Telegram Web Link
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ካውንስል አባላት የ2017 የትምህርት ዘመን የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የማለፊያ ውጤት 50% እንዲሆን በዛሬው እለት ወስነዋል።

(ሰኔ 25/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት መሰረት በከተማ አስተዳደሩ የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከ2015 የትምህርት ዘመን ጀምሮ መሰጠቱን እንዲሁም በ2017 የትምህርት ዘመን ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት በመስራቱ የተመዘገበው ውጤት አበራታች መሆኑን ተናግረዋል።

ዶክተር ዘላለም አያይዘውም በ2017 ዓ.ም የሒሳብና እንግሊዘኛ ትምህርትን ለማሻሻል ተግባራዊ የተደረገው ስትራቴጂ በተማሪዎች ውጤት መረጋገጡን በተጨማሪም የከተማ አስተዳደሩ በትምህርት ዘርፉ ላይ ባደረገው ትኩረት ውጤቱ መመዝገቡን ተናግረው ፈተናውን በአጭር ጊዜ በማረም ውጤቱ ይፋ እንዲሆን ቀን ከሌት ሲሰሩ ለቆዩ የፈተና ክፍል ባለሙያዎችና ሂደቱን ሲደግፉ ለነበሩ አመራሮች ምስጋና አቅርበዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዲናኦል ጫላ በበኩላቸው በከተማ አስተዳደሩ በ2017 ዓ.ም 79,034 ተማሪዎች ፈተናውን መውሰዳቸውን ገልጸዋል፡፡

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
በአዲስ አበባ ከተማ የ2017 ዓ.ም የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል 95 % ያህሉ 50% እና ከዛ በላይ በማምጣት ወደ ቀጣዩ የክፍል ደረጃ መሸጋገራቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ አስታወቁ።

(ሰኔ 25/2017 ዓ.ም) ኃላፊው በዛሬው እለት የ2017 ዓ.ም የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤትን በማስመልከት ለተለያዩ የመንግስትና የግል የመገናኛ ብዙኃን ጋዜጣዊ መግለጫ ሰተዋል።

በከተማ አስተዳደሩ የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት በየአመቱ አበረታች ውጤት ማሳየት ላይ መሆኑን ኃላፊው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫው ጠቁመው በ2017 ዓ.ም ፈተናውን ከወሰዱ 79,034 ተማሪዎች መካከል 75,085 ተማሪዎች ማለትም 95 በመቶ የሚሆኑ ተማሪዎች 50% እና በላይ አስመዝግበው ወደ ቀጣዩ የክፍል ደረጃ መሸጋገራቸውን አስታውቀዋል።
ዶክተር ዘላለም አያይዘውም የ2017 ዓ.ም የ6ኛ ክፍል ፈተና ውጤታማ እንዲሆን ከተማ አስተዳደሩ ለትምህርት ሴክተሩ ትኩረት በመስጠት የትምህርት ቤት ምገባን ጨምሮ የደንብ ልብስ እና ሌሎች ተጨማሪ የትምህርት ግብአቶች ማቅረቡ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ገልጸው በየትምህርት ቤቱ የማጠናከሪያ ትምህርትን ጨምሮ ተማሪዎች በቴሌቪዥን የሚማሩበት አማራጭ መመቻቸቱ እና ባለድርሻ አካላት በቅንጅት መስራታቸው ለውጤቱ መገኘት ተጠቃሽ ምክንያቶች መሆናቸውን አመላክተዋል።

ዘንድሮው በከተማ ደረጃ ከፍተኛ ውጤት ካስመዘገቡ ተማሪዎች መካከል ከ1 እስከ 4 የሚሆኑት ከመንግስት ትምህርት ቤቶች መሆናቸው በግልና በመንግስት ትምህርት ቤቶች መካከል ያለዉን የውጤት ልዩነት እጅግ እየተቀራረበ መምጣቱን ኃላፊው በመግለጫቸው ጠቁመው መምህራንን ጨምሮ በየደረጃው የሚገኙ ባለድርሻ አካላት ተማሪዎቹ ውጤታማ እንዲሆኑ ላበረከቱት አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል።

ተፈታኝ ተማሪዎች ከታች የተቀመጠውን ሊንክ በመጠቀም ከዛሬ ጀምሮ ውጤታቸውን ማየት እንደሚችሉ በጋዜጣዊ መግለጫው ተጠቁሟል።

LINK https://aa6.ministry.et/#/result
Telegram bot; @emacs_ministry_result_qmt_bot

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
የመምህራን እና የትምህርት አመራር ልማት ዳይሬክቶሬት በ2017 ዓ.ም አፈጻጸም እና በ2018 ዓ.ም እቅድ ዙሪያ ውይይት አካሄደ።

(ሰኔ 26/2017 ዓ.ም) በውይይቱ የክፍለከተማ የመምህራን እና የትምህርት አመራር ልማት ቡድን መሪዎች እንዲሁም የዳይሬክቶሬቱ ባለሙያዎች የተሳተፉ ሲሆን በመርሀግብሩ የ4ኛ ሩብ አመት አፈጻጸምን መሰረት ያደረገ የድጋፍና ክትትል ግብረ መልስ በቢሮ የመምህራን ልማት ባለሙያ በወይዘሮ ፍሬሕይወት አስፋ ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የመምህራን እና የትምህርት አመራር ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ አበራ ስራ ክፍሉ በየሩብ አመቱ በዘርፉ የተከናወኑ ተግባራትን ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ በመሆን ሲገመግም መቆየቱን ገልጸው የዛሬው ውይይት በበጀት አመቱ የተከናወኑ ተግባራትን በመገምገም በ2018ዓ.ም የተሻለ ስራ ለመስራት የሚያስችል መሆኑን አስታውቀዋል።

ዳይሬክተሩ አያይዘውም ስራ ክፍሉ የ4ኛ ሩብ አመት አፈጻጸምን መሰረት ያደረገ ድጋፍና ክትትል ማድረጉን ገልጸው የድጋፍና ክትትል ግብረመልሱን የጋራ በማድረግ በቀጣይ የተሻለ ስራ የሚሰራ መሆኑን አመላክተዋል።

በመርሀግብሩ በዘርፉ በ90 ቀናት በሚከናወኑ ተግባራት ዙሪያ ውይይት ከመካሄዱ ባሻገር በ2017 ዓ.ም የመምህራን ኦዲት ሪፖርትን የጋራ የማድረግና በ2018 ዓ.ም የመምህራን ፍላጎት ዙሪያ ውይይት ተደርጎ ቀጣይ አቅጣጫ ተቀምጧል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
2025/07/07 16:52:05
Back to Top
HTML Embed Code: