በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በበይነ መረብ (online) የሚሰጠው የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና 2ኛ ዙር በዛሬው እለት መሰጠት ተጀመረ ።
(ሰኔ 26/2017 ዓ.ም) ፈተናው በከተማ አስተዳደሩ በ108 የማስፈተኛ ጣቢያዎች ሙሉ በሙሉ በበይነ መረብ በመሰጠት ላይ የሚገኝ ሲሆን በዛሬው የ2ኛ ዙር ፈተና ከ13ሺ በላይ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተናውን በበይነ መረብ በመውሰድ ላይ ይገኛሉ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ከምክትል ቢሮ ኃላፊው አቶ ዲናኦል ጫላ እና ከንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ትምህርት ቤት ኃላፊ ከአቶ በላይ ነጋሽ እንዲሁም ከኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ ከአቶ ገነነ ዘውዴ ጋር በመሆን 2ኛው ዙር ፈተና ከሚሰጥባቸው ጣቢያዎች መካከል በሆኑት ሆፕ ኢንተርፕራይዝ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ፣ ሳውዝ ዌስት አካዳሚ ፣ በዶንቦስኮ ትምህርት ቤት እንዲሁም በአየር ጤና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተገኝተው የፈተናውን ሂደት በመመልከት ተማሪዎችን አበረታተዋል።

ፈተናው ስኬታማ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ቢሮው ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ቀደም ሲል ተማሪዎቹ የልምምድ ፈተና እንዲወስዱ መደረጉ ፣ በቂ ኦረንቴሽን መሰጠቱ እንዲሁም በየመፈተኛ ጣቢያው መሰረተ ልማቶቹችን ዝግጁ የማድረግ ስራን ጨምሮ ሌሎች የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መሰራታቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ጠቁመው ፈተናው በበይነ መረብ መሰጠቱ ተማሪዎቹ በተረጋጋ ሁኔታ እንዲፈተኑ ከማስቻሉ ባሻገር ከኩረጃ ነጻ የሆነ የፈተና ስርአት እንዲሰፍን የሚያግዝ መሆኑን በመጀመሪያው ዙር ፈተና መረጋገጡን አስታውቀዋል።
በአዲስ አበባ ከተማ ከ280 አስፈታኝ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ 51,259 የተፈጥሮ እና የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በአራት ዙር የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና እንደሚወስዱ ቀደም ሲል መገለጹ ይታወቃል።
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc

የመንግስትን የ2017 ዓ/ም በጀት ዓመት የዕቅድ አፈፃፀንም በተመለከተ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለተነሱት ጥያቄዎች ዶ/ር ዐብይ አህመድ ከሰጡት ማብራሪያ :- ትምህርትንና ጤናን በተመለከተ፡-
(ሰኔ 26/2017 ዓ.ም) ትምህርትን በተመለከተ፡-
በዚህ ዓመት 4 ነጥብ 2 ሚሊዮን ህጻናትን በቅድመ መደበኛ ትምህርት ተቀብለናል። 26 ሺህ ደግሞ የልዩ ፍላጎት ህጻናት ናቸው። በዚህ ልክ የቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች መገንባትና መምህራንን ማፍራት ላይም ሰርተናል።
የመምህራን ልማትን በሚመለከት ወደ 68 ሺህ መምህራን ሰልጥነዋል፤
ዘንድሮ 80 ሺህ መምህራን በትምህርትና መማር ማስተማር ይሰለጥናሉ።
30 ገደማ ሞደል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እየተገነቡ ነው።
ማህብረሰቡ በትምህርት ለትውልድ ባዋጠው ገንዘብ፤ በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የመፅሐፍና ትምህርት ጥምርታን ማሟላት ተችሏል።
ጤናን በተመለከተ፡-
የጤና ተቋማትን በተመለከተ ከ22 ሺህ ገደማ ተቋማት መካከል 6 ሺህ ያህሉ ከለውጡ ወዲህ የተገነቡ ናቸው።
የግል ዘርፍ የህክምና ተቋማትም እየተስፋፉ ነው። ሆኖም አሁንም ችግር አለ፣ ከመሰረተ ልማትና ከጤና ባለሙያዎች ጥያቄ አንጻር ምላሽ እየሰጠን መጓዝ ያስፈልጋል፤
ማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህንን በማስፋት የጤና ስርዓቱን ማጠናከር ያስፈልጋል።
እነዚህን ተግባራት እያጠናከርን ስንሄድ ተጨባጭ ውጤት ይመጣል።
#የጠሚሩምላሾች
#PMOEthiopia

በ25/75 ፕሮግራም የተደራጁ ቤት ፈላጊ መምህራንን ወደ ስራ ለማስገባት እንዲቻል የተቋቋመው የቴክኒክ ኮሚቴ እስካሁን ባከናወናቸው ተግባራት ዙሪያ ውይይት ተካሄደ።
(ሰኔ 27/2017 ዓ.ም) በመርሀ ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ስትራቴጂክ ካውንስል አባላትን ጨምሮ የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ የስራ ኃላፊዎች ፣ የመሬት አስተዳደር ቢሮ እና የህብረት ስራ ኮሚሽን አመራሮች እንዲሁም የመምህራን ማህበር ተወካዮች ተሳታፊ ሆነዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ የቴክኒክ ኮሚቴው የመምህራንን አቅም እና ወቅታዊ ዋጋን ታሳቢ በማድረግ ባቀረባቸው የዲዛይን አማራጮች ዙሪያ በማህበር ለተደራጁ መምህራን ግንዛቤ በመፍጠር በቀጣይ በፍጥነት ወደ ግንባታ እንዲገቡ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ጠቁመው በመሬት ልማት አስትዳደር ቢሮ በኩል ለግንባታው የሚሆን ቦታ ዝግጁ የማድረግ እና ተያያዥ ጉዳዮችን መስራት የሚጠበቅ መሆኑን አመላክተዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ቅድስት ወልደጊዮርጊስ በበኩላችው የቴክኒክ ኮሚቴው ያቀረባቸው አማራጮች የመምህራኑን አቅም ታሳቢ ያደረጉ እና በፍጥነት ወደግንባታ የሚያስገቡ በመሆናቸው በፍጥነት ወደ ግንባታ በመግባት መምህራኑ የቤት ባለቤት እንዲሆኑ ተቋማቸው በትኩረት የሚሰራ መሆኑን አስገንዝበዋል።
ለግንባታ የተለዩ ቦታዎችን በፍጥነት ርክክብ በማድረግ በቀረቡት የዲዛይን አማራጮች መሰረት ወደ ግንባታ መግባት እንዲቻል የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በተሰጣቸው ኃላፊነት መሰረት በቅንጅት መስራት እንደሚጠበቅባቸው የቴክኒክ ኮሚቴው ባቀረበው ሪፖርት አስታውቋል።