Telegram Web Link
በትምህርት ሴክተሩ በርካታ ውጤታማ ተግባራት መከናወናቸውን በመስክ ምልከታ ማረጋገጡን ከከተማ አስተዳደሩ የተውጣጣ የሱፐርቪዥን ቡድን አስታወቀ።

(ሰኔ 27/2017 ዓ.ም) የሱፐርቪዥን ቡድን ከቢሮ ጀምሮ እስከ ትምህርት ቤት ድረስ ባካሄደው የድጋፍና ክትትል ግብረ መልስ ዙሪያ የቢሮው ስትራቴጂክ ካውንስል አባላት በተገኙበት ውይይት ተካሂዷል።

የሱፐርቪዥን ቡድኑ ከቢሮ ጀምሮ በተመረጡ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ባካሄደው የመስክ ምልከታ በርካታ ውጤታማ ስራ በመሰራት ላይ እንደሚገኝ መረጋገጡን በግብረ መልሱ የተገለጸ ሲሆን በ2017 ዓ.ም የተማሪዎችን የሒሳብና እንግሊዘኛ ውጤት ለማሻሻል የተዘጋጀው ስትራቴጂ በተማሪ ውጤት ላይ መታየት መጀመሩ ፣ በትምህርት ተቋማት መካከል ተቀራራቢ አፈጻጸም እንዲኖር ተከታታይ የድጋፍና ክትትል ስራ መሰራቱ ፣ የትምህርት ተደራሽነትን ለማረጋገጥ በርካታ ትምህርት ቤቶች መገንባታቸው ፣ የትምህርት ለትውልድ ንቅናቄን ውጤታማ ለማድረግ የ90 ቀን እቅድ ተዘጋጅቶ ወደ ተግባር መገባቱ ፣ የ2018 ዓ.ም እቅድ ከባለድርሻ አካላት ጋር የጋራ መደረጉ ፣ ከቢሮ ጀምሮ በየደረጃው የተቀናጀ አመራር በመፍጠር የመማር ማስተማር ሂደቱ የሚደገፍበት ስርአት መፈጠሩ እንዲሁም የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የተሰሩ ስራዎች ሴክተሩ ውጤታማ እንዲሆን ከተከናወኑ ተግባራት መካከል የሚጠቀሱ መሆናቸው ተጠቁሟል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ የሱፐርቪዥን ቡድኑ ከቢሮ ጀምሮ እስከ ትምህርት ቤት ድረስ በመውረድ የትምህርት ዘርፉን ለመደገፍ ላደረገው ድጋፍና ክትትል ምስጋና አቅርበው በቀጣይ በሱፐር ቪዥን ቡድኑ የተሰጡ ግብረ መል ሶችን መሰረት በማድረግ የተሻለ ስራ እንደሚሰራ አስታውቀዋል።
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
የአራዳ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት የ2017 ዓ.ም የክረምት የተማሪዎችና የመምህራን ስፖርት ንቅናቄ ማስጀመርያ መርሃ ግብር አካሄደ ።

(ሰኔ 27/2017 ዓ.ም) የአራዳ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት የ2017 ዓ.ም የክረምት የተማሪዎችና የመምህራን ስፖርት ንቅናቄ ማስጀመርያ መርሃ ግብር በዳግማዊ ሚኒሊክ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አካሂዷል።

በመርሃ ግብሩ ላይ በክፍለ ከተማው ስር የሚገኙ ከሁሉም ትምህርት ቤቶች የተወጣጡ መምህራን፣ የትምህርት ቤት አመራሮች፣ ተማሪዎች እና የትምህርት ባለሙያዎች የተሳተፉ ሲሆን በዕለቱም ሁሉም አካላትን ባሳተፈ መልኩ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ተደርጓል።

በንቅናቄ መስጀመሪያው ላይ የአራዳ ክፍለ ከተማ ትምህርት ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ደሣለኝ ደበሌ ትውልድን በአካል ብቃት እና በስነልቦና ማብቃት አንዱ የትምህርት ተግባር እንደሆነና በHንድሮም አመት በክረምት ወቅት በሁሉም ትምህርት ቤቶች የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ያለማቋረጥ መካሄድ ስላለበት ከዛሬ ጀምሮ ባሉት ቀናት ተማሪዎች እና መምህራን እንዲሁም የትምህርት ማህበረሰቡ የሚሣተፋበት የስፖርት እንቅስቃሴ እንደ አንድ ተግባር ተወስዶ በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ አሳውቀዋል ።


መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ በ2017 ዓ.ም የበጀት አመት ከተለያዩ ተቋማት ጋር ትስስር ፈጥሮ በቅንጅት መስራቱ ውጤታማ እንዳደረገው በከንቲባ ጽህፈት ቤት የተቋማት ቅንጅታዊ አሰራር ክትትልና ድጋፍ ዘርፍ ቢሮ ኃላፊው አቶ ሞላ ንጉስ አስታወቁ።

(ሰኔ 28/2017 ዓ.ም) ቢሮው የ2017 ዓ.ም የቅንጅታዊ አሰራር እና የመልካም አስተዳደር እቅድ አፈጻጸም እንዲሁም በ2018 ዓ.ም የዘርፉ እቅድ ዙሪያ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ውይይት አካሂዷል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በከተማ አስተዳደሩ ከሚገኙ ተቋማት መካከል በየአመቱ ውጤታማ በመሆን በተደጋጋሚ ዕውቅና ከሚሰጣቸው ተቋማት መካከል ግንባር ቀደም መሆኑን በከንቲባ ጽህፈት ቤት የተቋማት ቅንጅታዊ አሰራር ክትትልና ድጋፍ ዘርፍ ቢሮ ኃላፊ አቶ ሞላ ንጉስ በመርሀግብሩ መክፈቻ ባስተላለፉት መልዕክት ጠቁመው ቢሮው ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ትስስር ፈጥሮ በቅንጅት መስራቱ ለተገኘው ውጤት ዋነኛ ምክንያት እንደመሆኑ ዘንድሮ የተገኙ ውጤቶችን በማስቀጠል እና ቀሪ ተግባራትን በመገምገም በ2018 ዓ.ም የተሻለ ስራ መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በበኩላቸው በ2017 ዓ.ም የበጀት አመት የተማሪዎችን ውጤትና ስነምግባር ከማሻሻል ጀምሮ አጠቃላይ የመማር ማስተማር ስራው ውጤታማ እንዲሆን ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት መሰራቱ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ገልጸው በቅንጅታዊ አሰራርም ሆነ በመልካም አስተዳደር ዘርፍ የተመዘገቡ ውጤታማ ስራዎችን በማስቀጠል በ2018
በ2018 ዓ.ም የተሻለ ስራ የሚሰራ መሆኑን በመጥቀስ ከቢሮው ጋር በትስስር እየሰሩ የሚገኙ ባለድርሻ አካላትም ለመማር ማ ስተማር ስራው ውጤታማነት የሚያበረክቱትን አስተዋጽኦ አጠናክረው መቀጠል እንደሚገባቸው አመላክተዋል።

ቢሮው በየወቅቱ በተፈራረመው የትስስር ሰነድ መሰረት ከተለያዩ ተቋማት ጋር በቅንጅት ያከናወናቸውን ተግባራት እየገመገመ የተሻለ ስራ ለሰሩ ተቋማት ዕውቅና በመስጠት ላይ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የቢሮ ኃላፊ አማካሪ እና የዘርፉ አስተባባሪ ወይዘሮ አበበች ነጋሽ ጠቁመው በ2017 ዓ.ም በተደረገ የቅንጅታዊ አሰራር ፍረጃ መሰረት ከቢሮው ጋር ትስስር ፈጥረው ወደተግባር የገቡ ተቋማት በሙሉ አፈጻጸማቸው በከፍተኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ መረጋገጡን ገልጸዋል።

በመርሀ ግብሩ ከከንቲባ ጽህፈት ቤት እና ከፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ የመጡ የድጋፍና ክትትል ባለሙያዎች ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ካውንስል አባላት ፣ የክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊዎች እንዲሁም ከቢሮው ጋር የስምምነት ፊርማ ተፈራርመው በቅንጅት በመስራት ላይ ከሚገኙ ተቋማት የመጡ የስራ ኃላፊዎች የተገኙ ሲሆን በመድረኩ በቀጣይ በጋራ ለመስራት የሚያስችል የስምምነት ሰነድ ፊርማ ከመፈረሙ ባሻገር በ2017 ዓ.ም ከቢሮ ጋር በቅንጅት ሰርተው ውጤታማ ለሆኑ ተቋማት ዕውቅና ተሰቷል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
2025/07/06 00:38:39
Back to Top
HTML Embed Code: