ተወዳጆች

አባቶቻችን ሲያስተምሩ

የሚደርሱበትን መመኘት ብልሐት ሲሆን
የማይደርሱበትን መመኘት ምቀኝነት ይባላል ይላሉ፡፡

ምቀኝነት ማለት ላያገኙት ነገር ሌላውም እንዳያገኘው በአጉል ምቀኝነት ማጥፋት ማለት ነው፡፡

ሄሮድስ መሲሕ እንደሚወለድ ያውቃልና ተነግሮታል፡፡ የተወለደው ሕፃን የዓለም ንጉሥ ቢሆን በምድር በሰማያት መልቶ ያለ ነው እንጂ በምድር ዙፋን ዘርግቶ የሚኖር አይደለም፡፡ ስለዚህ ከእግዚአብሔር ጋር መዋጋት የት ያደርሳል?

አባ ጊዮርጊስ እንዲህ ያመሠጥረዋል፡-

“ሄሮድስ የማያገኘውን ፈለገ፡፡
ጌታም በፈጣን ደመና ተጭኖ ወደ ግብጽ ወረደ፡፡
ኢሳይያስ እግዚአብሔር በፈጣን ደመና ተጭኖ ወደ ግብጽ ወረደ እንዳለ፡፡

ቅድስት ድንግል ሆይ

ደመና ቀሊል አንቺ ነሽ፤
ሄሮድስ ነፋስን በአዳራሽ ዘግቶ ሊያስቀር ወሰነ፤
ነፋስን በአዳራሽ አፍኖ ማስቀረት ወዴት ይቻላል?
ሄሮድሰ የፀሐይ ብርሃንን በእጁ ይጨብጥ ዘንድ ወደደ፡፡
የፀሐይ ብርሃንን መጨበጥ ከወዴት ይቻላል?
እግዚአብሔር በጀርባሽ ታዝሎ ወደ ግብጽ ተሰደደ፡፡”

✍️ / ዑራኤል
3
ተወዳጆች

አሞራ ያላያት መንገድ የተባለች ማን ናት ?

እመቤታችን ድንግል ማርያም ናት ኢዮ(፳፰÷፯)፡፡

አሞራ የተባለው ዲያብሎስ ነው፡፡
ንሥር አጥርቶ እንደሚያይ ይታወቃል፡፡

እንዲህ ከሆነ ለምን ያላያት መንገድ ተገኘች?

ንሥር አጥርቶ እንዲያይ

ዲያብሎስ የአዳምንና የሔዋንን የውድቀት መንገድ አውቆ ምሥጢራቸውን አስወጥቶ በበደል ጥሏቸዋል፡፡

ከዚህ የተነሣ

ሁሉም የአዳም ልጅ
ዲያብሎስ በኃጢአት የፈተነው የመረመረው ሆነ፡፡

እመቤታችንን ግን

ዲያብሎስ በዚህ የፍዳ ማሰሪያ ሊይዛት ያልተቻለው
ይልቁንም ማእሰረ ሔዋን ማኅመሚ በእርስዋ የተቆረጠባት
ትእምርተ ድኂን ሆነች፡፡

ሔዋንን በጎበኘበት ኃጢአት
ድንግል ማርያምን መያዝ አልቻለምና አሞራ ያላያት መንገድ ተባለች::

ዲያብሎስ የእመቤታችን ነገር መቼም ቢሆን አይገባውም፡፡
ሁል ጊዜ ይጠረጥራል ይሸበራል እንጅ አያውቃትም፡፡ የማይመረመረው እናት ናትና ማን ይመረምራታል?

የእመቤታች አማላጅነት አይለየን🙏

✍️ / ዑራኤል
3
ተወዳጆች

ቅዱስ ዳዊት፦

መድኀኒታችን ክርስቶስ

ኀይሉን በቅድስት ድንግል ማርያም ይገልጣል፤
እንዲሁም ሰዎች በእርስዋ በኩል ወደ እርሱ የሚቀርቡ ሆነዋልና”

አቤቱ መንገድህ በመቅደስ ውስጥ ነው” አለ፡፡(መዝ፸፮÷፲፫)

ይህ በሕያዊት መቅደሱ በድንግል ማርያም❣️
ክርስቶስ ያደረገው መገለጥ ነው፡፡

እንዲህ ማለትም

የቀናች ወደ አንተ የምታደርሰው ሃይማኖት

ቅድመ ዓለም ከአብ

👉እንበለ ተድኅሮ(ወደ ኋላ ሳይሆን)፡
👉እንበለ አገብሮ(ያለፈቃዱ ያይደለ በፈቃዱ)፥
👉እንበለ መንጸፈ አንስት(ያለ እናት) ተወለደ፤

በኋለኛው ዘመን ደግሞ፦

👉ያለመለወጥ፥ ያለመከፈል፥
👉ያለመጉደል፥ ያለማነስ፥
👉ያለመለያየት፥ ያለወንድ ዘር፥
👉ከአማናዊት የሰው እጅ ካልሠራት መቅደሱ
በተዋሕዶ ተገለጠ ብሎ ማመን ናት
ማለት ነው፡፡
ሃይማኖት ይህ ነው፡፡

ስለዚህ

ርትዕት ሃይማኖት ክርስቶስ
በሥራዋ ሁሉ ንጽሕት ከሆነች እናቱ መገለጡ ነውና

ቅዱስ ዳዊት እንደዘመረው እኛም አብረን

አቤቱ መንገድህ በመቅደስ ውስጥ ነው እያልን እንዘምራለን፡፡

መንገዳችን ይቀናልን ዘንድ ቸሪቱ አማላጂቱ
እመብርሃን ከልጇ ከወዳጇ ታማልዳን አሜን🙏


✍️ / ዑራኤል
ተወዳጆች

መናፍቃን ክርስቶስን አማላጅ እንጂ
ጌታ የባሕርይ አምላክ ብለው አያምኑትም፡፡


ስለዚህም ሃይማኖት የላቸውም፡፡

ሃይማኖት ስለሌላቸውም
ለከሐዲ መንግሥተ ሰማያት አትገባምና
ድንግል ማርያም የለቻቸውም፡፡

መናፍቃን ድንግል ማርያምን የሚክዷት
ጌታን ለማመን ሳይሆን ክርስቶስ በውስጣቸው ስለሌለ ነው::

የደስታ ሁሉ ፍፃሜ መንግሥተ ሰማያት ነው ያለው፡፡
በመንግሥተ ሰማያት የሌለ ነገር የለም::
ሙሉ ደስታ በመንግሥተ ሰማያት ናት፡፡

ድንግል ማርያምም

ጸጋን ሁሉ የተመላች የክብር ሁሉ ምንጭ ናት፡፡
ከእርስዋ የማይገኝ ጸጋ የለም፡፡
የጸጋ ሁሉ ራስ እግዚአብሔር ነው፡፡
ራሱን እግዚአብሔርን የተመላች
ምልዕት ባዕለ ጸጋ ንግሥት
ድንግል ማርያም ናት፡፡

እግዚአብሔር ምስሌኪ -
እግዚአብሔርከአንች ጋር ነው” እንዳለ ቅዱስ ገብርኤል፡፡

✍️ / ዑራኤል
2
ተወዳጆች

ዳግም መወለድ ምንድን ነው ?

አማን አማን እብለክሙ ዘኢተወልደ ዳግመ እማይ ወእመንፈስ ቅዱስ ኢይሬእያ ለመንግሥተ እግዚአብሔር - ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔርመንግሥት አይገባም” እንዳለ (ዮሐ.፫፥፭)፡፡

ዳግም መወለድ ማለትም ብዙ ነው፡፡

አንዱ ከውኃና ከመንፈስ ቅዱስ መወለድ ነው፡፡
አንድ ደግሞ የድንግል ማርያም ልጅ ይሆኑ ዘንድ ከእርስዋ በጸጋ መወለድ ነው፡፡

👉 ለአምላክ እንኳን ዓለምን ያድን ዘንድ ቢሻ ከእርስዋ ይወለድ ዘንድ ግድ ከሆነ ወዳጄ የድንግል ማርያም እናትነት አያሻኝም ትል ዘንድ አንተ ማን ነህ?

👉እግዚአብሔር ዓለምን ለማዳን የእርስዋ እናትነት አያሻኝም ካላለ አንተ ለመዳን እርስዋ አታስፈልገኝም የምትል አንተ ከእግዚአብሔር ትበልጣለህን?

👉እግዚአብሔርሁሉን ቻይ ነኝ ብሎ እንኳን እናት ሁኝኝ አላለም፡፡ አጓዳጅ አማላጅ ቅዱስ ገብርኤልን ላከ እንጂ፡፡

👉 አምላክ እባክሽ እናት ሁኝኝ ያላትን አንተ እርስዋን ሰዓሊ ለነ ቅድስት አልልም የምትል አንተ ሰይጣን ነህን? ወይ ልጁ ልትሆን እንደ ሆነ እንጂ! የክርስቶስ ልጆች አምላካቸውን መስለው በግብር አምላካዊ የጸኑ ናቸውና፡፡

👉ሰው ደግሞ ከጥምቀት ዳግመኛ እንደሚወለድ እመቤታችን የአበው ልጅ ስትሆን መልሳ ደግሞ የአበው እናት ናት፡፡ የዳዊት ልጅ ናት፥ ዳዊትም ግን “እምነ ጽዮን ይብል ሰብእ - ሰው እናታችን ጽዮን ይላል" ሲል እናቴ ጽዮን ብሏታል (መዝ.፹፮፥፭)።

የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
አማላጅነት ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን

✍️ / ዑራኤል
6
👆👆👆👆👆

ከላይ ባለው ቻናል የብዙ መንፈሳዊ ጥያቄ መልስ ታገኛላችሁ
👆👆👆👆👆

ከላይ ባለው ቻናል የብዙ መንፈሳዊ ጥያቄ መልስ ታገኛላችሁ
1
ተወዳጆች

ሔዋን ማለት ምን ማለት ነው ?

መድኃኒት ክርስቶስ ብቻ ነው
ድንግል ማርያም መድኃኒት አትባልም
ለሚለውስ ምን መልስ አለ ?


ሔዋን ማለትም ሕይወቴ ነሽ ማለት ነው።

ሔዋን ለአዳም ምን ሕይወት አመጣችለትና ነው ? ሕይወቴ ነሽ መባሏ! በሲኦል ተጥሎ በእግረ አጋንንት ተረግጦ እንዲኖር ከማድረጓ በቀር። ከተባለ

እንኪያስ

“እነ ውእቱ ትንሣኤ ሕይወት- እኔ ትንሣኤና ሕይወት ነኝ " (ዮሐ ፲፩፥፳፭) ሲል አሰምቶ የተናገረውን ሕያው የአብ አካላዊ ቃልን ያመጣችለት የአዳም ሕይወቱ ማርያም ናት።


እኔ የማደንቅባችሁ በዚህ ላይ በዚህ ቅር የሚላችሁ ሰዎች ናችሁ።

ሕይወት ክርስቶስ ነው እንጅ ማርያም አትባልም ትላላችሁና።

ሔዋን ማለት ሕይወት ማለት ነውና ምን ልትሉ ይሆን? አዳምን ተከራከሩታ! “ቆይ! ሕይወት እግዚአብሔርነው እንጅ ለምን ሔዋንን ሕይወቴ ነሽ ትላለህ በሉት!

ምሳሌዋ ሕይወት መባል ከተገባት አማናዊቷ ወላዲተ ሕይወትማ እንደምን መባል አይገባትም? ችግሩ ምንድን ነው? ምን መሰላችሁ? ሁል ጊዜ እየተቀላቀለባችሁ እንደሆነ ይረዳኛል።

ማርያምን ሕይወት መድኃኒት ማለታችን ከክርስቶስ ጋር ማስተካከል እየመሰላችሁ ነው ማለቴ ነው፤ ግን አይደለም።

ሔዋንን አዳም ሕይወቴ ነሽ ሲል ከእግዚአብሔር ጋር እያስተካከላት ነበርን ? አይደለም።

ይልቁንም “ ሕይወትየ ይቤላ አዳም ለብእሲቱ አእሚሮ ከመ ትወጽእ እግዝእትነ ማርያም እምሐቌሁ ወእምከርሠ ብእሲቱ- ኣዳም እመቤታችን ማርያም ከእርሱ አብራክከሔዋንም ማኅፀን እንድትወልድ አውቆ ሚስቱ ሔዋንን ሕይወቴ ነሽ ይላት ነበር" እንዳሉ አበው


በእርስዋ በእኩል መዳኑ እንደሚደረግለት አውቆ እንዲህ አለ እንጅ። ሕይወት ስንላትም የሕይወት እናት፥ የድኅነት ምክንያት፥ ድኅነትን ያገኘንባት ማለታችን ነው።

ሔዋን ማለትም የሕያዋን እናት ማለት ነው።

ይህም የሆነው ምክንያተ ድኂን ድንግል ማርያም ሕይወተ ዓለም ክርስቶስ ከእርስዋ ስለሚወለድ ነው። እንዲህስ ባይሆን ቀዳማዊት ሔዋን ልጆቿን ሁሉ በእርስዋ ምክንያት ሞት ገዝቷቸዋልና የሙታን እናት መባል በተገባት ነበር። አዲሲቷ ሔዋን ግን ልጇቿ በእርስዋ ምክንያት ድነውላታልና የሕያዋን እናት መባል ለእርስዋ በእርግጥ የተገባ ነው። “

ተፈሥሒ ኦ ቅድስት እሞሙ ከኩኰሙ ሕያዋን- የሕያዋን ሁሉ እናት ነሽና ቅድስት ሆይ ደስ ይበልሽ “ ብሎ ቅዱስ ኤፍሬም በውዳሴ ማርያም እንዳመሰገናት።


በሕይወት ክርስቶስ የዳኑ የጻድቃን ሁሉ እናት ሲላት ነው።

✍️ / ዑራኤል
2
ተወዳጆች

ሔዋን ለድንግል ማርያም ምሳሌ እንዴት እንደሆነች እንመልከት።

ሔዋን ምክረ ከይሲን የሰማች የመጀመሪያይቱ ሴት ናት።
ድንግል ማርያም ምክረ እግዚአብሔር የተገለጠባት የመጀመሪያይቱ ሴት።

ሔዋን የወደቀውን መልአክ ያዳመጠች ሴት ስትሆን
ዳግሚት ሔዋን ግን ብርሃናዊ መልአክን የሰማች ሴት ናት።

ሔዋን ድንግልናዋን በርኩሰት ያጣች ስትሆን፤
ዳግሚት ሔዋን እመቤታችን ደግሞ ድንግልናዋ በንጽሕና ተጠብቆ አምላክን ለመውለድ ያበቃት ዘለዓለማዊት ድንግል ናት።

ሔዋን የወደቀውን መልአክ ሰምታ ነፍሰ ገዳዩን ቃየንን ወለደች፥ ድንግል ግን ብሥራተ መልአክን ሰምታ ሕይወተ ሙታንን ወለደች፥

ሔዋን የውድቀትና የሞት ምክንያት፥
ድንግል ማርያም የትንሣኤና የሕይወት ምክንያት ሆነች።

ሔዋን የመተዳደፋችን መጀመሪያ ሆነችን፥
ድንግል ማርያም የንጽሕናችን መሠረት ሆነችን።

ሔዋን ባለመታዘዝ ስሕተትን ወደዚህች ዓለም አስገባች፤
ድንግል ማርያም ግን በመታዘዝ ድኅነትን አመጣች።

በሔዋን ምክንያትባርነት ሲመጣ
በዳግሚት ሔዋን ግን ነጻነት ተሰጠን።

በሔዋን ምክንያት ገነት ተዘጋች፤
በድንግል ማርያም ግን ተከፈተች።

በሔዋን ምክንያት ዐቅም አጣን፤
በድንግል ማርያም ምክንያት ግን “ወአልቦ ዘይሰእነከሙ- የሚሳናችሁ ምንም የለም" ለመባል በቃን። (ማቴ ፲፯፥፳)

በሔዋን ምክንያት ከአጋንንት ጋር በሲኦል እንኖር ነበር፤
በድንግል ማርያም ምክንያት ግን ከመላእክት ጋርለመዘመር በቃን።

ከሔዋን የተወለደው ቃኤን “የሚያገኝኝ ሁሉ ይገድለኛል" እያለ ይቅበዘበዝ ነበር።
ከድንግል የተወለደው ኖላዊነ ሔር ክርስቶስ ግን የተቅበዘበዙትን ፈልጎ ወደ በረቱ መለሳቸው። “…
እንዘ ከመ አባግዕ ትሳኮዩ ወይእዜኒ ግብኡ ኀበ ኖካዊክሙ ወዐቃቢ ሃ ለነፍስከሙ- እንደ በጎች ትቅበዘበዙ ነበርና፥ አሁን ግን ወደ ነፍሳችሁ እረኛና ጠባቂ ተመለሱ” እንዳለ ሐዋርያው “ (፩ ጴጥ ፪፥፳፭) ስለዚህም “ተፈሥሒ ኦ እግዝእትየ ቅድስት ድንግል ዘወዘጽአ እምኔኪ ኖላዊ ሔር ዘበአማን ዘኀሠሦ ለበግዕ ግዱፍ ወሶበ ረከቦ ጾሮ ዲበ መትከፍቱ- የጠፋ በግ አዳምን የፈለገው ባገኘውም ጊዜ በትክሻው የተሽከመው እውነተኛ ቸርጠባቂያችን ክርስቶስ ከአንቺ ተወልዶ የተገለጠልን እመቤቴ ማርያም ሆይደስ ይበልሽ” ብለን በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ቃል እናመሰግናታለን።

በሔዋን የሞት ፍሬ በልተን ጠፋን፤
ወላዲተ አምላክ ግን የሕይወትን ፍሬ አፈራችልን።

ሔዋን ባበላችን ፍሬ ሲኦልንና ሞትን አወቅን።
በድንግል ማርያም ምክንያት የሕይወታችንን ራስ አወቅነው።

ተወዳጆች

በጥንት በደሏ የደረሰብንን ፍዳ መርገም መናገራችን ነው እንጅ ሔዋንም ግን ለድኅነት ያደረገችውን አስተዋጽኦ መርሳት ተገቢ አይደለም። ንስሐ ገብተው የድኅነት ቀጠሮ ለማግኘት በቅተዋልና።

✍️ / ዑራኤል
ተወዳጆች

አዳምና ሔዋን በበደላቸው ምክንያት ለፍጥረተ ዓለም ሞትን አስተዋወቁ።
የፍጥረታት ፈጣሪ እግዚአብሔር ግን በአንድ ልጁ በወልድ፥ በድንግል ማርያም በኩል ሕይወትን ሰጠን።

በእባብአማካኝነት የኃጢአት መርዝ በሔዋን ጆሮ ፈሰሰ፥
ብቻውን መልካም የሆነ ዘልማዱ ኂሩት እግዚአብሔር ግን ቸርነቱ በድንግል ማርያም ጆሮ ፈሰሰ። ሞት በገባበት በር ሕይወት ገባ”

ቅዱስ ኤፍሬም ❣️

✍️ / ዑራኤል
1
ተወዳጆች

ሔዋን ነፍሰ ገዳዩን ወለደች፤
ድንግል ማርያም ግን ሕይወትን የሚያድለውን ወለደች።

የቀደመችው ሔዋን የወንድሙን ደም ያፈሰሰውን ነፍሰ ገዳይ ቃየልን ወለደች፤
አዲሲቷ ሔዋን ግን ደሙን ስለወገኖቹ ያፈሰሰውን ወለደች።

የመጀመሪያይቱ ሔዋን ከምድር ርግማን የተነሣ የሚቅበዘበዘውን ልጇን አየች።
አዲሲቷ ሔዋን ግን በመስቀል ተሰቅሎ እርግማንን ጠርቆ ያስወገደው ልጇን አየች።
የመጀመሪያው አዳም መልሶ ወደ እናቱ ማኅፀን (ወደ ምድር ወደ መቃብር) ገባ፤

ነገር ግን ተመልሶ ወደ እናቱ ማኅፀን ባልገባው በዳግማዊ አዳም በክርስቶስ በእናቱ ማኅፀን ተቀብሮ የነበረ አዳም ከመቃብር ወጣ

ቅዱስ ኤፍሬም❣️

✍️ / ዑራኤል
1
ተወዳጆች

ቀድሞ ሔዋን ድንግል ነበረች ነገር ግን ዲያብሎስ አሳታት እንጅ።
ድንግል ማርያምን ግን ገብርኤል አበሠራት።

ነገር ግን ሔዋንን

ዲያብሎስ አሳታት፥ የሞት ምክንያት ቃኤንን ወለደች።

ማርያም ግን መልአክ በአበሠራት ጊዜ

ሁሉን ወደ ዘለዓለማዊ ሕይወት የሚመራ
አካላዊ ቃልን በሥጋ ወለደች።

የሔዋን ልብላ ልብላ ማለቷ

ዕፀ በለስ የሞት ምክንያት እንደሆነ አስረዳ።
በዚያም ዕፅ አዳም ተድላ ደስታ ካለበት ገነት ወጣ።

ከድንግል የተወለደ አካላዊ ቃል ግን

መስቀል የድኅነት ምክንያት እንደሆነ ገለጠ።
በዚያም መስቀል ቀማኛ ወንበዴ የነበረው ሰው
ከአባቱ ከአዳምና ከቀድሞ አባቶች ሁሉ ጋር
ተድላ ደስታ ወዳለበት ገነት ገባ"

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ❣️

✍️ / ዑራኤል
1
👆👆👆👆👆

ከላይ ባለው ቻናል የብዙ መንፈሳዊ ጥያቄ መልስ ታገኛላችሁ
የእናታችን የሔዋን ልጆች ወንድሞቼ ሆይ

የተለወጠች ድንግል ማርያም የምትልቃትን የሔዋንን ታሪክ አድምጡኝ።

በቀደመችው ጆሮ በኩል ሞት ወደ ማኅጸኗ ገባ፤
በድንግል ማርያም ጆሮ ግን ሕይወት ገባ፤ ለእኛም ተሰጠ።

የቀድሞው ዛፍ የሞት ምክንያት ሆነን።
ሁለተኛው ዛፍ ግን የሕይወት ምክንያት ሆነን።

በመጀመሪያው ዛፍ ሞት ድል ተነሣን፤
በሁለተኛው ዛፍ ግን ሞት ራሱ ድል ተነሳ”

ቅዱስ ኤፍሬም❣️


✍️ / ዑራኤል
ተወዳጆች

የመጀመሪያይቱ ሴት ሔዋን የኃጢአትን በር ከፈተች፤
ዳግሚት ሔዋን ግን የምሕረትና የጽድቅን መንገድ መራችን።

ቀዳማዊቷ ምክረ ከይሲን ተከተለች፤
ዳግሚት ሔዋን ግን የእባቡን መርዝ የሚሽረውን ፤
ጥልን አጥፍቶ መርዘኛውን እባብ ገድሎ
ወደ ውጭ የጣለውን አመጣችልን።

ቀዳማዊቷ ሴት ኃጢአትን በእንጨት አመጣች፤
ዳግሚት ሔዋን ግን ሞገስን ባለሟልነትንና ጸጋን በዕፀ መስቀሉ የሰጠንን አመጣችልን


ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ❣️

✍️ / ዑራኤል
2
ተወዳጆች

ሔዋን ድንግል የነበረች ቢሆንም ግን በእርስዋ በኩል ሞት መጣ። ስለዚህም ሕይወትን የምታመጣ ድንግል ወይም ከድንግልና የሚበልጥ ድንግልና ያላት ድንግል ታስፈልግ ነበር።

ስለዚህ ነገር የቀድሞዋን ሔዋን እባብ እንዳታለላት
ለአዲሲቱ ድንግል ግን ቅዱስ ገብርኤል
አዲስ ብሥራተ ዜናን ሊያመጣላት የተገባት ሆነች

ቅዱስ ቄርሎስ ዘኢየሩሳሌም❣️
1
2025/10/21 07:44:22
Back to Top
HTML Embed Code: