Telegram Web Link
መለኮታዊ እግር

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፤

68፥42 እግር የሚገለጥበትን ከሓዲዎች ወደ መስገድም የሚጠሩበትን እና የማይችሉበት ቀን አስታውስ፡፡ يَوْمَ يُكْشَفُ عَن سَاقٍۢ وَيُدْعَوْنَ إِلَى ٱلسُّجُودِ فَلَا يَسْتَطِيعُونَ

“ሣቅ” سَاق ማለት “እግር” ማለት ነው፤ አምላካችን አላህ የትንሳኤ ቀን ከሓዲዎችን ወደ መስገድ የሚጠራበት እና የማይችሉበት ቀን ነው፤ በተቃራኒው ጌታችን እግሩን ይገልጣል፤ ሁሉም ምእመናንና ምእመናት ይሰግዱለታል፤ ታላቁ ሙፈሲር ኢብኑ ከሲር”ረሒመሁላህ” የኢማም ቡኻርይን ሐዲስ ይዞ ይህንን አንቀጽ በዚህ መልኩ ፈስሮታል፦
ኢማም ቡኻርይ : መጽሐፍ 65, ሐዲስ 4919
አቢ ሠዒድ”ረ.ዐ.” እንደተረከው፤ ነብዩ”ﷺ” እንዲህ ሲሉ ሰማው፦ “ጌታችን እግሩን ይገልጣል፤ ሁሉም ምእመናንና ምእመናት ይሰግዱለታል፤ عَنْ أَبِي سَعِيدٍ ـ رضى الله عنه ـ قَالَ سَمِعْتُ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم يَقُولُ ‏ “‏ يَكْشِفُ رَبُّنَا عَنْ سَاقِهِ فَيَسْجُدُ لَهُ كُلُّ مُؤْمِنٍ وَمُؤْمِنَةٍ،

ሚሽነሪዎች ይህንን እሳቤ ይዘው የአላህ እግር ልክ እንደ ፍጡራን እግር ፍጥረታዊ እግር ለማስመሰል ሲዳዱ ይታያል፤ ይህ ስሁት ሙግት ልከክልህ እከክልኝ በሚል ቁጭት ነው፤ ምክንያቱም ኢየሱስ ፍጥረታዊ እግር ስላለው የግድ አላህንም እንደዛ ለማድረግ ነው፤ ሲጀመር የኢየሱስ እግር አካላዊና ፍጥረታዊ እግር ማለትም ስጋ፣ አጥንት፣ ነርቭ፣ ጅማት እና ጡንቻ ያለው ነው፦
ሉቃስ 7፥38 በስተ ኋላውም *በእግሩ* አጠገብ ቆማ እያለቀሰች በእንባዋ *እግሩን* ታርስ ጀመረች፥ በራስ ጠጕርዋም ታብሰው *እግሩንም* ትስመው ሽቱም ትቀባው ነበረች።
ሉቃስ 7፥44 ወደ ሴቲቱም ዘወር ብሎ ስምዖንን እንዲህ አለው፦ ይህችን ሴት ታያለህን? እኔ ወደ ቤትህ ገባሁ፥ ውኃ ስንኳ *ለእግሬ* አላቀረብህልኝም፤ እርስዋ ግን በእንባዋ *እግሬን* አራሰች በጠጕርዋም አበሰች።

ሲቀጥል ይህ እግር በቁመት የሚያድግ ፍጥረታዊ እግር ነው፦
ሉቃስ 2፥52 ኢየሱስም ደግሞ በጥበብና *በቁመት* በሞገስም በእግዚአብሔርና በሰው ፊት *ያድግ* ነበር።

አስቡት የጫማ ቁጥሩ 30, 35, 40, 41, 42 እያለ የሚተልቀው እግሩ ስለሚያድግ ነው።
ሲሠልስ የኢየሱስ እግር እናቱ ማህጸን ውስጥ ከመፈጠሩ በፊት የኢየሱስ እግርን የፈጠረ ፈጣሪ የእራሱ መለኮታዊ፣ አምላካዊ እና መንፈሳዊ እግር አለው፦
ኢሳይያስ 66፥1 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሰማይ ዙፋኔ ነው፥ ምድርም *የእግሬ* መረገጫ ናት፤
መዝሙር 99፥5 አምላካችንን እግዚአብሔርን ከፍ ከፍ አድርጉት፥ ቅዱስ ነውና ወደ *እግሩ* መረገጫ ስገዱ።
ኢሳይያስ 60፥13 *የእግሬንም* ስፍራ አከብራለሁ።
ናሆም 1፥3 እግዚአብሔር በወጀብና በዐውሎ ነፋስ ውስጥ መንገድ አለው፥ ደመናም *የእግሩ* ትቢያ ነው።

ፈጣሪ የሚመስለው ምንም ነገር ከሌለ የእርሱን መለኮታዊ እግር ከፍጥረታዊ እግር ጋር ማመሳሰል ነውር ነው፦
ኢዮብ23፥13 እርሱ ግን ብቻውን ነው፤ *እርሱንስ የሚመስለው* ማን ነው?
ኢሳይያስ 40፥18 እንግዲህ *ያህዌህን በማን ትመስሉታላችሁ? ወይስ በምን ምሳሌ ታስተያዩታላችሁ?*

የፈጣሪ ባህርይ ከፍጡር ባህርይ ጋር ማመሳል ነውር ከሆነ የአላህንም መለኮታዊና አምላካዊ እግር ከፍጥረታዊና ከአካላዊ እግር ጋር ማመሳሰል ነውር ነው፤ አላህ የሚመስለው ምንም ማንም የለም፤ ለእርሱ አንድም ቢጤ የለውም፦
42፥11 *የሚመስለው ምንም ነገር የለም*፡፡ እርሱም ሰሚው ተመልካቹ ነው፡፡ لَيْسَ كَمِثْلِهِۦ شَىْءٌۭ ۖ وَهُوَ ٱلسَّمِيعُ ٱلْبَصِيرُ
112፤4 *ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም*፡፡ وَلَمْ يَكُن لَّهُۥ كُفُوًا أَحَدٌۢ

ከወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም

የበለጠ ለማወቅ
ጥሪያችን Tiriyachen

ወሰላሙ አለይኩም
#ጥሪያችን
አካል እና መንፈስ

ክፍል አንድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

መግቢያ
በማህበራዊ ሚድያ ላይ፦ አላህ ምንድን ነው? አካል ወይስ መንፈስ የሚል አለሌ እና ቅሪላ ጥያቄ ይጠየቃል፤ ለዚህ አንኮላ እና እንኩቶ ቃላት መልሳችን አላህ ምንድን ነው? ብለን ስንጠየቅ ህላዌን ታሳቢ እና ዋቢ ያደረገ ነው፤ “ዛት” ذات ማለት “ህላዌ”essence” ማለት ሲሆን “ምንድን” ተብሎ በመጠይቅ ተውላጠ-ስም የሚቀመጥ “ክዋኔ-ምንነት” ሲሆን የቅዋሜ-ማንነት መሰረት ነው።
በስነ-ኑባሬ ጥናት”ontology” ውስጥ “ኢስም” ٱسْم ማለትም “ስም” ባህርይ የተሰየመበት መጠሪያ ሲሆን “ሲፋ” صِفَة ማለትም “ባህርይ” ደግሞ የህላዌ መግለጫ“description” ነው፣ አላህ ምንድን ነው? ለሚለው የህላዌ ጥያቄ መልሱን የምናገኘው በባህርይ ነው፣ አላህ ምንድን ነው ለሚለው ጥያቄ የህላዌ መገለጫ የሆኑትን ባህርያት እራሱ አላህ በተከበረው ከሊማ ይነግረናል፤ አሏህ ﺍﻟﻠﻪ ማለት፦ አር- ረህማን ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ነው፣ አር-ረሂም ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ ነው፣ አል-ሙልክ ﺍﻟﻤﻠﻚ ነው፣ አል-ቅዱስ ﺍﻟﻘﺪﻭﺱ ነው፣ አስ-ሰላም ﺍﻟﺴﻼﻡ ነው፣ አል-ኻሊቅ ﺍﻟﺨﺎﻟﻖ ነው፣ አል-ዓሊም ﺍﻟﻌﻠﻴﻢ ነው እያልን ባህርያት የተሰየሙበትን መልካም ስሞቹን እንዘረዝራለን፤ አላህ ከፍጡራኑ ጋር የማይመሳሰል “አስማኡል ሁስና” الْأَسْمَاءُ الْحُسْنَىٰ ማለትም “መልካም ስሞች” አሉት፦
59:24 እርሱ አላህ ፈጣሪው ከኢምንት አስገኚው ቅርጽን አሳማሪው ነው፤ ለእርሱ “መልካም ስሞች” الْأَسْمَاءُ الْحُسْنَىٰ አሉት፤
20:8 አላህ ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም ለእርሱ “መልካም የሆኑ ስሞች” الْأَسْمَاءُ الْحُسْنَىٰ አሉት።
17:110 ፦አላህን ጥሩ፤ ወይም አልረሕማንን ጥሩ፤ ማንኛውንም ብትጠሩ፣ መልካም ነው፤ ለእርሱ “መልካም ስሞች” الْأَسْمَاءُ الْحُسْنَىٰ አሉትና በላቸው፤
7:180 ለአላህም “መልካም ስሞች” الْأَسْمَاءُ الْحُسْنَىٰ አሉት፤ ስትጸልዩ በርሷም ጥሩት እነዚያንም ስሞቹን የሚያጣምሙትን ተውዋቸው፤

ከላይ ለቀረበው የሽሙጥና የለበጣ ጥያቄ ይህ ምላሽ በቂ ቢሆንም ሞኝ የያዘው ፈሊጥ ውሻ የደፋው ሊጥ ይባላልና አላህ አካል እና መንፈስ ነውን? ተብሎ ለተጠየቀው ቅጥ አንባሩ ለጠፋበት ጥያቄ አካል እና መንፈስ ምን እንደሆኑ ነጥብ በነጥብ ቅድሚያ እናያለን፦

ነጥብ አንድ
“አካል”
“ጀሰድ” جَسَد”የሚለው ቃል “አካል”body” ማለት ሲሆን ፈሳሽ”liquid”፣ ጠጣር”solid” እና ጋዝ”gas” ነው፤ ይህም ግዙፍ ነገር ነው፤ አለቃ ኪዳነ-ወልድ ክፍሌ 1948 መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ላይ፦ “አካል” ማለት አፍአዊ ወይም ውጫዊ ትርጉሙ ጀማትና አጥንትን የያዘ ተክለ-ሰውነት ወይም ገላ አሊያም ግዝፈተ-ስጋ”body” ማለት ነው፤ ይህንን ሃሳብ ደስታ ተክለ-ወልድ መዝገበ ቃላት ሆነ ከሳቴ-ብርሃን ተሰማ መዝገበ ቃላት ተመሳሳይ ፍቺ አስቀምጠዋል፤ “ጀሰድ” የሚለው ቃል በቁርአን ውስጥ 4 ጊዜ ተጠቅሷል፤ ይህም ቃል በሁለት ይከፈላል፦
አንደኛው ህያው አካል ነው፤ ህያው አካል ማለት ሩህ ያለው ማለት ሲሆን የሚበላ እና የሚጠጣ ነው፦
21፥8 ምግብን የማይበሉ “አካልም” አላደረግናቸውም፡፡ ዘውታሪዎችም አልነበሩም وَمَا جَعَلْنَٰهُمْ جَسَدًۭا لَّا يَأْكُلُونَ ٱلطَّعَامَ وَمَا كَانُوا۟ خَٰلِدِينَ ፡፡

ሁለተኛው ደግሞ ግኡዝ አካል ነው፤ ግኡዝ አካል ማለት ሩህ የሌለው ማለት ነው፦
7፥148 የሙሳም ሕዝቦች ከእርሱ መኼድ በኋላ ከጌጦቻቸው ወይፈንን “”አካልን”” ለእርሱ ማግሳት ያለውን ያዙ፡፡ እርሱ የማያናግራቸው መንገድንም የማይመራቸው መኾኑን አይመለከቱምን? አምላክ አድርገው ያዙት፡፡ በዳዮችም ኾኑ وَٱتَّخَذَ قَوْمُ مُوسَىٰ مِنۢ بَعْدِهِۦ مِنْ حُلِيِّهِمْ عِجْلًۭا جَسَدًۭا لَّهُۥ خُوَارٌ ۚ أَلَمْ يَرَوْا۟ أَنَّهُۥ لَا يُكَلِّمُهُمْ وَلَا يَهْدِيهِمْ سَبِيلًا ۘ ٱتَّخَذُوهُ وَكَانُوا۟ ظَٰلِمِينَ ፡፡
20፥88 ለእነሱም “”አካል”” የኾነ ጥጃን ለእርሱ መጓጎር ያለውን አወጣላቸው፡፡ ተከታዮቹ «ይህ አምላካችሁ የሙሳም አምላክ ነው ግን ረሳው» አሉም فَأَخْرَجَ لَهُمْ عِجْلًۭا جَسَدًۭا لَّهُۥ خُوَارٌۭ فَقَالُوا۟ هَٰذَآ إِلَٰهُكُمْ وَإِلَٰهُ مُوسَىٰ فَنَسِىَ ፡፡
38፥34 ሱለይማንንም በእርግጥ ፈተንነው፡፡ በመንበሩም ላይ “አካልን” ጣልን፡፡ ከዚያም በመጸጸት ተመለሰ وَلَقَدْ فَتَنَّا سُلَيْمَٰنَ وَأَلْقَيْنَا عَلَىٰ كُرْسِيِّهِۦ جَسَدًۭا ثُمَّ أَنَابَ ፡፡

ስለዚህ በኢስላም አላህ ህያው ወይም ግኡዝ አካል የለውም፤ “አካል” ፍጡር ነውና። ወደ ባይብል ስንመጣ በብሉይ ግሪክ ሰፕቱጀንት እና በአዲስ ግሪክ ኮይኔ ውስጥ “ሶማ” σῶμα ማለት “አካል” ማለት ሲሆን ሌንስ የያዘ አይን፣ ሃመር የያዘ ጆሮ፣ እግር ወዘተ የያዘው የብልት ጥርቅም እንደሆነ ያስቀምጣል፦
1ኛ ቆሮንቶስ 12፥14-16 “አካል” ብዙ ብልቶች እንጂ አንድ ብልት አይደለምና። እግር። እኔ እጅ አይደለሁምና የአካል ክፍል አይደለሁም ብትል፥ ይህን በማለትዋ የአካል ክፍል መሆንዋ ይቀራልን? ጆሮም። እኔ ዓይን አይደለሁምና የአካል ክፍል አይደለሁም ቢል፥ ይህን በማለቱ የአካል ክፍል መሆኑ ይቀራልን? አካል ሁሉ ዓይን ቢሆን መስማት ወዴት በተገኘ? ሁሉም መስማት ቢሆን ማሽተት ወዴት በተገኘ?።
ዘሌዋውያን 21፥18 ዕውር፥ ወይም አንካሳ፥ ወይም አፍንጫ ደፍጣጣ፥ ወይም ትርፍ “አካል” ያለው፥
ዘዳግም 14፥1-2 ስለ ሞተው ሰው “አካላችሁን” አትንጩ፥
መዝሙር 139፥15-136 እኔ በስውር በተሠራሁ ጊዜ፥ “አካሌም” በምድር ታች በተሠራ ጊዜ፥ አጥንቶቼ ከአንተ አልተሰወሩም። ያልተሠራ “አካሌን” ዓይኖችህ አዩኝ፤ የተፈጠሩ ቀኖቼ ሁሉ አንድ ስንኳ ሳይኖር በመጽሐፍህ ተጻፉ።

የሚገርመው የባይብል አምላክ መንፈስ ነው እየተባለ ይዶስኮርለት እንጂ አካል የያዘውን ላባና ክንፍ፣ ከንፈርና ምላስ፣ ዓይንና ቅንድብ፣ አፍንጫና አፍ እና እግር ከነጫማው እንዳለው ተቀምጧል።
ላባና ክንፍ፦
መዝሙር 91፥4 *በላባዎቹ ይጋርድሃል፥ በክንፎቹም* በታች ትተማመናለህ
ከንፈርና ምላስ፦
ኢሳይያስ 30፥27 እነሆ፥ የእግዚአብሔር ስም ከሚነድድ ቍጣ ከሚትጐለጐልም ጢስ ጋር ከሩቅ ይመጣል፤ *ከንፈሮቹም* ቍጣን የሞሉ ናቸው፥ *ምላሱም* እንደምትበላ እሳት ናት፤
ዓይንና ቅንድብ፦
መዝሙር 11፥4 እግዚአብሔር በተቀደሰው መቅደሱ ነው፤ እግዚአብሔር፥ ዙፋኑ በሰማይ ነው፤ “ዓይኖቹ” ወደ ድሃ ይመለከታሉ፥ *ቅንድቦቹም* የሰው ልጆችን ይመረምራሉ።
አፍንጫና አፍ፦
ዘጸአት 15፥8 *በአፍንጫህ* እስትንፋስ ውኆች ተከመሩ፥
መዝሙር 33:6 በእግዚአብሔር ቃል ሰማዮች ጸኑ፥ ሠራዊታቸውም ሁሉ *”በአፉ”* እስትንፋስ፤”
ክንድና ብብት፦
ኢሳይያስ 40፥11 መንጋውን እንደ እረኛ ያሰማራል፥ ጠቦቶቹን *በክንዱ ሰብስቦ በብብቱ* ይሸከማል፥ የሚያጠቡትንም በቀስታ ይመራል።
እግርና ጫማ፦
ሕዝቅኤል 43:7 እንዲህም አለኝ። የሰው ልጅ ሆይ፥ በእስራኤል ልጆች መካከል ለዘላለም የምቀመጥበት የዙፋኔ ስፍራና “የእግሬ ጫማ” መረገጫ ይህ ነው።
መንፈስ ማለት የማይታይ ነው ከተባለ የእስራኤል አምላክን ሰዎች አይተውታል ይለናል፦
ዘጸአት 24:10 የእስራኤልንም አምላክ “”አዩ””፤ “ከእግሩም” በታች እንደ ሰማይ መልክ የሚያበራ እንደ ብሩህ ሰንፔር ድንጋይ የሚመስል ወለል ነበረ።

አይን፣ እጅ፣ እግር፣ ጆሮ ስጋዊ ሳይሆን መለኮታዊ ነው ይሉናል፦
ኢዮብ 10፥4 በውኑ የሥጋ ዓይን አለህን?
ወይስ ሰው እንደሚያይ ታያለህን?

አየህ አይን፣ እጅ፣ እግር፣ ጆሮ ስጋዊ ሳይሆን መለኮታዊ ከሆነ ፈጣሪ አፍአዊ ወይም ውጫዊ ትርጉሙ ያለው ጀማትና አጥንትን የያዘ ተክለ-ሰውነት ወይም ገላ አሊያም ግዝፈተ-ስጋ”body” የለውም ማለት ነው። ነገር ግን ውሳጣዊ ወይም ውስጣዊ ትርጉም ቅዋሜ-ማንነት እገሌ ተብሎ በእኔነት፣ “በአንተነት”፣ “በእርሱነት” የሚገለጥ ነባቢ ባለቤት”person” ብሎ አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ አሌፍ 218 ገፅ 218 ላይ እና በተመሳሳይ አለቃ ደስታ ተክለ ወልድ አሌፍ 97 ገፅ 97 ላይ ያስቀመጠውን ነባቢ ማንነት ፈጣሪ አለው፤ ፍፁም ገፅ ማለትም መታወቂያ”identity” ፍፁም መልክ ማለትም መለያ ወይም መገለጫ”intity” አለው። ይህ በኢስላም “ሸኽስ” شخص ይባላል፤ “ሸኽስ” ዛትን “በእኔነት” ወይም “በማንነት” የሚገልጥ ሲሆን “ማን” ተብሎ በመጠይቅ ተውላጠ-ስም የሚቀመጥ “ቅዋሜ-ማንነት” አለው፤ “ሸኽስ” የሚለውን ቃል በግሪክ “ፕሮሶፓን” πρόσωπον ሲሆን ፐርሰን”person” የሚለው የኢንግሊሹ ቃል እና ፐርሶና የሚለው የላቲኑ ቃል ከግሪኩ ፕሮሶፓን የመጣ ሲሆን “ቅዋሜ-ማንነት” ማለት ነው፤ ይህንን ቃል በአማርኛ ቃል ሲጠፋለት አለቃ ኪዳነ-ወልድ ክፍሌ መዝገበ ቃላት፣ ደስታ ተክለ-ወልድ መዝገበ ቃላት ሆነ ከሳቴ-ብርሃን ተሰማ መዝገበ ቃላት “አካል” ብለውታል፤።
“ሸኽስ” የሚለው ቃል “አሐድ” ለሚለው ቃል ተለዋዋጭ ነው፤ “አሐድ” أَحَد የሚለው ቃል “ላ “አሐደ” አግየሩ ሚነልላህ” لاَ أَحَدَ أَغْيَرُ مِنَ اللَّهِ ተብሎ በኢማም ቡኻሪይ ላይ ሲዘገብ “ሸኽስ” شخص ደግሞ “ወላ “ሸኽሰ” አግየሩ ሚነልላህ” وَلاَ شَخْصَ أَغْيَرُ مِنَ اللَّهِ ተብሎ በኢማም ሙስሊም ላይ በተመሳሳይ ሰዋስው ተዘግቧል፦
ኢማም ቡኻሪይ መፅሐፍ 65, ሐዲስ 4637
لاَ أَحَدَ أَغْيَرُ مِنَ اللَّهِ، فَلِذَلِكَ حَرَّمَ الْفَوَاحِشَ مَا ظَهَرَ مِنْهَا وَمَا بَطَنَ، وَلاَ أَحَدَ أَحَبُّ إِلَيْهِ الْمِدْحَةُ مِنَ اللَّهِ، فَلِذَلِكَ مَدَحَ نَفْسَهُ
ኢማም ሙስሊም መፅሐፍ 19, ሐዲስ 22
وَلاَ شَخْصَ أَغْيَرُ مِنَ اللَّهِ وَلاَ شَخْصَ أَحَبُّ إِلَيْهِ الْعُذْرُ مِنَ اللَّهِ مِنْ أَجْلِ ذَلِكَ بَعَثَ اللَّهُ الْمُرْسَلِينَ مُبَشِّرِينَ وَمُنْذِرِينَ وَلاَ شَخْصَ أَحَبُّ إِلَيْهِ الْمِدْحَةُ مِنَ اللَّهِ مِنْ أَجْلِ ذَلِكَ وَعَدَ اللَّهُ الْجَنَّةَ

ስለዚህ አላህ የራሱ ዛትን “በእኔነት” ወይም “በማንነት” የሚገልጥ፣ “ማን” ተብሎ በመጠይቅ ተውላጠ-ስም የሚቀመጥ “ቅዋሜ-ማንነት” አለው፤ የእርሱ እውቀት፣ እይታ፣ መስማት እና መናገር ከፍጡራን ጋር የማይመሳሰል መለኮዊዉ እንጂ ሰዋዊ አይደለም፦
60:1 #እኔ የምትደብቁትንና የምትገልጹትን #የማውቅ ስሆን ወደ እነርሱ በፍቅር ትመሣጠራላችሁ?፤
34:11 #እኔ የምትሠሩትን ነገር ሁሉ ተመልካች ነኝና።
2:186 ባሮቼም ከእኔ በጠየቁህ ጊዜ፡- #እኔ ቅርብ ነኝ፡፡ የለማኝን ጸሎት በለመነኝ ጊዜ #እቀበለዋለሁ፡፡ ስለዚህ ለኔ ይታዘዙ፤ በእኔም ይመኑ፤ እነርሱ ሊመሩ ይከጀላልና፡፡
21:92 “#እኔም” ጌታችሁ #ነኝ እና “አምልኩኝ”።

አላህ ዛት እንዳለው በሐዲስ ተገልጿል፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 60, ሐዲስ 38:
አቢ ሁረይራህ”ረዳየሏሁ ዐንሁ” እንደተረከው፦ “ኢብራሒም አልቀጠፈም በሶስት ጉዳይ ላይ ቢሆን እንጂ፤ ሁለቱ ለአላህ “ዛት” ذَاتِ ብሎ፦ እኔ አሞኛል እና እኔ አልሰራሁም ግን ትልቁ ጣዖት ይህንን ሰራ ባለበት ጊዜ ሲሆን፤ ሶስተኛው እርሱ እና ሳራ በተጓዙ ጊዜ عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ ـ رضى الله عنه ـ قَالَ لَمْ يَكْذِبْ إِبْرَاهِيمُ ـ عَلَيْهِ السَّلاَمُ ـ إِلاَّ ثَلاَثَ كَذَبَاتٍ ثِنْتَيْنِ مِنْهُنَّ فِي ذَاتِ اللَّهِ عَزَّ وَجَلَّ، قَوْلُهُ ‏{‏إِنِّي سَقِيمٌ ‏}‏ وَقَوْلُهُ ‏{‏بَلْ فَعَلَهُ كَبِيرُهُمْ هَذَا‏}‏، وَقَالَ بَيْنَا هُوَ ذَاتَ يَوْمٍ وَسَارَةُ إِذْ أَتَى عَلَى جَبَّارٍ مِنَ الْجَبَابِرَةِ فَقِيلَ لَهُ إِنَّ هَا هُنَا رَجُلاً مَعَهُ امْرَأَةٌ مِنْ أَحْسَنِ النَّاسِ ።

ኢንሻላህ ስለ መንፈስ በክፍል ሁለት ይቀጥላል….

ከወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም

የበለጠ ለማወቅ
ጥሪያችን Tiriyachen
https://www.facebook.com/tiriyachen
ወሰላሙ አለይኩም
እንኳን ለ1446ኛው የዒድ አል‐አድሃ አረፋ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።
በእኔም በእናንተም ምን እንደሚሠራም ዐላውቅም

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

43፥43 ያንንም ወደ አንተ የተወረደልህን አጥብቀህ ያዝ፡፡ *አንተ በቀጥተኛው መንገድ ላይ ነህና*፡፡ فَٱسْتَمْسِكْ بِٱلَّذِىٓ أُوحِىَ إِلَيْكَ ۖ إِنَّكَ عَلَىٰ صِرَٰطٍۢ مُّسْتَقِيمٍۢ

መቼም ሚሽነሪዎች ቆዳዬ ጠበበኝ ብለው የሚያላዝኑት ነገር ቢገርምም የአገራችን ሰዎች ደግሞ እነርሱን በቁርኣን ላይ የሚያነሷቸውን ኂሶች እንደ ገደል ማሚቱ ሲያስተጋቡ ማየት ያስደምማል፤ ሚሽነሪዎች እራሳቸው መጽሐፍት ላይ ያሉትን አበሳና አሳር እንደማይወጡት ስለሚያውቁት በጊዜ ቁርኣን ላይ መደበቁን መርጠዋል፤ የእኛ ጥያቄ ግን ተከድኖ ይብሰል ከተባለ ይኸው ጊዜ አስቆጠረ፤ እኛም ጠቃሚውን ነገር ከማይጠቅም ነገር ጋር ሳይሆን ጠቃሚውን ነገር ከሚጐዳ ነገር ጋር እያነጻጸርነው እንገኛለን። መቼም ስላቅና ፈሊጥ በአሉታዊ ሳይሆን በአውንታዊ ተመልክተን እዳው ገብስ ስለሆነ ሰው እንዲማርበት መልስ እንሰጣለን፤ ወደ ጉዳዩ ስንገባ ነቢያችን”ﷺ” ወሕይ ከመጣላቸው በኃላ በቀጥተኛው መንገድ ላይ እንደሆኑ አምላካችን አላህ ተናግሯል፦
43፥43 ያንንም ወደ አንተ የተወረደልህን አጥብቀህ ያዝ፡፡ *አንተ በቀጥተኛው መንገድ ላይ ነህና*፡፡ فَٱسْتَمْسِكْ بِٱلَّذِىٓ أُوحِىَ إِلَيْكَ ۖ إِنَّكَ عَلَىٰ صِرَٰطٍۢ مُّسْتَقِيمٍۢ

አላህ ነቢያችን”ﷺ” በቀጥተኛ መንገድ መሆናቸው ብቻ ሳይሆን ጀነት ገብተውም በጀነት ያለው ፀጋ እንደሚሰጣቸው ቃል ገብቶላቸዋል፦
108፥1 *እኛ በጣም ብዙ በጎ ነገሮችን ሰጠንህ*፡፡ إِنَّآ أَعْطَيْنَٰكَ ٱلْكَوْثَرَ

በዚህ አንቀጽ ላይ “በጎ ነገር” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ከውሰር” كَوْثَر ሲሆን በጀነት ውስጥ ያለ ከወተት የነጻና ከማር የጣፈጠ ወንዝ ነው፤ ይህ ከውሰር ለነቢያችን”ﷺ” የተሰጠ ዋስትና ነው፦
ጃምዒ አት-ተርሚዚ መጽሐፍ 47, ሐዲስ 3684
አነስ ኢብኑ ማሊክ እንደተረከው፦ “እኛ ከውሰርን ሰጠንህ” ነቢዩም”ﷺ” አሉ፦ *"በጀነት ወንዝ ነው፤ በጀነት ወንዝ ድንኳኖቹ ከድንጋይ የተሠሩ አየው፤ ጂብሪል ሆይ! ምንድን ነው? አልኩት፤ እርሱም ከውሰር ነው፤ አላህ ለአንተ የሰጠህ” አለኝ"*።
عَنْ أَنَسٍ ‏:‏ ‏(‏ إناَّ، أَعْطَيْنَاكَ الْكَوْثَرَ ‏)‏ أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏”‏ هُوَ نَهْرٌ فِي الْجَنَّةِ ‏”‏ ‏.‏ قَالَ فَقَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ رَأَيْتُ نَهْرًا فِي الْجَنَّةِ حَافَتَاهُ قِبَابُ اللُّؤْلُؤِ قُلْتُ مَا هَذَا يَا جِبْرِيلُ قَالَ هَذَا الْكَوْثَرُ الَّذِي قَدْ أَعْطَاكَهُ اللَّهُ ‏”‏ ‏.‏ قَالَ أَبُو عِيسَى هَذَا حَدِيثٌ حَسَنٌ صَحِيحٌ


ነቢያችን”ﷺ” ጀነት አይደለም መግባት በተጨማሪ የጀነት ጀረጃቸውንም አላህ እንደነገረን ከላይ ያለው አንቀጽ በወፍ በረር ለቅምሻ ያክል በቂ ነው፤ ታዲያ ይህ ዋስትና እያለ አላህ ነቢያችንን”ﷺ” “በእኔም በእናንተም ምን እንደሚሠራም ዐላውቅም” በል ሲላቸው እውን ሚሽነሪዎች እንደሚሉት "ወደ ፊት የት እንደምንገባ ዐናውቅም" በል ማለታቸውን ያሳያልን? ይህንን የተንሸዋረረና የተወላገደ መረዳት ጥንልልና ጥንፍፍ ባለ መልኩ እንየው፦
46፥9 *ከመልክተኞች ብጤ የሌለኝ አይደለሁም፤ በእኔም በእናንተም ምን እንደሚሠራም ዐላውቅም፤ ወደ እኔ የሚወረደውን እጅግ ሌላን አልከተልም፤ እኔም ግልጽ አስጠንቃቂ እንጅ ሌላ አይደለሁም* በላቸው። قُلْ مَا كُنتُ بِدْعًۭا مِّنَ ٱلرُّسُلِ وَمَآ أَدْرِى مَا يُفْعَلُ بِى وَلَا بِكُمْ ۖ إِنْ أَتَّبِعُ إِلَّا مَا يُوحَىٰٓ إِلَىَّ وَمَآ أَنَا۠ إِلَّا نَذِيرٌۭ مُّبِينٌۭ

ነጥብ አንድ
“ብጤ የሌለኝ አይደለሁም”
ከነቢያችን”ﷺ” በፊት የመጡት በእርግጥ ምግብን የሚበሉ፣ በገበያዎችም የሚሄዱ ሰዎች ነበሩ፣ በተመሳሳይም ነቢያችን”ﷺ” ሰው ናቸው፣ በደረጃ እንጂ በሃልዎት ከሰው የተለዩ አልነበሩም፣ ከበፊቱ መልክተኞች በእርግጥ ያለፉ የሆኑ መልክተኛ ነበሩ፦
36፥3 አንተ በእርግጥ *ከመልክተኞቹ ነህ*። إِنَّكَ لَمِنَ ٱلْمُرْسَلِينَ
2፥252 አንተም *በእርግጥ ከመልክተኞቹ ነህ*፡፡ وَإِنَّكَ لَمِنَ ٱلْمُرْسَلِينَ
3፥144 ሙሐመድም *ከበፊቱ መልክተኞች በእርግጥ ያለፉ የሆነ መልክተኛ እንጅ ሌላ አይደለም*፤ وَمَا مُحَمَّدٌ إِلَّا رَسُولٌۭ قَدْ خَلَتْ مِن قَبْلِهِ ٱلرُّسُلُ

ነጥብ ሁለት
“ዐላውቅም”
ነቢያችን”ﷺ” በራሳቸውና በሰዎች ምን እንደሚከናወን የወደፊቱን ዐያውቁም፣ ያ ማለት ሰዎች የሚያስጠነቅቁበት ቅርብ ይሁን እሩቅ ዐያውቁም፣ ከሚወርድላቸው ግህደተ-መለኮት ውጪ ምንም ዐያውቁም፦
6፥50 «ለእናንተ የአላህ ግምጃ ቤቶች እኔ ዘንድ ናቸው አልልም፡፡ *ሩቅንም አላውቅም*፡፡ ለእናንተም እኔ መልአክ ነኝ አልልም፡፡ *ወደ እኔ የሚወርድልኝን እንጅ ሌላን አልከተልም*» በላቸው፡፡ قُل لَّآ أَقُولُ لَكُمْ عِندِى خَزَآئِنُ ٱللَّهِ وَلَآ أَعْلَمُ ٱلْغَيْبَ وَلَآ أَقُولُ لَكُمْ إِنِّى مَلَكٌ ۖ إِنْ أَتَّبِعُ إِلَّا مَا يُوحَىٰٓ إِلَىَّ ۚ قُلْ هَلْ يَسْتَوِى ٱلْأَعْمَىٰ وَٱلْبَصِيرُ ۚ أَفَلَا تَتَفَكَّرُونَ
7፥188 አላህ የሻውን በስተቀር ለራሴ ጥቅምንም፣ ጉዳትንም፣ ማምጣት አልችልም፣ *ሩቅንም የማውቅ በነበርኩ ኖሮ* ከመልካም ነገር ባበዛሁና ክፉም ነገር ባልነካኝ ነበር፤ እኔ ለሚያምኑ ሕዝቦች አስጠንቃቂና አብሳሪ እንጂ ሌላ አይደለሁም”* በላቸው። قُل لَّآ أَمْلِكُ لِنَفْسِى نَفْعًۭا وَلَا ضَرًّا إِلَّا مَا شَآءَ ٱللَّهُ ۚ وَلَوْ كُنتُ أَعْلَمُ ٱلْغَيْبَ لَٱسْتَكْثَرْتُ مِنَ ٱلْخَيْرِ وَمَا مَسَّنِىَ ٱلسُّوٓءُ ۚ إِنْ أَنَا۠ إِلَّا نَذِيرٌۭ وَبَشِيرٌۭ لِّقَوْمٍۢ يُؤْمِنُونَ
21፥109 እምቢም ቢሉ በማወቅ በእኩልነት ላይ ሆነን የታዘዝኩትን አስታወቅኋችሁ፤ *የምትስፈራሩበትም ነገር ቅርብ፣ ወይም ሩቅ፣ መሆኑን ዐላውቅም*፤ በላቸው። فَإِن تَوَلَّوْا۟ فَقُلْ ءَاذَنتُكُمْ عَلَىٰ سَوَآءٍۢ ۖ وَإِنْ أَدْرِىٓ أَقَرِيبٌ أَم بَعِيدٌۭ مَّا تُوعَدُونَ
21፥111 እርሱም *ቅጣትን ማቆየት ምናልባት ለእናንተ ፈተናና እስከ ጊዜው መጣቀሚያ እንደኾነም “አላውቅም”*፤ በላቸው። وَإِنْ أَدْرِى لَعَلَّهُۥ فِتْنَةٌۭ لَّكُمْ وَمَتَٰعٌ إِلَىٰ حِينٍۢ
ነጥብ ሶስት
“ሚወረደው”
ወደ ነቢያችን”ﷺ” የሚወርደው ለቀደሙት መልክተኞች የሚወርደው የነበረው የአንድ አምላክ አስተምህሮት ነው፣ ከነቢያችን"ﷺ" በፊት ለነበሩት መልክተኞች የተባለው ይህ የተውሒድ ተስተምህሮት ነው ነቢያችን”ﷺ” የሚከተሉት፦
21፥108 «ያ ወደ እኔ የሚወረደው፦ *”አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው”* ማለት ነው፤ ታዲያ እናንተ ፍጹም “ታዛዦች” ናችሁን» *በላቸው*፡፡ قُلْ إِنَّمَا يُوحَىٰٓ إِلَىَّ أَنَّمَآ إِلَٰهُكُمْ إِلَٰهٌۭ وَٰحِدٌۭ ۖ فَهَلْ أَنتُم مُّسْلِمُونَ
18፥110 እኔም ቢጤያችሁ ሰው ብቻ ነኝ፤ ወደ እኔ የሚወረድልኝ፦ *”አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው” ማለት ነው”*፤ የጌታውንም መገናኘት የሚፈልግ ሰው፤ መልካም ሥራን ይሥራ፡፡ በጌታውም አምልኮ አንድንም አያጋራ» *”በላቸው”*፡፡ قُلْ إِنَّمَآ أَنَا۠ بَشَرٌۭ مِّثْلُكُمْ يُوحَىٰٓ إِلَىَّ أَنَّمَآ إِلَٰهُكُمْ إِلَٰهٌۭ وَٰحِدٌۭ ۖ فَمَن كَانَ يَرْجُوا۟ لِقَآءَ رَبِّهِۦ فَلْيَعْمَلْ عَمَلًۭا صَٰلِحًۭا وَلَا يُشْرِكْ بِعِبَادَةِ رَبِّهِۦٓ أَحَدًۢا
21፥25 ከአንተ በፊትም፣ እነሆ *ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና አምልኩኝ፣ በማለት ወደ እርሱ የምናወርድለት ቢሆን እንጅ ከመልክተኛ አንድንም አልላክንም*። وَمَآ أَرْسَلْنَا مِن قَبْلِكَ مِن رَّسُولٍ إِلَّا نُوحِىٓ إِلَيْهِ أَنَّهُۥ لَآ إِلَٰهَ إِلَّآ أَنَا۠ فَٱعْبُدُونِ
41፥43 ከአንተ በፊት ለነበሩት መልክተኞች *የተባለው ቢጤ* እንጅ ለአንተ ሌላ አይባልም፤ مَّا يُقَالُ لَكَ إِلَّا مَا قَدْ قِيلَ لِلرُّسُلِ مِن قَبْلِكَ ۚ إِنَّ رَبَّكَ لَذُو مَغْفِرَةٍۢ وَذُو عِقَابٍ أَلِيمٍۢ

ነጥብ አራት
“አስጠንቃቂ”
አላህ የነቢያችን”ﷺ” ቢጤዎች መልክተኞችን አብሳሪና አስጠንቃቂ አድርጎ ከነቢያችን”ﷺ” በፊት ልኳል፦
18፥56 መልክተኞችንም *አብሳሪዎችና አስጠንቃቂዎች* ሆነው እንጂ አንልክም፤ وَمَا نُرْسِلُ ٱلْمُرْسَلِينَ إِلَّا مُبَشِّرِينَ وَمُنذِرِين
4፥165 ከመልክተኞቹ በኋላ ለሰዎች በአላህ ላይ አስረጅ እንዳይኖር *አብሳሪዎችና አስጠንቃቂዎች* የሆኑን መልክተኞች ላክን፤ رُّسُلًۭا مُّبَشِّرِينَ وَمُنذِرِينَ لِئَلَّا يَكُونَ لِلنَّاسِ عَلَى ٱللَّهِ حُجَّةٌۢ بَعْدَ ٱلرُّسُلِ ۚ وَكَانَ ٱللَّهُ عَزِيزًا حَكِيمًۭا
2፥213 አላህም ነቢያትን *አብሳሪዎችና አስጠንቃቂዎች* አድርጎ ላከ፡፡ وَٰحِدَةًۭ فَبَعَثَ ٱللَّهُ ٱلنَّبِيِّـۧنَ مُبَشِّرِينَ وَمُنذِرِينَ

በተመሳሳይ መልኩ በጀነት አብሳሪ በጀሃነም አስጠንቃቂ ይሆኑ ዘንድ ነቢያችንን”ﷺ” አብሳሪና አስጠንቃቂ አድርጎ ልኳል፦
2፥119 እኛ *አብሳሪና አስጠንቃቂ* ኾነህ በእውነት ላክንህ፡፡ ከእሳትም ጓዶች አትጠየቅም፡፡ إِنَّآ أَرْسَلْنَٰكَ بِٱلْحَقِّ بَشِيرًۭا وَنَذِيرًۭا ۖ وَلَا تُسْـَٔلُ عَنْ أَصْحَٰبِ ٱلْجَحِيمِ
34፥28 አንተንም ለሰዎች ሁሉ በሙሉ *አብሳሪና አስጠንቃቂ* አድርገን ቢሆን እንጂ አላክንህም፤ وَمَآ أَرْسَلْنَٰكَ إِلَّا كَآفَّةًۭ لِّلنَّاسِ بَشِيرًۭا وَنَذِيرًۭا وَلَٰكِنَّ أَكْثَرَ ٱلنَّاسِ لَا يَعْلَمُونَ
33፥45 አንተ ነቢዩ ሆይ! እኛ መስካሪ *አብሳሪና አስጠንቃቂ* አድርገን ላክንህ። يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّبِىُّ إِنَّآ أَرْسَلْنَٰكَ شَٰهِدًۭا وَمُبَشِّرًۭا وَنَذِيرًۭا

አላህም፦ ”አላህን እንጂ ሌላን አታምልኩ፤ አንድ ከኾነው አላህ በቀር ምንም አምላክ የለም፤ እኔ ለእናንተ ከእርሱ የተላክሁ አስጠንቃቂ ነኝ” በል በማለት አስጠንቃቂ መሆናቸውን አውርዷል፦
11፥2 እንዲህ በላቸው ፦ አላህን እንጂ ሌላን አታምልኩ፤ *እኔ ለእናንተ ከእርሱ የተላክሁ አስጠንቃቂ ነኝ*። أَلَّا تَعْبُدُوٓا۟ إِلَّا ٱللَّهَ ۚ إِنَّنِى لَكُم مِّنْهُ نَذِيرٌۭ وَبَشِيرٌۭ
22፥49 ፦ እላንተ ስዎች ሆይ እኔ ለእናንተ *ግልጽ አስጠንቃቂ ብቻ ነኝ*፣ በላቸው። قُلْ يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّاسُ إِنَّمَآ أَنَا۠ لَكُمْ نَذِيرٌۭ مُّبِينٌۭ

ስለዚህ ከላይ ያለውን አንቀጽ የወረደበትም ዐውድ ስንመለከተው ነቢያችን”ﷺ” ጀነት ስለ አለመግባታቸው ምንም የሚያወራው ነገር የለም። ዐውዱ ለማስተላለፍ የፈለገውን በግድ ጠምዝዞ ይህን ለማለት ነው የፈለገው ብሎ ማጣመም ከሥነ-አፈታት ጥናት “hermeneutics” ጋር መላተም እና የደፈረሰ የተሳከረ መረዳት ነው፣ ይህ ሙግት የዐውድ ሙግት”contextual approach” ታሳቢና ዋቢ ያደረገ ነው።

ከወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም
የበለጠ ለማወቅ
ጥሪያችን Tiriyachen
ወሰላሙ አለይኩም
ያህዌህ ነውን?

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

5፥72 እነዚያ *«አላህ እርሱ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ነው»* ያሉ በእርግጥ ካዱ፡፡ لَقَدْ كَفَرَ الَّذِينَ قَالُوا إِنَّ اللَّهَ هُوَ الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ

የሥላሴ አማንያን ኢየሱስን አምላክ ለማድረግ የማይፈነቅሉት ድንጋይ የማይደረምሱት መሬት የለም። መዝሙር ላይ "ያህዌህ ዐረገ" ስለሚል ያ ያረገው ያህዌህ ኢየሱስ ነው ብለው ድምዳሜ ላይ ደርሰዋል፦
መዝሙር 47፥5 አምላክ በእልልታ፥ *"ያህዌህ በመለከት ድምፅ ዐረገ*"። (KJV) God is *"gone up"* with a shout, the LORD with the sound of a trumpet.

"ዐረገ" የሚለው የዕብራይስጥ ቃል "ዓላህ" עָלָ֣ה ሲሆን "ወጣ" ወይም "ከፍ አለ"gone up" ማለት ነው። ወደ ሰማየ ሰማያት አብ ወጥቷል፦
መዝሙር 68፥33 በምሥራቅ በኩል *"ወደ ሰማየ ሰማያት ለወጣ ለያህዌህ ዘምሩ"*፤ የኃይል ቃል የሆነ ቃሉን፥ እነሆ፥ ይሰጣል።
መዝሙር 68፥4 *"ወደ ሰማያት ለወጣም መንገድ አድርጉ፤ ስሙ “ያህ” בְּיָ֥הּ ነው"*፥
(KJV) Sing unto God, sing praises to his name: extol him that rideth upon the heavens by his name JAH, and rejoice before him.

ያህ የያህዌህ ምጻረ-ቃል ነው። በእነዚህ ጥቅስ መሰረት ወደ ሰማይ የወጣው ማን ነው? ያህዌህ! ይህን ታውቅ እንደ ሆንህ ስሙ ማን ነው? ያህዌህ! የልጁ ስምስ ማን ነው? ኢየሱስ፦
ምሳሌ 30፥4 ወደ ሰማይ የወጣ የወረደስ ማን ነው? ነፋስንስ በእጁ የጨበጠ ማን ነው? ውኃንስ በልብሱ የቋጠረ ማን ነው? የምድርን ዳርቻ ሁሉ ያጸና ማን ነው? ይህን ታውቅ እንደ ሆንህ፥ ስሙ ማን ነው? የልጁስ ስም ማን ነው?

በዚህ ጥቅስ መሰረት የልጁ ባለቤት ወደ ሰማይ ወጣ የተባለው አብ ነው። ስለዚህ እግዚአብሔር ወጣ የተባለው አብ ነው። አይ አይደለም! ወደ ሰማይ የወጣ የወረደስ ማን ነው? ኢየሱስ! ይህን ታውቅ እንደ ሆንህ ስሙ ማን ነው? ኢየሱስ! የልጁ ስምስ ማን ነው? ኢየሱስ! ያስኬዳልን? አየሱስ የአብና የወልድ ስም ነውን? ኢየሱስ ልጅ አለውን? የኢየሱስ ልጅ የሚባል ኢየሱስ አለን? ቅሉ ግን የወጣው ያህዌህ አብ ሲሆን የልጁ ስም ኢየሱስ ነው ካላችሁ እንግዲያውስ ወጣ የተባለው በመዝሙር ላይ አብ ነው። ያህዌህ አብ ይወርዳል፦
ዘፍጥረት 46፥4 እኔ ወደ ግብፅ አብሬህ *"እወርዳለሁ"*፥ ከዚያም ደግሞ እኔ አወጣሃለሁ፤ ዮሴፍም እጁን በዓይንህ ላይ ያኖራል።
ዘጸአት 19፥18 *ያህዌህም በእሳት ስለ ወረደበት"* የሲና ተራራ ሁሉ ይጤስ ነበር፤
ዘኍልቍ 11፥17 *እኔም እወርዳለሁ*፥ በዚያም እነጋገርሃለሁ፥

የወረደው እንደሚወጣ ከላይ አይተናል። ያህዌህ መውረድ መውጣት ብቻ ሳይሆን ክንፉና ላባ አለው ይበራል፦
መዝሙር 91፥4 *በላባዎቹ ይጋርድሃል፥ በክንፎቹም* በታች ትተማመናለህ።
2ኛ ሳሙኤል 22፥11 በኪሩብም ላይ ተቀምጦ *"በረረ"*፤
መዝሙር 18፥10 በኪሩቤልም ላይ ተቀምጦ *"በረረ"*፥

ስለዚህ "ዐረገ" "ወጣ" "ወረደ" "በረረ" ስለአብ ነው የሚናገረው። ለመሆኑ ያህዌህ አንድ ነው። ያ አንዱ ያህዌህ ዐረገ ሲባል ኢየሱስን ካመለከተ ይህ አንዱ ያህዌው አምላኩ ማን ነው? ምክንያቱም ዐራጊው ማንነት የሚያርገው ወደ እግዚአብሔር አምላኩ ነው፤ ዐርጎም የሚቀመጠው በእግዚአብሔርም ቀኝ ነው፦
ማርቆስ 16፥19 ጌታ ኢየሱስም ከእነርሱ ጋር ከተናገረ በኋላ *ወደ ሰማይ ዐረገ በእግዚአብሔርም ቀኝ ተቀመጠ*።
ዮሐንስ 17፥11 *”እኔም ወደ አንተ እመጣለሁ”*።
ዮሐንስ 20፥17 *እኔ ወደ አባቴና ወደ አባታችሁ ወደ አምላኬና ወደ አምላካችሁ ዓርጋለሁ”* ብለሽ ንገሪአቸው፥ አላት።

ልብ አድርጉ ኢየሱስ እራሱን በመጀመሪያ መደብ “እኔ” እያለ እግዚአብሔር ደግሞ በሁለተኛ መደብ “አንተ” እያለ በጸሎት ሲናነጋግረው ተመልከቱ፤ ዓራጊው ኢየሱስ ሲሆን ከሚያርግበት ከእግዚአብሔር ማንነት ለመለየት “ወደ” የሚል መስተዋድድ ተጠቅሟል፤ “ወደ አምላኬ ዓርጋለሁ” የሚለው ሃይለ-ቃል ይሰመርበት፤ “አምላኬ” ማለቱ የሚያርገው ማንነት አምላክ አለው። እግዚአብሔር ከሆነ ወደ እግዚአብሔር የሚያርገው እግዚአብሔር አምላክ አለውን? አዎ! ብሎ ማመን ምን አይነት ድራማና ቁማር ነው? ኢየሱስ ያያረገው በአካል እንጂ በመለከት አይደለም። ሲቀጥል "ያህዌህ ወጣ" ትንቢት ሳይሆን አላፊ ግስ ነው፥ ትንቢት ነው ከተባለ ወደ ሰማይ የወጣ ኤልያስ ያህዌህ ነውን? ምክንያቱም ኤልያስም ወደ ሰማይ ወጣ ስለሚል፦
2 ነገሥት 2፥11 *"ኤልያስም በዐውሎ ነፋስ ወደ ሰማይ ወጣ"*።

ስለዚህ ያህዌህ ወጣ የሚለውን ትንቢት ነው ብሎ መሞገት ውኃ የማይቋጥርና የማያነሳ ስሁት ሙግት ነው።
"አላህ እርሱ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ነው" ያሉ በእርግጥ ካዱ፦
5፥72 እነዚያ *«አላህ እርሱ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ነው»* ያሉ በእርግጥ ካዱ፡፡ لَقَدْ كَفَ-رَ الَّذِينَ قَالُوا إِنَّ اللَّهَ هُوَ الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ

ከወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም

የበለጠ ለማወቅ
ጥሪያችን Tiriyachen
ወሰላሙ አለይኩም
#tiriyachen
ያህዌህ ነውን?

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

5፥72 እነዚያ *«አላህ እርሱ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ነው»* ያሉ በእርግጥ ካዱ፡፡ لَقَدْ كَفَرَ الَّذِينَ قَالُوا إِنَّ اللَّهَ هُوَ الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ

የሥላሴ አማንያን ኢየሱስን አምላክ ለማድረግ የማይፈነቅሉት ድንጋይ የማይደረምሱት መሬት የለም። መዝሙር ላይ "ያህዌህ ዐረገ" ስለሚል ያ ያረገው ያህዌህ ኢየሱስ ነው ብለው ድምዳሜ ላይ ደርሰዋል፦
መዝሙር 47፥5 አምላክ በእልልታ፥ *"ያህዌህ በመለከት ድምፅ ዐረገ*"። (KJV) God is *"gone up"* with a shout, the LORD with the sound of a trumpet.

"ዐረገ" የሚለው የዕብራይስጥ ቃል "ዓላህ" עָלָ֣ה ሲሆን "ወጣ" ወይም "ከፍ አለ"gone up" ማለት ነው። ወደ ሰማየ ሰማያት አብ ወጥቷል፦
መዝሙር 68፥33 በምሥራቅ በኩል *"ወደ ሰማየ ሰማያት ለወጣ ለያህዌህ ዘምሩ"*፤ የኃይል ቃል የሆነ ቃሉን፥ እነሆ፥ ይሰጣል።
መዝሙር 68፥4 *"ወደ ሰማያት ለወጣም መንገድ አድርጉ፤ ስሙ “ያህ” בְּיָ֥הּ ነው"*፥
(KJV) Sing unto God, sing praises to his name: extol him that rideth upon the heavens by his name JAH, and rejoice before him.

ያህ የያህዌህ ምጻረ-ቃል ነው። በእነዚህ ጥቅስ መሰረት ወደ ሰማይ የወጣው ማን ነው? ያህዌህ! ይህን ታውቅ እንደ ሆንህ ስሙ ማን ነው? ያህዌህ! የልጁ ስምስ ማን ነው? ኢየሱስ፦
ምሳሌ 30፥4 ወደ ሰማይ የወጣ የወረደስ ማን ነው? ነፋስንስ በእጁ የጨበጠ ማን ነው? ውኃንስ በልብሱ የቋጠረ ማን ነው? የምድርን ዳርቻ ሁሉ ያጸና ማን ነው? ይህን ታውቅ እንደ ሆንህ፥ ስሙ ማን ነው? የልጁስ ስም ማን ነው?

በዚህ ጥቅስ መሰረት የልጁ ባለቤት ወደ ሰማይ ወጣ የተባለው አብ ነው። ስለዚህ እግዚአብሔር ወጣ የተባለው አብ ነው። አይ አይደለም! ወደ ሰማይ የወጣ የወረደስ ማን ነው? ኢየሱስ! ይህን ታውቅ እንደ ሆንህ ስሙ ማን ነው? ኢየሱስ! የልጁ ስምስ ማን ነው? ኢየሱስ! ያስኬዳልን? አየሱስ የአብና የወልድ ስም ነውን? ኢየሱስ ልጅ አለውን? የኢየሱስ ልጅ የሚባል ኢየሱስ አለን? ቅሉ ግን የወጣው ያህዌህ አብ ሲሆን የልጁ ስም ኢየሱስ ነው ካላችሁ እንግዲያውስ ወጣ የተባለው በመዝሙር ላይ አብ ነው። ያህዌህ አብ ይወርዳል፦
ዘፍጥረት 46፥4 እኔ ወደ ግብፅ አብሬህ *"እወርዳለሁ"*፥ ከዚያም ደግሞ እኔ አወጣሃለሁ፤ ዮሴፍም እጁን በዓይንህ ላይ ያኖራል።
ዘጸአት 19፥18 *ያህዌህም በእሳት ስለ ወረደበት"* የሲና ተራራ ሁሉ ይጤስ ነበር፤
ዘኍልቍ 11፥17 *እኔም እወርዳለሁ*፥ በዚያም እነጋገርሃለሁ፥

የወረደው እንደሚወጣ ከላይ አይተናል። ያህዌህ መውረድ መውጣት ብቻ ሳይሆን ክንፉና ላባ አለው ይበራል፦
መዝሙር 91፥4 *በላባዎቹ ይጋርድሃል፥ በክንፎቹም* በታች ትተማመናለህ።
2ኛ ሳሙኤል 22፥11 በኪሩብም ላይ ተቀምጦ *"በረረ"*፤
መዝሙር 18፥10 በኪሩቤልም ላይ ተቀምጦ *"በረረ"*፥

ስለዚህ "ዐረገ" "ወጣ" "ወረደ" "በረረ" ስለአብ ነው የሚናገረው። ለመሆኑ ያህዌህ አንድ ነው። ያ አንዱ ያህዌህ ዐረገ ሲባል ኢየሱስን ካመለከተ ይህ አንዱ ያህዌው አምላኩ ማን ነው? ምክንያቱም ዐራጊው ማንነት የሚያርገው ወደ እግዚአብሔር አምላኩ ነው፤ ዐርጎም የሚቀመጠው በእግዚአብሔርም ቀኝ ነው፦
ማርቆስ 16፥19 ጌታ ኢየሱስም ከእነርሱ ጋር ከተናገረ በኋላ *ወደ ሰማይ ዐረገ በእግዚአብሔርም ቀኝ ተቀመጠ*።
ዮሐንስ 17፥11 *”እኔም ወደ አንተ እመጣለሁ”*።
ዮሐንስ 20፥17 *እኔ ወደ አባቴና ወደ አባታችሁ ወደ አምላኬና ወደ አምላካችሁ ዓርጋለሁ”* ብለሽ ንገሪአቸው፥ አላት።

ልብ አድርጉ ኢየሱስ እራሱን በመጀመሪያ መደብ “እኔ” እያለ እግዚአብሔር ደግሞ በሁለተኛ መደብ “አንተ” እያለ በጸሎት ሲናነጋግረው ተመልከቱ፤ ዓራጊው ኢየሱስ ሲሆን ከሚያርግበት ከእግዚአብሔር ማንነት ለመለየት “ወደ” የሚል መስተዋድድ ተጠቅሟል፤ “ወደ አምላኬ ዓርጋለሁ” የሚለው ሃይለ-ቃል ይሰመርበት፤ “አምላኬ” ማለቱ የሚያርገው ማንነት አምላክ አለው። እግዚአብሔር ከሆነ ወደ እግዚአብሔር የሚያርገው እግዚአብሔር አምላክ አለውን? አዎ! ብሎ ማመን ምን አይነት ድራማና ቁማር ነው? ኢየሱስ ያያረገው በአካል እንጂ በመለከት አይደለም። ሲቀጥል "ያህዌህ ወጣ" ትንቢት ሳይሆን አላፊ ግስ ነው፥ ትንቢት ነው ከተባለ ወደ ሰማይ የወጣ ኤልያስ ያህዌህ ነውን? ምክንያቱም ኤልያስም ወደ ሰማይ ወጣ ስለሚል፦
2 ነገሥት 2፥11 *"ኤልያስም በዐውሎ ነፋስ ወደ ሰማይ ወጣ"*።

ስለዚህ ያህዌህ ወጣ የሚለውን ትንቢት ነው ብሎ መሞገት ውኃ የማይቋጥርና የማያነሳ ስሁት ሙግት ነው።
"አላህ እርሱ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ነው" ያሉ በእርግጥ ካዱ፦
5፥72 እነዚያ *«አላህ እርሱ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ነው»* ያሉ በእርግጥ ካዱ፡፡ لَقَدْ كَفَ-رَ الَّذِينَ قَالُوا إِنَّ اللَّهَ هُوَ الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ

ከወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም

የበለጠ ለማወቅ
ጥሪያችን Tiriyachen
ወሰላሙ አለይኩም
#tiriyachen
ያህዌህ አይደለም

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

5፥72 እነዚያ *«አላህ እርሱ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ነው»* ያሉ በእርግጥ ካዱ፡፡
ሥላሴአውያን መዝሙር ላይ "ያህዌህ ይመጣል" ስለሚል ያ የሚመጣው ያህዌህ ኢየሱስ ነው ብለው ድምዳሜ ላይ ደርሰዋል፦
መዝሙር 50፥2-3 ከክብሩ ውበት ከጽዮን *"ያህዌህ ግልጥ ሆኖ ይመጣል"*። *"አምላካችን ይመጣል"* ዝምም አይልም፤

ያህዌህ ለፍርድ እንደሚመጣ ብዙ የብሉያት አናቅጽ ይናገራሉ፦
መዝሙር 96፥13 ይመጣልና፤ *በምድር ላይ ሊፈርድ ይመጣልና፤ እርሱም ዓለምን በጽድቅ አሕዛብንም በቅንነት ይፈርዳል"*።
1ኛ ዜና መዋዕል 16፥33 *"በምድር ሊፈርድ ይመጣልና"*፥
መዝሙር 98፥8 ወንዞችም በአንድነት በእጅ ያጨብጭቡ፤ ተራሮች ደስ ይበላቸው፥ *"በምድር ሊፈርድ ይመጣልና"*።
ኢሳይያስ 66፥15 እነሆ *"ያህዌህ መዓቱን በቍጣ፥ ዘለፋውንም በእሳት ነበልባል ይመልስ ዘንድ ከእሳት ጋር ይመጣል"*፥

ያህዌህ ለፍርድ እንደሚመጣ በእነዚህ ጥቅሶች ካየን ዘንዳ ይህ ያህዌህ አብ እንደሆነ በሰከነ እና በሰላ አእምሮ ማየት ይቻላል፦
ዳንኤል 7፥22 *በዘመናት የሸመገለው እስኪመጣ ድረስ፥ ፍርድም ለልዑሉ ቅዱሳን እስኪሰጥ ድረስ"*፥

"በዘመናት የሸመገለው" መጥቶ ፍርድን ለልዑል ቅዱሳን እንደሚሰጥ ይናገራል። "በዘመናት የሸመገለው" እዛው ዐውድ ላይ ለሰው ልጅ ግዛትና ክብር መንግሥትም እንደሰጠው ይናገራል፦
ዳንኤል 7፥13-14 በሌሊት ራእይ አየሁ፤ እነሆም፥ *"የሰው ልጅ የሚመስል ከሰማይ ደመናት ጋር መጣ በዘመናት ወደ ሸመገለውም ደረሰ"*፤ ወደ ፊቱም አቀረቡት። ወገኖችና አሕዛብ በልዩ ልዩ ቋንቋም የሚናገሩ ሁሉ ይገዙለት ዘንድ *"ግዛትና ክብር መንግሥትም ተሰጠው"*።

በዘመናት የሸመገለው አባት አብ ከሆነ የሰው ልጅ የተባለው ወልድ ነው ካላችሁ፥ ወልድ ወደ አብ ደርሶ ግዛትና ክብር መንግሥትም ከተሰጠው እንግዲያውስ "በዘመናት የሸመገለው እስኪመጣ ድረስ፥ ፍርድም ለልዑሉ ቅዱሳን እስኪሰጥ ድረስ" የተባለው አብ ነው። አብ ለፍርድ ይመጣል ማለት ነው። "በዘመናት የሸመገለው" ለመፍረድ በዙፋኑ ይቀመጣል፦
ዳንኤል 7፥9 ዙፋኖችም እስኪዘረጉ ድረስ አየሁ፥ *"በዘመናት የሸመገለውም ተቀመጠ"*፤

ልጁን የላከው የወይን አትክልት ጌታ አብ ሲመጣ ክፉዎችን በክፉ ያጠፋል፦
ማቴዎስ 21፥33 ሌላ ምሳሌ ስሙ። *"የወይን አትክልት የተከለ ባለቤት ሰው ነበረ"*፤
ማቴዎስ 21፥37 በኋላ ግን፦ *"ልጄንስ ያፍሩታል፡ ብሎ ልጁን ላከባቸው"*።
ማቴዎስ 21፥40 እንግዲህ *የወይኑ አትክልት ጌታ በሚመጣ ጊዜ"* በእነዚህ ገበሬዎች ምን ያደርግባቸዋል? እነርሱም፦ *"ክፉዎችን በክፉ ያጠፋቸዋል"*፥ አሉት።

ልብ አድርግ "የወይን አትክልት ጌታ" በሚመጣ ጊዜ እንደተባለ። ራእይ ላይም ያለውና የነበረው የሚመጣው ጌታ አምላክ ከኢየሱስ "እና" በሚል መስተጻምር ተለይቷል፦
ራእይ 1፥4 *"ካለውና ከነበረው ከሚመጣውም "እና" በዙፋኑም ፊት ካሉት ከሰባቱ መናፍስት "እና" ከታመነውም ምስክር ከሙታንም በኵር የምድርም ነገሥታት ገዥ ከሆነ ከኢየሱስ ክርስቶስ"* ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን። KJV
Ο Ιωάννης προς τις επτά εκκλησίες στην επαρχία της Ασίας: Χάρη και ειρήνη σε σας από αυτόν που είναι, και ποιος ήταν και ποιος θα έρθει, και από τα επτά πνεύματα πριν από το θρόνο του, και από τον Ιησού Χριστό, ο οποίος είναι ο πιστός μάρτυρας, ο πρωτότοκος εκ των νεκρών, και ο άρχων των βασιλέων της γης.

ጸጋና ሰላም፦
1. ካለውና ከነበረው ከሚመጣውም
2. ከሰባቱ መናፍስት
3. ከኢየሱስ ክርስቶስ
ለእናንተ ይሁን! ይላል። ልክ ጸጋና ሰላም "ከእግዚአብሔር ከአባታችን እና ከጌታም ከኢየሱስ" ለእናንተ ይሁን! እንደሚል እንደ ጳውሎስ ሰላምታ። በግራንቪል ሻርፕ የግሪክ ሰዋስው አምስተኛው ሕግ "ካይ" και ማለትም "እና" የሚል መስተጻምር እና "አፓ" από ማለትም "ከ" የሚለው መስተዋድድ ተያይዘው የሚመጣውን አብን እና ኢየሱስን ሁለት የተለያዩ ማንነቶች"persons" አድርጎ አስቀምጧቸዋል።
አብ ይመጣል ማለት ቃል በቃል ሳይሆን የእርሱ አላማ መፈጸምንና የእርሱ ክብር መገለጥ ያመለክታል፣ ምክንያቱም አብ ብዙ ጊዜ በብሉይ ኪዳን እንደመጣ ስለሚናገር፦
ዘኍልቍ 23፥3 በለዓምም ባላቅን፦ በመሥዋዕትህ ዘንድ ቆይ፥ እኔም እሄዳለሁ፤ ምናልባት *"ያህዌህ ሊገናኘኝ ይመጣል"*፤ እርሱም የሚገልጥልኝን እነግርሃለሁ አለው።
ዘፍጥረት 18፥14 በውኑ ለያህዌህ የሚሳነው ነገር አለን? *"የዛሬ ዓመት እንደ ዛሬው ጊዜ ወደ አንተ አንተ እመለሳለሁ"*፤ ሣራም ልጅን ታገኛለች።

ያህዌህ በዓመቱ ከይስሐቅ ልደት በኃላ መጥቶ ሲመለስ ቃል በቃል ጽንፈ-ዓለሙን ለቆና ትቶ መጣ ማለት እንዳልሆነ እሙንና ቅቡል ነው። ከላይ የብሉያት እና የአዲሳት አናቅጽ የአብን ለፍርድ መምጣት በዚህ ልክና መልክ ተረዱት። ስለዚህ ያህዌህ ለፍርድ ይመጣል ማለት አብ ሊፈርድ ይመጣል ማለት እንጂ ኢየሱስ ይመጣል ስለተባለ ያህዌህ ነው ማለት በፍጹም አይደለም። በላይ ባለው በመዝሙር 50፥2-3 ጥቅስ መሠረት ኢየሱስ ያህዌህ አይደለም። ኢየሱስ ያህዌህ ነው ብሎ መሞገት ውኃ የማይቋጥርና የማያነሳ ስሁት ሙግት ነው።
"አላህ እርሱ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ነው" ያሉ በእርግጥ ካዱ፦
5፥72 እነዚያ *«አላህ እርሱ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ነው»* ያሉ በእርግጥ ካዱ፡፡

ከወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም

የበለጠ ለማወቅ
ጥሪያችን Tiriyachen

ወሠላሙ ዐለይኩም
ፈጣሪ ፍጡር አይደለም!

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

13፥16 *አላህ ሁለመናውን ፈጣሪ ነው*፤ እርሱም አንዱ አሸናፊው ነው፤ በል፡፡ قُلِ اللَّهُ خَالِقُ كُلِّ شَيْءٍ وَهُوَ الْوَاحِدُ الْقَهَّارُ

አምላካችን አላህ የሁሉን ነገር ፈጣሪ ነው፥ አላህ በፈጣሪነቱ ላይ ፍጡርነት የሚባል የነውር እና የጎደሎ ባሕርይ የለውም። አላህ ሁለመናው ፈጣሪ ነው፥ ነገርንም ማስገኘት በሻ ጊዜ ለእርሱ የሚለው፡- «ኹን ነው» ወዲያውም ይኾናል፦
13፥16 *አላህ ሁለመናውን ፈጣሪ ነው፥ እርሱም አንዱ አሸናፊው ነው"* በል፡፡ قُلِ اللَّهُ خَالِقُ كُلِّ شَيْءٍ وَهُوَ الْوَاحِدُ الْقَهَّارُ
2፥117 ሰማያትንና ምድርን ያለብጤ ፈጣሪ ነው፤ *ነገርንም ማስገኘት በሻ ጊዜ ለእርሱ የሚለው፡- «ኹን ነው» ወዲያውም ይኾናል*፡፡ بَدِيعُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۖ وَإِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ

ፈጣሪ እና ፍጡር ሁለት ተቃራኒ ባሕርይ ናቸው፥ "ኢየሱስ ማህጸን ውስጥ የተፈጠረ ፍጡር ነው" ስንላቸው፥ እነርሱም ቅብል አርገው፦ "አዎ! ኢየሱስ ፍጡርም ፈጣሪም ነው" ይሉናል፦
ሃይማኖተ-አበው ስምዓት 124:19
ቄርሎስም አለ፦
“ለሊሁ ፍጡር ወለሊሁ ፈጣሪ”

ትርጉም፦
“እርሱ ፍጡር ነው እርሱ ፈጣሪ ነው”

ይህንን ስብጥር እሳቤ አዕምሮአችሁ ይቀበለዋልን? "እርሱ ፍጡር ነው እርሱ ፈጣሪ ነው" ምን ማለት ነው? ሁሉን ቻይ እና ሁሉን የማይችል፥ ሁሉን ዐዋቂ እና ሁሉን የማያውቅ" ሁለት ባሕርይ እንዴት አንድ ላይ ይዋሕዳል? "አይ ፈጣሪ ፍጡር ሆነ" ብለውን አረፉት፦
ሃይማኖተ-አበው ዘአክርስቶዶሎስ 112:31
አክርስቶዶሎስም አለ፦
“ወፈጣሪ ኮነ ፍጡረ እንተ ይእቲ እምህላዌነ ድንግል ዘበአማን ማርያም”

ትርጉም፦
“ፈጣሪ ከእኛ ባሕረይ ከተገኘች በእውነት ድንግል ከምትሆን ከማርያም ፍጡር ሆነ”

እሰይ! ይቀጥሉና፦ "ዓለም ሳይፈጠር ዘመን ሳይቆጠር አብን መስሎና አህሎ ከአብ ማንነትና ምንነት የተገኘ ነው" ይሉናል። አብ ማለት “አስገኚ” ሲሆን ወልድ ደግሞ “ግኝት” ነው። በ 325 ድኅረ-ልደት"AD" የተሰበሰበው የኒቅያ ጉባኤም፦
ግሪኩ፦ Φῶς ἐκ Φωτός, Θεὸν ἀληθινὸν ἐκ Θεοῦ ἀληθινοῦ,

ግዕዙ “ብርሃን ዘምብርሃን፤ አምላክ ዘምአምላክ”

ትርጉም፦
“ከብርሃን የተገኘ ብርሃን፤ ከአምላክ የተገኘ አምላክ” ብሎታል።

አምላክ አምላክን ካስገኘ ሁለት አምላክ አይሆንም ወይ? አምላክ ተገኘ የሚለው ሲያስገርም አምላክ ተፈጠረ ደግሞ ያስደምማል፦
አማርኛ፦
ምሳሌ 8፥22 *እግዚአብሔር ከሁሉ በፊት ፈጠረኝ*፥ (1980 አዲስ ትርጉም)

ግዕዝ፦
ምሳሌ 8፥22 “ፈጠረኒ እግዚእ መቅድመ ተግባሩ”

ኢንግሊሽ፦
Proverbs 8፥22 “The LORD made me as he began his planning, (International Standard Version)

ዕብራይስጥ፦
ምሳሌ 8፥22 יְהוָה–קָנָנִי, רֵאשִׁית דַּרְכּוֹ: קֶדֶם מִפְעָלָיו מֵאָז.

ግሪክ ሰፕቱአጀንት፦
Proverbs 8፥22 κύριος ἔκτισέν με ἀρχὴν ὁδῶν αὐτοῦ εἰς ἔργα αὐτοῦ

በተለይ በግሪኩ ሰፕቱአጀንት”LXX” ላይ “ኪትዞ” ἔκτισέν ማለት “ፈጠረኝ” ማለት ነው፤ በተመሳሳይ ዕብራይስጡ “ቃናኒ” קָ֭נָנִי ማለት “አስገኘኝ” ማለት ነው፤ ይህ ቃል ሔዋን “አገኘሁ” ብላ ለተጠቀመችበት የዋለው ቃል “ቃኒቲ” קָנִ֥יתִי ሲሆን ዳዊት ደግሞ ኲላሊቴን “ፈጥረሃል” ለሚለው የተጠቀመው “ቃኒታ” קָנִ֣יתָ ብሎ ነው፦
ዘፍጥረት 4፥1 ወንድ ልጅ ከእግዚአብሔር *አገኘሁ* קָנִ֥יתִי አለች።
መዝሙር 139፥13 አቤቱ፥ አንተ ኵላሊቴን *ፈጥረሃልና* קָנִ֣יתָ ፥
ዘዳግም 32፥6፤ ለእግዚአብሔር ይህንን ትመልሳለህ? የገዛህ አባትህ አይደለምን? *የፈጠረህ* קָּנֶ֔ךָ እና ያጸናህ እርሱ ነው።

የመጨረሻው ጥቅስ ላይ “የፈጠረክ” ለሚለው የገባው “ቃነካ” קָּנֶ֔ךָ መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። እግዚአብሔር “የገዛህ አባትህ” መባሉ “አባት” ማለት ለእግዚአብሔር ፈጣሪ ማለት እንደሆነ ይህ ጥቅስ ያስረዳል።
እንግዲህ “መገኘት” እና “መፈጠር” ተለዋዋጭ ቃል ከሆነ ኢየሱስ ፍጡር እና ግኝት እንደሆነ ሊሰመርበት ይገባል። ይህንን ጥቅስ ተሃድሶና እና ፕሮቴስታት ስለ ኢየሱስ አይደለም ብለው ሽምጥጥ አርገው ቢክዱም፤ ቀደምት ኦርቶዶክስ፣ካቶሊክ፣ አንግሊካን እና የኒቂያ ጉባኤ ስለ ኢየሱስ ፍጥረት ሳይፈጠር መወለዱን ያሳያል ይላሉ፤ በ 325 AD በኒቂያ ጉባኤ አርዮስንና አትናቲዎስ ኢየሱስ ፍጡር ነው ወይስ አይደለም ለሚለው ክርክራቸው ይህ ጥቅስ ነበር፤ አንዳንድ ኦርቶዶክሳውያንም ይህ ስለ ኢየሱስ አይደለም ብለው ሊያቅማሙ ሲሞክሩ አንድምታው ሆነ ሃይማኖተ-አበው አጋልጧቸዋል፤ ቄርሎስ በሃይማኖተ-አበው ላይ ለኢየሱስ ነው ይለናል፦
ሃይማኖተ-አበው ዘቄርሎስ 76:12
ቄርሎስም አለ፦
“ተፈጥረ ጥበብ ዘውእቱ ቃል”

ትርጉም፦
*“ጥበብ ተፈጠረ ይኸውም ቃል ነው”*

ቄርሎስም አለ፦
“ወይእዜኒ ጥበብ ትቤ ፈጠረኒ እግዚእ መቅድመ ተግባሩ”

ትርጉም፦
*“ከፍጥረት አስቀድሞ የነበርኩኝ በቀድሞ ተግባሩ ጌታ ፈጠረኝ አለች”*

የመቃብያን ጸሐፊም ሰሎሞን በምሳሌ መጽሐፍ ላይ ስለ ኢየሱስ፦ “ዛሬም የሚታየው ሁሉ ሳይታይ ዛሬም የሚጠራው ስም ሁሉ ሳይጠራ ፈጠረኝ” ማለቱን ተናግሯል፦
3ኛ መቃብያን 4፥18 ሰሎሞን ፦ *“ዛሬም የሚታየው ሁሉ ሳይታይ ዛሬም የሚጠራው ስም ሁሉ ሳይጠራ ፈጠረኝ”* ብሎ ተናገረ፤

እንግዲህ አባት ማለት “አስገኚ” ወይም “ፈጣሪ” መሆኑን እንዲሁ ልጅ ማለት “ተገኚ” ወይም “ፍጡር” መሆኑን ካየን ዘንዳ ኢየሱስ በየትኛው መልኩ ፍጡር ነው።
የዓለማቱ ጌታ አላህ ጌታችሁ ነው፥ ከእርሱ በቀር አምላክ የለም፡፡ ነገርን ሁሉ ፈጣሪ ነው፤ እርሱን በብቸኝነት አምልኩት፤ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ተጠባባቂ ነውና፦
6፥102 ይህ ጌታችሁ አላህ ነው፡፡ ከእርሱ በቀር አምላክ የለም፡፡ *ነገርን ሁሉ ፈጣሪ ነው፤ ስለዚህ አምልኩት*፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ተጠባባቂ ነው፡፡ ذَٰلِكُمُ اللَّهُ رَبُّكُمْ ۖ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ ۖ خَالِقُ كُلِّ شَيْءٍ فَاعْبُدُوهُ ۚ وَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ وَكِيلٌ

ከወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም

ጥሪያችን Tiriyachen
https://www.facebook.com/tiriyachen

ወሠላሙ ዐለይኩም
2025/07/05 12:55:13
Back to Top
HTML Embed Code: