቃላት ባዕደ-ቃላት እና ኢላህ ለሚለው ቃል ትርጉም ናቸው እንጂ አሏህ ለሚለው ቃል ትርጉም አይደሉም።
ነጥብ ሁለት
"አሏህና ነብያቱ"
አላህ ጥንት ነቢያቶች የሚያመልኩት የነቢያት አምላክ መሆኑን የምናውቀው ከጥንቶቹ ነቢያት ጋር የነበረውን መስተጋብር ለመግለጽ፦
"ቁልና" قُلْنَا *አልን* ፣
"አርሰልና" أَرْسَلْنَا*ላክን*፣
"አውሃይና" أَوْحَيْنَا *አወረድን*
በማለት ጥንትም ነቢያትን ሲልክ የነበረው፣ ግልጠተ-መለኮት*Revelation* ሲያወርድ የነበረውና በተለያየ መንገድ ሲያናግራቸው የነበረው እርሱ መሆኑን ይገልጻል፦

❶. አልን፦
20:116 ለመላእክትም፣ ለአዳም ስገዱ፣ *ባልን* ጊዜ አስታውስ፤
2:35 «አደም ሆይ! አንተ ከነሚስትህ በገነት ተቀመጥ፤ ከርሷም በፈለጋችሁት ስፍራ በሰፊው ተመገቡ፤ ግን ይህችን ዛፍ አትቅረቡ፤ ከበደለኞች ትኾናላችሁና» *አልንም*፡፡
11:40 ትእዛዛችንም በመጣና እቶኑም በገነፈለ ጊዜ፣ በርሷ ውስጥ ከየዓይነቱ ሁሉ ሁለት ሁለት፣ ወንድና ሴት ቤተሰቦችህንም ቃል ያለፈበት ብቻ ሲቀር ያመነንም ሰው ሁሉ ጫን *አልነው*፤
22:26 ለኢብራሂምም የቤቱን ስፍራ መመለሻ ባደረግንለት ጊዜ፣ በኔ ምንንም አታጋራ፤ ቤቴንም፣ ለሚዞሩትና ለሚቆሙበት፣ ለሚያጎነብሱትና በግንባራቸውም ለሚደፉት ንጹሕ አድርግላቸው፣ *ባልነው* ጊዜ አስታውስ።
2:125 ወደ ኢብራሂምና ወደ ኢስማዒልም ቤቴን ለዘዋሪዎቹና ለተቀማጮቹም ለአጎንባሾች ሰጋጆቹም አጥሩ *ስንል* ቃል ኪዳን ያዝን፡፡
2:60 ሙሳም ለሕዝቦቹ መጠጥን በፈለገ ጊዜ የኾነውን አስታውሱ፡፡ «ድንጋዩንም በበትርህ ምታ» *አልነው*፡፡
17:2 ሙሳንም መጽሐፉን ሰጠነው፤ ለእስራኤልም ልጆች መሪ አደረግነው፤ ከኔ ሌላ መጠጊያን አትያዙ *አልናቸውም*።

❷. ላክን፦
16:36 በየሕዝቡም ሁሉ ውስጥ አላህን ተገዙ፤ ጣዖትንም ራቁ፤ በማለት መልክተኛን በእርግጥ *ልከናል*፤
57:25 መልክተኞቻችንን በግልጽ ማስረጃዎች በእርግጥ *ላክን*፤
23:32 በውስጣቸውም ከእነሱ የኾነን መልክተኛ አላህን ተገዙ ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የላችሁም አትጠነቀቁምን በማለት *ላክን*፡፡
7:59 ኑሕን ወደ ወገኖቹ በእርግጥ ላክነው፤
11:50 ወደ ዓድም ወንድማቸውን ሁድን ላክን፤
11:61 ወደ ሠሙዶችም ወንድማቸውን ሷሊህን ላክን፤
11:84 ወደ መድየንም ወንድማችውን ሹዐይብን፣ ላክን፤

❸. አወረድን፦
4:163 እኛ ወደ ኑሕና ከርሱ በኋላ ወደ ነበሩት ነቢያት *እንዳወረድን*፣ ወደ አንተም *አወረድን*፤ ወደ ኢብራሂምም፣ ወደ ኢስማዒልም፣ ወደ ኢስሐቅም፣ ወደ ያዕቆብም፣ ወደ ነገዶቹም ወደ ዒሳም፣ ወደ አዮብም፣ ወደ ዩኑስም፣ ወደ ሀሩንና ወደ ሱለይማንም *አወረድን*፤ ለዳዉድም ዘቡርን ሰጠነው።
21:25 ከአንተ በፊትም፣ እነሆ ከኔ ሌላ አምላክ የለምና ተገዙኝ፣ በማለት ወደርሱ *የምናወርድለት* ቢሆን እንጅ ከመልክተኛ አንድንም አልላክንም።
12:109 ካንተ በፊትም ከከተሞች ሰዎች ወደ እነርሱ ራዕይ *የምናወርድላቸው* የሆኑን ወንዶችን እንጂ አልላክንም፤
21:7 ከአንተም በፊት ወደ እነርሱ *የምናወርድላቸው* የኾኑ ሰዎችን እንጂ ሌላን አልላክንም፤
16:43 ከአንተም በፊት ወደ እነርሱ ወሕይን *የምናወርድላቸውን* ሰዎችን እንጂ፣ ሌላን አልላክንም፤

አላህ የነቢያት አምላክ ነው፤ ኑሕ፣ ሁድ፣ ሷሊህ፣ ኢብራሒም፣ ሹዐይብ፣ ሙሳ እና ኢሳ አላህ እያሉ ይጠቀሙ እንደነበር ቃሉ ይነግረናል፦
16:36 በየሕዝቡም ሁሉ ውስጥ "አላህን" አምልኩ፤ ጣዖትንም ራቁ፤ በማለት መልክተኛን በእርግጥ ልከናል፤

"ኑሕ"
11:25-26 ኑሕንም ወደ ሕዝቦቹ በእርግጥ ላክን፤ አላቸውም ፦ እኔ ለናንተ ግልጽ አስፈራሪ ነኝ። አላህን እንጂ ሌላን አትገዙ፤ እኔ በናንተ ላይ የአሳማሚን ቀን ቅጣት እፈራላችኋለሁና።

"ሁድ"
11:50 ወደ ዓድም ወንድማቸውን ሁድን ላክን አላቸው ፦ ወገኖቼ ሆይ አላህን ተገዙ ከእርሱ ሌላ ምንም አምላክ የላችሁም፤ እናንተም ቀጣፊዎች እንጂ ሌላ አይደላችሁም።

"ሷሊህ"
11:61 ወደ ሠሙዶችም ወንድማቸውን ሷሊህን ላክን፤ ፦ሕዝቦቼ ሆይ አላህን ተገዙ፤ ከርሱ ሌላ ለናንተ አምላክ፣ የላችሁም፤ .. አላቸው።

"ኢብራሒም"
19:48 እናንተንም ከአላህ ሌላ የምትግዙትንም እርቃለሁ፤ ጌታየንም እግዛለሁ፤ ጌታየን በመገዛት የማፍር አለመኾኔን እከጅላለሁ።

"ሹዐይብ"
11:84 ወደ መድየንም ወንድማችውን ሹዐይብን፣ ላክን፤ አላቸው ሕዝቦቼ ሆይ! አላህን ተገዙ፤ ከርሱ ሌላ ለናንተ አምላክ የላችሁም፤ ስፍርንና ሚዛንንም አታጉድሉ፤ እኔ በጸጋ ላይ ሆናችሁ አያችኋለሁ፤ እኔም በናንተ ላይ የከባቢን ቀን ቅጣት እፈራለሁ።

"ሙሳ"
7:104-105 ሙሳም አለ፦ፈርኦን ሆይ! እኔ ከዓለማት ጌታ የተላክሁ መልክተኛ ነኝ፤ በአላህ ላይ ከእውነት በቀር አለመናገር ተገቢዬ ነው፤ ከጌታችሁ በታምር በእርግጥ መጣኋችሁ፤ የእስራኤልንም ልጆች ከኔ ጋር ልቀቅ።

ኢሳ"
3:51 አላህ ጌታየና ጌታችሁ ነዉ፤ ስለዚህ ተገዙት፤ ይህ ቀጥተኛ መንገድ ነዉ አላቸዉ።

ነጥብ ሶስት
"አሏህና ታሪካዊ ፍሰት"
አሏህ የሚለው ስም ነብያችን ነብይ ሆነ ከመላካቸው በፊትና ቁርአን ከመውረዱ በፊት በሴመቲክ ዳራ ደግሞ ከሁሉ በላይ የሆነው አንዱ አምላክ ሲጠራበት የነበረ ስም እንደነበር የተለያየ መድብለ-እውቀቶች*Encycolopedias* ሆኑ ታሪካዊ ፍሰቶች ያትታሉ፦
❶. የሃይማኖት መድብለ-እውቀት 1987: “አላህ የሚለው ስም ስረ-መሰረት የጋራ በሆኑ በተለያዩ ጥንታዊ የሴም ቋንቋዎች ይገኛል” ገጽ 27.
Encycolopedia of religion 1987: “the orgin of Allah is found in a root common to various ancient semetic languages” p27.
❷. የክርስትና መድብለ-እውቀት 2001: “ ቅድመ-ቁርአን አረብ ተናጋሪ ክርስቲአንና አይሁድ እንዲሁ አላህ ለታላቁ አምላክ ይጠቀሙበት ነበር” ገጽ 101.
Encyclopedia of Christianity 2001: “before Quran Arabic-speaking Christians and Jews also refer to supreme God as Allāh” page 101.
❸. የኢስላም መድብለ-እውቀት 1913: “አረቦች ቅድመ-ነቢዩ ሙሃመድ በነበሩት ዘመናት አላህ የሚባል ታላቅ አምላክ ያመልኩ ነበር” ገጽ 302.
Encyclopedia of Islam 1913: “Before prophet Muhammad Arabian was worshiping supreme God who is Allah” page 302.
❹. የብሪታኒካ መድብለ-እውቀት 1996: “ቅድመ-ቁርአን በነበሩት አረቢያን መጽሐፍት ውስጥ አላህ የሚለው ቃል ይገኛል” ገጽ 106.
Encyclopedia of britannica 1996: “Before Quran The word Allah was in the Arabic books” page 106.

ከነዚህ ምሁራዊና እውቀታዊ መረጃ ተነስተን የምንደመድመው ነገር ቢኖር አላህ የሚለው ስም ነቢያችን የገለጡት አሊያም ቁርአን የገለጠው ስም ብቻ ሳይሆን ስረ-መሰረቱ ቀዳማይ መሆኑን ነው፣ የትኛውም ምሁራዊና እውቀታዊ መረጃ አላህ የጣኦት ስም ነው ብሎ ያሰፈረ የለም፣ አለ የሚል ሰው ካለ ተግዳሮትና ጋሬጣ ሆኖ መቅረብ ይችላል። ቁሬሾች አላህ የሁሉ ነገር ፈጣሪ ነው ብለው ያምናሉ እንጂ ከጣኦቶቻቸው መካከል አንዱ ጣኦት ነበር የሚል የቡና ዲቃላ ወሬ የላቸውም፦
31:25 ሰማያትንና ምድርንም የፈጠረ ማን እንደኾነ ብትጠይቃቸው በእርግጥ አላህ ነው ይላሉ፤ ምስጋና ለአላህ ይገባው፣ በላቸው፤ ይልቁንም አብዛኞቹ አያውቁም።
29:61 ሰማያትንና ምድርን የፈጠረ ፀሐይንና ጨረቃንም የገራ ማን እንደሆነ ብትጠይቃቸው በእርግጥ አላህ ነው ይሉሃል፤ ታዲያ እንዴት ይመለሳሉ።
10:31 «ከሰማይና ከምድር ሲሳይን የሚሰጣችሁ ማን ነው መስሚያዎችንና ማያዎችንስ የፈጠረ ማን ነው ከሙትም ሕያውን የሚያወጣ ከሕያውም ሙትን የሚያወጣስ ማን ነው ነገሩን ሁሉ የሚያስተናብርስ ማን ነው» በላቸው፡፡ «በእርግጥም አላህ ነው» ይሉሃል፡፡ «ታዲያ ለምን ታጋራላችሁ አትፈሩትምን» በላቸው፡፡
43:87 ማን እንደፈጠራቸው ብትጠይቃቸው፣ በእርግጥ አላህ ነው፣ ይላሉ።ታዲያ ከእምነት ወዴት ይዞራሉ።
39:38 ሰማያትንና ምድርን የፈጠረ ማን እንደ ሆነ ብትጠይቃቸው አላህ ነው፣ ይሉሃል።
29:63 ከሰማይም ውሃን ያወረደና በርሱም ምድርን ከሞተች በኋላ ሕያው ያደርጋት ማን እንደ ሆነ ብትጠይቃቸው አላህ ነው፣ይሉሃል።
23:84-89 «ምድርና በውስጥዋ ያለው ሁሉ የማን ነው የምታውቁ ብትኾኑ ንገሩኝ» በላቸው፡፡ «በእርግጥ የአላህ ነው» ይሉሃል፡፡ «ታዲያ አትገሰጹምን» በላቸው፡፡«የሰባቱ ሰማያት ጌታና የታላቁ ዐርሽ ጌታ ማን ነው» በላቸው፡፡ «በእርግጥ አላህ ነው» ይሉሃል፡፡ «እንግዲያ አትፈሩትምን» በላቸው፡፡ «የነገሩ ሁሉ ግዛት በእጁ የኾነ እርሱ የሚጠብቅ በእርሱ ላይ የማይጠበቅ ማን ነው የምታውቁ እንደኾናችሁ መልሱልኝ» በላቸው፡፡ «በእርግጥ አላህ ነው» ይሉሃል፡፡ «ታዲያ እንዴት ትታለላላችሁ» በላቸው፡፡

ማጠቃለያ
አላህ ህያው የሆነ ሁሉን የሚያውቅ፣ የሚያይ፣ የሚሰማ እና በእኔነት የሚናገር አምላክ ነው፦

❶. ሁሉን የሚያውቅ ነው፦
60:1 #እኔ የምትደብቁትንና የምትገልጹትን #የማውቅ ስሆን ወደ እነርሱ በፍቅር ትመሣጠራላችሁ፤

❷. ሁሉ ተመልካች ነው፦
34:11 #እኔ የምትሠሩትን ነገር ሁሉ ተመልካች ነኝና።

❸. ሁሉን የሚሰማ ነው፦
2:186 ባሮቼም ከእኔ በጠየቁህ ጊዜ፡- እኔ ቅርብ ነኝ፡፡ የለማኝን ጸሎት በለመነኝ ጊዜ #እቀበለዋለሁ፡፡ ስለዚህ ለኔ ይታዘዙ፤ በእኔም ይመኑ፤ እነርሱ ሊመሩ ይከጀላልና፡፡

❹. እኔነት ያለው ተናጋሪ ነው፦
21:92 “#እኔም” ጌታችሁ #ነኝ እና “አምልኩኝ”።
2:160 እነዚህም በእነርሱ ላይ ጸጸታቸውን እቀበላለሁ፤ #እኔም ጸጸትን በጣም ተቀባይ አዛኙ #ነኝ፡፡

ኡሥታዝ ወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም

FACEBOOK ፦ጥሪያችን Tiriyachen
https://www.facebook.com/tiriyachen

ወሰላሙ አለይኩም
የዘካህ አወጣጥ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

2፥110 ሶላትንም አስተካክላችሁ ስገዱ፡፡ ዘካንም ስጡ፡፡ وَأَقِيمُوا الصَّلَاةَ وَآتُوا الزَّكَاةَ

የዘካ ገንዘብ ከተቀማጭ ላይ ከመቶ 2.5 % የሚሰጥ ነው፥ ነቢያችን”ﷺ” ከሁለት መቶ ዲርሀም 5 ዘካህ እንደሚወጣ ተናግረዋል። ያ ማለት የዘካህ ሒሳብ በመቶ ዲርሀም 2.5 ይሆናል፥ ስሌቱ 5፥2=2.5 ነው፦
ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 9, ሐዲስ 18 ዐሊይ”ረ.ዐ” እንደተረከው፦ “ነቢዩም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ ”ሁለት መቶ ዲርሀም ለአንተ በሆነች ጊዜና ዓመት ከሞላች አምስት ደራሂም ይወጣል፥ በአንተ ምንም ነገር አይሆንም ሃያ ዲናር እስኪሆን ድረስ”። عَنْ عَلِيٍّ، – رضى الله عنه – عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم بِبَعْضِ أَوَّلِ هَذَا الْحَدِيثِ قَالَ ‏”‏ فَإِذَا كَانَتْ لَكَ مِائَتَا دِرْهَمٍ وَحَالَ عَلَيْهَا الْحَوْلُ فَفِيهَا خَمْسَةُ دَرَاهِمَ وَلَيْسَ عَلَيْكَ شَىْءٌ – يَعْنِي فِي الذَّهَبِ – حَتَّى يَكُونَ لَكَ عِشْرُونَ دِينَارًا

በዚህ ሐዲስ መሠረት የአንድ ሰው ካፒታል 20 ዲናር ወይም 200 ዲርሀም ሲሆን ዘካህ ይወጅበታል። በሸሪዓህ የዘካህ አነስተኛ የክፍያ መጠን “ኒሷብ” نِصاب ይባላል፥ ይህም ኒሷብ የሚለካው 20 ዲናር ወይም 200 ዲርሀም ሲሆን ነው። “ዲናር” دِينَار‎ ማለት “የወርቅ ሳንቲም”gold coin” ማለት ሲሆን “ዲርሀም” دِرْهَم‎ ማለት ደግሞ “የብር ሳንቲም”silver coin” ማለት ነው። ይህ በጥንት ጊዜ የሸቀጥ ገንዘብ”commodity money” ነው። “ዲናር” እና “ዲርሀም” የሚለኩት በሚስቃል ነው፥ “ሚስቃል” مِثْقَال የሚለው ቃል “ሰቀለ” ثَقَلَ ማለትም “ከበደ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ክብደት” ማለት ነው።
1 ሚስቃል ወርቅ 4.25 ግራም ነው፥ 20 ሚስቃል ወርቅ ደግሞ 4,25x 20 = 85 ግራም ወርቅ ይሆናል ማለት ነው።
1 ሚስቃል ብር 2.975 ግራም ነው፥ 200 ሚስቃል ብር ደግሞ 2.975x 200= 595 ግራም ብር ይሆናል ማለት ነው።

በዘካህ ላይ የሚወጅበው ኒሷብ 85 ግራም ወርቅ ወይም 595 ግራም ብር ነው።
አንድ ሙሥሊም ያስቀመጠው ካፒታል ዓመት ከሞላው እና ያም ካፒታል 85 ግራም ወርቅ ወይም 595 ግራም ብር ያክል ከሆነ ዘካህ ማውጣት ግዴታው ነው።
ዘካቱል ማል የሚወጣበት አነስተኛ ዋጋ የብር ኒሷብ ስለሆነ አብላጫው ምሁራን የብር ኒሷብን መሠረት ባደረገ መልኩ ከዚያ እንዲወጣ ፈትዋ ሰተዋል፥ ስለዚህ አንድ ሰው ዓመት የተቀመጠ 148,750 ብር(ገንዘብ) እና ከዛ በላይ ካለው ዘካህ ማውጣት ግዴታ አለበት።

እንዴት? ካላችሁ የብር ኒሷብ ወደ ወረቀት ገንዘብ”Fiat money” ለመቀየር ብርን ዛሬ ባለው የወቅቱ ግብይት ለናሙና ያክል መሥራት ይቻላል። በኢትዮጵያ አንድ ግራም ብር"silver" አሁን ባለኝ መረጃ 250 ብር"ገንዘብ" ነው፥ ስናሰላው 250×595= 148,750 ብር(ገንዘብ) ይሆናል።
ለምሳሌ፦ እኔ 200 ሺህ ብር ቢኖረኝ ከ 200 ሺህ ብር ላይ 2.5 % ዘካህ ሲሰላ 5,000 ይወጅብብኛል፥ ስናሰላው 200,000×2.5፥100= 5,000 ይሆናል። ስለዚህ ዓመት የሞላው 148,750 ብር እና ከዛ በላይ ዘካህ ማውጣት ስለሚወጅብ ዘካህን መስጠት አንርሳ፦
2፥110 ሶላትንም አስተካክላችሁ ስገዱ፡፡ ዘካንም ስጡ፡፡ وَأَقِيمُوا الصَّلَاةَ وَآتُوا الزَّكَاةَ

አምላካችን አሏህ ዘካን ከሚሰጡ ባሮቹ ያድርገን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
ጥሪያችን Tiriyachen
FACEBOOK ፦ጥሪያችን Tiriyachen
https://www.facebook.com/tiriyachen

ወሠላሙ ዐለይኩም
እውነቱን በውሸት ለምን ትቀላቅላላችሁ?

ክፍል አንድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡

«የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! እውነቱን በውሸት ለምን ትቀላቅላላችሁ እውነቱንም እናንተ የምታውቁ ስትኾኑ ለምን ትደብቃላችሁ»

ቅጥፈት አንድ
የሐዋርያት ሥራ 7:15-16 ያዕቆብም ወደ ግብፅ ወረደ እርሱም ሞተ "አባቶቻችንም"፤ ወደ ሴኬምም አፍልሰው #አብርሃም #ከሴኬም #አባት #ከኤሞር ልጆች #በብር በገዛው መቃብር "ቀበሩአቸው"።

በአብርሃምና በሴኬም መካከል የትውልድ ልዩነት አለ፤ ሴኬም ይቅርና የሴኬም አባት ኤሞር የነበረው በአብርሃም ጊዜ ሳይሆን የአብርሃም የልጅ ልጅ በሆነው በያዕቆብ ጊዜ ነው፦
ዘፍጥረት 34:4-6 #ሴኬምም አባቱን #ኤሞርን ይህችን ብላቴና አጋባኝ ብሎ ነገረው። #ያዕቆብም ልጁን ዲናን እንዳስነወራት ሰማ፤ ልጆቹም ከከብቶቻቸው ጋር በምድረ በዳ ነበሩ፤ ያዕቆብም እስኪመጡ ድረስ ዝም አለ። #የሴኬም #አባት #ኤሞርም ይነግረው ዘንድ ወደ #ያዕቆብ ወጣ።

ልብ በሉ ሴኬም የያዕቆብን ልጅ ዲናን ሲያስነውር ማለት ሲደፍራት አይደለም አብርሃም አያቱ ይቅርና አባቱ ይስሐቅ ሞቷል፤ ታዲያ አብርሃም ከሴኬም አባት ከኤሞር ልጆች በብር መቃብር የገዛው መቼ ነው? ይህ እልም ያለ ቅጥፈት ነው፤ ታዲያ ማን ነው መቃብሩን ከሴኬም አባት ከኤሞር ልጆች የገዛው? ስንል የዘፍጥረት ዘጋቢ ያዕቆብ ነው ይለናል፦ ዘፍጥረት 33:18-19 #ያዕቆብም ከሁለት ወንዞች መካከል በተመለሰ ጊዜ በከነዓን ምድር ወዳለችው ወደ #ሴኬም ከተማ በደኅንነት መጣ፤ በከተማይቱም ፊት ሰፈረ። ድንኳኑን ተክሎበት የነበረውንም የእርሻውን ክፍል #ከሴኬም #አባት #ከኤሞር #ልጆች #በመቶ #በጎች ገዛው።

ውሸት ሁሌም ውሸት ነው፤ ልብ በሉ አብርሃም በህይወት ሳይኖር ያልገዛውን ገዛ ማለቱ ሲገርመን አብርሃም ገዛ የተባለው #በብር ሲሆን ያዕቆብ ግን #በመቶ #በጎች ነው፦
ኢያሱ 24:32 የእስራኤልም ልጆች ከግብፅ ያወጡትን የዮሴፍን አጥንት #ያዕቆብ #ከሴኬም #አባት #ከኤሞር ልጆች #በመቶ #በግ በገዛው #እርሻ በሴኬም ቀበሩት፤ እርሻውም ለዮሴፍ ልጆች ርስት ሆነ።

የሐዋርያት ሥራ ጸሐፊ ሉቃስ ወይም እስጢፋኖስ አሊያም የግሪክ እደ-ክታባትን ገልባጮች ቀጥፈዋል፤ አብርሃም በእርግጥም የመቃብር ስፍራ ገዝቷል የገዛው ከሴኬም አባት ከኤሞር ልጆች ሳይሆን ከኬጢያዊ ከኤፍሮን እርሻ ላይ ነው፤ የገዛውም በመቶ በግ ሳይሆን #በአራት #መቶ #ሰቅል ነው፦
ዘፍጥረት 23፥16-17 #አብርሃምም* የኤፍሮንን ነገር ሰማ አብርሃምም በኬጢ ልጆች ፊት የነገረውን #አራት #መቶ #ሰቅል መዝኖ #ለኤፍሮን ሰጠው ብሩም ለመሸጫ ለመለወጫ የሚተላለፍ ነበረ። በመምሬ ፊት ያለው ባለድርብ ክፍል የሆነው የኤፍሮን እርሻ ለአብርሃም ጸና።
ዘፍጥረት 49፥29-30 እንዲህ ብሎም አዘዛቸው። እኔ ወደ ወገኖቼ እሰበሰባለሁ በኬጢያዊ በኤፍሮን እርሻ ላይ ባለችው ዋሻ ከአባቶቼ ጋር ቅበሩኝ፤ እርስዋም በከነዓን ምድር በመምሬ ፊት ያለች፥ #አብርሃም ለመቃብር ርስት #ከኬጢያዊ #ከኤፍሮን ከእርሻው ጋር የገዛት፥ ባለ ድርብ ክፍል ዋሻ ናት።

ቅጥፈትን በጋራ እንከላከል፤ ኢንሻላህ ይቀጥላል......

✍🏻ኡሥታዝ ወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም
የበለጠ ለማወቅ
Follow us on:
https://fb.me/tiriyachen
https://www.tg-me.com/tiriyachen
https://tiriyachen.org
https://bit.ly/3eVixKv
https://www.tiktok.com/@tiriyachen

ወሰላሙ አለይኩም
የሙሐመድ"ﷺ" ሸፋዓ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

17፥79 ከሌሊትም ላንተ ተጨማሪ የኾነችን ሶላት በእርሱ በቁርኣን ስገድ፡፡ *ጌታህ ምስጉን በኾነ ስፍራ በእርግጥ ያቆምሃል*፡፡ وَمِنَ اللَّيْلِ فَتَهَجَّدْ بِهِ نَافِلَةً لَّكَ عَسَىٰ أَن يَبْعَثَكَ رَبُّكَ مَقَامًا مَّحْمُودًا

“ሐምድ” حَمْد ማለት “ሐመደ” حَمَّدَ ማለት “አመሰገነ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ምስጋና” ማለት ነው፤ ሐምድ የአምልኮ አይነት ነው፤ በቁርኣን ውስጥ ከተዋቡ የአላህ ስሞች አንዱ “አል-ሐሚድ” الْحَمِيد ሲሆን “እጅግ በጣም የተመሰገነ” ማለት ነው፦
31፥26 በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የአላህ ነው፡፡ *አላህ እርሱ ተብቃቂ ምስጉን ነው*፡፡ لِلَّهِ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۚ إِنَّ اللَّهَ هُوَ الْغَنِيُّ الْحَمِيدُ

አላህ አምላኪዎች “ሓሚዱን” حَٰمِدُون ማለትም “አመስጋኞች” ይባላሉ፦
9፥112 እነርሱ ተጸጻቺዎች፣ ተገዢዎች፣ *”አመስጋኞች”*፣ ጿሚዎች፣ አጎንባሾች፣ በግንባር ተደፊዎች፣ በበጎ ሥራ አዛዦች ከክፉም ከልካዮች፣ የአላህንም ሕግጋት ጠባቂዎች ናቸው ምእምናንንም አብስር፡፡ التَّائِبُونَ الْعَابِدُونَ الْحَامِدُونَ السَّائِحُونَ الرَّاكِعُونَ السَّاجِدُونَ الْآمِرُونَ بِالْمَعْرُوفِ وَالنَّاهُونَ عَنِ الْمُنكَرِ وَالْحَافِظُونَ لِحُدُودِ اللَّهِ ۗ وَبَشِّرِ الْمُؤْمِنِين

ነቢያችን”ﷺ” ደግሞ “ሙሐመድ” مُحَمَّ በሚል ስም አራት ጊዜ በቁርኣን ተዘክረዋል፤ የስማቸውም ትርጉም “ምስጉኑ” ማለት ነው፦
3፥144 *ሙሐመድም ከበፊቱ መልክተኞች በእርግጥ ያለፉ የኾነ መልክተኛ እንጅ ሌላ አይደለም*፡፡ وَمَا مُحَمَّدٌ إِلَّا رَسُولٌ قَدْ خَلَتْ مِن قَبْلِهِ الرُّسُل
33፥40 *ሙሐመድ ከወንዶቻችሁ የአንድም ሰው አባት አይደለም፡፡ ግን የአላህ መልክተኛና የነቢዮች መደምደሚያ ነው*፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡ مَّا كَانَ مُحَمَّدٌ أَبَا أَحَدٍ مِّن رِّجَالِكُمْ وَلَـٰكِن رَّسُولَ اللَّهِ وَخَاتَمَ النَّبِيِّينَ ۗ وَكَانَ اللَّهُ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمًا
47፥2 እነዚያም ያመኑ፣ በጎዎችንም የሠሩ፣ *በሙሐመድ ላይም የወረደው እርሱ ከጌታቸው ሲኾን እውነት ስለ ኾነ ያመኑ ከእነርሱ ላይ ኃጢአቶቻቸውን ያባብሳል*፡፡ ኹኔታቸውንም ሁሉ ያበጃል፡፡ وَالَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ وَآمَنُوا بِمَا نُزِّلَ عَلَىٰ مُحَمَّدٍ وَهُوَ الْحَقُّ مِن رَّبِّهِمْ ۙ كَفَّرَ عَنْهُمْ سَيِّئَاتِهِمْ وَأَصْلَحَ بَالَهُمْ
48፥29 *የአላህ መልክተኛ ሙሐመድ እነዚያም ከእርሱ ጋር ያሉት ወዳጆቹ በከሓዲዎቹ ላይ ብርቱዎች በመካከላቸው አዛኞች ናቸው*፡፡ مُّحَمَّدٌ رَّسُولُ اللَّهِ ۚ وَالَّذِينَ مَعَهُ أَشِدَّاءُ عَلَى الْكُفَّارِ رُحَمَاءُ بَيْنَهُمْ

“አሕመድ” أَحْمَد የሚለው ቃል የሙሐመድ ተለዋዋጭ ቃል ሲሆን ትርጉሙ “ተመስጋይ” ማለት ነው፤ ይህም ስም በቁርኣን አንድ ጊዜ ተወስቷል፦
61፥6 የመርየም ልጅ ዒሳም፡- «የእስራኤል ልጆች ሆይ! እኔ ከተውራት በፊቴ ያለውን የማረጋግጥና *ከእኔ በኋላ በሚመጣው መልክተኛ ስሙ አሕመድ በኾነው የማበስር ስኾን ወደ እናንተ የተላክሁ የአላህ መልክተኛ ነኝ» ባለ ጊዜ አስታውስ*፡፡ በግልጽ ተዓምራቶች በመጣቸውም ጊዜ «ይህ ግልጽ ድግምት ነው» አሉ፡፡ وَإِذْ قَالَ عِيسَى ابْنُ مَرْيَمَ يَا بَنِي إِسْرَائِيلَ إِنِّي رَسُولُ اللَّهِ إِلَيْكُم مُّصَدِّقًا لِّمَا بَيْنَ يَدَيَّ مِنَ التَّوْرَاةِ وَمُبَشِّرًا بِرَسُولٍ يَأْتِي مِن بَعْدِي اسْمُهُ أَحْمَدُ ۖ فَلَمَّا جَاءَهُم بِالْبَيِّنَاتِ قَالُوا هَـٰذَا سِحْرٌ مُّبِينٌ
ኢማም ሙስሊም መጽሐፍ 43, ሐዲስ 163
ኢብኑ ጁበይር ከአባቱ አግኝቶ እንደተረከው፤ ነቢዩም”ﷺ” አሉ፦ *“እኔ ሙሐመድ ነኝ፣ “እኔ አሕመድ ነኝ”፣ እኔ ማሒ ማለትም ያ ከሃዲ ሲያጠፋ የምገስጽ ነኝ፣ እኔ ሰዎች በሚሰበሰቡት ጊዜ ሐሺር(ሰብሳቢ) ነኝ፣ ከዚህ በኃላ ነቢይ የለም፤ እኔ ዓቂብ(መጨረሻ) ነኝ*። بْنَ جُبَيْرِ بْنِ مُطْعِمٍ عَنْ أَبِيهِ، أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ” أَنَا مُحَمَّدٌ وَأَنَا أَحْمَدُ وَأَنَا الْمَاحِي الَّذِي يُمْحَى بِيَ الْكُفْرُ وَأَنَا الْحَاشِرُ الَّذِي يُحْشَرُ النَّاسُ عَلَى عَقِبِي وَأَنَا الْعَاقِبُ ” . وَالْعَاقِبُ الَّذِي لَيْسَ بَعْدَهُ نَبِيُّ .

በታሪክ ላይ ሙሐመድ”ﷺ” በሚል ስም የተጠራ ከእርሳቸው በፊት ማንም ፍጡር የለም። ይህንን ስም ኢብኑ ሠዐድ ባዘጋጀው ሲራህ “ኪታብ ጠበቃተል ኩብራህ መጽሐፍ 1″ ላይ መልአኩ ጂብሪል ለእናታቸው ለአሚናህ በህልም ያወጣው ስም ነው።
አንዳንድ ኀያሲ አላህ ምስጉን ተብሏልና ለነቢያችን”ﷺ” “ምስጉን” መባሉ ማሻረክ አይሆንም ወይ? የሚል ጥያቄ ያነሳሉ፤ ሲጀመር አላህ ምስጉን የተባለበት ቃል “አል-ሐሚድ” الْحَمِيد እንጂ “ሙሐመድ” مُحَمَّ አይደለም፤ ሲቀጥል አላህ ምስጉን የተባለው ፍጡራን ስለሚያመልኩት ነው፤ ነቢያችን”ﷺ” ምስጉን የተባሉበት ግን አላህ ስላከበራቸው ነው፤ ሢሰልስ ኢብራሂም እና ቀጥተኛው መንገድ “ምስጉን” ተብለዋል፦
11፥73 «ከአላህ ትዕዛዝ ትደነቂያለሽን የአላህ ችሮታና በረከቶቹ በእናንተ በኢብራሂም ቤተሰቦች ላይ ይሁን *እርሱ ምስጉን ለጋስ ነውና*» አሉ፡፡ قَالُوا أَتَعْجَبِينَ مِنْ أَمْرِ اللَّهِ ۖ رَحْمَتُ اللَّهِ وَبَرَكَاتُهُ عَلَيْكُمْ أَهْلَ الْبَيْتِ ۚ إِنَّهُ حَمِيدٌ مَّجِيدٌ
22፥24 ከንግግርም ወደ መልካሙ ተመሩ፡፡ *ወደ ምስጉንም መንገድ ተመሩ*፡፡ وَهُدُوا إِلَى الطَّيِّبِ مِنَ الْقَوْلِ وَهُدُوا إِلَىٰ صِرَاطِ الْحَمِيدِ

እንግዲህ ኢብራሂም እና ቀጥተኛው መንገድ “ምስጉን” ከተባሉ ነቢያችን”ﷺ” “ምስጉኑ” ወይም “ተመስጋኙ” መባላቸው አያስደንቅም፤ አይ “ምስጉን” የሚለው ቃል “መሽኩር” مَّشْكُور በሚል ቀመር እና ስሌት እንረዳዋለን ካላችሁ እንግዲያውስ ከላይ ያለውን በዚህ ሒሳብ ተረዱት። እንኳን ነቢያችን”ﷺ” በትንሳኤ ቀን የሚቆሙበት ስፍራ “መሕሙድ” ተብሏል፤ “መሕሙድ” مَّحْمُود ማለት “ምስጉን” ማለት ሲሆን ለስፍራ ገላጭ ሆኖ የመጣ ቃል ነው፦
17፥79 ከሌሊትም ላንተ ተጨማሪ የኾነችን ሶላት በእርሱ በቁርኣን ስገድ፡፡ *ጌታህ ምስጉን በኾነ ስፍራ በእርግጥ ያቆምሃል*፡፡ وَمِنَ اللَّيْلِ فَتَهَجَّدْ بِهِ نَافِلَةً لَّكَ عَسَىٰ أَن يَبْعَثَكَ رَبُّكَ مَقَامًا مَّحْمُودًا
ጃምዒ አት-ተርሚዚ መጽሐፍ 47, ሐዲስ 3430
አቢ ሁረይራ እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” አሉ፦ *”አላህ በቃሉ፦ “ጌታህ ምስጉን በኾነ ስፍራ በእርግጥ ያቆምሃል”። ስለዚህ አንቀጽ ተጠይቀው “ይህ ሸፋዓ ነው” ብለው መለሱ*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم فِي قَوْلِهِ ‏:‏ ‏(‏ عَسَى أَنْ يَبْعَثَكَ رَبُّكَ مَقَامًا مَحْمُودًا ‏)‏ سُئِلَ عَنْهَا قَالَ ‏”‏ هِيَ الشَّفَاعَةُ ‏

“ሸፋዓ” شَفَٰعَه ማለት “ምልጃ” ማለት ሲሆን የነቢያችን”ﷺ” ምልጃ በትንሳኤ ቀን የሚያገኘው ከልቡ ወይም ከነፍሱ፦ “ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም” ያለ ሰው ነው፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 3, ሐዲስ 41
አቢ ሁረይራ እንደተረከው፦ *”እኔም፦ የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” ሆይ! በትንሳኤ ቀን ማነው እድለኛ ሰው የእርስዎን ምልጃ የሚያገኘው? አልኩኝ፤ የአላህ መልእክተኛም”ﷺ”፦ “አቢ ሁረይራ ሆይ! ንግግር ለመማር የአንተን ቆይታ ዐውቃለው፤ እንደማስበው ስለዚህ ጉዳይ ከአንተ በፊት ማንም አልጠየቀኝም። በትንሳኤ ቀን የእኔን ምልጃ የሚያገኝ እድለኛ ሰው ከልቡ ወይም ከነፍሱ፦ “ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም” ያለ ነው*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، أَنَّهُ قَالَ قِيلَ يَا رَسُولَ اللَّهِ، مَنْ أَسْعَدُ النَّاسِ بِشَفَاعَتِكَ يَوْمَ الْقِيَامَةِ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ لَقَدْ ظَنَنْتُ يَا أَبَا هُرَيْرَةَ أَنْ لاَ يَسْأَلَنِي عَنْ هَذَا الْحَدِيثِ أَحَدٌ أَوَّلُ مِنْكَ، لِمَا رَأَيْتُ مِنْ حِرْصِكَ عَلَى الْحَدِيثِ، أَسْعَدُ النَّاسِ بِشَفَاعَتِي يَوْمَ الْقِيَامَةِ مَنْ قَالَ لاَ إِلَهَ إِلاَّ اللَّهُ، خَالِصًا مِنْ قَلْبِهِ أَوْ نَفْسِهِ ‏”‌‏.‏

በአላህ አምልኮ ላይ ሌላ ማንነትን እና ምንነት ያላሻረከ ነገር ግን ዐበይት ወንጀሎችን የሠራ በነቢያችን”ﷺ” ምልጃ ከጀሃነም ቅጣት ነጻ ወጥቶ ወደ ጀነት ይገባል፦
ጃምዒ አት-ተርሚዚ መጽሐፍ 37, ሐዲስ 2622
አነሥ እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” አሉ፦ *”የእኔ ምልጃ ከእኔ ኡማህ ዐበይት ወንጀሎችን ለሰሩ ሰዎች ነው*። عَنْ أَنَسٍ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ شَفَاعَتِي لأَهْلِ الْكَبَائِرِ مِنْ أُمَّتِي
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 81, ሐዲስ 155
ዒምራን ኢብኑ ሑሴይን”ረ.ዐ.” እንደተረከው፦ “ነቢዩም”ﷺ” አሉ፦ *”ጥቂት ሕዝብ ከእሳት ወጥተው ወደ ጀነት በሙሐመድ”ﷺ” ምልጃ ይገባሉ፤ ጀሀነሚዪን ተብለው ይጠራሉ*። حَدَّثَنَا عِمْرَانُ بْنُ حُصَيْن ٍ ـ رضى الله عنهما ـ عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ يَخْرُجُ قَوْمٌ مِنَ النَّارِ بِشَفَاعَةِ مُحَمَّدٍ صلى الله عليه وسلم فَيَدْخُلُونَ الْجَنَّةَ، يُسَمَّوْنَ الْجَهَنَّمِيِّينَ ‏

ይህም የሚሆነው በትንሳኤ ቀን ነው፦
ኢማም ሙስሊም መጽሐፍ 1, ሐዲስ 402
አነሥ ኢብኑ ማሊክ እንደዘገበው የአላህ ነቢይም”ﷺ” አሉ፦ *ሁሉም ነቢይ ለኡመቱ ወደ አላህ ዱዓ ያረጋል፤ በትንሳኤ ቀን የእኔ ዱዓ ለዓኡመቴ ምልጃ ነው*። عَنْ قَتَادَةَ، حَدَّثَنَا أَنَسُ بْنُ مَالِكٍ، أَنَّ نَبِيَّ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ لِكُلِّ نَبِيٍّ دَعْوَةٌ دَعَاهَا لأُمَّتِهِ وَإِنِّي اخْتَبَأْتُ دَعْوَتِي شَفَاعَةً لأُمَّتِي يَوْمَ الْقِيَامَةِ ‏”‏

አምላካችን አላህ በትንሳኤ ቀን በነቢያችን"ﷺ" ሸፋዓ ተጠቃሚ ያድርገን! አሚን።

ኡሥታዝ ወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም

የሚለጠ ለማወቅ
ጥሪያችን Tiriyachen

ወሰላሙ አለይኩም
አሥ ሠላሙ ዐለይኩም ወራሕመቱላሂ ወበረካቱሁ!

እንኳን ለዒድ አል ፊጥር በሰላም አደረሳችሁ!
ተናፍቆ የሚመጣ እና ሳይጠገብ የሚሄድ ብቸኛው ወር የረመዷን ወር ነው።

አሏህ ከእኛም ከእናንተ መልካም ሥራዎችን ይቀበለን! አሚን።
ዘካቱል ፊጥር

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

41፥7 ለእነዚያ ዘካን ለማይሰጡት እነርሱም በመጨረሻይቱ ዓለም እነርሱ ከሓዲዎች ለኾኑት ወዮላቸው፡፡ الَّذِينَ لَا يُؤْتُونَ الزَّكَاةَ وَهُم بِالْآخِرَةِ هُمْ كَافِرُونَ

“ዘካህ” زَكَاة ጥቅላዊ የግዴታ ምፅዋት ማለት ሲሆን የዘካህ ብዙ ቁጥር “ዘካት” زَكَوَات ሲሆን በተናጥል ዘካት በሁለት ይከፈላል፥ እነርሱም “ዘካቱል ማል” زَكَاة المَال እና “ዘካቱል ፊጥር” زَكَاة الفِطْر ናቸው። “ፊጥር” فِطْر ማለት “ፆም መግደፊያ” ማለት ሲሆን የፊጥር ብዙ ቁጥር ደግሞ “ፉጡር” فُطُور ነው፥ የረመዷን ፆም ማብቂያ በዓል እራሱ “ዒዱል ፊጥር” عِيدُ ٱلْفِطْر ይባላል። “ዘካቱል ፊጥር” زَكَاة الفِطْر ደግሞ ለመሣኪን በዒዱል ፊጥር ቀን ለማስፈጠሪያነት የሚውል ገንዘብ ነው፥ “መሣኪን” مَسَاكِين ማለት የዕለት ጉርስ የዓመት ልብስ የሌላቸው “ነዳያን” ማለት ነው። “ለግው” لَّغْو ማለት “ውድቅ ንግግር” ማለት ሲሆን “ረፈስ” رَّفَث ማለት ደግሞ “ስሜት ቀስቃሽ ንግግር” ማለት ነው፥ ዘካቱል ፊጥር ለፆመኛ ውድቅ ንግግር እና ስሜት ቀስቃሽ ንግግር ማፅጃ እንዲሁ ለመሣኪን መብል ነው፦
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 8, ሐዲስ 45
ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ “የአሏህ መልእክተኛ”ﷺ” ዘካቱል ፊጥርን ለፆመኛ ለግው እና ረፈስ ማፅጃ እንዲሁ ለመሣኪን መብል እንዲሆን ግዴታ አድርገዋል”። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ، قَالَ فَرَضَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ زَكَاةَ الْفِطْرِ طُهْرَةً لِلصَّائِمِ مِنَ اللَّغْوِ وَالرَّفَثِ وَطُعْمَةً لِلْمَسَاكِينِ .‏

“ግዴታ አድርገዋል” ለሚለው የገባው የግስ መደብ “ፈረዶ” فَرَضَ መሆኑ በራሱ ዘካቱል ፊጥር ፈርድ መሆኑ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፥ “ፈርድ” فَرْض የሚለው ቃል እራሱ “ፈረዶ” فَرَضَ ማለትም “ግዴታ አደረገ” ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ግዴታ” ማለት ነው። ነዳያን ሲቀሩ ይህ ገንዘብ ወደ ሶላቱል ዒድ ከመሄዳችን በፊት መክፈል በሁሉም ሙሥሊም ላይ የተጣለ ፈርድ ነው፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 24, ሐዲስ 109
አቢ ዑመር”ረ.ዐ.” እንደተረከው፦ “ነቢዩ”ﷺ” ዘካቱል ፊጥርን ሰዎች ወደ ዒድ ሶላት ከመሄዳቸው በፊት እንዲከፈል አዘዋል”። عَنِ ابْنِ عُمَرَ ـ رضى الله عنهما ـ أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم أَمَرَ بِزَكَاةِ الْفِطْرِ قَبْلَ خُرُوجِ النَّاسِ إِلَى الصَّلاَةِ‏.‏
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 24, ሐዲስ 104
አቢ ዑመር”ረ.ዐ.” እንደተረከው፦ “የአሏህ መልእክተኛ”ﷺ” ከሙሥሊም በሁሉም ተገልጋይ ሆነ አገልጋይ አሊያም ወንድ ሆነ ሴት ላይ ከተምር አንድ ሷዕ ወይም ከገብስ አንድ ሷዕ ዘካቱል ፊጥር እንዲከፈል ግዴታ አድርገዋል”። عَنِ ابْنِ عُمَرَ ـ رضى الله عنهما ـ أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم فَرَضَ زَكَاةَ الْفِطْرِ صَاعًا مِنْ تَمْرٍ، أَوْ صَاعًا مِنْ شَعِيرٍ، عَلَى كُلِّ حُرٍّ أَوْ عَبْدٍ، ذَكَرٍ أَوْ أُنْثَى، مِنَ الْمُسْلِمِينَ‏.‏

በሐዲሱ “ሷዕ” صَاع ማለት እና በቁርኣኑ 12፥72 ላይ “ሡዋዕ” صُوَاع ማለት “የእህል መስፈሪያ” ማለት ነው፥ አንድ ሷዕ በክብደት ከ 2.04 እስከ 2.5 kg የሚመዝን ወይም በመጠን በሁለት እጆች 4 እፍኞች ሲሆን ወደ ዓለም ዓቀፍ የመለኪያ ሥርዓት”metric system” ገንዘብ ሲቀየር 5.5 ፓውንድ ይሆናል። በሸቀጥ ገንዘብ ግብይት ዘካቱል ማል የሚወጣው ከብር፣ ከወርቅ እና ከቤት እንስሳት ሲሆን ዘካቱል ፊጥር ደግሞ ከእህል ዓይነት ነው። ዘካን የማይሰጥ “በመጨረሻይቱ ዓለም ከአሏህ ዘንድ መተሳሰብ የለም” ብሎ የሚክድ ሰው ነው፦
41፥7 ለእነዚያ ዘካን ለማይሰጡት እነርሱም በመጨረሻይቱ ዓለም እነርሱ ከሓዲዎች ለኾኑት ወዮላቸው፡፡ الَّذِينَ لَا يُؤْتُونَ الزَّكَاةَ وَهُم بِالْآخِرَةِ هُمْ كَافِرُونَ

ዘካን ካለመስጠት ከሚያስቀጣ ቅጣት አሏህ ይጠብቀን! አሚን።

ከ ኡሥታዝ ወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም
የበለጠ ለማወቅ
ጥሪያችን Tiriyachen

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሸዋል

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

59፥7 *መልክተኛውም የሰጣችሁን ማንኛውንም ነገር ያዙት፡፡ ከእርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ*፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና፡፡ وَمَا آتَاكُمُ الرَّسُولُ فَخُذُوهُ وَمَا نَهَاكُمْ عَنْهُ فَانتَهُوا ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۖ إِنَّ اللَّهَ شَدِيدُ الْعِقَابِ

ሚሽነሪዎች የማያውቁትን ከመጠየቅ ይልቅ፦ “ዘካህ ከመቶ 2.5% ስጡ የሚል መረጃ የለም፣ ሪባ ማለት አራጣ ማለት እንጂ ወለድ ማለት አይደለም፥ የቁርኣን አወራረድ ሁለት አይነት ነው የሚል መረጃ ከቁርኣንም ከሐዲስም መረጃ የለም” እያሉ ዲስኩራቸውን ሲደሶክሩ ነበር። ለእናንዳንዱ አርስት ከቁርኣና ከሐዲስ ከዚህ ቀደም ምላሽ ሰተናል። ዛሬ ደግሞ፦ “ሸዋልን ጹሙ! የሚል ቁርኣን ላይ የለም” እያሉ ይደሶክራሉ። ሚሽነሪዎች ሆይ! ጮቤ ረግጣችሁ አንባጒሮ አትፍጠሩ። ተረጋጉ! የጅብ ችኩል አትሁኑ! በሰላና በሰከነ መንፈስ ጠይቁ መልስ ይሰጣችኃል። ከሆያ ሆዬ ወደ አንቺ ሆዬ ትንሽ እንኳን እደጉ።
የወሮች ቁጥር አላህ ዘንድ በአላህ መጽሐፍ ዐሥራ ሁለት ወር ነው፥ እነዚህም፦
1ኛ ወር ሙሐረም
2ኛ ወር ሰፈር
3ኛ ወር ረቢዑል-አወል
4ኛ ወር ረቢዑ-ሣኒ
5ኛ ወር ጀማዱል-አወል
6ኛ ወር ጀማዱ-ሣኒ
7ኛ ወር ረጀብ
8ኛ ወር ሻዕባን
9ኛ ወር ረመዷን
10ኛ ወር ሸዋል
11ኛ ወር ዙል-ቀዒዳህ
12ኛ ወር ዙል-ሒጃህ ናቸው፦
9፥36 *የወሮች ቁጥር አላህ ዘንድ በአላህ መጽሐፍ ውስጥ ሰማያትንና ምድርን በፈጠረበት ቀን ዐሥራ ሁለት ወር ነው፡፡ ከእነርሱ አራቱ የተከበሩ ናቸው*፡፡ إِنَّ عِدَّةَ الشُّهُورِ عِندَ اللَّهِ اثْنَا عَشَرَ شَهْرًا فِي كِتَابِ اللَّهِ يَوْمَ خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ مِنْهَا أَرْبَعَةٌ حُرُمٌ

ከእነዚህ አስራ ሁለት ወራት አንዱ 10ኛ ወር “ሸዋል” ነው፥ “ሸዋል” شَوَّال ማለት “ማንሳት” ወይም “መሸከም” ማለት ሲሆን የወር ስም ነው። ነቢያችን”ﷺ” እንድናደርገው ሙስተሐብ አድርገው ከሰጡት ሱና መካከል ከሸዋል ወር ስድስት ቀናትን መጾም ነው፦
ጃምዒ አት-ተርሚዚ መጽሐፍ 8, ሐዲስ 78
አቢ አዩብ እንደተረከው፦ “ነቢዩ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *ማንም ረመዷንን የጾመ ከዚያም ከሸዋል ወር ስድስት ቀናትን ያስከተለ ዋጋው ዓመቱን ሙሉ እንደጾመ ነው”*። عَنْ أَبِي أَيُّوبَ، قَالَ قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ مَنْ صَامَ رَمَضَانَ ثُمَّ أَتْبَعَهُ سِتًّا مِنْ شَوَّالٍ فَذَلِكَ صِيَامُ الدَّهْرِ ‏

የረመዷን ሰላሳ ቀን እና የሸዋል ስድስት ቀን ጾም ጾመን ዓመት እንደጾምን የሚያስቆጥርበትን ስሌት ማወቅ ይቻላል። አምላካችን አላህ አንድ መልካም ሥራ ምንዳው አሥር እጥፍ እንደሆነ በቅዱስ ቃሉ ነግሮናል፦
6፥160 *”በመልካም ሥራ የመጣ ሰው ለእርሱ ዐሥር ብጤዎችዋ አሉት”*፡፡ በክፉ ሥራም የመጣ ሰው ብጤዋን እንጅ አይመነዳም፡፡ እነርሱም አይበደሉም፡፡ مَن جَاءَ بِالْحَسَنَةِ فَلَهُ عَشْرُ أَمْثَالِهَا ۖ وَمَن جَاءَ بِالسَّيِّئَةِ فَلَا يُجْزَىٰ إِلَّا مِثْلَهَا وَهُمْ لَا يُظْلَمُونَ

ስለዚህ አንድ መልካም ሥራ አሥር ብጤዎች ካሉት የረመዷን አንድ ወር መጾም የአሥር ወር ምንዳ አለው። 1×10=10 ወር ይሆናል። እንዲሁ የሸዋል ስድስት ቀን መጾም የስድሳ ቀን ምንዳ አለው፥ ስድስት ቀናት በአሥር እጥፍ ስድሳ ቀን ነውና፥ 6×10=60 ቀን ወይም 2 ወር ይሆናል። ሲጠቀለል የረመዷን የአሥር ወር ምንዳ እና የሸዋል ሁለት ወር ምንዳ 12 ወር ይሆናል፥ 10+2=12 ወር ይሆናል። አንድ ዓመት ደግሞ 12 ወር መሆኑ እሙን ነው። አሊያም ሠላሳ የረመዳን ቀን እና ስድስት የሸዋል ቀን በአስር ምንዳ ሲባዛ 360 ቀናት ይሆናሉ፥ 36×10= 360 ይሆናል። አንድ ዓመት ደግሞ ጨረቃ ወፀሐይ"lunisolar" የሆነው የአይሁዳውያን አቆጣጠር 360 ቀናት መሆኑ ቅቡል ነው።
አምላካችን አሏህ በተከበረ ቃሉ፦ “መልክተኛውም የሰጣችሁን ማንኛውንም ነገር ያዙት” ይለናል፦
59፥7 *መልክተኛውም የሰጣችሁን ማንኛውንም ነገር ያዙት፡፡ ከእርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ*፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና፡፡ وَمَا آتَاكُمُ الرَّسُولُ فَخُذُوهُ وَمَا نَهَاكُمْ عَنْهُ فَانتَهُوا ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۖ إِنَّ اللَّهَ شَدِيدُ الْعِقَابِ

ስለዚህ ኢሥላም ሰው ሠራሽ ሕግና ሥርዓት ሳይሆን ዐቂደቱ አር-ረባንያህ ነው። ይህንን ስንል አርቲ ቡርቲና ቶራ ቦራ የሆነ ስሑትና መሪር የቡና ወሬ ይዘን ሳይሆን ቁርኣንና ሐዲስን ያማከለ ስሙርና ጥዑም ማስረጃ ይዘን ነው።

ኡሥታዝ ወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም

Follow us on:
https://fb.me/tiriyachen
https://www.tg-me.com/tiriyachen
https://tiriyachen.org
https://bit.ly/3eVixKv
https://www.tiktok.com/@tiriyachen

ወሠላሙ ዐለይኩም
2025/07/07 12:36:04
Back to Top
HTML Embed Code: