Telegram Web Link
የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የመጀመሪያ ዙር ተፈታኝ ተማሪዎች እሁድ በ22/10/2017 ዓ.ም በኦላይን ፈተና መስጫ ጣቢያ በሚሰጠው የፈተና ገለጻ/Orientation/ ላይ መገኘት ይጠበቅባቸዋል፡፡

(ሰኔ 21/2017 ዓ.ም) በከተማ አስተዳደሩ የ2017 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተናን በኦላይን ለመስጠት ዝግጅቶች የተጠናቀቁ ሲሆን ፈተናው ከሰኞ ጀምሮ የሚሰጥ በመሆኑ ተማሪዎች በፈተና መስጫ ጣቢያዎች በወጣው መርሀ ግብር መሰረት በመገኘት ፈተናዉን ሊወስዱ ይገባል፡፡

የፈተና አሰጣጡን አስመልክቶም ገለጻ በፈተና ጣቢያዎች የሚሰጥ በመሆኑ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የመጀመሪያ ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች እሁድ በ22/10/2017 ዓ.ም ጠዋት 2፡30 ፣ የሁለተኛ ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች እሁድ በ22/10/2017 ዓ.ም ከቀኑ 7፡30 ፣ የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች እሁድ በ29/10/2017 ዓ.ም ጠዋት 2፡30 ፣ የሁለተኛ ዙር የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች እሁድ በ29/10/2017 ዓ.ም ከቀኑ 7፡30 በኦላይን ፈተና መስጫ ጣቢያዎች በመገኘት የሚሰጠውን የፈተና ገለጻ/Orientation/ መከታተልና የመፈተኛ ቦታቸዉንና ክፍላቸዉን ማየት ይጠበቅባቸዋል፡፡


መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
74👎17🤬11🥰2👏2👍1😁1
የ6ኛ ክፍል ተማሪ ሳለች ለእናቷ የገባችውን ቃል ያሳካችው ተመራቂ፡፡

(ሰኔ 21/2017 ዓ.ም) የአብስራ ሽፈራው ትባላለች። የ6ኛ ክፍል ተማሪ ሳለች አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በእናቷ ምርቃት ላይ ተገኝታ ነበር። ያኔ ታዲያ "በዚህ ግቢ ተምሬ እመረቅበታለሁ" ስትል ለእናቷ ቃል ገብታላት ነበር።


እንሆ ዛሬ የአብስራ ያን ቃሏን አሳክታለች። ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሳይኮሎጂ ትምህርት ክፍል 3.5 በማምጣት በከፍተኛ ማዕረግ በዲግሪ ተመርቃለች።


አካል ጉዳተኝነት ያልበገራት የአብስራ በመምህሮቿ የተመሰገነች ታታሪ ተማሪ ስትሆን፤ ለዚህ ስኬቷ ደግሞ የእናቷ አበርክቶ ትልቅ ድርሻ ይወስዳል።


በ4 ዓመታት የዩኒቨርሲቲ ቆይታዋ እናቷ እርሷን በማመላለስ እና በማበረታታት ለዚህ አብቅታታለች።


የአብስራ እናት "ልጆቻችን አካል ጉዳተኞች ናቸው ብለን በየቤቱ ደብቀን ይበልጥ ከምንጎዳቸው ፤ መስዋዕት ከፍለን ካሰቡበት እናድርሳቸው" ስትል ለወላጆች መልዕክት አስተላልፋለች።


#EBC #EBCdotstream #AAU #Graduation


መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
107👍19👏12
በአዲስ አበባ ከተማ የ2017 ዓ.ም የአረንጓዴ አሻራ ማስጀመሪያ መርኃ ግብር በመካሄድ ላይ ይገኛል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ፤የከተማ አስተዳደሩ ሌሎች አመራሮች፤ የሃይማኖት አባቶች ፤ የሃገር ሽማግሌዎች ፤ የሃገር መከላከያ ሰራዊት አባላት፤ ፖሊስና ሌሎች የጸጥታ አካላት፤ መምህራን፤ ህክምና ባለሙያዎች ፤ መገናኛ ብዙሃን፤ ወጣቶች፤ ሴቶች፤ ተማሪዎችና ሌሎች በርካታ የህብረተሰብ ክፍሎች በተገኙበት የ2017 ዓ.ም የአረንጓዴ አሻራ ማስጀመሪያ መርኃ ግብር በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡
20👏10💔5😁1
የልዩ ፍላጎትና ጎልማሶች መሰረታዊ ትምህርት ዳይሬክቶሬት በተግባር የተደገፈ የምልክት ቋንቋ የክህሎት ስልጠና ሰጠ።


(ሰኔ 22/2017 ዓ.ም) የክህሎት ስልጠናው ለልዩ ፍላጎት መምህራን፣በየትምህርት ቤቱ በተቋቋሙ የድጋፍ መስጫ ማዕከላት እና በዙሪያቸው የሚገኙ ትምህርት ቤቶችን ለሚደግፉ ተዘዋዋሪ መምህራን እንዲሁም ለርዕሳነ መምህራን እና ለትምህርት ባለሙያዎች የተሰጠ ሲሆን ስልጠናውን የምልክት ቋንቋ መጽሐፍ በማዘጋጀት እና በዘርፉ የማሰልጠን ከፍተኛ ልምድ ባላቸው ባለሙያ መሰጠቱን ከስራ ክፍሉ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።



የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የልዩፍላጎትና ጎልማሶች መሰረታዊ ትምህርት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ገመቺስ ፍቃዱ በከተማ አስተዳደሩ ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ፍትሀዊ የሆነ የትምህርት ስርአት ተግባራዊ መደረጉን ተከትሎ 2,321 የሚሆኑ መስማት የተሳናቸው ተማሪዎች የትምህርት አገልግሎት በማግኘት ላይ መሆናቸውን ገልጸው እነዚህን ተማሪዎች በአግባቡ መደገፍ እንዲቻል ለመምህራን እና ርዕሳነ መምህራን የምልክት ቋንቋ የክህሎት ስልጠና መስጠት በማስፈለጉ መርሀግብሩ መዘጋጀቱን አመላክተዋል።
14👍3
2025/07/11 22:08:00
Back to Top
HTML Embed Code: