በትላንትናው ዕለት የተጀመረውና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በበይነ መረብ (online) የሚሰጠው የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና በዛሬው ዕለትም በመሰጠት ላይ ይገኛል።
(ሰኔ 24/2017 ዓ.ም) ፈተናው በከተማ አስተዳደሩ በ108 የማስፈተኛ ጣቢያዎች ሙሉ ለሙሉ በበይነ መረብ በመሰጠት ላይ የሚገኝ ሲሆን ፈተናው ስኬታማ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ቀደም ሲል ተማሪዎቹ የልምምድ ፈተና እንዲወስዱ መደረጉን እና በቂ ኦረንቴሽን መሰጠቱ እንዲሁም በየመፈተኛ ጣቢያው መሰረተ ልማቶቹን ዝግጁ የማድረግ ስራን ጨምሮ የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ሲሰሩ መቆየቱ ይታወቃል።
ሁለተኛ ቀኑን ባስቆጠረው የመጀመሪያ ዙር ፈተና ከ13ሺ በላይ ተማሪዎች ፈተናውን በበይነ መረብ በመውሰድ ላይ የሚገኙ ሲሆን የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ፣ የቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ ዲናኦል ጫላና አቶ ሳምሶን መለሰ በጋር በመሆን ፈተናው ከሚሰጥባቸው ጣቢያዎች መካከል በአድዋ ድል መታሰቢያ እና አብሮህት ቤተ መጻሕፍት ተገኝተው የሁለተኛዉን ቀን ፈተና በማስጀመር ተማሪዎችን አበረታተዋል።
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc

በበይነ መረብ (online) እየተሰጠ የሚገኘው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ለ2ኛ ቀን እየተሰጠ ይገኛል ።
(ሰኔ 24/2017 ዓ.ም) በከተማ አስተዳደሩ በ2017 ዓ.ም በበይነ መረብ (Online) እየተሰጠ የሚገኘው የ 12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ሁለተኛ ቀን እየተካሄደ ይገኛል::
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ከቢሮው ምክትል ቢሮ ሀላፊዎች ከአቶ ወንድሙ ዑመር ፣ ከአቶ ዲናኦል ጫላና ከአቶ ሳምሶን መለሰ እንዲሁም ከቦሌ ክፍለ ከተማ ትምህርት ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ መስፍን ታደሰ እና ከቂርቆስ ክፍለ ከተማ ትምህርት ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰማህኝ አስታጥቄ ጋር በመሆን በዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ፣ ቦሌ ሕብረተሰብና አሳይ የፈተና መስጫ ጣቢያዎች ላይ ተዘዋውረው የፈተናውን ሂደትን በመመልከት ተማሪዎችን አበረታተዋል፡፡
ተማሪዎች በሁለተኛ ቀን ፈተና በጠዋቱ ክፍለ ጊዜ Apttitude በከሰዓቱ መርሀ ግብር ደግሞ physics የትምህርት አይነቶችን የሚፈተኑ ይሆናል::

የዘርፈ ብዙ ጉዳዮችና ቀዳማይ ልጅነት ትግበራ ዳይሬክቶሬት በ2017 ዓ.ም እቅድ አፈጻጸም እና በ2018 ዓ.ም እቅድ ዙሪያ ውይይት አካሄደ።
(ሰኔ 24/2017 ዓ.ም) በመርሀ ግብሩ የክፍለከተማ የዘርፈ ብዙና ልዩፍላጎት ቡድን መሪዎች እንዲሁም የስርአተ ጾታና ዘርፈ ብዙ ባለሙያዎችን ጨምሮ የዳይሬክቶሬቱ ባለሙያዎች የተሳተፉ ሲሆን በዘርፉ በ90 ቀናት የሚከናወኑ ተግባራት እቅድ ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የዘርፈ ብዙ ጉዳዮችና ቀዳማይ ልጅነት ትግበራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወይዘሮ በላይነሽ የሻው ስራ ክፍሉ በየሩብ አመቱ በዘርፉ የተከናወኑ ተግባራትን ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ሲገመግም መቆየቱን ገልጸው የዛሬው ውይይት በበጀት አመቱ የተከናወኑ ተግባራትን በመገምገም በ2018ዓ.ም የተሻለ ስራ ለመስራት እንዲቻል ታስቦ መዘጋጀቱን አስታውቀዋል።
ዳይሬክተሩዋ አያይዘውም በትምህርት ሴክተሩ በ90 ቀናት የተለያዩ ተግባራትን ለማከናወን እቅድ መዘጋጀቱን ገልጸው ከነዚህ ተግባራት መካከል በ2018 ሞዴል የሚሆኑ የቅድመ አንደኛ ደረጃ ተቋማትን መረጃ ከማደራጀት ጀምሮ ለህጻናቱ ምቹ የመማሪያ ቦታ እንዲሆኑ የማድረግ ፣ በየትምህርት ተቋማቱ የስርአተ ጾታ እና የጤና እንክብካቤ ክበባት ቢሮ እንዲኖር ፣ ለሴት ተማሪዎች የንጽህና መጠበቂ ክፍል ማዘጋጀትን ጨምሮ በእቅዱ የተቀመጡ ተግባራት ውጤታማ እንዲሆኑ የክፍለ ከተማ ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች በትኩረት መስራት እንደሚገባቸ አስገንዝበዋል።

የውይይቱ ተሳታፊዎችም በቀረቡት የ2017 አፈጻጸም፣ በ2018 እቅድ እንዲሁም በ90 ቀናት በሚከናወኑ ተግባራት ዙሪያ የተለያዩ አስተያየቶችን እና ጥያቄዎችን አቅርበው ምላሽ ተሰቷል።
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
የ2017 የትምህርት ዘመን የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት ዛሬ ከሰዓት ይፋ ይሆናል፡፡
(ሰኔ 25/2017 ዓ.ም) የ2017 የትምህርት ዘመን የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት ዛሬ ከሰዓት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ካውንስል አባላት በማለፊያ ነጥቡ ላይ ውይይት ካደረጉ በሃላ ይፋ ይደረጋል።
የ2017 ዓ.ም የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና በአጭር ጊዜ ታርሞ ይፋ መደረጉ ተማሪዎች ለቀጣዩ የትምህርት አመት ከወዲሁ በቂ ዝግጅት እንዲያደርጉ የሚያስችል ሲሆን የ2017 የትምህርት ዘመን የ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ከሰኔ 10-12/2017 ዓ.ም ድረስ በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ 192 የመፈተኛ ጣቢያዎች ለተከታታይ ሶስት ቀናት መሰጠቱ ይታወሳል፡፡ ።