ተወዳጆች
አዳም
ከሕቱም ምድር የተወለደ በተፈጥሮ ነው፡፡
እኔን ግን የጠቀመኝ የለም፡፡
ሔዋንም
ከአዳም ግራ ጐን ተወለደች እርሷም በተፈጥሮ ነው፡፡
ለኔ ግን የጠቀመችኝ የለም፡፡
ቃየልም
እንደ ሰው ሁሉ በዘር በሩካቤ ተወለደ የጠቀመኝ የረባኝ የለም፡፡
ስንኳን እኔን እራሱንም አልጠቀመም፡፡ እሊህ ሦስቱ ልደታትም ለማንም ለማን አይረቡም አይጠቅሙም፡፡
ክርስቶስ ግን
ያለዘር ያለሩካቤ ከድንግል ተወለደ ለሁሉ የሚረባ የሚጠቅም ሆነ፡፡
የሔዋን ደኅንነቷ እመቤታችን ሆይ
የድንግልናሽ ኃይል እጅግ የሚያስደንቅ ዕጹብ ነው፡፡
የአዳምን መርግመ ሥጋ መርገመ ነፍስ ያጠፋሽለት
እመቤታችን ሆይ
የማይመረመር ረቂቅ ምሥጢር ባንቺ ተደረገ፡፡
የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት አይለየን❣️
እግዚአብሔር ከሰው ልጅ የማይተባበሩ ሥስት ልደታትን ተወለደ፡፡ እኔም ዐውቄ አደነቅሁ፡፡ ባራተኛው እንጂ የበጎ ዕረፍት አላገኘሁም፡፡
አዳም
ከሕቱም ምድር የተወለደ በተፈጥሮ ነው፡፡
እኔን ግን የጠቀመኝ የለም፡፡
ሔዋንም
ከአዳም ግራ ጐን ተወለደች እርሷም በተፈጥሮ ነው፡፡
ለኔ ግን የጠቀመችኝ የለም፡፡
ቃየልም
እንደ ሰው ሁሉ በዘር በሩካቤ ተወለደ የጠቀመኝ የረባኝ የለም፡፡
ስንኳን እኔን እራሱንም አልጠቀመም፡፡ እሊህ ሦስቱ ልደታትም ለማንም ለማን አይረቡም አይጠቅሙም፡፡
ክርስቶስ ግን
ያለዘር ያለሩካቤ ከድንግል ተወለደ ለሁሉ የሚረባ የሚጠቅም ሆነ፡፡
የሔዋን ደኅንነቷ እመቤታችን ሆይ
የድንግልናሽ ኃይል እጅግ የሚያስደንቅ ዕጹብ ነው፡፡
የአዳምን መርግመ ሥጋ መርገመ ነፍስ ያጠፋሽለት
እመቤታችን ሆይ
የማይመረመር ረቂቅ ምሥጢር ባንቺ ተደረገ፡፡
የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት አይለየን❣️
👍5
ተወዳጆች
ጥበበኛው ሰሎሞን
“ተንሥኢ ወንዒ” የነፍሴ ደስታ የኾንሽ ውድ እናቴ ሆይ ተነሥተሽ ወደ እኔ ነዪ (መኃ ፪፥፲) ብሏታል።
ቅዱስ ያሬድም
«ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ ሞታ ለማርያም የዐጽብ ለኲሉ፤ ሞት ለማናቸውም ሰው ሁሉ የተገባ ነው የማርያም ሞት ግን ሁሉን ያስደንቃል» በማለት ገልጾታል።
አስተርእዮ ማለት መታየት፣ መገለጥ ማለት ነው። ቃሉ አስተርአየ ታየ፣ ተገለጠ ከሚለው የግዕዝ ግሥ የተገኘ ነው። ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በገባው ቃል ኪዳን መሠረት በሥጋ የተገለጠበት(የታየበት) ፣ አንድነት ሦስትነቱም የተገለጠበት ወቅት በመሆኑ ከልደት በዓል እስከ ጥር መጨረሻ በሙሉ ዘመነ አስተርእዮ በመባል ይታወቃል።
የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ሞትና ትንሣኤ በነገረ ማርያም አበው እንደሚያስረዱት ዕረፍቷ በጥር ፳፩ እሑድ ነው ። አባቶቻችን በጾመ ፍልሰታ ውዳሴ ማርያም ቅዳሴ ማርያም ሲተረጉሙ የእረፍቷን ነገር እንዲህ ብለው ይተርካሉ።
የእረፍቷስ ነገር እንደምን ነው ቢሉ ስድሳ አራት ዓመት በዚህ ዓለም ኖራ ጥር ፳፩ በእሑድ ቀን ጌታ እልፍ አዕላፋት መላእክቱን አስከትሎ መጥቶ እናቴ ሆይ ከዚህ ዓለም ድካም ላሳርፍሽ መጣሁ አላት። ልጄ ሰማይና ምድር የማይወስኑህ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በማህጸኔ ተሸክሜ በድንግልና ወልጄህ እሞታለሁን? አለችው። በሲዖል የሚሰቃዩ ነፍሳትን አሳይቶ እናቴ ሆይ ሞትሽ ለእነዚህ ቤዛ ይሆንላቸዋል አላት። እሊህን ከማርክልኝስ ይሁን አለችው። ቅድስት ሥጋዋን ከቅዱስ ነፍሷ ለይቶ በቃለ አቅርንት በዝማሬ መላእክት አሳረጋት። ደቀመዛሙርቱንም ከያሉበት በደመና ጠቅሶ ካለችበት አድርሶ እመቤታችሁን ስጋዋን በክብር አሳርፉ አላቸው። ሐዋርያት በአጎበር አድርገው ወደ ጌቴሰማኒ ይዘው ሲሄዱ አይሁድ ቀድሞ ልጇን ተነሳ ዐረገ እያሉ ሲያውኩን ይኖራሉ አሁን ደግሞ እሷን ተነሳች ዐረገች እያሉ ሊያውኩን አይደለምን በእሳት እናቃጥላታለን ብለው ተነሱ። ታውፋንያ የሚባል አይሁዳዊ ተራምዶ አጎበሩን ጨበጠው። መልአክ መጥቶ በሰይፍ ሁለት እጁን ቀጣው ከአጎበሩ ተንጠልጥሎ ቀረ። በድያለሁ ማሪኝ ብሎ ቢማጸናት እጁ ተመልሶለታል። ከዚህ በኋላ ዮሐንስን ጨምሮ በደመና ነጥቆ ከገነት አግብቶ ከዕፀ ሕይወት ሥር አኖራት።
ቅዱስ ዮሐንስን እንደምን ሆነች አሉት ከገነት ከዕፀ ሕይወት ሥር አለች አላቸው ቅዱስ ዮሐንስ አይቶ እኛ ሳናይ ብለው በነሐሴ መባቻ ጾም ጀመሩ ሁለት ሱባዔ ሲፈጸምም እሑድ አምጥቶ ሰጥቷቸው ቀብረዋታል በሶስተኛው ቀን ማክሰኞ “ከመ ትንሳኤ ወልዳ” እንደ ልጇ ተነሥታለች።

❤7👍7
ተወዳጆች
የሰው ዘር መገኛዎች የነበሩት አዳምና ሔዋን
የእግዚአብሔርን ትእዛዝ አፍርሰው የእባብን ምክር ሰምተው ዕፀ በለስን በመብላታቸው ምክንያት ጸጋቸው እንደተገፈፈ በዘፍ ፫፥፯ ላይ ስናነብብ “እነርሱም ዕራቁታቸውን እንደ ኾኑ ዐወቁ የበለስንም ቅጠሎች ሰፍተው ለእነርሱ ለራሳቸው ግልድም አደረጉ” ይላል
ከዚያም እግዚአብሔር “አዳም ወዴት ነኽ?” ባለው ጊዜ አዳም ለአምላኩ “በገነት ድምፅኽን ሰማኊ ዕራቁቴንም ስለ ኾንኊ ፈራኊ ተሸሸግኹም” በማለት ጸጋው ተገፍፎ ዕርቃኑን እንደ ቀረ ተናግሯል (ዘፍ ፫፥፲)፤
በዚኽም የአዳምና የሔዋን ስሕተት ምክንያት የሰው ልጆች ከጸጋቸው ተራቁተው “ኹላችን እንደ ርኵስ ሰው ኾነናል፤ ጽድቃችንም ኹሉ እንደ መርገም ጨርቅ ነው፤ ኹላችንም እንደ ቅጠል ረግፈናል፤ በደላችንም እንደ ነፋስ ወስዶናል” (ኢሳ ፷፬፥፮)
በሚሉበት ምልአተ ኀጢአት የሰውን ልጆች በመላ እንደ ደመና በከበበበት ዘመን ቅድስት ድንግል ማርያም ግን ምንም ዐይነት የጸጋ ጕድለት የሌለባት አስቀድሞውኑ ከእናቷ ማሕፀን ዠምሮ በመንፈስ ቅዱስ የተጠበቀች በመኾኗ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል “ጸጋን የተመላሽ ሆይ” አላት እንጂ “ገና ወደ ፊት ይመላብሻል" አላላትም፤
በዚኽም እውነተኛ ምስክርነቱ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጥንተ አብሶ ባመጣው የጸጋ መራቈት ውስጥ ነበረች የሚሉ የክሕደት ትምህርቶችን ሙሉ በሙሉ አጥፍቷቸዋልና (ሉቃ ፩፥፳፰)፡፡ .
አንድም ቀዳማዊዉ አዳም መርገም ካልደረሰባት ከኅትምት ምድር እንደተገኘ ኹሉ ክብር ይግባውና ዳግማይ አዳም የተባለ ኢየሱስ ክርስቶስም ጥንተ መርገም ካልደረሰባት ከድንግል ማርያም በኅቱም ድንግልና ተወልዷል፡፡
አንድም ቀዳማዊቷ ሔዋን ከአዳም ጐን ስትገኝ ምንም ጥንተ መርገም እንዳላገኛት፤ ዳግሚት ሔዋን የተባለች ቅድስት ድንግል ማርያምም ስትፀነስ ኾነ ስትወለድ በመንፈስ ቅዱስ ጸጋ ምልእተ ጸጋ ነበረችና ጥንተ መርገም አላገኛትም፡፡
አንድም ሰው ኹሉ በበደል ጕድጓድ በወደቀበት ጊዜ ቅድስት ድንግል ማርያም ብቻ በመንፈስ ቅዱስ ጸጋ ከእናቷ ማሕፀን ዠምራ ከጥንተ መርገም የተጠበቀች ናትና በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ “ጸጋን የተመላኽ" የተባለ ወይም “ጸጋን የተመላሽ” የተባለች ከቅድስት ድንግል ማርያም በቀር ማንም የለምና ሊቁ ከዚኽ በመነሣት አመሰገናት፡፡
የመልክዓ ማርያም አንድምታ❣️

👍12❤4
ድንግል ሆይ🕯🕯🕯️
እንወድሽ ዘንድ ምክንያታችን ብዙ ነው።
✅ ድንግል ሆይ እንወድሻለን
የህይወታችንን ምግብ ክርስቶስን ወልደሽልናልና አይርበንም
የህይወታችንንም መጠጥ ክርስቶስን ወልደሽልናልና
አይጠማንም
ስለዚህ በእውነት ድንግል ማርያም እመቤታችን ሆይ እንወድሻለን
ወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያም ሆይ
አዛኝቱ የኔ እናት
✅ አንቺ የወርቅ መሶብ ነሽ እልሻለሁ
ይህን ማለቴ ወርቅ የሆነ ክርስቶስን ስለወለድሽ ነው
✅ አንቺ የህይወት ውሃ ጉድጓድ ነሽ እልሻለሁ
ይህን ማለቴ የህይወት ውሃ ክርስቶስ ካንቺ ስለፈለቀ ነው
✅ አንቺ የህይወት እንጀራ መሶብ ነሽ እልሻለሁ
ይህን ማለቴ የህይወት ምግብ ክርስቶስን ስለጋገርሽ ነው
✅ አንቺ የመድሃኒት ተክል ነሽ እልሻለሁ
ይህን ማለቴ እውነተኛ መድሃኒት ፍሬ ክርስቶስ ካንቺ ስለበቀለ ነው
✅ አዛኝቱ ድንግል ሆይ ፦
የሚያስፈልገንን ሁሉ ሰጥተሽናል ፡ አንቺ ከሰጠሽን ሌላ አንዳች እንኳን አያስፈልገንም አንዳች እንኳን ፤ ቢርበን እርሱን እንበላዋላን ቢጠማን እርሱን እንጠጣዋለን ቢበርደን እርሱን እንለብሰዋለን ቢያመን እርሱ ሃኪማችን ነው መድሃኒታችን ፡ አስታማሚያችን ነው
✅ ድንግል ሆይ ፦
ልጅሽ ክርስቶስ አንድ ሲሆን ምግብነቱ ግን ለሁሉ የሚያጠግብ ነው
መጠጥነቱ ሁሉን የሚያረካ ነው
ልብስነቱ ሁሉን የሚያሞቅ ነው
መድሃኒትነቱ የሚሹትን ሁሉ የሚፈውስ ነው
✅ ድንግል ሆይ
አንድ ወንድ ብቻ ወለድሽልን
እርሱ ግን ለሁሉ የሚበቃ ነውና
አንቺ ለእኛ የሚያስፈልገውን ሁሉ ወለድሽልን
ስለዚህ በእውነት ድንግል ማርያም እመቤታችን ሆይ እንወድሻለን እናገንሻለን ከፍ ከፍም አናደርግሻለን !!!

❤20👍1
ድንግል ሆይ
ልጅሽ የጎሰቆለውን ብላቴና እንደተቀበለ እኔንም ደግሞ ይቀበለኝ ዘንድ እወዳለሁ፡፡ ልጅሽ ቸር ይቅር ባይ ርኅሩኅ ነውና፡፡ (ሉቃስ ፲፭፣ ፲፬-፲፮)
የተራበ ሆድ ለምግብ እንዲቸኩል ክርስቶስ ደግሞ ይቅር ለማለት ይቸኩላል፡፡
ይህንንም ማለቴ ለጥምቀት ልጆች በፍጹም ንስሐ በተቃጠለም የእግዚአብሔር ፍቅር ለተመለሱት ነው ላልተመለሱት ግን ይቅርታ የላቸውም፡፡
✅ ድንግል ሆይ
የልጅሽ የሥጋው መታረጃ የደሙ መቅጃ ወደሚሆን መጋረጃ ውስጥ ያስገባኝ ዘንድ እታመናለሁ
✅ ድንግል ሆይ
የምስሢር ጠረጴዛ ወደተዘጋጀበት በላዩም የመለኮት ማዕድ የሚሆን የሰማይ እንጀራ በተሠራበት ስፍራ ያስቀምጠኝ ዘንድ እታመናለሁ በጌታችን፡፡
የምሥጢሩ ጽዋዕ ከመለኮት ትስብእት ጎን የመነጨው አምላካዊ ወይን ወደተመላበት ያስቀምጠኝ ዘንድ እታመናለሁ፡፡
✅ ድንግል ሆይ
ነፍስና ሥጋን ባንድነት የሚፈውሰውን ቅዱስ ምሥጢር ያሳትፈኝ ዘንድ እታመናለሁ ድንግል ሆይ መለኮታዊውን ቁርባን ሥጋው ደሙን ለመቀበል እንዲያበቃኝ ደጅ እጸናለሁ፡፡
በተቀበልሁትም ጊዜ ለወቀሳ ለመፈራረጃ አይሁንብኝ ለነፍሴና ለሥጋዬ መድኃኒት ይሁነኝ እንጂ
ድንግል ሆይ
እድል ፈንታዬ ጽዋ ተርታዬም የተቀደሰውን ለውሾች አትስጡ ዕንቋችሁንም በዕሪያዎች ፊት አታኑሩ ከተባለባቸው ጋር አይሁን
ሥጋዬን የበላ ደሜን የጠጣ ሞት አያገኘውም ቢሞትም ይድናል ለዘለዓለምም ይኖራል ተብሎ ከተነገረላቸው ጋራ እንዲሆን ደጅ እጸናለሁ፡፡ (ማቴ ፯፣ ፮)
የእመብርሃን በረከት አይለየን ❣️

🙏3👍2❤1
ነፍስ ሆይ
በእሳት አለንጋ መገረፍ ለኃጥኣን የተገባ እንደሆነ ዕወቂ፡፡ ኩነኔውም የሚያስፈራ ነው እሳቱ የማይጠፋ ትሉ የማያንቀላፋ ነውየሚገርፉትም አይሰንፉም ከመግረፍ አያቋርጹም የሚያስጨንቁትም አያርፉም አያንቀላፉም፡፡
✅ ነፍስ ሆይ
ጨለማ የለበሱ የገሃነም ሠራዊት መላእክተ ጽልመት ይቆዩሻል ፊታቸውም የሚያስፈራ ነው፡፡ ከርሳቸውም ፊታቸው የአንበሳ የሆኑ አሉ፡፡ ፊታቸውም የእባብ ፊት የሆነ ከርሳቸው ውስጥ አሉ፡፡ ከርሳቸውም ፊታቸው የጓጉንቸር ፊት የሆኑ አሉ ዓይናቸውም እንደሚነደው እሳት ነው ጥርሳቸውም በማናፊያ እንዳናፉት ከእሳትም ውስጥ እንደወጣ ብረት ችንካር ነው፡፡
✅ ነፍስ ሆይ
ከልዑል ፍርድ በክርክር መውጫ ማምለጫ እንደሌለሽ ዕወቂ፡፡ የፍጥረቱንም ሁሉ ገዥ ልታሳብይው አትችዪም ኃጢአት ሳትሠሪ አስቀድሞ እርሱ ያውቃል ስትበድዪም መርምሮ ያውቃል፡፡
የዕዳ በደልሽም ደብዳቤ በፈቃዱ ተጽፏል ስላንቺ ደግሞ ምስክር አይሻም ሥራሽም ይመሰክርብሻል የዕዳ በደልሽም ደብዳቤ አንቺው ባፍሽ ታነቢዋለሽ ከሠራሽው ሁሉ የሚሠወርልሽ የለም፡፡
✅ ነፍሴ ሆይ
የምትድኝበትን እኔ እነግርሻለሁ ከዚህ ሁሉ ይልቅ ወደ ቅድስት ድንግል ጩሂ እንዲህም በይ የብርሃን እናት ሆይ በልጅሽ ፊት በደልሁ ኃጢአቴን አስተስርይልኝ፡፡
በኃጢአት የቆሰለውንም ሥጋየን ፈውሽው
የቆሰለውንም ሰውነቴን ለመዳሰስ እጅሽን ዘርጊ
ደዌ ሥጋ ከሚሆን ኃጢአት እንድድን
ከኃጢአትም ደዌ ሁሉ ጤነኛ እንድሆን፡፡
✅ ስለዚህም አንቺን እሻለሁ
ከሲኦልም እኔን ለማዳን እንድትቸይ ዐውቄ የቤትሽን ደጅ መታሁ
ሙሽራ ሆይ እንድገባ ክፈችልኝ የሙሽርነት ቤትሽንም እንዳይ ድንኳንሽንም ዞርሁ መሥዋዕትም ሠዋሁ፡፡
ነገር ግን ከሰቡት መንጎች የእንስሳ መሥዋዕት የምሠዋልሽ አይደለም የምሥጋና መሥዋዕት እሠዋልሻለሁ እንጂ ለልጅሽ ቸርነት ምስጋና አቀርባለሁ፡፡
ከከንፈሮቼም ፍሬ ንጹሑን ቁርባን አሳርጋለሁ እንዲህ ያለው መሥዋዕት ለእግዚአብሔር ያማረ የተወደደ ነውና ዳዊት በመዝሙር እንደናገረ እንዲህ ሲል ለእግዚአብሔር የምስጋና መሥዋዕት ሠዋ ጸሎትህንም ለልዑል ስጠው በመከራህ ቀን ትጠራኛለህ አድንሃለሁ ታመሰግነኝማለህ፡፡
አባ ጊወርጊስ ዘጋስጫ❣️

❤5
ድንግል እመቤቴ ማርያም ሆይ
በኃጥኣን እጅ ከመውደቅ አድኝኝ
በእግዚአብሔር እጅ መውደቅ ስንኳን እጅግ ያስፈራል
✅ ይሁን እንጂ
በሰው እጅ ከመውደቅ በእግዚአብሔር እጅ ብወድቅ ይሻለኛል፡፡
ቁጣው ብዙ እንደሆነ ምሕረቱ ብዙ ነወና እርሱ መሐሪ ነው፡፡
ቁጣውንም በትዕግስት መመለስ ያበዛል በመቅሠፍቱም ሁሉ አያቃጥልም (መዝ ፸፰፣ ፴፰)
ድንግል ሆይ
ከዓመፅ ከሽንገላ አድኝኝ፡፡
በልቡናው ሸንጋይ ሰው የእግዚአብሔርን ምሕረት አያይምና
ድንግል ሆይ
ከመታበይ ልቡናን ከማደንደን አድኝኝ፡፡
ልበ ደንዳና ሰው እግዚአብሔርን ይቃወማልና፡፡
ድንግል ሆይ
ከርኩሰት ሁሉ ከሥጋም መተዳደፍ ከማመንዘርም አድኝኝ የሚያመነዝር የውሻ ደምና ደሙንም ለሰይጣን የሚሠዋ ይመስላልና፡፡
አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ❣️

👍10❤7
ሰአሊ ለነ ማርያም ማኅቶተ ዓለም ስብሕት በአርያም። /3/
እመቤታችን ሆይ ለምኝልን በሰማይ የተመሰገንሽ የዓለም መብራት ነሽና። /3/
ሰአሊ ለነ ማርያም ምዕዳው እምሰርም ዘጽድቅ ተንከተም።
እመቤታችን ሆይ እውነተኛ ድልድይ የረግረግ መሻገሪያ ነሽና።
ሰአሊ ለነ ማርያም አክሊለ ንጹሐን ወብርሃነ ቅድሳን።
እመቤታችን ሆይ ለምኝልን የቅዱሳን ብርሃን የንጹሐን አክሊል ነሽና።
ሰአሊ ለነ ማርያም ሙዳየ ዕረፍት ዘክህነት ወመንግሥት።
እመቤታችን ሆይ ለምኝልን የመንግሥትና የክህነት የሚሆን የሽቱ ሙዳይ ነሽና ለምኝልን።
ሰአሊ ለነ ማርያም ዘወርቅ ማኀየብ ምቅዳሕ ዘሐሊብ።
እመቤታችን ሆይ የወተት መቅጃ የወርቅ ገንዳ ነሽና ለምኝልን።
ሰአሊ ለነ ማርያም አዘቅተ ክብር ምቅዳሕ ዘምሥጢር።
እመቤታችን ሆይ የምሥጢር መቅጃ የክብር ጉድጓድ ነሽና ለምኝልን
ሰአሊ ለነ ማርያም ሙኃዘ ትፍሥሕት ምቅዳሕ ዘትንቢት።
እመቤታችን ሆይ የትንቢት መቅጃ የደሰታ መፍሰሻ ነሽና ለምኝልን።
ስብዓ ለዕለትየ እሴብሐኪ እስመ ተነድፈ ልብየ በፍቅርኪ።
እንዲህ እያልኩ በቀን ሰባት ጊዜ አመሰግንሻለሁ ልቡናዬ በፍቀርሽ ተነድፏልና።
ወትቤ ማርያም ተዓብዮ ነፍስየ ለእግዚአብሔር ወትትሐሠይ መንፈስየ በአምላክየ ወመድኀንየ።
እመቤታችን ሰውነቴ እግዚአብሔርን ታመሰግነዋለች ።
በፈጣሪዬ በመድኀኒቴ አምና ሰውነቴ ደስ ይላታል።

❤9👍7🙏1
እኅቴ ሙሽራ ሆይ
እነሆ የተዋብሽ ነሽ።
ሁለቱ ጡቶችሽ ከወይን ይልቅ ያምራሉ።
ፍቅርሽም የጸና ነው።
ሆድሽም ስንዴ የተጨመረበት በአበባም የታጠረ ነው።
የአፍሽ መዓዛም ከሽቶዎች ሁሉ እንደሚሽት እንደ እንኮይ ነው። ይኸውም የሕያው እግዚአብሔር ልጅ የማሕፀንሽ ፍሬ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
እርሱም
👉 የቅዱሳን ክብራቸው
👉የሌዋውያኑ የክህነታቸው መዓዛ፣
👉ለተመረጠ እስራኤል ልጆችም የንግሥናቸው ቅባት
👉ለተራቡ ስቃይ ከሚከተለው ከጥፋት ሞት በአንቺ ለዳኑ የወንጌል ልጆች /ክርስቲያኖችም/ የቁርባናቸው መዓዛ ነው።

🙏11❤8👍4
የእንድርያስ የሕይወቱ መርከብ፣ የዘብዴዎስ ልጅ ለሆነው ለያዕቆብም የስብከቱ መጽኛ ብፁዕ ለሚሆን ለማቴዎስም የምልክቱ ዘንባባ የምትሆኝ ማርያም ሆይ ነይ። የቶማስ የድንግልናው ቅናት የእልፍዮስ ልጅ ለሆነው ለያዕቆብም የቃሉ ትምህርት፣ ብፁዕ ለሆነ ለታዴዎስም የስንዴ እሸቱ የሆንሽ ማርያም ሆይ ነይ።
የሐዋርያው በርቶሎሜዎስ የወይኑ ፍሬ፣ የአፍራቅያው ሰው የፊልጶስም የማስተማሩ ጸጋ የሰማርያው ናትናኤል የጵጵስናው ሹመት ማርያም ሆይ ነይ። ማትያስን ከስር ቤት ያዳንሽው፣ ያዕቆብን ያሳደግሽው ማትያስን የረዳሽው እጁ ከተቆረጠ በኋላ ተመልሶ የዳነብሽ የሉቃስ አዳኝ ማርያም ሆይ ነይ።
የመላእክት እኅታቸው፣ የነቢያት ትንቢትና ምሳሌ፣ ልጃቸውም፣ ለሐዋርያት የስብከታቸው ሞገስ የሰባ ሁለቱ ደቀመዛሙርት የመመኪያቸው ጽናት፣ የአምስት መቶው ጓደኞች ዘውድ የጻድቃንና የጳጳሳት ማኅበር ሽልማታቸው ማርያም ሆይ ነይ።
የሰማዕታት የክብር አክሊላቸው የሕፃናት እናታቸው የአብያተ ክርስቲያናት መመኪያ፣ የደናግልና የመነኮሳት የንጽሕናቸው መሠረት በሁለት ወገን ድንግል የምትሆኝ ማርያም ሆይ ነይ።

❤11👍6🙏6
ተወዳጆች
እመቤታችን
✅ በዕለተ ዐርብ ትመሰላለች።
በዕለተ ዐርብ በኵረ ፍጥረት አዳም ተገኝቷል፤
ዳግማይ አዳም ጌታችን መድኃኒታችን
ኢየሱስ ክርስቶስ ከእርሷ ተገኝቷልና በዕለተ ዐርብ ትመሰላለች።
✅ በዕለተ ቀዳሚት ሰንበት ትመሰላለች።
በዕለተ ቀዳሚት ሥጋዊ ዕረፍት ተገኝቷል።
“እግዚአብሔርም የሠራውን ሥራ በሰባተኛው ቀን ፈጸመ በሰባተኛውም ቀን ከሠራው ሥራ ሁሉ ዐረፈ”
እንዲል ከእርሷም የመንፈሳውያን ዕረፍት ጌታ ተገኝቷልና።
አዳኝ ከሆነው ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና
ሥርጉት በቅድስና እመቤታትን
ፀጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኝልን።
አእምሮዉን ለብዖውን ጥበቡን እንዳይነሳን ለምኝልን።

❤19