ተወዳጆች
✅ ድንግሊቱ ምድር
የምድር ንጉሥ የሆነውን አዳም
በኅቱምነት ሳለች አስገኘችው፤
✅ ዳግሚት ምድር ሠናይት አማናዊት ድንግል ማርያም ግን
የሰማያትን ሁሉ ንጉሥ
ዛሬ በኅቱም ድንግልናዋ ወለደችው"
በማለት ምሥጢሩን በመዝሙር አመሥጥሮታል።
ቅዱስ ኤፍሬም❣️
✍️ / ዑራኤል
✅ ድንግሊቱ ምድር
የምድር ንጉሥ የሆነውን አዳም
በኅቱምነት ሳለች አስገኘችው፤
✅ ዳግሚት ምድር ሠናይት አማናዊት ድንግል ማርያም ግን
የሰማያትን ሁሉ ንጉሥ
ዛሬ በኅቱም ድንግልናዋ ወለደችው"
በማለት ምሥጢሩን በመዝሙር አመሥጥሮታል።
ቅዱስ ኤፍሬም❣️
✍️ / ዑራኤል
🙏3
ተወዳጆች
✅ ድንግል ማርያም እኮ
ከምድራውያን ተገኝታ መርዓት ዘመንፈስ መንፈሳዊት ሙሽራ ሆናለች። የምድራውያን ወገን ስትሆን ከኅሊና መላእክት በሚበልጥ ንጽሕና ተገኝታለች። የምድራውያን ልጅ ለሰማያውያን ንጉሥ እናት ሁናለች።
✅ ገነት
አዳምና ልጆቹ የከበሩባት ክብረ መንግሥታቸው ናት።
✅ ድንግል ማርያም
በሐዲስ ተፈጥሮ የሰው ልጆች ለክብረ መንግሥት የበቁባት ናት።
✅ በገነት
ሁለቱ ነገሥታት ብርሃን ለብሰው ይኖሩ ነበር።
✅ በወላዲተ አምላክ ግን
ሰዎች ሁሉ ክርስቶስን ለብሰው ለባስያነ እግዚአብሔር ሆኑ።
✅ ቀድሞ በገነት
ሁለት ሰዎች ነገሡ፥
✅ ዛሬ ግን
ጻድቃን በአባታቸው መንግሥት ከፀሐይ ሰባት እጅ ያበሩ ዘንድ ተሰጣቸው።
✅ በመጀመሪያዋ ገነት
የሞት ዛፍ ነበር።
✅ ሁለተኛዋ ገነት ግን
የሕይወት ዛፍ ናትና የሕይወት ፍሬ አፈራችልን።
✅ በቀደመችው ገነት
የሞት ፍሬ በልተን ጠፋን።
✅ በሁለተኛይቱ ገነት
የሕይወት ፍሬ በልተን ተነሣን።
ያች ያልሰጠችንን ዕፀ ሕይወት
በአማናዊት ገነታችን ጠገብነው።
በገነት ውበት የማይደሰት ገነት የማትናፍቀው ማን አለ ?
የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ❣️አማላጅነት አይለየን
✅ ድንግል ማርያም እኮ
ከምድራውያን ተገኝታ መርዓት ዘመንፈስ መንፈሳዊት ሙሽራ ሆናለች። የምድራውያን ወገን ስትሆን ከኅሊና መላእክት በሚበልጥ ንጽሕና ተገኝታለች። የምድራውያን ልጅ ለሰማያውያን ንጉሥ እናት ሁናለች።
✅ ገነት
አዳምና ልጆቹ የከበሩባት ክብረ መንግሥታቸው ናት።
✅ ድንግል ማርያም
በሐዲስ ተፈጥሮ የሰው ልጆች ለክብረ መንግሥት የበቁባት ናት።
✅ በገነት
ሁለቱ ነገሥታት ብርሃን ለብሰው ይኖሩ ነበር።
✅ በወላዲተ አምላክ ግን
ሰዎች ሁሉ ክርስቶስን ለብሰው ለባስያነ እግዚአብሔር ሆኑ።
✅ ቀድሞ በገነት
ሁለት ሰዎች ነገሡ፥
✅ ዛሬ ግን
ጻድቃን በአባታቸው መንግሥት ከፀሐይ ሰባት እጅ ያበሩ ዘንድ ተሰጣቸው።
✅ በመጀመሪያዋ ገነት
የሞት ዛፍ ነበር።
✅ ሁለተኛዋ ገነት ግን
የሕይወት ዛፍ ናትና የሕይወት ፍሬ አፈራችልን።
✅ በቀደመችው ገነት
የሞት ፍሬ በልተን ጠፋን።
✅ በሁለተኛይቱ ገነት
የሕይወት ፍሬ በልተን ተነሣን።
ያች ያልሰጠችንን ዕፀ ሕይወት
በአማናዊት ገነታችን ጠገብነው።
በገነት ውበት የማይደሰት ገነት የማትናፍቀው ማን አለ ?
የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ❣️አማላጅነት አይለየን
❤4
ተወዳጆች
ኧረ! እስኪ እንዲ እያልን ድንግል ማርያምን እናመስግናት
ቡሩካን ኩሎሙ እለ ያፈቅሩኪ ኦ ድንግል ቡሩካን ኩሎሙ እለ ያከብሩኪ ኦ ንግሥት ቡሩካን ኩሎሙ እለ ይዌድሱኪ ኦ ንጽሕት ቡሩካን ኩሎሙ እከ ይሴብሑኪ ኦ ፍሥሕት ቡሩካን ኩሎሙ እለ ያስተበጽዑኪ ኦ ልዕልት ቡሩካን ኩሎሙ እለ ይገንዩ ለንግሥኪ ኦ ውድስት-
✅ ድንግል ሆይ
የሚወዱሽ ሁሉ የተባረኩ ናቸው፥
✅ ንግሥት ሆይ
የሚያከብሩሽ ቡሩካን ናቸው፥
✅ ንጽሕት ሆይ
የሚያወድሱሽ የተባረኩ ናቸው፤
✅ ደስተኛይቱ ሆይ
የሚያመሰግኑሽ የተባረኩ ናቸው፥ ከፍጥረታት በላይ ከፍ ያልሽ ሆይ ንዕድ ክብርት የሚሉሽ የተባረኩ ናቸው፥
✅ የተመሰገንሽ ሆይ
ለእመቤትነትሽ የሚገዙ ንዑዳን ክቡራን ናቸው
አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ❣️
✍️ / ዑራኤል
ኧረ! እስኪ እንዲ እያልን ድንግል ማርያምን እናመስግናት
ቡሩካን ኩሎሙ እለ ያፈቅሩኪ ኦ ድንግል ቡሩካን ኩሎሙ እለ ያከብሩኪ ኦ ንግሥት ቡሩካን ኩሎሙ እለ ይዌድሱኪ ኦ ንጽሕት ቡሩካን ኩሎሙ እከ ይሴብሑኪ ኦ ፍሥሕት ቡሩካን ኩሎሙ እለ ያስተበጽዑኪ ኦ ልዕልት ቡሩካን ኩሎሙ እለ ይገንዩ ለንግሥኪ ኦ ውድስት-
✅ ድንግል ሆይ
የሚወዱሽ ሁሉ የተባረኩ ናቸው፥
✅ ንግሥት ሆይ
የሚያከብሩሽ ቡሩካን ናቸው፥
✅ ንጽሕት ሆይ
የሚያወድሱሽ የተባረኩ ናቸው፤
✅ ደስተኛይቱ ሆይ
የሚያመሰግኑሽ የተባረኩ ናቸው፥ ከፍጥረታት በላይ ከፍ ያልሽ ሆይ ንዕድ ክብርት የሚሉሽ የተባረኩ ናቸው፥
✅ የተመሰገንሽ ሆይ
ለእመቤትነትሽ የሚገዙ ንዑዳን ክቡራን ናቸው
አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ❣️
✍️ / ዑራኤል
👍4
ተወዳጆች
አባ ሕርያቆስ
ቅዳሴ ማርያምን ሲቀድስ ተመስጦውን እንስማው፡፡
✅ እመቤታችን❣️
👉 እሳትን ፀንሳ ያለመለወጧን፣
👉ታናሽ ብላቴና ሁና ሰማይና ምድር የማይችሉትን የመወሰኗን ነገር፣
👉ድንግልስትሆን እናት፥ እናት ስትሆን ድንግል የመሆኗን ነገር፣
👉በብሥራተ መልአክእንደ ንብ የመፅነሷን ነገር፣
👉ሐሊብ ከድንግልና ጋር የመያዟ ነገር፣
👉ድንግል ሆና አጥብታ የማሳደጓ ነገር ሕሊናውን መስጦት ጨልጦ ገርኝቶ ወደ ሰማያት አምጥቆት ነበርና፤ እንዲህ ይላል፡-
“ወሶበ እሔሊ ዘንተ ይፈቅድ ሕሊናየ ይፅብት ዕመቀ አብሕርቲሁ ለወልድኪ - ልቡናዬ የልጅሽን የባሕርዩን ምሥጢር ርቀት ሊመረምር ይወዳል” ይላል፡፡
✅ በሌላ አገላለፅ፥
👉 ድንግል ስትሆን እንደ ምን እናት ሆነችህ?
👉 ጠባብ ስትሆን እንዴት ወሰነችህ?
👉 እሳት ስትሆን እንዴት ፀነሰችህ?
👉 ድንግል ስትሆን እንዴት አጠባችህ?
👉ገረድህ ስትሆን እንዴት ልጇ ሆንህ?
👉ይህን ያደረግህ በምን ምሥጢር ይሆን?
ብዬ ሕሊናዬ ይሰቀላል" ይላል፡፡
የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት አይለየን
አባ ሕርያቆስ❣️
✍️ /ዑራኤል
አባ ሕርያቆስ
ቅዳሴ ማርያምን ሲቀድስ ተመስጦውን እንስማው፡፡
✅ እመቤታችን❣️
👉 እሳትን ፀንሳ ያለመለወጧን፣
👉ታናሽ ብላቴና ሁና ሰማይና ምድር የማይችሉትን የመወሰኗን ነገር፣
👉ድንግልስትሆን እናት፥ እናት ስትሆን ድንግል የመሆኗን ነገር፣
👉በብሥራተ መልአክእንደ ንብ የመፅነሷን ነገር፣
👉ሐሊብ ከድንግልና ጋር የመያዟ ነገር፣
👉ድንግል ሆና አጥብታ የማሳደጓ ነገር ሕሊናውን መስጦት ጨልጦ ገርኝቶ ወደ ሰማያት አምጥቆት ነበርና፤ እንዲህ ይላል፡-
“ወሶበ እሔሊ ዘንተ ይፈቅድ ሕሊናየ ይፅብት ዕመቀ አብሕርቲሁ ለወልድኪ - ልቡናዬ የልጅሽን የባሕርዩን ምሥጢር ርቀት ሊመረምር ይወዳል” ይላል፡፡
✅ በሌላ አገላለፅ፥
👉 ድንግል ስትሆን እንደ ምን እናት ሆነችህ?
👉 ጠባብ ስትሆን እንዴት ወሰነችህ?
👉 እሳት ስትሆን እንዴት ፀነሰችህ?
👉 ድንግል ስትሆን እንዴት አጠባችህ?
👉ገረድህ ስትሆን እንዴት ልጇ ሆንህ?
👉ይህን ያደረግህ በምን ምሥጢር ይሆን?
ብዬ ሕሊናዬ ይሰቀላል" ይላል፡፡
የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት አይለየን
አባ ሕርያቆስ❣️
✍️ /ዑራኤል
❤6🙏1
ተወዳጆች
የክርስቶስ ሰው መሆን እንግዳ ነው፡፡
ከዚያ በፊት አምላክ ሰው ሆኖ አያውቅም፡፡
እንግዲህም ሰው አይሆንምና፡፡
✅ የአቴና ሰዎች
ቅዱስ ጳውሎስ ገብቶ ነገረ ክርስቶስን ሲያስተምራቸዉ “አዲስ ትምህርት" ነበር ያሉት (ሐዋ.፲፯፥፳፩)።
✅ ምክንያቱም
አምላክ ሆኖ ሳለ ሰው የሆነ አምላክ ከእርሱ በቀር ሌላ የለምና፡፡
ሞቶ የሚያድን ከእርሱ በቀር የለምና፡፡
በቀዳማዊነቱ ብልየት፣ እርጅና
በደኃራዊነቱ፣ ኅልፈተ ሞት፣ መለወጥ
በንጉሥነቱ ሽረት፣
በሕያውነቱ ሞት የሌለበት ለዘለዓለም አዲስ ጌታ እርሱ ነው፡፡
✅ የእርሱ ወደ ዓለም መምጣት እንግዳ ነው፡፡
የማይወሰነው መወሰኑ፣
ኃያሉ መድከሙ፣
ሕያዉ መሞቱ ሁሉም እንግዳ ነው፡፡
ይህም እንኳንስ አምላክ ይቅርና
ክቡር ሰውም እንኳን ሲመጣ ክቡር ቤት ያሻል፡፡
✅ ስለዚህም ነገር
ርኵሰት የማይስማማው ንጹሐ ባሕርይ ነውና
ንጽሕት ድንግልን መረጠ፡፡
መርገም የማይስማማው ቡሩክ ነውና
ቡርክት እመቤታችንን ወደደ፡፡
“ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ” ተብሎ የሚመሰገን ነውና
ቅድስት እርስዋን አገኘ፡፡
ርዕሰ ሊቃውንት አባገብረ ኪዳን❣️
✍️/ ዑራኤል
የክርስቶስ ሰው መሆን እንግዳ ነው፡፡
ከዚያ በፊት አምላክ ሰው ሆኖ አያውቅም፡፡
እንግዲህም ሰው አይሆንምና፡፡
✅ የአቴና ሰዎች
ቅዱስ ጳውሎስ ገብቶ ነገረ ክርስቶስን ሲያስተምራቸዉ “አዲስ ትምህርት" ነበር ያሉት (ሐዋ.፲፯፥፳፩)።
✅ ምክንያቱም
አምላክ ሆኖ ሳለ ሰው የሆነ አምላክ ከእርሱ በቀር ሌላ የለምና፡፡
ሞቶ የሚያድን ከእርሱ በቀር የለምና፡፡
በቀዳማዊነቱ ብልየት፣ እርጅና
በደኃራዊነቱ፣ ኅልፈተ ሞት፣ መለወጥ
በንጉሥነቱ ሽረት፣
በሕያውነቱ ሞት የሌለበት ለዘለዓለም አዲስ ጌታ እርሱ ነው፡፡
✅ የእርሱ ወደ ዓለም መምጣት እንግዳ ነው፡፡
የማይወሰነው መወሰኑ፣
ኃያሉ መድከሙ፣
ሕያዉ መሞቱ ሁሉም እንግዳ ነው፡፡
ይህም እንኳንስ አምላክ ይቅርና
ክቡር ሰውም እንኳን ሲመጣ ክቡር ቤት ያሻል፡፡
✅ ስለዚህም ነገር
ርኵሰት የማይስማማው ንጹሐ ባሕርይ ነውና
ንጽሕት ድንግልን መረጠ፡፡
መርገም የማይስማማው ቡሩክ ነውና
ቡርክት እመቤታችንን ወደደ፡፡
“ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ” ተብሎ የሚመሰገን ነውና
ቅድስት እርስዋን አገኘ፡፡
ርዕሰ ሊቃውንት አባገብረ ኪዳን❣️
✍️/ ዑራኤል
❤1
ተወዳጆች
እንደዚህ እንጸልይ
አቤቱ በደልኩ በፊትህም የማይገባኝን አደረኩ::
በበደልኩህም ጊዜ ወደ እናትህ ልመና ተመልከት::
✅ በአመነዘርሁ ጊዜ
👉በተግባርም ቢሆን፣
👉በማሰብም ቢሆን፣
👉በመናገርም ቢሆን
✅ በአመነዘርሁ ጊዜ
👉ተነግሮ ስለማያልቅ
👉አከናውኖም አንደበት ሊናገረው ወደማይችል
👉ወደ እናትህ ንጹሕ ድንግልና ተመልከት::
✅ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ብበድልህ
👉በማኅፀኗ የተሸከመችህን፣
👉በጀርበዋ ያዘለችህን፣
👉በእጆቿ የታቀፈችህን
👉ስለ እኔ በርኅራኄ የምታለቅስልኝን
👉የእናትህን ልመና ምልጃ ተመልከትልኝ"
እያልን ስንለምነው ነው ምሕረት ድኅነት የሚገኘው
የእመብርሃን በረከት አይለየን❣️
✍️ / ዑራኤል
እንደዚህ እንጸልይ
አቤቱ በደልኩ በፊትህም የማይገባኝን አደረኩ::
በበደልኩህም ጊዜ ወደ እናትህ ልመና ተመልከት::
✅ በአመነዘርሁ ጊዜ
👉በተግባርም ቢሆን፣
👉በማሰብም ቢሆን፣
👉በመናገርም ቢሆን
✅ በአመነዘርሁ ጊዜ
👉ተነግሮ ስለማያልቅ
👉አከናውኖም አንደበት ሊናገረው ወደማይችል
👉ወደ እናትህ ንጹሕ ድንግልና ተመልከት::
✅ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ብበድልህ
👉በማኅፀኗ የተሸከመችህን፣
👉በጀርበዋ ያዘለችህን፣
👉በእጆቿ የታቀፈችህን
👉ስለ እኔ በርኅራኄ የምታለቅስልኝን
👉የእናትህን ልመና ምልጃ ተመልከትልኝ"
እያልን ስንለምነው ነው ምሕረት ድኅነት የሚገኘው
የእመብርሃን በረከት አይለየን❣️
✍️ / ዑራኤል
❤4🙏3
ተወዳጆች
ለፍጡራን ለእኛ እናት መሆንም ትርፍና ቀላል ነው፡፡
ከባድ ነገርእኮ ለፈጣሪ እናትነት መብቃት ነው።
✅ የማማለድ ሥልጣንማ እኮ
በባርነት በኃጢአት፣
በመርገም ዘመን ሙሴም ነበረው፡፡
✅ እመቤታችን ግን
እናት ናትና እግዚአብሔርን እባክህ ፊትህን አሳየኝ አትልም፡፡
👉ወልዳ ታቅፈዋለችና፣
👉በከንፈሮቿም ስመዋለችና፣
👉በጀርባዋ አዝለዋለችና፣
👉በማኅፀኗ ወስናዋለችና፤
👉ሀሊበ ድንግልናዋን አጥብተዋለችና፡፡
✅ እርሱም እንደ ሙሴ
ጀርባዬን ታያለሽ አይላትም፡፡
ለሙሴ የታየበት ሥጋ የእርስዋ ሥጋ ነውና፡፡
✅ የወደዳችሁትን በስሜ ብትለምኑ አደርግላችኋለሁ ማለት
ሐዋርያትም ተብለዋል፡፡
እርስዋማ ከዚሁ ሁሉ በላይ ለማንም ያላደረገውን እናትነትን ሰጥቷታል፡፡
✅ ታዲያ እግዚአብሔር
👉ለዝምድና መልአክን አጓዳጅን ልኮ የለመናትን እመቤት
እኛ ከእርስዋ መዛመድን እንተውን?
👉እግዚአብሔር ለእናትነት በመልአክ ያስለመናትን
እኛ እናት ሁኚኝ ብለን በውዳሴዋ አንማጸናትምን?
👉ለንጹሑ ድንግል ለዮሐንስ እናት ትሆነው ዘንድ
ያለ እርስዋ እናትነት የሚሆን ነገር እንደሌለ ዐውቆ፣
በኃጢአት ለተያዝን ለእኛ እንደ ምን እናትነቷ አያሻን!
እንድን ዘንድ ከእመቤታችን ጋር እንዛመድ፡፡
እናቴ እናቴ እንበላት፡፡
በንጽሕና እንመስላት ዘንድ እንውተርተር፡፡
ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን❣️
✍️ / ዑራኤል
ለፍጡራን ለእኛ እናት መሆንም ትርፍና ቀላል ነው፡፡
ከባድ ነገርእኮ ለፈጣሪ እናትነት መብቃት ነው።
✅ የማማለድ ሥልጣንማ እኮ
በባርነት በኃጢአት፣
በመርገም ዘመን ሙሴም ነበረው፡፡
✅ እመቤታችን ግን
እናት ናትና እግዚአብሔርን እባክህ ፊትህን አሳየኝ አትልም፡፡
👉ወልዳ ታቅፈዋለችና፣
👉በከንፈሮቿም ስመዋለችና፣
👉በጀርባዋ አዝለዋለችና፣
👉በማኅፀኗ ወስናዋለችና፤
👉ሀሊበ ድንግልናዋን አጥብተዋለችና፡፡
✅ እርሱም እንደ ሙሴ
ጀርባዬን ታያለሽ አይላትም፡፡
ለሙሴ የታየበት ሥጋ የእርስዋ ሥጋ ነውና፡፡
✅ የወደዳችሁትን በስሜ ብትለምኑ አደርግላችኋለሁ ማለት
ሐዋርያትም ተብለዋል፡፡
እርስዋማ ከዚሁ ሁሉ በላይ ለማንም ያላደረገውን እናትነትን ሰጥቷታል፡፡
✅ ታዲያ እግዚአብሔር
👉ለዝምድና መልአክን አጓዳጅን ልኮ የለመናትን እመቤት
እኛ ከእርስዋ መዛመድን እንተውን?
👉እግዚአብሔር ለእናትነት በመልአክ ያስለመናትን
እኛ እናት ሁኚኝ ብለን በውዳሴዋ አንማጸናትምን?
👉ለንጹሑ ድንግል ለዮሐንስ እናት ትሆነው ዘንድ
ያለ እርስዋ እናትነት የሚሆን ነገር እንደሌለ ዐውቆ፣
በኃጢአት ለተያዝን ለእኛ እንደ ምን እናትነቷ አያሻን!
እንድን ዘንድ ከእመቤታችን ጋር እንዛመድ፡፡
እናቴ እናቴ እንበላት፡፡
በንጽሕና እንመስላት ዘንድ እንውተርተር፡፡
ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን❣️
✍️ / ዑራኤል
❤3🙏1
ወዳጄ!
ሰይጣን
የሚድኑበትን ትቶ የማይድኑበትን ማስወደድ
ክርስቶስን አሳስሮ በርባንን ማስፈታት ልማዱ ነውና
✅ እመቤታችን አልባ
እድናለሁ የሚያስብልህ ሰይጣን እንጂ
መንፈስ ቅዱስ አይደለምና
✅ ጌታ ያስጠነቀቀው ቃል
“ኩን ጠቢበ ለዕድውከ ፍጡነ -ጠላትህን ፈጥነህ ዕወቅበት” (ማቴ1፭፥፳፭)፡፡
ከድንግል ማርያም ጋር ተዛመድ፧
ተወዳጅ፤ ውዳሴዋን ቅዳሴዋን ድገም፡፡
✅ ከዳዊት ጋርም
“ለቤትከ ይደሉ ስብሐት ለነዋህ መዋዕል -
አቤቱ ለቤትህ ለድንግል ማርያም ለዘለዓለም ምስጋና ይገባል” (መዝ፺፪÷፭)በል ብዬ እመክርሃለው፡፡
ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን❣️
✍️ / ዑራኤል
ሰይጣን
የሚድኑበትን ትቶ የማይድኑበትን ማስወደድ
ክርስቶስን አሳስሮ በርባንን ማስፈታት ልማዱ ነውና
✅ እመቤታችን አልባ
እድናለሁ የሚያስብልህ ሰይጣን እንጂ
መንፈስ ቅዱስ አይደለምና
✅ ጌታ ያስጠነቀቀው ቃል
“ኩን ጠቢበ ለዕድውከ ፍጡነ -ጠላትህን ፈጥነህ ዕወቅበት” (ማቴ1፭፥፳፭)፡፡
ከድንግል ማርያም ጋር ተዛመድ፧
ተወዳጅ፤ ውዳሴዋን ቅዳሴዋን ድገም፡፡
✅ ከዳዊት ጋርም
“ለቤትከ ይደሉ ስብሐት ለነዋህ መዋዕል -
አቤቱ ለቤትህ ለድንግል ማርያም ለዘለዓለም ምስጋና ይገባል” (መዝ፺፪÷፭)በል ብዬ እመክርሃለው፡፡
ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን❣️
✍️ / ዑራኤል
❤3👍1
ተወዳጆች
✅ ፍጡር
👉ቢያምንም ቢያመሰግንም፣
👉ቢጋደልም፣
👉ኃይላት፣ ተአምራት ወመንክራት ቢያደርግም
የአገልጋይነት ወይም የልጅነት ባለሟልነት ነው የሚያገኘው እንጂ
የእግዚአብሔር አባት ወይም እናት የመሆን ባለሟልነት አያገኝም፡፡
✅ መላእክት እንኳን
ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ እስከ ዘለዓለም ቢያመሰግኑ
ሠራዊተ እግዚአብሔር ይባላሉ እንጂ እናቱ አባቱ ለመሆን አይችሉም።
ከሰው ወገን የመጨረሻው ክብር የልብ ንጽሕና ነው፡፡
ማንም ለዚህ ማዕርግ ቢበቃ
እግዚአብሔርን ያያል እንጂ እግዚአብሔርን አይወልድም፡፡
✅የሰው
የመጨረሻው ክብሩ፣
መመኪያው እግዚአብሔርን ዐውቆ መስሎ መኖር ነው፡፡
“የሚመካ በዚህ ይመካ” እግዚአብሔርን በማወቅ ለዚያውም በዓቅሙ!
✅ ሰው
በመጨረሻ ክብሩ እግዚአብሔርን ያያል እንጂ
እግዚአብሔርን አይወልድም ፡፡
✅እመቤታችን ግን❣️
ለእግዚአብሔር “እናት የመሆን" ሥልጣን ተሰጥቶአታል፡፡
ቢሰጣትማ ምን ይደንቃል ቢሰጡት አይቀበል አለን? ቢሉ
ለዚህ ክብር የሚያበቃትን ንጽሕና ጠብቃ ይዛ ብትገኝ መረጣት እንጅ፡፡
ለፍጡራን ለእኛ እናት መሆንም ትርፍና ቀላል ነው፡፡
የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ❣️ አማላጅነት አይለየን🙏
✍️ /ዑራኤል
✅ ፍጡር
👉ቢያምንም ቢያመሰግንም፣
👉ቢጋደልም፣
👉ኃይላት፣ ተአምራት ወመንክራት ቢያደርግም
የአገልጋይነት ወይም የልጅነት ባለሟልነት ነው የሚያገኘው እንጂ
የእግዚአብሔር አባት ወይም እናት የመሆን ባለሟልነት አያገኝም፡፡
✅ መላእክት እንኳን
ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ እስከ ዘለዓለም ቢያመሰግኑ
ሠራዊተ እግዚአብሔር ይባላሉ እንጂ እናቱ አባቱ ለመሆን አይችሉም።
ከሰው ወገን የመጨረሻው ክብር የልብ ንጽሕና ነው፡፡
ማንም ለዚህ ማዕርግ ቢበቃ
እግዚአብሔርን ያያል እንጂ እግዚአብሔርን አይወልድም፡፡
✅የሰው
የመጨረሻው ክብሩ፣
መመኪያው እግዚአብሔርን ዐውቆ መስሎ መኖር ነው፡፡
“የሚመካ በዚህ ይመካ” እግዚአብሔርን በማወቅ ለዚያውም በዓቅሙ!
✅ ሰው
በመጨረሻ ክብሩ እግዚአብሔርን ያያል እንጂ
እግዚአብሔርን አይወልድም ፡፡
✅እመቤታችን ግን❣️
ለእግዚአብሔር “እናት የመሆን" ሥልጣን ተሰጥቶአታል፡፡
ቢሰጣትማ ምን ይደንቃል ቢሰጡት አይቀበል አለን? ቢሉ
ለዚህ ክብር የሚያበቃትን ንጽሕና ጠብቃ ይዛ ብትገኝ መረጣት እንጅ፡፡
ለፍጡራን ለእኛ እናት መሆንም ትርፍና ቀላል ነው፡፡
የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ❣️ አማላጅነት አይለየን🙏
✍️ /ዑራኤል
ኩለንታኪ ሠናይት እንተ ኀቤየ አልብኪ ነውር ወኢምንትኒ ላዕሌኪ -
ተወዳጆች
ድንግል ማርያም እኮ
ወዳጄ ሆይ ሁለንተናሽ ውብ ነው፤
ምንም ነውር የለብሽም” ተብሎ የተዘመረላት
“ቡርክት አንቲ እምአንስት -
ከሴቶች ተለይተሽ አንቺ የተባረክሽ ነሽ” ተብሎ የተመሰከረላት
ድንግል እንድትመጣ ለማብሠር ነው (መኃ.፬፥፯፣ ሉቃ.፩፥፳፰)፡፡
✅ የሙታን ሬሳ በወደቀበት
የሙታን መንደር ቄጠማ በአፏ ይዛ
በነጫጭ ክንፎቿ ትበር እንደ ነበረቸው ርግብ
✅ በኃጥአን ዓለም
👉በንጽሕና ክንፍ ትበር የነበረች፣
👉 ከወርቅ ይልቅ የጠሩ የንጽሕና ክንፎች ያሏት፣
👉 ሞትና ኃጢአት ያልሠለጠነባት ጽድልት እመቤታችን ናት ::
በውስጥ በአፍአ በንጽሕና ያጌጠች
በቅድስና የወርቅ ሐመልማል የተሸለመች
ክነፈ ርግብ በብሩር ዘግቡር
ወላዲተ አምላክ ናት፡፡
✍️ / ዑራኤል
ተወዳጆች
ድንግል ማርያም እኮ
ወዳጄ ሆይ ሁለንተናሽ ውብ ነው፤
ምንም ነውር የለብሽም” ተብሎ የተዘመረላት
“ቡርክት አንቲ እምአንስት -
ከሴቶች ተለይተሽ አንቺ የተባረክሽ ነሽ” ተብሎ የተመሰከረላት
ድንግል እንድትመጣ ለማብሠር ነው (መኃ.፬፥፯፣ ሉቃ.፩፥፳፰)፡፡
✅ የሙታን ሬሳ በወደቀበት
የሙታን መንደር ቄጠማ በአፏ ይዛ
በነጫጭ ክንፎቿ ትበር እንደ ነበረቸው ርግብ
✅ በኃጥአን ዓለም
👉በንጽሕና ክንፍ ትበር የነበረች፣
👉 ከወርቅ ይልቅ የጠሩ የንጽሕና ክንፎች ያሏት፣
👉 ሞትና ኃጢአት ያልሠለጠነባት ጽድልት እመቤታችን ናት ::
በውስጥ በአፍአ በንጽሕና ያጌጠች
በቅድስና የወርቅ ሐመልማል የተሸለመች
ክነፈ ርግብ በብሩር ዘግቡር
ወላዲተ አምላክ ናት፡፡
✍️ / ዑራኤል
ድንግል ሆይ
"ኦ ድንግል ጸቃውዕ እንተ ተቀድኃት
እምአፈ አንበሳ ምውት በእደ ወልደ ማኑሔ"
በማኑሔ ልጅ በሶምሶን እጅ ከሞተ አንበሳ
የተቀዳሽ የማር ወለላ አንቺ ነሽ
አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ❣️
✍️ / ዑራኤል
"ኦ ድንግል ጸቃውዕ እንተ ተቀድኃት
እምአፈ አንበሳ ምውት በእደ ወልደ ማኑሔ"
በማኑሔ ልጅ በሶምሶን እጅ ከሞተ አንበሳ
የተቀዳሽ የማር ወለላ አንቺ ነሽ
አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ❣️
✍️ / ዑራኤል
❤3
ተወዳጆች
ኤልሳቤጥ
የነቢያት መጨረሻ የሆነውን ነቢይ ወለደች፡፡
ታናሿ ሙሽራ ድንግል ግን
የመላእክትን ጌታ ወለደች፡፡
የአሮን ልጅ ኤልሳቤጥ
በምድረ በዳ የሚጮኸውን ድምፅ ወለደች፡፡
የዳዊት ልጅ ግን
ኃያል የምድሩን ጌታ ወለደች፡፡
መካኒቱ
ስለ ራሱም ስለ ሕዝቡም የኃጢአት ይቅርታ የሚለምነውን ወለደች፡፡
ድንግል ግን
ኃጢአትን የሚደመስሰውን ወለደች::
ኤልሳቤጥ
ሕዝቡን በንስሓ ከእግዚአብሔር ጋር የሚያስታርቀውን ወለደች።
እመቤታችን ማርያም ግን
ምድርን ሁሉ የሚያነጻውን የሚያጠራውን የሚቀድሰውን ወለደች፡፡
ቀዳማዊቷ መካኒት ኤልሳቤጥ
ለቤተ ያዕቆብ የሚያበራውን መብራት ፋና ወለደች፡፡
ታናሿ ድንግል ግን
ለዓለሙ ሁሉ የሚያበራውን የጽድቅ ፀሐይ ወለደች
የእመብርሃን አማላጅነት አይለየን
ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ❣️
✍️ / ዑራኤል
ኤልሳቤጥ
የነቢያት መጨረሻ የሆነውን ነቢይ ወለደች፡፡
ታናሿ ሙሽራ ድንግል ግን
የመላእክትን ጌታ ወለደች፡፡
የአሮን ልጅ ኤልሳቤጥ
በምድረ በዳ የሚጮኸውን ድምፅ ወለደች፡፡
የዳዊት ልጅ ግን
ኃያል የምድሩን ጌታ ወለደች፡፡
መካኒቱ
ስለ ራሱም ስለ ሕዝቡም የኃጢአት ይቅርታ የሚለምነውን ወለደች፡፡
ድንግል ግን
ኃጢአትን የሚደመስሰውን ወለደች::
ኤልሳቤጥ
ሕዝቡን በንስሓ ከእግዚአብሔር ጋር የሚያስታርቀውን ወለደች።
እመቤታችን ማርያም ግን
ምድርን ሁሉ የሚያነጻውን የሚያጠራውን የሚቀድሰውን ወለደች፡፡
ቀዳማዊቷ መካኒት ኤልሳቤጥ
ለቤተ ያዕቆብ የሚያበራውን መብራት ፋና ወለደች፡፡
ታናሿ ድንግል ግን
ለዓለሙ ሁሉ የሚያበራውን የጽድቅ ፀሐይ ወለደች
የእመብርሃን አማላጅነት አይለየን
ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ❣️
✍️ / ዑራኤል
❤5
ተወዳጆች
ዘካርያስ
ልብሰ ተክህኖውን ለብሶ በመቅደስ እንዳገለገለ
አማናዊ ሊቀ ካህናት ክርስቶስ
እናቱን ልብሰ ተክህኖ አድርጎ እርስዋኑ መቅደስ አድርጎ በማኅፀን ተወስኖ አገለገለ፡፡
ሰው ዕንጨት ጠርቦ የሠራት የፍጡር መቅደስ ያይደለች
መልክዐ ሥላሴ ያላት ንጽሕት፣
አካላዊ ቃል መሥዋዕት ይሆን ዘንድ
ከእርስዋ አካልን የነሣባት መንፈሳዊት መቅደስ እመቤትችን !
👉በዘር በሩካቤ ያይደለ
👉በመንፈስ ቅዱስ የጸነሰች
👉የሰው እጅ ያልሠራት መቅደስ እመቤታችን (ማቴ.፩፥፲፰)!
👉ሰው የማይመረምራት፣
👉ሰው ያልለመዳት ግርምት ዕጹት መቅደስ!
👉የቀድሞይቱ መቅደስ ስትከፈት አልተዘጋችም፤ ስትዘጋ አልተከፈተችም፡፡
ድንግል ማርያም ግን
👉እንደታተመች አካላዊ ቃል ወደ ማኅፀኗ ገባ፡፡
👉ማኀጸኗ እንደታተመ ወለደችው፡፡
“ይህ በርተዘግቶ ይኖራል እንጂ አይከፈትም፤
ሰው አይገባበትም
የእስራኤል አምላክእግዚአብሔር ገብቶበታልና ተዘግቶ ይኖራል"
እንዲል
በሰው ልማድ ያይደለ እርሱ በሚያውቀው ጥበብ ራሱ ገብቶ ያገለገለባት ክብርት ማደሪያው እርስዋ ናት (ሕዝ.፵፬፥፪)።
ተወልዶ በኋላም ሲያድግ ወደ መቅደስ ነበር የወሰደችው፤
ጠፍቶም ሲፈለግ በመቅደስ በሊቃውንት መኃል ነበር የተገኘው፡፡ ሊሰቀል ሲቀርብም በመቅደስ የሚሸጡትና የሚለውጡትን አስወጥቶ መቅደሱን አንጽቶ ነበር የተሰቀለው፡፡
የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ❣️ አማላጅነት አይለየን
ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን❣️
✍️ ዑራኤል
ዘካርያስ
ልብሰ ተክህኖውን ለብሶ በመቅደስ እንዳገለገለ
አማናዊ ሊቀ ካህናት ክርስቶስ
እናቱን ልብሰ ተክህኖ አድርጎ እርስዋኑ መቅደስ አድርጎ በማኅፀን ተወስኖ አገለገለ፡፡
ሰው ዕንጨት ጠርቦ የሠራት የፍጡር መቅደስ ያይደለች
መልክዐ ሥላሴ ያላት ንጽሕት፣
አካላዊ ቃል መሥዋዕት ይሆን ዘንድ
ከእርስዋ አካልን የነሣባት መንፈሳዊት መቅደስ እመቤትችን !
👉በዘር በሩካቤ ያይደለ
👉በመንፈስ ቅዱስ የጸነሰች
👉የሰው እጅ ያልሠራት መቅደስ እመቤታችን (ማቴ.፩፥፲፰)!
👉ሰው የማይመረምራት፣
👉ሰው ያልለመዳት ግርምት ዕጹት መቅደስ!
👉የቀድሞይቱ መቅደስ ስትከፈት አልተዘጋችም፤ ስትዘጋ አልተከፈተችም፡፡
ድንግል ማርያም ግን
👉እንደታተመች አካላዊ ቃል ወደ ማኅፀኗ ገባ፡፡
👉ማኀጸኗ እንደታተመ ወለደችው፡፡
“ይህ በርተዘግቶ ይኖራል እንጂ አይከፈትም፤
ሰው አይገባበትም
የእስራኤል አምላክእግዚአብሔር ገብቶበታልና ተዘግቶ ይኖራል"
እንዲል
በሰው ልማድ ያይደለ እርሱ በሚያውቀው ጥበብ ራሱ ገብቶ ያገለገለባት ክብርት ማደሪያው እርስዋ ናት (ሕዝ.፵፬፥፪)።
ተወልዶ በኋላም ሲያድግ ወደ መቅደስ ነበር የወሰደችው፤
ጠፍቶም ሲፈለግ በመቅደስ በሊቃውንት መኃል ነበር የተገኘው፡፡ ሊሰቀል ሲቀርብም በመቅደስ የሚሸጡትና የሚለውጡትን አስወጥቶ መቅደሱን አንጽቶ ነበር የተሰቀለው፡፡
የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ❣️ አማላጅነት አይለየን
ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን❣️
✍️ ዑራኤል
❤4
ተወዳጆች
ድንግል ማርያም እኮ
👉ከሰማያት ይልቅ የመጠቀች
👉ከብርሃን ይልቅ የጠራች
👉ከህሊና የራቀች ንዕድ ክብረት
👉የመብረቀ ስብሐት እናት
👉የቅዱሳንን ምስጋና በሰማችበት ጆሮቿ
የኃጥአንን ልመና የማትንቅ ርኅርኅት እመቤት
👉0ዘቅተ ክብር ( የክብር ምንጭ )
👉ምቅዳሕ ዘምስጢር (የምስጢር መቅጃ )
👉ስለ ደግነቷ እናታችን
👉ስለ ወላዲት አምላክነቷ ንግሥታችን
👉የመናንያን ተስፋቸው
👉የባሕታውያን ርግብ ናት።
የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት አይለየን
✍️ / ዑራኤል
ድንግል ማርያም እኮ
👉ከሰማያት ይልቅ የመጠቀች
👉ከብርሃን ይልቅ የጠራች
👉ከህሊና የራቀች ንዕድ ክብረት
👉የመብረቀ ስብሐት እናት
👉የቅዱሳንን ምስጋና በሰማችበት ጆሮቿ
የኃጥአንን ልመና የማትንቅ ርኅርኅት እመቤት
👉0ዘቅተ ክብር ( የክብር ምንጭ )
👉ምቅዳሕ ዘምስጢር (የምስጢር መቅጃ )
👉ስለ ደግነቷ እናታችን
👉ስለ ወላዲት አምላክነቷ ንግሥታችን
👉የመናንያን ተስፋቸው
👉የባሕታውያን ርግብ ናት።
የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት አይለየን
✍️ / ዑራኤል
🙏3❤2👍2
ተወዳጆች
ዲያብሎስ በሚገድል ማፅናናት
አይዟችሁ አምላክ ትሆናላችሁ እያለ ገድሎን ነበር፤
እርስዋ ደግሞ አይዟችሁ እኔ ዓለሙን አሸንፌዋለሁ
ደስታችሁን የሚወስድባችሁ የለም የሚለውን መድኀኒት ወለደችልን፡፡
እየተፅናናን ሞተን ነበር፤ እየተፅናናን ዳን፡፡
በውሸት ማፅናናት የጠፋነውን በእውነት ያፅናናችን እመብርሃን ናት፡፡
“ናዛዚትነ እምኀዘን ወኃይለ ውርዙትነ እምርስአን
በማኅፀንኪ ተጸውረ ብሉየ መዋዕል ኅፃን
ኦ ማርያም ተስፋ ለቅቡጻን
በጊዜ ጸሎት ወዕጣን
ወበጊዜ ቅዱስ ቁርባን
ለናዝዞትነ ንኢ ኀበ ዝ መካን"
ከኀዘን የምታፅናኝን ከእርጅና የምታድሽን አንቺ ነሽ፤
ቀዳማዊ ጌታ ሕፃን ሆኖ በማኅፀንሽ አድሯልና
እመቤታችን ማርያም ሆይ
ተስፋ የቆረጡት ተስፋቸው ነሽ፤
በጸሎትና በዕጣን በቁርባንም ጊዜ
ኃጢኣታችንንም አሥተሥርየሽ ለመቀበል ታበቂን ዘንድ
ወደዚህ ቦታ ነይልን” እያልን የምንማፀናት ለዚህ ነው፡፡
✍️ / ዑራኤል
ዲያብሎስ በሚገድል ማፅናናት
አይዟችሁ አምላክ ትሆናላችሁ እያለ ገድሎን ነበር፤
እርስዋ ደግሞ አይዟችሁ እኔ ዓለሙን አሸንፌዋለሁ
ደስታችሁን የሚወስድባችሁ የለም የሚለውን መድኀኒት ወለደችልን፡፡
እየተፅናናን ሞተን ነበር፤ እየተፅናናን ዳን፡፡
በውሸት ማፅናናት የጠፋነውን በእውነት ያፅናናችን እመብርሃን ናት፡፡
“ናዛዚትነ እምኀዘን ወኃይለ ውርዙትነ እምርስአን
በማኅፀንኪ ተጸውረ ብሉየ መዋዕል ኅፃን
ኦ ማርያም ተስፋ ለቅቡጻን
በጊዜ ጸሎት ወዕጣን
ወበጊዜ ቅዱስ ቁርባን
ለናዝዞትነ ንኢ ኀበ ዝ መካን"
ከኀዘን የምታፅናኝን ከእርጅና የምታድሽን አንቺ ነሽ፤
ቀዳማዊ ጌታ ሕፃን ሆኖ በማኅፀንሽ አድሯልና
እመቤታችን ማርያም ሆይ
ተስፋ የቆረጡት ተስፋቸው ነሽ፤
በጸሎትና በዕጣን በቁርባንም ጊዜ
ኃጢኣታችንንም አሥተሥርየሽ ለመቀበል ታበቂን ዘንድ
ወደዚህ ቦታ ነይልን” እያልን የምንማፀናት ለዚህ ነው፡፡
✍️ / ዑራኤል
❤4
ተወዳጆች
ቅዱስ ቄርሎስ ንስጥሮስን
ልጇንም አምላክ እርስዋንም ወላዲተ አምላክ በላት ቢለው እንቢ አለ፡፡
ምላስህ ለእኔ እንዳልታዘዘች ለአንተም አትታዘዝህ ብሎት ሞቷል፡፡
በእውነት ለድንግል ማርያም ያልታዘዘች አንደበት
የሰይጣን ሆና ካልሆነ በቀር ሌላ የማን ናት
✍️ / ዑራኤል
ቅዱስ ቄርሎስ ንስጥሮስን
ልጇንም አምላክ እርስዋንም ወላዲተ አምላክ በላት ቢለው እንቢ አለ፡፡
ምላስህ ለእኔ እንዳልታዘዘች ለአንተም አትታዘዝህ ብሎት ሞቷል፡፡
በእውነት ለድንግል ማርያም ያልታዘዘች አንደበት
የሰይጣን ሆና ካልሆነ በቀር ሌላ የማን ናት
✍️ / ዑራኤል
ተወዳጆች
ድንግል ማርያም እኮ
👉ደስታዋ የሰው መዳን የሆነ
👉ወሀቢተ ሰላም ( ሰላም ክርስቶስን መውለድ የተሰጣት )
👉የሰዉ ኀዘንን ሰምታ ሰላም ከእግዚአብሔር የምትመልስ (ሰላመ ሰጣዊት )
👉ቡርክት (የበረከት ምንጭ )
👉በአርአያ እግዚአብሔር በመልክዓ እግዚአብሔር የጸናች ቡርክት
👉በተረገመ አለም ቡርክት የሆነች
👉በጎስቆለ አለም ንጽህት ቅድስት ሁና የተገኘች
👉ነፍሰ ገዳዩን በደሙ የነጻውን መንጽሔ ኀጥአንን የወለዶች
👉የባህር ያችን መመኪያ
👉የሕይወት ዛፍ ዕፀ ሕይወት እርሱን ያፈራችልን
👉ለሚመረኮዟት የሕይወት ዛፍ ናት
የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት አይለየን🙏
✍️ / ዑራኤል
ድንግል ማርያም እኮ
👉ደስታዋ የሰው መዳን የሆነ
👉ወሀቢተ ሰላም ( ሰላም ክርስቶስን መውለድ የተሰጣት )
👉የሰዉ ኀዘንን ሰምታ ሰላም ከእግዚአብሔር የምትመልስ (ሰላመ ሰጣዊት )
👉ቡርክት (የበረከት ምንጭ )
👉በአርአያ እግዚአብሔር በመልክዓ እግዚአብሔር የጸናች ቡርክት
👉በተረገመ አለም ቡርክት የሆነች
👉በጎስቆለ አለም ንጽህት ቅድስት ሁና የተገኘች
👉ነፍሰ ገዳዩን በደሙ የነጻውን መንጽሔ ኀጥአንን የወለዶች
👉የባህር ያችን መመኪያ
👉የሕይወት ዛፍ ዕፀ ሕይወት እርሱን ያፈራችልን
👉ለሚመረኮዟት የሕይወት ዛፍ ናት
የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት አይለየን🙏
✍️ / ዑራኤል
❤3
ተወዳጆች
ድንግል ማርያም
የሕይወት ዛፍ ዕፀ ሕይወት መባሏ
ሰው መንገድ ሲሔድ ሐሩር ቢጸናበት
ድካም ቢያገኘው ከዛፍ ጥላ ተቀምጦ
ፍሬውን በልቶ ውኃ ጠጥቶ አርፎ ካሰበው ይደርሳል፡፡
✅ እኛም
ድንግል ማርያም ከለመለመው ረድኤቷ ተጠግተን
የማኅፀኗን ፍሬ ልጇን ተመግበን የሕይወት ውኃ እርሱን ጠጥተን
ከድካመ ነፍስ በርትተን ካሰብናት ገነት መንግሥተ ሰማያት እንደርሳለንና ነው፡፡ ስለዚህም “ዕፀ ሕይወት ይእቲ ለእለ ይትመርጐዝዋ ባቲ -ለሚመረኮዟት የሕይወት ዛፍ ናት”
እያልን ከጠቢቡ ጋር እናመሰግናታለን (ምሳ.፫፥፲፰)።
👉በገነት ስላልተመገብነው ዕፀ ሕይወት ፈንታ
ፍሬዋን መብላት የተቻለን ዕፀ ሕይወት እርስዋ ናት፡፡
👉የዛፉን ፍሬ የሚወድ ዛፉን ቆርጬ ልጣል አይበል፡፡
ክርስቶስን የሚወድ ከእናቱ ሥር ይገኛል እንጂ
እርስዋን የሚያሳድድ ሄሮድስ አይሆንም::
✅ ወዳጄ
እናቱን ስታሳድዳት
ልጇንም አዝላው ከአንተ እንደምትሸሽ አስተውል፡፡
ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን❣️
✍️ / ዑራኤል
ድንግል ማርያም
የሕይወት ዛፍ ዕፀ ሕይወት መባሏ
ሰው መንገድ ሲሔድ ሐሩር ቢጸናበት
ድካም ቢያገኘው ከዛፍ ጥላ ተቀምጦ
ፍሬውን በልቶ ውኃ ጠጥቶ አርፎ ካሰበው ይደርሳል፡፡
✅ እኛም
ድንግል ማርያም ከለመለመው ረድኤቷ ተጠግተን
የማኅፀኗን ፍሬ ልጇን ተመግበን የሕይወት ውኃ እርሱን ጠጥተን
ከድካመ ነፍስ በርትተን ካሰብናት ገነት መንግሥተ ሰማያት እንደርሳለንና ነው፡፡ ስለዚህም “ዕፀ ሕይወት ይእቲ ለእለ ይትመርጐዝዋ ባቲ -ለሚመረኮዟት የሕይወት ዛፍ ናት”
እያልን ከጠቢቡ ጋር እናመሰግናታለን (ምሳ.፫፥፲፰)።
👉በገነት ስላልተመገብነው ዕፀ ሕይወት ፈንታ
ፍሬዋን መብላት የተቻለን ዕፀ ሕይወት እርስዋ ናት፡፡
👉የዛፉን ፍሬ የሚወድ ዛፉን ቆርጬ ልጣል አይበል፡፡
ክርስቶስን የሚወድ ከእናቱ ሥር ይገኛል እንጂ
እርስዋን የሚያሳድድ ሄሮድስ አይሆንም::
✅ ወዳጄ
እናቱን ስታሳድዳት
ልጇንም አዝላው ከአንተ እንደምትሸሽ አስተውል፡፡
ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን❣️
✍️ / ዑራኤል
❤3