Telegram Web Link
ኢስላም ከይት መጠን ስምን መጣን ወደ ይት እንሄዳስን 👇🏻👇🏻👇🏻
https://vm.tiktok.com/ZMSJNGN51/
ፊተኛው እና ኋለኛው

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

መግቢያ
አላህ ከፍጡራኑ ጋር የማይመሳሰል "አል-አስማኡል ሁስና" الْأَسْمَاءُ الْحُسْنَىٰ ማለትም "መልካም ስሞች" አሉት፦
59:24 እርሱ አላህ ፈጣሪው ከኢምንት አስገኚው ቅርጽን አሳማሪው ነው፤ "ለርሱ መልካም ስሞች" الْأَسْمَاءُ الْحُسْنَىٰ አሉት፤
20:8 አላህ ከርሱ ሌላ አምላክ የለም ለርሱ "መልካም የሆኑ ስሞች" لْأَسْمَاءُ الْحُسْنَى ٰ አሉት።
17:110 ፦አላህን ጥሩ፤ ወይም አልረሕማንን ጥሩ፤ ማንኛውንም ብትጠሩ፣ መልካም ነው፤ ለርሱ "መልካም ስሞች" الْأَسْمَاءُ الْحُسْنَىٰ አሉትና በላቸው፤
7:180 ለአላህም "መልካም ስሞች" الْأَسْمَاءُ الْحُسْنَىٰ አሉት፤ ስትጸልዩ በርሷም ጥሩት እነዚያንም ስሞቹን የሚያጣምሙትን ተውዋቸው፤

እነዚህ ስሞቹ አላህ እንድንማፀንበት፣ እንድንዘክርበት፣ እንድናውቅበት በቁርአን የተጠቀሱ 99 ስሞች ሲኖሩት፤ እነዚህን ስሞች ተእዊል ማለትም ትርጉሙም ሳናዛባ፣ ተዕጢል ማለትም ቃሉን ሳናስተባብል እና ተሽቢህ ማለትም ከፍጡራን ጋር ሳናመሳስል አላህና መልእክተኛው ያፀደቁትን አፅድቀን እንቀበላለን፤ በቁርአን ከተገለፁት ስሞች መካከል "አል-አወል" الْأَوَّل እና "አል-አኺር" لْآخِر ነው፦
57:3 እርሱ "ፊትም ያለ"الْأَوَّلُ እና "ኋላም ቀሪ" وَالْآخِرُ ፣ ግልፅም ስውርም ነው፤ እር ሱም ነገርን ሁሉ ዐዋቂ ነው።

"ፊትም ያለ" እና "ኋላም ቀሪ" የሚለውን በእንግሊዝኛ ትርጉም ላይ "ፊተኛውና ኃለኛው"the first and the last" በማለት አስቀምጠውታል፤ ያ ማለት አላህ መጀመሪያ የሌለው ፊተኛ መጨረሻ የሌለው ኃለኛ ነው ማለት ነው፤ ፈጣሪ በተመሳሳይ በነብዩ ኢሳይያስ "እኔ ፊተኛ ነኝ እኔም ኋለኛ ነኝ" ብሎ ተናግሯል፦
ኢሳይያስ 44፥6 የእስራኤል ንጉሥ እግዚአብሔር፥ የሚቤዥም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እኔ "ፊተኛ" רִאשׁוֹן֙ ነኝ እኔም "ኋለኛ" אַחֲר֔וֹן ነኝ፥ ከእኔ ሌላም አምላክ የለም።
ኢሳይያስ 48፥12 ያዕቆብ ሆይ፥ የጠራሁህም እስራኤል ሆይ፥ ስማኝ፤ እኔ ነኝ፤ እኔ "ፊተኛው" רִאשׁ֔וֹן ነኝ እኔም "ኋለኛው" אַחֲרֽוֹן ነኝ።

ይህንን መለኮታዊ ስም ከፍጡር ስም ጋር ለማነፃፀር መሞከር የተውሒድ ሶስተኛውን ማእዘን ማስተባበል ነው፤ ፍጡር የሆነውን ኢየሱስን ከፈጣሪ አላህ ጋር ማነፃፀር ሽርክ ነው፤ ምክንያቱም ኢየሱስ አላህ ፊተኛና ኃለኛ የተባለበትን መስፈርት አለማሟላቱን የምናውቀው በልደት ጅማሬ ሲኖረው በሞት ፍፃሜ ስላለው ነው፤ ታዲያ ኢየሱስ ፊተኛውና ኃለኛው ነኝ ብሎ የለ ወይ? ብሎ አንድ ሰው ሊሞግት ይችላል፤ ግን ይህንን ንግግር ኢየሱስ ይናገው አይናገረው ከመነሻው ተናገረ ተብሎ የተባለበት ይህ መፅሐፍ አወዛጋቢ ነው፤ የዮሃንስ አፖልካሊፕስ መጽሐፍ ጸሃፊው ዮሃንስ ፕሪስፓይተር እንደሆነ ምሁራን ያትታሉ፣ ይህ ዮሃንስ ከኢየሱስ ሃዋርያ ዮሃንስ የተለየ ነው፣ የአፖልካሊፕስ መጽሐፍ የቀኖና መጽሐፍ የሆነው በ 397 AD በካርቴጅ ጉባኤ ነው፣ ከዚያ በፊት
መ/#ና/ ፍ/#ቃ/ #ን/ በሚባሉት በማርኮናይት እጅ ነው የነበረው፣ በ 313 AD የቂሳሪያው አውሳቢዮስና የፕሮቴስታንቱ መስራች ማርቲን ሉተርም ሳይቀበሉት ቀርተዋል። ነገር ግን የካርቴጅ ጉባኤ የኢየሱስ አምላክነት ይደግፋል በሚል መርህ የቀኖና መጽሐፍ አድርጎታል፣ ሙግቱ አጥበን እስቲ ላለመስማማት መስማማት በሚል መርህ ጥቅሱን እንመልከተው፦
ራእይ 1፥17 እንዲህም አለኝ፦ አትፍራ፤ "ፊተኛው" πρῶτος እና "ኃለኛው"ἔσχατος
ሕያውም እኔ ነኝ፥ ሞቼም ነበርሁ እነሆም፥
ራእይ 2፥8 በሰምርኔስም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ። ሞቶ የነበረው ሕያውም የሆነው ፊተኛው πρῶτος እና "ኃለኛው ἔσχατος እንዲህ ይላል፦

ነጥብ አንድ
"ፊተኛ"
"ፕሮቶስ" πρῶτος ማለት "ፊተኛ" ማለት ሲሆን ይህ ፊተኛ የሚለው ስም ከሞት ጋር ተያይዞ እንደመጣ አስተውሉ፤ ኢየሱስ እንደ ባይብሉ የሙታን ፊተኛ ነው፦
ቆላስይስ 1፥18 እርሱም የአካሉ ማለት የቤተ ክርስቲያን ራስ ነው፤ እርሱም በሁሉ ፊተኛ ይሆን ዘንድ፥ "መጀመሪያ ከሙታንም "በኵር" πρωτότοκος ነው።

"በኵር" ተብሎ የተቀመጠው የግሪኩ ቃል "ፕሮቶ-ቶኮስ" πρωτότοκος ሲሆን የሁለት ቃላት ጥምረት ነው፤ አንዱ "ፕሮቶስ" πρῶτος ማለት "ፊተኛ" ሲሆን ሁለተኛው τοκος "ቶኮስ" ማለትም "መወለድ" የሚል ፍቺ አለው፤ ኢየሱስ በብዙ ወንድሞች መካከል ፊተኛ በመሆን ከሙታን በአብ እንደተወለደ ይናገራል፦
ሮሜ 8፥29 "ልጁ በብዙ ወንድሞች መካከል "በኵር" πρωτότοκον ይሆን ዘንድ፥ አስቀድሞ ያወቃቸው የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ ደግሞ ወስኖአልና፤
ሐዋርያት ሥራ 13:33 ይህን ተስፋ እግዚአብሔር በሁለተኛው መዝሙር ደግሞ። አንተ ልጄ ነህ እኔ "ዛሬ ወለድሁህ" ተብሎ እንደ ተጻፈ፥ "ኢየሱስን አስነሥቶ" ለእኛ ለልጆቻቸው "ፈጽሞአልና"።

ጳውሎስ "ዛሬ ወለድሁህ" ተብሎ የተፃፈው "ኢየሱስን አስነሥቶ" ፈጽሞአልና" ካለን ኢየሱስ የሙታንና የወንድሞቹ ፊተኛ ነው ማለት እንጂ ሞትና ልደት የሌለበት አንዱ አምላክ ነው ማለት አይደለም።

ነጥብ ሁለት
"ኋለኛ"
ስካቶስ ἔσχατος ማለት "ኃለኛው" ማለት ሲሆን ይህ ማእረግ በአንፃራዊ ደረጃ መምጣቱን የምናውቀው
ኢየሰስ ተናገረ የተባለለት ጥቅስ ላይ፦ "ኃለኛው"
ሕያውም እኔ ነኝ፥ "ሞቼም" ነበርሁ፤ "ሞቶ የነበረው" ሕያውም የሆነው ፊተኛው እና "ኃለኛው" መባሉ በራሱ ከሞት መነፃፀሩ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ኢየሱስ እንደ ባይብሉ ከሞት ሲነሳ "ኋለኛው" ሆኗል፤ ኋለኛው ምን? ከተባለ "ኋለኛው አዳም"፦
1ኛ ቆሮንቶስ 15፥45 እንዲሁ ደግሞ፦ ፊተኛው ሰው አዳም ሕያው ነፍስ ሆነ ተብሎ ተጽፎአል፤ "ኋለኛው" ἔσχατος አዳም ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ ሆነ።

ይህንን ከተረዳን ኢየሱስ ብቻ አይደለም በአንፃራዊ ደረጃ ፊተኛ እና ኋለኛ የተባለው ሌሎች ሰዎችም ፊተኞች እና ኋለኞች ተብለዋል፦
ማቴዎስ 19:30 ነገር ግን ብዙዎቹ ፊተኞች πρῶτοι ኋለኞች ἔσχατοι ፥ ኋለኞችም ἔσχατοι ፊተኞች πρῶτοι ይሆናሉ።

ታዲያ እነዚህ ሰዎች ልደትና ሞት የሌለበትን አንዱን አምላክ አብን ናቸውን? በተመሳሳይ ኢየሱስና ሃዋርያት በቁርአን ፊተኞች እና ኋለኞች ተብለዋል፤ ከዚያም ባሻገር ሌሎችም፦
5:114 የመርየም ልጅ ዒሳ አለ ፦ጌታችን አላህ ሆይ! ለኛ ለመጀመሪያዎቻችን لِأَوَّلِنَا እና ለመጨረሻዎቻችን وَآخِرِنَا ባዕል መደሰቻ የምትሆንን ከአንተም ተአምር የሆነችን ማእድ ከሰማይ በኛ ላይ አውርድ፤ ስጠንም፤ አንተ ከሰጪዎች ሁሉ በላጭ ነህና።
77:16-17 የፊተኞቹን الْأَوَّلِينَ አላጠፋንምን? ከዚያም የኋለኞቹን الْآخِرِينَ እናስከትላቸዋለን።

መደምደሚያ
አላህ የሚመስለው ምን ነገር የለም፦
42:11 "የሚመስለው ምንም ነገር የለም"፤ እርሱም "ሰሚው ተመልካቹ" ነው።

ምንም ነገር የሚመስለው ከሌለ አላህ ሰሚና ተመልካች የሚለውን ቃላት ለሰው ሰሚና ተመልካች መሆን ተጠቅሞበታል፦
76:2 እኛ ሰዉን በሕግ ግዳጅ የምንሞክረዉ ስንሆን፥ ቅልቅሎች ከሆኑ የፍትወት ጠብታ ፈጠርነዉ፤ "ሰሚ ተመልካችም" አደረግነዉ።
ጥያቄአችን አላህ ሰሚና ተመልካች ነው ሲባል ሰው ሰሚና ተመልካች በተባለበት ሒሳብ ነው ወይ? ስንል አይ አላህ ይሰማል ሲባል ሁሉንም ነው፥ ጊዜ ሆነ ቦታ አይወስነውም፤ ያያል ሲባል ሁሉንም ነገር ነው፣ ብርሃን ሳይኖር ያያል፥ ለማየቱ ጊዜና ቦታ አይወስነውም፤ ሰው ግን ለመስማት ድምፅ ያስፈልገዋል፥ ሲሰማ ጊዜና ቦታ ይገድበዋል፤ ለማየት ብርሃን ያስፈልገዋል፥ ሲያይ ጊዜና ቦታ ይገድበዋል፤ ይህ የቃላት መመሳሰል እንጂ የባህርይ ስም መመሳሰል እንዳልሆነ ሁሉ ፍጡሮችም ፊተኞች እና ኋለኞች የተባሉት በአንፃራዊ ደረጃ እንጂ በፍፁማዊ ደረጃ በልደት መነሻ በሞት መዳረሻ የላቸውም ማለት አይደለም፤ ኢየሱስ ሟች ከሆነ አንዱ አምላክ በህያውነቱ ላይ ሞት የሌለበት ስለሆነ በእርግጥም እርሱ መጀመሪያ የሌለው ፊተኛ መጨረሻው የሌለው ኃለኛ ነው፦
25:58 በዚያም በማይሞተው ሕያው አምላክ ላይ ተመካ፤
ዕን.1:12 አቤቱ፥ የተቀደስህ አምላኬ ሆይ፥ አንተ ከዘላለም ጀምሮ አልነበርህምን? ""አንተ አትሞትም"" הֲל֧וֹא אַתָּ֣ה נָמ֑וּת ።
1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 1፥17 ብቻውን አምላክ ለሚሆን "ለማይሞተው" ἀφθάρτῳ ለማይታየውም ለዘመናት ንጉሥ ምስጋናና ክብር እስከ ዘላለም ድረስ ይሁን፤ አሜን።
1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 6፥16 "እርሱ ብቻ የማይሞት" ἀθανασίαν ነው፤ ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ይኖራል፤ አንድ ሰው እንኳ አላየውም ሊያይም አይቻለውም፤ ለእርሱ ክብርና የዘላለም ኃይል ይሁን፤ አሜን።

✍🏻ከወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም

ጥሪያችን በሁሉም ቦታ!
Follow us on:👇🏻
Telegram ፦ https://www.tg-me.com/tiriyachen
Website ፦ https://tiriyachen.org
Instagram ፦ https://bit.ly/3eVixKv
TikTok ፦ https://www.tiktok.com/@tiriyachen
ወሰላሙ አለይኩም
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ኢስላም ከይት መጠን
ለምን መጣን
ወደ ይት እንሄዳለን

✍🏻ከወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም
-------------------------------------------------------
ጥሪያችን በሁሉም ቦታ!
Follow us on:👇🏻
Telegram ፦ https://www.tg-me.com/tiriyachen
Website ፦ https://tiriyachen.org
Instagram ፦ https://bit.ly/3eVixKv
TikTok ፦ https://www.tiktok.com/@tiriyachen
የነገሥታት ንጉሥ ማን ነው?

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡

ነጥብ አንድ
"የነገሥታት ንጉሥ በቁርአን"
3:26 በል- "የንግሥና ባለቤት" مَالِكَ الْمُلْكِ የሆንክ አላህ ሆይ! ለምትሻዉ ሰዉ "ንግስናን" الْمُلْكِ ትሰጣለህ፤ ከምትሻዉም ሰዉ "ንግስናን" الْمُلْكَ ትገፍፋለህ፤ የምትሻዉንም ሰዉ ታልቃለህ፤ የምትሻዉንም ሰዉ ታዋርዳለህ። መልካም ነገር ሁሉ በእጅህ ነው፤ አንተ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነህና

"የንግሥና ባለቤት" ተብሎ የተቀመጠው ቃል "ማሊከል ሙልክ" مالك الملك ሲሆን "የነገስታት ንጉስ" የሚል ፍቺ አለው፣ አላህ ለሚሻው ሰው ንግስና ይሰጣል፦
2:247 አላህም "ንግሥናውን" الْمُلْكُ ለሚሻው ሰው ይሰጣል፡፡ አላህም ችሮታው ሰፊ ዐዋቂ ነው» አላቸው፡፡
2:251በአላህም ፈቃድ ድል መቷቸው፡፡ ዳውድም ጃሉትን
ገ/#ደ/#ለ/፡፡ "ንግሥናን" الْمُلْكَ እና ጥበብንም አላህ ሰጠው፡፡
2:258 ወደዚያ አላህ "ንግሥናን" الْمُلْكَ ስለሰጠው ኢብራሂምን በጌታው ነገር ወደ ተከራከረው ሰው አላየህምን?
5:20 ሙሳም ለሕዝቦቹ ባለ ጊዜ አስታውስ፤ ፦ ሕዝቦቼ ሆይ የአላህን ጸጋ በውስጣችሁ ነቢያትን ባደረገና "ነገሥታትም" مُلُوكً ባደረጋችሁ፣ ከዓለማትም ለአንድም ያልሰጠውን ችሮታ በሰጣችሁ ጊዜ በናንተ ላይ ያደረገውን ጸጋ አስታውሱ።
27:34 እርሷም አለች «"ነገሥታት" الْمُلُوكَ ከተማን በኀይል በገቡባት ጊዜ ያበላሹዋታል፡፡

የሚያጅበው ነገር ሰው በእንስሳ ላይ ንጉስ መሆኑንና ይህን ንግስና ከአላህ ማግኘቱ ነው፦
36:71-73 እኛ እጆቻችን ከሠሩት ለእነርሱ እንሰሳዎችን መፈጠራችንን አያውቁምን? እነርሱም ለእነርሱ ባለ መብቶች مَالِكُونَ ናቸው። ለነርሱም ገራናቸው ስለዚህ ከእነርሱም ይበላሉ። ለእነርሱም በእነርሱ ውስጥ ሌሎች ጥቅሞች መጠጦችም አሉዋቸው ፣ ታዲያ አያመሰግኑምን?

"ባለ መብት" ተብሎ የተቀመጠው ቃል ማሊክ مَٰلِك ሲሆን ንጉስ ወይም ባለቤት በሚል ይመጣል፣ የሃፍስ ቂርአት ሱረቱል ፋቲሃ 1፥4 ላይ "ማሊክ" مَٰلِك ብሎ ሚምን በሁለት ሃረካት ሚም ፈትሃ አሊፍ ስኩን "ማ" ብሎ ሲቀራው የወርሽ ቂርአት ደግሞ "መሊክ"مَلِيك ብሎ ሚምን ባለ አንድ ሃረካ ሚም ፈትሃ "መ" ብሎ ይቀራዋል። ወደ ነጥቡ ስንገባ ሰው የእንስሳት ንጉስ፣ ባለቤት፣ ባለመብት መሆኑን ነው።

አላህ ለነገስታት የሚሰጠው ንግስና እና የራሱ ንግስና ይለያያል፣ አላህ ንግስናው የራሱ ብቻ ሲሆን በንግስናው ተጋሪ የለውም፦
57:2 የሰማያትና የምድር "ንግሥና" مُلْكُ የርሱ ብቻ ነው፤ ሕያው ያደርጋል፤ ይገድላልም፤ እርሱም በነገሩ ሁሉ ቻይ ነው።
67:1 ያ "ንግሥና" الْمُلْكُ በእጁ የሆነው አምላክ ችሮታው በዛ፤ እርሱም በነገሩ ሁሉ ቻይ ነው።
25:2 እርሱ ያ የሰማያትና የምድር "ንግሥና" مُلْكُ የርሱ ብቻ የሆነ ልጅንም ያልያዘ፣ "በንግሥናውም" الْمُلْكِ ተጋሪ የሌለው፣ ነገሩንም ሁሉ የፈጠረና፣ በትክክልም ያዘጋጀው ነው።
17:111 ፦ምስጋና ለአላህ ለዚያ ልጅን ላልያዝነው ለርሱም "በንግሥናው" الْمُلْكِ ተጋሪ ለሌለው ለርሱም ከውርደት ረዳት ለሌለው ይግባው፣ በልም ማክበርን አክብረው።

"መለኩት" مَلَكُوت ተብሎ የተቀመጠው ቃል ትርጉሙ መለኮት፣ ስልጣን፣ ግዛት የሚል ፍቺ ሲኖረው፣ ይህም የአላህ መሆኑን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፦
36:83 ያ የነገሩ ሁሉ "ስልጣን" مَلَكُوتُ በጁ የሆነው ጌታ ጥራት ይግባው፤ ወደርሱም ትመለሳላችሁ። 23:88 «የነገሩ ሁሉ "ግዛት" مَلَكُوتُ በእጁ የኾነ እርሱ የሚጠብቅ በእርሱ ላይ የማይጠበቅ ማን ነው የምታውቁ እንደኾናችሁ መልሱልኝ» በላቸው፡፡
7:185 በሰማያትና በምድር "ግዛት" مَلَكُوتِ ውስጥ ከማንኛውም ነገር አላህ በፈጠረውም ሁሉ የሞት ጊዜያቸውም በእርግጥ መቅረቡ የሚፈራ መሆኑን አያስተውሉምን? ከርሱም ከቁርአን ወዲያ በየትኛው ንግግር ያምናሉ።
6:75 እንደዚሁም ኢብራሂምን እንዲያውቅና ከአረጋጋጮቹም ይኾን ዘንድ የሰማያትንና የምድርን "መለኮት" مَلَكُوتَ አሳየነው፡፡

ከአላህ ውጪ የነገስታት ንጉስ የለም፣ የነገስታት ንጉስ ነኝ ብሎ እራሱን የሰየመ አሊያም የጠራ በትንሳኤ ቀን የከፋ ሰው ነው፣ ከአላህ ውጪ የነገስታን ንጉስ የለም፦
ኢማሙል ሙስሊም መጽሃፍ 38 ሐዲስ 26
አቡሁረይራ እንደተረከው የአላህ መልእክተኛም አለ፦
أَغْيَظُ رَجُلٍ عَلَى اللَّهِ يَوْمَ الْقِيَامَةِ وَأَخْبَثُهُ وَأَغْيَظُهُ عَلَيْهِ رَجُلٌ كَانَ يُسَمَّى مَلِكَ الأَمْلاَكِ لاَ مَلِكَ إِلاَّ اللَّهُ
አላህ ዘንድ በትንሳኤ ቀን በጣም የከፋ ሰውና የቁጣው አላማ የነገስታት ንጉስ ተብሎ የተጠራ ነው፣ ግን ከአላህ ውጪ ንጉስ የለም።

ነጥብ ሁለት
"የነገሥታት ንጉሥ በባይብል"
አንድ መጣጥፍ ላይ ፦ቁርአን አላህን የነገሥታት ንጉሥ ይለዋል ባይብል ደግሞ የነገሥታት ንጉሥ የሚለው ኢየሱስን ነው ፤ ስለዚህ ኢየሱስ አምላክ ነው የሚል ጥራዝ ነጠቅ ሙግት አንብቤ ነበር፤ ከመነሻው መወዳደር የነበረበት ቁርአን ከባይብሉ ጋር ሳይሆን ቁርአን በቁርአን አሊያም ባይብል በባይብል ነበር፤ ሙግቱን ለማጥበብ ታዲያ ኢየሱስ የነገሥታት ንጉሥ መባሉ በቁርአን የተጠቀሰውን የነገሥታት ንጉሥ የሚለውን ባህርይ የሚያሳይ ከሆነ ብዙ አማልክት ሊኖሩ ነው፤ ምክንያቱም በባይብል የነገሥታት ንጉሥ የተባሉት እግዚአብሔር፣ ኢየሱስ፣ አርጤክስስ እና ናቡከደነፆር ናቸው፦

1. እግዚአብሔር
1ኛ ጢሞቴዎስ 6፥15 ያንም መገለጡን በራሱ ጊዜ ብፁዕና ብቻውን የሆነ ገዥ፥ "የነገሥታት ንጉሥ" እና የጌቶች ጌታ እግዚአብሔር ያሳያል።
አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2. ኢየሱስ
ራእይ 17፥14 እነዚህ በጉን ይወጋሉ፤ በጉም የጌቶች ጌታና "የነገሥታት ንጉሥ" ስለ ሆነ እነርሱን ድል ይነሣል፥ ከእርሱም ጋር ያሉ የተጠሩና የተመረጡ የታመኑም ደግሞ ድል ይነሣሉ።
ራእይ 19፥16 በልብሱና በጭኑም የተጻፈበት፦ "የነገሥታት ንጉሥ" እና የጌቶች ጌታ የሚል ስም አለው።

3. አርጤክስስ
ዕዝራ 7፥12 "ከነገሥታት ንጉሥ" ከአርጤክስስ ለሰማይ አምላክ ሕግ ጸሐፊ ለካህኑ ለዕዝራ፥ ሙሉ ሰላም ይሁን፤

4. ናቡከደነፆር
ሕዝቅኤል 26፥7 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ እነሆ፥ ከሰሜን "የነገሥታት ንጉሥ" የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነፆርን ከፈረሶችና ከሰረገሎች ከፈረሰኞችም ከጉባኤና ከብዙ ሕዝብ ጋር በጢሮስ ላይ አመጣለሁ።
ዳንኤል 2፥37 አንተ፥ ንጉሥ ሆይ፥ የሰማይ አምላክ መንግሥትንና ኃይልን፥ ብርታትንና ክብርን የሰጠህ "የነገሥታት ንጉሥ" አንተ ነህ።

አይ አርጤክስስና ናቡከደነፆር ንግስናቸውን ያገኙት ከአንዱ አምላክ ነው ከተባለ ኢየሱስም ንግስናውን ያገኘው ከአንዱ አምላክ በስጦታ ነው፦
ሉቃስ 1:32 ጌታ አምላክም የአባቱን የዳዊትን ዙፋን "ይሰጠዋል፤

ስለዚህ ኢየሱስ በቁርአን ከተነገረው የነገሥታት ንጉሥ ይቅርና በባይብል ከተነገረው የነገሥታት ንጉሥ ጋር በህልውናም ሆነ በኑባሬ አሊያም በሃልዎት ሆነ በቅዋሜ-ማንነት አንድ አይደለም።

ከወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም
አወዛጋቢው ዶክትሪን

ክፍል አንድ

ሙሥሊሙ፦ "ኢየሱስ የማን ባሪያ ነው?
ክርስቲያኑ፦ "የእግዚአብሔር ባሪያ ነው።
ሙሥሊሙ፦ "ኢየሱስ እራሱ የራሱ ባሪያ ነውን?
ክርስቲያኑ፦ "ኖ! የአብ ባሪያ እንጂ የራሱ ባሪያ አይደለም።
ሙሥሊሙ፦ "ኢየሱስ አብ ነውን?
ክርስቲያኑ፦ "አይደለም።
ሙሥሊሙ፦ "አብ ማን ነው?
ክርስቲያኑ፦ "እግዚአብሔር ነው።
ሙሥሊሙ፦ "ኢየሱስ እግዚአብሔር ነውን?
ክርስቲያኑ፦ "አዎ! በትክክል።

ሙሥሊሙ፦ "ኢየሱስ የማን ነቢይ ነው?
ክርስቲያኑ፦ "የእግዚአብሔር ነቢይ ነው።
ሙሥሊሙ፦ "ኢየሱስ እራሱ የራሱ ነቢይ ነውን?
ክርስቲያኑ፦ "ኖ! የአብ ነቢይ እንጂ የራሱ ነቢይ አይደለም።
ሙሥሊሙ፦ "ኢየሱስ አብ ነውን?
ክርስቲያኑ፦ "አይደለም።
ሙሥሊሙ፦ "አብ ማን ነው?
ክርስቲያኑ፦ "እግዚአብሔር ነው።
ሙሥሊሙ፦ "ኢየሱስ እግዚአብሔር ነውን?
ክርስቲያኑ፦ "አዎ! በትክክል።

ሙሥሊሙ፦ "ኢየሱስን የላከው ማን ነው?
ክርስቲያኑ፦ "እግዚአብሔር።
ሙሥሊሙ፦ "ኢየሱስ እራሱ በራሱ ላከው?
ክርስቲያኑ፦ "ኖ! አብ ነው የላከው እንጂ ራሱን በራሱ አላከውም።
ሙሥሊሙ፦ "ኢየሱስ አብ ነውን?
ክርስቲያኑ፦ "አይደለም።
ሙሥሊሙ፦ "አብ ማን ነው?
ክርስቲያኑ፦ "እግዚአብሔር ነው።
ሙሥሊሙ፦ "ኢየሱስ እግዚአብሔር ነውን?
ክርስቲያኑ፦ "አዎ! በትክክል።

ሙሥሊሙ፦ "ኢየሱስ ሰውነቱ ፍጡር ነው?
ክርስቲያኑ፦ "አዎ!
ሙሥሊሙ፦ "ማን ፈጠረው?
ክርስቲያኑ፦ "እግዚአብሔር።
ሙሥሊሙ፦ "ኢየሱስ እራሱ በራሱ ፈጠረው?
ክርስቲያኑ፦ "ኖ! አብ ነው የፈጠረው እንጂ ራሱ እራሱን አልፈጠረውም።
ሙሥሊሙ፦ "ኢየሱስ አብ ነውን?
ክርስቲያኑ፦ "አይደለም።
ሙሥሊሙ፦ "አብ ማን ነው?
ክርስቲያኑ፦ "እግዚአብሔር ነው።
ሙሥሊሙ፦ "ኢየሱስ እግዚአብሔር ነውን?
ክርስቲያኑ፦ "አዎ! በትክክል።

ሙሥሊሙ፦ "ኢየሱስ ሲጸልይና ሲሰግድ የነበረው ወደ ማን ነው?
ክርስቲያኑ፦ "ወደ እግዚአብሔር።
ሙሥሊሙ፦ "ኢየሱስ ሲጸልይና ሲሰግድ የነበረው ወደ ራሱ ነውን?
ክርስቲያኑ፦ "ኖ! ወደ አብ ነው ሲጸልይና ሲሰግድ የነበረው እንጂ ወደ ራሱ አይደለም።
ሙሥሊሙ፦ "ኢየሱስ አብ ነውን?
ክርስቲያኑ፦ "አይደለም።
ሙሥሊሙ፦ "አብ ማን ነው?
ክርስቲያኑ፦ "እግዚአብሔር ነው።
ሙሥሊሙ፦ "ኢየሱስ እግዚአብሔር ነውን?
ክርስቲያኑ፦ "አዎ! በትክክል።

ሙሥሊሙ፦ "ኢየሱስ አምላክ አለው?
ክርስቲያኑ፦ "አዎ!
ሙሥሊሙ፦ "አምላኩ ማን ነው?
ክርስቲያኑ፦ "እግዚአብሔር!
ሙሥሊሙ፦ "ኢየሱስ ራሱ የራሱ አምላክ ነውን?
ክርስቲያኑ፦ "ኖ! አምላኩ አብ ነው እንጂ ራሱ የራሱ አምላክ አይደለም።
ሙሥሊሙ፦ "ኢየሱስ አብ ነውን?
ክርስቲያኑ፦ "አይደለም።
ሙሥሊሙ፦ "አብ ማን ነው?
ክርስቲያኑ፦ "እግዚአብሔር ነው።
ሙሥሊሙ፦ "ኢየሱስ እግዚአብሔር ነውን?
ክርስቲያኑ፦ "አዎ! በትክክል።

የዚህ ዶክትሪን መልስ ኅሊና ይቀበለዋልን? መልስ ለኅሊና። ውዝግብ ክፍል ሁለት ኢንሻሏህ ይቀጥላል.....

ከወሒድ ዐቃቤ እሥልምና

የበለጠ ለማወቅ
ጥሪያችን Tiriyachen
ሥነ-ልቦና

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፤

17፥85 ከሩሕም ይጠይቁሃል፡፡ «ሩሕ ከጌታዬ ነገር ነው ከዕውቀትም ጥቂትን እንጂ አልተሰጣችሁም» በላቸው፡፡ وَيَسْـَٔلُونَكَ عَنِ ٱلرُّوحِ ۖ قُلِ ٱلرُّوحُ مِنْ أَمْرِ رَبِّى وَمَآ أُوتِيتُم مِّنَ ٱلْعِلْمِ إِلَّا قَلِيلًۭا

የሥነ-ልቦና ጥናት”Psychology” ጥናቱን ያደረገው በልብ ላይ ነው፤ “ሳይኮ” ψυχή ማለት “መንፈስ” “ነፍስ” “ልብ” “ህሊና” “አእምሮ” ማለት ነው፤ “ሎጂአ” λογία ደግሞ “ጥናት” ማለት ነው፤ የሰው መንፈስ ማዕከሉ “ልብ” ነው፤ እስቲ ስለ “ልብ”፣ ስለ እንቅልፍ ዓለም፣ ስለ የሞት ጊዜ እና በሞትና በትንሳኤ መካከል ስላለው ቆይታ አላህ በሰጠን ጥቂት ዕውቀት እናስተንትን፦

ነጥብ አንድ
“ልብ”
“ልብ” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ቀልብ” قَلْب “ፉዓድ” فُؤَاد እና “ሰድር” صَدْر ሲሆን የውስጥን ማንነት ለማሳወቅ የመጣ ቃል ነው፤ ሰዎች ውሳጣዊ ተፈጥሮን “ቆሌ” “ቆሽት” “አንጀት” “ናላ” ብለው በእማራዊ ቃላት ፍካሬአዊ ልብን ይገልጡታል፤ “ሕሊና” የሚለው ቃል “ሐለየ” ማለትም “አሰበ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ማሰቢያ” ማለት ነው፤ “ልብ” የሚለው ቃል “ለበወ” ማለትም “አመዛዘነ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ማመዛዘኛ” ማለት ነው፤ “አእምሮ” የሚለው ቃል “አእመረ” ማለትም “ዐወቀ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ማወቂያ” ማለት ነው፤ ልብ የኢማን መቀመጫ፣ በዚክር የሚረጥብ፣ በአላህ ንግግር የሚረጋጋ እና በአምልኮ የሚሰፋ ውስጣዊ ማንነት ነው፤ እነዚህ ከቃሉ መረዳት ይቻላል፦
“ቀልብ”
2፥97 ለጂብሪል ጠላት የኾነ ሰው በቁጭት ይሙት በላቸው፡፡ እርሱ ከበፊቱ ለነበሩት አረጋጋጭ ለምእመናን መሪና ብስራት ሲኾን በአላህ ፈቃድ *”በልብህ” ላይ አውርዶታልና፡፡ قُلْ مَن كَانَ عَدُوًّۭا لِّجِبْرِيلَ فَإِنَّهُۥ نَزَّلَهُۥ عَلَىٰ قَلْبِكَ بِإِذْنِ ٱللَّهِ مُصَدِّقًۭا لِّمَا بَيْنَ يَدَيْهِ وَهُدًۭى وَبُشْرَىٰ لِلْمُؤْمِنِينَ
26፥194 ከአስጠንቃቂዎቹ ትኾን ዘንድ *”በልብህ”* ላይ አወረደው፡፡ عَلَىٰ قَلْبِكَ لِتَكُونَ مِنَ ٱلْمُنذِرِينَ
13፥28 እነርሱም እነዚያ ያመኑ *”ልቦቻቸውም”* አላህን በማውሳት የሚረኩ ናቸው፡፡ ንቁ! አላህን በማውሳት *”ልቦች”* ይረካሉ፡፡ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَتَطْمَئِنُّ قُلُوبُهُم بِذِكْرِ ٱللَّهِ ۗ أَلَا بِذِكْرِ ٱللَّهِ تَطْمَئِنُّ ٱلْقُلُوبُ

“ፉዓድ”
11፥120 ከመልክተኞቹም ዜናዎች ተፈላጊውን ሁሉንም *”ልብህን”* በእርሱ የምናረካበትን እንተርክልሃለን፡፡ በዚህችም ሱራ እውነቱ ነገር ለምእምናን ግሳጼና ማስታወሻ መጥቶልሃል፡፡ وَكُلًّۭا نَّقُصُّ عَلَيْكَ مِنْ أَنۢبَآءِ ٱلرُّسُلِ مَا نُثَبِّتُ بِهِۦ فُؤَادَكَ ۚ وَجَآءَكَ فِى هَٰذِهِ ٱلْحَقُّ وَمَوْعِظَةٌۭ وَذِكْرَىٰ لِلْمُؤْمِنِينَ
25፥32 እነዚያ የካዱትም «ቁርኣን በእርሱ ላይ ለምን በጠቅላላ አንድ ጊዜ አልተወረደም» አሉ፡፡ እንደዚሁ በእርሱ *”ልብህን”* ልናረጋ ከፋፍለን አወረድነው፡፡ ቀስ በቀስ መለያየትንም ለየነው፡፡ وَقَالَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ لَوْلَا نُزِّلَ عَلَيْهِ ٱلْقُرْءَانُ جُمْلَةًۭ وَٰحِدَةًۭ ۚ كَذَٰلِكَ لِنُثَبِّتَ بِهِۦ فُؤَادَكَ ۖ وَرَتَّلْنَٰهُ تَرْتِيلًۭا

“ሰድር”
94፥1*”ልብህን”* ለአንተ አላሰፋንልህምን? أَلَمْ نَشْرَحْ لَكَ صَدْرَكَ
20፥25 (ሙሳም) አለ «ጌታዬ ሆይ! “ልቤን” አስፋልኝ፡፡ قَالَ رَبِّ ٱشْرَحْ لِى صَدْرِى
39፥22 አላህ *”ደረቱን”* ለእስልምና ያስፋለትና እርሱም ከጌታው ዘንድ በብርሃን ላይ የኾነ ሰው ልቡ እንደ ደረቀ ሰው ነውን? *”ልቦቻቸውም”* ከአላህ መወሳት ለደረቁ ሰዎች ወዮላቸው፡፡ እነዚያ በግልጽ መሳሳት ውስጥ ናቸው፡፡ أَفَمَن شَرَحَ ٱللَّهُ صَدْرَهُۥ لِلْإِسْلَٰمِ فَهُوَ عَلَىٰ نُورٍۢ مِّن رَّبِّهِۦ ۚ فَوَيْلٌۭ لِّلْقَٰسِيَةِ قُلُوبُهُم مِّن ذِكْرِ ٱللَّهِ ۚ أُو۟لَٰٓئِكَ فِى ضَلَٰلٍۢ مُّبِينٍ

ነጥብ ሁለት
“የእንቅልፍ ዓለም”
ሰው ውጫዊው ማንነቱ አካሉ ሲሆን ይህ አካል “እረፍት” ያስፈልገዋል፦
25፥47 እርሱም ያ ለእናንተ ሌሊትን ልብስ እንቅልፍንም “ማረፊያ” ያደረገ፤ ቀንንም መበተኛ ያደረገላችሁ ነው፡፡ وَهُوَ ٱلَّذِى جَعَلَ لَكُمُ ٱلَّيْلَ لِبَاسًۭا وَٱلنَّوْمَ سُبَاتًۭا وَجَعَلَ ٱلنَّهَارَ نُشُورًۭا
40፥61 አላህ ያ ለእናንተ ሌሊትን በውስጡ “ልታርፉበት”፤ ቀንንም ልትሠሩበት የሚያሳይ ያደረገላችሁ ነው፡፡ ٱللَّهُ ٱلَّذِى جَعَلَ لَكُمُ ٱلَّيْلَ لِتَسْكُنُوا۟ فِيهِ وَٱلنَّهَارَ مُبْصِرًا
10፥67 እርሱ ያ *”ሌሊትን በውስጡ ልታርፉበት”*፤ ቀንንም ልትሠሩበት ብርሃን ያደረገላችሁ ነው፡፡ *”በዚህ ውስጥ ለሚሰሙ ሕዝቦች በእርግጥ ታምራቶች አሉ”*፡፡ هُوَ ٱلَّذِى جَعَلَ لَكُمُ ٱلَّيْلَ لِتَسْكُنُوا۟ فِيهِ وَٱلنَّهَارَ مُبْصِرًا ۚ إِنَّ فِى ذَٰلِكَ لَـَٔايَٰتٍۢ لِّقَوْمٍۢ يَسْمَعُونَ

አላህ ሌሊትን በውስጡ እንቅልፍን ማረፊያ ማድረጉ ለሚሰሙ ሕዝቦች በእርግጥ ታምራቶች አሉ፤ ከታምራቶች አንዱ የሰው አካል እረፍት ሲያደርግ ነገር ግን የሰው መንፈስ ያለ ዓይን ታያለች፣ ያለ ጆሮ ትሰማለች፣ ያለ እግር ትሄዳለች፣ ያለ አፍ ትናገራለች፤ ምክንያቱም አላህ ያችንም ያልሞተችውን ነፍስ በእንቅልፏ ጊዜ ይወስዳታል፦
39፥42 አላህ ነፍሶችን በሞታቸው ጊዜ *”ይወስዳል”*፡፡ ያችንም ያልሞተችውን በእንቅልፏ ጊዜ ይወስዳታል፡፡ ٱللَّهُ يَتَوَفَّى ٱلْأَنفُسَ حِينَ مَوْتِهَا وَٱلَّتِى لَمْ تَمُتْ فِى مَنَامِهَا

የእንቅልፍ ዓለም መንፈሳችን ከአካላችን ጋር እንዴት እንደምትለያይ ልምምድ ላይ ናት፤ አላህ መንፈሳችንን በሞታችን ጊዜ ይወስዳታል፤ “ይወስዳል” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “የተወፍፈ” يَتَوَفَّى ሲሆን ያችንም ያልሞተችውን ነፍስ ደግሞ በእንቅልፏ ጊዜ ይወስዳታል፤ በሌላ አንቀፅ ላይ “የሚያስተኛችሁ” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “የተወፍፋኩም” يَتَوَفَّاكُمْ ሲሆን “የተወፍፈ” ሆነ “የተወፍፋኩም” የረባበት ቃል “ተወፍፋ” تَوَفَّىٰ “ወሰደ” “አስተኛ” ነው፤ አላህ ሩሐችንን በሌሊት በእንቅልፍ ጊዜ እንደሚወስድ እና አካላችንን እንደሚያስተኛ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፦
6፥60 እርሱም ያ በሌሊት *”የሚያስተኛችሁ”* በቀንም የሠራችሁትን ሁሉ የሚያውቅ ከዚያም የተወሰነው ጊዜ ይፈፀም ዘንድ በእርሱ በቀን ውስጥ *”የሚቀሰቅሳችሁ”* ነው፡፡ ከዚያም *”መመለሻችሁ ወደ እርሱ ነው”*፡፡ ከዚያም ትሠሩት የነበራችሁትን ሁሉ ይነግራችኋል፡፡ وَهُوَ ٱلَّذِى يَتَوَفَّىٰكُم بِٱلَّيْلِ وَيَعْلَمُ مَا جَرَحْتُم بِٱلنَّهَارِ ثُمَّ يَبْعَثُكُمْ فِيهِ لِيُقْضَىٰٓ أَجَلٌۭ مُّسَمًّۭى ۖ ثُمَّ إِلَيْهِ مَرْجِعُكُمْ ثُمَّ يُنَبِّئُكُم بِمَا كُنتُمْ تَعْمَلُونَ

ነጥብ ሶስት
“የሞት ጊዜ”
በሌሎች አናቅፅ ላይ አላህ መልአከ ሞትን ልኮ ነፍሶችን በሞታቸው ጊዜ “ይወስዳችኃል” ይላል፤ አሁንም “ይወስዳችኃል” ለሚለው ቃል የተጠቀመበት “የተወፍፋኩም” يَتَوَفَّاكُمْ ነው፦
32፥11 «በእናንተ የተወከለው መልአከ ሞት *”ይወስዳችኃል”*፡፡ ከዚያም ወደ ጌታችሁ ትመለሳላችሁ» በላቸው፡፡ قُلْ يَتَوَفَّىٰكُم مَّلَكُ ٱلْمَوْتِ ٱلَّذِى وُكِّلَ بِكُمْ ثُمَّ إِلَىٰ رَبِّكُمْ تُرْجَعُونَ
7፥37 የሞት መልክተኞቻችንም *”የሚወስዷቸው ኾነው በመጡባቸው ጊዜ”* «ከአላህ ሌላ የምትጠሯቸው የነበራችሁት የት አሉ» ይሏቸዋል፡፡ «ከእኛ ተሰወሩን» ይላሉ፡፡ እነርሱም
"ከሃ/ዲ / ያ/ ን" እንደነበሩ በነፍሶቻቸው ላይ ይመሰክራሉ፡፡
16፥70 አላህም ፈጠራችሁ፤ ከዚያም “ይወስዳችኃል”፡፡ ከእናንተም ከዕወቅት በኋላ ምንንም ነገር እንዳያውቅ ወደ ወራዳ ዕድሜ የሚመለስ ሰው አልለ፡፡ አላህ ዐዋቂ ቻይ ነው፡፡ وَٱللَّهُ خَلَقَكُمْ ثُمَّ يَتَوَفَّىٰكُمْ ۚ وَمِنكُم مَّن يُرَدُّ إِلَىٰٓ أَرْذَلِ ٱلْعُمُرِ لِكَىْ لَا يَعْلَمَ بَعْدَ عِلْمٍۢ شَيْـًٔا ۚ إِنَّ ٱللَّهَ عَلِيمٌۭ قَدِيرٌۭ

ስለዚህ “እንቅፍ” ማለት “ሞት” ማለት ነው፤ በእንቅልፍ ጊዜ ሩሓችንን በመውሰድ የሚያሞተን አላህ ነው፤ በሞትም ጊዜ አላህ መልአከ ሞትን ልኮ ነፍሶችን ያሞታል፤ “ማሞት” ግን የአላህ ስልጣን ብቻ ነው፦
2፥28 ሙታን የነበራችሁ ስትኾኑ ሕያው ያደረጋችሁ ከዚያም *”የሚ&ገ&ድ&ላ&ችሁ”* ከዚያም ሕያው የሚያደርጋችሁ ሲኾን ከዚያም ወደ እርሱ የምትመለሱ ስትኾኑ በአላህ እንዴት ትክዳለችሁ!

“የ&ሚ&ገ&ድ&ላ&ች&ሁ” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ዩሚቱኩም” يُمِيتُكُمْ ሲሆን “የሚያሞት” ማለት ነው፤ የሚ&ያሞ&ትም አንዱ አምላክ ብቻ ነው፦
15፥23 እኛም ሕያው የምናደርግ እና *”የ&ም&ን&ገ&ድ&ል”* እኛው *”ብቻ”* ነን፡፡ እኛም ፍጡርን ሁሉ የምንወርስ ቀሪ ነን፡፡

9፥116 አላህ የሰማያትና የምድር ንግስና የእርሱ ብቻ ነው፡፡ ሕያው ያደርጋል፤ *”ይ&ገ&ድ&ላ&ል&ም”*፡፡ ለእናንተም ከእርሱ በቀር ጠባቂም ረዳትም የላችሁም፡፡

10፥56 እርሱ ሕያው ያደርጋል፤ *”ይ&ገ&ድ&ላ&ል&ም”* ወደ እርሱም ትመለሳላችሁ፡፡ هُوَ يُحْىِۦ وَيُمِيتُ وَإِلَيْهِ تُرْجَعُونَ

ነጥብ አራት
“በርዘኽ”
“በርዘኽ” برزخ ማለት የቃሉ ትርጉም “ጋራጅ” ማለት ሲሆን “መለያ” እና “መቆያ” ነው፤ አላህ ሩሕን በሞት ጊዜ ይወስዳል፣ በእንቅልፍ ጊዜ የምንወሰደው ነገር ማለትም ያለ አይን ማየቱ፣ ያለ ጆሮ መስማቱ፣ ያለ እግር መሄዱ፣ ያለ አፍ መናገሩ ሩህ ከሞት በኋላ ያለውን ሁኔታ በጥቂቱ የምናይበት ነው፣ ምነው እንቅልፍ የሞት ታናሽ ወንድም ይባል የለ አይደል? ሩሕ እስከ ቂያማ ቀን ድረስ በበርዘክ ይቆያሉ፣ “በርዘኽ” በሞትና በትንሳኤ መካከል ያለ ሁኔታ”Intermediate zone” ነው፦
23:99-100 አንዳቸውንም ሞት በመጣበት ጊዜ እንዲህ ይላል «ጌታዬ ሆይ! ወደ ምድረ ዓለም መልሱኝ፡፡ በተውኩት ነገር በጎን ሥራ ልሠራ እከጅላለሁና፡፡» ይህን ከማለት ይከልከል፡፡ እርስዋ እርሱ ተናጋሪዋ የኾነች ከንቱ ቃል ናት፡፡ *”ከስተፊታቸውም እስከሚቀሰቀሱበት ቀን ድረስ “ግርዶ” አለ”*፡፡ لَعَلِّىٓ أَعْمَلُ صَٰلِحًۭا فِيمَا تَرَكْتُ ۚ كَلَّآ ۚ إِنَّهَا كَلِمَةٌ هُوَ قَآئِلُهَا ۖ وَمِن وَرَآئِهِم بَرْزَخٌ إِلَىٰ يَوْمِ يُبْعَثُونَ

የሁሉም ሩሕ ወደ አላህ ቢመለስም ነገር ግን የሙስሉምና የ/#ካ/#ፊ/#ር /ሩሕ እንዳይገናኙ በመካከላቸው “በርዘኽ” አለ፤ የበርዘኽ ምሳሌ ምንድን ነው? የበርዘኽ ምሳሌ በባህር ውስጥ በጣፋጩና በጨው ባሕር መካከል ግርዶ መኖሩን ምሳሌ ይጠቀማል፦
55:19-20 ሁለቱን ባሕሮች የሚገናኙ ሲሆኑ ለቀቃቸው። *”እንዳይዋሐዱ በመካከላቸው “ጋራጅ” አለ፤ አንዱ ባንዱ ላይ ወሰን አያልፍም”*፤ بَيْنَهُمَا بَرْزَخٌۭ لَّا يَبْغِيَانِ
25:53 እርሱም ያ ሁለቱን ባሕሮች፣ አጐራብቶ የለቀቀ ነው፤ ይህ ጥምን የሚቆርጥ ጣፋጭ ነው፤ ይህም የሚመረግግ ጨው ነው፤ *”በመካከላቸውም ከመቀላቀል መለያንና የተከለለን “ክልል” ያደረገ ነው”*። وَهُوَ ٱلَّذِى مَرَجَ ٱلْبَحْرَيْنِ هَٰذَا عَذْبٌۭ فُرَاتٌۭ وَهَٰذَا مِلْحٌ أُجَاجٌۭ وَجَعَلَ بَيْنَهُمَا بَرْزَخًۭا وَحِجْرًۭا مَّحْجُورًۭا
27:61 *”በሁለቱ ባሕሮችም በጣፋጩና በጨው ባሕር መካከል ግርዶን ያደረገ”* ይበልጣልን? ወስ የሚያጋሩት? ከአላህ ጋር ሌላ አምላክ አለን? ግን አብዛኞቻቸው አያውቁም። أَمَّن جَعَلَ ٱلْأَرْضَ قَرَارًۭا وَجَعَلَ خِلَٰلَهَآ أَنْهَٰرًۭا وَجَعَلَ لَهَا رَوَٰسِىَ وَجَعَلَ بَيْنَ ٱلْبَحْرَيْنِ حَاجِزًا ۗ أَءِلَٰهٌۭ مَّعَ ٱللَّهِ ۚ بَلْ أَكْثَرُهُمْ لَا يَعْلَمُونَ

ስለ ውስጥ ተፈጥሮ የምናስተነትንበት ትምህርት “አት-ተሰዉፍ” الْتَّصَوُّف‎ ይባላል፤ የሚያስተነትነው ሰው “ሙተሰዉፍ” مُتَصَوُّف‎ ይባላል። “ሩሕ” ከጌታችን ነገር ናት፤ ስለ “ሩሕ” የተሰጠን ዕውቀት ጥቂት ብቻ ነው፦
17፥85 ከሩሕም ይጠይቁሃል፡፡ «ሩሕ ከጌታዬ ነገር ነው ከዕውቀትም ጥቂትን እንጂ አልተሰጣችሁም» በላቸው፡፡ وَيَسْـَٔلُونَكَ عَنِ ٱلرُّوحِ ۖ قُلِ ٱلرُّوحُ مِنْ أَمْرِ رَبِّى وَمَآ أُوتِيتُم مِّنَ ٱلْعِلْمِ إِلَّا قَلِيلًۭا

ከወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም
የበለጠ ለማወቅ
ጥሪያችን Tiriyachen
ወሰላሙ አለይኩም
የቁርኣን አሰባሰብ

ገቢር አንድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

75፥17 *በልብህ ውስጥ መሰብሰቡ እና ማንበቡ በእኛ ላይ ነውና*፡፡ إِنَّ عَلَيْنَا جَمْعَهُ وَقُرْآنَهُ

"ቁርኣን" قُرْءَان ማለት "በልብ ታፍዞ በምላስ የሚነበነብ መነባነብ" ማለት ሲሆን ይህም ቁርኣን አምላካችን አላህ በጂብሪል ለነብያችን"ﷺ" የሚያስቀራቸው ቂራኣት ነው፦
2፥252 *እነዚህ በእውነት በአንተ ላይ የምናነባቸው ሲኾኑ የአላህ አንቀጾች ናቸው*፤ تِلْكَ آيَاتُ اللَّهِ نَتْلُوهَا عَلَيْكَ بِالْحَ
87፥6 *ቁርኣንን በእርግጥ እናስነብብሃለን፤ አትረሳምም*፡፡ سَنُقْرِئُكَ فَلَا تَنسَىٰ
75:18 *ባነበብነውም ጊዜ ንባቡን ተከተል*። فَإِذَا قَرَأْنَاهُ فَاتَّبِعْ قُرْآنَه
75፥17 *በልብህ ውስጥ መሰብሰቡ እና ማንበቡ በእኛ ላይ ነውና*፡፡ إِنَّ عَلَيْنَا جَمْعَهُ وَقُرْآنَهُ

"ማንበቡ" ለሚለው ቃል የገባው "ቁርኣነሁ" َقُرْآنَهُ ሲሆን የግስ መደብ ነው፤ የስም መደቡ ደግሞ "ቁርኣን" قُرْءَان ነው፤ ይህ የሚነበበው አንቀጽ የአላህ የራሱ ንግግር ስለሆነ አላህ በመጀመሪያ መደብ "አያቱና" آيَاتُنَا ማለትም "አንቀጾቻችን" በማለት ይናገራል፦
46፥7 *በእነርሱም ላይ አንቀጾቻችን ግልጾች ኾነው በተነበቡ ጊዜ* እነዚያ እውነቱን በመጣላቸው ጊዜ የካዱትን «ይህ ግልጽ ድግምት ነው» አሉ፡፡ وَإِذَا تُتْلَىٰ عَلَيْهِمْ آيَاتُنَا بَيِّنَاتٍ قَالَ الَّذِينَ كَفَرُوا لِلْحَقِّ لَمَّا جَاءَهُمْ هَـٰذَا سِحْرٌ مُّبِينٌ

"ቃሪእ" قَارِئ‎ ማለት "በልብ አፍዞ በምላስ አነብናቢ"reciter" ማለት ነው፤ የቃሪእ ብዙ ቁጥር "ቁርራ" قُرَّاء ነው፤ አንድ ቃሪ የሆነ ሰው ቁርኣንን ሲቀራ አዳማጩ የሚያደምጠው የአላህን ንግግር ነው፦
7፥204 *ቁርኣንም በተነበበ ጊዜ እርሱን አዳምጡ፤ ጸጥም በሉ፤ ይታዘንላችኋልና*፡፡ وَإِذَا قُرِئَ الْقُرْآنُ فَاسْتَمِعُوا لَهُ وَأَنصِتُوا لَعَلَّكُمْ تُرْحَمُونَ
9፥6 ከአጋሪዎችም አንዱ ጥገኝነትን ቢጠይቅ *የአላህን ንግግር ይሰማ ዘንድ አስጠጋው*፡፡ وَإِنْ أَحَدٌ مِّنَ الْمُشْرِكِينَ اسْتَجَارَكَ فَأَجِرْهُ حَتَّىٰ يَسْمَعَ كَلَامَ اللَّهِ

አምላካችን አላህ ይህንን የእርሱን ንግግር ነብያችን"ﷺ" በሰዎች ላይ በዝግታ ላይ ኾነው ያነቡት ዘንድ ቀስ በቀስ አወረደው፦
17፥106 *ቁርኣንንም በሰዎች ላይ በዝግታ ላይ ኾነህ ታነበው ዘንድ ከፋፈልነው*፤ ቀስ በቀስ ማውረድንም አወረድነው፡፡ وَقُرْآنًا فَرَقْنَاهُ لِتَقْرَأَهُ عَلَى النَّاسِ عَلَىٰ مُكْثٍ وَنَزَّلْنَاهُ تَنزِيلًا

ይህ የአላህ ንግግር በሁለት መልኩ ተሰብስቧል፤ አንዱ በሰዎች ልብ ውስጥ በመታፈዝ ደረጃ ሲሆን ሁለተኛው በጽሑፍ በመጻፍ ደረጃ ነው፤ ይህንን ነጥብ በነጥብ ጥርስና ምላሱን እየነቀስን እንመልከት፦

ነጥብ አንድ
"ዚክር"
“ዚክር” ذِكْر የሚለው ቃል “ዘከረ” ذَكَرَ ማለትም “አስታወሰ” ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ማስታወስ”memorization" ማለት ነው፤ አምላካችን አላህ ቁርኣን በልብ እንዲታፈዝ አግርቶታል፦
54፥17 *ቁርኣንንም ለማስታወስ በእርግጥ አገራነው፡፡ አስታዋሽም አለን?* وَلَقَدْ يَسَّرْنَا ٱلْقُرْءَانَ لِلذِّكْرِ فَهَلْ مِن مُّدَّكِرٍۢ

አላህ፦ እኔ ቁርኣንን በቃላችሁ እንድትዙት ገር አርጌዋለው፤ ሙደኪር የት አለ? ብሎ ይጠይቃል፤ "ሙደኪር" مُّدَّكِرٍۢ ማለት "አስታዋሽ"Memorizer" ማለት ነው፤ አላህ ቁርአንን በቀልባችን እንድናፍዘው ብቻ ሳይሆን ስንቀራው በምላስ እንዲቀል እና በዐረቢኛው ቋንቋ እንድንገነዘበው አግርቶታል፦
12፥2 *እኛ ትገነዘቡ ዘንድ ዐረብኛ ቁርኣን ሲሆን በእርግጥ አወረድነው*፡፡ إِنَّآ أَنزَلْنَٰهُ قُرْءَٰنًا عَرَبِيًّۭا لَّعَلَّكُمْ تَعْقِلُونَ
44፥58 *ቁርአኑን በምላስህ ያገራነው ይገነዘቡ ዘንድ ነው*። فَإِنَّمَا يَسَّرْنَاهُ بِلِسَانِكَ لَعَلَّهُمْ يَتَذَكَّرُونَ
And indeed, We have eased the Qur’an in your tongue that they might be reminded.

“ዩሥራ” يُسْرَىٰ ማለት “ገር” ወይም “ቀላል” ማለት ሲሆን በልብ ለማስታወስ፣ በምላስ ላይ ለመቅራት፣ በቋንቋው ለመረዳት አግርቶታል። “ሊሣን” لِسَان የሚለው ቃል “ምላስ” ወይም “ቋንቋ” ማለት ነው፤ አላህ ቁርአንን በልባችን እንደሚሰበስበው ቃል ገብቶልናል፦
75፥17 *በልብህ ውስጥ መሰብሰቡ እና ማንበቡ በእኛ ላይ ነውና*፡፡ إِنَّ عَلَيْنَا جَمْعَهُ وَقُرْآنَهُ
ኢማም ሙስሊም: መጽሐፍ 4, ሐዲስ 166
ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ *"በአላህ አዘ ወጀል ንግግር፦ "በቁርኣን ንባብ ልትቸኩል ምላስህን በእርሱ አታላውስ" ነብዩ"ﷺ" ጂብሪል ወደ እሳቸው ሲያወርድ ምላሳቸውና ከንፈራቸውን ለማንበብ በማንበብ ያላውሱ ስለነበር ነው፤ ይህ ችግር አልፎ አልፎ ይታይ ነበርና፤ አላህ ተዓላ፦ "በቁርኣን ንባብ ልትቸኩል ምላስህን በእርሱ አታላውስ" የሚለውን አወረደ፤ "በልብህ ውስጥ መሰብሰቡና ማንበቡ በእኛ ላይ ነውና" ብሎ ሰበሰበው፤ በእርግጥም በልብህ ውስጥ እንድትቀራው እንጠብቀዋለን አንተም ትቀራዋለህ" ማለት ነው፤ "ባነበብነውም ጊዜ ካለቀ በኋላ ንባቡን ተከተል፣ ከዚያም ማብራራቱ በእኛ ላይ ነው" ማለት "በምላስህ ላይ ማስቀመጡ በእኛ ላይ ነው" ማለት ነው፤ ጂብሪል ወደ እርሳቸው በሚመጣ ጊዜ ዝም ይላሉ፤ ከእርሳቸው በተለየ ጊዜ አላህ ቃል እንደገባላቸው ይቀራሉ*። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ، فِي قَوْلِهِ عَزَّ وَجَلَّ ‏{‏ لاَ تُحَرِّكْ بِهِ لِسَانَكَ‏}‏ قَالَ كَانَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم إِذَا نَزَلَ عَلَيْهِ جِبْرِيلُ بِالْوَحْىِ كَانَ مِمَّا يُحَرِّكُ بِهِ لِسَانَهُ وَشَفَتَيْهِ فَيَشْتَدُّ عَلَيْهِ فَكَانَ ذَلِكَ يُعْرَفُ مِنْهُ فَأَنْزَلَ اللَّهُ تَعَالَى ‏{‏ لاَ تُحَرِّكْ بِهِ لِسَانَكَ لِتَعْجَلَ بِهِ‏}‏ أَخْذَهُ ‏{‏ إِنَّ عَلَيْنَا جَمْعَهُ وَقُرْآنَهُ‏}‏ إِنَّ عَلَيْنَا أَنْ نَجْمَعَهُ فِي صَدْرِكَ ‏.‏ وَقُرْآنَهُ فَتَقْرَأُهُ ‏{‏ فَإِذَا قَرَأْنَاهُ فَاتَّبِعْ قُرْآنَهُ‏}‏ قَالَ أَنْزَلْنَاهُ فَاسْتَمِعْ لَهُ ‏{‏ إِنَّ عَلَيْنَا بَيَانَهُ‏}‏ أَنْ نُبَيِّنَهُ بِلِسَانِكَ فَكَانَ إِذَا أَتَاهُ جِبْرِيلُ أَطْرَقَ فَإِذَا ذَهَبَ قَرَأَهُ كَمَا وَعَدَهُ اللَّهُ
በአሰባሰቡ ጉዳይ ላይ ሚሽነሪዎች የሚያነሱት የመርሳት ጉዳይ ነው፤ አንድ ነብይ ማንኛውም ሰው እንደሚዘነጋ ይዘነጋል፤ አደም፣ ሙሳ፣ ነብያችንም"ﷺ" ቢሆኑ ይረሳሉ፦
20፥115 ወደ አደምም ከዚህ በፊት ኪዳንን በእርግጥ አወረድን፡፡ *ረሳም*፡፡ ለእርሱም ቆራጥነትን አላገኘንለትም፡፡ وَلَقَدْ عَهِدْنَا إِلَىٰ آدَمَ مِن قَبْلُ فَنَسِيَ وَلَمْ نَجِدْ لَهُ عَزْمًا
18፥73 *«በረሳሁት ነገር አትያዘኝ፡፡ ከነገሬም ችግርን አታሸክመኝ»* አለው፡፡ قَالَ لَا تُؤَاخِذْنِى بِمَا نَسِيتُ وَلَا تُرْهِقْنِى مِنْ أَمْرِى عُسْرًۭا
ሱነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 5, ሐዲስ 1260
ዐብደላህ እንደተረከው፦ *"የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" ሶላት ላይ ይጨምሩ ወይም ይቀንሱ ነበር፤ ኢብራሂምም፦ "ይህ መወዛገብ ከእኔ ነው" አለ፤ እንዲህ አለ፦ "የአላህ መልእክተኛ ሆይ! አንዳንድ ጊዜ ሶላት ላይ ይጨምራሉን? እርሳቸውም፦ "እኔ ሰው ብቻ ነኝ፤ እናንተ እንደምትረሱ እኔም እረሳለው፤ ማንም ከረሳ ሁለት ረከዐት ይስገድ። ከዚያም ነብዩ"ﷺ" ተመልሰው ሁለቴ ሰገዱ*። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ، قَالَ صَلَّى رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ فَزَادَ أَوْ نَقَصَ - قَالَ إِبْرَاهِيمُ وَالْوَهْمُ مِنِّي - فَقِيلَ لَهُ يَا رَسُولَ اللَّهِ أَزِيدَ فِي الصَّلاَةِ شَىْءٌ قَالَ ‏ "‏ إِنَّمَا أَنَا بَشَرٌ أَنْسَى كَمَا تَنْسَوْنَ فَإِذَا نَسِيَ أَحَدُكُمْ فَلْيَسْجُدْ سَجْدَتَيْنِ وَهُوَ جَالِسٌ ‏"‏ ‏.‏ ثُمَّ تَحَوَّلَ النَّبِيُّ ـ صلى الله عليه وسلم ـ فَسَجَدَ سَجْدَتَيْنِ ‏.‏

እዚህ ሐዲስ ላይ ነብያችን"ﷺ" እኔ ሰው ብቻ ነኝ፤ እናንተ እንደምትረሱት እኔም እረሳለው" ያሉት ሶላት ላይ ረከዐትን መጨመርና መቀነስ እንጂ በፍጹም ስለ ቁርኣን መርሳት ሽታው እንኳን የለም። ሌላው ሂስ ይህ ሐዲስ ነው፦
ኢማም ቡኻርይ: መጽሐፍ 66, ሐዲስ 62
ዓኢሻህ እንደተረከችው፦ *"የአላህ መልእክተኛም"ﷺ" አንድ ሰው በሌሊት ሱራህን ሲቀራ እና እንዲህ ሲል ሰምተውታል፦ "የአላህ ምህረት በእርሱ ላይ ይሁን! የረሳኃትን እንዲህና እንዲያ የሚሉ ከሱራህ አንቀጽ አስታወሰኝ*። عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ سَمِعَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم رَجُلاً يَقْرَأُ فِي سُورَةٍ بِاللَّيْلِ فَقَالَ ‏ "‏ يَرْحَمُهُ اللَّهُ لَقَدْ أَذْكَرَنِي كَذَا وَكَذَا آيَةً كُنْتُ أُنْسِيتُهَا مِنْ سُورَةِ كَذَا وَكَذَا ‏"‌‏.‏

ሐዲሱ ላይ እረሳሁት የሚለው ሰው በሌሊት ሲቀራ የነበረው ሰው እንጂ እርሳቸው አይደሉም።
ሲቀጥል የሐዲሱ አርስት ላይ፦ "የቁርኣን መርሳት እና "እንዲህና እንዲያ የሚሉ አንቀጽ እረሳሁኝ" የሚል" بَابُ نِسْيَانِ الْقُرْآنِ وَهَلْ يَقُولُ نَسِيتُ آيَةَ كَذَا وَكَذَا
ተብሎ ተቀምጧል።
ሢሰልስ በሌሎች ሐዲሶች ላይ እንዲህና እንዲያ የሚሉ አናቅጽ የሚረሳው ማን እንደሆነ በስፋት ተብራርቷል፦
ኢማም ቡኻርይ: መጽሐፍ 66, ሐዲስ 63
ዐብደሏህ እንደተረከው፦ *"ነብዩም"ﷺ" አሉ፦ "ለምን ከእነርሱ አንዱ፦ "እንዲህና እንዲያ የሚሉ አናቅጽ እረስቻለው ይላል? በእርግጥም እረስቶታል*። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ، قَالَ قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ مَا لأَحَدِهِمْ يَقُولُ نَسِيتُ آيَةَ كَيْتَ وَكَيْتَ‏.‏ بَلْ هُوَ نُسِّيَ ‏"‌‏.‏
ኢማም ቡኻርይ: መጽሐፍ 66, ሐዲስ 54
ዐብደሏህ እንደተረከው፦ *"ነብዩም"ﷺ" አሉ፦ "አሳፋሪ ነገር ከእነርሱ አንዱ፦ "እንዲህና እንዲያ የሚሉ የቁርኣን አናቅጽ እረስቻለው" የሚል ነው፤ በእርግጥም እረስቶታል፤ ቁርኣንን ከግመል ፍጥነት ይልቅ ከሰው ልብ ያመልጣልና በደንብ ያዙት*። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ، قَالَ قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ بِئْسَ مَا لأَحَدِهِمْ أَنْ يَقُولَ نَسِيتُ آيَةَ كَيْتَ وَكَيْتَ بَلْ نُسِّيَ، وَاسْتَذْكِرُوا الْقُرْآنَ فَإِنَّهُ أَشَدُّ تَفَصِّيًا مِنْ صُدُورِ الرِّجَالِ مِنَ النَّعَمِ ‏

ሲያረብብ አምላካችን አላህ ቁርኣንን ለእርሳቸው አስቀርቶ እንደማይረሱት ቃል ገብቷል፦
87፥6 *ቁርኣንን በእርግጥ እናስነብብሃለን፤ አትረሳምም*፡፡ سَنُقْرِئُكَ فَلَا تَنسَىٰ
87፥7 *አላህ ከሻው በስተቀር*፡፡ እርሱ ግልጹን የሚሸሸገውንም ሁሉ ያውቃልና፡፡ إِلَّا مَا شَاءَ اللَّهُ ۚ إِنَّهُ يَعْلَمُ الْجَهْرَ وَمَا يَخْفَىٰ

"አላህ ከሻው በስተቀር" ማለት አላህ አንድን አንቀጽ በማስረሳት በሌላ አንቀጽ ከመለወጥ በስተቀር ማለት ነው፤ ይህ ነሥኽ ይባላል፤ “ነሥኽ” نسخ ማለት “ሽረት”abrogation” ማለት ሲሆን ይህም ሽረት አንደኛው “ናሢኽ” الناسخ ማለትም “ሻሪ አንቀጽ”Abrogator” ሲሆን ሁለተኛው “መንሡኽ” المنسوخ ማለትም “ተሻሪ አንቀጽ”Abrogated” ነው፦
2፥106 *ከአንቀጽ ብንለውጥ ወይም እርሷን ብናስረሳህ ከእርሷ የሚበልጥን ወይም ብጤዋን እናመጣለን*፤ አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ መኾኑን አታውቅምን? مَا نَنسَخْ مِنْ آيَةٍ أَوْ نُنسِهَا نَأْتِ بِخَيْرٍ مِّنْهَا أَوْ مِثْلِهَا ۗ أَلَمْ تَعْلَمْ أَنَّ اللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ

ነብያች"ﷺ" ሰው ናቸው ለጊዜው ቁርኣንን ይረሱ ነበር ቢባል እንኳን ጂብሪል በዓመት አንድ ጊዜ በረመዳን ወር ለዓመት ያክል ያስቀራቸውን ይደግምላቸው ነበር፤ እርሷቸውም ለዓመት የወረደውን በእርሱ ፊት ይቀሩ ነበር፤ ሊሞቱ ሲሉ ሁለቴ ደግሞላቸዋል፤ አንዱ ዓመታዊ ልማዱን ለመድገም ሲሆን ሁለተኛው አጠቃላይ ቁርኣንን ለማሳፈዝ ነው፦
ኢማም ቡኻርይ: መጽሐፍ 66, ሐዲስ 20
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ” እንዳለው፦ *“ጂብሪል ቁርኣንን በየዓመት አንዴ ለነብዩ"ﷺ" ይደግምላቸው ነበር፤ በሚሞቱበት ዓመት ግን ሁለቴ ደገመላቸው*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ كَانَ يَعْرِضُ عَلَى النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم الْقُرْآنَ كُلَّ عَامٍ مَرَّةً، فَعَرَضَ عَلَيْهِ مَرَّتَيْنِ فِي الْعَامِ الَّذِي قُبِضَ،
ኢማም ቡኻርይ: መጽሐፍ 61, ሐዲስ 63
ኢብኑ ዐባሥ"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ *"ነብዩ"ﷺ" ለሁሉም ሰው በጣም ለጋስ ነበሩ፤ የበለጠ በረመዷን ወር ጂብሪል በሚገናኛቸው ጊዜ ለጋስ ነበሩ፤ ሁልጊዜ በረመዳን ሌሊት ጂብሪል ሰላም በእርሱ ላይ ይሁን! ቁርኣንን ሊደግምላቸው ይገናኛቸው ነበር*። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ ـ رضى الله عنهما ـ قَالَ كَانَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم أَجْوَدَ النَّاسِ، وَأَجْوَدُ مَا يَكُونُ فِي رَمَضَانَ، حِينَ يَلْقَاهُ جِبْرِيلُ، وَكَانَ جِبْرِيلُ ـ عَلَيْهِ السَّلاَمُ ـ يَلْقَاهُ فِي كُلِّ لَيْلَةٍ مِنْ رَمَضَانَ، فَيُدَارِسُهُ الْقُرْآنَ
ኢማም ቡኻርይ: መጽሐፍ 66, ሐዲስ 19
ኢብኑ ዐባሥ"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ *"ነብዩ"ﷺ" በጣም ለጋስ ነበሩ፤ የበለጠ በረመዷን ወር ረመዷን እስኪያልቅ ድረስ ጂብሪል በሚገናኛቸው ጊዜ ለጋስ ነበሩ፤ የአላህ መልእክተኛም"ﷺ" ቁርኣንን ይቀሩለት ነበር። ጂብሪል በተገናኛቸው ጊዜ ከነፋስ ፍጥነት ይልቅ ለጋስ ነበሩ*። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ ـ رضى الله عنهما ـ قَالَ كَانَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم أَجْوَدَ النَّاسِ بِالْخَيْرِ، وَأَجْوَدُ مَا يَكُونُ فِي شَهْرِ رَمَضَانَ لأَنَّ جِبْرِيلَ كَانَ يَلْقَاهُ فِي كُلِّ لَيْلَةٍ فِي شَهْرِ رَمَضَانَ حَتَّى يَنْسَلِخَ يَعْرِضُ عَلَيْهِ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم الْقُرْآنَ، فَإِذَا لَقِيَهُ جِبْرِيلُ كَانَ أَجْوَدَ بِالْخَيْرِ مِنَ الرِّيحِ الْمُرْسَلَةِ‏.‏

ይህ በቃል ደረጃ"oral form" የተሰበሰበው ቁርኣን በሙተዋቲር ከነብያችን"ﷺ" ወደ ሶሐባቦች፣ ከሶሐባዎች ወደ ታቢኢይዎች፣ ከታቢኢይዎች ወደ አትባኡ ታቢኢይዎች እያለ በሙተዋቲር አስራ አራት ትውልድ አሳልፎ መጥቷል፤ “ሙተዋቲር” مُتَواتِر ማለት ቁርኣን ከአንድ ኢስናድ በላይ በጀመዓ የሚደረግ ዘገባ ነው። አላህ ቁርኣንን እራሱ አውርዶ ከኋላውም ከፊቱም ውሸት እንዳይመጣበት እራሱ በአማኞች ልብ እንዲሰበሰብ ገር በማድረግ እና በምላስ እንዲቀራ ገር በማድረግ ይጠብቀዋል፦
15፥9 *እኛ ቁርኣንን እኛው አወረድነው፡፡ እኛም ለእርሱ ጠባቂዎቹ ነን*፡፡ إِنَّا نَحْنُ نَزَّلْنَا ٱلذِّكْرَ وَإِنَّا لَهُۥ لَحَٰفِظُونَ
41፥42 *ከኋላውም ከፊቱም ውሸት አይመጣበትም*፡፡ ጥበበኛ ምስጉን ከኾነው ጌታ የተወረደ ነው፡፡ لَّا يَأْتِيهِ ٱلْبَٰطِلُ مِنۢ بَيْنِ يَدَيْهِ وَلَا مِنْ خَلْفِهِۦ ۖ تَنزِيلٌۭ مِّنْ حَكِيمٍ حَمِيدٍۢ

ኢንሻላህ በገቢር ሁለት በጽሑፍ ደረጃ የተሰበሰበውን ሙስሐፍ ጥልልና ጥንፍፍ አርገን እናያለን...

ከወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም


ጥሪያችን በሁሉም ቦታ!
Follow us on:👇🏻
Telegram ፦ https://www.tg-me.com/tiriyachen
Website ፦ https://tiriyachen.org
Instagram ፦ https://bit.ly/3eVixKv
TikTok ፦ https://www.tiktok.com/@tiriyachen

ወሰላሙ አለይኩም
2025/07/05 21:34:18
Back to Top
HTML Embed Code: