Telegram Web Link
ጸጋ ክብርን የተመላሽ ድንግል ሆይ

👉 ከመግፋት ከመገፋት አድኝኝ፡፡ ቅድስና የተመላሽ ድንግል ሆይ ከመበደል ሌላውንም ከመበደል አድኝኝ፡፡ ከደም አፍሳሽ አድኝኝ፡፡ እኔም ደግሞ የሌላውን ደም ከማፍሰስ ሠውሪኝ፡፡

👉 የተድላ መፍሰሻ ድንግል ሆይ ከሽንገላ አድኝኝ፡፡ ከሸንጋይም ደግሞ ሠውሪኝ፡፡ የምስጋና መፍሰሻ ድንግል ሆይ ከሽሙጥ ከስድብ ከሚያስሽሟጥጥና ከሚሰድብ ደግሞ ሠውሪኝ፡፡

👉 የባለ ጸግነትና የክብር መፍሰሻ ድንግል ሆይ ሰውን ከሰው ከማጣላት አድኝኝ፡፡ ሰውን ከሰው ከሚያጣላ ሐሰተኛ ደግሞ ሰውሪኝ የሕይወት የመድኃኒት ምንጭ ሆይ ከቂምና ከቅናት አድኝኝ ከቂመኛ ከቀናተኛ ደግሞ አድኝኝ፡፡

👉የፈውስ መቅጃ የበረከት አዘቅት ድንግል ሆይ ከፀብ ከክርክር አድኝኝ፡፡ ከሚጣላና ከሚከራከር አድኝኝ፡፡ እሳት የሚለብሱ ኪሩቤልና ሱራፌል በመብረቅ ክንፍ የሚጋርዱሽ የንጉሠ ነገሥት ማደሪያ የምትሆን የብርሃን ድንኳን ሆይ፡፡ በሕይወት በመድኃኒት ጋሻ ጋርጅኝ ከአጋንንት ፍላፃ እንድድን፡፡


የእመብርሃን እረድኤት በረከት አይለየን!!! አሜን
12🙏8
አስታርቂኝ ድንግል ማርያም
5
ተወዳጆች

ለ 0ይን

ከቅንድብ በላይ ማንም ፈጥኖ አይደርስለትም
ዘመድ ቢሆን አክስት ቢሆን የፈለገ ቢሆን
ለ 0ይን ፈጥኖ ደራሽ ቅንድብ ነው።
ከራሳችን እጅ እራሱ ቅንድብ ይደርሰለታል ።

ቅንድብ ከአይን ከሚደርሰው ፍጥነት
ድንግል ማርያም ለሰው የምትደርሰው ፍጥነት ይቀድማል


ድንግል ማርያም ፈጥና ትድረስልን!!!
27🙏1
ተወዳጆች

መስቀሉ

ጌታችንን የተሸከመው ለ 3ት ሰአት ነው።

ድንግል ማርያም ግን

ጌታ ክርስቶስን የተሸከመችው 9 ወር ከ 5 ቀን ነው።

አይደንቃችሁም

ይህ እኮ ከታዕምርም በላይ ነው።
እርሷ እራሷ ድንግል ማርያም እኮ ታአምር እኮ ናት።

የ ወላዲተ አምላክ አማላጅነቷ አይለየን❣️
🙏71
ተወዳጆች

ተአምር ይላችኋል የድንግል ማርያም ማህፀን ነው ።

ሁኖ ማያውቅን ነገር ያመነች ብፅእት
ሄዋን የሌላትን እምነት ይዛ በመገኘት
የሄዋን ጠበቃዋ (ቤዛዋ ) ድንግል ማርያም ናት ።

ሔዋን

በለሱን ስትበላ አምላክነትን ተመኘች
የትዕቢት ሁሉ ዋናውን ተመኘች

ትህትና ዘይት ነው የመንፈስ ቅዱስ ፀጋ መብራት ነው።
ዘይቱ ሲያልቅ መብራቱ ይጠፋል ።

ትህትና

ከሰው ሰውነት ሲጠፋ መንፈስ ቅዱስ ከሰው ይርቃል ።

አዳምና ሔዋን

👉የትህትናቸው ዘይት ሲያልቅባቸዉ
👉የመንፈስ ቅዱስ ብርሃን ከነሱ ራቀ
👉ራቁታቸውን ሆኑ
👉በለስን ቅጠል በልተው አገለደሙ

ድንግል ማርያምሳ

ደስተኛይቱ ሆይ ደስ ይበልሽ ሲላት
እንዲህ ያለ ሰላምታ ለኔ ይገባኛል ? ለፍጡር አለችው
ተመልከቱ ትህትናዋን !!!

በሔዋን

በአለቀው ዘይት ውስጥ
ሞት ወደዚህ አለም ገባ

ነገር ግን

ትህትናን በተሞላቸው እውነተኛይቱ የህይወታችን ማሰሮ
በድንግል ማርያም በኩል መንፈስ ቅዱስ መጣ

ዘይቱ ካለ መብራቱ እንደሚኖር
ትህትና ካለበት መንፈስ ቅዱስ ይኖራልና

ይሄ እንዴት ያለ ሰላምታ ነው ባለች ጊዜ
ፀጋን የተመላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ ያሰኛት ይሄ ነው ።

የድንግል ማርያም አማላጅነት አይለየን🙏

ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን❣️
9🥰1
ተወዳጆች

ሙሉ ናት ድንግል ማርያም
ትህትና የጎደለውን የእናቷን ትህትና ይዛ በመገኘት
የ ሔዋን ቤዛዋ ናት ድንግል ማርያም

በእምነት ማጣት ሞት በ ሔዋን ጆሮ ገባ
በድንግል ማርያም እምነት
ህይወት ቃል ወደ እርሷ ማህፀን ገባ

በሔዋን ትህትና ማጣት ሞት ወደ እኛ ገባ
በድንግል ማርያም ትህትና
ህይወታችን ክርስቶስ ከእርሷ እንዲወለድ ሆነ

የትህትናዋ በር ነው አምላክ ልጇ እንደሆን ያደረገው


ትህትና

የቅድስና ሁሉ መሰረት ነውና

በትህትና በመዋደድ በፍቅር እንኖር ዘንድ
ፈጣሪ ኢየሱስ ክርስቶስ ይርዳን🙏

የእመቤታችን አማላጅነትን በረከት አይለየን🙏
5👍2
ተወዳጆች

ጥበበኛው ሰሎሞን በመኃልይ እንዲህ ይላል

ርግቤ አንዲት ናት መኃልየ 6 ፡ 9

ይህ ምን ማለት ነው ? ብቸኛ ናትማለት ነው ?

አይደለም ብቸኛ ማለት ሳይሆን ልዩ ናት ማለት ነው።

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም

አምላክ ለሰው ልጅ ባደረገው የማዳን ስራ አንዲት ናት ።
ልዩ ናት ያለእርሷ ሊገኝ የማይቻለው ማለት ነው ።

ብዙ ደናግል አሉ

ነገር ግን እርሷ የሰጠችውን የነገረ ድኅነት ስራ መስጠት የሚቻላት እርሷ ብቻ ነች ።

ጥምቀት አንዲት ናት አዎ ጥምቀት ብዙ ነው

ግን የልጅነት ጸጋ የምታሰጥ ጥምቀት አንድ ናት

ብዙ ጌቶች አሉ

እውነተኛ ድህነት የሚሰጥ ጌታ አንድ ነው።

ስለ እመቤታችን ስናወራ ስለ ክርስቶስ እያወራን ነው ስለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እያወራን ነው

እንዴት ያልን እንደሆነ

ስለ መድኃኒቱ እንጨት መናገር ስስ ስለ መድሃኒቱ መናገር ነውና። ስለተክሏ መናገር ስለፍሬዋ መጠንቀቅ ነውና ።


የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት አይለየን🙏
👏6🙏21
ተወዳጆች

ድንግል ማርያም እኮ

እውነተኛይቱ የሐምሌ የነሐሴ ደመና ናት
ዙሮ የማይበተነው ማለት ነው

ቅዱስ ያሬድም ሲናገር

"እራቁ ደመና ዘአልቦ ሙስና ይላል"

ደረቅ ደመና ናት ድንግል ማርያም ይላል።

ቅዱስ ኤፍሬም ደግሞ

"እራቃ ደመና " ይላታል
እርጥብ ደመና ናት አለ ድንግል ማርያም

ምን ማለት ነው ስንል

ደረቅ ደመና መባሏ

👉የወንድ ዘር ያላረፈባት
👉እርግማን ያልወደቀባት ስለሆነች
👉ነውር የሌለባት ስለሆነች
ደረቅ ደመና ትባላለች

እርጥብ ደመና መባሏ እንደምንድን ነው ቢሉ

👉ዝናብ ማየ ሕይወት ውሀ ክርስቶስን
👉ለተጠሙ ነፍሳት ይዛ ስለመጣች
👉እርጥብ ደመና እንላታለን

ደረቁ ደመና እና እርጥቡ ደመና ሲጋጭ

👉መብረቅ እንደሚፈጥር ሁሉ
👉ደረቅ ደመና እና እርጥብ ደመና ከምትባል
👉ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም
መብረቅ ኢየሱስ ክርስቶስ ተወለደ

የ ድንግል ማርያም አማላጅነት አይለየን❣️

ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን
9👎1
ድንግል ሆይ

ከዓመፅ ከሽንገላ አድኝኝ፡፡
በልቡናው ሸንጋይ ሰው የእግዚአብሔርን ምሕረት አያይምና


ድንግል ሆይ

ከመታበይ ልቡናን ከማደንደን አድኝኝ፡፡
ልበ ደንዳና ሰው እግዚአብሔርን ይቃወማልና፡፡


ድንግል ሆይ

ከርኩሰት ሁሉ ከሥጋም መተዳደፍ ከማመንዘርም አድኝኝ የሚያመነዝር የውሻ ደምና ደሙንም ለሰይጣን የሚሠዋ ይመስላልና፡፡

አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ❣️
🙏158👏1
ድንግል እመቤቴ ማርያም ሆይ

በኃጥኣን እጅ ከመውደቅ አድኝኝ
በእግዚአብሔር እጅ መውደቅ ስንኳን እጅግ ያስፈራል
🥰9👏21
ተወዳጆች

አለም ሁሉ ተደምሮ
የአንዷን የፀጉሯን ዘላላ ያህል ክብር የለውም 
የአንዷን የፀጉሯን ዘላላ
አሁን ስለ እመቤታችን ስለምኗ ትናገራላችሁ ?
ሰው ስለምኗ ይናገራል ?
3🙏2👏1
ድንግል ሆይ እታመንሻለሁ ከተሠወረው መከራ በግልጽም ከሚመጣብኝ ጥፋት ሁሉ በዚህ ዓለም እንድታድኝኝ በሚመጣውም ዓለም ከገሃነመ እሳት ጥርስ ማፋጨት ጽኑ ልቅሶም ካለበት ከሚያስጨንቅ መቅሠፍት ትሠውሪኝ ዘንድ እኔም ባንቺ አማላጅነት በልጅሽም ምሕረት የታመንሁ ነኝ፡፡ በፈረሰኞች ሰልፍ በሠረገላም መንኮራኩር የምታመን አይደለሁም፡፡ ባንቺና በልጅሽ ብቻ እታመናለሁ እንጂ፡፡
11🙏3
ድንግል ሆይ

አንድ ወንድ ብቻ ወለድሽልን
እርሱ ግን ለሁሉ የሚበቃ ነውና
አንቺ ለእኛ የሚያስፈልገውን ሁሉ ወለድሽልን
ስለዚህ በእውነት ድንግል ማርያም እመቤታችን ሆይ እንወድሻለን
🙏86
የሰማዕታት የክብር አክሊላቸው የሕፃናት እናታቸው የአብያተ ክርስቲያናት መመኪያ፣ የደናግልና የመነኮሳት የንጽሕናቸው መሠረት በሁለት ወገን ድንግል የምትሆኝ ማርያም ሆይ ነይ።
12🙏1
ድንግል ማርያም እኮ

እውነተኛይቱ የሐምሌ የነሐሴ ደመና ናት
ዙሮ የማይበተነው ማለት ነው
🙏2
ተወዳጆች

መንገድ የሚሄድ ሰው ብዙ ዕንቅፋቶች አሉበት።

የክርስትና ሕይወትም

ሥጋ፣ ዓለም፣ አጋንንት የሚፈትኑት ጉዞ ነው።
ከእነዚህ የሚያድነን የሕይወት መንገድ
ራሱ መድኃኒታችን ክርስቶስ ነው።

መንገድ የሚሄድ ሰው ምልክት አለው።
የሕይወታችን ራስ ክርስቶስም እርሱን እንከተል ዘንድ
እናቱን የመንገዳችን ምልክት አድርጎ ቀድሞ በትንቢት ኋላ በእናትነት ሰጥቶናል።ኢሳ፯፥፲፬ ፣ዮሐ ፲፱፥፳፮

ተወዳጆች

ድንግል ማርያምን በጸሎትም ሆነ በአርአያነት እየተከተልን
ልጇን ልናመልክ ይገባል።

እናት

ልጇን እጁን ይዛ መንገድ ታስተምረዋለች።

እመቤታችንም

👉 የክርስትናን ጉዞ በእናትነት ትመራናለች፤
👉የልጇን ፍለጋ ታሳየናለች።
👉እንደ እናትነቷም ትደግፈናለች።


የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት አይለየን

ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን

✍️ /ዑራኤል
3🙏3
ተወዳጆች

ኧረ! ይሄ ነገር እንደምን ይደንቅ

ሱራፌልና ኪሩቤል አያዩትም።
ቁጥር ስፍር የሌላቸው መላእክት ያገለግሉታል።

ከጌትነቱ ክብር ሳይጎድል ከሰማይ ወረደ።

ሰማይና ምድር የማይችለውን

የድንግል ማርያም ማኅፀን እንደምን ቻለው?
ድንግል ማርያምስ እንደምን ወሰነችው?
እንደምን ቻለችው?”


መምህርነ ቅዱስ ያሬድ❣️

✍️ /ዑራኤል
6🙏1
ተወዳጆች

አለም ሳይፈጠር
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
በአምላክ ልቡና ታስባ ትኖር ነበር


ሰማይ ሲታሰብ

ብርሃናት ሊመላለሱበት ነው።

ድንግል ስትታሰብ ግን

ፀሐየ ጽድቅ ክርስቶስ በሞት ጥላ በክሕደት ጨለማ ለተያዙ የሕይወትን ብርሃን የሚያበራው እውነተኛው ብርሃን ሊገለጥባት ነው።

እግዚአብሔርን ለብሳ የታሰበች ከእርስዋ በቀር ሌላ የለምና እርስዋን ከሁሉ ለይቶ ቅድመ ዓለም የታሰበች ማለት ቢያንስብን ቋንቋ ብናጣ እንጅ መብዛቱስ ዘበት ነው።

ምድር ስትታሰብ

ምግበ ሥጋ ታስገኝ ዘንድ ነው።

ድንግል ማርያም ስትታሰብ ግን

ኅብስተ ሕይወት ፍሬ ሕይወት ክርስቶስን ታፈራ ዘንድ ነው።

ምድር

ለመቃብር ትሆነን ዘንድ ታስባለች።

እመቤታችን ግን

መፍረስ መበስበስን ያስቀረልን ሞትን ድል አድርጎ፥ ከሞት ረግረግ አውጥቶ በተስፋ ትንሣኤ ዐለት ላይ እግረ ልቡናችን ያጸናውን፥

ሞት ሆይ መውጊያህ ወዴት አለ ብለን በሞት ላይ የምንመካበትን ሐዲስ ምስጋና በአንደበታችን ያፈሰሰውን የትንሣኤያችን በኩር ትወልድ ዘንድ የታሰበች ናት።

ርዕሰ ሊቃውንት አባገብረ ኪዳን❣️

✍️ /ዑራኤል
🙏3
ተወዳጆች

ፍጥረታት ክርስቶስን በሚመስሉበት ለእርሱ ክብር ይመሰክራሉ። እናቱን በሚመስሉበት ደግሞ ለእናቱ ክብርይናገራሉ። ምሳሌ፦

ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት

“ሰማያት ይነግራ ስብሐተ እግዚአብሔር- ሰማያት የእግዚአብሔርን ክብር ይናገራሉ” ሲል ዘምሯል። መዝ፲፰፥፩

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

ደግሞ ሰማይ በምን መልኩ የእግዚአብሔርን ክብር ይናገራል የሚለውን ያመሠጥረዋል። ሰማይ ልዑል ነው እግዚአብሔርም ልዑለ ባሕርይ ነው። ሰማይ ብሩህ ነው እግዚአብሔር ብሩህ ነው። ሰማይ ውብ ነው፥ እግዚአብሔር መልካም ነው። ሰማይ ቋንቋ አይገድበውም እግዚአብሔር አበ ልሳናት ነው። ሰማይ የትም ዳርቻ ድረስ አለ እግዚአብሔር ምሉዕ በኩለሄ ነው። ሰማይ ጽኑዕ ነው። እግዚአብሔር ጽኑዐ ባሕርይ ነው። ሰማይ አልተለወጠም፤እግዚአብሔር አይለወጥም።

በዚሁ አንደበታችን ድንግል ማርያምን

በአፈ በረከት ቅዱስ ኤፍሬም ቃል “ዳግሚት ሰማይ ዲበ ምድር-

በምድር ያለች የሰማይ ሁለተኛ ነሽ” እንላታለን

በጠፈር ስንመስላት ሰማይ የብርሃናት መመላለሻ ነው። ወላዲተ አምላክማርያምም የፀሐየ ጽድቅ ክርስቶስ እናት ናት። ሰማይ ከአድማስ ጋር የተያያዘ ነው። ድንግል ማርያምም እናትነትን ከድንግልና አስተባብራ የያዘች ናት። ሰማይ ያማረ ነው። ወላዲተ አምላክም ንጉሠ ሰማይ እግዚአብሔር በእርስዋ ያድር ዘንድ ከዙፋኑ የሳበች ሠናይት ናት። ሰማይ ሐኖስ የሚባለውን ውኃ ጋርዶልን ይኖራል። ድንግል ማርያም ማዕበለ ጌጋይ በንጽሕናዋ ምክንያት እንዲገታ ምክንያት ናት። እግዚአብሔር እንዳይቆጣ ጥበብን ማጽናት በተሳነን ጊዜ ስለ እርስዋ ከገጸ መዐቱ የምንድንባት ሰማይ ናት። ሰማይየዐይን ማረፊያ ናት። ዳግሚት ሰማይ ድንግል ማርያምም የፈጣሪና የፍጡርዐይን ማረፊያ ናት። ፈጣሪ ሰውን ያድን ዘንድ የተመለከታት ተመልክቶ ለመመረጥ የምትገባ ሁኖ ቢያገኛት ለድኅነት ሱታፌ የመረጣት ሰማይናት። ፍጥረታትም ሁሉ ያዩት ዘንድ የሚመኙት ደገኛው ብርሃን ከእርስዋ እንዲወጣላቸው ዐይናቸውን ያሳረፉባት ሰማይ ናት። በመላእክት ከተሞች በሦስቱ ሰማያትም ብንመስላት በዚያ ስብሐተ እግዚአብሔር ሲያቀርቡ እንደሚኖሩ እርስዋንም ከበው ስብሐት ከእግዚአብሔር በሰማያት ወሰካም በምድርሥምረቱ ከሰብሕ- በሰማይ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን በምድርም ለሰው ግዕዛኑ ቢሰጠው ዕርቅ ተወጠነ እያሉ አዲስ ምስጋናቸውን ያሳረጉባት ናት። መላእክት በሰማያቸው ከትመው እንዲኖሩ እመቤታችንም በቤተ ልሔም በዙሪያዋ ከትመው የዋሉባት ምንጊዜም የማይለዩዋት ሀገር መንፈሳዊት ናት። በጽርሐ አርያምም ብንመስላት ያች የእግዚአብሔር ከተማ እንደሆነች ወላዲተ አምላክም የእግዚአብሔር አማናዊት ከተማ ናት። በዚያ መንበረ እግዚአብሔር እንዳለ ብርሃን የሚከባት ፀሐይን የተሸለመች መንበሩ ለንጉሠ ነገሥት በእውነት ከእርስዋ በቀር ማን ነው?

በጣዕመ ፍቅሯ ጨውነት ከጣፈጡት አበው አንዱ ቅዱስ ያዕቆብ ዘስሩግም እንዲህ ይላል፤ “የሰማያት አምላክ በማኅፀኗ የኖረ፥ በእርስዋም ሁኖ ድቅድቁን ጨለማ ከምድር ያስወግድ ዘንድ በጸዳለ ብርሃኑ ያጽደለደለባት ዳግሚት ሰማይ ድንግል ማርያም ናት"

✍️ /ዑራኤል
1🙏1
2025/10/22 15:21:45
Back to Top
HTML Embed Code: