Telegram Web Link
የኤርባካንን ለቅሶ የተበቀለው ኤርዶጋን
----
ክፍል አንድ
-----
ጸሐፊ: አፈንዲ ሙተቂ
-----
እ.ኤ.አ. 1996 ነበር። በዚያ ዓመት የተካሄደው የቱርክ ምርጫ ማንም ባልጠበቀው መልኩ የቱርክ ፕሬሶች "ወግ አጥባቂ ናቸው" እያሉ የሚያነሷቸው አንድ ታዋቂ ምሁር ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲሆኑ ዕድል የፈጠረ ሆነ።

ነጅመዲን ኤርባካን ይባላሉ። ከ1977-1980 ባሉት ዓመታት የቱርክ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ነበሩ። ከዚያ በፊት ደግሞ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ሆነው ሰርተዋል። በሙያቸው ሜካኒካል ኢንጂነር ናቸው። የኢስታንቡል የቴክኒክ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰርም ነበሩ።

ኤርባካን በ1996 ምርጫ ያሸነፉት "ሬፋሕ" (Refah Partisi) የሚባል ፓርቲ መሥርተው ነው። ይህ ፓርቲ "ቱርክ ወደ ቀድሞው እስላማዊ ማንነቷ መመለስ አለባት፣ ይህንን የምናደርገው ግን በዲሞክራሲያዊ መንገድ ብቻ ነው" የሚል አቋም ነበረው (እዚህ ላይ አንድ ነገር ልብ ይበሉ። ፓርቲው እንደዚህ ሲል ቱርክን በሸሪዓ ህግ አስተዳድራለሁ ማለቱ አልነበረም። ይሁንና ከሌሎች የሙስሊም ሀገሮች በተለየ መልኩ የቱርክን ህዝብ ሞራል የጎዱና ከሙስሊሞች የኑሮ ዘይቤ ያፈነገጡ ብዙ አድራጎቶች ተፈቅደው ነበር። ለምሳሌ በቱርክ ውስጥ የግብረ ሰዶም ጋብቻ የተፈቀደው በ1980ዎቹ ነው። ይህ የተደረገው የቱርክ ህዝብ ሶዶማዊነትን ስለሚቀበል አይደለም። "የቱርክ አውሮጳዊ መለያ አስጠባቂዎች ነን" የሚሉትና በመንግሥቱ ውስጥ የነበሩት ስውር እጆች ናቸው ህጉ እንዲወጣ ያደረጉት)።

የቱርክ ፖለቲከኞች "የሬፋሕ ፓርቲ በምርጫው ላይ የሚያሳርፈው ተጽእኖ ኢሚንት ነው" ብለው ነበር ያሰቡት። በምርጫው የፓርላማውን ብዙ ወንበሮች ማሸነፉ ሲታወቅ ግን ሁለመናቸው ተሸበረ። "ቱርክ ሴኩላር ማንነቷን ልታጣ ነው" እያሉ ብዙ ተናገሩ። የምርጫ ኮሚሽኑ ውጤቱን እንዲሰርዘውም ወተወቱ። ይሁን እንጂ "የምርጫውን ውጤት መሰረዝ የዲሞክራሲ ጽንሰ-ሃሳብን መጣስ ነው" የሚል ተቃውሞ ከህዝቡና ከፕሬሱ በርትቶ ስለመጣ ውጤቱ ሳይሰረዝ ቀረ። ኤርባካንም የቱርክ ሪፐብሊክ 23ኛ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆኑ።

ታዲያ ኤርባካን ጠቅላይ ሚኒስትር ቢሆኑም በእርሳቸው ላይ የሚካሄደው የማጥላላት ዘመቻ አልቆመም። "Kamalist" የሚባሉት የሙስጠፋ ከማል አታቱርክ ርእዮተ ዓለም አቀንቃኞች ኤርባካንና ፓርቲያቸውን እያንቋሸሹ ከስልጣን ሊያወርዷቸው ቀን ከሌሊት ጥረት ማድረጋቸውን አላቋረጡም። "የቱርክ ሪፐብሊካዊነት አስጠባቂ ነኝ" የሚለውና በሲቪሉ አመራር ይፈራ የነበረው የወታደሩ ክፍል በፕሮፌሰር ኤርባካን የሚመራውን መንግሥት በየጊዜው ያስፈራራ ነበር። ምዕራባዊያን ደግሞ "አውሮጳዊት የሆነችው ቱርክ በኢስላሚስት ጠቅላይ ሚኒስትር መመራት የለባትም" እያሉ የተለያዩ መግለጫዎችንና ማስንደበሪያዎችን ሲያወጡ ነው የሰነበቱት። ከዚህም አልፈው ከወታደሩና ከKamalist ፖለቲከኞች ጋር ሲዶልቱ ኖረዋል።

ኤርባካን በሀገር ውስጥ ፕሮፓጋንዳ እና በምዕራባዊያን ዛቻ እየተዋከቡ እንደ ምንም ብለው ቱርክን ለአንድ ዓመት መሩ። በ1997 ግን ሲጠበቅ የነበረው ሁሉ በግልጽ ተፈጸመ። ኤርባካን "ቱርክ የNATO አባል ከምትሆን በሙስሊም ሀገራት የሚመሰረት የሰላም አስከባሪ ሃይል አባል ብትሆን ይሻላታል" በማለት በፓርቲ ስብሰባ ወቅት የተናገሩት ንግግር እንደ ሰበብ ተቆጥሮ የስልጣን ዘመናቸው ፍጻሜ ማጠንጠኛ እንዲሆን ተቆረጠ። የቱርክ ወታደራዊ ምክር ቤት "የሪፐብሊኩ ሴኩላርነት አደጋ ውስጥ ገብቷል" በማለት መንፈቅለ መንግሥት አካሄደ። ኤርባካንም ከስልጣን ተወግደው ወደ እስር ቤት ተላኩ። የቱርክ ህገ መንግሥታዊ ምክር ቤት ደግሞ ከዓመት በኋላ "ሬፋሕ" የሚባለው ፓርቲ እንዲፈርስ ትእዛዝ አስተላለፈ (ኤርባካን ከእስር ከወጡ በኋላ ለሰባት ዓመት ፖለቲካ ውስጥ እንዳይገቡ ታግደዋል)።

ይህ ድርጊት ብዙዎች በተሳተፉበት ሴራ የተከናወነ ነው። CIA እና የእንግሊዙ የስለላ ድርጅት እጃቸውን እስከ ትከሻቸው ጨምረበታል። CIA በ1973 በቺሊ ሪፐብሊክ በዲሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጡትን ሳልቫዶር አየንዴን "ሶሻሊስት ናቸው፣ እርሱ ስልጣን ከያዘ በምዕራብ ንፍቀ ክበብ ኮሚኒዝም ይስፋፋል" በሚል ከወታደሩ ጋር ተመሳጥሮ ከስልጣን እንዳስገደላቸው ሁሉ ኤርባካንም ከስልጣን እንዲወገዱ ከፍተኛ ስራ ሰርቷል።
-----
በዚያን ወቅት ለሬፋሕ ፓርቲ ህልውና በመፋለም እና ጸረ-ዲሞክራሲ የነበረውን የመንፈቅለ መንግሥት እርምጃ በመቃወም ድምጹን በከፍተኛ ሁኔታ ያሰማ አንድ ቱርካዊ ነበር። ከኤርባካን ከስልጣን መነሳት በላይ የዓለም ሚዲያዎችን ትኩረት ስቦ የነበረው ይህ ቱርካዊ ያደረገው ንግግር ሲሆን እርሱም እንዲህ የሚል ነበር።

"በኤርባካን ላይ የተወሰደውን ህገወጥ እርምጃ አንቀበልም። ይህንን ህገ-ወጥ እርምጃ እስከ መጨረሻው ድረስ እንቃወማለን"

ሰውዬው ይህንን ከተናገረ በኋላ ዚያ ጎካልፕ የሚባለው እውቅ የቱርክ ገጣሚ ከገጠመው ግጥም የሚከተሉትን ስንኞች ለህዝቡ አነበበ።

መስጅዶቻችን ምሽጎቻችን ናቸው።
ቁባዎቻችን የብረት ቆቦቻችን ናቸው
ሚናራዎቻችን ሰንጃዎቻችን ናቸው።
ሙእሚኖች ወታደሮቻችን ናቸው"

ንግግሩን ያደረገው ሌላ ሰው እንዳይመስላችሁ። እንዲህ ብሎ የተናገረው በወቅቱ የኢስታንቡል ከንቲባ የነበረውና አሁን የቱርክ ፕሬዚዳንት የሆነው ረጀብ ጠይብ ኤርዶጋን ነው። ኤርዶጋን የሬፋሕ ፓርቲን ወክሎ በኢስታንቡል ከተማ ምርጫ ምክር ቤት ያሸነፈው በ1994 ነበር። በከንቲባነት ስልጣን ላይ በነበረባቸው አራት ዓመታት ውስጥ ውጤታማ ስራ በመሥራቱ የኢስታንቡል ህዝብ "እጅግ በጣም ምርጥ ከንቲባ" ብሎት ነበር። ታዲያ ኤርባካን ከስልጣን ሲወገድ እርሱ አልተነካም። የሬፋሕ ፓርቲም አልተዘጋም። ኤርዶጋን ከላይ የተጠቀሰውን ንግግር ሲያደርግ ነው ሀይለኞቹ የቱርክ ጄኔራሎች "ሬፋሕ" የሚባለውን ፓርቲ ለማፍረስ የተንቀሳቀሱት።

የሬፋሕ ፓርቲ መፍረስ እውን ሲሆን ኤርዶጋንም ከስልጣኑ መነሳት ግድ ሆነበት። ለሶስት ዓመት ፖለቲካ ውስጥ እንዳይሳተፍም ታገደ።
----
ኤርዶጋን በዚያ ጊዜ በተፈጠረው ሁኔታ የተገነዘበው አንድ ትልቅ ቁም ነገር አለ። ይኸውም ከነጅመዲን ኤርባካን ጋር በአንድ ፓርቲ ውስጥ መሳተፍ ከባድ መስዋእትነት የሚያስከፍል እና መጪውን ጉዞ ጠጣር የሚያደርግ ስለመሆኑ ነው። ኤርባካንን ይዞ ዳግመኛ ወደ ምርጫ መግባት ብዙ እንደማያስኬድም ያወቀው ያኔ ነው። በመሆኑም ከኤርባካን ተለይቶ አዲስ ፓርቲ ለመመሥረት ተንቀሳቀሰ። እነ ዐብዱላህ ጉል እና አሕመድ ዳቪቱግሉን ይዞ AKP (Adalet ve Kalkınma Partisi) የሚባል አዲስ ፓርቲ መሠረተ። ይህ ፓርቲ እጩ አድርጎ ያቀረበው አብዱላህ ጉል በ2002 በተካሄደው የቱርክ ምርጫ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆኖ ተመረጠ። ከዓመት በኋላ በብዙ የፓርቲው ፖለቲከኞች ላይ ተጥሎ የነበረው ገደብ ሲነሳ ደግሞ ረጀብ ጠይብ ኤርዶጋን ሀያ አምስተኛው የቱርክ ጠቅላይ ሚኒስትር ለመሆን በቃ።
------
አፈንዲ ሙተቂ
ጥቅምት 20/2013
© Afendi Muteki, 2020
@umeralfarukk
• • • • •
[••( #አርጦግሩል )••]
• • • • •
•••••••••••••| #ክፍል ➊ |•••••••••••••

በቱርከኛ ቋንቋ "አርጦግሩል" የሚለው ስም ከሁለት ቃላቶች የተመሰረተ ነው። "አር" ማለት ወንድ ወይም ጀግና ማለት ሲሆን "ጦግሩል" ማለት ደግሞ ንስር ማለት ነው። የስሙም ፍቺ "ጀግና ንስር" የሚል ትርጉም ይሰጠናል።

አርጦግሩል እ.ኤ.አ #በ1191 በአኽላጥ ከተማ ተወለደ። ለቤተሰቡ 3ኛ ልጅ ሲሆን Songortikinና Gondogdo የተባሉ ሁለት ታላላቅ ወንድሞችና Dundar የተሰኘ አንድ ታናሽ ወንድም ያሉት ሲሆን የአመራር ብቃቱ፣ እንደ ፅናትና ድፍረት ያሉ ባህሪያቶቹ ግን ከቀሪ ወንድሞቹ እንዲለይ አድርጎታል።

በአርጦግሩል ወላጅ አባት ማንነት ዙሪያ የታሪክ ምሁራኖች ለሁለት ተከፍለዋል። ከፊሎቹ ወላጅ አባቱ ሱለይማን ሻህ ነው ሲሉ ሌሎቹ ደግሞ ጉንዱዝ አልፕ ነው ይላሉ። ለዚህም እንደ ማስረጃ የሚያቀርቡት በዑስማን ቢን አርጦግሩል ዘመን የተሰራ ሳንቲም መገኘቱንና በሱም ላይ የዑስማን፣ የአርጦግሩልና የወላጅ አባቱ ጉንዱዝ አልፕ ስም የተቀረፀበት መሆኑን ነው። ይህ እንዲ ሁኖ ሳለ ግን አብዛኛዎቹ የታሪክ ፀሀፊያን ወላጅ አባቱ ሱለይማን ሻህ ነው በሚለው አቋማቸው ፀንተዋል።

የአርጦግሩል አባት የ"ካይ" ጎሳ መሪ ነበር። ይህ ጎሳ ከቀሪ የቱርክ ጎሳዎች አንፃር ሲታይ ጠንካራ የሚባል አይነት ነው። የአርጦግሮል አባት ከአያቶቹ የወረሰውን ወግና እሳቤ መሬት ላይ ለማውረድ ትልቅ ጥረት ያደረገ ሰው ነው። ልጆቹንም እንደ ጀግንነት፣ ሀይማኖተኝነትና ተበዳይን እንደ መርዳት ባሉ ሰናይ ባህሪያት ኮትኩቶ ነው ያሳደጋቸው።

እ.ኤ.አ በ1227 አርጦግሩል ከሰልጁቃዊት ልዕልት ሀሊማ ጋ የጋብቻ ስነ-ስርአት ፈፀመ። ዘገባዎች የሚያመላክቱት የሀሊማ አባት ከሰልጁቅ ንጉሶች ውስጥ አንዱ የሆነው ሱልጧን ጊያሱዲን መስዑድ መሆኑን ነው። ልዕልት ሀሊማ በሰልጁቆች ቤተመንግሥት ውስጥ ያደገችና በ"ካይ" ጎሳ ታሪክ ውስጥ፣ ከዛም አልፋ የOttoman Empire እንዲመሰረት ትልቅ አስተዋፅኦ ያደረገች ጅግና ናት።

በዚህን ግዜ የ"ካይ" ጎሳ "ቡልግ" አቅራቢያ የምትገኘው "መሀም" ከተማ ውስጥ ሰፍረው ነበር። የሞንጎሎች ንጉስ የሆነው ዢንኪዝ ኻን ወደዚህ በመምጣት የኸዋሪዝሞች ንጉስ የሆነውን አላዑዲን ኸዋሪዝም ሻህ ደምስሶ ከዚህ ስፍራ በሚያወጣበት ግዜ የከተማይቱ ነዋሪዎች ተበታተኑ። የቱርክ ጎሳዎችም ከሞንጎሎች ወረራ ራቅ ብለው ወደሚኖሩበት ስፍራ መሰደድ ጀመሩ። አብዛኞቹ ወደ ኢራንና ሶርያ የተሰደዱ ሲሆን አንዳንዶች ደግሞ ወደ ግብፅ አቀኑ። እንግዲህ በዚ ግዜ ነበር የ"ካይ" ጎሳ መሪ የሆነው የአርጦግሩል አባት ጥገኝነት ፍለጋ የሶርያ ከተማ ወደሆነችው ሀለብ/Aleppo የሄደው። ይቺ ከተማ በቱርኮች ማንነት ላይ ትልቅ የሆነ አሻራ አላት። እንዲሁም የዑስማኒያ Empire እንዲቋቋም የራሷ የሆነ አስተዋፅኦም አድርጋለች።

---------------ይቀጥላል------------

ተቀላቀሉን
👇👇👇👇👇
@umeralfarukk
❤️❤️❤️❤️❤️❤️

[••( #አርጦግሩል )••]
• • • • •
•••••••••••••| #ክፍል 2 |•••••••••••••


•••• ጊዜውም ሄደ። የአርጦግሩል አባት መሞቻ ሰዐቱም ደረሰ። የአርጦግሩል አባት የኤፍራጥስን ወንዝ በሚሻገርበት ጊዜ ወድቆ በህይወት መትረፍ አልቻለም። አርጦግሩልም ከአባቱ ሞት በኋላ የሱን ህልም ለማሳካት በመፈለግ ህዝቦቹን ወደ ተሻለ፣ ሰላም ወደሆነና ዘላቂነት ወዳለው ቦታ ሊወስዳቸው ወሰነ። ነገር ግን የሁለት ታላላቅ ወንድሞቹ (የጎንዶግዶና ሶንጉርትኪን) "የዚህ መንገድ ጉዳቱ ከባድ ነውና በፊት ወደነበርንበት ወደ አኽላጥ እንመለስ" የሚለው ሀሳባቸው ትልቅ እንቅፋት ሆነበት። በዚህም ምክንያት ጎሳው ለሁለት ተከፈለ። አርጦግሩልም እናቱን፣ ታናሽ ወንድሙንና ሀሳቡን የደገፉትን ስዎች በመያዝ ከአናዶል (በአሁኑ ስዓት የቱርክ ኤዢያዊ ክፍል) በስተደቡብ በኩል ወደ ቤዛንታይኖች (የጥንት አውሮፓ ምስራቃዊ ግዛት) ድንበር አመራ።

በመንገድ ላይ ሳሉም አርዚንጃን የተባለ አከባቢ ሲደርሱ አንድ ክስተት ተመለከቱ። ሁለት ሰራዊቶች ሀይለኛና ሞቅ ባለ ጦርነት ውስጥ ናቸው። አንደኛው ጦር የእስልምናን ባንዲራ ተሸክሟል። አርጦግሩልም ከፍ ባለ ቦታ ላይ በመውጣት ጦርነቱን ከሩቁ መከታተል ጀመረ። ብዙም ሳይቆይ ግን የእስልምናው ጦር መዳከምና ወደ ሽንፈት ማምራት ጀመረ። ይህን የተመለከተው አርጦግሩልም ውስጡን የውጊያ ስሜት ወረረው። እነማን እንደሆኑ ሳያውቅና ራሱን ወደ ጦርነቱ በማስገባቱ በራሱና በጎሶቹ ላይ ሊደርስ የሚችለውን ነገር ሳይፈራ የኢስላሙን ጦር ለመደገፍ ከሰራዊቶቹ ጋር በፍጥነት ወረደ። በልቦቻቸው ላይ ፍርሃት እስኪነግስና መራር የሆነ ሽንፈትን እስከሚያቀምሳቸው ድረስ የተቃራኒውን ሀይል በፍጥነትና በሀይለኛው አጠቃ። በዚህም ምክንያት የሙስሊሙ ጦር ሊቀምሰው የነበረውን ሽንፈት ወደ ድል አድራጊነት ቀለበሰው።

በኋላ ላይም ይህ ከሽንፈት ያዳናቸው የኢስላም ጦር የሰልጁቆች (ኢስላማዊ የቱርክ ግዛት) ንጉሥ የሆነው የሱልጣን አላዑዲን ኬይኮባድ ጦር መሆኑን አወቀ። ነገር ግን ከተቃራኒ ሰልፍ የነበረው ሰራዊት የማን ጦር እንደነበር በትክክል አይታወቅም። አንዳንዶች የሞንጎሎች(ከሩቅ ምስራቅ ተነስተው ኤዥያንና አውሮፓን በደም ያጥለቀለቁ ወራሪዎች) ጦር ነበር ይላሉ፤ ከፊሎቹ ደግሞ የቤዛንታይን ጦር ነው ሲሉ የተቀሩት ደግሞ የኸዋሪዝሞች (ከትክክለኛው እስልምና አፈንግጦ የወጣ ቡድን) ንጉሥ የሆነው የሱልጣን ጀላሉዲን ኸዋሪዝም ጦር ነበር ይላሉ። ያም ሆነ ይህ ግን ሶስቱም ጎራዎች የሚስማሙበት አንድ ነገር አላቸው። እሱም አርጦግሩል የሱልጣኑን ጦር ባይረዳ ኖሮ አስከፊ ሽንፈት ይቀምሱ እንደነበር ነው።

ሱልጧን አላዑዲን ኬይኮባድ በዚ ጀግናና ወደር የለሽ መሪ እጅግ ተደሰተ። ከዚ በኋላ ነበር በሱልጣኑና በአርጦግሩል መካከል ትልቅ የሆነ ትስስር የተፈጠረው። አርጦግሩልም ለሰልጁቆች Empire ተከታይ ሆነ።

---------------ይቀጥላል------------

ይቀላቀሉ
👇👇👇👇👇👇👇
@umeralfarukk
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️

[••( #አርጦግሮል )••]
• • • • •
••••••••| #ክፍል 3_(የመጨረሻ )|••••••••••


••••ሱልጣኑም ከቤዛንታይኖች ድንበር አቅራቢያ ከምትገኘው ምዕራብ አናዶልያ (Anatolia) የተወሰነ መሬት በመቁረጥ ጎሳዎቹ የሚሰፍሩበትን ቦታ ሸለመው። የካይ ጎሳም እዛ ሰፈረ። ሱልጧኑ ይህን ቦታ የሰጣቸው በዚ በኩል ያለው የሰልጁቆች ድንበር ከቤዛንታይኖች ጥቃት እንዲጠበቅለት በማሰብ ነበር ተብሏልም። ከዚ ድል በኋላም የተቀሩት የቱርክ ጎሳዎች አርጦግሩልን የራሳቸው መሪ አድርገው በላያቸው ላይ ሾሙት።

ሱልጧኑ ለአርጦግሩል ከቤዛንታይኖች ድንበር ባሻገር በመቆጣጠር ወደ ሰልጁቅ empire እንዲጨምራቸው ፈቀደለት። ብዙም ሳይቆይ ግን አርጦግሩል ሁሉንም በጀግንነቱ አስደነቃቸው።
ከተወሰነ ግዜ በኋላ ሱልጧኑ ለአርጦግሩል የሱጉት ከተማን ፈቀደለት። የዚ ቦታ ስፋት ከ1000 እስከ 2000 ኪ/ሜ square ይገመታል። ነገር ግን ይቺ ትንሽዬ ቦታ ወደፊት በልጁ ዑስማን የምትመሰረተው የዑስማኒያ ስርወ መንግሥት መሰረተ ድንጋይ ነበረች።

እ.ኢ.አ በ1258 በሂጅራ አቆጣጠር ደግሞ በ656 ልጁ ዑስማን ቢን አርጦግሩል በሱጉት ከተማ ተወለደ። ይህ አመት የሞንጎሎች መሪ የሆነው ሆላኮ ኻን ባግዳድን የተቆጣጠረበትና ያንኮታኮተበት አመት ነበር። ነገር ግን ሞንጎሎችም ሆኑ የአውሮፓው አለም ይህ የተወለደው ህፃን በዚች ህዝብ ላይ በድጋሚ ነብስ እንደሚዘራ፣ ፡ሀይማኖቷንም እንደሚያድስና አለምን ለ600 አመት የሚመራ ጠንካራ empire እንደሚመሰርት አላወቁም ነበር።

አርጦግሩልም እጅግ ከረዘመ የትግልና የድል ኑሮ በኋላ አጥንቱ ሰውነቱን መሸከም አልቻለም። ቀኑም ደረሰ። አርጦግሩል በ1281 ይቺን ምድር በመሰናበት ወደ ማይቀረው አለም ተጓዘ። በዚህም ጊዜ እድሜው ከ90 አመት ያልፍ ነበር።

ከአርጦግሩል ህልፈት በኋላ የሱ ተተኪ የሆነው ታናሽ ልጁ ዑስማን ነበር። ዑስማን ጋዚ ልክ እንደ አባቱ አርጦግሩል ትክክለኛ ሙስሊም፣ ጀግናና ደፋር ሰው ነበር። እንዲሁም የአባቱን አርጦግሩል ህልም በማሳካት ከብዙ ትላልቅ ድሎች በኋላ ለ600 አመታት አለምን የገዛውን፣ ሶስት አህጉራትን (ኤዥያ፣ አፍሪካና አውሮፓ) ተሻግሮ የዘለቀውንና ከ20 ሚሊዮን ኪ/ሜ square በላይ ስፋት የነበረውን የOttoman Empire አቋቋመ።

የአርጦግሩል መቃብር በሱጉት ከተማ ውስጥ ይገኛል። በአሁን ስዓት ያለው የሱ መቃብር የተገነባው በሱልጣን አብዱልሃሚድ ሁለተኛው ጊዜ የነበረ ሲሆን የTurkmenistan መንግሥትም ለአርጦግሩል ክብር ስትል በ1998 በዋና ከተማዋ Ashgabat ውስጥ በሱ ስም መስጂድ አስገንብታለታለች።

-----------ተፈፀመ-----------


ይቀላቀሉን
👇👇👇👇👇👇👇
@umeralfarukk
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️

የጆ ባይደን ማሸነፍ ለሙስሊም ሀገራት ያለው አንድምታ ጥቅም ምንድን ነው ?

| ~ በስተመጨረሻ ለሌሎችም ሼር #SHARE ያድርጉ

#የቀድሞው ምክትል ፕሬዝዳን ጆ ባይደን የአሜሪካ 46 ኛው ፕሬዝዳንት ሆነው በነጩ ቤተመንግስት ኦቫል ቢሯቸው አሜሪካን ብቻ ሳይሆን ከነቻይና እና ሩሲያ ጋር ሆነው እየተፋጩ አለምን ሊዘውሩ አንድ እግራቸውን አስገብተዋል። በአሜሪካ የምርጫ ታሪክ የኦባማን ሪከርድ በመስበር በርካታ ምራጮችን ማግኘት የቻሉት ባይደን ፕሬዝዳንትነታቸውን ሊያውጁ በጣት የሚቆጠሩ ድምፆች ብቻ ነው የቀራቸው።

በዚህ ከፍተኛ ፉክክር በተስተዋለበት ምርጫ ጆ ባይደን የሙስሊም አሜሪካዎችን ድምፅ በማግኘት ከትራምፕ በጣም ይልቃሉ። ከ 70 % በላይ የሚሆኑት ሙስሊም አሜሪካዊያን የመረጡት አንጋፋውን ፖለቲከኛ ጆ ባይደንን ነው።
ለመሆኑ የባይደን መመረጥ ለሙስሊም ሀገራት በአጠቃላይ ለሙስሊሞች ምን ማለት ነው ? ለዛሬ ጥቂት ሀገራትን እንመልከት!

1 #ቱርክ :- የአሁኑ የአሜሪካ ምርጫ በከፍተኛ ሁኔታ ይነካታል የምትባለው ሀገር የኤርዶጋኗ ቱርክ ናት። በኤርዶጋን ላይ ከተሞከረው የመፈንቅለ መንግስት በሗላ ከምእራባዊያን ጋር ያላትን ግንኙነት በከፍተኛ ሁኔታ የቀነሰችውና ፊቷን ወደ ሌላ አቅጣጫ ያዞረችው ቱርክ በዘመነ ትራምፕ ወጣ ገባ ግንኙነትን ከአሜሪካ ጋር አሳልፋለች። ከአሜሪካው ፓሴተር ብሩንሰን መታሰር ጋር ተያይዞ አሜሪካ በቱርክ ላይ ማእቀብ ከመጣል ጀምሮ ከፍተኛ የኢኮኖሚ አሻጥር ስትፈፅምባት ብትቆይም በሌላ መልኩ ቱርክ ከትራምፕ የተሻለ የሚባል ጥቅምንም ማግኘት ችላለች።

ነገር ግን አሁን ወደ ስልጣኑ ሊመጡ ከጫፍ የደረሱት ባይደን በቱርክ እና በመሪዋ ኤርዶጋን ላይ የሰነዘሩት ዛቻ እና የሚያቃቅር ገለፃን ተከትሎ ቱርክ ባይደን ባይመረጡ የምትፈልግ ሀገር ነበረች ። ቱርክ ባይደን ቢመረጥስ? በሚል ከፍተኛ ስትራቴጂዎችን እና አካሔዶችን ስትቀምር መቆቷ የሚያጠያይቅ አይሆንም። እናም ባይደን አሁን ወደ ስልጣኑ መጥቷል ይህ ለቱርክ ምን ማለት ነው?

ባይደን ቱርክ ከሩሲያ የ S-400 ፀረሚሳኤልን በመግዛቷ ክፉኛ የተቆጣ ሰው ነው። እናም ቱርክ መሳሪያውን የምትጠቀም ከሆነ ማእቀብ እንደሚጥል ሲዝት ከርሟል። ከዚህ በተጨማሪም በሶሪያ እና አዘርባጃን ጣልቃ ትገባለች በሚል ቱርክን በተደጋጋሚ አውግዟል። መሪዋን ኤርዶጋንንም " አምባገነን " በማለት መዝለፉ ይታወቃል ። ከዚህም አልፎ " በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ተጠቅመን ተቃዋሚዎችን በማጠናከር ኤርዶጋንን ከስልጣን ማስወገድ አለብን" እስከማለትም ደርሷል። ይህ ለቱርክ ከባድ ምልክትን የሚሰጥ ነው።

በትራምፕ ዘመን አሜሪካ ከአውሮፓ ህብረት ጋር የተቃቃረች እና የመካከለኛው ምስራቅ የፖለቲካ ተሳትፎዋን በከፍተኛ ሁኔታ የቀነሰች በመሆኑ ቱርክ ክፍተቱን በሚገባ ተጠቅማበታለች። እናም የአሜሪካን ቦታ ተክታ የቀጠናው አድራጊ ፈጣሪ መሆን ችላለች። ነገር ግን አሁን ባይደን ከአውሮፓ ህበረት ጋር ያለውን ትስስር ማጠናከር ይፈልጋል ። አሜሪካ በአለምአቀፍ መድረክ ያላትን ተሰሚነት እና ተፅእኖም ማሳደግ ይፈልጋል ። ስለዚህ ይህ ከቀጠናው ሀያል ሀገር ቱርክ ጋር የሚያላትመው ይሆናል ።

ባይደንን በአሉታዊ ጎኑ ይህንን ካልን ለቱርክ ሊጠቅም የሚችልበትን ሁኔታ እንይ:-

ጆ ባይደን ሩሲያ እና ቻይናን በከፍተኛ ሁኔታ መገዳደር ይፈልጋል። ልክ እንደ ቱርክ ሁሉ ሩሲያ እና ቻይና እንዲመረጥ የሚፈልጉት ዶናልድ ትራምፕን ነበር። እናም ባይደን ከነዚህ ሀገራት ጋር በሚያደርገው ትግል ውስጭ የኔቶን ወሳኝ እና ከአሜሪካ ቀጥሎ ባለግዙፍ ሀያል ጦር ባለቤት የሆነችውን ቱርክን ማጣት አይፈልግም። በቱርክ ላይ ማእቀብ መጣል ማለት ቱርክን ወደነ ቻይና እና ሩሲያ ምህዋር የበለጠ መግፋት ነው ። ስለሆነም ባይደን ከቃላት ፉከራ የዘለለ በቱርክ ላይ የከፋ ማእቀብ አይጥልም የብዙዎች ግምት ነው።

ከዚህ በተጨማሪ የሚነሳው መልካም ጎን ባይደን ከትራምፕ የበለጠ አስተዋይ እና ተገማች መሆኑ ነው። ይህም በጣም በሳል ለሆነው ለረጀብ ጦይብ ኤርዶጋን የባይደንን አሰላለፍ እና እንቅስቃሴ በሚገባ እንዲገምት እና ተገቢውን ዝግጅት እንዲያደርግ የሚያስችለው ነው። በአለማችን ላይ ካሉ ፖለቲከኞች ሁሉ በጮሌነቱ ተወዳዳሪ የለውም የሚባለው ኤርዶጋን የባይደንን ተገማች አካሔድ የሚያውቅ በመሆኑ ለቱርክ የባይደንን እንቅስቃሴ መቋቋም አይከብዳትም ነው የብዙዎች ሀሳብ። እናም ቱርክ የአሜሪካ ዋና የትኩረት አቅጣጫ ሆና ትቀጥላለች አሜሪካም ቱርክን ልታጣት አትፈልግም ነው እዚህ ጋር የሚነሳው።

2 #ሳኡዲ_አረቢያ :- አንጋፋው መፅሔት Foreign policy ዛሬ ይዞት በወጣው ሀተታው "ሙሀመድ ቢን ሰልማን በባይደን ከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ ነው " በማለት በርእስ አንቀፁ ላይ አስፍሯል። ትራምፕ ለሙሀመድ ቢን ሰልማን እንደ አንድ ወዳጅ መሪ ብቻ አይደለም። እንደ አባትም ፣ እንደ ዋስም ፣ እንደ አዛዥም ጭምር እንጅ። ትራምፕ ቢን ሰልማንን አድርግ ብሎት የማያደርገው አንድት ነገር አይኖርም። ትራምፕ ሳዑዲን ቢሰድባት ቢዘልፋት ቢያዋርዳት የምትታለብ ላም ናት እያለ ቢሳለቅባት የሳኡዲ ንጉሳዊያን ትራምፕን ቀና ብለው አያዩም። ቢን ሰልማንን ከብዙ ፈተናዎች አውጥቶ እዚህ ያደረሰው ትራምፕ እንደመሆኑ ቢንሰልማን የትራምፕን ውለታ ለመመለስ ብዙ ለፍቷል። የ 400 ቢሊዮን ዶላር ስምምነትን ለትራምፗ አሜሪካ ያጎረሰችው ሳኡዲ አሜሪካ ትጠብቃት ዘንዳ ይህን አድርጋለች። ከሁሉ በላይ አንጋፋውን ጋዜጠኛ ጀማል ኻሾቅጂን በግፍ የገደለው ቢን ሰልማን ከአለም አቀፉ ማህበረሰብ እና አሜሪካ ሳዑዲ ሊደርስባት የነበረውን ቅጣት እና ውግዘት የመከተላት ትራምፕ ነበር። በየመን የምታደርገውን ወረራም አይዞሾ ግፊ እያለ የሚያስታጥቃት ትራምፕ ነበር።

አሁን ግን ባይደን እንደዚያ አይደለም። ባይደን የጀማል ኻሾቅጂ ደም በከንቱ ፈሶ አይቀርም ሲልዝቷል! ሴለ ጀማል ኻሾቅጂ ስንል ለነፃነት ለድሞክራሲ እና ፍትህ እንታገላለን ብሏል ባይደን።
ባይደን አክሎም ሳኡዲ አረቢያ ለምትፈፅማቸው የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ተጠያቂ እናደርጋታለን ፤ በየመን በምታደርገው ወረራ የምናደርግላትን ድጋፍም እናቆማለን ፣ እስረኞችን እንድትፈታ ፤ አፈናዋን እንድታቆም ጫና እናደርግባታለን ቦሏል። ትራም ለሳኡዲ እና መሰል ሀገራት ያደረገውን ከድሞክራሲ የሚፃረር ተግባር ሁሉ እንቀለብሳለን ብሏል ጆ ባይደን።

ባይደን አክሎም በሳኡዲ አረቢያ እና በትራምፕ መካከል የተፈረሙ ስምምነቶችን እንደሚቀድ ዝቷል። እነዚህ ስምምነቶች የመላው አለም ሙስሊሞችን ያስቆጡትን ሳኡዲ ከእስራኤል ጋር ያደረገቻቸውን ስምምነቶችን ሳይቀር ያካትታል። በተለይ አሜሪካ አሁን የሳኡዲ የነዳጅ ጥገኛ ባለመሆኗ እና የሳኡዲ ስትራቴጂካዊ አጋርነትም አሁን ያን ያክል በመሆኑ ፤ ከሙስሊሙ አለም ያላት ተቀባይነት እና ተፅእኖ ፈጣሪነትም በከፍተኛ ሁኔታ ያሽቆለቆለ በመሆኑ አሜሪካ ያን ያክል የምትጨነቅላት አይነት ሀገር አትሆንሞ። ይህም ሳኡዲን ከሙስሊሙ አለምም ከአሜሪካም ሳያደርጋት ከሁለት የወጣ ጎመን ያደርጋታል ነው ። እናም ሳኡዲ የተገለለች እና ተፅእኖዋ የተዳከመ ሀገር ትሆናለች ነው። ይህም ለሳኡዲ በተለይም ለሙሀመድ ቢን ሰልማን ቅዠት ነው።

ለዛሬ እንዳይበዛ በዚህ ይብቃን ። በክፍል ሁሉ ስለ ኢራን ፣ ፍልስጤም ፣ ኢራቅ ፣ አፍጋኒስታን ፣ ፓኪስታን ወዘተ እንተነትናለን!

ጸሐፊ አዘጋጅ » Seid Mohammed Alhabeshiy
☺️እስኪ ፈገግ እንበል😉
ፈገግታ ሱናም አይደል?

ሶስት(3) ወጣቶች አንዲትን ልጅ ለትዳር ፈልጉና አባቷን
በየተራ መጠይቅ ይጀምራሉ

አባትየው የመስጂድ ኢማም ነበሩና ለምርጫ እንዲረዳቸው
አንድ ዘዴ ለመጥቀም አሰቡ

አንደኛውን ልጅ ስምህ ማን ይባላል ብልው ጠየቁት?

#ኢብራሂም እባላልው
በል ሱረቱል ኢብራሂምን ቅራ አሉት
ልጁም በሚያምር ድምፅ ቀራላቸው

ሁለተኛውንም ስሙን ጠየቁት
#ዩሱፍ እባላለው ሲላቸው በል
ሱረቱል ዩሱፍን ቅራ አሉት
ልጁም አሳምሮ ቀራላቸው

ሶስተኛውንም ስሙን ጠይቁት ልጁም ፊቱ በላብ ተጥልቅልቆ
#ያሲን እባላለው
ነገር ግን ጋደኞቼ ሰፈር ሲያቆላምጡኝ ቁልሁወላሁአሃድ
፣እያሉ ነው ሚጠሩኝ ብሎ አረፈው😂
"#የቱርክ_ወታደሮች_በቀጥታ_ወደ_ጦርነቱ_እንዲገቡ_ለመጥራት_እንገደዳለን " - ፕሬዝዳንት ኢልሃም አልዬቭ ዛሬ ከሰጡት መግለጫ
¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤

፨ ጦርነቱ እጅግ ከሚጠበቀው ፍጥነት በላይ እየተጓዘ ነው። አዘርባጃን በትላንትናው እለት የናጎርኖ ካራባኽን ሁለተኛ ግዙፍ ከተማ ሹሻን ነፃ ካወጣች በሗላ ዛሬ ፈፅሞ በማይታሰብ ፍጥነት 71 አካባቢዎችኝ ፣ 8 ስትራቴጂካዊ ከፍታዎችን ፣ አንድ ከተማን በአንድ ቀን ውስጥ ነፃ አውጥታለች። ይህ ለአዘርባጃን የማይታሰብ ድል ነው። አዘርባጃን ዛሬ ያወጣቻቸውን 71 አካባቢዎች ጨምሮ በአጠቃላይ እስካሁን 240 አካባቢዎችን ከ አርሜኒያ ነፃ አውጥታለች። ሹሻ ፣ ጂብራይል እና ፉዙሊ የመሳሰሉ ከተሞችን ጨምሮ በርካታ ግዛትችን የከተማ አስተዳደሮችን እና ስትራቴጂካዊ ከፍተኛ ቦታዎችን ነፃ አውጥታለች። አዘርባጃን እየተቀዳጀች ባለችው ከፍተኛ የድል ሞራል ተነሳስታ የጥቃት ፍጥነቷን በከፍተኛ ሁኔታ ጨምራለች። የአርሜኒያ መደምሰስ የሳምንታት ጉዳይ ይመስላል!

፨ የአዘርባጃኑ ፕሬዝዳንት ኢልሃም አልዬቭ በጦርነቱ ጣልቃ ለመግባት የሚፈልጉ ሀገራትን አስጠነቀቁ። እርሳቸው ዛሬ በሰጡት መግለጫ "የትኛውም ሀገር ከአርሜኒያ ወግኜ በዚህ ጦርነት ላይ እሳተፋለሁ ካለ ቱርክ ወደ ጦርነቱ በቀጥታ እንድትገባ ለመጥራት እንገደዳለን " በማለት አስጠንቅቀዋል። እርሳቸው " አሁን የማንንም ጣልቃ ገብነት አንሻም ቱርክ በጦርነቱ በቀጥታ እንድትገባ አንፈልግም ያለን አቅም አርሜኒያን መደምሰስ የሚያስችለን ነው ነገር ግን የትኛውም ሀገር ጣልቃ ለመግባት ቢሞክር እኛም ቱርክ እንጠራለን " በማለት ለሩሲያ የሚሰጥ ማስጠንቀቂያ የሚመስል መግለጫ ዛሬ ሰጥተዋል።
አዘርባጃን አሁን ለተቀዳጀችው ድል ቱርክ የአንበሳውን ድርሻ ትወስዳለች። የቱርክ የአካባቢው ሚዛን ቀያሪነት ሩሲያን እንቅልፍ የነሳ ጉዳይ ሆኗል!!

፨ ይህ በእንድህ እንዳለ በዛሬው እለት በአርሜኒያ ግዛት ውስጥ ይበር የነበረን የሩሲያን ሄሊኮፕተር አዘርባጃን በሚሳኤል መትታ ጣለች። ይህ ጦርነቱን ወደሌላ አቅጣጫ እንዳይወስደው የተሰጋ ሲሆን አዘርባጃን በበኩሉ ሔሊኮፕተሩ ተመቶ የወደቀው በስህተት ነው በዚህም ከፍተኛ ይቅርታ እጠይቃለሁ ብላለች። አዘርባጃን ከዚህም አልፋ በሚሳኤል ለጋየው ሄሊኮፕተር ለሩሲያ ካሳ እንደምትከፍል ገልፃለች ። በሄሊኮፕተሩ ውስጥ የነበሩ ሁለት የሩሲያ ወታደሮች ህይወታቸው አልፏል።

፨ አርሜኒያ ከረጅም ማስተባበል በሗላ የናጎርኖ ካራባኽ ሁለተኛ ግዙፍ ከተማ ሹሻ በአዘርባጃን ቁጥጥር ስር መግባቷን አመነች። ሹሻ ከፍተኛ ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ያላት ከተማ ስትሆን በትላንትናው እለት ነበር ከ 28 አመታት በሗላ ነፃ የወጣችው። አዘርባጃን ሹሻን ነፃ ማውጣቷን በገለፀች ጊዜ አርሜኒያ "ውሸት ነው አሁንም በቁጥጥሬ ስር ናት " ስትል አስተባብላ ነበር። ይሁን እንጅ ዛሬ ሹሻን ማጣቷን አምናለች።

፨ የናጎርኖ ካራባኽ ትልቋ ከተማ #ስቴፓናከርት በአዘርባጃን ሙሉ ቁጥጥር ስር ልትገባ ከጫፍ መድረሷን የአርሜኒያ ናጎርኖ ካራባኽ አስተዳደር አሰታወቀ ። በትላንትናው እለት በአዘርባጃን ነፃ የወጣችው ሹሻ ከተማ ከስቴንፓናከርት 10 ኪሎሜትር ብቻ ነው የምትርቀው ። ይህም የዋና ከተማዋ ነፃ መውጣት የቀናት ጉዳይብቻ አድርጎታል።

አሁን በከተማዋ እና በሌሎችም የአዘርባጃን ግዛቶች የሚኖሩ አርሜናዊያን ግዛቱን እየለቀቁ ወደ አርሜኒያ በከፍተኛ ሁኔታ እየፈለሱ ይገኛሉ። አርሜኒያ በ 30 አመት በፊት በሩሲያ ታግዛ የአዘርባጃንን 20% ግዛት በወረራ ቀምታ ቀተቅጣጠረች ጊዜ በቦታው የሚኖሩ አዘርባጃናዊያን ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈፅማለች ።መስጅዶችኝ ጨምሮ በርካታ ታሪካዊና የአዘርባጃን ነፀብራቅ የሆኑ ተቋማትን ግንባታዎችን አውድማለች። በዚህም በሚሊዮን የሚቆጠሩ አዘርባጃናዊያን ግዛቱን ለቀው ሲሰደዱ የአርሜኒያ ዜጎች መጥተው ሰፍረውበት ነበር። አሁን ግን ግዛቱ ነፃ እየሆነ መምጣቱን ተከትሎ ሰፋሪዎቹ አርሜናዊያን ወደ መጡበት አርሜኒያ በከፍተኛ ሁኔታ እየተሰደዱ ነው!! አሁን ስቴፓናከርት ባዶ ከተማ እየሆነች ነው።

፨ ካለ ቱርክ እና ፓኪስታን ሰንደቅ አላማ የአዘርባጃን ሰንደቅ አላማ ሙሉ አይሆንም በማለት አዘርባጃን ዛሬ ለሁለቱ ሀገራት ያላትን ቦታ ገልፃ የሶስቱ ሀገራት ሰንደቅ አላማ ቀጋራ ሲውለበለብ ውሏል! አዘርባጃን የሰንደቅ አላማ ቀኗን እያከበረች መሆኗን ተከትሎ ነው ካለ ወንድሞቼ የቱርክ እና ፓኪስታን ባንድራ የኔ ባንድራ ሙሉ አይሆንም ስትል የገለፀችው። የቱርክ ፓኪስታን እና አዘርባጃን ሰንደቅዓላማዎች በእኩል በአዘርባጃን ሰማይ ሲውለበለቡ ውለዋል። ሁለቱ ሀገራት ለአዘርባጃን ጠንካራ ድጋፍ በመስጠት ቀዳሚዎቹ ሀገራት ናቸው !

ተጨማሪ ፅሁፎችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሌን ይቀላቀሉ
@umeralfarukk
Forwarded from Kayreddin Official Tube (ما فاتك لم يخلق لك، وما خلق لك لن يفوك.)
Forwarded from Kayreddin Official Tube (ما فاتك لم يخلق لك، وما خلق لك لن يفوك.)
ማሻ አላህ ተመራቂዎች ደስ በሚል በሰላም ዝግጅታቸውንም አጠናቀው፣ እንዲሁም በርካታ ሽልማቶችንም አግኝተዋል።
Comment👉 @kayre_Bot
---------------------------------------
https://www.tg-me.com/kayreddin
https://www.tg-me.com/kayreddin
💐ማሻ አላህ ማሻ አላህ!💐
ወንድሜ #መዕሩፍ_አባስ እጅግ በጣም በማራኪው በውብ ድምፁ፣ የመርከዙን ምርቃት የመክፈቻ፣ ቁርኣን ስነ ስርዓት አደረገ።
ማሻ አላህ፣ አላህ ይጨምርልህ!💐 👉 @kayre_Bot
_______________________
https://www.tg-me.com/kayreddin
https://www.tg-me.com/kayreddin
እናታችን ዓኢሻ (ረድየላሁ አንሀ) እንዲህ ትለናለች፦

➢ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) የተቀበሩት በቤታቸው ውስጥ ነበር እንዲሁም አባቷም አቡበከር (ረድየላሁ አንሁ) ከእርሳቸው ጋር አብሮ ነበር የተቀበረው። ማለትም በእናታችን ዓኢሻ ቤት ማለት ነው።

➢« ሁለቱም ሞተው ከተቀበሩ በኋላ እዛ ቤት እገባ ነበር ስገባም ሂጃቤን ባልተሟላ መልኩ ሳልለብስ ነበር
«እዚህ ቤት ውስጥ የተቀበሩት አባቴና ባሌ ናቸው ሌላ ሰው የለም» እልም ነበር።

➢በአላህ ይሁንብኝ ዑመር ኢብኑል ኸጧብ አብሯቸው ከነሱ ጋር ከተቀበረ በኋላ ግን እዛ ቦታ ላይ አንድም ቀን ሂጃቤን በትክክል ለብሼ (ፊቴን ተሸፍኜ) ቢሆን እንጂ ገብቼ አላውቅም። ምክንያቱም ዑመር ረድየላሁ አንሁ (አጅነብይ በመሆኑ) ሀያዕ አደርጋለው ። »
🙏 #Share 🙏 #Share 🙏
(አህመድ ዘግበውታል )
https://www.tg-me.com/umeralfarukk
https://www.tg-me.com/umeralfarukk
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🇪🇹 #ከጁሙዓ_ቀን_ሱናዎች!
➩ገላን መታጠብ (ትጥበት)።
➩ጥሩ ልብስ መልበስ።
➩ለወንዶች ብቻ! ሽቶ መቀባት

➩ መፋቂያ መጠቀም(ሷክ)።
➩ሱረቱል ከሀፍን ማንበብ።
➩በነብዩ ላያ ሰለዋት ማውረድ።
➩በግዜ ወደ መስጂድ መሄድ።
➩ዱዓ ተቀባይ የሚሆንበትን ሰዓት (ከዐሷር በኋላ) መጠባበቅ።

😘#ውብ_ጁሙዓ ይሁንላችሁ!
ውዶቼ ለአላህ ብዬ እወዳችኋለሁ!
https://www.tg-me.com/Umeralfarukk
https://www.tg-me.com/Umeralfarukk
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🇪🇹 #ከጁሙዓ_ቀን_ሱናዎች!
➩ገላን መታጠብ (ትጥበት)።
➩ጥሩ ልብስ መልበስ።
➩ለወንዶች ብቻ! ሽቶ መቀባት

➩ መፋቂያ መጠቀም(ሷክ)።
➩ሱረቱል ከሀፍን ማንበብ።
➩በነብዩ ላያ ሰለዋት ማውረድ።
➩በግዜ ወደ መስጂድ መሄድ።
➩ዱዓ ተቀባይ የሚሆንበትን ሰዓት (ከዐሷር በኋላ) መጠባበቅ።

😘#ውብ_ጁሙዓ ይሁንላችሁ!
ውዶቼ ለአላህ ብዬ እወዳችኋለሁ!
https://www.tg-me.com/Umeralfarukk
https://www.tg-me.com/Umeralfarukk
Forwarded from Kayreddin Official Tube (I Love Prophet Mohammed!)
Oduu gammachiisaa 🆕

#QAYYABACHIISAA

👇 magaalaa👇👇

#jimmaa_fi_aggaaroo

#qayyabachiisaa
barbaadduu?
👉#Qur'aanafi
barnoota
#sheriaa waliin (#shamarran_shamarraniin
gosa barnootaa hunda
Keessattuu warra afaan #inglizii fi
#afaan_oromoo
Akkasumas hubannoo #ICT barbaaddan hundaaf
karaa laafaa fi gabaabaa ta'een
👉#Keegii kg hanga kutaa #kudha-12 tti dafaa bil.

bilbilaa📱 0917508596
Telegram📲 @fuado2
በሌለህበት ላንተ በጣም የሚከላከልልህ)
#ስነ ምግባርህ ነው‼️‼️
@Kayre_Bot
:¨·.·¨: ❀
 `·. @Kayreddin
___🍃🌸🍃___
🎉ከስር በሊንኩ ይቀ
ላቀሉን👇
https://www.tg-me.com/joinchat-AAAAAFANuIvzkU6jioY53Q
‏بعض الثقوب في صدرك قد توصلك لعالم آخر ترى به الحياة بِشكل واضح 🖤
በልብህ ውስጥ ያሉ አንዳንድ ቀዳዳዎች ሌላ አለም ጋር ሊያገናኙ ይችላሉ ሕይወትን በግልፅ ከሚመለከቱበት 🖤
# የአላህን ማስታወስ አይርሱ

#لا_تنس_ذكر_الله

:¨·.·¨: ❀
 `·. @Kayre_Bot
Http://T.me/Kayreddin
Http://T.me/Kayreddin
💜 የዛሬዋ ሴት ልጅ
ከተዋዋበች ትፈትናለች
ፈገግ ካለች ታስደምማለች
ግን ስታበስል ትገላለች

Https://www.tg-me.com/Kayreddin
Https://www.tg-me.com/Kayreddin
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🇪🇹 #ከጁሙዓ_ቀን_ሱናዎች!
➩ገላን መታጠብ (ትጥበት)።
➩ጥሩ ልብስ መልበስ።
➩ለወንዶች ብቻ! ሽቶ መቀባት

➩ መፋቂያ መጠቀም(ሷክ)።
➩ሱረቱል ከሀፍን ማንበብ።
➩በነብዩ ላያ ሰለዋት ማውረድ።
➩በግዜ ወደ መስጂድ መሄድ።
➩ዱዓ ተቀባይ የሚሆንበትን ሰዓት (ከዐሷር በኋላ) መጠባበቅ።

😘#ውብ_ጁሙዓ ይሁንላችሁ!
ውዶቼ ለአላህ ብዬ እወዳችኋለሁ!
https://www.tg-me.com/kayreddin
https://www.tg-me.com/kayreddin
💜 ብቸኛ ከሆንክ ሀዘን አይሰማህ
ጨረቃ ብቸኛ ሆናም ግን ሰማይ ላይ
ካሉ ነገሮች ውስጥ ውቧ መሆኗን
አስታውስ ።
https://www.tg-me.com/joinchat-UA24iyqyJOqxU2O1
2024/05/22 23:32:38
Back to Top
HTML Embed Code: